You are on page 1of 12

በእንተ ሃይማኖተ ሐራ (ስለ ጨዋ ሃይማኖት

)
ፍሥሓ ታደሰ ፈለቀ
መስከረም፥ 2006
የሃይማኖት እዳው ገብስ አይደለም። ምናልባት ለነ ራስ-ብቻ-ደኅኔ ለነ ለኾድ-ብቻዐደሮች

እንዲያ

አይኾነውም።

ሊመስላቸው
ወርቅም

ቢችልም

ብርም

ቅሉ፤

አይኾኑም።

ውዱ

አልማዝም

ጤፍም

እንኳ

ዕንቍም

ዋጋ

እንዲኹ።

ወገኖቼ፦ የሃይማኖት እዳው ደም ነው። ቢመርርም እቅጩ የኸው ነው።
የሃይማኖት እዳው ደም ነው።
እንዲኽም ስለኾነ፤ አፍ አለኝና ነገር አሳምራለኍ ተብሎ ስለሃይማኖት እንዳገኙ
አይቀሠፈትም። ጉልበት አለኝና እያስፈራራኍ እኖራለኍ ተብሎም በሃይማኖት ላይ
አይደነፋም። በተለይ ባኹኑ ጊዜ። በተለይ ባገራችን በኢትዮጵያ። እዳውን ካንዴም
ኹለት ሦስቴ በዐይናችን በብረቱ እያየነው!
በምር እንወያይ ከተባለ አንድ ነገር ነው። ለዚያ ደግሞ ሥራት አለው። በሥራቱ
የሚደረግ ውይይት እንዲጀመር ስመኝ ዓመታት ተቆጠሩ። ከምኞት በዘለለ ቢያንስ
በመርበብቱ

አደባባይ

አንድ

ውል

ያለው

ባደርግም፤ እስካኹን አልተሳካልኝም።

1

መድረክ

ለመፍጠር

ጥቂት

ጥረት

በእኔም ይኹን በሌላ አነሣሽነት መድረኩ

የተከፈተ እንደኾነ በንቃት ለመሳተፍ በበኩሌ ዝግጁ ነኝ። መርሔም ይኽ ነው፦
እንዲያው ዝም ብሎ - በየሥርቻው - አንገት ላንገት - ከመተናነቅ
የልብን ተናግሮ - በጣይ በጉባይ - ርስ በርስ - መጠላለቅ2
                                                                                                               
1

እንዲኽ ያለው መድረክ ማናቸውም የሚመለከተው አካል ገና ከውጥኑ መክሮበት ሲጀምረው

እንጂ፤ አንዱ ባደላደለው ሌላው ተጋባዥ ሲኾን ውጤት አይኖረውም በሚል፤ ለወንድሜ
ለጃዋር በአንድ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሦስት ሃይማኖት ተከታዮች የሚያደርጉትን
ጤናማ ውይይት ምሳሌ በማድረግ እኛም ተመሳሳይ ነገር እንድንጀምር ጠይቄው ነበር። ርሱም
መልካም ፈቃዱን ነግሮኝ በዝግጅት ላይ ሳለኍ በዳኅፀ ልሳን ይኹን ከምሩ ዐስቦበት “አንገት”
ምናምን የሚሉት ነገር ሲያመጣ ግን ይቅርብኝ ብዬ ሰብሰብ አልኍ። አንገቴን እወዳታለዃ!
ዐሳቡን ግን ወይ እሱው ተስተካክሎ ወይ ሌላ ዐይናማ ሙስሊም ምሁር ተገኝቶ በትብብር
ብንገፋበት መልካም ይመስለኛል።
2

“ጠ” በ“ተ” ምትክ የገባች የትየባ ስሕተት መሰላ ይኾናል። እንዲያ የመሰለው አንባቢ፤

“መጠላለቅ” ያለውን “መተላለቅ” ብሎ ሲያነብብ፤ “ይኸንን የሚጥፍ የዕልቂት ሐዋርያ

ከዚኽ ቀደም በቋንቋ ምክንያት በተነሣ አንድ ክርክር የሰጠኹትን አስተያየት ሊተች የፈለገ አንድ ዝልጉስ ጸሐፊ፤ “ላም ባልዋለበት…” እንደሚባለው ጉዳዩን ከሃይማኖቴ ጋራ በማያያዝ ሊያንቋሽሸው ስለሞከረ፤ የነገሩን ውድቅነት ለማሳየት “በእንተ ሃይማኖት” በሚል ርእስ አንድ አጭር ጽሑፍ አስነብቤኣለኍ። በዚያች ጽሑፍ መግቢያ ላይም እንዲኽ ብየ ነበር፦ እንዲኽ ባለ (እንደ ኢትዮሜዲያ ባለ) የመገናኛ ብዙኃን መድረክ አወዛጋቢ የውሳኔ ሃይማኖት (dogmatic) ጕዳዮችን አምጥቶ መነታረክ ወይም የሃይማኖት ቀኖና እና የቤተ ክሲያን አስተዳደር-ነክ በኾኑ ጕዳዮች (canonical. ecclesiastical matters) የማያስደስተን ነገር ሲነሣ ዛቻ-ቢጤ አስተያየት፥ የልባችን ሲደርስ ደግሞ ያቋም መግለጫ-ቢጤ ድጋፍ፥ መስጠት ሳይኾን ጕዳዩ የቤተ እምነትን ገደፍ አልፎ ሲፈስ ብቻ በዚሁ ገጽ እንዳነበብነው እንደ እስክንድር ነጋ ያለ በልክ የተመተረ ቍጥብ አስተያየት ማቅረብ እንደሚያስፈልግ አምናላኹ። ይኽ አስተያየቴ እንደተጠበቀ፤ ዛሬ “በእንተ ሃይማኖት” ብየ ብዕሬን ያነሣኹበት ምክንያት የቤተ እምነትን ገደፍ አልፎ የፈሰሰ ጉዳይ ስለገጠመኝ ነው። በግልጥ አነጋገር፦ ሰሞኑን አቶ በረከት መሩት በተባለ አንድ ስብሰባ “ሲቪል ሰርቪስ” (“የጨዋ አገልግሎት”) የሚባለው የመንግሥት አሽከሮች ሚንስቴር “የሃይማኖት ጉዳይን የሠራተኛው አንዱ መመዘኛ በማድረግ ለቅጥር፤ ለእድገት እና ለዝውውር መስፈርት አድርጎ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲሰራ የ2006 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ ተቀርጹዋል” ማለቱን የሚገልጽ ዜና ስላነበብኍ ነው። “ለጨዋ አገልግሎት” ክፍሉ “የጨዋ ሃይማኖት” መቋቋሙ ነውን? ዜናው እንዲኽም የሚል ዝርዝር ይዟል፦                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                           መኾን አለበት” የሚል ዐሳብ ላንዳፍታም ሊወድቅበት ግድ ነው። የዚች ግርጌ ማስታወሻ ዐላማ እንዲያ ያለውን ሰው መርዳት ነው። “መጠላለቅ” ሲነበብ “ጠ” ትጠብቃለች፤ ትርጕሙም “ተጠየቅ፤ ተጠለቅ! (=ተመርመር)” እንዲሉ፤   “መመራመር” ማለት ነው፤ አንዱ ሌላውን ሌላው አንዱን መመርመር። .

በኢትዮጵያ ታሪክ በዩዲት ጉዲት እና በግራኝ አህመድ ዘመን በከፍተኛ ሁኔታ የደረሰውን የመንግስት ውድመት3 ዳግመኛ ሊፈጥር የሚችል አዝማሚያ አለው ሲሉ የተናገሩት አቶ በረከት፣ ይህንን በተማረው ህብረተሰብ እየታየ ያለውን በመንግስት ላይ ሊፈጠር የሚችለውን በማንኛውም ሁኔታ በህዝብና ማዳመጥ፤ የሐይማኖትን አደጋ ለመቋቋም ያስችል ዘንድ፣ በመንግስት መልእክት ተቋማት የሚያንፀባርቁ ውስጥ መዝሙር ማንኛውንም ሃሳብ መለጠፍ፤ መስበክ፤ የሞባይ መጥሪያ ድምጽ ማድረግ ፈጽሞ መከልከሉን ገልጸዋል። ይኽ እንግዲኽ (በከፊልም ቢኾን) እነ አቶ በረከት የፈጠሩት የጨዋ ሃይማኖታቸው ጨዋ ዶግማ መኾኑ ነው። ተከብሮ በተግባር ሊፈጸምም ኾነ፤ ተንቆ በቸልታ ሊታለፍ የማይቻል ነገር! ምክንያቱም አክብረው እንዳይፈጽሙት ዕብደት ነው፤ ችላ ብለው እንዳያልፉት የሚያቀነቅኑት ያገር መሪ ነን የሚሉ ስለኾኑ ብዙ የዋሃንን ሊያጠፉ ኾና! እንዲኽም ስለኾነ ብዕሬን አነሣኍ። ብርዕ ስላነሣኍ ግን ጉድዩ በምር ሊታሰብበት የሚገባ መኾኑን ለመጠቆም ያኽል እንጂ የተሟላ ትች ለማቅረብ ቀለምም ጊዜም ያጥረኛልና ኾዳችኹን ጠበብ እንድታደርጉት ከወዲኹ እለምናለኍ። በግእዝ “ሐራ” ባማርኛ “ጨዋ” ብዙ ጭነት የተሸከሙ ቃላት ናቸው። ሸክማቸውን ግን እንዲኽ ባለች ቍርጭኝ ክታብ አራግፎ መጨረስ የሚቻል አይመስለኝም።                                                                                                                 3 እንዲኽ ያለው ተራ ሽወዳ “ድንቄም!” ያሰኛል። ግራኝ ካጠፋቸው ቦታዎች አንዱን ላስታውሳችኍ።እነ ዱባይ ሳይቆረቆሩ፤ እነ በርሊን ሳይሠሩ እነ ኒውዮርክ ሳይፈጠሩ ከነበሩ የመካከለኛው ዘመን ከተሞች በቀዳሚነት የሚጠቀስ ከተማ። እንደሌሎች ያገራችን ከተሞች ኹሉ ስሙን የነሣው በዚያው ከተማ ማኽል የኹለት ነገሥታት ዘመን ጨርሶ ከታነጸው ከአግያ ሶፍያ ይወዳደር ከነበረው እንዲያውም በወርቅና በአልማዙ ብዛትማ ይበልጣትም እንደነበረ ከተነገረለት ቤተ ክርስቲያን ነበር፤ መካነ ሥላሴ ይባላል። ዛሬ ወደዚያ አካባቢ ጎራ ብትሉ… ባጭሩ ፍርስራሽ ነው የምታገኙት። በሌላ በኩል ግራኝም ሌሎችም ያፈረሱትን እየገነቡ አገሪቱን እንደገና ያቋቋሙት አጤ ምኒልክ አዲስ አበባን ያገሪቱ ማእከል ሲያደርጉ ባሳነጹት ደብር የመካነ ሥላሴን ታቦት እንዲገባ አድርገዋል። ሕዝቡም ፈሪሀ እግዚአብሔር ሳይለየው ሕግን አክብሮ አንድነቱን እንዲጠብቅ በማድረጋቸው ዓለም ያወቀውን ድል ለማስመዝገብ በቅተዋል። ይኽንን ያስታወስኹት፤ እነ አቶ በረከት ከዐቅማቸው በላይ በመኾኑ አልቻሉም እንጂ፤ በዚኽ ታሪክ ኪኮሩ ይልቅ፤ ድምጥማጡን ለማጥፋት የሚያደርጉትን ጥረት እያየነው፤ ዛሬ ሙስሊም ወገኖቻችን እንደ ግራኝ ዘመን ያለ ችግር ሊያመጡብን የተንሡ በማስመሰል “በዮዲት ጉዲት እና በግራኝ…” እያሉ፤ ርስ በርሳችን እንድንፈራራ እና እንድንጠላላ የሚያደርግ መርዝ ለመንዛት መሞከራቸው ገርሞኝ ነው። .

theologia naturalis.ይኹንና ቢያንስ ለጊዜው የአንድ የሮማይስጥ ቃል ፍቺ አድርጌ ተጠቅሜኣቸዋለኍ፤ “civil” የሚለው ቃል ፍች አድርጌ። ስለዚኽ ከ“ሃይማኖት” ጋር በተገናኝ “ሃይማኖተ ሐራ”፥ “የ/ጨዋ ሃይማኖት” በሚለው ርእስ ለመግለጥ የፈለግኹት ፈረንጆቹ “civil religion” የሚሉትን ነው። “civil religion”፦ በግእዝ “ሃይማኖተ ሐራ”፥ ባማርኛ “የጨዋ ሃይማኖት” ወይም “ጨዋ ሃይማኖት” ያሰኛል። ዐይነታ ነገሩም (ባጭርና ግርድፍ አነጋገር) የመንግሥት አሽከሮች፥ ያገር ዜጎች እምነት ነው። ወደው የተቀበሉት ወይም በግድ የተጫነባቸው። ረዥም ታሪክ አለው። በውጭም ባገራችንም። ስለጨዋ ሃይማኖት እንደ ቫሮ (Varro) 4 ያሉ ጥንታውያን ሊቃውንት ቢቀሩ፤ ባሥራ ስምንተኛው ምእት ዓመት ተነሥቶ የነበረው ዘመናዊ ፈላስማ ሩሶ (Rousseau) “Social Contract” በሚባለው ጥራዝ አራተኛ መጽሐፉ ስምንተኛ ምዕራፍ ላይ ርእሱን ቆርቶ ያስቀመጠውን (በምዕራፉ ርእስ በግልጥ “civil religion” ብሎ ያተተውን) እና አኹን በፈረንጆቹ ከሃያኛው ምእት ዓመት ኹለተኛ አጋማሽ ወዲኽ ገንኖ ኖሮ ገና ባለፈው ጁላይ ያለፈው አሜሪካዊ (የሃይማኖት) ሶሺዎሎጂስት ቤላህ (Bellah) “American civil religion” በሚል ርእስ የከተበውን በመጠኑ መዳሰስ ይገባ ነበር። ይኹንና በጊዜ እጥረት ምክንያት እታሪኩ ውስጥ ጠልቆ መግባትን አልፈለግኹም። ይልቅ እንደገና ወደ ቃሉ። በቃሉ አማካይነት ፅንሰ ሐሳቡን ለመረዳት። በፅንሰ ሐሳቡም አማካይነት ባሕርየ ነገሩን ለማግኘት፤ ጽድቀ ባሕርዩን ለማየት። አይቶም የሚገባውን ለማኾን፤ ተገቢውን ዐሳብ ለማጽደቅ። ከላይ እንደጠቆምኹት የ“ጨዋ”ን ሰፊ አንድምታ እዚኽ ዘርግፎ ለመጨረስ ባይቻልም፤ ይኽ ቃል “civil” በሚያሰኘው ስሜቱ የቋጠረው ዕሳቤ ግን ጥቂት መፍታታትን ይሻል። ባግባቡ ሲፍታታ ያንዳንዶችን ዕመም ሊቀሰቅስ፥ የጥቂቶችንም ዛር ሊያስነሣ የሚችል ነገር ቢወጣው፤ ዕመምተኞቹ ጋር ዐብሬ እየታመምኍ                                                                                                                 4 doctissimus romanorum (the most learned of the Romans) እንደነበረ ሴኔካ (Seneca) የመሰከረለት፤ ፔትራርካም (Petrarca) ከሲሴሮ (Cicero) እና ከቨርጂል (Vergil) ቀጥሎ “ሦስተኛው ታላቅ የሮም ብርሃን” (the third great light of Rome) እንደነበረ የተናገረለት ቫሮ (Varro) የሃይማኖትን መንገድ:.የዜጋ፥ የማእምር፥ የባለቅኔ (theologia civilis. theologia mythica/fabulosa/poetica) በማለት ለይቶ አስቀምጧል። ከዚኽ እና ከሌሎች ሥራዎቹም ጠባይ በመነሣት ጀርመናዊው ካርል ጉስታቭ አዶልፍ ፎን ሃርናክ (Carl Gustav Adolf von Harnack) “የስለታ ፈጣሪ” (ein Genie der Klassifikation = a genius of classification) ብሎታል። .

መዳኒቱን ለመሻት ከምሞክር በቀር፤ አንዱም አንዱ ዛሩን እንዳመሉ ያስተናግድ እንጂ ከባለዛር ጋራ ግን ዐብሬ አላጎራም። የኔ መርሕ “ወጽድቅ ታግዕዘክሙ” (እውነትም ነጻ ታወጣችዃለች) ነው። “ጨዋ” የሚለውን ቃል ያገራችን ዘመናውያን “ሊንጒስቶች” እንዴት እንደሚተረጉሙት ለመረዳት ያደረግኹት ጥረት ፍሬ ቢስ ስለኾነብኝ፤ የጥንቶቹ ዐይናሞች ሊቃውንት በ“ዘይቤ”ም (literally. connotatively) የሰጡትን ፍቺ መሠረት አደርጋለኍ። የነርሱም አፈታት ቃሉ በኑሯችን እስከቅርብ ጊዜ የነበረውን አጠቃቀም የሚያንጸባርቅ ነው። “ጨዋ” በደስታ ተክለ ወልድ ያማርኛ መዝገበ ቃላት እንዲኽ ተተርጉሟል፦ ጨዋ፤ (ልሂቅ)፦ ዐዋቂ፥ ዐዛውንት፥ ሽማግሌ፥ አስታራቂ፥ ገላጋይ። “ጨዋ ዐር ያበላል” እንዲሉ። ጨዋ በልጅነቱ ሲሠራው የነበረውን ልጆች ሲሠሩት ቢያይ ይነቅፋል። ጨው ምግብን ኹሉ እንደሚያስማማ ጨዋም መክሮ ያስታርቃል፤ ዘክሮ በጠብ “አንተም የተለያየውን ተው አንተም በፍቅር አንድ ተው” ብሎ ያደርጋልና፤ የተጣላን ጨው እንደማለት ጨዋ ተባለ። ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን “እናንተ የምድር ጨው ናችኹ” እንዳለ (ማቴ 5፡13) ጨዋነት፦ ጨዋ መኾን፥ ሽምግልና። ጨዋ (ሐራ)፦ የንጉሥ አሽከር፥ ዘማች፥ ወታደር፥ የጦር ሰው፥ ምሪተኛ፥ ስላገልግሎቱ በባላገር ላይ እየተሠራ በቀን ብዛት መልከኛ ባላባት የኾነ፤ ይኸውም ዐማራ (ዐም ሐራ) ነው። “የጨዋ ልጅ” እንዲሉ። “የጨዋ ልጅ ተዋርዶ፥ ዕንጨት ሰበራ ቈላ ወርዶ፥ ሲያነደው ያድራል ሌሊቱን፥ ቀን የሰበረውን” (አዝማሪ)። ዳግመኛም “ጨዋ” ግእዝ “ጼዋ” ካለው ቢወጣ የምርኮኛን ባላባትነት ክብርና ማዕርግ ያሳያል። (ዳን 1፡3፥ 4 .6። 3፡ 12) ዐይናማው ሊቅ አለቃ አፈ ወርቅ ዘውዴ በበኩላቸው “ሀገረ መጻሕፍት፦ ሰዋስወ ግእዝ ወዐማርኛ” በሚባለው መጽሐፋቸው ምዕራፍ 28 “ጨዋ በሚል ርእስ” የሚከተለውን ዐተታ አስፈረዋል፦ . denotatively) በ“ሲኼድ ዐደር”ም (tropically.

usage. The term with social reference is c´äwa. ´gentleman´ c´äwa might meant best something fit quite contemporary different.” In this case the original phrases are mäkwannent and yäc´äwa lejoc. In his original bequeathal to Gälawdewos. some of the witnesses were “from the nobility” and some were ”from the sons of the gentry. … C´äwa has a more complex history and diffuse usage. “let him be satisfied with what is due to him as a member of the gentry.” The Amharic here is yäc´äwa serat yebäqaw. From the                                                                                                                 5 “ጨዋ” የሚለው ቃል “ጨው” በሩቂቱ ሴት ሲዘረዘር ነው። “ሰላም” ብሎ “ሰላሟ” ወይም “ድርሻ” ብሎ “ድርሻዋ” እንደማለት። በዚኽ አጋጣሚ፤ ጥቅሱ እንዳለ የተቀጠፈው ከመጽሐፉ መኾኑን ላስታውስ። በትእምርተ ጥቅሱ እና በሥርዐተ ነጥቡ ግን የእኔም እጅ አለበት። ከዝኽም ጋር በባለማዕዝኑ ቅንፍ ውስጥ የሚገኙትም ቃላት የእኔው ናቸው። . Two generations later. Wäldä Giyorgis stated. when Gälawdewos and his son passed the aläqenät on to their descendant Wälättä S´eyon and her husband Eshäté. the terms with social reference being mäkwannent and. c´äwa These terms are common in the historical literature concerning Ethiopia and c´äwa is still used in a certain colloquial contexts. In the singular. Originally. I have translated it as ´gentry´ when the sense is a collective one. again.…ጨዋ ማለትም “ጼው” (ጨው) የተባለውን ቃል ይዞ “ጼዋ ለኢትዮጵያ” ([የኢትዮጵያ] ጨዋ)5 ማለት ነው። የአነጋገሩም አምሳል “ሰላማ” እንደማለት ይኾናል። “ዐም [=] ዘመን” ያለውን ቃል “ሐራ = ጨዋ ወታደር” ከሚለው ቃል ጋር አዛርፎ፤ እንዳንድ ስም አድርጎ ይተቻል። ይኸውም “ዘመናዊ” “ሐራ ዘመን” እንደማለት ይታሰባል። [እንዲኽም ስለኾነ] …“ዐም ሐራ” ማለት “ጨዋ ዘበናይ”…ነው። የፈረንጅ ጽሑፍ ለሚርበው ዐይን ደግሞ ዶናልድ ክራሚ (Donald Crummy) በደረሰበት መጠን ያተተውን በረጅሙ ልጥቀስና ላጥግበው፦ Two terms referring to social class appear in the documents referring to aläqenät: c´äwa and mäkwannent.

6 [ሐራ ንጉሥ] ጨዋ እንዲኽ ከኾነ ሃይማኖቱስ ምን ይመስል ነበር? “Civil Religion” እንደ ሩሶ አቀራረብ ከነባር ሃይማኖቶች አንዱ ሲኾን፤ እንደ ቤላህ ደግሞ ያንድ አገር ዋነኛ ሃይማኖቶች ከሚመሩባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት የተውጣጣ ነው። በነገሥታቱ ዘመን የነበረውን የራሳችንን ታሪክ መለስ ብለን ከተመለከትነው ወደ ሩሶ አስተያየት ይቀርባል። ማለትም፤ ሃይማኖተ ሐራ/የጨዋ ሃይማኖት ከነባሮቹ ሃይማኖቶች አንዱ፤ ይኸውም የክርስትና ሃይማኖት ነበር። እስከቅርብ ጊዜ ድረስ “እገሌ ክርስቲያን ነው እስላም?” ለማለት “ዐማራ ነው እስላም?” እንዲሉ። ሐራ = ጨዋ ዐም = ዘመን ዐምሐራ (ዐማራ) = ዘበናይ ጨዋ = ክርስቲያን የሐራ/የጨዋ/ያማራ ሃይማኖት = የክርስትና እምነት ዃላ ግን ያ ቀርቶ ሌላ ዘፈን መምጣቱን አልዘነጋኹም። “ሃይማኖት የግል ነው አገር የጋራ ነው” የሚሉት ዘፈን። ይኽንን መፈክር ስንቱ ጮኸው! ነገር ግን እንዲኽ ያለው መፈክር ቍጥሩ፤ ፈረንጆቹ “easier said than done” ከሚሉት ነው። ለዚኽም ምክንያቱ ብዙ ነው፤ አኹን ግን ከብዙው አንዱ እና ዋናው ያገሪቱ ታሪካዊ መሠረት መኾኑን ከመጠቆም በቀር እዚኽ የትኛውንም ምክንያት ለማተት አልሞክርም። ይልቅ በዚኽ አጋጣሚ፤ ዐዲሱን ዘፈን ለኹሉ ጆሮ የሚጣፍጥ፥ የኹሉን ልብ የሚመስጥ አድርጎ ለማቀንቀን ይቻል ዘንድ የታሪክን መሰንቆ እንዴት አድርጎ መቃኘት እንደሚበጅ፤ ለጎሳ ወይም ለጎጥ ሳይኾን፤ በእውነት ላገሩ ለኢትዮጵያ ለመላ ሕዝቧም የሚገደው ዐይናማው ሊቅ ፕሮፌሶር መሳይ እንዲኽ ብሎ ያስቀመጠውን አስታውሳለኍ፦ The Kibre Negest is therefore a “national epic” in that “it defines the secular and religious foundation of Ethiopian nationhood. 2000) p. . 126. Land and Society in the Christian Kingdom of Ethiopia: From the Thirteenth to the Twentieth Century. (Urbana and Chicago: University of Illinois Press.fourteenth through to the seventeenth centuries the c´äwa were military regiments under royal control. Donald. it depicted Ethiopian nationhood in terms of the                                                                                                                 6 Crummy.” Specifically.

It sets the task in the light of which the history of Ethiopia appears as its unfolding… There is therefore need for a new Kibre Negest. . pp. one defining Ethiopian identity in such a way that it includes the Muslim community. Survival and Modernization: Ethiopia’s Enigmatic Present: A Philosophical Discourse. Christianity had become the raison d'être of a people and of its social and political system. provides the canon of Ethiopian history and the driving force of its historicity. 77. way of life. (Lawrenceville and Asmara: Red See Press. culture. then. 1999).7 በሌላ በኩል መሰንቆውን ባግባቡ መቃኘት ሳይኾን፤ የቀድሞ ቅርጹ ምናልባት ወደፊት እንኳ እንዳያስታውቅ “አከርካሪውን” እንክትክት አድርገው ሰባብረው፤ ዘፈኑን ቅሉ የባሰ አበለሻሽተው፤ ረ እንዲያውም ድምጥማጡን አጥፍተው፤ በረግዶ፥ በሙሾ ለመተካት ሌት ተቀን እየጣሩ እና፤ “ጸረ ሐራ" (የጨዋ ጠላት) መኾናቸውን ባደባባይ በግልጥ እየለፈፉ ያሉ፤ አካላት ለሐራው (ለጨዋው) የሃይማኖት ሕግ እናውጣልኽ ብለው መነሣታቸው ፌዝ ነው። ፌዝ ባማርኛ። ፌዙን ትተን በጨዋ ደንብ ቍም ነገር እናውራ ከተባለ፤ እንደ አቶ በረከት ያሉ ባገሪቱ እርግና ምክንያት የተፈጠሩ የሚመስሉ ጃርቶች ለጨዋው ሊያውጁለት የሚችሉት “ሳታኒዝም” ካልኾነ በቀር “ሃይማኖት” የላቸውም። ይኹንና ሳታኒዝማቸው የትኛው ዐይነት እንደኾነ ጠንቅቆ በመረዳት፤ እንደጉም ተንኖ እንደትቢያ በንኖ የሚጠፋበትን ምሱን መፈለግ እንጂ፤ እዚያው አምላካቸው ዲያብሎስ ይወቀው ብሎ መተው ግን አይገባም።                                                                                                                 7 Messay Kebede. 83.oneness and common destiny of Church and stat… In addition to being an official religion. This definition must not put aside the myth of the guardianship of Christianity. and polity… The Kibre Negest. Rather. 395. from ascription the myth must grow into an achieving ethos in line with the requirement of modernization. It was everything—at once religion.

Appendix 1 .

http://etext. Have a blessed weekend bro . Maybe just a two way conversation (Christian-Muslim) as the Jewish element seems now to have already been severed.html Journal of Scriptural Reasoning Forum etext. 4:35pm Jawar Mohammed Fisseha.edu/journals/jsrforum/index. Thanks for sharing this. 2012 • 11/8. The second is a conversation between religious leaders and political leaders. a condition that is allowing all kind of internal and external actors to fill the void and exploit our people.edu Welcome to the website of the Society for Scriptural Reasoning. 2:38pm Fisseha Feleke Do you think time is ripe to establish something like the following? By Ethiopians. One is an across faiths dialog among intellectuals and spiritual leaders of each religion. The third would a conversation within each religion. The objective this one would be to provide internal critique and build consensus about that specific religions relation to other faiths and also to the political society. Each of this are serious lacking in Ethiopia. I actually think such dialog is a longer over for Ethiopia. • 11/8. This would to clarify and demarcate the boundary between religion and politics. that is. I think we need a three way conversation on religion. I wish you could start some initiative and I would be glad to contribute my share.virginia. This site offers hospitality to all those interested in Scriptural Reasoning and to those currently praciticing SR.virginia. The aim of this conversation would be to broaden mutual understanding and respect through continuous flow of information and civil engagement.Appendix 2 ከወንድሜ ከጃዋር ጋራ ስንመካከር የነበረው! • Conversation started November 8.lib.lib.

. dear Jawar. brother. for your prompt response. 4:53pm Fisseha Feleke Thanks a lot. Thanks again and God bless. I look forward hearing from you. 4:53pm Jawar Mohammed That would be wonderful.• 11/8. I shall thus prepare a draft plan for a concrete procedure and contact you for your comments. • 11/8. I agree with what you said and God willing we may start it at one level and go from there.

Appendinx 3 አጤ ምኒልክ በቁፋሮ (excavation) እንዲወጣ ያደረጉት የመካነ ሥላሴ ሕንፃ ፍርስራሽ .