You are on page 1of 3

የዯብረ ዘይት ትዝታ፦ ስሇሰው ተፈጥሮኣዊ ፖሇቲከኝነት

ታዋቂው ጥንታዊ ፈሊስፋ አርስጣጣሇስ ሰው በተፈጥሮው ፖሇቲከኛ እንስሳ (political animal) ነው ይሊሌ።
ያርስጣጣሇስ “ወሌደ ዋሕዴ ወእሩዩ” (አንዴያ እና እኩያ ሌጁ፦ the only begotten and co-equal son)
እንዯኾነ የተነገረሇት ዘመናዊ ፈሊስፋ ሄግሌ፤ የሰውን ተፈጥሮኣዊ ፖሇቲከኝነት ሲያጦዘው፤ ሰው ኹለ ካንዴ
ጠቅሊይ መንፈስ (absoluter Geist) ሱታፌ ያሇው እንዯኾነ አዴርጎ አስቀምጦታሌ።

የሇም! ሰው ባሇአእምሮ እንስሳ (rational animal) ነው ተብል ዏይነተኛ ባሕርዩ በእንስሳነት መዯብ ሉታይ
አይገባውም በማሇት ባርስጣጣሇስ እና በዘመናዊውም ሳይንስ አንጻር (በዚህ ረገዴ አርስጣጣሇስንም ዘመናዊ
ሳይንስንም ተቃውሞ) የቆመው ሃይዱገር የተባሇ የቅርብ ጊዜ ፈሊስፋ ዯግሞ፤ ሰው የህሊዌ መ-እነሆ-ዊያ፦ ማሇትም
የህሊዌ/የኑሮ ፍሬ ተሸፍኖ ከተቆሇሇበት ክምር እነሆኝ ብል እየወጣ ነድ በነድ የሚነሰነስበት ብልም እየተወቃ
የሚፈሇፈሌበት ምንጥር ዏውዴማ (the “There” of Being [Dasein]—the Clearing of Being [Lichtung
des Seins]—Openness!) እንዯኾነ ይናገራሌ። የሃይዱገር ዕሳቤ ታዱያ የሰውን በእንስሳ መዯብ መገምገም
አጥብቆ ይነቅፋሌ እንጂ ተፈጥሮኣዊ ፖሇቲከኝነቱን አይቃወምም። እንዱያውም መጀመሪያ ተማሪው፥ ዃሊ ሞጋቹ
የኾነው ላቪናስ እንዯሚነግረን “ህሊዌ” ራሱን የሚገሌጠው በጦርነት መሌክ ነውና (“Being reveals itself as
war”) የሃይዱገር “ዲዛይን” የጦርነት ዏውዴማ ነው፤ ፖሇቲካ ዯግሞ ጦርነትን አስቀዴሞ አይቶ በኾነው መንገዴ
የማሸነፍ ጥበብ ነውና የአእምሮ ተግባር ኾኖ ይሰፍናሌ (“The art of foreseeing war and of winning it by
every means—politics—is henceforth enjoined as the very exercise of reason”)።
እኛም እንዯገና በጠየቅን መሌካም ነበር፦ “ሰው ምንዴር ነው?” ብሇን። ምናሌባት የቀዯሙት እንዯሚያስረደን ይህ
የጥያቄ አተካከሌ ያሌተቃና ከኾነም (ሰው ነባቢ አካሌ [person] እንዯመኾኑ “ማን” እንጂ እንዯማናቸውም ዕቃነገር [thing] “ምን” ሉባሌ አይገባውምና) “ሰው ማን ነው?” ብሇን ብንጠይቅ መሌካም ነበር። በሌማዴም ይኹን
እንዯ ሶቅራጥስ አምነንበት “ምንነት” ሊይ ሙጭጭ ማሇት ከሻንም፤ “የሰው ፍጥረቱ/ባሕርዩ ምንዴር ነው?” ብሇን፤
አሇያም ላሊ የበሇጠ ምቹ አገሊሇጥ ፈሌገን ጥያቄኣችንን በተከሌንና ክሥተቱን፤ ማሇትም ማንነታችንን፤ ሉያሳየን
ወዯሚችሌ ግንዛቤ በዯረስን እንዳት ባማረ። ነገር ግን ስሇማናቸውም ሰው ፖሇቲከኝነት በፍሌስፍናው አብነት
የሚባሇውን ሇመጠቆም ያኽሌ ይኸው ይብቃንና ወዯሃይማኖቱ አብነት ጎራ ብሇን ጥቂት እንጨሌፍ፦ ስሇሰው
ተፈጥሮኣዊ ፖሇቲከኝነት።

አዲም የምዴር ንጉሥ ነበር፤ ሔዋንም የምዴር ንግሥት። እንዱህም ስሇኾነ፤ እያንዲንደ ሰው የአዲምና የሔዋን ሌጅ
እንዯመኾኑ መጠን በ(ገናኛ)ክሂሌ (potentially) ንጉሥ/ንግሥት ነው። ነገር ግን ባንዴ ሕግ የሚተዲዯርን አንዴ
ሕዝብ በአንዴ ዘመን በተግባር (actually) የሚመራው አንዴ ንጉሥ ስሇኾነ፤ አንደ ሲነገሥ የቀረው የዚያች አገር
ሕዝብ ከፊለ የንጉሡ አሽከር ኾኖ በተዋረዴ ያስተዲዴራሌ ከፊለም ዜጋ ኾኖ ይተዲዯራሌ፤ ባስተዲዯሩ የተከፋም
ያምፅና ወይ መስተዲዴሩን ሇቆ ይወጣሌ አሇያም እዚያው ኾኖ ይፈጣፈጣሌ። እዚህ ሊይ የሄግሌ “What is
rational is actual and what is actual is rational” ብል ነገር አይሠራም ማሇት ነው! ይኽም ሉታወቅ
ሇአዲም የተሰጠው ሀብት የመንግሥት ብቻ አሌነበረም፤ ሀብተ ትንቢትም ተሰጥቶታሌ፦ መጻኢውን በማየት
ጊዜውን ("status quo"ውን) የመተቸት እና የመገሠጥ ሀብት። ሀብተ ክህነትም አሇ፤ ሰማያዊውን መንግሥት
የማገሌገሌ ሀብት።
ይህም ይህ ነው፤ እንዱህም ስሇኾነ ፖሇቲካም ኾነ ሃይማኖት እየቅሌ እየቅሌ የሚሠሩትን እየሠሩ በሚናበቡበት
ዯግሞ መናበብ ግዴ ነው። በኾነው ረገዴ መሠረታዊ ሇውጥ እናምጣም ቢለ በዚሁ መሌክ የሚመጣ
(differential transformation) ሉኾን ይገባዋሌ። ዛሬ ባገራችን ግንኖ እንዯምናየው ግን እየቅሌ ሉሠሩት
በሚገባው፦ አንደ በላሊው ጣሌቃ መግባት፤ ሉናበቡበት በሚገባው፦ “ምንአገባኽ” መባባሌ ጥፋት ነው።
እንዱሁም በተግባር የዃሌዮሽ እየተጓዙ እንዱያው የሇውጥ ዏማርኛ በማማረጥ ሕዲሴ ቅብርጥሶ እያለ ሰውን
በወሬ ብቻ ማዯናገር ፋይዲ የሇውም።

...በየውሀተ-ሌቡ.. የውሀትን በያዘ ሌቡናው...ክህነትም ኾነ ትንቢት እንዯ መንግሥት ኹለ በ(ገናኛ)ክሂሌ የማናቸውም ዯቂቀ አዲም/ውለዯ ሔዋን ሀብት ናቸው። እሉህ ሀብታት በግሌጥ በቅባት የተሰጧቸውም፥ ፍት ርት ሲጎዴሌ ዴኻ ሲበዯሌ የሚከተሇውን ፍዲ በማስረዲት እንዯመገሠጥ፤ ከጊዜው ነገሥታት ጋራ ሽር ጉዴ ካለ የሚዯርስባቸውን በኢሳይያስ አይተናሌ። ከሕዝብ የሚነጥሌ ዯዌ ይዲዯቃቸዋሌ/ያገኛቸዋሌ። [ረ ይኸ ነገር፤ በዘመነ ጥናትና ምርምር እንዱህ እንዯወረዯ እየዘረገፍኍ አንባቢን እንዲሊዯክም ብቻ ሳይኾን ቁም ነገሩም ጕሥዏተ ሌብ እንዲይመስሌ ፈራኍ። በዚያውስ ሊይ ምስጢር የባቄሊ ወፍጮ አይዯሇ! እንግዱህ እዚሁ ይብቃኝና ወዯተንሣኹበት ነገር በቀጥታ ሌግባ።] ዛሬ ወዯዚች ምክታብ ያመጣኝ ነገር ትዝታ ነው። የኻች ዓምናው በዓሇ ዯብረ ዘይት ትዝታ። በተሇይም በዕሇተ በዓለ ካገራችን ታሊሊቅ አዴባራት ባንደ ሲያስገመግም ያዯረው ማሕላት፤ ይሌቁንም የቅኔው ማዕበሌ ትዝታ። ዝርዝሩን ሊውጋው ብሌ ጣዕሙን አበሊሸው ይኾናሌና ሇኔው ይቅር። በዚያች ላሉት ሇዯብሩ እንግዲ ስሇነበሩ ይመስሇኛሌ ቅኔው (ከዕጣነ ሞገሩ በቀር) የተሇቀቀሊቸው አንዴ መሪጌታ ነበሩ። ርሳቸውም እንዳት ያለ ዓይናማ ሉቅ ኖረዋሌ፤ ይኸን የምስጢር ድፍ አወረደታ። የምስጢር ድፉ የፈጠረው ጎርፍ ያጥሇቀሇቃቸው ሉቃውንትም ሌብን በሚመስጥ አቋቋም መቋሚያቸውን እየወዘወዙ ሲቀዝፉት (ሲያዜሙት፥ ሲዘምሙት) መስማትና ማየት የፈጠረብኝን ስሜት ሇመግሇጥ ከፍሥሓ እና ከሐሴት በሊይ ላሊ ቃሌ ፈሌጉሌኝ ያሰኛሌ። ታዱያ ያ ሉቅ ካበረከቷቸው ቅኔዎች መካከሌ አንደ የሚከተሇው ነበር፦ ሇምንት ንብሌ ጊዜ ይባቤ፤ መስተብቍዏ ንጉሥ ሌዐሌ በእንተ ንጉሥ ዘይቤ? እስመ ዱበ መንበር ዘዲዊት ጥቀ ንጉሠ ነገሥት ኢረከብነ/ኢርኢነ ኀቤ። ዏማርኛ፦ በዲዊት ዙፋን ሊይ ፈጽሞ ንጉሠ ነገሥት ሳናገኝ (ሳናይ)፤ "በእንተ ንጉሥ” የሚሇውን ስሇንጉሥ የሚጸሇይ የምሌጃ ጸልት በምስጋና ማሕላት ጊዜ ሇምን እንሊሇን (እናቀርባሇን)? የቅኔውን ጥሌቅ ምስጢር ራሳቸው ባሇቤቱ ሲያራቅቁት ሰምቼ በርሳቸው ቃሌ ባቀረብኍት መሌካም ነበር። ይኹን እንጂ፤ ርሳቸው ያሰቡበት መንገዴ እቅጩ ይኸ ነው ሇማሇት ሳሌዯፍር፤ ሉቁን ባለበት ይቅርታ እየጠየቅኍና ከተሳሳትኍም ሇመታረም ዝግጁ መኾኔን እየገሇጥኍ እኔ በወቅቱ ቅኔውን ስሰማው ዃሊም በትንሿ ዏቅሜ ሳሰሊስሇው የተረዲኹትን በጥቂቱ ሌግሇጠው፦ ባኹኑ ጊዜ አገራችን መሪ ንጉሥ የሊትም። ባፄ ምኒሌክ ቤተ መንግሥት የተቀመጡት መንግሥት ተብየዎች፤ ራሳቸው ሇራሳቸው ባወጡት ስም “ወያነዎች” (ዏመጸኞች) ናቸውና። ተግባራቸውም ቢኾን ያው እንዯስማቸው ነው፤ ከቅንነት ጋራ ፈጽመው አይተዋወቁም።ስሇቤተ ክርስቲያኗም የሚያስቡት የምትጠፋበትን መንገዴ እንዯኾነ በጎሊ በተረዲ ነገር ታውቋሌ። እንዱህም ስሇኾነ "ወኀረዮ ሇዲዊት ገብሩ..በፈሉጥ ቃለ። መዝ ፸፯፡፸) እንዯተባሇሇት እንዯዲዊት በፈቃዯ እግዚአብሔር ተሹሞ ሕግን ጠብቆ የሚያስጠብቅ አገርን በቅንነት የሚያስተዲዴር ንጉሥ ገና አሊገኘንም። አሊገኘንምና “በእንተ ንጉሥ”ን ሇማን ነው የምንጸሌየው? በማሇት ጠይቀዋሌ። ጥያቄውን ሇማዲበር ሇብዙዎቻችን ቅርብ የኾነ ነገር ሊስታውሳችኍ። ቅዲሴ አስቀዴሳችኍ ታውቃሊችኍ? መሌሳችኍ “አዎ” ከኾነ፤ አኹን የምነግራችኍ በቀሊለ ይገባችዃሌ። በቅዲሴ ጊዜ ሌኡካኑ ዴርገት ሉወርደ ሲለ (ቍርባን ሉያቆርቡ ከመቅዯስ ሉወጡ ሲለ) ከሕዝቡ እየተቀባበለ የሚያዯርሱት መሌከአ ቍርባን የሚባሌ ዴርሰት አሇ። የዚህ ዴርሰት መጨረሻ የሚከተሇው ነው፦ እግዚኦ ኵነኔከ ሀቦ ሇንጉሥ፤ ጽዴቀከኒ ሇወሌዯ ንጉሥ። ..በጥበበ-እዯዊሁ" (አገሌጋዩ ባሇሟለ ዲዊትን ሇመንግሥት መረጠው።.

..አግርር ጸሮ ታሕተ እገሪሁ፤ ዕቀብ ንግሦ ወሠራዊቶ ሇንጉሥነ… ዏማርኛው፦ አቤቱ ፍርዴኽን ሇንጉሡ ስጠው፤ ጽዴቅኽንም ሇንጉሡ ሌጅ፤ ጠሊቱን ከእግሩ በታች አስገዛሇት፤ የንጉሣችን የ...ን መንግሥት ሠራዊቱንም ጠብቅ። ሇዚህም መሠረቱ መዝሙረ ዲዊት ነው። ዛሬ ግን ይኽንን ባዋጅ ሳይኾን በሇኈሳስ ሇውጠን እንዱህ ነው የምንሇው፦ እግዚኦ ኵነኔከ ሀባ ሇሀገር፤ ጽዴቀከኒ ሇውለዯ ቤተ ክርስቲያን አግርር ጸራ ታሕተ እገሪሃ፤ ዕቀብ ሕዝባ ወሠራዊታ ሇሀገሪትነ ኢትዮጵያ ዏማርኛው፦ አቤቱ ፍርዴኽን ሊገራችን ስጣት፤ እውነትኽንም ሇቤተ ክርስቲያን ሌጆች፤ ጠሊቶቿን ከእግሮቿ በታች አስገዛሊት፤ የኢትዮጵያን ሕዝቧንና ሠራዊቷን ጠብቅሊት። በተመሳሳይም አንዲንዴ የቅርብ ጊዜ ኅትመቶች "በእንተ ንጉሥ" የሚሇውን መስተብቍዕም ኾነ ዘይነግሥ "በእንተ ሀገር" ብሇው የዴርሰቱን ይዘት በዚያው መሠረት እንዲስተካከለት አይቻሇኍ። ባገሌግልት ግን ባብዛኛው ያው በቃሌ የተያዘው የጥንቱ ስሇሚባሌ፤ ሇንጉሥ የሚቀርበው ምሌጃ እንዯተዜመ ነበር ከሊይ የጠቀስዃቸው ሉቅ ከዚያው አያይዘው በቅኔያቸው ጥያቄውን ያቀረቡት። ከዚህም በቀር በመሃይምን አነጋገር የሚባሌ ተመሳሳይ ጸልት አሇ። "እግዜር መንግሥትን ይጠብቅ፤ ዏመፀኛን ያውዴቅ፤ ሐሰተኛን ያርቅ፤ ፍት ርት ይጠንቅቅ" የሚሌ። ነገር ግን ፍርዴ የሚገመዴሇው ዲኛ ሲኾን፤ እንዲሮጌ ቴትሮን በሐሰት የሚቀዯዯው ነቢይ ሲኾን፥ ሇኾደ አጎብዴድ ፍጡር የሚያመሌከው ካህን ሲኾን፤ ዴኻ የሚቀማውም ስግብግብ መንግሥት ሲኾን፤ ምን ይባሊሌ? እንዱህ ባሇው ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ሇማን እንዳት ሌትጸሌይ ይገባታሌ? ወገንተኝነቷ ሇሕዝብና ሇአገር ከኾነ፤ ይኽንኑ በተግባር የምትገሌጠው እንዳት ነው? እንግዱህ ሉቁ የጠየቁትን ጠይቀዋሌ። እኛም እንዱሁ እንጠይቃሇን። ፍጥረታችን ስሇኾነ። ይኽንና ይኽንን የመሳሰሇውን አስተያየት ማቅረብን፥ ፍት ርትን መጠየቅን፥ ሇተገፉ ሰዎች ጥብቅና መቆምን፥ ሇአበው መነኮሳት መቆርቆርን፥ ወዘተ "ይኸማ ፖሇቲካ ነው" በማሇት እንዯነውር መቍጠርና ሰው ኹለ አፉን እንዱሇጉም ማሸማቀቅ አይበጅም። እዚህ አዯናግሮ መውጣት ቢቻሌ ስንኳ፤ ዃሊ በምጽኣት በዏውዯ ሥሊሴ በታተቱ ጊዜ መሌስ ማጣት አሇና። .ያቁመነ በየማኑ!!! .