You are on page 1of 55

~1~

ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08
*

ላቢሪንት/ፈሩ ሲጠፋ – ርዕሰ አንቀጽ

ምድራዊ ገሓነምመጥፎ መናፍስትና አጋንንቶች
የተከለከለ መጠሪያ፤ የማይረሳ ፍጅት :-„ቱቲስ እና ሁቱ“

ጠንካራ ክንድና ነጻነት
አባይ :- ኢትዮጵያና ግብጽ

ጊዜና ሰው፣ የአዛውንት ጉባዔ

*

—-

~2~

ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08

ላቢሪንት/ፈሩ ሲጠፋ – ርዕሰ አንቀጽ

ላበሪንት

– የአዙሪት መናፈሻ ውስጥ ገብቶ መዝናናት -ውድ
አንባባቢ- ቀላል ነው። ከዚያ ሳይረፍድ ወይም ሳይመሽ በቀላሉ
መውጣት
ደግሞ
ከባድ
ነው።
አይቻልም።
የገቡበት በር ይጠፋል።ያቋረጡት መንገድ አንድ ይመስላል። ግራ ቀኙ
ተመሳስሎ ያደናግራል። የመውጫ በሩ እንደ መግቢያው አንድ ብቻ
ነው።
ታዲያ ከተገባበት መከራ መውጫ መንገዱ ብልሃቱ ምንድን ነው?
ግንቡን በመሰላል መዝለል? ወይስ ወደ ላይ መንጠልጠል? ጫካ ውስጥ
ቆሞ መጮህ?… በድፍረት መፏጨት? …መጸለይ? አንድ ተአምር ከላይ
እሰከ
ሚወርድ
ቁጭ
ብሎ
መጠበቅ?
ወይስ….?
ደራሲዎች አእምሮአቸው ክፍት ስለሆነና ብዙ ነገር እነሱ በአንዴ ማየት
ስለሚችሉ ቀላል መልስ መሰንዘር ይችሉበታል።

~3~

ኡምቤርቶ ኢኮ ያ „…በጽጌረዳ ስም..“ ብሎ ስለ አንድ የመካከለኛ ክፍለዘመን የገዳም መጽሓፍት ቤት ታሪክና የአርስጣጥለስ የፍልስፍና
ትምህርቶቹ ተማሪዎች እጅ ገብቶ (በአውሮፓ) ከመንፈሳዊ ትምህርትና
ከመልካም ሥራ ወጣት ልጆቹን አርቆ
„እንዳያበላሻቸው“
እነሱን
ስለሚጠብቀው አይነ ስውር ሊቀ ካህን
በተረከው ትልቁ የልብ ወለድ ድርሰቱ
ላይ አንድ ሰው የላበሪንት ገዳም- ሕንጻ
ውስጥ ገብቶ እንዴት እንደሚወጣ
በቀላሉ
ያሳየናል።
ብርድ የሚመክት ሹራብ ግን መልበስን
ይጠይቃል።
ደራሲው
ይህንኑ
ለወጣቱ
አልብሶታል።
ከአስተማሪው ጋር የአርስጣጥለስን መጽሓፍ የሚፈልገው ወጣቱ ልጅ
የገባበት ሕንጻና እግሩ የረገጠው ክፍሎች ከነመስተዋቱ እያነጸባረቁበት
ደረጃዎቹ መውጫና መግቢያውን ስለአዞሩበት ሽራቡን ሳያወልቅ ቀስ
እያለ ተርትሮ እንደ መንገድ ቀያሽ መሓንዲስ በእሱ እየተመራ የት የት
እንደ ነበረ ምንን እንዳለፈ በሚቀጥለው እርምጃ ምን ማድረግ እንደ
አለበት ያ ልጅ በዚያች በለበሰው ሹራብ ጉዞውን ሊረዳ ችሎአል።
መሓል
ላይ
የሹራቡ
ክርስ
ቢያልቅበትስ?
የአዙሪት መናፈሻ ውስጥ ተገብቶ በቀላሉ የማይወጣበትን ጫካ እንደ
ምሳሌ የወሰድነው አለ ምክንያት አይደለም። ውቅያኖስ ውስጥ ገብቶም
ወዴት እንደሚዋኝ (ደሴትም መሬትም ተራራም በማይታይበት
ወሃ)ግራ የተጋባውን ሰው እንደ ምሳሌም ልንወስድ እንችላለን።

ዓሣ ነባሪዎቹ ብቅ ቢሉበትስ!
አሁንም ከዚያ ከተገባበት ችግርና መከራ ለመውጣት እንደ ጫካው ጉዞ
መውጫ በሩ ማምለጫ መንገዱ ድፍንፍን ብሎ ጨልሞ ጠፍቶናል።
ይህን የማይመለከቱ አሉ።
እስቲ እራሳችንን አንድ ጥያቄ ብቻ እንጠይቅ። ከዚህ ሁሉ ግርግርና
ትርምስ
በሁዋላ
ምን
አተረፍን?
ለመሆኑ አሁን ማን ምን አተረፈ? ምንም ማለት እንችላለን!
~4~

ሁሉም ባዶ እጁን ነው የወጣው።
ንጉሣዊ ቤተሰቦች -ይህ አያነጋግርም- ምንም ያተረፉት ነገር የለም።
..አላተረፉም። መሣፍንቱና መኳንንቱ እንደዚሁ ባዶ እጃቸውን
ቀርተዋል።
ያ የሚፈራውና ግርማ ሞገስ የነበረው የኢትዮጵያ ሠራዊትና ፖሊስም
በመጨረሻው ወይ ሞተዋል ወይ ተበትኖአል። ደርግ ከአለ
ኮ.መንግሥቱና ከፍቅረ ሥላሴ ድርስቶች ሌላ ምንም ከእነሱ የተረፈና
የቀረ ነገር የለም።ጨፍረው ጨፍረው የት ደረሱ? ስደት እሥራት ሞት።

ብዙ የሚነገርለትና የሚወደስለት የተማሪው እንቅስቃሴ እና
ከእነሱ አብራክ የወጡት የፖለቲካ ደርጅቶች -እጭኣት
ኢህአፓ መኢሶን ወዝ ማሌሪድ …ዛሬ የት ናቸው?
ከጥቂት አመታት በፊት ጊዜው ለኢትዮጵያ „ነጻ-አውጪዎች ነው“
ተብሎ በሰፊው ተነግሮ አላስቀምጥ አላስቆም ብለውን ነበር።
ግን እነ ኦነግ እና እነ የደቡብ ሕዝቦች መላ አማራና አማራጭ
ኃይሎች…እራሳቸው አንዳንዶቹ የእህዴግ ተከታዮች ጭምር አሁን የት
ናቸው? የት ነው ያሉት?
ሻብዕያና ጀበሃ ሕዝባዊ ወያኔና ኦጋዴን አፋርና …እነሱ አሸናፊ ሁነው
ወጡ ሊባል ይችላል። ግን ምን አዲስ ነገር ለአገሪቱ ለሕዝቡ
ለተከታዮቻቸው
አመጡ?
ምን ያህል ሰው ነው እነሱን አሁን የሚከተላቸው? ምን ተአምር ሰሩ?
በእነሱ የሚያለቅስ የለም?
ምናልባት በኢትዮጵያ ውስጥ በተነሳው ትርምስ ያተረፉት ቻይና እና
ሕንድ አረቦችና አሰፍስፈው መሬቱዋን ለመግዛት የሚጠብቁ የውጭ
ኃይሎችና መንግሥታት ናቸው ልንል እንችላለን። አሁን ጥሩ ጨዋታ
ተጀመረ!

~5~

ሌላው እላይ የተባለውን እንደገና ለመድገም ከንጉሣዊ ቤተ ሰብ እሰከ
ተማሪው ድረስ ባዶ እጁን ነው የወጣው።
ለዚህ ደግሞ የስደተኛው ቁጥር ምስክር ነው። የደሃው ብዛት፣
የሚያማርረው ገበሬ፣ ልጆቻቸውን እያስታወሱ የሚያለቅሱ ወላጆች በቂ
ማስረጃ ናቸው።
ኤርትራ ተገነጠለች ተባለ።
ገነትን/ፓራዲይዝን አገኙ?

የተባለውንና

የተወራለትን

በአለፉት ሃምሳ አመታት ….ኦሮሞ ትግሬ አማራ ተባለ።
ለመሆኑ„አዲሲቱዋ ኢትዮጵያ ተመስርታ“ አንዲት የምታኮራ መርፌ
ብጤ እንኳን አገሪቱዋ ሰርታ የዓለም ገበያ ላይ አወጣች?
ትርፉ በሁሉም አቅጣጫ ኪሳራና ቢበዛ ደግሞ አለመደማመጥ ነው።
መደማመጥ እንኳን (እንደ አረቦቹ በአለመንጫጫታችን በጨዋነታችን
የምንታወቀው) ጠፍቶ (በኢትዮጵያኖች መካከል) በያለበት አሁን
መደናቆር ነው።
ቀደም ተብሎ የተሰማው እንደ አዲስ ነገር ዛሬ ተነስቶ ይደገማል። ጊዜና
ታሪክ መልስ ሰጥቶበት የታለፈው ነገር እንደ አዲስ ተአምር ይነሳል።
ሰው የሰለቸው መፈክር እንደ ገና ይወረወራል። በዘመናቸው
በጊዜአቸው ቁም ነገር ያልሰሩ ሰዎች ምንም ነገር እንዳልሆነና
እንዳልተደረገ „እንደገና እድሉን ስጡን“ ይላሉ። ችግሩ (የኢትዮጵያ)
ችግር ያለው ተራው ሰው ጋ አይደለም።
ችግሩ ያለው ፊደል የቆጠረው ሰው ጋ ነው። ችግሩ ያለው እነሱ
ያስተመሩአቸው
የሰበሰቡአቸው
ልጆችም

ነው።
አገሪቱ ከገባችበት ችግርና ቀውስ የምትወጣው ደግሞ በተያዘው
የስህተት ጉዞ ዝም ተብሎ በጭፍኑ ወደፊት ሲራመዱ አይደለም።
~6~

አንድ ቡድን ወይም አንድ ድርጅት ወይም ደግሞ አንድ ሰው ብቻውን
ወይም „ማዕከላዊ ኮሚቴው“ እንደሚባለው በሚሰጠው ውሳኔና መልስ
ላይ ብቻ ተመስርቶ አገር አይገነባም። መልሱ ለተገባው ችግር እሱ
አይደለም ።
እንደዚህማ ቢሆን ኑሮ ሶቭየት ኅብረት ምሥራቅ ጀርመን ሓንጋሪና
ፖላንድ ሩሜንያና ቡልጋሪያ…ደርግና ኢዲ አሚን ቦካሳና ቦታ ኢያን
ስሚዝ …እነዚህ ሁሉ ተንኮታኩተው በአልወደቁም ነበር።
ታዲያ ምንድነው ከተገባበት ላበሪንት- ከአዙሪት ጫካና ከዞረበት
መናፈሻ ለመውጣት መንገዱ? መድሓኒቱ? ብልሃቱ? ዘዴው የት ነው
ያለው?
በዚህ እትማችንም እንደ አለፈው ጊዜ ይህን ጥያቄ ቀስ እያልን እያነሳን
ለመመለስ እንሞክራለን።
ስለ ሰው ልጆች ባሕሪ እናነሳለን። …ክፋትና መጥፎ መናፍስቶችና
አጋንንቶች ከየት እንደመጡ እነሱን እንዴት መቆጣጠር እንደሚገባን
ከብዙ በጥቂቱ በጉዳዩ ላይ እንመላለስበታለን።
ስለታሪክ እናነሳለን። ስለ ፍልስፍና እንጠቅሳልን። ስለ መንግሥትና
አስተዳደር (እነዚህ ነገሮች አንድ አይደሉም) ስለ የፖለቲካ ሰዎች
ኃላፊነት ነካ ነካ አድርገን እናልፋለን።
ስለ ታሪክና ስለ ፖለቲካ ፍልስፍና ሲነሳ የሚናደዱና የሚቆጡ
የሚያላግጡና የሚያሾፉ፣ አለፈው ተርፈውም „ደማቸው የሚፈላ
ሰዎች“ እንዳሉ እናውቃለን።
ግን ደግሞ አለ ታሪክና አለ ፍልስፍና አለ ሃይማኖትና አለ ሞራል አለ
~7~

ምርምርና አለ ጥናት የኢትዮጵያን ባህልና ኢትዮጵያዊነትን መረዳት
አይቻልም።
እንዲያውም አውጥተን አውርደን የደረስንበት አንድ ነገር ቢኖር
የአገራችን
በሽታ
ያለው
አንድ
ቦታ
ላይ
ነው።
እሱም „መንግሥት“ የሚባለው ጽንሰ ሓሳብ ላይ ነው። ከእሱ ለየት
የሚለው „አስተዳደር“ የሚባለውም ነገር ላይ ነው። „አገር“ የምባለውም
ቃል ትክክለኛ ትርጉም ተፈልጎ በአለመገኘቱና መልስ ስለአልተሰጠውም
እንላለን።
እነዚህ ሦስቱ (ስቴት ኔሽን ገቨርንመንት) የሰው ልጆችን አሰባስበው
በተለያዩ ባህሎችና በተለያዩ ትውፈት በተለያዩ ትሩፋትና እሴቶች …ሥነ
-ምግባር እንዲኖሩ ያደረጉ ኮንሰፕቶች (የቻይናው ከሕንድ ይለያል
የጀርመኑ ከፈረንሣይ…) በኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ዘንድ „አንድ“
ተደርገው ተጨፍልቀው በመታየታቸው ነው።
ይህ ደግሞ ሁሉም ሕዝቡም አገሩም መንግሥትም አስተዳደርም „የኔ
ነው“
ወደሚለው
የአንድ
ቡድን„ጠለፋ
ይወስደናል።
ዕውነቱን
ከተናገርን
ከዚያም
አልፎ
ይሄዳል።
…አገርም ብቻ ሳይሆን የአገር ንብረትም መሬቱም ባንኩም ሠራዊቱም
ጦሩም የጸጥታ ፓሊሱም ትምህርት ቤቱም ዩኒቨርስቲውም ንግዱም
ሕንጻውም መንገዱም እርሻውም „የአንድ ፓርቲ የአንድ ቡድን …“
ተደርጎ ይታያል። ከዚያም አልፎ “አንተ አታስብ እኔ ነኝ ለአንተ
የማውቀውም” ወደሚለው ዛቻና ጥላቻም ተሸጋግሮአል።
ምን ይደረግ ነገሥታቱም እንደዚህ አድርገው አገሪቱዋን ቀደም ሲል
ስለአዩ ወጣቱ ትውልድም “ለእሱ ብቻ” በየፊናው „አደራ ተብሎ
የተሰጠው“ ይመስለዋል።
ይህ ደግሞ ወደ „…ይገባኛል …ለእኔ ብቻ ይገባኛል“ የሚል ቋንቋና
አመለካከት ፍልስፍና የድርጅት መሪዎችንና ተከታዮቹን ወስዶ
ኢትዮጵያን እዚህ አሁን ያለችበት ደረጃ ላይ አድርሶአታል።
ይህ ብዙ ነገሮችን እንድንረዳ ይጠቅማል።
~8~

የኢህፓና የመኢሶን „ጠብ“ የምንረዳው የደርግና የሻብዕያ የጀበሃና
የሻብዕያ የወያኔእና የኢዲዩን የኦነግና የወያኔን የደቡብና የኦጋዴን አንዱ
ከአንዱ ጋር ግንባሩን እየቀየረ „መዋጋት“ የምንረዳው „አገሪቱን
ለመግዛት ሕዝቡን ለመምራት መሬቱን ለመያዝ በትረ-መንግሥቱን
ለመጨበጥ ሠራዊቱን ፓሊሱንና ፍርድ ቤቱን እሥር – ቤቱን
ለመቆጣጠርና ለማዘዝ …እኔ ብቻ ታሪካዊ ኃላፊነት አለኝ ይገባኛል“
ከሚለው ፍልስፍና የመነጨ ነው። ችግራችን እሱ ነው።መኳንንቱም፣
መሣፍንቱም ይህን ብለው ይህ ከአልሆነ ብለው ተናንቀዋል።
ነገሥታቶችም።
ይህን የሚቃወምና የሚተች ሌላም መፍትሔም አለ እኮ እስቲ እሱን
እናሰላስል የሚል ሰው ወይ „ይደመሰሳል“ ወይ „ ይቀጣል“ ወይም
አገሩን ጥሎ „እንዲሰደድ“ ይገረጋል። ወይም ደግሞ አፉን በጠበንጃ
ፍረሃት ይዞ እንዲቀመጥ ይገደዳል። አልፎም የስም ማጥፋት ዘመቻ
ይወርድበታል።ነገሮችን ለመረዳት፣ ስለ እብሪተኛው ቄሣር ስለኔሮም
ያነሳነው ለዚህ ነው።
እሱን ብቻ አይደለም።
ስለ እባብም አንስተናል።
ስለ ሰይጣናና ስለ ሳጥናኤል ተርከናል። የፕላቶና የሶቅራጥስንም ምክሮች
ጎትተን የጠቆምነውም ከገባንበት ለመውጣት ማሰብ ማጥናት ማመዛዘን
አለብን የሚለውን ጥበብ ለመጠቆም ነው።
ሰይጣን አለ ወይ ? ብለን እራሳችንን ጠይቀናል። ለመሆኑ እንደሚባለው
እኛ ጥቁሮቹ ተረግመናል? ወይስ ነጮች ተመርቀዋል? የሚለውንም
ጥያቄ ሰንዝረናል።
ጥፋተኛው ገዢው መደብ ብቻ ሳይሆን ሰዎችም „ጠንካራ ክንድ“
የማየት ድክመት እንዳላቸውም አብረን አንስተናል።
ወረድ ብለን ከስንት አመት በሁዋላ ተለያይተው ስለ ተገናኙት ስለ
አዛውንቶች ጉባዔም -ከዚህ ሁሉ የትርምስ ዘመን በሁዋላ – ስለ እነሱም
~9~

በዚሁ ጽሑፋችን አንስተናል። ተገናኝተው እነሱ ሰለካሄዱት ወጎችም
ከብዙ በጥቂቱ ጠቅሰናል። ይህ ደግሞ ከገባንበት ላበሪንቱ ለመውጣት
በሚደረገው ጥረትና ሙከራ ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል የሚያሳይ
ይመስለናል።
ፖለቲካና የፖለቲካ መፍትሔዎች በንግግር እንጅ በጡንቻ አይፈቱም።
ድል አድራጊውም ይመስለዋል እንጂ ድሉ ቋሚ አይደለም። ሁሉ ነገር
ይቀየራል ። ይለወጣል። ይሻሻላል። ያልፋል። ሰውም ይሞታል አዲስ
ነገርም ይበቅላል። ከጨለማ በሁዋላ የጸሃይ ብርሃን ቦግ ይላል።
ጥያቄው ዱሮም አሁንም በምን አይነት ሥርዓት ውስጥ በእሱም ሥር
እንኑር የሚል ነው?
ሰው ሰይጣን ነው። ሰይጣንም ሰው ነው። ሁሉ ሰው ግን ሰይጣን
አይደለም። በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ማንም መብቱን
የማይረግጠው ነው።
መልካም ንባብ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ዋና አዘጋጅ
—-

—-

ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08

~ 10 ~

ምድራዊ ገሓነም
መጥፎ መናፍስትና አጋንንቶች
ሰይጣንሰውነውሰውምሰይጣንነው

…ገሓነም ባዶ ነው። አጋንንቶች ሁሉ ከዚያ አምልጠው ሸሽተው
የሚገኙት እኛው መካከል ነው። አንዳንዶቹ አታላይ መሲህሆች ናቸው።
ሌላው በነብይ ስም ቆሞአል። ነጻ-አውጪ አለ።ከችግር ጠባቂ ዘበኛ።
እራሱን ከመሬት ተነስቶ የነፍስ አባት ያደረገ አለ።መንገድ መሪ።የጦር
አዛዥ ፊታውራሪ።አርበኛ መሳይ። ከባውን የቀየረ ቄስ። ሰባኪ።
ግማሹ ብድግ ብሎ ከመሬት ተነስቶ እራሱን የሾመ አገረ ገዢም
ወጥቶታል።
ዕውነተኛውን ከአታላዩ ዱሮም ዛሬም እንዴት ማወቅ እንዴት መለየት
ይቻላል?
በሥራው!
~ 11 ~

የሮሙ ቄሣር ኔሮ በዕብሪት ልቡ አብጦ – እሱ እራሱን አምላክ አድርጎ
አይቶም ሊሆን ይችላል – እሳት ለኩሶ ከተማይቱን ሲያጋይ ሠገነቱ ላይ
ቁጭ ብሎ ሙዚቃ እየሰማ እና ክራሩን እየተጫወተ ሰው ሁሉ ነፍሱን
በዚያን ሰዓት ለማዳን ብድግ ብሎ ሲያመልጥ ከተማይቱዋም በዚያን
ዘመን ያኔ ፈርሳ አመድ ሲትለብስ ትርምሱን እግሩን ዘርግቶ – በዘመኑ
የነበሩት እንደጻፉት እና እንዳስተላለፉልን እሱ ከላይ ሁኖ እሱ እየሳቀ
ግርግሩን ይመለከት ነበር።
ለቀናት ለተራቡ አንበሳና ነብር ክርስቲያኖችን ወርውሮ እሱ በሌላ
ጊዚያቶች እዚያው ኮለሲዩም ስታዲዮም ውስጥ -ዳቦና ጨዋታ ለተራው
ሕዝብ በሚባለው ፍልስፍና- በአውሬዎች እነሱ ሲቦጫጨቁ እሱ ቄሣሩ
ከትዳር ጓደኛዋ ጋር ወይኑን እየተዝናና ይጎነጭ ነበር ።

ሳይናገር በአውራ ጣቱ ብቻ ይወስናል። ደስ እንዳለው አንዴ ወደ ላይ
ወይም ወደ ታች በማሳየት በግላዲያተሮች ሕይወት እዚያው (ጠበቃ
የለ) ፍርዱን ይሰጣል። አጃቢዎችም የእሱን ፊት እያዩ -ደስ ለማሰኘት
አብረው ይስቁ ይሳለቁም ነበር።
በአረመኔነቱ በታሪክ የሚታወቀው ኔሮ ብቻ አይደለም። አነጣጣሪ
ተኳሾች አሉ። እሥረኛ ሲገርፉና ሲያሰቃዩ የማይከብዳቸው ሰዎች ብዙ
ናቸው።ሲያዋክቡ ሲቆጡ የሚረኩ አሉ። አብዮታዊ እርምጃ ሌላው
አስገራሚ ውሳኔ ነው ።
~ 12 ~

አንዱ የሮማው ቄሣር በእብሪት መንፈስ ተነሳስቶ ጥቁር ፈረሱን የሕዝብ
እንደራሴ አድረጎ ሾሞታል። ቄሣሩም ካሊ ጉላ ይባላል።
ይህን ለመረዳት ጨርሶ ጥንታዊ ሮም ላይ መቆየት አያስፈልግም።
በመካከለኛው አፍሪካ በቅርቡ አንዱ ጎረቤቱን ገድሎ ታፋውን ቆርጦ
እዚያው የፈረንሣይ ወታደሮች እያዩት በያዝነው 21ኛው ክፍለ ዘመን
በልቶአል። ሌሎቹ ቤንዚን አርከፍክፈው የወደቁትን ጎረቤቶቻቸውን
ተመልካቹ እያጨበጨበ አቃጥለዋል።
አይሁዶችን ሒትለር ሰብስቦ ፈጅቶአል። ስታሊን „ጸረ-ሶዣሊዝም „
የሚላቸውን ለየት በአለ መንገድ ሳቤሪያ አድርሶ እነሱን ጓደኞቸን ወደ
ሞት ሽንቶአል።
በቀበሌ እጅ በአብዮታዊ እርምጃ በጫካና በጦር ሜዳ …ኢትዮጵያኖች
ከዳተኛ ተባብለው እርስ በእራሳቸው ተጨራርሰዋል። በኡጋንዳ ስምንት
መቶ ሺህ ሰው አልቆአል። በሱማሌ ቅጥራቸው አይታወቅም።
ለምንድነው የሰው ልጆች/ የሰው ልጅ የሌላውን ሰው ደም የወንድሙን
ከመሬት ተነስቶ በከንቱ የሚያፈሰው?
ሰይጣን ስለተጠጋቸው? አእምሮአቸውን አጋንንት ሰለ አሸነፈው?
በመናፍስቶች ስለተከበቡ? ልባቸው በሳጥናኤል ስለ ተሰለበ? ጋኔን
ስለሚጋልባቸው? ወይስ እነሱ ወደው ጋኔን ስለሚጋልቡ?
መልሱ መልሶቸ ቀላል አይደሉም።
“..እኛን ጥለህ አነተ መሄድህ ነው።… እንዴት ብለን እንጸልይ ብለው
ክርስቶስን ሲጠየቁት:„…አባታችን ሆይ ስምህ ይቀደስ መንግሥትህ ትምጣ ፈቃድህ በሰማይ
እንደሆነ…ከክፉ! ከክፉ ሁሉ አድነን ብላችሁ…ጸልዩ አላቸው።“
~ 13 ~

በአገራችን ኦርቶዶክስ ኢትዮጵያኖች „…እመቤታችን ሆይ…“ የሚለውን
የጸሎት መስመሮች ከካቶሊኮቹ
ጋር ሁነው ጨምረውበታል።
ከዚያ ወዲህ ወይም ከዚያም በፊት
„…ክፋት እና መጥፎ ሥራን
በደልንና ጭቃኔን መዋሸት እና
ማታላልን“ አንድን ልጅ አባቶች
ሲመክሩ ከዚህ ራቅ ከዚህም
ተጠንቀቅ ይህን ከልብህ አውጣ
…ተው“ ብለው ያስተምራሉ።
ከክፋትና ከክፉ ሰው ከአረመኔና ከቀመኛ ከመጥፎ ሥራና ሃሳብ
ከአጸያፊ ተግባሮች…ወላጆች ይህን ከሚያደርጉና ከሚመክሩ ሰዎች
ቢቻላችሁ ራቁ እናንተም አታድርጉ በእንደዚህ ዓይነት አስተሳሰብ
የተበከሉትን አጠገባችሁ አታድርሱ ብለውም ያስጠነቅቃሉ።
„…ይመክራሉ ያስተምራሉ“ የሚለው ቃል የሰውን ልጅ ወደ ሚገራው
ወደ ትምህርትና ወደ መልካም አስተዳደግ ወደ ወግና ወደ ሥርዓት ወደ
ጥበብና ወደ ዕውቀት አንድን ሰው – በሕይወት ዘመኑ ኮትኮቶ
የሚወስድ ተጨማሪ መንገድ እንዳለ ያሳያል።
ይህን ተገንዝቦ ፕላቶ በሰው ልጆች ታሪክ (የአይሁዶች ትምህርት ቤት
ነበር)
የመጀመሪያውን
አካዳሚ
መሰረተ።
በግሸን አምባ ሌላው የኢትዮጵያ መሣፍንት ልጆች ትምህርት
የሚቀስሙበት አዳሪ ትምህርት ቤት -ይህን አንዳዶቹ እሥር ቤት
ይሉታል- ተከፍቶ እዚያ ወጣቶች አስተዳደርና አነጋገር ነገር ማየትና
ማገናዘብ ይማሩበት ነበር።
ከዚህ ጋር-ቀደም ሲል- በርካታ ጥንታዊ ገዳሞች ትላልቅ በሁዋላ
አገሪቱን የሚመሩና የመሩ ሰዎች የፈለቁበት ትምህርት ቤቶች
ተቆርቁረው ተከፍተዋል ።
በአክሱም ቤተ- መንግሥት በጥንታዊት ኢትዮጵያ የግሪክ አስተማሪዎች
~ 14 ~

ያኔ መጥተው ፍልስፍና እና አስተዳደር፣ ክርክርና ሪቶሪክ ሎጆክና ታሪክ
በሚያስተምሩበት ዘመን የቤተ መንግሥቱ ቅጥር ግቢና የመሣፍንቶቹ
ቪላ የወጣቶች መኮትኮቻ ትምህርት ቤት እንደ ነበር ተጸፎአል።
ግሪኮች „ክፋትና የኃጢአት ሥራ“ ከአለማወቅ የሚመጣ ባህሪ ነው
ይላሉ። ይህ አነጋገር ዕውነት ይሆን?
ፈላስፋው ሆብስ ነው – ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይሆን ሌሎቹን ከእሱ በፊት
የነበሩትን አሰተማሪዎቹን ተከትሎ „…የሰው ልጅ አውሬ ነው። እንደ
አውሬ እንድን ሰው እንድ ተኩላ አንድ ቀን አረሳስቶት ቦጭቆት
የሚሄደው ያ ሰው እሱን የሚመስል ሌላ ሰው ነው።“ ከእሱና ከእነሱ
እነሱንም ከሚመስሉ ተጠንቀቁ ብሎ ሌቪታን በመባል የሚታወቀውን
መጽሓፉን እሱ ደርሶአል።
ለጆን ሎክ ይህ መቦጫጫቅ እንዳይመጣ እሱ የሰጠው መልስ አጭር
ነው።
መቻቻልና የሌላውን አመለካከት አክብሮ ማዳመጥ መደማመጥ ዋና
የመግባባት መነሻ ነው ይላል። እሱም ብቻውን በቂ እንዳልሆነም
ያነሳል። አልፎም ሄዶ ሎክ ቁጥጥር እንደ ሌሎች ምሁሮች በሰው ላይ
ማካሄድ
ያስፈልጋል
ይላል።
በአራተኛው
ክፍለ-ዘመን
የተነሳው
የክርስቲያና ሃይማኖት የሃዋሪያትን ወንጌል
አስተማሪ የሰሜን አፍሪካው ተወላጅ
አጉስቲኖስ
ኢንስቲትውሽን
-ተቋማት
መዘርጋት አለበት ይላል። ለእሱ ለአጉስቲኖስ
የሰው ልጅ በአውሬና በአምላክ መካከል
የሚገኝ ሳይሆን በተፈጥሮና በአምላክ
መካከል የሚገኝ ፍጡር ነው ይለናል።
የሰውን ልጅ በአራዊትና በአምላክ መካከል
በባህሪው የመደበው ሌላው ሰው የጀርመኑ
ፈላስ ሼልንግ ነው። እሱም ተመራምሮ
በደረሰበት ዕውቀቱ ይህን ፍጡር ሰውን ዝም ብለን አንየው
~ 15 ~

እንቆጣጠረው ብሎ ተጣርቶአል። ምክንያት አለው ምክንያቱም ሰው
ክፉም ደግም ነገር ለመሥራት ችሎታ ስለአለው ያለውም በመሆኑ ይህን
እሱ ሼልንግ ተገንዝቦ አደገኛነቱን በዘመኑ ጠቁሞአል። ማሠሪያው
ደግሞ ፍቅርና ሃይማኖት እንደሆነም አያይዞ ጽፎአል።
ቶማስ ጄፈርሰን ነው የሰውን ልጆች ጎትቶ በመላእክቶችና በአጋንንቶች
መካከል ያስቀመጠው።
በአንድ በኩል የሰው ልጆች በእሱ ዓይን -ምንም እንኳን ጥሩ ሰው
ለመሆን እንደ መላአክ በሥራቸው ለመምሰል ጥረት ቢያደርጉም- ሰዎች
በምንም ዓይነት ቅዱሳን አይደሉም ይለናል። እትመኑአቸው ብሎም
ያስጠነቅቃል።
በሌላ በኩል የሰው ልጆች እንደ ከይሲው እርኩሱ ፍጡሮች ሰይጣኖች
እንዳልሆኑም አንስቶ መልሶ ያጽናናል።
እንግዲህ ሰይጣን አይደለንም። ግን ለምን የሰይጣን ሥራ
በወንድሞቻችንና እህቶቻችን በጎረቤትና በዘመዶቻችን ላይ
እንጠነስሳለን?
ፈላስፋዎች እና ሳይኮሎጂስቶች „ሰዎች ሰይጣን አይደሉም „ስለዚህ
የሰውን ልጆች ሁሉ ዝም ብለን በጭፍኑ ከማመን እጅና እግራቸውን
በሕግና በሥልጣን ክፍፍል በትምህርትና በቅጣት ተብትበን እንያዝ
አለበለዚያ አይቻሉም ይሉናአል።
ጄፈርሰን ከቢጤዎቹ ጋር በዚያ የግለሰብን ነጻ-መብትን የሚያውቀውን
የአሜሪካንን ሕገ-መንግሥት ሁለቱን „ቁጥጥርና ነጻነትን“ አጥምሮ አብሮ
ነድፎአል

ክፉና መጥፎ ሰው አለ። ለምንድነው አንዱ ሰው ክፉ ሌላው ርሕሩህ
የሚሆነው?
ክፉና
መጥፎ
ሰው
ምንድነው?ምንድናቸው?
ለምንድነው ክፋትና ጥፋት በእንስሶችና በልጆች ዘንድ ሳይሆን በሰው
ልጆች ዘንድ ነፍሳቸውን በአወቁና ነገር በገባቸው ሰዎች ዘንድ በብዛት
የምናየው?
ክርስቶሰ እንደ ልጆች „ንጹሕ“ ሁኑ ብሎ ያስተምራል።
~ 16 ~

ለምንድነው
ሕጻናት
ክፋትን
አያውቁም
የሚባለው?
ሰይጣን እነሱን (ሕጻናትን) ፈርቶ ሰለማይጠጋቸው ይሆን? አጋንንቶችና
መናፍስቶች ልጆችን አይተው ሰለሚሸሹአቸው ይመስለናል?
ሰይጣን ወይም መጋኛ ወይም አጋንንት.. ዲያብሎስ አተላ ይወዳል
ይባላል። አመድ የሚፈስ ቦታ ይገኛል። በቀትር እየተዘዋወረ አላፊ
አግዳሚውን ጫካ ውስጥ ይለክፋል ይባልለታል። ደም መጠጣት
ይወዳል። ወንዝ ዳር ተኝቶ ድልድይ ሥር ተጋድሞ አድፍጦ ለቀም
ለማድረግ ይጠብቃል ተብሎም ይነገርለታል። መብረቅ ሲመጣ ደንግጦ
ሰው ላይ ይለጠፋል የሚሉ አሉ። …ፈሱም ኃይለኛ ሽታ አለው ይገማል
ይባላል።
የቬኑዙዌላ መሪ ሁጎ ቻንሰስ የአሜሪካውን ፕሬዚዳንት ሚስትር ጆርጅ
ደብሊዩ ቡሽን (ታናሹ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጉባዔ ላይ
ንግግር አድርገው ሲወርዱ ተራውን ተቀብለው አትራኖሱ ጋ ሲጠጉ
„ስለ ሰይጣን አንስተው አንድ ነገር ይሸተኛል…እሱ እዚህ ነበር። ጠረኑ
የእሱ ነው ይሸታል…“ የሚለውን ቃላታቸውን ለመንግሥታት መሪዎች
ወርውረው እኚህ ሰው አንዳንዶቹን ደጋፊዎቻቸውን እዚያው አስቀዋል።
ሌሎቹን ደግሞ አስቆጥቶአል።
ሰይጣን የሚባል ነገር ለመሆኑ አለ?ከአለስ የትነው ያለው? ወይስ
ለማስደንገጥ ብቻ የሚነሳ ስም ነው?
ለመሆኑ ሰይጣን ማን ነው?
አዲስ
ኪዳን
„…ከከፉ
ሁሉ
ጠብቀን“
በሚለውአረፍተ-ነገር እንደጀመረው ሁሉ ብሉይ
ኪዳንም ላይ ደግሞ „ ከዚህች ፍሬ አትብሉ
…አለበለዚያ ክፉና ደጉን አውቃችሁ ትሞታላችሁ“
በተባለው የጥበብና የሕይወት ዛፍ ታሪክ የሰውን
ልጆች ድራማ ይጀምራል።
„…ዝምታው ምንድነው በጥሳችሁ ብሉ እንጅ! „ ብላ በመጀመሪያ
ሔዋንን በሁዋላ አዳምን በተንኮል ምክርዋ በታለለቺው በዚያች እባብ
~ 17 ~

ታሪክ ይቀጥላል።አለ ምክንያት አይደለም የኢትዮጵያ ታሪክም በአንድ
ዘንዶ ታሪክ የሚጀምረው። በዚያ እንደ መስዋዕት በየጊዜው
በሚቀርቡለት ሴቶችም ወንዶችም ልጆች በመብላት በአስቸገረው ዘንዶ
ትረካ የሚጀምረው ታሪክ በንግሥና
ይቀጥላል።
በደፋሩ በአጋቦስ ብልሃትና ዘዴ ያ
ወጣት ልጆችን በየወሩ የሚበላው
ዘንዶው ይገደላል። አጋቦስ ሕዝቡ
ቃል በገባለት ውል እሱ በኢትዮጵያ
ላይ ይነግሣል። ልጁ ማክዳም ንግሥት
ሳባ ተብላ አልጋውን ትወርሳለች።
ሰይጣን አንዴ- በመጽሓፍ ቅዱስ- እባብ ተመስላ ብቅ ትላለች። ሌላ ጊዜ
ሰይጣን ተቀይራ በአለሰባት አንገት አውሬ ትሆናለች።
ሔዋንን በመጀመሪያ ነጥላ የሸነገለቺው እባብ በሁዋላ በተጻፈው
መጽሓፍ ላይ እንደምናነበው „…ሳጥናኤልን የዋጠቺው እሱም እራሱ
ዋጪኝ ብሎ እባቡዋን አታሎ ሸንግሎ በግንቡ ላይ በእሱዋ ብርታት
ከገሃነም ተስቦ አጥሩን ዘሎ ተንሸራቶ ገነት የገባው በእሱዋም አፍ
„…ዝምታው ምንድነው ከጥበብ ዛፍ ብሉ“ ብሎ የታናገረው ሰይጣን
ነው።
ተመሳሳይ ትረካ በቅዱስ ቁርኣን መግቢያም ላይ እናገኛለን።
መከራና ኃጢያአት ሞትና ጭንቀት ከዚያ ከበለሱ ፍሬ በሁዋላ በሰው
ልጆች ላይ የመጣ „መዓት“ ነው ብለው የሃይማኖት አባቶችም ይህን
ያስተምራሉ። እንግዲህ የሰይጣንም መነሻ የሰው ልጆችም መከራ በትንሹ ሲተረክ -እንደዚህ ነው።
ምድራዊ ፈላስፋዎች ግን ይህን
ታሪክ እግዚአብሔር አውቆ ሰዎችን
ለመፈተን ያስቀመጠው „ግሩም
ፈተና“ ነው ብለው በተራቸው
በሌላመልክ ነገሩን ተርጉመው
ያቀርቡልናል።
~ 18 ~

… እንዴት እንደምንኖር? እንዴትስ መኖር እንደአለብን? ለመኖርና
በሕይወት ዘመናችን ምን ምን መሥራት እንደሚያስፈልገን? የትኛው
ሥርዓት ውስጥ ብንኖር መንፈሳዊና ምድራዊ ደስታ እናገኛለን ብለን
በጭንቅላታችን
ተመራምረን
እንድንደርስበትና
አእምሮአችን
እንድንጠቀምበት „…የምርጫ ነጻነት“ አምላክ የሰጠበት ሰዓት ነው
ብለው እርምጃውን ብዙ ፈላስፋዎች (ሰለ ሰይጣን ሳይጨነቁ) ይህን
ጉዳይ አንስተው በእግዚአብሄር ሥራ ይደነቃሉ።
በገነት መናፈሻ ውስጥ ከአሉት ብዙ ዛፎች ውስጥ እግዚአብሔር
አዳምንና ሔዋንን „…ከዚህች ከጥበብ ዛፍ አንዲት ፍሬ እንዳትበሉ
ከበላችሁ ደግሞ ክፉና ደጉን ታውቃላችሁ…ትሞታላችሁ “ ማለቱ
በአንድ በኩል „ ትዕዛዙና ሕጉ እዲከበር“ ማስጠንቀቁ ቢሆንም
ይህን ባታደርጉ ደግሞ በሌላ
በኩል ትዕዛዙን ከአልሰሙ „
እራሳችሁን
ችላችሁ“
አእምሮአችሁን
ተጠቅማችሁ
በዚህች ምድር ላይ ጥራችሁ
ግራችሁ
ላባችሁን
አንጠፍጥፋችሁ
ትኖራላችሁ
ብሎ
እሱ
እራሱ
(ገና
ከመጀመሪያው)
አስጠንቅቆ
መልቀቁ ተገቢ ምርጫና የመምረጥ መብት ነው ይላሉ ። እንግዲህ
በየትኛው ሥርዓት ውስጥ ለመኖር እንደምንፈልግ ወሳኙ እኛ ነን።
የሆነውና የተከሰተው የሁለተኛው መንገድ ነው።
ከፍሬው በልተው ዓይናቸው ተከፈተ። እራቁታቸው መሆኑንም
አወቁት። ይህ ደግሞ በሌላ ቋንቋ የሥልጣኔ መጀመሪያ ነው።
በመጀመሪያ ቅጠል በጥሰው -መጽሓፉ እንደሚለው- ሓፍረታቸውን
ሸፈኑ። ቀጥለው ወደ እርሻና ከብት እርባታ ተሰማሩ። ደበሎና ሱፍ
ደረቡ። ቆይተው ጥጥ ዘርተው ለቅመው ፈትለው ሸማ ሠርተው
አጌጡ።
~ 19 ~

ለምንድነው ሌሎቹ ሲጌጡ የተቀሩት ራቁታቸውን አሁን ድረስ
የሚሄዱት? ለምንድነው ከልብስም በዘመናዊ ልብስ አጊጦ ተኳኩሎ
መውጣት በአውሮፓ እየተስፋፋ የሄደው? ለምንድነው በሌላው አካባቢ
መሸፋፈን
የነገሰው?
ለምንድነው ሌሎቹ ከአፈርና ከጭቃ ቤት ሲሰሩ የድንጋይ ቤቶች ጥበብ
ቪላና ትላልቅ ቤተ-መንግሥት መሥራት ሌላ አካባቢ የተጀመረው?
ለምንድነው የሮምና የፓሪስ የበረሊንና የሊሳቦን ሕንጻዎችና ቪላዎች
ከአፍሪካውያኖቹ በአሰራራቸው በውበታቸው በአቀማመጣቸው
የሚያማመምሩት?
ለምንድነው ነጮች ተከባብረው ተቻችለው አብረው ተስማምተው
ሲኖሩ አፍሪካ እርስ በእራሱ የሚጣበሰው?
ቆየት ብለን ወደ በሁዋላ እንደምናየው ገበሬው ቃዬል ከብት አርቢ
ወንድሙን አቤልን „በቅናት“ ተነሳስቶ ደብድቦት ይገድለዋል። ትንሽ
ዘግይቶ በሰው ልጆች ሥራ -አሁንም መጽሓፉ እንደሚለውእግዚአብሔር አዝኖ የወሃ ጥፋት ይከተላል። በአባቱ እርቃንነት ያላገጠ
ልጁን ኖህ ካምን ይረግመዋል። ሰዶምና ጎሞራ በእሳት ይቃጠላል።
የባቢሎን ግንብ ይፈርሳል።
„ከእንግዲህ አላጠፋችሁም“ የሚለው የመጀመሪያው ውልና ቃል-ኪዳን
ቀስተ-ደመና በእግዚአብሔርና በሰው ልጆች መካከል ይደረጋል።
በሁዋላ እንደምናውቀው ብዙ ፈላስፋዎች ይህን ሓሳብ መሠረት
አድርገው „ሶሻል ኮንትራት“ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተቻችለውና
ተከባብረው በጋራ የሚኖሩበት „የጋራ ቃል-ኪዳን“ ብለው የፖለቲካ
ቲዎሪአቸውን ነድፈዋል።
ይህ እንደዚህ አሁን እንደ ዋዛና ፈዛዛ እዚህ የሚተረከው ታሪክ አንድ
ሰው ከመሬት ተነስቶ ወንድሙን ወይም ጎረቤቱን ጠላቱንም ቢሆን
እንኳን „ አርዶ እንዳይበላው“ አጥብቆ ያግዳል። በዚህም…አትግደል
አትስረቅ አትዋሽ በሃሰት አትመስክር እናትህና አባትህን አክብር …የሚሉ
~ 20 ~

የሞራልና የኤትክ ሕግጋት ጋር የሰው ልጅ ይተዋወቃል። ያ ሕግ እነዚህ
ሕግጋት የሠፈሩበት የሙሴ ጽላትም የመጀመሪያው መተዳደሪያ ደንብ
ኢትዮጵያ በቀጥታ እንደ ደረሰም በታሪካችን ላይ እንመለከታለን። እሱን
ተከትሎ የክርስትና ሃይማኖት አገራችን ይገባል። ለመጀመሪያ ጊዜም
በዓለም ላይ የአንድ መንግሥት ሃይማኖት ሁኖ የክርስትና ሃይማኖት
በአገሪቱ ይታወጃል።
ባህላችን ታሪካችን ሥርዓትና ደንቡ ባህሪያችን በአገራችን የተመሠረበት
በአይሁድ በክርስቲያና ሃይማኖት ላይ ነው የሚባለውም ለዚሁ ነው።
ይህ አንደኛውን የሥልጣኔ በዚያውም የሰይጣን አመጣጥ መነሻ ታሪክ
ነው።-ቅዱስ ቁርኣንም ይህን ቦታ በቅጠሎቹ ላይ ይጠቅሳል ።
ሌላው አካባቢ ሌላው ባህልና ሥልጣኔ ሌላ እራሱን የቻለ አተራረክ
አለው። ከእኛ ባልራቁት በግብጻዊያን ቤት ከዚህ ለየት ያለ አቀራረብ
እንዳለ እናነባለን።በግሪክ አማልክቶችና
በጃፓኖች ዘንድ የፍጥረት አጀማመር
በሌላ ዓይነት ቀርቦአል።
የነፋሱ ንጉሥ ሹ በጥንታዊ ግብጾች
አመለካከት እንደ አክንባሎ አናታችን
ላይ የተዘረጋው ሰማይ አንድ ቀን
ተንኮታኩቶ ወድቆ ዓለምንና የሰውን
ልጆች እንዳይጨርስ እሱን ቀጥ አድረጎ እንደ ምሶሶ የያዘው ጀግናው
ንጉሥ „ንፋሱ ሹ“ ነው ብለው ያኔ እነሱ ያምኑ ነበር።
ሰማይና መሬትም ሚዛናቸውን ጠብቀው እንዲኖሩም የእሱ ፈቃድ
ብቻውን ወሳኝ ነበር። ሳት ብሎት ይህ ንጉሥ ወይም ተቆጥቶ ወይም
ጀርባውን ለማከክ አንድ እጁን መሸከሙን ትቶ ለቀቅ ከአደረገው ሰማዩ
ተንኮታኩቶ ወርዶ የሰውን ልጆች ሁሉ -መናገር አያስፈልግምያጠፋዋል ብለው ይህ እንዳይሆን እነሱ ይሰግዱለት ነበር።
ተንዶ ሰማዩ ከተሰበረ አማልክቶቹ ከሰማይ ላይ ተንሸራተው ወርደው
ከሰዎች ጋር ተደባልቀው ያልታወቀ ችግር በሁለቱ መካከል ይፈጥራሉ
~ 21 ~

ብለውም
ይፈሩ
ነበር።
ከዚያ
በፊትስ
ምን
ነበር?
የፈርዖኖቹ ታሪክ እንደሚለው ቀደም ሲል አማልክቶቹና የሰው ልጆች
በንፋሱ ንጉሥ ሳይለያዩ አንድ ላይ በዚህች ምድር ላይ ተደበላልቀው
ይኖሩ ነበር። በዚያም ዘመን የሰው ልጆች እየረበሹ የአምልክቶቹን
ጸጥታ ነስተው ረብሻ እዚህም እዚም ተነስቶ ግርግር ጩኸትን ትርምስ
በአገሪቱ ነግሦም ነበር። አማልክቶቹም ተቸግረው ሰዎችን ዝም
ለማሰኘት እነሱን እያሳደዱ ይቀጡ በጦራቸውም ይዋጉ ነበር።
ለጃፓኖች ሥርዓቱንና ደንቡን በሰው ልጆች መካከል ሳያዳለ እየዘረጋ
እንዲፈርድም እየፈረደም እንዲገዛ የጸሓይ ልጅ ንጉሥ ሁኖ እነሱን
እየተቆጣና እየቀጣ እንዲያስተዳድር ከሰማይ ለእነሱ -ታሪካቸው
እንደሚለው- ተልኮላቸዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እሰከ አሁን ድረስ
ሲወርድ ሲዋረድ ንጉሥ አኩሂቶ ላይ ደርሶአል።
በግሪክ አገር የአማልክቶች ጦርነት እኔ እበልጥ እኔ እሻል በሚባል
ፉክክር ገብተው ሶይስ የተባለው የአማልክቶች አለቃ (ተወልዶ)
እስከሚነሳ ድረስ በመካከላቸው ረብሻ ነግሶ በጦር እንደተፈላለጉ
ጊዜውን ገፍተው ነበር። ሶይስ ከመምጣቱ በፊት በምድርም በሰማይም
ላይ ይህ ነው የማያባል ረብሻና ትርምስ ብቻ ሳይሆን ግዲያና ፍጅት
ጋብቻና ቅሚያ ድፍረትና አመንዝራነት በአማልክት ልጆችና
በወላጆቻቸው በወንድምና በእህት (እንደ ሰው ልጆች እነሱም ይጋቡና
ይዋለዱ ነበር) ዝብርቅርቁ የወጣ የተጨማለቀ ልማድ በመካከላቸው
ሰፍኖ አንዱ ሌላውን ጭምር ይበላውም ነበር። (i
ሶይስ ብቻ አፈ-ታሪኩ እንደሚለው እናቱ አንድ አማልክት ሊደርሱበት
ከማይችሉበት ዋሻ ውስጥ ደብቃው እሱ ከሞት ይተርፋል።
አድጎ ጉልበት ገዝቶ ከዋሻው ሲወጣ ጦርነት በአባቱና በእህቶቹ
በወንድሞቹም ላይ ይከፋታል። አሽናፊ ሁኖ ወጥቶ ድል አድራጊው
ሶይስ- አፈ ታሪካቸው እንደሚለው- በቂም በቀል አባቱንም እህቶቹንም
ሳያጠፋ ምህረት አድርጎላቸው አባቱን በግዞት የእንድ ደሴት ንጉሥ
እህቶቹንና ከሞት የተረፉትን ወንድሞቹን ደግሞ የባህር ንጉሥ
የውቅያኖስ ንጉሥ የፍቅር የጦርነት የሐዘን …ንጉሥ እያለና እየሾመ እሱ
የሰማይ ንጉሥ ሁኖ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ሰማይና ምድርን ይገዛል።
የሥልጣን ክፍፍል በማድረጉ ሰላምና ጸጥታ በምድርም በሰማይም ላይ
ሰፈነ። ይህ ሁሉ ሲሆን የሰው ልጆች ቦታ የት ነበር? በግሪክ ትረካ የሰው
ልጆች ከየት መጡ? ለሚለው ጥያቄ የተለያዩ የአመጣጥ ታሪክ እንደ
~ 22 ~

አላቸው ይነገራል። (ii ጥንታዊ ግሪኮች ሰይጣንን እኛ በምናውቀው
ዓይነት እነሱ አያውቁትም። „ክፋትን“ ግን ምን እነደሆነ በደንብ
አድርገው ያውቃሉ። እንዲያውም „ክፋትን መክቶ የሚከላከል
አምላክ/አማልክት“
አለ
ይላሉ።
ይህ ደግሞ ለምን እኛን የሰው ልጆችን የሚፈታተን ሰይጣን
እግዚአብሔር ላከብን? ለምን ሰይጣንን ከእኛ አያርቅም? ለምን እንደዚያ
እየተፈራረቁ ሲያስቸግሩን ዝም ብሎ ያያል? እጁን ዘርግቶ ለምን
አያድነንም? የሚሉትን አቤቱታዎች ያስነሳል።
እናሳጥረው።
…ሰው ሰይጣን ነው። ሰይጣንም ሰው ነው።
ይህ አባባል ዕውነት ይሆን?
ወይስ ሰይጣን/ሰይጣኖች በአየር ላይ
ከንፈው/ከንፎ ሳይታሰብ ሰውን ወይም አንድን
አገር
አንድን
ሕዝብ
የሚያሰቃዩ
መናፍስት/መናፍሰቶች ናቸው?
ይህንና ይህን የመሰሉ ጥያቄዎች…ከቃዬልና
አቤል ከዳዊት እና ከጎሊያድ ከዩሊዮስ ቄሣር
እስከ ኔሮ እስከ ካሊ ጉላና እስከ ከኢቫን
ጨፍጫፊው ከስታሊን እሰከ ሒትለር ያሉትን ሰዎች የምንረዳውና
የምንመልሰው አእምሮአችንን ከፍተን ነገሮችን በትክክል ለማየት ስንችል
ነው።
ሕጻናትን የሚዳፈሩ የከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቄሶች አሉ። በኮሙንዝም
ስም እነ ኪም ኢል ሱንግ ሥልጣን ላይ ወጥተው
ውርርሱን ወደ ንጉሣዊ አገዛዝ ወደ አልጋ ወራሾች
ሥርዓት ቀይረውታል።
ትላንት ጫካ አንድ ላይ የነበሩ ሰዎች ዛሬ ጠላት
ሁነዋል። ትላንት „ዲሞክራሲና እኩልነት“ ይል
የነበረው ሰው ዛሬ ጊዜው አይደለም ይላል።
„…ሰው ሰይጣን ነው ሰይጣንም ሰው ነው“
~ 23 ~

የሚለውን አነጋገር የምንረዳው አንዴ ብቻ ሳይሆን አራት አምስት ጊዜ
አገላብጠን ስናየው ብቻ ነው። በኢትዮጵያ እና በኤርትራ በአሜሪካንና
በአውሮፓ በአረብ አገሮችና በቻይና በሕንድ በሩሲያና በጀርመን…
በአንድ ዘመን „ጨዋ“ የነበረ ሰው በሌላ ዘመን እንደዚያ አስፈሪ የሆነ
“አረመኔ ጦረኛ“ ይወጣዋል። ለምን? በምን ምክንያት ? ለምንድነው
በአስተሳሰብ የማይስማሙ ሰዎች ብዙ ቦታ በጭካኔ ተነሳስተው
የሚጋደሉት ? ለምንድነው በሌላ አካባቢ ሌሎቹ የተለያዩ አመለካከቶች
ቢኖራቸውም
የሚስማሙት?
ምናልባት በአንዳንዱ አካባቢ ሰይጣኖች ስለጠፉ? በሌላው አካባቢ
ሰይጣኖች አለቅጥ ስለ ተራቡ? አንዱ አካባቢ በእግዚአብሔር ስለ
ተረገመ ? ሌላው አካባቢ በእሱ ስለተቀደሰ? አንዳዶቹን እግዚአብሔር
በጣም ስለ ሚወዳቸው? ሌሎቹን በተቃራኒ ሰይጣን ስለ
ሚያፈቅራቸው? ወይስ ለእነሱ አሳልፎ ስለ ሰጣቸው? ወይስ
እግዚአብሄር እኛን ለመቅጣት ፈልጎ?
ፈጽሞ አይመስለንም።
ለነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች መልስ የምናገኘው ስለ ልቦና ስለ አእምሮ ስለ
ነፍስና ስለ ሥጋ…ስለ መንፈስ ደስታና ስለ ሓዘን ስለ ሰው ልጆች ባህሪ
„ጠለቅ „ ብለን „ጠጋ“ ብለን ለመመልከት ጥረት ስናደርግ ብቻ ነው።
ጥንታዊ ግሪኮች ከዕውቀታቸው ሲያካፍሉን መልሱ ይህን ይመስላል።
ሁለት አዛውንቶች ለብዙ አመታት ተለያይተውና ተራርቀው ከሰነበቱ
በሁዋላ አንድ ቀን ተገናኝተው ስለ የባጥ የቆጡ ስለ ዓለምና ስለ
እግዚአብሔር ስለ መንፈሳዊ ኑሮና ስለ ዓለማዊ ችግሮች ይጫወታሉ።
ሁለቱም በሁለት የተለያዩ ነገሮች የታደሉ ናቸው።
አንደኛው በስምና በዝና በአካበተው ሐብትና ንብረቱ በመንደሩና
በአካባቢው የተከበረ ጥሩ ስም ያተረፈ ትልቅ ሰው ነው። ሁለተኛው
ጥበብና በዕቀውት በብሩህ አእምሮው ከአገር ድንበር አልፎ የሚሄድ
እሱም እንደ ጓደኛው ትልቅ ስም ያተረፈ አዛውንት ነው። ከዚያም በላይ
~ 24 ~

ሁለቱም የእድሜ ባለጸጎች ናቸው። ሊቀ ሊቃውንቱ የልጅነት ጓደኟውን
ከስንት አመት በሁዋላ ሊጎበኘው በሩን አንኳኩቶ ገብቶ መጠጥም
ምግብ ቀርቦለታል። ሁለቱም ስለሚያሳስባቸው ስለ ፍርድና ፍትህ ስለ
መልካም አስተዳደር የቀረበላቸውን የወይን ጠጃቸውን እየቀመሱ ግሩም
ጨዋታ ይዘው ሐሳቦቻቸውን ይለዋወጣሉ። „…እርጅናው እንዴት
ያደርገኻል? እባክህን እስቲ ንገረኝ አጫውተኝ ወንድሜ።… እንደያው
እንደ ዱሮ እንደ ወጣትነት ዘመንህና ዕድሜ ወዲያ ወዲህ በእግርህም
በፈረስህም እንደልብህ አለማለትህ ትንሽ ቅር አያሰኘህም…ወይ “ ሊቁ
ይለዋል። ዕድሜም ገንዘብም የተሰጠው ሓብታሙ „…አይ አንተ ደግሞ!
እሱማ እየደከሙ መሄድ የተፈጥሮ ሕግ ነው። በዚህ ዕድሜአችን
የማይመጣ ነገር የለም። እንደ አመጣጡ ከተቀበልነው ደግሞ
አይቆረቁረንም።“
ሊቁ:- „የፍቅር ነገር፣ የስሜት ዓለምህስ እንዴት ነው? ስሜትህ
በመብረዱ አታዝንም?“ ቱጃሩ „…ይገርመኻል አታምነኝም እሱን
መገላገሌ አንደ ከባድ ነገር ከትከሻዬ ላይ አራግፌ እንደጣልኩት ሽክም
ይህል ነው። ተገላግዬ አለሁ።“ ሊቁ:- „…ሰላምና ጸጥታ ዕረፍትም
ጭምር እድሜ ከፍ ሲል ለእንደ እኛ ዓይነት ሰዎች ሰውነታችን የሚሻው
ነገር ነው። እጅግ ደስ ይላል። ግን ካለሓብትና ከአለንብረት ሁሉ ነገር
ይጨንቃል።…ለእነሱስ -ገንዘብ አስፈላጊ አይደለም?“ ቱጃሩ:- „ በእርግጥ
ንብረትና ሓብት ብዙ ነገሮችን ያቃልሉልናል። ከዚያ በላይ ግን አስፈላጊ
አይደለም። በሓብት መካበት የሚደሰት ሰው ጥቂት ነው። ሁሉም ሰው
አይደሰትም። ለእኔ ንብረት ማለት የሚገባኝን ሠርቼ ማግኘት እንጂ
ሰዎችን መክፈል ከሚገባቸው በላይ ጠይቄ ሓብትን በማይሆን መንገድ
ማካበት አልፈልግም። እንደ ደንቡ ሰዎች የሚፈለጉትን
አቀርብላቸዋለሁ። የሚገባውንም ሒሳብ እጠይቃለሁ። የቸገረውንም
እረዳለሁ። ለአምላክም ተገቢውን አሥራትና መስዋዕት አቀርባለሁ።
አገባለሁ። በሐብት ብዙ ጥሩ ነገሮችን ማድረግም ይቻላል። „
ሶቅራጠስና ሓብታሙ ጓደኛው ኬፋሎስ ይህን የመሰለ ውይይት
ሲያደርጉ አጅበውት የነበሩት ተማሪዎቹ ከባዱን የፍልስፍና ውይይት
አስተማሪአቸው እገረ መንገዱን ይከፍታል ብለው ተስፋ አድርገው
ይጠባበቁ ነበር። ሶቅራጠስ ግን ጓደኛው በሕይወት ዘመኑ ሠርቶ ጥሮ
ግሮ በደረሰበት ደስተኛ ውጤቱና የሕይወት ልምምዱ ከእሱም
~ 25 ~

በሰበሰበው ተመክሮው በውይይቱ ላይ በማዳመጡ እጅግ ተደስቶአል።
የተደሰተበትም ምክንያት አለው። ይህ ሰው በትውፈት የተደገፈ
የተስተካከለ ሕይወት በመምራቱ ነው። ኬፋሎስ የተማሪዎቹን
መቁነጥነጥ አይቶ “ከእንግዲህ የተቀረውን እናንተው ተፈላሰፉበት እኔ
ግን ለአማልክቶቼ መስዋዕቶቼን ለማደርስ እወጣለሁ” ብሎ ሜዳውን
ለፈላስፋዎቹ ለአስተማሪውና ለተማሪዎቹ ለቆ ይወጣል። መልካም ሥራ
አንግዲህ -ከንግግሩ ላይ እንደምናየው ፖለቲያም የተባለው መጽሓፍም
ላይ ተጽፎ እንደምናነበው- እንደዚህ ዓይነቱ ነገር ነው። ተቃራኒው
ደግሞ „ክፋት“ ነው።
ክፋትና አጥፊ እርምጃ ምንድናቸው?
ኪፋሎስ ሜዳውን ለቆ እንደወጣ
የሶፊስቱ
ቁንጮ
ዋና
መሪ
ትራሲማኮስ የሚባለው ፖለቲከኛ
መድረኩን ተረክቦ „…ጥሩ ነገር
መሥራት ማለት እኔን የሚጠቅም
ሥራ መሥራት ነው።“ ብሎ
ንግግሩን ለተማሪዎች ይከፍታል። „..
በተፈጥሮ ሁሉም የሰው ልጅ እኩል አይደለም። ስለዚህ ጠንካራው
ጊዜው የሰጠውን ሓብትና ሥልጣንም ከሌሎቹ ተከላክሎ ለእራሱ
ሕልውና መቆየት ሲል ጥዋት ማታ መሥራት አለበት። ሁሉንም ነገር
ጠቅልሎ በእጁ ሲያስገባ ብቻ ነው እሱ አርፎ መተኛት የሚችለው።
አስፈላጊ ከሆነም ቢቻለው ፈላጭ ቆራጭ -ታይረን መሆን አለበት።
ከጠንካራ አመራርና ከጠንካራ ሕብረት አንጻር ስንመለከተውና ስናየው
እንደዚህ ዓይነቱ ሥርዓት መኖር ደግሞ ተገቢና ትክክል ነው።“
የሚለውን አስተያየቱን ይሠነዝራል።
„ይህማ!… ይህን ማድረግና ይህን እንደ ትክክለኛ አማራጭ ማየት
መጪውን የእርስ በእርስ ጦርነትና ግጭት በሕዝብ መካከል በቀጠሮ
እንደ ማሳደር ነው። ይህ ከሆነ በገዢና በተገዢዎች መካከል ያለው
ጥላቻና ለመተናነቅ መፈለለግ አንድ ቀን መምጣቱ የማይቀር ጉዳይ
ነው።“
~ 26 ~

ተገዢው ክፍል ዝም ቢል እነሱን መርተው ሥልጣኑን ለመንጠቅ
የሚፈልጉት ክፍሎች እሳት ከመለኮስ አይመለሱም። ገዢውም ደህና
እንቅልፍ ሳይወስደው ሁሌ እንደቃዣ -ከአሁን አሁን መጥተው አነቁኝ
ብሎ በሰቀቀን የሚኖር ነው። እንደዚህ ዓይነቱ አስተዳደር መገላመጥ
ያበዛል። የእራሱን ጥላ እንኳ ሲያይ ይደነግጣል። እንደ ተደበቀ
እንተቅበዘበዘ እንደ ተጣደፈና ከሰው እንደራቀ አንድ ቀን ሳይደላው
እፎይ ብሎ ሳያርፍና የሰበሰበውን እንኳን ሳይበላ ልጆቹም ምንም
ሳያገኙ ጠላቶቹ እጅ ይወድቃል። መልካም አስተዳደር አመጣለሁ ብሎ
የተነሳው ሰው ወደ ጭቆና ይሸጋገራል። እገነባለሁ ያለውን ሕብረተሰብ
በዚህ መንገድ ያፈርሳል። እረዳለሁ ብሎ የተናገረውን ቃሉን ወደ ጭቃኔ
ይቀየራል።
ሥልጣን ለእሱ ለገዢው ጣፋጭ እንደሆነቺው ሁሉ ለተራ ሰው
ለተገዢው
ቋቅ
የሚል
መራራ
ሬት
ትሆናለች።”
ሶቅራጠስ ይህን ዘርዝሮ እስቲ እንደ ሐኪም ለአንድ ሕብረተስብ አንድ
መፍትሔ ዝም ብለን ከመወርወራችን በፊትና ተቀበሉት ብለን
ከማስጨነቃችን በፊት እንደ እነሱ እንደ ሓኪሞቹ ረጋ ብለን
እናስብ”ይላል። ሐኪሙ መራራ መድሓኒቱም ለበሽተኛ ከመስጠቱ በፊት
ምን ዓይነት መድሓኒት በሽተኛው እንደሚስፈልገው ጠጋ ብሎ ጊዜ
ወስዶ መመርመር ይኖርበታል። መርምሮ ከዚያ በሁዋላ ተገቢውን
መድሓኒትና ሕክምናም ያዝለታል። እሱንም ያደርግለታል።
ብዙ ሰዎች አንድ ላይ ተሰባስበው ለዘመናት በሚኖሩበት ሕብረተሰብም
ውስጥ አንድ መፍትሔ አንድ ሰው ወይም ሁለት ሰዎች ከማቅረባቸው
በፊት እንደ ሓኪሙ እነሱ በመጀመሪያ በዘመናዊ አነጋገር ለመናገር ያን
አካባቢ የግድ መመርመር ይኖርባቸዋል። ሶቅራጠስ እነዚህ ሰዎች
መፍትሔ መድሓኒት ለአንድ ሕብረተሰብ ከማዘዛቸውና ከመስጠታቸው
በፊት የሰዎችን /የሰውን ልጅ የተፈጥሮ ባህሪ በመጀመሪያ መመርመር
ይኖርባቸዋል ይላል።
ምንድነው የሰው ልጆች ከእንሰሳ የሚለያቸው የተፈጥሮ ባህሪ? ይህን
ባህሪ ለመረዳት ሁለት መንገዶች አሉ።

~ 27 ~

አንደኛው የፕላቶ ተማሪ የታላቁ እስክንድር አስተማሪ የሆነው
አርስጣጥለስ የነደፈው
ኢምፔሪካል ጥናት ነው።

ዘመናዊ

ሳይንስም

አሁን

የሚከተለው

ሁለተኛው መንገድ ፕላቶና አስተማሪው ሶቅራጠስ የሚሉት የሰው ልጅ
እራሱን ከፍ አድርጎ አስተካክሎ ሊደርስባቸው የሚፈልጋቸው የመኖር
ዘይቤ ናቸው። ይህን ለማስረዳት ፕላቶ ሙዚቃንና የከዋክብቶች
አቀማመጥን እንደ ምሳሌ ይወስዳል።
መንፈስን የሚያድሰው እንደ የሂሳብ ትምህርት ሥርዓት የተቀነባበረው
የሙዚቃ ድርሰትና ማታ ማታ አንገታችንን ከፍ አድረግን ሰማዩን
ስንመለከት የምናያቸው የክዋክብቶች ቅንብር ቁንጅናቸው -ሓርሞኒ
ይለዋል- አቀማመጥ ናቸው። ፕላቶ ይህን ነገር በሌላ ምሳሌ ለማስረዳት
ብዙ ፈረሶች በአንድነት የሚጎትቱን ሠረገላም አድርጎ ያቀርበዋል።
ፈረሶቹ በአንድነት ካአልረገጡና ሠረገላውን በሶምሶማቸው
አስተካክለው ከአልሳቡት ወይ ሠረገላውን ይገለበጡታል ወይም
ይሰብሩታል ወይም ደግሞ ከቆሙበት ፈቀቅ አይሉም። ይህ „ይሰበራል“
የሚባለውን ነገር ደግሞ እንደ ፕላቶ እንደ እሱ የሚያስፈራው ነገር
የለም። አንድ ሕብረተሰብ ተንኮታኩቶ ከወደቀ ደግሞ ከዚያ በሁዋላ
ምን እንደሚመጣ? ማን እንደሚተካው? ምንም የሚታወቅ ነገር ስለ
ሌለ አትንቀጅቀጁ ተማሪዎቹን ይላል ። ፕላቶ “አብዮት” የሚባላውን
ነገር ከዚህ ተነስቶ አይወደውም። ይህም የክፋት ሥራ ከየት
እንደሚመጣ መልስ እንድንፈልግ ይረዳናል።
ለምንድነው ሰዎች ክፉ መጥፎ ሥራ
የሚሠሩት? ….አውቀው ነው ወይስ
ሳያውቁ? እነሱ እራሳቸውን ገደል
ለመክተት ፈልገው ነው ወይስ “ጥሩ”
ሥራ
እየሰራን
ነው
ብለው
በማመናቸው ነው?
ለእነዚህ ጥያቄዎች አንደኛው ፈላስፋ
ሶቅራጠስ ጥሩ መልስ የዛሬ ስንት ሸህ
አመት መልስ ሲሰጥ „ሳያውቁ ምንም
ነገር በአለማወቃቸው መሓይም
~ 28 ~

በመሆናቸው ነው…“ ይላል። በዚህ መልሱ ከጥፋታቸው እነሱን „ነጻ“
ሊያወጣቸው ፈልጎ አይደለም።የማያውቁት ነገር ውስጥ ገብቶ ያውም
በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩትን የተለያዩ ሕዝቦችን ማስተዳደር ቀላል
ነገር እንዳልሆነ ለማሳየት ብቻ ነው።እሱ እራሱ „…እኔ የማውቀው
አለማወቄን ነው“ ሲል አንድ ሰው በየቀኑና በየጊዜው እንደ ችሎታውና
ዝንባሌው ማጥናት መመራመር ጥበብና ዕውቀትን መሻት እንጂ እንደ
አራቱ መደብ አዋቂ የጨበጥኩት ዕውቀት „በቂ ነው“ ስለዚህ እኔም
ጨረቃ ላይ ከንፎ የሚያስወጣውን መንኮራኩር እንዳው በደፈናው
እንደ አሜሪካኖቹና እንደ ሩሲያኖቹ „እሠራለሁ“ የሚያግደኝ የለም ብሎ
መፎከር እንደማይበቃ ለማሳየት ነው።ሶቅራጠስ አልፎ ሄዶ „ለእራሱ
ጥሩ ነገር እሠራለሁ“ ብሎ ግን ደግሞ ባለማወቅ„መጥፎና ክፉ ሥራ
የሚሰራው ሰው እራሡን ጭምር የሁዋላ ሁዋላ እንደሚጎዳ እንኳን
አያውቅም“ ይላል።ለዚህ ነው ሁለቱ ፈላስፋዎች አስተማሪውና ተማሪው
ፕላቶን ለዕውቀትና ለጥበብ ትልቅ ቦታ የሚሰጡት። ለመልካም
ሕብረተስብ ለመልካም አስተዳደር ለሰው ልጆች አብሮ በሰላምና ደስታ
መኖር ብዙም ቢያስቡም ከከተማ ግርግርና ከሰውነት ስሜት ” ባርነት”
ከሁለቱም፣ ሁለቱም አዋቂዋች ተላቀውና ርቀው በመንፈሳዊ
በኮንቴምፕላቲቭ ዓለም ውስጥ መኖርን የሚሹት። የፈለጉት። ይህ
ደግሞ ጊዜ የሚሽረውን ሥራ ሳይሆን ዘለዓለማዊ ሁኖ የሚቆየውን ሥራ
ሰርቶ ለማለፍ የተነሳሱበት ነው። እሱም ፍልስፍና ነው። እሱም ድርሰት
ነው። እሱም ሙዚቃና የኪነት ጥበብ ነው።እሱም ጥናትና ምርምር
ነው። እሱም-ወደ ቅጀት ዓለም ሳንሄድ በአንድ ሕዝብ ታሪክ ውስጥጊዜያዊ ሳይሆን ቋሚ ሁኖ የሚጠቀስ ሥራ ነው። መዓት “እብዶች”
ከመሬት ተነስተው እዚህማ ላይ “እኛም አለንበት” ሊሉ ይችላሉ። ይህ
ግን ወርቅ በእሳት እንደሚፈተነው እሳት በላሱት ጭንቅላቶች አንድ ቀን
የሚፈተን ሥራ መሆን አለበት። ደግሞ የትኛው ሥራ ?
ሁለት ነገሮች፣
አውሮፓ እዚህ ደረጃ ላይ ለመድረስ ብዙ አመታት ፈጅቶባታል። ለምን
ይህን ያህል ጊዜ ፈጀባት? ለምንስ ለእኛ ይህን ያህል ጊዜ ተሰውሮብን
ግራ አጋባን?

~ 29 ~

አንደኛው የፍልስፍና የምርምርና -የሳይንስ ጥናት መንገድ ነው።
ሁለተኛው የመልካም አስተዳደር ዘይቤ ብልሃትና ዘዴ፣ በሌላ አነጋገር
ተቻችሎና ተከባብሮ በዲሞክራቲክ ሕብረተሰብ ውስጥ አብሮ መኖር
ነው። እዚያ ደረጃ ላይ ለመድረስ ለእኛም ለእነሱም ብዙ አመታት
ፈጅቶብናል። ያለፈው ምሥጢር እነዲህ ነው።
አውሮፓውያኖች-ሮም ቀደም ብላ ከጥበቡ እንደ እኛው ቀምሳለች –
ከእንቅልፋቸው የነቁት፣ የግሪኮች ትምህርት የአውሮፓ ገዳም ከገባ
ወዲህና የገዳሙ ትምህርት ወደ ዩኒቨርስቲዎች እዚሁ ገዳም ውስጥ ቀስ
እያሉ ከተቀየሩ በሁዋላ ነው። የሚታወቀውን ለመድገም- ግሪኮቹ አራት
መቶ አመት ከክርስቶስ ልደት በፊት ነጻ አስተሳሰብን ማራመድና
መመራመርን እንዲሁም የሰው ልጆች ነጻነትን ማለት ዲሞክራሲን
(ባሪያና ሴቶች ልጆችና የውጭ አገር ሰዎች እኩል መብት
አልነበራቸውም እንጂ!) ፈልገው አግኝተው መዳፋቸው ውስጥ
አስገብተው በሥልጣኔአቸው ሌሎቹን ቀድመው ለመሄድ ችለዋል።
እንዴት ነጻነትን አርነትን ዲሞክራሲን መራመርና መፈላሰፍን ሌሎቹን
ቀድመው አገኙ? አግኝተውም በደንብ ሊጠቀሙ ቻሉ? አንዴትስ
ግሪኮች ወደቁ? ሮም እንዴት ተነሳች? እሱዋስ እንዴት ወደቀች? ይህ
ማደር የሚያስፈልገው አርዕስት ነው።
አንድ ግን ለማሳረጊያ ማንሳት የምንፈልገው ነገር ቢኖር እኛ ተከባብረንና
ተፋቅረን አብረን በሰላም ለመኖር ከአወቅንበት እንደሚባለው እንደ
አውሮፓውያኖች ገና ብዙ አመታት መጠበቅ ሳይሆን ነገ ማድረግ
የምንችለው ነገር ነው። ያገኘነው ልምምድ የቀመስናቸው መከራዎች በቂ
ትምህርቶች ናቸው። ነጻነትና ነጻ አስተሳሰብ ማለት ደግሞ ማንኛውንም
ዓይነት “ባርነትን” አልፈልግም ማለት ነው።እንደ ክርስትና ትምህርት
ደግሞ “እኩልነትና ፍቅርን ነጻነትን ወንድማማችነትና … የሚያስተምር
ትምህርት የለም።” ግን እሱንም ቢሆን ቫቲካን ሆነች የእኛ ቤተክርስቲያን ወንጌላዊት ሆነች የአሜሪካ የተለያዩ ሴክቶች በደንብ
~ 30 ~

አንስተው ሰውን አለላስተማሩም። ቢያደርጉማ ኑሮ “ባርነት የዘር
ጥላቻ…ለሁለት ሺህ አመታት በተከታታይ በአልነገሰ ነበር።
ሰው ሰይጣን ነው።ሰይጣን ሰው ነው። “ከክፉ ሁሉ አድነን የሚባለውም
ለዚሁ ነው።
ሰው ሁሉ ግን ሰይጣን አይደለም።
——————————–
i/ ሰማይና ምድር -ጋያና ኤሮስ – ወንድና ሴት ሁነው ይገናኛሉ።ልጃቸው ኡራኖስ ይወለዳል። እሱ ከእናቱ ከመሬት
ከጋያ ጋር ተገናኝቶ ብዙ ልጆች ይወለዳሉ። የእሱ ልጅ አንዱ ክሮኖስ የሚባለው አባቱን ይሰልብና እሱ እረሱ የአባቱን
ቦታ
ወርሶ
ገዢ
ሁኖ
በወንድሞቹና
በእህቶቹ
ላይ
ይነሳል።
ክሮኖስ እንድ ግብጾቹ ፈርዖኖች ከእህቱ/ከእህቶቹ ጋር ተገናኝቶ ሦስተኛውን ትውልድ በሁዋላ ጠንካራ አማልክት
የሚሆኑትን እነ ዴሜተርን እነሓዴስን እነ ፖሳይዶንን እና በመጨረሻው ሁሉንም አሸንፎ ንጉሥ የሚሆነውን ሶይስን
በጠቅላላው
በርካታ
ልጆችን
ይወልዳል።
በአንዱ ልጅህ እጅ አንድ ቀን ነፍስህ ታልፋለች የሚባል ንግርት ከአባቱ ሰምቶ ስለነበር ክሮኖስ ከመሬት ተነስቶ
በፍረሃቻ የወላዳቸውን ሥጋውን ወንዶች ልጆቹን እንደተወለዱ እሱ እየያዘዛና እየለቀመ ይውጣቸው ጀመር።
ii/ ፕሮሜቴዎስ የሚባለው አምላክ ፈጠራቸው የሚለውን አተራረክ ከወሰድን የሰውን ልጆች ይህ አማልክት
ከተቃጠሉት የ …ልጆች ከቲታን አመድ ጠፍጥፎ እሰኑን እንደፈጠራቸው ከግሪክ ታሪክ እናነባለን። ሶይስ የሰው ልጆች
በፕሮሜቴዎስ እጅ ከአመድ ተጠፍጥፈው በመሠራታቸው እሱ ፈጽሞ እንደ አልተደሰተም ። እሱ በተራው ሶይስ
ቀጥቃጩንና አንጣሪውን ሔፓኢስቶስን ከሸክል ድንጋይ አንዲት መልከ መልካም ሴት ልጅ ጠፍጥፎ ሠርቶ እንዲልክለት
እንደአዘዘው
እንመለከታለን።
ይህቺ ልጅ በሁዋላ ፓንዶራ የሚባለውን ስም የያዘቺው በሶይስ ትዕዛዝ ወደ ሰው ልጆች መኖሪያ መንደር ተልካ እዚያ
ፕሮሜቴዎስ ቆልፎበት የነበረውን ሳጥን ሰርቃ እዚያ ውስጥ ያሉትን የተለያዩ በሽታዎችን፣ እንደ ሞትና ሐዘንን ነገር
መርሳትን መዣዠትን ጥላችን ምቀኝነትን… በሰው ልጆች መካከል ሳጥኑን ከፍታ እንድተረጨው ትደረጋለች። በዚያም
በዚህም የሰው ልጆች በአንድ በኩል ከውጭ ከሚመጣባቸው ችግሮች በሌላ በኩል እራሳቸው በእራሳቸው በማወቅም
ሆነ በአለማወቅ በሚጠነስሱት ሥራዎቻቸው ተተብትበው ጦርነት በእራሳቸው ላይ ከፈቱ። ሌላም ሦስተኛ በስንት
መከራ በሁዋላ ተፈልጎ የተገኘም ችግር አለ። ይህም በእያንዳንዳችነ ደረትና አእምሮ በልቡና እና በጨኝቅላታችን ውስጥ
ያሉ ሁለት ዓለሞች ናቸው ። ይህንንም በመንፈሳዊ ትምህርት የሥጋና የነፍስ ፉክክርና ትንቅንቅ ልንለው እንችላለን።
ወይም ደግሞ በፍልስፍናው ዓለም ከሃይማኖት በተለየ ዓይን ፣ ሥጋና አእምሮ ወይም መንፈስ ወይም ደግሞ ነፍስ
የሚባለው ነገር ነው። ነፍስ ወይም መንፈስ በግሪኮች ዘንድ በሦስት ይከፈላል። ማሰብና ማመዛዘን ፍቅርና ስሜት
ጀግንነት ናቸው።
ሶቅራጠስ አልፎ ሄዶ „ለእራሱ ጥሩ ነገር እሠራለሁ“ ብሎ „መጥፎና ክፉ ሥራ የሚሰራው ሰው እራሡን ጭምር የሁዋላ
ሁዋላ እንደሚጎዳ እንኳን አያውቅም“ ይላል።
ለዚህ ነው ሁለቱ ፈላስፋዎች ለዕውቀትና ለጥበብ ትልቅ ቦታ የሚሰጡት።
ለመልካም ሕብረተስብ ለመልካም አስተዳደር ለሰው ልጆች አብሮ በሰላምና ደስታ መኖር ብዙም ቢያስቡም ከከተማ
ግርግርና ከሰውነት ስሜት ባርነት ከሁለቱ ተላቀውና ርቀው በመንፈሳዊ በኮንቴምፕላቲቭ ዓለም ውስጥ መኖር
ይፈልጋሉ። ይህ ደግሞ ጊዜ የሚሽረውን ሥራ ሳይሆን ዘለዓለማዊ ሥራ ሰርቶ ማለፍን ነው። እሱም ፍልስፍና ነው።
እሱም መዚቃነን።እሱም ድርሰት ነው።እሱም ኪነት ነው። እሱም ሳይንስ ነው።
በግሪክ ላይ ከቆየን -በትክክል የአቴን ሥልጣኔ ላይ ትንሽ ጊዜ ወስደን አካሄዳቸውን ከተመለከትን- እነሱ ይህን አታድርግ
ይህን አታስብ ይህ ክልክል ነው፣ይህ ደግሞ ለአንተ አይደለም የሚል እንደ ፋርስ አያቶላዎች ወይንም እነደ ግብጽ
ፈርኦንች ዓይነት የሰውን ልጆች አእምሮና ሥራ የሚቄጣጠሩ „ካህናቶች“ በአናታቸው ላይ ተቀምጠው እነሱን አፋቸውን
ለጉመው እግራቸውን አሥረው አልገዙአቸውም።
ይህ አንደኛው ምክንያት ነው።
ሁለተኛው ምክንያት አዲስ ነገር ለማወቅ ኃይለኛ ጉጉት ያላቸው ሰዎች ነበሩ።
ይህም ይከተሉት በነበረው ፍልስፍና ላይ የተመሠረተ ነው። አካባቢአቸውን ተንቀሳቅሰው ያጠኑ ነበር። የሌላውን አገርና
ሕዝብ ዕውቀትና ጥበብ ተዘዋዉረዉ ይሰበስቡ ነበር።
ወደ ግብጽ ተጉዘዋል።ፋርስ ደርሰዋል። ሕንድን አይተዋል። ኢትዮጵያ ሔሮዶቱስ ወርዶ ሊጽፍ የቻለው በዚሁ ምክንያት
ነው።
በሒሳብ በድርሰት በሕንጻ ሥራ በታሪክ ምርምር በመድሓኒት ቅመማ በሕክምና ጦር ቴክኒክና በመርከብ ሥራ በእርሻ
ምርትና በከብት እርባታ በወይራ ዘይትና በምግብ ዓይነቶች በልብስና በቤት ቁሳቁሶች በቅኔ ውበትና በኢስቴትክ

~ 31 ~

በቁንጃ…ከሁሉም ከሁሉም በፍልስፍና እና በፖለቲካ ዲሞክራሲ በምርጫና በውይይት በክርክርና በውድድር አምነው
ከሌሎቹ የተሻላ ቋሚ የጋራ ቤታቸውን በጋራ ሊሠሩ የቻሉት -ይህ ነው ብልሃቱ- ለነጻነት በአላቸው ፍቅር ነው።
አሜሪካንና ጀርመን ፈረንሣይና ታላቁዋ ብሪታንያ… አሁን እነሱ ሌሎቹን ቀድመው የሄዱት ልክ የአቴኖቹን ፈለግ
በመከተላቸው ነው። አቴኖች መፈላሰፍን መናገርን መከራከርን ውይይትን አዲስ ነገር ማየትና መስማት የማይፈልጉትን
የሚቃወሙትን ፈላጭ ቆራጭ አምባገነኖችን ታይረንን እንደ ዛሬ የምዕራብ አገሮች አጥብቀው የሚቃወሙ ናቸው።
እንዲያውም በሕዝብ ላይ በእነሱ ላይ አምባገነን ሁኖ ፈላጭ ቆራጭ ሠርዓቱን ለመዘርጋት የሚሞክረውን ሰው
„ግደሉት“ የሚል ሕግ አላቸው። ነበራቸው።
ውይይትና ክርክር ከመናገር ከመጻፍ ነጻነት ከመሰብሰብና ከመደራጀት እንዲሁም ከመንቀሳቀስ መብት ጋር በጥብቅ
የተያያዘ ነው።
ግን ደግሞ መወያየት መከራከር ዝም ብሎ ተናታርኮ ተጣልቶ ለመለያየት ሳይሆን አንድ ሁሉንም ወገን ሊያሳምን
የሚችል እውነትና ሓቅ ላይ ለመድረስ ነው።
እንዴት እንኑር? ችግሮቻችንን እንዴት እንፍታ? ረሃብን እንዴት እናስወግድ? በሽታን እንዴት እንከላከል? ነገ ምን
ዓይነት ቀን ይመጣል?….ለእነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች አንድ መልስ ብቻ የለም።
አንድ ሰው ወይም አንድ ድርጅት ብቻውን ትክክለኛ መልስ የለውም።
ወይም ደግሞ የተለያዩ ሰዎች በምሥጢር ተሰብስው „እኛ ብቻ እንውቃለን መልሱም እኛ ጋ ነው። እናንተ ግን ዝም
በሉ…“ የሚባልበት አይደለም።
ትክክለኛው መልስ ለአንድ አገርና ለአንድ ሕዝብ ውስጣዊ ችግር ወይም ለሌሎች ችግሮች „ሁሉም የሚሉት ተጨምቆ
አንድ ላይ ሲቀመጥ“ ሊሆን ይችላል።
ወይም እነሱ ፖለቲከኞቹ ያልታያቸው ሌላ ጠለቅ ያለ ዕውቀት ያላቸው ጠበብቶች የሚሠነዝሩት ለየት ያለ አስተያየትና
ሓሳብ ሊሆንም ይችላል።
ወይም ሰዎች ሳያዉቁ የሚከራከሩበት ጉዳይ ሌላ አገር ቀደም ሲል መልስ የተሰጠበትም ነገር ሊሆን ይችላል።
ወይም ደግሞ አገሪቱ ቀደም ሲል ከአሳለፈቺውም ታሪክ ጋር የበለጠ ሊቀራረብ ይችላል።
አዲስ ነው ተብሎ የሚነገርለት ነገር ቀደም ሲል ከተካሄደው ስህተትም ጋር አንድ ሊሆን ይችላል።
ለምሳሌ የአንድ ፓርቲ አምባገነን ሥርዓት። ለምሳሌ „በቂ ዲሞክራሲና በቂ ነጻነት አገሪቱዋ ውስጥ አለ“ የሚለው
አነጋገር። ለምሳሌ „ጊዜ ስጡን“ የሚለው ሽንገላ።
ከአስተሳሰብ ዓለም በምንም ዓይነት ልንወጣ አንችልም። ማንም ሰው ከተለያዩና ከማይጣጣሙ እርስ በእራሳቸው
ከሚቃረኑ ወይም ከሚደጋገፉ አስተሳሰቦች ዓለም ፈጽሞ ሊያመልጥ አይችልም።
ግን እነዚህ የተለያዩ የማይጣጣሙ አስተያየቶችና አመለካከቶች ተበጥረውና ተለቅመው -ሁሉንም ወይም አብዛኛውን
ሊያስማሙ የሚችሉ – የጥራት ደረጃ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ።
እንዴት?
በሕዝብ ዘንድ በሰዎች ዘንድ ትክክለኛና ዕውነተኛ በመሆናቸው ተቀባይነት ሲያገኙ ብቻ ነው። ይህም ሥነ-ስርዓት
በአለው ክርክርና ውይይት ከሓሳቦች መፋጨት በሁዋላ „…ክፋት ሳይኖረው በጥሩነቱና በደግነቱ በመልካም መፍትሔው
ሰው ሁሉ የተቀበለው የሚቀበለው አስተሳሰብ ሲሆን ብቻ ነው።“
ብዙሃኖቹም ሊሳሳቱ ይችላሉ። ግን ብዙሃኖቹ ተቀበሉት ተብሎ የጥቂቶቹ ጩሀት ቦታ የለውም አይባልም። በሸንጎም
ውስጥ ሆነ በአደባባይ በጋዜጣ ሆነ በራዲዮና ቴሌቪዥን በቡና ቤት ሆነ በትላልቅ ወይም ትናንሽ አዳራሶች ፊርማ
በመሰብሰብ በሰላማዊ ሠልፍ ማንም ሰው እንደገና ለሓሳቡና ለአቋሙ መከራከር መሟገት ድምጽ መሰብሰብ ይችላል።
ለዚህ ዓይነቱ አካሄድና የአኗኗር ዘዴ ደግሞ ከክርስቶስ ልደት አራት መቶ አመት በፊት የነበረውን ሁኔታ መለስ ብሎ
መመልከት ጠቃሚ ትምህርት ይሰጣል።
ክፉና ደግ መልካም ሥራና አረመኔነት የሁለቱን ልዩነት ለማወቅ ይህን ያህል ከባድ አይደለም። እንደሚባለው ሰይጣን
አይደለም ዓለምን በዚያውም ኢትዮጵያን የሚያተረማምሰው። ሰው እራሱ ነው። ሰው ደግሞ ሰይጣን ሰይጣንም ሰው
ነው።
ሰው ሁሉ ግን እንደምናውቀው ሰይጣን አይደለም።

ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08
~ 32 ~

የተከለከለ መጠሪያ፤ የማይረሳ ፍጅት :„ቱቲስ እና ሁቱ“

የተከለከለ

መጠሪያ የማይረሳ ፍጅት :- „ቱቲስ እና ሁቱ“
የእርስ በእርስ ጦርነቱ የፈነዳው ሳይታሰብ ነው። እነሱም ይህ ይሆናል ።
ይህ አንድ ቀን ይመጣል፣ ብለው አላሰቡም።
አንድ ቀን አንዱ ተነስቶ ሌለውን በቆንጨራና በቢላ በመጥረቢያና
በሳንጃ የገዛ ጉረቤቱን ዘመዱን ሚስቱንና ልጆቹን አማቸን ጭምር
ይገድላል፣ያርዳል በእሱ እጅ ይሞታል/ ትሞታለች ነፍሱንም ያጣል ብሎ
ያሰበ ሰው አልነበረም።
ትንሽ ቀስቃሾች የታጠቁ ወታደሮችና ሚሊሻዎች እንደ ዋዛ የጀመሩት
ፍጅት በሁዋላ ተቆጥሮ እንደተሰማው ሁሉንም አሳብዶ በመጨረሻው
ከስምንት መቶ ሺህ በላይ የሚሆኑትን የአገሪቱን ሰዎች ሕይወትና ነፍስ
ይዞ ሄዶአል።
በቤታቻውና በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ሰዎች እሳት ተለኩሶባቸው
~ 33 ~

ጋይተዋል። ሲሸሹ በጥይት እንደ አውሬ ታድነዋል። መሮጥ የማይችሉት
ተይዘው ታርደዋል።
ማን ምን እንዳደረገ በሁዋላ ፍርድ ቤት አንዳንዶቹ ተይዘው ቀርበው
ቃላቸውን ሰጥተዋል።
ጥላቻውና መዘዘኛው የዘር ልዩነት የተጀመረው በቤልጅጎቹ የከፋፍለህ
ግዛ ተንኮልና ሥራ የቅኝ ግዛት ዘመን ነው።
ከመሬት ተነስተው እንደፈለጉት በ1920 አጋማሽ ላይ አንተ „ቱሲ“ አንተ
ደግሞ „ሁቱ“ ብለው ሰውን በዘር ግንድና በአጥንት ቆጠራ እዚያ
ሽንሽነውና ከፋፍለው መታወቂያ ወረቀታቸው ላይ ይህን የዘር መለያ
ምልክታቸውን ጽፈው ኑዋሪውን አናክሰው አለያይተዋል። ጣሊያንም
በኢትዮጵያ ሞክሮ ሳይሳከለት ቀርቶአል።
ይህ ሆን ተብሎ ቀደም ተብሎ
የተረጨው መርዝ ሥር ሰዶ ሰውን
በሩዋንዳ
የዛሬ
20
አመት
አፋጅቶአል።
አሁን በሩዋንዳ ሕዝቡን በዘር
መከፋፈልና በመታወቂያው ወረቀት
ላይ „ሁቱ እን ቱሲ“ ብሎ ለይቶ
መጻፍ በህግ የሚያስቀጣ በመሆኑ እዚያ ተከልክሎአል። ሁሉም አሁን
ረዋንዳ ሩዋንዳዊ ናቸው።
በደቡብ አፍሪካም የአንድን ሰው ዘር መታወቂያ ወረቀቱ ላይ መጻፍ
እዚያም እንዲከለከል እነ ማንዴላ አድርገዋል።
በዘር እና በሃይማኖት በመደብና በከረረ አይዲኦሎጂ መበጣበጥ
መጨረሻው ማለቂያ የሌለው ፍጅት ነው።
~ 34 ~

ለዚህም 20ኛው ክፍለ ዘመን ምስክርም ነው።ፋሽሽቶች አይሁድንና
ሲንቶወችን ጥቁሮችና ደካማዎችን ፈጅተዋል።
በመላው ዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ ይህን የሩዋንዳ ፍጅት ሳይረሳ በሕሊና
ጸሎት ሰው ሁሉ አስታውሶታል።
የሚያስፈራው የሚቀጥለው ሁለተኛው ሩዋንዳ ነው።
ማን ይሆን?… ማን ትሆን?
ከመካከለኛው አፍሪካ አስፈሪ ዜና ይሰማል።
ሌላም ቦታ በአፍሪካ ወደዚያው የሚያመሩ አገሮች ጥቂት አይደሉም
ይባላል።
እነማን ይሆኑ? የዕብዶች ዓለም!
……

—-

ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08

~ 35 ~

ጠንካራ ክንድና ነጻነት

ሰው ምን እንደሚፈልግ ለማወቅ አስቸጋሪ ነው። በዚያ ሲሉት በዚህ
ይታለል። ያን ሲያቀብሉት እጁ ላይ ያለውን ጥሎ እንደ ህጻን ልጅ
ያኛው ያምረዋል። ይህን ሲሰጡት ጨምር- አልበቃኝም ይላል።ሲበዛበት
ደግሞ ቋቅ ሲለው ይ… ሰው አስቸጋሪ ነው። እንደ ሰው አስቸጋሪ ፍጡር
የለም።
እሩቅ ቦታ ሳንደርስ በቅርቡ በተካሄደው በቱርኩ ኤርድዋን በሩሲያው ፑቲን
በእነሱ እርምጃ ያልተደሰተ በተቃራኒው ያልተበሳጨ ሰው የለም። የግብጹ
ሙርሲና ፊልድ ማርሻል አዚዚ አሉ።
ሁለተኛውን ትተን የመጀመሪያዎቹን እንውሰድ።
„ፑቲንን ለሩሲያ ኤርድዋን ለቱርክ እግዚአብሔር መርቆ የሰጣቸው መሪዎች
ናቸው!“ ብዙ ሰዎች ይላሉ። በተለይ ቪላዲሚር ፑቲን „ትልቅ ቦታ“ በአንዳንድ
ኢትዮጵያኖች ዘንድ አላቸው።
ከልብ ይሁን ከምኞት፣ እነሱን ከገቡበት የሚያወጣቸው ሰው አጥተው ይሁን
ወይም ተመሳሳይ ሰው ናፍቀው፣ወይም ከአለፉት ታሪክ ተነስተው -ሁሉም
በየፊናው የሚሰጠው አስተያየት የተለያየ ነው- ምኑንም ከመገመት በላይ ይህ
~ 36 ~

ነው ብሎ አሁን መናገር አይቻልም። ግን ነገርን ለመረዳት ዓለምን በሌላ ዓይን
ለማየት ታሪኩ ይሰጣል።
በሙስና እና በዘመድ ሥራ „ከእነ ቤተሰባቸው ተጨማልቀዋል “ ተብለው
በብዙ ሰዎች ዘንድ የተከሰሱሱት የቱርኩ ጠቅላይ ሚንስትር በምን ተአምር
ይሁን በምን- እንተርኔቱንም ዘግተውም ስልክም ተቆጣጥረው – እሳቸውና
ድርጅታቸው ያ ሁሉ ሆኖ „በሕዝባቸው ድጋፍ “ በ45% እንደገና ተመርጠዋል።
በቅርቡ የተካሄደውን ምርጫ አጭበርብረዋል የሚሉም አልጠፉም። ከክሪም
ወዝግብ በሁዋላ ፕሬዚዳንት ፑቲን „በሕዝባቸው“ ዘንድ ያልተጠበቀ ድጋፍ
እሰከ 70% ድረስ አግኝተዋል።
ምንድነው ምክንያቱ?
ምንድ ነው ? …የሰዎችን ፍላጎትና የልብ ትርታቸውን አንዴ ከፍ የሚያደርገው
ሌላ ጊዜ የሚያሸፍተው ነገር? ሰዎችን እጃቸውን ይዞ ጥቅጥቅ ከአለ ጫካ፣…
ሰው ከማይደርስበት በረሃ እና ከገደል አፋፍ ወይም ከሚነድ እሳትና ከመከራ
ከጥፋትና ከውድቀት እነሱን ጎትቶ የሚያወጣቸው „መሪ“ ከሙሴና ከአሮን
ታሪክ ወዲህ እነሱ እንደ ሚሹ እንደሚፈልጉ እንደሚመኙ ብዙዎቻችን በደንብ
እናውቃለን።
በሕዝብየተመረጡት ሙርሲ እሥር ቤትተወርውረውፊልድ ማርሻል አዚዚ
መለዮአቸውን አውልቀው የግብጽ ፕሬዚዳንት ለመሆን ሲነሱከዚያየተላለፈው
“የድጋፍ” ሥዕል ያስደነግጣል።
አከታትሎ ከአምስት መቶ በላይ የሚሆኑ የሞስሊም ወንድማማቾች”የሞት
ፍርድ”በግብጽተፈረዶባቸዋል። ሰዎች ምንድነው የሚስቡት?
ከሚካኤል ጎርባቾቭ እና ከባሪስ ዬልሲን ከሶቪየትም መፈረካከስ መበተን ወዲህ
ቪላዲሚር ፑቲን መጥተው „ጸጥታና ሰላምን የደስታን ዘመን የሩሲያ ታላቅነትን
አድሳለሁ“ ብለው እንደተነሱ – ይህ አዲስ አይደለም ብዙዎቻችን ቀደም ሲል
ሰምተናል።
ታይፔን ኤርድዋን በኢስታንቡል የከተማው ከንቲባ በነበሩበት ዘመን ከተማውን
ከወንበዴዎችና ከቀማኞች እጽድተዋል፣ የወሃ ቧንቧ ዘርግተዋል ደስ ሲለው
የሚበራውንና የሚጠፋውን የከተማውን መብራት ገመዱን አድሰው ሰውን
ከማታ ጨለማ አውጥተዋል።
~ 37 ~

የሆቴል እና የቡና ቤት ባለቤቶች ነጋዴና ተማሪዎች…ሐኪምና ወላጆች ሁሉም
በሰውዬው ሥራ -ቱርኮቹ እንደሚሉት ተደስተዋል።
በአስቸጋሪ ዘመን በመጥፎና መከራ ጊዜ ሰዎች አንድ መሪ ጠንካራ ክንድ ያለው
መሪ ቢመጣላቸው ይፈልጋሉ።ይመኛሉ። እንዲመጣላቸውም ይጸልያሉ።
በጥንታዊት ግሪክ የጦር ስልት የሚቀይስ ቀይሶም ሠራዊቱን የሚመራ አንድ
„ቆራጥ የጦር መሪ ጀግና:- ፊታውራሪ“ ፈልገው ይሾማሉ። እሱም ሳያስቡት
ተገለባብጦባቸው በአንድ ሌሊት ተቀይሮ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ አናታቸው ላይ
ሊጨፍርም ይችላል።
ይህን ከአዩ ደግሞ እሱን ያኔ እነሱ አይለቁትም።
ሮምና ሮማውያን „በየት መንገድ“ እንደሚኬድ ፣ችግርም እንዴት እንደሚፈታ፣
ከመከራ የሚያወጣቸው ሰው… ለሠራዊቱም ለሕዝቡም „መንገድ የሚያሳይ
መሪ“ እነሱ „ዲክታተር“ ይሉታል (የጊዜ ገደብ ሰጥተው) ከአገኙ እሱን ሰይመው
እሱን ይከተሉታል። ሳት ቢል ከመንገዱ ወለም ዘለም ከአለ ዩሊየስ ሴዛርን
እንዳደረጉት አጋድመው ያርዱታል። እሱም እነኔሮና ሌሎቹ ቄሣቹ እንዳደረጉት
አልሰማ ብለው „ያፈነገጡትን ይዞ ይፈጃቸዋል!“
የነገሥታቶችስ ሥራ እንዴት ነው?
እነሱ “በቅባ ቅዱስ” ይጨርሱታል።
ቤኒቶ ሞሰሊኒ በ1925 አጋማሽ ላይ „ዱቼ“ „መሪ „ የሚለውን ሹመት እሱ
እራሱ መርጦ አናቱ ላይ ደፍቶአል። እሱን አይቶ አዶልፍ ሒትለር „ደር
ፊውረር“ ያው መሪአችን ብለው ተከታዮቹ እንዲጠሩት ትዕዛዙን
አስተላልፎአል። „መለኮታዊነቱን“ እየዘላበዱ እንዳያበላሹበት አብሮ አደጎቹን
ከአጠገቡ
ተራ
በተራ
ጠራርጎ
ገድሎአቸዋል።
የጆርጂያው ተወላጅ የሩሲያ ኮሚኒስት ፓርቲው መሪ – እሱም ጓደኞቹንና
አብሮ አደጎቹን ከአገጠገቡ በጽዳት ዘመቻ ቀስ በቀስ ከጠራረገና ከጨረሰ ወዲህ
„…አባት! የአገር ሁሉ አባት!“ የሚባለውን ቅጽል ስም ትከሻው ላይ ለጥፎ
ሁሉንም ጭጭ አድርጎአል። የኪዩባው ካስትሮ „ማክሲሞ ሊደር:- ታላቁ መሪ“
የሚለውን አጠራር መርጠዋል። ሳዳም ሁሴን „ተተኪ የሌለው መሪ“ እራሱን
ሲያሰኝ „ወንድማዊ መሪ“ የሚለውን ጥሪ ኮነሬል ሞአመር ጋዳፊ መርጦ ለእራሱ
ብቻ አድርጎአል።
~ 38 ~

ቆይተውም ኮነሬል ጋዳፊ ጥቂት የአፍሪካ „ንጉሦችን ከጋና እና ቤኒን ሰብስበው
እራሳቸውን „ንጉሠ ነገሥት „ ብለው ሹመው የአፍሪካን መሪዎች ለእነዚያ
አዳዲስ ማርቼዲስ ገዝተው የሚሸልሙት ሰዎች አዲስ አበባ ሲገቡ „…ንጉሣችሁ
ሲመጣ እንዴት አይሮፕላን ጣቢያ ድረስ መጥታችሁ አትቀበሉም „ ብለው
ተቆጥተዋቸዋል።
ኪም ኢል ጆንግ የኮሪያው „የበላይ መሪ“ የሚለውን ቃል ስም እና ዝና ክብርና
ወግ ለብቻው ጨብጦ ይዞአል። ልጁም (አልጋ ወራሹም) ተመሳሳይ ጥሪ
ወደፊት ይኖረዋል።
ግጥም ገጣሚዎች፣ ሞራ ገላጮች፣ ትንቢት ተናጋሪዎች ለሒትለርም ለሞሰለኒም
ለሳዳም ሁሴን ለቢንላዲንም „….የእግዚአብሔር ስጦታ“ የሚለውን ሐረግ
ፈልገው በዘመናቸው ሰጥተው ሰው እንዲያምንበት አድርገዋል።
በኢትዮጵያ አንዱ ዘፋኝ “አቤት ቅንድቡ…” ብሎ ሰውን አስጨፍሮአል። “ክቡር
ሊቀ- መንበር አማራጭ የሌለው መሪ ” የሚለው ቃል “ከቀዳማዊት” ጋር አብሮ
በአለፉት ዘመናት ከደርግ ዘመን ጊዜ ጀምሮ ተሰምቶአል።
አብዛኛዎቹ ይህን የሚሉትና ሰው እንዲያምነው ለማድረግ ጥረት የሚያደርጉ
ክፍሎች
የፕሮፓጋንዳና
ቅስቀሳ
ክፍል
“ካድሬዎች”
ናቸው።
የሚገርመው ሰዎች ሰዎችን አሳዶ የሚፈጅ ሰው -እንደ ሂትለርና ሞሰለኒ እንደ
ስታሊንና እንደ…ያሉትን ሰዎች በጭፍን ተከትለው (በሰሜን ኮሪያ መሪው
ሲሞት የግድ ይለቀሳል) እነዚህን ሰዎች„….የሚወዱአቸው“ በምን ምክንያት
ነው?..ለምንድነው ጠንካራ ክንድ ለአለው ጨካኝ ሊሆን ይችላል ወይም…
አስቸጋሪ ሰው “ሕዝቡ ጭፍን “ድጋፉን የሚሰጠው?
„መሪን መውደድ“ ወይም መከተል ጊዜያዊ ነገ ንፋስ የሚመታው አቋም ነው ?
ወይስ ቋሚ ነገር? ለምንድነው ሰዎች በአንድ ዘመን አንድን “አደገኛ ሰው”
የሚከተሉት በሌላ ጊዜ እሱን “እንደማያዉቁት ሰው” የሚክዱት?
ይህ ደግሞ ወደ በአለ ግርማ ሞገሱ ወደ „ካርስማቲክ መሪ“ አመጣጥና ውድቀት
ምርምር ይወስደናል። ይህቺ ዓለም ሁሌ አዳዲስ ነገር አምጥታ ታሰደነግጣለች።
ወይስ በእኛ ላይ ለመቀለድ ትደግማለች? ምርጫ - አንድን መሪን ለተወሰነ ጊዜ
ብቻ መምረጥ እሱ ደግሞ ምንድነው?

ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08
~ 39 ~

አባይ :- ኢትዮጵያና ግብጽ

አንድ

መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ የሚፈሱትን ወንዞች ሌሎች
የጎረቤት አገር ከመድረሳቸው በፊት መገደብ ይችላል ? ወይስ አይችልም
? በሚል አርዕስቱ ሥር „ሱድ ዶቸ ሳይቱንግ“ የተባለው የደቡብ ጀርመኑ
ዕለታዊ ጋዜጣ አንድ ሙሉ ገጹን ለዚሁ ወደፊት ዓለምን ሳያበጣብጥ
አይቀርም ተብሎ ለሚገመተው ጉዳይ ጊዜውን ወስዶ ቅጠሉን ለግሶ
የሚከተለውን
አስተያየት
አምዱ
ላይ
አሥፍሮአል።
ሌሎቹ የአፍሪካና የሰሜን አሜሪካ ጋዜጣዎች ስለ አፍሪካ ምን እንደጻፉ
መለስ ብለን ዝርዝር ሁኔታ ውስጥ ሳንገባ ይህኛውን አርዕስት ብቻ
ለመመልከት ወስነናል።ጉዳዩ አሳሳቢና ቅድሚያ የሚሰጠው ነው።
መጪው
ጦርነት
እንደ
ዘጠናዎቹ
ዓ.ም
“በዘርና
በጎሣ….በብሔር/ብሔረሰብ” ላይ የተመሠረተ ሳይሆን ጠበብቶች
ተስማምተው እዚህ እንደሚሉት መጪው ጦርነት በሕይወት ጥያቄ ላይ
ያተኮረ ነው።
~ 40 ~

… ምን እንብላ? ሰዎች ይላሉ።
ምን እንጠጣ?
ምን እንልበስ?
ማን ውጋታችንን ያስታግስ?
ምን እንሥራ?
የሥራ ዕድልና ትምህርት ጡረታና አንገት ማስገቢያ መጠለያ ቤት፣
…የሚላስ የሚቀመስ…
የሚሉ ተጨባጭ የሰው ልጆች ጩኸቶች ናቸው።
ያኛው የመጀመሪያው ግጭት ኢትዮጵያንም ያበጣበጠው „የዘሩ ጉዳይ“
እንዲያው „የጠገቡ ልጆች“ ከመሬት ተነስተው አብሮ ለዘመናት
ተጋበተውና ተካልሰው በመልካም ጉርብትና እና በአበልጅነት
የሚኖሩትን ሰዎችና የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮችን „ሆን ብሎ አጋጭቶ“
ሥልጣን ለይ፣ ጠበብቶች አሁን ደርሰውበት እዚህ እንደሚሉት
“ሥልጣን ላይ ለመውጣት የሚያነሱት የሚጠቀሙበት መሰላልላና
አወናባጅ ዘዴና ብልሃት ነው።”ለዚህ ኤርትራ ጥሩ ምሳሌ ናት።
ምንተገኘ አሁን እሷ ተገንጥላ? በመጨረሻውስ የት ተደረሰ? ማን
ተጠቀመ?
ይህኛው አሁን „ሳይቀር ይመጣል“ የሚሉት ግጭትና ጦርነት በሞትና
በሽረት በመኖር በአለ- መኖር በሕይወትና በመከራ ላይ የተመሠረተ
ነው።
ሰዎች በአፍሪካ እንደ ሌላው ሕዝብ በልተው ጠግበው ማደር
ይፈልጋሉ። የሚጠጣ ንጹህ ወሃ የሚለበስ ልብስ እንደሌላው ሕዝብ
እነሱም…ይሻሉ። በተለይ ወጣቱ ትውልድ እንደ ወላጆቹ በቀላሉ ተታሎ
ዝም ብሎ የሚገዛ-እነሱ እንደሚሉት- አይደለም።
~ 41 ~

ከዚህ አንጻር ሲታይ የወሃና የዳቦ….የልብስና የመድሓኒት የቤትና….
ጥያቄዎች የተቀበሩ ፈንጅ ቦንቦች ናቸው። አፍሪካ ደግሞ በተለይ
መሪዎቹ ለነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች ተገቢውን መልስ ሳትሰጥ እንደ አለፉት
ዘመናት ነገሮችን ሁሉ ሸፋፍና እና አድበስብሳ ለማለፍ
ከሞከረች/ከሞከሩ – ሌሎች ቦታዎች ተጽፎ አንደሚነበበውድብልቅልቁ አንድ ቀን መውጣቱ የማይቀር ነገር ነው።
የሚፈልሱትን ስደተኞቹን አይተው ረሃብተኛውን ቆጥረው …ትርምሱ
ተጀምሮአል በርካታ ጋዜጣዎች ወደ ማለቱ ተሸጋግረዋል። በተለይ በወሃ
አጠቃቀም ጉዳይ ላይ ከአልተነጋገሩ ከአልተደማመጡ መፍትሔም
በጋራ (ከአገርም ሰው ከጎረቤትም ጋር) ቁጭ ብለው ከአልተለሙ
መተናነቅ ጋዜጣው እንደሚለው የማይቀር ነገር ነው።
አብዛኛው ከግማሽ በላይ የሚሆኑ የሰው ልጆች ዘር ሁሉ ቢቆጠሩ
የሚኖሩት በወሃ ዳር ከእሱም በሚገኘው የእርሻ ምርት ነው።
“ሰዎች ከአልተስማሙ በወሃ ጥያቄ ጦርነት መታወጁ የማይቀር ነው”
የሚለው የጀርመኑ ጋዜጣ በደቡብ አፍሪካና በሊሶቶ በኖቤል ሽልማት
ተሸላሚው በኔልሰን ማንዴላ አንዴ በታወጀው የክተት አዋጅ ታሪክ
(ስንቱ ያኔ ይህን ዜና እንደሰማ አይታወቅም) በእሱ ይጀምራል።
ደቡብ አፍሪካን የሚያጠጡ ጅረቶች የሚፈሱት ከሊሶቶ ተራራ
የሚወርዱ ንጽህ ወሃ ናቸው። አንድ ቀን ሊሶቶ ወሃዬን እንደፈለኩት
አደርጋለሁ ብላ የማንዴላን መንግሥት ለማሸበር አንድ ፕላን ጋዜጣው
እንዳለው አውጥታለች። ይህም የሰላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊውን
ማንዴላን አስደንግጦ „…ወሃውን ልቀቂ አለበለዚያ የክተት ጦር
ይከተላል“ የሚል ማስጠንቀቂያን ያስነሳል። በደቡብ አፍሪካ
የተከበበቺው ሊሶቶ ከጀመረቺው ሓሳብ እራሱዋን ቶሎ ብላ ታርቃለች።
እንደዚያው ለኢትዮጵያም ከግብጽ አንድ ቀን ማስጠንቀቂያ መምጣቱ
የማይቀር ነገር ነው ብሎ ቪኪሊክስ ላይ አንዴ የተነበበውን ሚሥጢር
ጋዜጣው ያነሳል። „…ኢትዮጵያን እንመታለን!“ያሉትን ዛቻ መልሶ
ጋዜጣው ያስታውሳል። አሁን ብዙ ቦታ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሱዳን
„በድብቅ መሬት ሸለመ /ሸጠ „ የሚባሉ ዜናዎችን በምናነብበት ሰዓት
„ሱድ ዶች ሳይቱንግ “ የተባለው የጀርመኑ ጋዜጣ „የሱዳን መንግሥት
~ 42 ~

ለግብጽ የጦር አይሮፕላኖች ማረፊያ መሬት -ያውም የኢትዮጵያ ድንበር
አጠገብ- ሰጠች“ የሚለውን አረፍተ ነገር ይዞልን ብቅ ብሎአል።
የአባይ ወንዝ የሚነሳባቸውና የሚያቋርጣቸው አገሮች ብዙ ናቸው።
ብሩንዲና ኬንያ ሩዋንዳና ሁለቱ ሱዳኖች ታንዛኒያና ኡጋንዳ በትንሴም
ቢሆን ከኢትዮጵያ የተገነጠለቺው ኤርትራና እራሱዋ ትልቁዋ የጥቁር
አባይ ወንዝ አቅራቢ ኢትዮጵያ እነዚህ ሁሉ ናቸው።
ግብጽ በጦር አይሮፕላኖቹዋ
ተነሳታ ልትደባደብና ልትማታ
የፈለገችው አገር ሌሎቹን
ሳይሆን ኢትዮጵያን ያውም
ድፍን ኢትዮጵያን ሳይሆን
ከሱዳን የማይርቀውን የወሃ
ግድብ ነው። ለግብጽ የጦር
አይሮፕላን ማረፊያ ሱዳን ሰጠች
የተባለውም መሬት ከዚያ ቦታ
የማይርቅ ነው።
ሕጉ- የዓለም አቀፍ ሕጉ
የአባይን
ወሃ
ለመጠቀም
የሚፈቅደው
ለማን
ነው?
ለግብጽ ወይስ ለኢትዮጵያ?
መነጋገር የለም እንጂ መነጋገር
ቢኖር መመካከር የለም እንጅ መመካከር ቢኖር እዚህ ጀርመን አገር
ሰው የሚጠቀመውና የሚገለገልበት ወሃ ቢያንስ ከአምስት ጊዜ በላይ
ተመልሶና ተጣርቶ በቧንቧ የሚመጣ ወሃ ነው።
ወሃ “ቆሻሻ”ተብሎ አንዴ የተጠቀምነው ወሃ ቢሆን እንኳን አይደፋም።
ወሃን እንዲጣራና ተመልሶ እንደገና እንድንጠቀምበት ንጹህ ወሃው
በቧንቧ እቤት ድረስ ሰተት ብሎ እንደመጣው ሁሉ በተማሳሳይ ዘዴ
ተመልሶ በቧንቧ ያ ወሃ አንዲት ጠብታ ደጃፍ መሬት ላይ ሳትወድቅና
ሳትደፋ ወደ ጥራት ገንዳው በቶቦ እዚያ እንዲደርስ ይላካል።
~ 43 ~

ነገሩ አጸያፊ ነገር ይመስላል። አክ የተባለበትንና የተተፋበትን ቆሻሻ
ወኃን ወይም ደግሞ የሽንት ቤት መጸዳጃ ውሃን ሺህ ጊዜ ተጣርቶ
ተመልሶ ቢመጣ እሱን እንደገና ማን ይጠቀመዋል? …ይዘገንናል።
ሳይንሱ ግን ሌላ ነው።1የአባይን ውሃ የምድቴረኒያን ባህር ፈሶ ከመግባቱ
በፊት አሥር ጊዜ መልሶ መላልሶ በኢትዮጵያም በሱዳንም በግብጽም
አገር መጠቀም ይቻላል። ጋዜጣው ስለዚህ እንደዚህ ዓይነቱ የአጠቃቀም
ዘዴ አያነሳም። ጋዜጣው በአጠቃላይ ያተኮረው በዓለም ሕግ መሠረት በ1997 እአእ የወጣ ግልጽ ያልሆነ በሠላሣ መንግሥታት ብቻ የተደገፈ
የተባበሩት መንግሥታት ደንብ አለ- በዚያ መሰረት የኢትዮጵያና የግብጽ
መጪው ውዝግብ የት ያደርሳል ?ብሎ ይጠይቃል። እግረ መንገዱንም
ስለ ኮንጎ ወንዝ ያነሳል። እዚያም የጎረቤት አገሮች በጋራ አንድ ግድብ
ገድበው የኤሌትሪክ መብራት ኃይል አመንጨተው በጋራ ለመጠቀም
እንደፈለጉም ይጠቅሳል። በተጋሊጦሹ የኮንጎ መንግሥት ይህን ሓሳብ
በጥርጣሬ ዓይን ያየዋል ብሎ ዘገባውን ጸሓፊው ይዘጋል። የዞረበት
ዓለም!
ትላንት ለጥራት የተላከው ወሃ ነገውን ተጣርቶ ለመጠጥ ወይም ለወጥ
ሥራ በሁለተኛው ቀን አይቀርብም። የተጣራው ውሃ በክረምት
ከወረደው ዝናብና ከበረዶ ወሃ ጋር ተደባልቆ መሬት ውስጥ
ከተቀበረውም ንጸህ ወሃ ጋር ተቀላቆሎ ከአሥር አመትበ ሁዋላ በደንብ
ጸድቶ አገልግሎትለላ ይውላል።
እራሱን የቻለ ሳይንስና ገንዘብ ጠሚያመጣ ሐብት ነው። ወሃ
ለአወቀበት ሕዝብ አይደፋም። ጅረትም ዝም ብሎ አይፈስም።

ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08

~ 44 ~

ጊዜና ሰው
የአዛውንት ጉባዔ

ለማሳረጊያ ከምግብ በሁዋላ በዚያ በበጋ ወራት ወደ ማምሻው ላይ
ከቡና ጋር የቀረበው ጣፋጩ ዲሰርት መንጋጋን ብቻ ሳይሆን ዓይንንም
ከሩቁ ማርኮ ምራቅ የሚያስውጥ ነው። ማነው ኢትዮጵያ ዲሰርት
የላትም? እሱንም አታውቅም የምለውን ጥያቄ አንዴ ያነሳው? ይህን
ቢያይ እሱ ደንግጦ አፉን ይይዛል።
ከዓሣና ከጎድን ጥብስ ከዶሮ መረቅና ከቀይ ወጥ ከአልጫና ከአታክልት
ከምስርና ከሽሮ ከክ ወጥና ከሽቡራ ዓሣ ከክትፎና ከቁርጥ ከአይብና
ጎመን ከፍርፍርና… ከቅልጥም ከፍትፍትና – የአገራችን ምግብ ከቻይና
ቀጥሎ በዓይነቱም በብዛቱም ሁለተኛ ነው ይባላል – የግሪክ
አማልክቶች ታላቁ የመጀመሪያው ደራሲ ሆሜር እነደ ጻፈው ግሩም
ምግብ ንጹህ አየር ደስ የሚል አስተናግዶ ሲያምራቸው ወደ ኢትዮጵያ
ይወርዱ ነበር ይላል – ከእነዚህ ሁሉ ግሩም ጠረጴዛው ላይ ከተዘረጉት
የባህል ምግቦችና የቀቃይ ጥበቦች በሁዋላ ለማሳረጊያ ከቡና ጋር
የቀረብልን ዲሰርት ጣፋጩ የነጮች አይስ ክሬም አልነበረም።
~ 45 ~

ጠረጴዛው ላይ ከለተለያዩ አበባዎች ጋር የተለያዩ
ፍራ ፍሬዎች መሶቡ ላይ በመልክ በመልካቸው
ተቀምጠዋል። ብርቱካን ሎሚ ፓፓያ ማንጎ አናናስ
መደሪን የወይን ዘለላ ሙዝ ፕላም ሸሪ ሮማንና
…ከየት
እንደመጣ
አይታወቅም
ትርንጎ
ተዘርግተዋል። በፈላ ዘይት-ድስት ውስጥ የተጠበሱት ከዚያ ውስጥ
ጥቂቶቹ ናቸው። ክብ የአናናስ ቀለበቶችና ለሁለት ከመሓከሉ የተሰነጠቁ
ሙዞች የፈላው ዘይት ውስጥ ገብተው ቀለማቸውን ቀይረዋል። በሁዋላ
የማር ወለላ ፈሶባቸዋል። ከርሸም ሲሉና ከሞቀው ማሩ ጋር አፍ ውስጥ
ሲፈሱ ግሩም ናቸው።
ይህን ቀምሶ ነው አንዱ „ይህማ
ያስኮራል! በአገራችን „የጠፋው ዲሰርት
አለ
እንዴ?“
ያለው።
ትንሽ እሳት የመታው ሽንኮራም ሞቅ
ብሎ ተቆራርጦ ቢመጣ አልጠላም አለ
ሌላው።ጥርስ ቢኖር አይደለ? …ከሳቅ
ጋር
አለሦስተኛው።
„ጥንቅሽ ብትል አይሻልም?“ አለ ሌላው።አይስክሪም ለሚፈገልጉት
በሞቀ እንጆሪና ቀይ የቡና ፍሬ የሚመስል ሸሪ በተገመሰ ሮማንና
በመንደሪን በኮክና በጥቁር ወይን ፍራ ፍሬዎች አንድ ላይ (እነዚህ ሁሉ
ኢትዮጵያ ይበቅላሉ) በጎድጓዳ ሳህኖች ተዘጋጅተውና አሸብርቀው ከላዩ
ላይ ክሬም እንደ አክሊሊ ጣል ተደርጎ ቀርቦላቸዋል።
ይህን ሲቀምሱት አንዳዶቹ „አበዱ“።
ከሠላሣ አመት በሁዋላ ጓደኞቼን ለማየት ጓጉቼ ነበር የገባሁት።
የቀመስኩት ድግስ የሚገርም ነው።
ስነሳ ከቤቴ ተቀይረው ይሆን? አርጅተው? ደክመው? ወይስ
አስተሳሰቦቻቸውን ለውጠው? ምን ያህል ዕውቀት ሰበሰቡ? ምን
ያደርጋሉ? ልጆችስ አሉአቸው? ተጋብተዋል? ተፋተዋል? ልክ አውሮፓ
ያኔ ገብቼ አካባብዬን መጽሓፍቶችን ሰውን ሴቱን ታሪኩን ለማወቅ
~ 46 ~

የጓጓሁትን ያህል አሁን በእስተእርጅና ስለ የቀድሞ ጓደኞቼ ከአየሁዋአቸው ብዙ ዘመን ነውና ተቿኩዬአለሁ።
በተለይ ያን የተማሪዎች መሰባሰቢያ አዳራሽ/አዳራሶች ከሁሉም በ1974
ዓ.ም (እአአ) የተሰበሰብንበት ሂትለር ያኔ ያሰራው ምናልባት ወደ አንድ
ሺህ የምንሆን ወጣት የአውሮፓ ተማሪዎች ከየትነውየመጡት ከሞስኮ
እስከ ፓሪስ ከለንደን እሰከ ስቶክሆልም ከለንደን እሰከ ሮም
አምስተርዳም ካርቱም የተሰበሰብንበት የኦሎምፒክ ስታዲዮም(የዓለም
ዋንጫ ጨዋታ ሲተላለፍ አንዴ አይቼአለሁ) እሱን እንደገና
በሚቀጥሉት ቀናት ለማየት በጣም ጓጉቼ ነበር።
ከዲዘርት በሁዋላ ነው የደፈረው ኮኟኩን ሌላው ውስኪውንና
ጂንቶኒኩን አረቄውንና ኡዞውን የተቀሩት በዚያ ሙቀት የተቃጠሉት
ደግሞ ወሃና ነጭ ወይናቸውን ከሲጋራቸው ጋር ይዘው ወደ ሳሎኑ
ዘለቁ። ከብት የሚረባበት ወተት ያለበት አገር – እኛ እኮ ቻይና ወይም
ጃፓን አይደለንም- ጣፋጩን አይስክርም መሥራት (ማቀዝቀዣውና
የስኳር መሥሪያው ሸንኮራ እስካለ ድረስ ማንም የሚሰራው ነው።
(ጣፋጭ ነገርን ከምግብ በሁዋላ- እንዲያው ታሪክን ለመጥቀስመቅመስን አውሮፓን ያስተማሩት ያስተዋወቁት ደግሞ -አያውቁትም
ነበር ቱርኮች ናቸው። ስለዚህ የሰው ልጆች ሥራ ነው።)
መለኪያዬን ይዤ እኔም አጥንቴ በዚያ የከተማ ዙረት መድከሙ
የታወቀኝ ሶፋው ላይ ዝርግፍ ብዬ የተቀመጥኩ ሰዓት ነው።
ድካም የጨመረብኝ የቤቱ ደረጃ
ነው። ያን ረጅም ደረጃ ከተማይቱዋን
ስቃኝ
ረፍዶ
ስለነበር- በዚህ ዕድሜዬ ረስቼው
ነው እንጅ – ይህን አሁን ሳየው
ማድረግ አይገባኝም ነበር – አንዴ
ሮጬ ቁና ቁና መተንፈስ የጀመርኩት ከምግብ በፊት ነው። በሩን
በፈገግታ የከፈቱልኝ ልጆች አስደንግጠውኛል።
ከያዙት ሰታቴ ሳህን ላይ ይህን? ወይስ ይህን? ይውሰዱ ! ብለው
ከማስተናገዳቸው በላይ ኮረዳዎቹ -አንዱዋ ነጭ ጠጉር አላት ሌላዋ ቀይ
አንደኛዋ ጥቁርና አራተኛዋ በአለ ቡና ቀለም- በዕድሜአቸውም
~ 47 ~

በቁንጅናቸውም በግልጽነታቸውም በአነጋገራቸው የቀድሞውን
የወጣትነት ዘመኔን የሰባውን አመተ ምህርት የበርሊን ኑሮ እንዳለ
አስታወሱኝ።
ገጽታቸውና
ፊታቸው
በየዩኒቨርስቲው
የምግብና
የሌክቸር አዳራሽ በየሰላማዊ
ሠልፉና በየቲች ኢኑ በ
የመናፈሻውና
በየቡና
ቤቱ
በተማሪዎች መኖሪያ ቤትና እነሱ
በነበራቸው
ቢራ
ቤቶቹ
በየመንገዱና
ሱቁ
ያኔ
የማውቃቸው አብረውኝ ያኔ
የነበሩ ተማሪዎች መሰለኝ። ዛሬ እነሱ የት እንዳሉ? ምን እንደሚሰሩ
ጓደኛዬን እጠይቃለሁ ነገሩን አሳደርኩኝ።
የጀርመኑን የቀዘቀዘ ነጭ ወይን ጠጅ „አመሰግናለሁ“ ብዬ በአልተረሳኝ
ጀርመንኛዬ ከአንዱዋ ተቀብዬ አንድ ሁለት በረዶ እንዳይመታኝ ጣል
አድርጌበት አምቦ ወሃ በላዩ ላይ ከልሼበት ወደ ውስጥ ጓደኞቼ ወደ
ተቀመጡበት ሳሎን በሁለቱ
ኮረዳዎች ታጅቤ እየተመራሁ
ወደ ውስጥ ገባሁ።
በ1999 ዓ.ም. (እ.አ.አ)
ስድሳኛውን
አመቱን
ያከበረው እኛ ሁላችንን
እንደገና የጋበዘን ወዳጄ
መሓል ቆሞ ሰውን በሙሉ ከተለያዩ ቦታ የመጡ ስለሆነ እገሌ ሙያው…
እንደዚህ ነው። እገሌ ደግሞ…የተማረው ይህን ነው…. እያለ
ያስተዋውቃል።
~ 48 ~

የደረስኩበት „…ይህ አሁን ሸብቶ ጨዋ ሰው መስሎ ዝም ብሎ
መሓላችሁ ተቀምጦ የምታዩት ሰው በዘመኑ ቢያገኛችሁ ይሻጣችሁ
ነበር። የፖለቲካ ዝንባሌው አትርሱት በዚያ በስድሳው መጨረሻና
በሰባው አመተ ምህረት ሰው ሁሉ ጸረ-አሜሪካን በነበረበት ዘመን እሱ
የአሜሪካንና የሆሊውድ የቴክስና የዘናጮች ወዳጅ ነበር። በሁዋላ
ምናልባት ሶሻል ዲሞክራት እንኳን ብትሆኑ ይሻላል ይለን ነበር።“ እያለ
የሚያስተዋውቀው ሰው ላይ ነው።
„ይህኛው ደግሞ ከአራት ጓደኞቹ ጋር ፔኪንግ ሪቪውን የሚያነቡ
ማኦኢሰቶችና እነ ቹኤንላይንና እነ ሁዋ ኩዋ ፌንግን የሚያመልኩ ነበሩ።
“ ብሎ ይቀልዳል።
“ ካላቸራል ሪቮሉሽንን የሚያደንቁ ቴንግ ሲያዮ ፒንግን የማይወዱ
በሁዋላ ደግሞ እሱ አሸናፊ ሁኖ ሴንትራል ኮሚቴውን ሲመራ
ፊታቸውን አዙረው የማኦን ሚስት ዓይኑዋ አፈር ይብላ ያሉም ነበር…“
የሌሎቹን ስም ይጠራል።
„እሱ
ደግሞ
በቀኝ
በኩል
የተቀመጠው ወዳጄ -ምንም እንኳን
አብሮ አደጌ ቢሆንም ልቡን ያኔ
የሳበው ቻይና ሳይሆን ሞስኮ ነበር።“
ይላል።
ቤቱ መቼም ሰፋፊና ረዣዥም ክፍል
አለው። በቆሙበት ሁሉ ሁለት በር
በግራና በቀኝ ይታያል። ጣራው ሦስት ተኩል ወይም አራት ሜትር
ይሆናል።
ክፍሎቹን ጥንታዊ የግሪክና የሮማ ቅርጾች ሥዕሎችና መጽሃፍቶች
ሞልተውታል። እኔን ትዝ የሚለኝ ከአእምሮዬ በርሊን ስደርስ
ያልወጣው የዱሮ የተማሪዎች መኖሪያ ቤታችን ነበር።
~ 49 ~

ከነበሩት ሴቶች ውስጥ ለአንዱዋ ዕድል ሰጥቶ እነሱን በማስተዋወቁ
ቀጠለ።
እነደገና አንደኛዋን እሷ አጠገብ የተቀመጠቺውን ዘሎ እንግዳ
አስተናጋጁ „…ያ ደግሞ „ በጣቱ እያሳየ „…የቀድሞውን የዘውድ አገዛዝ
የኃይለ ሥላሴን መንግሥት አልጋውን የኢትዮጵያ መፍትሔ እሱ ነው
እያለ ፊት ለፊት ይደግፍ ነበር…“ የሚለውን ሰው ጠቆመ። „የተማሪዎች
ስብሰባም ስንሄድ ቆይ `ዋጋሽን` አንድ ቀን ታገኚአለሽ እያለ ይዝትብን
ነበር…“ እያለ የጠረጴዛው ግራና ቀኝ የተቀመጡትን በስማቸው እየጠራ
ሲያስተዋውቅ በመካከሉ አንድት ቁንጅናዋ በምንም ዓይነት ከዚህ ሁሉ
ዘመን በሁዋላ ያልከዳት ሳቂታዋ ወይዘሮ…ሴት ልጅዋን አስከትላ ሳሎን
ውስጥ ገብታ ጠቅላላ አተኩሮውን በሁለት ደቂቃ ስባ እሱዋ እራሱዋ
እንግዳ ሳትሆን ቤተኛ ሆና ያ ጎደለ ይሄ ቀረ ማለት ጀመረች።
ዱሮውንም በቀልጣፋነቱዋ እወዳት ነበር። በፈገግታዋና በጥቅሻ ያኔ
በርሊን ስትመጣ አንገታችንን የምታዞረው ልጅ አሁን ቤቱን በአንዴ
ተቆጣጠረች።
ይዛት የመጣች ልጅዋ ከመቅላቱዋ ሌላ (አባቱዋ ፈረንጅ መሆን
አለበት)ቁርጥ እናቱዋን ነው። እሱዋን ማስተዋወቅ አያስፈልገኝም ብሎ
ወደ“ አናርኪስቶቹ“ ወደ ሰሜን ኮሪያኖቹ ወደ ቼና ወደ ካስትሮ
„ተከታዮች „ ከእነሱም ጋር ወደ ሁለቱ „አልባኒስቶቹ“ ፊቱን አዞረ።
እንጂነሮችና መሓንዲሶች ነበሩ።ቄሶችና ዲያቆኖች ተገኝተው ነበር ።
እነሱ ዝም ብለው ይህን ጉድ ይህን ታሪክ እየጠጡ ያዳምጣሉ።
„እሱ አቶ…የማሪያምና የክርስቶስን ሥዕል ግድግዳው ላይ ሰቅሎ ሲጸልይ
እነ እገሌ የማርክስና የሌኒን የስታሊንና የ…ፎቶዎች የቤት ግድግዳቸው
ላይ ይሰቅሉ ነበር“ አለ።„ እሱ ድርሳነ ሚካኤልን ሲያነብ እኛ ማርክስ
…“ ሲባል ሁሉም ይስቃሉ።
~ 50 ~

አንድ ወጥት ወንድ ልጅ እግሩን አጣምሮ አባቱ አጠገብ ቁጭ ብሎ
ይህን ሁሉ ጉድ በሚችለው አማርኛ ለመረዳት ይሞክራል። ከእሱ
አጠገብ የግሪክ ሐውልቶች አሉ።
ግድግዳው ላይ የንግሥት ሳባ ጉዞ ግሩም
ተደርጎ ተስሎ ተሰቅሎአል።
በሁዋላ ስሰማ በሩ ላይ ከተቀበሉኝ
ሴቶች
ውስጥ
አንደኛዋ
የእሱ
የተቀመጠው ጎልማሣ እህት ስድሳኛውን
አመቱን
ያኔ
ያከበረው
ጓደኛዬ
ልጅ/ልጆች ናቸው።
እኛም ያኔ በእነሱ ዕድሜ በነበርንበት ዘመን- በስድሳውና በሳባው አመተ
ምህርት „ያዙኝ ልቀቁኝ“ እንል ነበር። እነሱ ግን ረጋ ያሉ ናቸው።“
እያልኩ እራሴንም ትውልዴን እታዘባለሁ።
ትንሽ ቆይተው „…ሁላችሁም ጥቁር ናችሁ።
ለምንድነው እኔ ትግሬ እኔ ኦሮሞ አፋር ሱማሌ
ሓማሴን እያላችሁ የምትጣሉት ?“ ብለው
ሰውን ሁሉ ይጠይቃሉ።
ለዚህ መልስ የለም። ዝም ብሎ ታለፈ። ሌላም
አርዕስት ተነሳ።
„የፕሮሌታሪያን
ያኔእንደሚባለው
የላብ
አደሩ/ወዝ አደሩ አምባገነን መንግሥት…“ምን ታይቶን ነው ይህን ሐሳብ
ርዕዮተ ዓለም የተቀበልነው? አለ አንደኛው። ቤቱ ሳቀ። -ዱሮ ይህ
ቢሆን መግቢያም ቦታ የለም።…ትወገዛለህ! ትኮነናለህ!ለእነሱ -ለወጣቱ
ትውልድ እንደዚህ ዓይነቱ ፖለቲካ ምናቸውም አይደለም። „ለመሆኑ
ለዚህ አመለካከት ለመሞት ዝግጁ ነህ ወይ ? ተብለው ቢጠየቁ …ምን
~ 51 ~

አልክ?“ ብለው የሚቀልዱ ናቸው።ወደ ሰባው መጨረሻ ላይ ቀስ እያለ
ብቅ ያለው ከሰማንያው ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ የተደራጁበትን ቤት
እየጣሉ ወደ „ነጻ-አውጪዎቹ „ እየፈለሱ የገቡትን ሰዎች ሰውዬው
እንደጀመረው በቦታው ላይ ነበሩ ማስተዋወቁን ቀጠለበት።
ቆይቶ በአርባ አመት ውስጥ ስንት ጎዳና ያ የተማረ ሰው ሁሉ እንደተጓዘ
ይተረክ ጀመር።
ለመሆኑ ከዚህ ሁሉ ድካም በሁዋላ… ምን አገኘን? ተባለ። ….ምን
አተረፍን? ለመሆኑ ለአገራችን ምን ሰራን? የትስ ደረስን? የት ነው
ቀልጠን የቀረነው? …ስንቱ ሞተ? ለምንስ ሞቱ?… እገሌ አሁን የት ነው
ያለው? የሚሉ ጥያቄዎች ተነሱ።በመጨረሻውስ ኢትዮጵያ ምን አገኝች?
ተባለ።…ለዚህ ሁሉ ጥያቄና መልስ ፍለጋ ምሽቱ እንዳለ በውይይት ፉት
ብሎ አለቀ።
አንድ ፈረንጅ ሲቀልድ „ኢትዮጵያ- ኤርትራ በመገንጠሉዋ- በተባበሩት
መንግሥታት ድርጅት ውስጥ ሁለት ድምጽ ያላት አገር በአሁኑ ጊዜ
እሱዋ ብቻ ናት“ ብሎ የቀለደብን ነገር ተነሳ። እነሱም ይህ በተባለላቸው
ማግስት ማንም እንደሚያውቀው ጦር ተማዘው ተዋጉ። ይህ ደግሞ ሌላ
እራሱን የቻለ አርእስት ሁኖ ተከፈተ። መቼም እንደ ኢትዮጵያኖች
“ክርክር” የሚወድ ሕዝብ የለም። የቆየ ባህላችን ነው። ዱሮ ሥርዓት
ነበረው። አሁን…
ነገ የመርከብ ሽርሽር እና የበርሊን አጥር ጉብኝት ዝነኛው የኦለምፒክ
ስታዲዮም አዳራሽ… ፕሮግራም ስለአለን በጊዜ ብንተኛ ሲባል ሰው ሁሉ
ተቃወመ። ከዚህ ሁሉ አመት በሁዋላ ወይኑ እየተቀዳ ማን ይተኛል!
ቀልዱ መጣ። ዘፈን ተዘፈነ። ግጥሙ ወረደ። የዱሮ ታሪክ ተነሳ።አለ
ጣጣመንጣጣ የምንሄድባቸው ዳንስ ቤቶች የተማሪ ማህበር ጉባዔ
በበርሊን ከተማ በትልቁ ስታዲዮም በዚያን ጊዜ በተለኮሰው የክፍፍሉ
ዘመን የነበሩ ነገሮች ሁሉ ተጠቀሱ። የፌደረሼሽን መቋቋም የአውሮፓ
~ 52 ~

ማህበር ለሁለት መሰነጠቅ የደርግ ደጋፊዎች መሰባሰብ…ወዘተ …ወዘተ…
ታሪክ ቀጠለ።
እንደገና የዚህ ሁሉጉዞ ድካም ለአገሪቱ ምን አመጣ ተባለ?
ቁም ነገሩ እሱ ሳይሆን አንደኛዋ ዝም ብላ የምታዳምጠን ጓደኛችን
እንዳለችው „…ቁም
ነገሩ ወንድሞቼ
ያለው፣
ያለፈው
ታሪክ
ላይ
መነታረክ ሳይሆን
ቁም ነገሩ ያለው
እኛ
የቀረነውና
የተረፍነው ሰዎች
እንደዚህ ተገናኝተን
ስንጫወትና
ያለፈውን
ዘመን
ግንዛቤአችን
ውስጥ አስገብተን
አንዳንዴ
የሚያከራክር ቢሆንም መነጋገር አብረን መቻላችን ነው።….መነጋገር
በመካከላችን እሰከ አለ ድረስ ደግሞ ኢትዮጵያ አለች ማለት እንችላለን።
ዱሮ ተለያይቶ ተበታትኖ የነበረ ሰው አሁን እኛ እንደምናደርገው
በየአለበት መነጋገር ከጀመረ ደግሞ ትልቅ ነገር ነው።
ዘመኑ ተቀይሮአል።
ይህ ደግሞ ተቀራርቦ መነጋገሩ የአገሪቱ የኢትዮጵያ ተስፋ ነው።እንደዚህ
ዓይነቱ ነገር መኖር ደግሞ አዲስ አመለካከትን በሰው ልጆች ዘንድ
የሚፈጥረው ነው። በእኔ ግምት“ ቀጥላ እንዳለቺው“ የዕብደት ዘመን
በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ትውልድ ያለ ነገር ነው።“
„ልንገራችሁ“ አለች አየር ስባ። „የሓዘን ዘመን አለ። የአእምሮ ቀውስ
ዘመን አለ። የኢኮኖሚና የፖለቲካ ክሪዝም ዘመን አለ። ኢትዮጵያን
በአለፉት አርባና ሃምሣ አመታት የመታት ቀውስ አውሮፓን አንዴ
በሃያኛው ክፍለ -ዘመን ከመታው የአእምሮ ቀውስ ጋር የሚነጻጻር ነው።
ከማድሪድ እሰከ ሞስኮ ከባልካን አስከ ፓሌርሞና ኦስሎ የተለያዩ
አይዲኦሎጂዎች ተነስተው ይህቺን አህጉር አተራምሰዋታል።“
„ታዲያ አሁን እኛ ከገባንበት ቀውስ ልንወጣ እንችላለን ነው
የምትይው?“ አላት አንዱ።
~ 53 ~

አዎን አለ-ሌላው ጣልቃ ገብቶ።
እንዴት? የሚባለው ጥያቄ ተወረወረ።
„…ዘለዓለማዊ አስተሳሰብ፣ጊዜ የማይሽረውና ጊዜ የማይቀይረው
አመለካከት፣ የለም። እራሱ የሳይንስ ምርምር እንኳን ቢሆን ከተወሰነ
አመት በሁዋላ የሚቀየር የሚለወጥ የሚሻሻል ነው። ከዚያም በላይ
ሁላችንም ከተወሰነ ጊዜ በሁዋላ
-ሕይወት ገደብ አላት- ከዚህቺ
ዓለም ሁላችንም ተሰናብተን
የምንሄድ ነን። የበርሊን ግንብ
ይፈርሳል።ሶቪየት
ሕብረት
ይወድቃል።ኮሚኒስቶች ሥልጣን
በሕዝብ ድጋፍ እንደወጡት
በሕዝብ አመጽ አንድ ቀን
ወድቀው ሥልጣኑን ያስረክባሉ
ብሎ የገመተ ሰው አልነበረም።
ግን እንደምናየው እነሱም ሄደዋል።…“ አለች።
ዝምታ ለጊዜው ሰፈነ። ቀልደኛው ጓደኛችን ለሞቱትም ለተረፉትም
ለአሉትም ለተወለዱትም መለኪያችንን አንስተን እንጠጣ አለ። ሁሉም
መለኪያቸውን አነሱ።
አንደኛው ለእናት አገር ለኢትጵያ ቀስ ብሎ አለ።
የተሰበሰብንበት ምክንያት እላይ እንደተጠቀሰው ጓደኛችን ስድሳኛውን
አመቱን ከእኛ ጋር ለማክበር ከስድስት ወር በፊት በ1999 ዓ.ም. (እአአ)
በአደረገልን ጥሪ መሰረት ነው።ቀደም ብለው የደረሱት እንዳጫወቱኝ
እነሱ ሲደርሱ ሽንኩርቱ ጅንጅብሉ ሥጋው ኳኳ እያለ ሰው ሁሉእ
የተተረማመስ ሲከተፍ እነሱ ያዩትን ለአልነበረነው አጫውተዋል።
ሰውዬው ፊውዳል ነው ብለው እሰከ መጠራጠር ድረስ እንደሄዱም
ነግረውኛል።
~ 54 ~

ከአንድ ሳምንት በፊት ከፈረንጅ ጓደኞቹ ጋር በተመሳሳይ ድግስ አብሮ
ከእነሱ ጋር አክብሮአል። የጥሪው ደብዳቤውና የስልክ ንግግሩ ማርኮኝ
ነው የመጣሁት። ከዚያም በላይ ስንት አመት ያላየሁትን ጓደኞቼን
ለማየት ነው።
ደብዳቤው እንደዚህ ይላል።
….ይቀጥላል። ይቀጥላል።

ዘመነ፥ብርሃን / Enlightenment

እስከ ነገው ብርሃን በትዝታ እንቆይ
ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08

~ 55 ~