You are on page 1of 50

~ 1 ~

የአፍሪቃው የፖለቲካ እንቆቅልሽ/ ርዕስ አንቀጽ

አሁንም በ21ኛው ክፍለ-ዘመን ያልተፈታው

ትልቁ የአፍሪቃ የፖለቲካ እንቆቅልሽ

ነጻነት ወይስ ባርነት ?

እንቆቅልሽ ነጻነት ወይስ ባርነት ? ለጥቂት ደቂቃ ለአንድ ሰከንድ ስለ

ለጥቂት ደቂቃ ለአንድ ሰከንድ ስለ የባህር በርና ስለ አሰብ ስለ ኤርትራም መገንጠል እንርሣ። ስለ ገዳ ሥርዓትና ስለ ኦሮሞ ጉዳይ ስለ ኦጋዴን ልጆች ጥያቄ በአጠቃላይ ከሩሲያ ተነስቶ ኢትዮጵያ ስለ ገባው „ስለ ብሔር/ብሔረሰብ መብት እሰከ መገንጠል ድረስ…“ ስለ እሱም የስታሊንን ድረሰት ማሰብ ለጊዜው ለትንሽ ደቂቃ እናቁም። ትልቁ የአፍሪቃ እንቆቅልሽ ከባድ ይመስላል እንጅ አንዲት በጣም ትንሽ ነገር ናት።

ሳይታወቀን ግን ይህን ነገር ደህና ነው ብለን ተሸክመነው ስንከራተት ከርመናል። ብዙዎቹ ሕይወታቸውን እሰከ መሰዋት ድረስ ሄደዋል። ሌሎቹ ሐብታቸውን የተቀሩት ጉልበታቸውን አብዛኛው ጊዜአቸውን በእሱ ላይ አሳልፈዋል።

~ 3 ~

ይህ „ነጻነት“ አንድ ቀን ይመጣል ብለው ሁሉም ተስፋ አድርገው ነበር። ፋታ ስለማይሰጠው ስለ ዳቦና እንጀራ ጥያቄ (ይህን ማንሳቱን የኢትዮጵያ ፖለቲከኛ ረስቶታል) ስለ የሥራ ዕድልና የጡረታ ገንዘብ ስለ ሕክምናና ስለ ጤና ጉዳዮች ለጊዜው እነሱንም ወደ ጎን እንተው።

በእነሱ ፋንታ ስለ ሥልጣን አያያዝና ሥልጣን ላይ መውጣት ሥልጣንም ላይ መሰንበትና ከእሱም አልወርድም ማለት ምን እንደሆነ እናሰላስል።

*

ጊዜውን በደንብ ማስታወስ ያስቸግራል እንጂ ይህን ዛሬ ሳነሳ አንድ ሁኔታ ትዝ ይለኛል።

በአንዱ የጥቅምት ሃያ ሦስት „የዘውድ በዓል ቀን“ አጼ ኃይለ ሥላሴ በዚያ በአንዱ በቀዩ ሮልስ ግልጽ መኪናቸው ውስጥ ከእቴጌይቱ ጋር ተቀምጠው በነጫጭ ፈረሶችና የደመቀ ልብስ በለበሱ ፈረሰኞች ታጅበው ሲሄዱ መንገድ ዳር የሰማሁት ነገር አሁን ስለ ሥልጣን በማነሳበት ሰዓት – አይረሳምና- እንደገና በአእምሮዬ ብቅ ይላል።

በእጅ መኪናውን መንካት ነው እንጂ የሚቀረው በዚያ ጠባብ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጎዳና (ንጉሡ አይፈሩም) ክቡራን ልዑላንና ልዕልቶች የአገሪቱን ትላልቅ መሣፍንቶችን መኳንንቶች የጦር ጄነራሎችና ሚኒስትሮች የፓርላማ አባሎችና አገረ ገዢዎች…በአጠገባችን ሲያልፉ የሚቀልጠው እልልታ የሚሰማው ጭብጨባና ሁካታ ለንጉሡ „ታቦት“ የወጣ ይመስላል።

ለጥ ብለው እጅ የሚነሱ አሉ። የጠቅል አሽከር ብለው የሚፎክሩ። …ዕድሜህን ያርዝመው ብለው የሚመርቁ። በዚያ ትርምስ የካበው ቀለም ዓይን ይስባል የልዕልቶቹ የአልማዝ አክሊል ይማርካል አንዲት ትንሽ ልጅ እዚያ መንገዱ ላይ በሚታየው ግርግርና ተአምር በዚያ ትርምስ በውበቱም ተደንቃ የእናቱዋን ቀሚስ ጎትታ „…ለእኔም አንድ ቀን አንደዚህ ይደረግልኛል?… እኔም እንደነሱ

~ 4 ~

መሆን እፈልጋለሁ…አይደለም እማዬ…እማዬ!“ ስትል እንደ እስዋ እንደ እህቱ የፈነደቀው ታናሽ ወንድሙዋ ቀበል አድርጎ „…እኔ ግን እነደዚያ ሰውዬ -ንጉሡን እያሳየ – በትልቁ መኪና ውስጥ ተቀምጬ መሄድ እፈልጋለሁ…“ሲል አባትዬው ደንግጦ „…ዝም በል! ቀዥቃዣ…“ ብሎ ሲቆጣው ልጁ -ጥፋቱ ስለ አልገባው ማልቀስ ጀመረ።

ይህን ሰምተው ፈገግ ያሉ አርበኞች አጠገቤ ነበሩ። እናቱ እጅ ላይ ሁኖ -እንዳያለቅስ አባብለው- ይህ ልጅ ትርምሱን ዓይኑን ከፍቶ መከታተሉን ቀጠለበት።

ይህን ያለፈ ገጠመኝ እኔ እዚህ የማነሳው፣ አንዳንዱ ቸኩሎ ስም እንደሚያወጣው፣ የለፈው ስርዓትና ወግ ናፍቆኝ ሳይሆን፣ ስረ መሰረት ያለው ጉዳይ ላይ አእምሮዋችንን ለማሳረፍ እንድንችል ያህል ነው!

ስለ ትልቁ የዛሬው የአፍሪቃ እንቆ ቅልሽ፤ ስለ ሥልጣን አያያዝና ሥልጣን ላይ መውጣት፣ ሥልጣንም ላይ መሰንበትና ከእሱም አልወርድም ማለት ምን እንደሆነ እንድናስብ እንድንመረምር ነው።

ያ ልጅ ምን ታይቶት ይሆን? ይህ የልጆች ምኞት ከየት መጣ?… ይህ ብዙው ሰው የሚመኘው ግን ለመናገር የሚከብደው „የሥልጣን ጥማት“ ምንድነው? …ይህንንስ ለማሰብ ከጀርባው የሚገፋፋው ምክንያት ምንድነው?

ወጣቱ ቦካሣ፣ ተማሪው ሙጋቤ በሁዋላ ወታደር የሆነው መንግሥቱ ኃይለ ማሪያም ኢሳያስ አፈወርቂ እና መለሰ ዜናዊ ወይም ጆን ኤፍ ኬነዲና ቶማስ ጄፈርሰን ወይም ሙሴ ወይም ደግሞ በግ ጠባቂው (ንጉሥ) ዳዊት ማኦ ሴቱንግ ስታሊንና ሒትለር ካስትሮና ኬንያታ ማንዴላና ሑፌት ቧኜ…እነ አንጌላ ሜርክልና እነ ማርግሬት ቴቸርና ደጃች ተፈሪ መኮንን እና አጤ ቴዎድርስ ናፖሊዮንና… ሌሎቹ በልጅነት ዘመናቸው እላይ እንደተጠቀሱት ሁለቱ ልጆች „ሥልጣንን ተመኝተው የእናታቸውን ቀሚስ ይጎትቱ አይጎትቱ -ተጽፎ የተላለፈልን ነገር ስለ ሌለ ምንም የምናውቀው ነገር የለም።

~ 5 ~

በደንብ የምናውቀው ነገር ቢኖር እነዚህ እላይ ዝም ተብሎ ስማቸው የተጠቀሰ የተለያዩ ሰዎች በተለያዩ መንገዶችና ዘዴዎች… ሥልጣን ላይ ወጥተው „ሥራቸውን ሰርተው“ አልፈዋል። ጥቂቶቹ አሁንም ሥልጣን ላይ ናቸው። አንዳንዱ ለረዥም አመታት ገዝቶአል።

ሌላው ለጥቂት አመታት ኃላፊነቱን ተቀብሎ መልሶ ሥልጣኑን ለሕዝቡ አስረክቦአል። አብዛኛው በሰላም በምርጫ ተሸንፎ ተተኪውን ጨብጦ ጠረጴዛውን በገዛ ፈቃዱ ጠርጎ ወንበሩንና የቢሮ ቁልፉን ለተከታዩ ሰጥቶአል። ሌላው አምባገነን የሚጠረጥራቸውን „ተቀናቃኞቹን“ ፈጅቶ አልለቅም ብሎ ተቀምጦአል።

ማናቸው እነዚህ የተለያዩ የሥልጣን ሰዎች? ምንድናቸው እነዚህ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች? ምን ዓይነት የፖለቲካ ዓላማ ነው የሚከተሉት? ድርጅታቸው የተገነባበት የርዕዮተ- ዓለሙ ሕንጻቸው ምን ይመስላል? ተከታዮቻቸውስ ምን ያስባሉ? እነሱን መቆጣጠር ይቻላል ወይ? ይህ ከሆነስ…እንዴት መቆጣጠር ይቻላል?

እነዚያ ሁለቱ ልጆች „አንዱ ንጉሥ አንደኛዋ ንግሥት በኢትዮጵያ ላይ ለመሆን…“ ገና አፍንጫቸውን ሳያብሱ የተመኙት ሚጢጢዎች በዚያ ሓሳባቸው የት እንደ ደረሱ አይታወቅም።

ምናልባት ኢህአፓና መኢሶን በሚባለው የተማሪዎች ክፍፍል ውስጥ ገብተው እነሱም ተከፋፍለው በባዶ ሜዳ ተናንቀው ይሆናል። ወይም አንዱ ኤርትራ ሄዶ ሌላው አዲስ አበባ ቀርቶ ይሆን?። ወይ ሁለቱም በስደት ላይ ናቸው?…ወይስ አንዱ የአባቱን ዘር ሌላው የእናቱን ወገን መርጦ ይሆን? ደርግ ጨርሶአቸውስ ቢሆን?… በአለፈው እትማችን ስለ „ፖለቲካ እንደ ሙያ“ ስናነሳ ስለ ሦስት „የአስተዳደር ሥርዓቶች „ አንስተን – ሲውርድ ሲዋረድ ስለመጣው የዘውድ ውርሰ መንግሥት ትራዲሽና ሥርዓት ተርከናል።

በሕግ ላይ የተመሰረተ ራሽናል የሚባለው በሁለተኛ ደረጃ ጠቅሰን ስለ ሦስተኛው „ጊዜ የሚወልደው ጊዜ የወለደው ባለ ግርማ ሞገሱ የታምራተኛው የካርስማቲክ ሰው ሥርዓትና አስተዳደር (ይህ የሃይማኖት መሪዎችን ነቢዮችንም ይጠቀልላ)- የጀርመኑን ማክስ ቬበርን

~ 6 ~

ጥናትና አተናተን ተመልክተን እሱንም ተከትለን ስለ እነሱ ስለ ሦስቱ ሥርዓቶች ከብዙ በጥቂቱ እቅርበናል።

ዞሮ ዞሮ ሁሉም ሥርዓት በሕዝቡ ዘንድ „ተቀባይነት ሌጂትሜስ „ እንዲኖረው የግድ ያስፈልጋል። ተቀባይነት የሌለው „አስተዳደር“ ደግሞ ታሪክ እንደሚያሳየውና እንደሚያስተምረው መጨረሻው ያው የማይቀርለት ውድቀት ነው።

በአፍሪካ የምናየው የፖለቲካ እንቆቅልሽ አባት ለልጁ- ኮንጎን የካቢላን ሥራ ተመልከት- ሥልጣኑን በቀጥታ እንደ ዘውድ አገዛዝ የሚያወርስበት አካባቢና ቦታ ሁኖአል።

ሌላም አዲስና አዳዲስ ነገሮች ቢያንስ ከሃያ አመት ወዲህ ብቅ ብሎአል። እሱም„የነጻነትና የባርነት“ ትክክለኛ ትርጉሙ ተምታቶና ተቀያይሮ „ባርነት“ ማለት በአንድ ፓርቲ አምባገነን አገዛዝ ሥር እየተሰቃዩ መኖር እንደ „ነጻነት“ ተቆጥሮአል።

ለሰበአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበር ለእነሱም በሥራ ላይ እንዲውሉ መጠየቅና ለዜጋ ነጻነት ድምጽን ማሰማት ደግሞ እነደ “ወንጄል“ ተቆጥሮ የሚያስከስስ የሚያስወነጅል አህጉር ሁኖአል። ነጻነት ምንድነው? ባርነትስ አሁን በያዝነው ዘመን እሱ ምንድነው?

ሰሙና ወርቁን „የነጻነትና የባርነትን“ ፈልፍሎ አውጥቶ ይህን እንቆቅልሽ የዛሬው እትም ለመፍታት ይሞክራል። የሥልጣን ሰዎች ምንድናቸው?

መልካም ንባብ

ዋና አዘጋጁ

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ነጻነት ወይስ ባርነት ? ሥልጣን እና የሰው ልጆች!

ባርነት ? ሥልጣን እና የሰው ልጆች ! ነጻነት ወይስ ባርነት? * ሥልጣንና

ነጻነት ወይስ ባርነት?

*

ሥልጣንና ሰው!

ወይስ ባርነት? * ሥልጣንና ሰው! የገዢዎች የረቀቀ ብልሃት ጠንክሮ

የገዢዎች የረቀቀ ብልሃት ጠንክሮ የዜጎችች ፍረሃት ግልጽ ሁኖ የሚታይበት ቦታ አፍሪካ ነው። እንደልባቸውም አምባገነኖች የሚርመሰመሱበት አንድ የቀረች ሜዳ አለ ቢባል እዚያው:- አፍሪካ ነው። ግን ማነው አምባገነን? ማነው የቶታሊቴሪያን አስተሳሰብ

~ 8 ~

አራማጅ? ማነው ለዲሞክራሲና ሰበአዊ መብቶች መከበር የቆመው ? ይህን መረዳት ደግሞ እዚያ አስቸጋሪ ነው።

መረዳት ደግሞ እዚያ አስቸጋሪ ነው። በብዙ ቦታ፣ በዓለም ዙሪያ፣

በብዙ ቦታ፣ በዓለም ዙሪያ፣ አምባገነኖችና የቶታሊቴሪያን ፍልስፍና አራማጆች ተባረዋል። በአሜሪካና በካናዳ ዱሮም ቢሆን የሉም። አልነበሩም። በአውሮፓ ከሃያ አመት በፊት ድራሻቸው ጠፍቶአል። በደቡብ አሜሪካ ነጻነታቸውን ተቀምተዋል። በእሲያ ቁጥራቸው በጣም እየቀነሰ መጥቶ አንድና ሁለት አገሮች ብቻ አምባገነኖቹን ለጉድ ታቅፈው ቁጭ ብለዋል።

ለጉድ ታቅፈው ቁጭ ብለዋል። በአፍሪካ ግን ማንም እንደሚያውቀው

በአፍሪካ ግን ማንም እንደሚያውቀው ተራብተው ተባዝተው እግራቸውን ዘርግተው ተቀምጠዋል። አንዱን ከአንዱ መለየት ያስቸግራል። ይህም በመሆኑ ትክክለኛ አመለካከት በዚህ ጥያቄ – በነጻነትና በባርነት – ላይ የለም።

~ 9 ~

አንዱን ተገላገልን ስንል ሌላው ከተፍ ይላል። አንድን ሕዝብ መከራ አሳይቶ ጊዜ የጣለውና የተባረረውም – እሱ አያፍርም እንደገና ለመምጣት ሽር ጉድ ይላል። ከፊሉ ዕድሉን ለመሞከር ዱር ገብቶአል። ሌላው ከተማውን ይዞአል። የተቀረው ስደት ወርዶ ጊዜውን ተራውን

ስደት ወርዶ ጊዜውን ተራውን ይጠብቃል። በትናንሽ ቡድኖች

ይጠብቃል።

በትናንሽ ቡድኖች በየአለበት እንደምናየው ቶታሊቴሪያን አስተሳሰብ በስውር የሚያራምዱ ሰዎች ተሰባስበዋል።

በጋዜጣ አታሚዎች ቢሮና በቴሌቭዠን ጣቢያዎች እነዚህ አምባገነኖች ተሰግስገው ተቀምጠዋል። የአፍሪካ ቤተ-መንግሥት የእነሱ መግቢያና መውጫ ማደሪያቸውም ሁኖአል። የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን በአፍሪካ በብዙ አገሮች እነሱ ተከፋፍለው አስፈራርተው ይዘዋል።

መንገድ ላይ ትላልቅ መኪናዎቻቸውን ይዘው „ልቀቁ“ እያሉ እግረኛውንም ሹፌሩነም ሲያባርሩ እንመለከታቸዋለን። አደባባዩና ቡና ቤቱ ሆቴሉና ባንኩ በእነሱ ቁጥጥር ሥራ ነው። የፖሊሲ ሠራዊቱን ቤታቸው ቁጭ ብለው ያዙታል። ዳኛውን ትዕዛዝ እየሰጡ ያራውጡታል።

ወታደሩን በፈለጉበት ቦታና ሜዳ በቀንና በማታ በብርድና በቁር በሁሉም አቅጣጫ ያሰማሩታል።

መሸት ሲል ደግሞ በቴሌቪዥን ብቅ ብለው ማን እንደሆኑ ፊታቸውን አስመትተው ዞር ይላሉ። መንገድ ላይ ሽጉጥና ጠበንጃቸውን ይዘው ይንጎራደዳሉ።

ችግር-

ሌሎቹ

በየፊናአቸው ጫካ ገብተው „ሥልጣን „ ላይ ለመውጣት እርስ

እምባገነኖች

-ይህ

ነው

አንዱ

የአፍሪካ

ሌላው

~ 10 ~

በእራሳቸው ሳይቀር መዋጋቱን ተያይዘውታል። ገዢውን መደብ አምባገነኑን

በእራሳቸው ሳይቀር መዋጋቱን ተያይዘውታል። ገዢውን መደብ አምባገነኑን እነሱ ደፍረው በማስፈራራታቸው ብቻ ትናንሾቹን – የሚመጣባቸውን ሳያዩ- „በርቱ“ የሚሉ ተበራክተዋል። ጥቂቶቹ ትናንሽ አምባገነኖች መጪውን ዕድሉን ለመጠቀም በመሰባሰብና በመደራጀት ላይ ይገኛሉ። „…እኔ እሻላለሁ። እኔ አውቅልኻለሁ። ይህን ልበስ። ይህን ቅመስ። ያን ተው። መገንጠል ከፈለግ እኔን ተከተል። ….ጊዜው ዘንድሮ የእኛ ነው !“ ባዩ ብዙ ነው።

የገዢውን ቡድንም ሆነ የተቃዋሚውን ሠፈር አንድ በአፍሪካ አህጉር የሚያደርግ ነገር ቢኖር ሁለቱም በአምባገነን አስሰተሳሰብና ፍልስፍ በርዕዮተ-ዓለሙና በፖለቲካ ጉዞው እነሱ – በርካታ ጥናቶችና ብዙ ተመልካቾች በግልጽ እንደሚሉትና በዓይንም እንደሚታየው- „የተጠመቁ“ ናቸው።

ለምንድነው አምባገነኖች ከሌላው ዓለም ተራ በተራ የተባረሩት?

ከሌላው ዓለም ተራ በተራ የተባረሩት? በአፍሪካ በየጊዜው በተለያዩ ስሞች

በአፍሪካ

በየጊዜው በተለያዩ ስሞች እነሱ እዚያ የሚፈለፈሉት?

ለምንድነው አንዱ አምባገነን ሲወድቅ በሌላው ከእሱ በአልተሻለው አምባገነን የሚተካው? ለምንድነው ዓለምና ሰው ሁሉ በአፍሪካ ይህንን ሁኔታ ዝም ብሎ የሚያየው?

ብዙ ቦታ በዓለም ዙሪያ በተለያዩ ቀለምና ስም የተደራጁ አምባገነኖችና ተከታዮቻቸው ተራ በተራ እነሱ -በርካታ ጽሑፎች እንደሚመሰክሩት- መድረኩን ለቀው ተሰናብተዋል። በአፍሪካ ግን መሽገው ተቀምጠዋል።

ቁጥራቸው ሳይቀንስ በእያንዳንዱ አገር ቢያንስ ከሃያና ሰላሳ ድርጅቶች በላይ ሁነው ሜዳውን ይዘውታል።

እንዴትስ

ነው

የተባረሩት?…ለምንድነው

~ 11 ~

በሱዳን ከጥቂት አመታት በፊት አንድና ሁለት ነበሩ። በናይጄሪያ እንደዚሁ

በሱዳን ከጥቂት አመታት በፊት አንድና ሁለት ነበሩ። በናይጄሪያ እንደዚሁ ትንሽ ነበሩ። በኮንጎ በጣት ይቆጠራሉ። በኢትዮጵያ ከጥቂት አመታት አንድና ሁለት ሦስት እና አራት ነበሩ ።

አሁን ግን ከፖርት ሱዳን እስከ ደቡብ ሱዳን ከኮንጎ እሰከ ምዛምቢክ፣ በሱማሌና በሊቢያ… ከኤርትራ እሰከ ኡጋዴን ከአፋር እሰከ ደንቢዶሎ ከወልቃይት እሰከ ሞያሌ የአምባገነን አስሰተሳብ ተከታይ ድርጅቶች ቁጥር በምዕራብ አፍሪካና በመካከለኛው በምሥራቅና በደቡቡ- አፍሪካ

በምሥራቅና በደቡቡ - አፍሪካ ጨምሮ ተበራክቶአል። „ኤርትራውና

ጨምሮ ተበራክቶአል።

„ኤርትራውና ትግሬው“ አንዱ እነደጻፈው “ አትረብሹኝ ለብቻዬ ለብቻችን እንግዛ “ ይላሉ። እነሱን አይተው „…የኦሮሞና የኦጋዴን ድርጅት መሪዎች ደጋግመው እነደሚሉት እኛም ተገንጠለን እኛም ዕድሉ ደርሶን ብቻ እንግዛ …“ ይላሉ።

እንደሚባለው…አማራው አሁንም ይገባኛል ባይ ነው።…አፋሩ ጉራጌው የደቡቡ ሕዝብ ተወካይ ግለሰቦች ሌላ ልዩ ልዩ ነገሮች ያነሳሉ።… በዚያ ላይ መድረክ አማራጭ ኦብነግ ኢህአዴግ መኢሶን ኢህአፖ ደርግ ግንቦት ሰባት (አዲዩ አለች?)…ደቡብ ሕዝቦች ….የሚባሉ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ በይገባኛል ጥያቄ ተያይዘዋል ።“

„… ሁሉም -ሌላው ከንቱ ነው- ለአገሪቱ ችግር/ ስለ አንተም ጉዳይ ፍቱን መፍትሔ የአለኝ እኔ ብቻ ነኝ „ባይ ሁኖአል። ይህን ማለት ተገቢ ነው? ይህን ማለት ስተት ነው?

ለምንድነው ተቃዋሚውም ቡድን ሆነ ገዢውም መደብ „እኔ ብቻዬን አውቃለሁ“ በሚለው በቶታሊቴሪያን ፍልስፍና እና አስስተሳሰብ የተማረኩት?

~ 12 ~

ለምንድነው ሕዝቡና የአገሪቱ ዜጎቹ በአምባገነን አስተሳሰብ አራማጆች በቀላሉ በአለፉት አርባና ሃምሣ አመታት በትንሹ ለመቁጠር የተታለሉት?… ወይም የተማረኩት? …አሁንም በዚያው አስተሳሰብ ላይ እነደ ቆረበ ሰው የረጉት? እሱን ስንል የሃይማኖት አክራሪዎች ብቅ ብለዋል። እሱን ስንል መለዮ ለባሽ ወታደሮች ስለ አስተዳደር እናውቃለን ብለው እንደገና አንሰራርተዋል።

ለመሆኑ ዲክታተሮች እንደሚነግርላቸው እነሱ“ ጂኒየስ“ ማንም የማይደርስባቸው ብሩህ አእምሮ ያላቸው ሰዎች ናቸው? …ወይስ

አእምሮ ያላቸው ሰዎች ናቸው? …ወይስ „ሳይኮፓት“ …„ዕብዶች ናቸው“?

„ሳይኮፓት“ …„ዕብዶች ናቸው“?

ወይስ „…ልዩ ፍጡር? እግዚአብሔር ለቅጣት የላካቸው? ወይስ አንዳች ዓይነት ከጨለማ ቤት የተላከብን „ዲያቢሎስ የሚጋልባቸው“? ይህ ከአልሆነ…የቶታሊቴሪያን አስተሳሰብ አራማጆች ታዲያ ምንድንናቸው?

እነዚህን ጥያቄዎች አንስተን (በአንድ

አንጨርሰውም) ቀስ እያልን እያዘገምን ችግሩን ከበን ጥያቄውን

ቀን ፈጽሞ አብራርተን

ጥያቄውን ቀን ፈጽሞ አብራርተን አገላብጠን ለመመለስ፣ ለመፍታት

አገላብጠን ለመመለስ፣ ለመፍታት እንሞክራለን !

የፖለቲካ ቲዎሪ/ቲዎሪዎች-ብዙ ይመስላሉ እንጂ ወዳጄ- በጣም ጥቂቶችና በጣት የሚቆጠሩ ናቸው። ወደ ሥልጣን የሚወስዱ መንገዶችም ወደዚሁ ወደ ሥልጣን የሚያደርሱና እዚያው ሥልጣን የሚያቆዩ ብልሃትና ዘዴዎች -ቴክኒኮቹም ውስን ናቸው። እነሱም በዚህች ዓለም አንድ ሁለት ተብለው ይቆጠራሉ።

~ 13 ~

ንጉሥ ቦካሳ አገሪቱን በዚያውም ሕዝቡን ለመቆጣጠር የተጠቀመው ዘዴና

ንጉሥ ቦካሳ አገሪቱን በዚያውም ሕዝቡን ለመቆጣጠር የተጠቀመው ዘዴና ብልሃት ከኢዲ አሚን ዳዳ አይለይም። የሁለቱ ብልሃት ከመንግሥቱ ኃይለማሪያም፣ የመንግሥቱ ኃይለ ማሪያም ጉዞ ከኢሳያስ አፈወርቂ፣ የእሱ አካሄድ ወይም የእነሱ ሁሉ ጉዞ… ከካስተሮና ከማኦ ከስታሊንና ከኪም ይህ ሁሉ ደግሞ ከሆቺሚንና ከፖልፖት

ይህ ሁሉ ደግሞ ከሆቺሚንና ከፖልፖት ብልሃት እምብዛም አይርቅም።

ብልሃት እምብዛም አይርቅም።

የምናወራው -እንደማመጥ ከአልን- ስለ አገዛዝ ብልሃትና ወደ ሥልጣን ወደሚያወጣው ቴክኒክ ነው! ሒትለር ደመኛ ጠላቱን እስታሊንን በሥራውና በቆራጥነቱ -ተጽፎ እነደሚነበበው- እጅግ አድርጎ ያደንቀው

- እጅግ አድርጎ ያደንቀው ነበር። ያመልኩ ነበር ። ሁሉም

ነበር። ያመልኩ ነበር ።

ሁሉም (ቁጥራቸው ብዙ ነው በስም ይለያያሉ እንጂ) ከታች ተነስው ነው እዚያ ማንም ተንጠራርቶ ደርሶባቸው ሊያወርዳቸው የማይቻልበት ዙፋን ላይ – አለ የሕዝብ ምርጫ ፍላጎትና ልመና ሊቀመጡ የቻሉት

ሞሰሊኒ

ሌኒንን።

ሁለቱ

ደግሞ

ማኪያቬሊን

የተወሰነ ብልሃት በመጠቀማቸው ነው።

ሌኒንን። ሁለቱ ደግሞ ማኪያቬሊን የተወሰነ ብልሃት በመጠቀማቸው ነው። ~ 14 ~

~ 14 ~

ምን ዓይነት ብልሃት ነው እነሱ የተጠቀሙት? ምን ዓይነት አመቺ ሁኔታ አግኝተው ነው? እነሱ እዚያ ላይ መጥቀው ወጥተው የቤተ-መንግሥቱ አልጋ ላይ በቀላሉ ለመውጣት የቻሉት?

እንዴትስ ለረጅም አመታት አረፍ ብለው ለመግዛት የቻሉት? በምንስ ብልሃት ነው ተቀናቃኞቻቸውን እንዳይደርሱባቸው ሥልጣናቸውንም እንዳይጋሩአቸው ከሩቁ እዚያው በአሉበት ማቀው እንዲቀሩ ያደረጉት? የሥልጣንና የኃይል ዘዴው ምንድነው?

የኃይል ዘዴው ምንድነው? ፭ ሳዳም ሁሴንና ጋዳፊ ገማል

ሳዳም ሁሴንና ጋዳፊ ገማል አብደልናስርና ቾምቤ አዚዚና አያቶላ ሆሜኒ ታሊባናና አልባሽር ሁፌት ቧኜና ሴክቱሬ …እነዚህ ሁሉ ከታች ተነስተው -ዘውዱን እንደ ቦካሣ መድፋት ብቻ ነው አንዳዶቹ የቀራቸው- እላይ ማንም እነደሚያውቀውና እንደተመለከተው የተንጠለጠሉ ሰዎች ናቸው።

በምን ብልሃት ነው? በምን ተዓምር ነው? ተራ ሰዎች ዓላማቸው በቀላሉ ለእነሱ ሊሰምር የቻለው?

በቀላሉ ለእነሱ ሊሰምር የቻለው? ከእነዚህ ሁሉ የፈረንሣዩን ናፖሊን

ከእነዚህ ሁሉ የፈረንሣዩን ናፖሊን ፖናፓርትን አረአያው አድርጎ ሥልጣን ወጥቶ በሃያኛው ክፍለ ዘመን እንደ እሱ እንደ ናፖሊዮን ዘውዱን አናቱ ላይ ደፍቶ ወደሚስቱ አክሊሉን ሊጭን ዞር ያለው ሰው እላይ እንደተባለው„…ንጉሠ ነገሥት „ ቦካሳ ብቻ ነው።

ቦካሣ ማንም ይህ ሰው ተንጠራርቶ አንድ ቀን እዚያ መሰላል ላይ ይወጣል ብሎ ያልገመተው ሰው ነው። ማንም ይህን ሰው ለንጉሠ- ነገሥትነት አላጨውም።

~ 15 ~

ግን ደግሞ ከእሱ በምንም ዓይነት ያላነሰ ፈላጭ ቆራጭ ሥልጣን የነበራቸው ሰዎችን የ20ኛው ክፍለ-ዘመን – እንደ ሌኒንና ሞሰሊን እንደሒትለርና እንደ ስታሊን እንደ ካስትሮና እነደ ሆኔከር እንደ ቻው ቼስኮ እንደ …ያሉትን ሰዎች ይህቺ ዓለም አስተናግዳለች።

ሰዎች ይህቺ ዓለም አስተናግዳለች። እነሱስ እንዴት ሥልጣን ላይ

እነሱስ እንዴት ሥልጣን ላይ አምልጠው ወጡ? እንዴትስ ሥልጣናቸው ላይ ከረሙ?

ይህን እና ይህን የመሰሉ ጉዳዮችና ጥያቄዎች አንስተን ከዚህ በፊት በጀመርነው የኢንላይትሜንት -የብርሃን ጉዞ ጥረታችን መልስ ለመስጠት ሙከራ አናደርገናል።

እንግዲህ በጀመርነው ሓሳብ እንቀጥልበት። ሁሉም የድርጅት መሪ በአፍሪካ እንደ „ቦካሣ ነው“ ብንል ዘለፋም ወቀሳም ወይም ደግሞ ሙገሳም አይደለም። ትልቁም ትንሹም „የቶታሊቴሪያን አጋንንት“ በአፍሪካ ሆነ በሌላ አካባቢ እንደ „ንጉሥ ቦካሣ“ – በሕዝብ ሳይመረጥ- ቢያንስ አንድ ቀን ብትሆንም ቤተ-መንግሥት ገብቶ በሰው ላይ ቀልዶ በሕይወቱ ለትንሽ ደቂቃና ለጥቂት ቀናት – አመታቱንማ የሚመኘው ብዙ ነው- ተደስቶ መሞት ይፈልጋል። ለምን?

ይህ ፍላጎት

ይህ ምኞት

ከየት

መጣ

? የሰው

ልጅስ ለምን ይህን

ያልማል?

ሌላ ጥያቄ።

ለመሆኑ በአፍሪካ ይህን ማለም ሲቻልና ይህን ማድረግ „ሲፈቀድ“ ሌላውስ ጋ ለምን ወይም በምን ምክንያት እንደዚህ ዓይነቱ ቅዠት „ይከለከላል“?

…ለመሆኑ በምን ዘዴ አድርገው እነሱ ተቆጣጥረው ያዙት?

~ 16 ~

ተወደደም ተጠላም፣ አውቀንም አላወቅንም ምናልባት በቃላት ጨዋታ መታለልም አለ- ብዙ ሰው ብዙ „አምባገነን ቦካሣዎችን“ ዝም ብሎ ተቀብሎ በትከሻው ላይ ጭኖ እነሱን „በደስታም ወይም በሐዘንም“ በደንብ „የማስተናገድ በሽታም“ በዓለም ላይ -አከባቢአችንን ማየት ይበቃል-ይታያል። ለምን እነደዚህ ሆነ?

…ይህ ደግሞ ምክንያት አለው።

የሰው ልጆች በአንድ በኩል በባሕሪአቸው ደካማ ናቸው። በሌላው ጎኑ የሰው ልጆች መንገዱን የሚያሳያቸው መሪ/መሪዎች ይፈልጋል። አንደኛው ምክንያት„ደህና ቀን ይመጣል“ ብሎ በተስፋም ያንቀላፋል። „ሆዳም!“ – ብዙዎቹ እንደሚሉት- ብቻ ሳይሆን „…ምን አገባኝ ልጆቼን ላሳድግበት፣ ለምን የእሳት ራት ልሁን …“ብሎም ሊያስብ ይችላል። አልፎ ተርፎም „…ሁሉም አንድ ናቸው።… ልዩነት በመካከላቸው የለም። … ያም አምባገነን ይህም አምባገነን… „ ብሎም እርሙን አውጥቶ ተስፋ ቆርጦም ይሆናል። (አንድ ሰው ደግሞ አይቶ አውጥቶ አውርዶ ይህን ከአለ አይፈረድበትም!)

የሰው ልጅ/ልጆች -ጥቁሩም ነጩም- ከገባበት ችግር የሚያወጣውን „አለቃ“ ፈልጎ ከአገኘ ይከተለዋል።

አንዳንዴ ሌላው ብድግ ብሎ የተከተለውን መሪ „…ይኼ ሁሉ ሰው አይሳሳትም „ ስለዚህ “እኔም ብቻዬን ከምቆም” ብሎ እራሱን አታሎ እሱም ተነስቶ አብሮ ይጮሃል።

ብቻዬን ከምቆም” ብሎ እራሱን አታሎ እሱም ተነስቶ አብሮ ይጮሃል። ~ 17 ~

~ 17 ~

ይህን የተገነዘበ አንድ እሳት የላሰ መሪ ደግሞ ጸሐፊዎች በትክክል እንደአሰፈሩት „…እንደ ከብት አንድ ቀን የሚነዳውን አገልጋይ ተከታታይ ወይም የሚሞትለትን ከመሞት የማይመለሰውን ሎሌ“ ቀስ በቀስ „ሳይታወቅበት በብልሃት ኮትኩቶ አዘጋጅቶ አስታጥቆ ወደ ጦር ሜዳ ይልከዋል።“ እንዴት? በምን ዘዴ?

የሰው ልጆችን ከገቡበት ችግሮች ጎትቶ የሚያወጣ „መሪ ነብይ“ አንድ ሳይሆን እነሱ “ብዙ” ናቸው። እንደሚታወቀው የተለያዩ መሪዎች እኔ እሻላለሁ እኔ እብልጣለሁ ብለው ይነሳሉ። እነሱም የሰውን ልጆች አእምሮ „አስክረው ለመያዝ“ ታሪክ ላይ ብዙ አካባቢዎች እንደምናየው “የሰበካ ፉክክር” ውስጥ ገብተው ይገጥማሉ።

አንዱ ቡድን(- ኢትዮጵያን -ጥሩ ምሳሌ ናት -) ተነስቶ አንድ ነገር ይላል። ሌለው ቡድን ለየት ያለ ብልሃት ይቀይሳል። ሦስተኛው ሁለቱን ገፍትሮ የራሱን አዲስ አስተሳሰብ ለማስፋፋት ይሞክራል። አራተኛው ዱላ ወይም ጠበንጃ ይዞ ሁሉንም ጭጭ ለማድረግ ይነሳል። አምስተኛው ላስታርቅ ብሎ ቤንዚን አርከፍክፎ እሳቱን በሁሉም

ቤንዚን አርከፍክፎ እሳቱን በሁሉም አቅጣጫ ይለኩሳል። ስድስተኛው

አቅጣጫ ይለኩሳል።

ስድስተኛው ከጎረቤት ጠላት ከባዕድ ጋር ገጥሞ ሁሉንም ለመውጋት መላ ይመታል። ሰባተኛው ኅብረትና አንድነት ብሎ ከፋፍሎ ተራ በተራ ተቀናቃኞቹን መቶ ኮርቻው ላይ ጉብ የሚልበትን መንገድ ያመቻቻል። ስምነተኛው ….ረጋ ብሎ የሚያስብ ሰው ደግሞ ለመሆኑ ትክክለኛው ከእናንተ ሁሉ ማን ነው? ብሎ ይጠይቃል።

ለመሆኑ ከእነሱ ሁሉ ትክለኛው ማን ነው? ሁሉም? …ወይስ አንዱ? ወይስ የተወሰኑት? ወይስ ሌላ ገና ያልተወለደው?

~ 18 ~

….ብቻ! እዚህ ላይ አንድ ሓቅ ቢጠቀስ በሰው ልጆች ላይ በተለያዩ አካባቢዎች – ከድንጋይ ዳቦ ዘመን – ከኦሪት ዘ-ፍጥረት እስከ አሁን ጊዜ ድረስ እስከ 21ኛ ክፍለ-ዘመን በአታላይ የፖለቲካ መሪዎች ብልጣ ብልጥነት ብዙ እጅግ ብዙ ተቀልዶበታል።

መቀለድ ብቻ ሳይሆን በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የዓለም ሕዝቦች- አንደኛና ሁለተኛ ዓለም ጦርነት ተመልከት፣ በመደብ ትግል ስም የተለኮሱትን ጥፋቶች መለስ ብለህ እይ፣ በማራኪ ስም የተካሄዱትን አብዮቶች ቁጠር፣…የብሔር ትግል የሚባለውን የሕዝቦች ፍጅት ጨምረህ አብረህ አስተውል- በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች ንጹህ ሰዎች

ሁሉ ምክንያቶች ንጹህ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። የፖለቲካ

ሕይወታቸውን አጥተዋል።

የፖለቲካ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ አንዳንድ የሃይማኖት „አባቶችም“ እንደሚባለው „አታላይ ነቢዮችም“ (ስለ የተለያዩ የዓለም ሃይማኖቶች

(ስለ የተለያዩ የዓለም ሃይማኖቶች ነው የምናወራው) በሰው ልጆች

ነው የምናወራው) በሰው ልጆች አእምሮና ልብ ላይ ቀልደው ወደሚፈልጉበት መንደርና ሠፈር -ደም እየፈሰሰ- ሰውን እየነዱት አስገብተዋል።

እንግዲህ ለመሆኑ የትኛው የፖለቲካ ቲዎሪ ነው ከሁሉም ዕውነተኛው? የትኛው እምነት ነው ከአሉት እምነቶቹ ሁሉ ትክክለኛ ነው?…የዱሮው ሃይማኖት ወይስ አዲሱ? የዱሮ ፖለቲካ ወይስ አዲሱ? አምባገነኖች ከአውሮፓና አሜሪካ ተባረዋል።… እንዴት ተባረሩ? አንዴትስ አምባገነኖች በአፍሪካ ብቻ መሽገው ተረፉ?

የአምባገነኖች አካሄድና ጉዞ፣ የፖለቲካ አመለካከታቸው፣ ዓለምንና ሰውን የሚያዩበት ዓይናቸው እንዴት ነው?

አነሱን

ለመሆኑ

“የሚያስደስታቸው ነገር”?

አምባገነኖች

ምን

ይፈልጋሉ?

ምንድነው

~ 19 ~

ለምንድነው አንድ ሰው ሥልጣን ሲወጣ ልዩ ፍጡር ሁኖ ታይቶበትና ተሰምቶበት የማይታወቅ ባህሪና ገጽታ የሚያሳየው?

ለጊዜው „የብሔር/ብሔረሰብን ጥያቄ የሚባለውን ነገር…የኤርትራን ነጻነት ጉዳይ „ ወደ ጎን እናድርገው።

የኦሮሞን መገንጠል፣ የኦጋዴንን ጥያቄ የፖለቲካ ደርጅቶችን አላማና ግብ – እነሱንም ለጊዜው- ይህን ጉዳይ እናሳድረው።

የዳቦና የሥራ የጡረታና የጤና የሕክምና እና የትምህርት በብዙ ሚሊዮን የሚቄጠሩ ሰዎችን የሚያሳስበውን የዋጋ መወደድ የማደሪያ ቦታ ማጣት …አነዚህን ሁሉ ለጊዜው ለነገ እናስተላልፈው።

በእሱ ፋንታ ነገሮችን በቅጡ ለመረዳት „የሥልጣን ሰዎችን አስተሳሰብ ከእነሱ ጋር ወደ ሥልጣን እርካን ለመውጣት“ የሚፈልጉትን ሰዎች ባህሪ ምን እንደሆነ መለስ ብለን እንመልከት።

ሮበርት ግሪን፥ “ስልጣንና አርባ ስምንት መላዎቹ” Robert Greene „Power – the 48 laws of Power“

Robert Greene „Power – the 48 laws of Power“ በሚለው አስደናቂ ጽሑፉ በአለፉት

በሚለው አስደናቂ ጽሑፉ በአለፉት ሦስት ሺህ አመታት ጊዜ ውስጥ ወደ ሥልጣን የሚወስደውን ለአንድ ተራ ሰው ለማወቅ ሆነ ለመረዳት ድብቅና አስቸጋሪ የሆነውን የብልሃተኞች መንገድ ቁጭ ብሎ አጥንቶ እሱ በአወጣልን መጽሓፉ ላይ የሚከተሉትን አብይ የሆኑ ፍሬ ነገሮች - እነሱ ማን መሆናቸውን እንድንረዳ – እንደሚከተለው አስቀምጦልናል። „…በአንደኛ ደረጃ ዓላማህን ለመምታት ከፈለግህ አለቃህን ከመሬት ተነስተህ እሱን አትፈታተነው። አትፎካከረው ።

~ 20 ~

ወዳጆችህን የትግል ጓደኞችህም ቢሆኑ እነሱን አትመናቸው። ጠላቶችን እንዴት እንደምትጠቀምባቸው ግን ሁል ጊዜ አሰላስለህ መላ- ምታ። ከመምታትም ችላ አትበል።እቅድህንና የመጨረሻ ዓላማህን ለማንም ሳትናገር በልብህ ለራስ ብቻ ያዘው። በምንም ዓይነት የጠበቀ ግንኙነት ከማንም ሰው ጋር አታድርግ። ያገኘኸውን ሰው ግን አጥንተህ አስጠግተህ እሱን ያንተ ታማኝ ሎሌ ከማድርግ አትስነፍ።

ሌሎቹ ለአንተ እንዲሰሩልህና በአንተ ሥር እንዲሰሩ ይህን ከማድረግ አትስነፍ። እነሱን ከማድነቅና ከማሞገስ ችሮታም ከመስጠት ችላ አትበል።

ዕድለ ቢስ የሆኑ ሰዎችና ቀና ነገር የማያስቡ ሰዎችን ከአንተ አጠገብ አታድርስ ። አርቃቸው።

ሊያታልሉህና አታለው አንተን ለመያዝ የሚፈልግቱን ሞኞችና የዋሆች አንተው እራስህ ሞኝ ሆነህ ሞኝ መስለህ ቀርበኻቸው ቀስ ብለህ አረሳስተህ ማጅራታቸውን ለቀም አድርገህ ተቆጣጠራቸው።

ሁል ጊዜ ወዳጅ መስለህ ሰውን ሁሉ አስተናግድ ። ግን እነደ ሰላይ ጆሮህን ሰጥተህ የሚናገረውን በደንብ አዳምጣው።

ጠላትህንና ተቀናቃኝህን እጅህ አስገብተህ አለአንዳች ርህራሄ እሱን ደምስሰው። ፍጀው።

ሰዎች በአንድ ነገር እንዲያምኑ ሁልጊዜ ፈትፍተህ ቀባብተህ አንዳች ነገር አቅርብላቸው። በዚያውም ልባቸውን በልተህ እምነታቸውን በአንተ ላይ ገንብተው እንዲከተሉህ አድርጋቸው።

ሌሎቹን ደግሞ አንተው ፐውዘህ ደበላልቀህ የምትሰጣቸውን ካርታ ብቻ ይዘው -ከቁጥጥርህ ሳይወጡ እንዲጫወቱ እነሱን አድርጋቸው።

~ 21 ~

ሰዎች የተደበቀ ሕልምና ምኞት አላቸው። ይህን አውቀህ ገና ለገና ይመጣል ብለው የሚመኙትና የሚቋምጡትን ሐሳቦች ሁሌ እያነሳህ አጓጓቸው።“

በመጨረሻም- አርባ ስምነቱን የሮበርት ግሪንን ዝርዝር „ተንኮሎችን“ እናሳጥረው- „ …እረኛውን ጠብቀህ ሳያስበው አናቱን ብለህ ቀጥቅጠህ ግደለው። ያኔ በጎቹ ደንግጠው በያለበት ፈርጥጠውና ተበትነው ሁዋላ የሚገቡበት አጥተው በደጅህ ያድራሉ።“

አጥተው በደጅህ ያድራሉ።“ ብሎ የሦስት ሺህ ዓመቱን ብልሃት

ብሎ የሦስት ሺህ ዓመቱን ብልሃት በዚህ ዓረፍተ ነገር ይዘጋል።

አስተዋይ አንባቢ እንደሚረዳው እንደዚህ ዓይነቱ የአምባገነኖች ተንኮል በአውሮፓና በአሜሪካ አሁን በያዝነው በ21ኛው ክፍለ ዘመን - ተዘዋውረን ስንመለከተው አንድም ቦታ -ቢያንስ በአገራቸው- ተከታይ የለውም።

በአፍሪካ ግን እንደምናውቀውና ተጨባጩ ሁኔታ እንደሚያሳየው ለአንድ አምባገነን ለዚያም አስተሳሰብ ልቡን ለሸጠ ሰው ይህ ብልሃት አሁንም ቢሆን እነደ አለፉት ሺህ አመታት ትልቅ ቦታ አለው።

በአሜሪካና በአውሮፓ አንድ አምባገነን መሪ እላይ የተጠቀሱትን መመሪዎች መሠረት አድርጎ ሥልጣን ላይ ለመውጣት ወይም ሥልጣን ላይ ለመቆየት ይህን ያህል መድከም አያስፈልገውም አልን እንጂ አንድ የፋብሪካ ሥራ አስከያጅ በጀርመን ሆነ በፈረንሣይ ወይም የሠራተኛ ማህበር ተጠሪ በስፔን ወይም ለተወሰነ አመት የተመረጠ የድርጅት መሪ

~ 22 ~

ወይም አንድ የሃይማኖት አባት፣ የጦር አዛዥ…አስተማሪ ወይም ሐኪም…አጠገቡ ያሉትን (ከቦታ ቦታ ይለያያል) ተንኮሉን እያውጠነጠነ አንዱን አቅርቦ ሌላውን አርቆ እነሱን እርስ በራሳቸው ሥልጣኑን መከታ አድርጎ ተብትቦ መከራ ፍዳቸውን አንድ በአንድ ተራ በተራ ሊያሳያቸው ይችላል።

እሱ እራሱ ደግሞ በተራው በሌላው ከበላዩ በአለው አንዳች ኃይል መዳፍ ውስጥ ወድቆ ጥዋት ማታም ተሰቃይቶ ሊያለቅስም ይችላል።

ግን እዚህ ሕግ በሚከበርበት አገር ሕግም ያለበትና ያ ሕግ በትክክል መተርጎሙ በሚመረመርበት ቦታዎችና አካባቢ አንድ ሰው ዕድሜ ልኩን እያለቀሰ እያማረረ ሕይወቱን አይገፋም። ጠበቃ ይዞ መከራከር ይችላል።…ይከራከራል። ታሪኩን ለነጻ-ጋዜጠኞች አቅርቦ ተራው ሕዝብ እንዲፋረደው ያደርጋል። ካሣም እስከ መጠየቅ ሰውዬውንም እሰከ ማስቀጣት ይሄዳል።

ግን ለእኛ ጠቅላላውን ሁኔታ ለመገንዘብ „ሥልጣን ምንድነው?“ ብለን እንጀምራለን።

„ ሥልጣን ከየት ይመጣል? ሥልጣን የአንድን ሰው ባህሪና ተፈጥሮ እንዴት ይቀይራል ። ለምንስ ይቀይራል?

ለምንድነው አንዳንድ ሰዎች ሥልጣንን የሚወዱት? ለምንድነው እነሱ ከሥልጣንም አንወርድም ብለው ተኩስ የሚከፍቱት? ለምንድነው ሌሎች ሰዎች ሥልጣንን እንደ ጦር ፈርተው የሚሸሹት?…አምባገነኖች ከሥልጣን አንወርድም አንለቅም ብለው ሲሟገቱ፣ ለምንድነው ሌሎቹ ከሥልጣን በገዛ ፈቃዳቸው ለመውረድ ወይም ለማስረከብ ዝግጁ የሚሆኑት?“

„ሥልጣን እንደ ሞቀ ወሃ እንደ ወርቅ ሓብት ትጥማለች“ የሚባለው አነጋገር ዕውነት ነው ወይ?… የሥልጣን ሰዎች በሙሉ አታላይ ናቸው የሚባለውስ አነጋገር ምን ያህል ዕውነት ነው?

~ 23 ~

ሥልጣን እንደ „ሴሰኛ“ የሚያሳብድ “በሽታ” ነው ይባላል። ይህስ ዕውነት አለው ?“ እነዚህንና እነዚህን የመሰሉ ጥያቄዎች አንስተን „ስለ ሥልጣንና የሥልጣን ተሸካሚዎችን ሰዎች ባህሪና ተፈጥሮ“ እንመለከታለን። የሥልጣን ሰዎች ምንድንናቸው? አነሱን ከእኔና ከአንተ ምን ይለያቸዋል?

„በእግዚአብሔር የተመረጠ“ መሪ አለ። ይህስ እውነት ነው? በጠበንጃ ዕድሉን ሞክሮ እዚያ ላይ የተሰቀለ ሰው አለ። ይህ ስለሆነ ዕድሜ ልኩን ሥልጣን ላይ መቀመጥ አለበት?

ለአንተ የሚሆንንህን ጥሩ ሠርዓት እኔ አውቅልኻለሁ የሚሉ ቡድኖች አሉ። ይህን ሲሉ ዕውነታቸውን- ከልባቸው ነው? ለመሆኑ ለእኔ የሚስማማ ምን ዓይነት ሥርዓት ያመጡልኛል?… ምኑን ነው? የትኛው ነው? ለእኔና ለአንተ የሚሆን ጥሩ ሥርዓት? የተለያዩ መፍትሔ ይዘው ከቀረቡት ድርጅትና ሰዎች መካከል የትኛው ነው ትክክለኛው? የቱን አንማንን? የቱን እንከተል?

ሊንዲ እንግላንድ የምትባለው ያቺ የኢረቅን እሥረኞች በአቡግሬብ እሥር ቤት እንደ ውሻ ሰንሰለት አንገታቸው ላይ አሥራ በአራት

አንገታቸው ላይ አሥራ በአራት እግራቸው ራቁታቸውን ሳታስኬዳቸው

እግራቸው ራቁታቸውን ሳታስኬዳቸው በፊት አንድ የአገሩዋ ሰው የአሜሪካው የሳንፎርድ ዪኒቨርሲቲ አስተማሪና ተመራማሪ „…እንደዚህ ዓይነት ጭካኔ ከየት ይመጣል ? ሥልጣንና ጭቆና የተሞላበት ፈላጭ ቆራጭነት መነሻ ምክንያቱ ምንድነው? ምን ይሆን ከጀርባው ያለው ነገር? „ ብሎ ለጥያቄው መልስ ለመስጠትና ለመመራመር አንድ መንገድ ተከትሎ ነበር። እሱ በጥቂት ቀናት ምርመራው የደረሰበት ውጤት ያስደነግጣል።

ፕሮፌሰር ፊልፕ ሲምባርዶ አውጥቶ አውርዶ በሚያስተምርበት ዩኒቨርስቲ ቀደም ሲል በ1971 ዓ.ም. (እአአ)ለምርመራው ፈቃደኛ የሆኑ ወጣቶችን እፈልጋለሁ ብሎ አንድ ማስታወቂያ ያወጣል።

~ 24 ~

ያን„ ከሃያ አመት በላይ የሚሆኑ ወንዶች የሳይኮሎጂ ትምህርት ተማሪዎችን

ያን„ ከሃያ አመት በላይ የሚሆኑ ወንዶች የሳይኮሎጂ ትምህርት ተማሪዎችን እፈለጋለሁ“ የሚለውን ማስታወቂያ ተመልክተው ከሰባ በላይ የሚሆኑ ወጣት ጎረምሶች መልስ ይልኩለታል።

ምሁሩም ለእሱ ምርመራ የሚፈልገውን ጥሩ ክራይቴሪያ – አስፈላጊ የሆኑ ዝግጅቶችን ያሟላሉ የሚላቸውን 24 ልጆች መርጦ ሌሎቹን አሰናብቶ (ምናልባት መድሓኒት በየጊዜው የሚወስዱትን አልፈለግም ብሎ ይሆናል) ወደ ሥራ ይራመዳል።

በ1971 እ.አ.አ ዓ.ም በወጣው ጥናቱ ላይ እንደተነበበው ሥራውን በሁለት ቡድኖች ከፍሎ ይጀምራል።

በመጀመሪያ ተማሪዎቹን ዝም ብሎ ለሁለት ቡድን እጁ እንደአመጣለት ሰንጥቆ ከፊሉን ቡድን አሥራ ሁለቱን በአንድ በኩል ሌላውን አሥራ ሁለቱን በሌላ ወገን አቁሞ ሳንቲም ወደ ላይ በመወርወር „ዘውድ“ ያሉትን „የወህኒ ቤት“ ዘበኛ -ፖሊስ ያደርጋቸዋል።

„ጎፈር“ ያሉትን ደግሞ„እሥረኛ“ አድረጎ የተመደበላቸውን „ጨዋታ“ እንዲጫወቱ ሜዳውን አዘጋጅቶ ወደ ዩኒቨርስቲው ምድር ቤት ወደ እሥር ቤቱ እነሱን አሰናብቶ ለሚቀጥሉት 14 ቀናት ፖሊሶቹን በተለይ „በእስር ቤቱ ውስጥ ጸጥታ እንዳይደፈርስ ረብሻ እንዳይነሳ የጠበቀ ቁጥጥር እንዲያደርጉ „ ትዕዛዝ ሰጥቶ ሁለቱንም ቡድን ይልካቸዋል።

ሁሉም ነገር ዋዛና ፈዛዛ የልጆች ጨዋታ እንዳይሆንና ዝብርቅርቁ ወጥቶ ድካሙ ከንቱ እንዳይሆን „…የእሥረኞቹን ቡድን“ የፖሊስ ዩኒፎርም በለበሱ ሰዎች አስይዞ ጸጉራቸውን አስላጭቶ ልብሳቸውን እሰከ የውስጥ ሱሪ ድረስ አስወልቆ ስስ የእሥረኛ ቀሚስ አልብሶ የራሳቸውን ቅል በስቶኪንግ ሹራብ ሸፍኖ በብረት በተሰራው ቀፎ ውስጥ ማንም እሥረኛ

~ 25 ~

መብቱን ተገፎ እንደሚወረወረው እነሱን እዚያ የዩኒቨርስቲ ምድር ቤቱ ውስጥ ይወረውራቸዋል።

ለፖሊሶቹም ዱላና ጥቁር መነጽር ዩኒፎርምም አልብሶ እሥረኞቹን እንደ ገና „በደንብ እንዲቆጣጠሩ „ትዕዛዝ ስጥቶ እሱ ተደብቆ የሚያይበት የምርመራ ጠረጴዛው ክፍል ይመለሳል።

የመጀመሪያው ቀን -እሱ እነደ ጻፈው- በሰላምና በቀልድ በሳቅና በጨወታ ወሬአቸውን -ፖሊሶቹም እሥረኞቹም – እየከኩ ሌሊቱን ያሳልፉታል። የሚቀጥሉት ቀናት ሌላ መልክ ይይዛል።

በሁለተኛው ቀን የእሥረኛ ጠባቂ ፖሊሶቹ ሥራ ከምንፈታ፣…

ዝምታውስ ለምንድነው ? ብለው አንዳንድ የተንኮል ሓሳብ – በአንዳንዶቹ አእምሮ ብቅ ይላል። ይመጣል። ከምሽቱ ስምንት ሰዓት ማለት ከእኩለ ሌሊት በሁዋላ እሥረኞቹን ዓለም ጤና ብለው ከተኙበት ጥሩ እንቅልፋቸው ለመቀስቀስ ፖሊሶቹ ይስማማሉ። የብርድ ልብሳቸውን ገፈው ቀስቅሰው „ተነሱ! …አልጋችሁን በትክክል እንጥፉ!“ እያሉ እየተቆጡ አልነሳም ያሉትን እሥረኞቻቸውን እያዋከቡና እየገፈተሩ ያላገጠውንም መርጠው አውጥተው እንደገና ደግሞ ደጋግሞ አንሶላውን እንዲያስተካክል እያስገደዱ ሌሊቱን እነሱ ዘበኞቹ እየሳቁ

እንቅልፍ

ይህን የጠነሰሱት ፖሊሶቹ ከሌሊት ሥራቸው ተመልሰው አልጋቸው ላይ ቀኑን በሙሉ ተኝተው ያሳልፋሉ።

በዚህ የተሰበሳጩትና ለመተኛት ያልቻሉት እሥረኞች በተነጋተው አድማ መተው ከአልጋቸው አንነሳም፣ ክፍላችውንም አንጠርግም ደረታቸው ላይ የተለጠፈውን (ስም ሳይሆን በቁጥር ነው የሚጠሩት) የእሥረኛ መለያ ቁጥራቸውን ቦጭቀው ወርውረው… የቀን ተረኞቹን ዘበኞች የፖሊሶቹን ትዕዛዝ አንቀበልም ፣አንሰማም ብለው በአመጽ ያስቸግራሉ።

ይህን በማድረጋቸውም የፖሊሶቹ አዛዥ የአድማው መሪ/መሪዎች እነማን እነደሆኑ ፈልጎ አውጥቶ ለመቅጣት ምርመራ ይጠራል።

ነስተዋቸው

ያድራሉ።

~ 26 ~

ቀስቃሽ አድመኞቹን በአንዴ ነጥለው አውጥተው ፖሊሶቹ ብርሃን የማያገኙበት ጨለማ የቁም ሳጥን ውስጥ ወርውረው ያስገቡዋቸዋል ።

በሦስተኛውና በአራተኛው ቀን አንዳንድ እሥረኞች የዘበኞቹን የቀንና የሌሊት የእንቅልፍ መንሳት ተንኮል ቁጣና ቅጣት የሚደርስባቸውን በደል መቋቋም አቅቶአቸው „እሥር ቤቱን ለቀን እንውጣ“ ብለው መጮህ ይጀምራሉ። ይባስ ብለው ጸጥታ አስከባሪዎቹ ፖሊስ ይህን የእሥር ቤት ጸጥታ በኃይል በዱላና በተለያዩ ቅጣቶች ለማስከበርና ለመቆጣጠር ሌላ ያልታሰበ የእሥረኞቹን ቅስምና ሞራል የሚሰብር ከፍተኛ እርምጃ ተመካክረው ይዘው ይቀርባሉ። ክፍሉን በእሳት

ይዘው ይቀርባሉ። ክፍሉን በእሳት ማጥፊያ ጢስ ያፍናሉ። ወሃ

ማጥፊያ ጢስ ያፍናሉ። ወሃ ይረጩአቸዋል።

ሞቃት አየር ወይም ብርድ ይለቁባቸዋል። ይህን ሁሉ ነገር የእሥረኞቹ ጩኸት ተመራማሪው በቪዲዮና በድምጽ መቅጃው ቴፑ እሱ በተከለው ካሜራ በቀደደው ቀዳዳ በፊልሞቹ ቁጭ ብሎ ፖሊሶቹና እሥረኞቹ የሚሰሩትን ሥራ ሁሉ አንድ በአንድ እየመዘገበ ይከታተላል።

አንደኛው እራሱን ስቶ አስተማሪውን ላነጋግር ብሎ ለምኖ ከተመራማሪው ጋር ተገናኝቶ እሱን እንዲያሰናብተው እግሩ ላይ ወድቆ ይለምነዋል። ተመራማሪ አስተማሪውም „…አይዞህ ትንሽ ቀናት ነው፣ ቻለውና ቆይ። አንተን የእኔ ሰላይ ነው ብዬ …እነግራቸዋለሁ።ምንም አትሆንም በርታ…እኔ አለሁልህ!“ ብሎ አታሎት ወደ ምድር ቤቱ ወደ ገራፊዎቹ በገዛ ፈቃዱ እንዲወርድ መልሶ ይሸኘዋል። እየመሸ ሲነጋ ቀኑም እየገፋ ሲሄድ እሱና አንዳንድ ልጆች በየጊዜው እየተቀያየሩ ፍዳቸውን የሚያሳዩትን ፖሊሶች ጭቃኔ መቋቋም የማይችሉበት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ።

ፖሊሶቹም በጀመሩበት የጭቃኔ ሥራ ቀጥለውበት -ጥናቱ እንደሚለው- በየቀኑ አዳዲስ እያውጠነጠኑና እየጨመሩበት የትምህርት ቤት

~ 27 ~

ጓደኞቻቸውን ሕይወት ሲኦል ውስጥ እንደተወረወረች ነፍስ አለአንዳች ርህራሄ ወደማሰቃየቱ ይሸጋገራሉ። አንዱማ ፖሊስ ልብሳቸውን አውልቀው ራቁታቸውን እንዲተኙ ያዛል። ሌላው የሽንት ቤቱን መቀመጫ ሳህን በእጃቸውና በእስረኛ ቀሚሳቸው እንዲጠርጉት ያዛል። ሌላው ከመሬት ተነስቶ እላያቸው ላይ ተቀምጦ ሃያና ሰላሳ „ፑሺ አፕ ጂምናስቲክ“ ከአልጋቸው ወርደው እንዲሰሩ ያዛቸዋል። ዕንቅልፍ ከመንሳት አልፎ ሌላም ቅጣት በየቀኑ እያሰቡ ይቀጡአቸዋል።

በሚቀጥሉት ቀናት እሥር ቤቱ በክቶ በሽንት ባልዲና በሠገራቸው እንዲከረፋ አድረገውታል። አንዳንዶቹ እሥረኞችን እራሳቸውን ስተው አብደው ብቻቸውን -ይኸው ጥናት እንደሚለው- ማውራት ጀምረዋል።

በመካከሉ አንዱ ፖሊስ ማንም ሥራዬን አያይም ብሎ -በፊልም ግን እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ይቀረጻል- እሥረኞቹን (ጓደኞቹን) ጥናቱ ላይ እንደተጻፈው „አብረው ተኝተው የግብረ ሰዶም ሥራ እየተፈራረቁ እንዲሰሩ ያስገድዳቸዋል።”

ኤክስፐርመንቱ የሰው ልጅ ሥልጣንና ኃይል በአንዱ ላይ ከአለው እሰከ

ምን ድረስ ይሄዳል? የሚለው ምርመራ አንዲት የዩኒቨርሲቲው አስተማሪ ሴትዮ እሱዋ በአነሳቸው ጥያቄ – ልኩን እያጣ ስለሄደ- ሌላ ደረጃ ላይ ሳይደርስ እንዲቋረጥ ይደረጋል። እሱዋም „…በምን ዓይነት የሒሊና ጭንቅላትህ ነው? አንተ ይህን ሁሉ ነገር የምታደርገው?… ሞራልህ ለመሆኑ አይወቅስህም ወይ? …እንዴት በተማሪዎች ሕይወት ትቀልዳለህ?“ ብላ ባቀረበችለት ጥያቄ ፣አስተማሪው ደንግጦ ምርመራው

እንዲቋረጥ

ለካስ ሳያውቀው እሱ እራሱ ተመራማሪው አስተማሪ ፕሮፌሰር ሲምባርዶ ነገሩ ጥሞት „…ተባባሪ ፣ …ጨካኝ የወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪና አዛዥ የእሱን ቦታና ሥልጣን…“(አብዛኛው እንደዚህ ነው) ሰተት ብሎ ገብቶ ይዞ ተቀምጦ ልጆቹ ሲሰቃዩ እሱ ምንም ሳይሰማው ያይ ነበር። አንዱ „ፖሊስ“ ሁኖ በምርመራው ላይ የተሳተፈው ተማሪ እንዴት ቀስ እያለ እሱ ሳያውቀው ወደ ጨካኝ ግን ደስ እያለው እሱ ወደ „ሳዲስድትነት“ እንደተቀየረ በማስታወሻ ደብተሩ ላይ አስፍሮ ነገሩን እንደዚህ አደድርጎት አስቀምጦታል። „…እኔ በተፈጥሮዬ ሰላም ወዳድ

~ 28 ~

ተደርጎአል።

ማንም ሰው ለመጉዳት የማልፈልግ ፍጡር በመሆኔ እሥረኞቹን አለአግባብ ለማሰቃየት ምንም ዓይነት ፍላጎት የለኝም ። በደልንና ጭካኔን ፓሲፍሲት ስለሆንኩ የማንንም ጦርነት እኔ አልደግፍም።ሰው ለምን ጨካኝ እንደሚሆን አይገባኝም…“ የሚለውን አቋሙን ሥራውን ከመጀመሩ በፊት ደብተሩ ላይ ይህ ወጣት አሥፍሮ ነበር። ከሦስት ቀን በሁዋላ ደግሞ„…ለመጀመሪያ ጊዜ በሕይወቴ ሥልጣንን መከታ አድርጌ ደስ ያለኝን ነገር እንደ ልቤ ለማድረግና ለማዘዝ ትዕዛዜም በሥራ ላይ እንዲውል ያገኘሁት የበላይነት ምን ያህል የሚያረካና ደስ የሚያሰኝ መሆኑን የተረዳሁት አሁን ነው።…ትዕዛዜን ተቀብለው እሥረኞቹ የተባሉትን ሁሉ ያደርጋሉ።አይገርምም…ደስ ሲል…“ የሚለውን አረፍተ ነገሩን ይኸው ልጅ የማስታወሻ ደብተሩ ላይ ያሰፍራል።

እሱ ብቻ ሳይሆን ሌሎቹም በዚያች በአገኙት የትንሽ ቀናት የሥልጣን ሰዓታቸው ሕልማቸውንና ምኞታቸውን – ፋንታዚያቸውን በደንብ ለቀውት በሥራ ላይ- እላይ እንደ ተጠቀሰው ፖሊሶቹ ሊተረጉሙት ችለዋል። እንዲያውም ፉክክር ውስጥ ገብተው „እኔ እበልጣለሁ እኔ አውቅበታለሁ“ ውስጥ ደርሰዋል። ለሁለት ሳምንት የታሰበው ኤክስፐርመንት በስድስት ቀናት ጊዜ ውስጥ የተቋረጠውም በዚሁ „በሥልጣን መባለግ“ ቁጥጥር የሌለው ጭካኔ በዪኒቨርሲቲው ምድር ቤት ውስጥ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ በመምጣቱ ነው።

ወደ ቀን እየጨመረ በመምጣቱ ነው። በዕውነተኛው ሕይወት፣ በአፍሪካ -

በዕውነተኛው ሕይወት፣ በአፍሪካ -ለዚህ ነው ታሪኩን ያነሳነው- አምኒስቲ እንተርናሽናልና ሒውመን ራይት ወች በየአመቱ እንደሚሉት ከዚህ የባሳ ነው።

~ 29 ~

ሥልጣንን ምን እንደሆነ እና ሥልጣን ይዞ በሰው ልጆች ሕይወት ላይ አለርህራሄ የጭካኔ መዓት ማውረድ ምን ማለት እንደሆነ የሒትለርንና የዮሴፍ ስታሊንን ደርጊት እንደገና መለስ ብሎ ማስታወስ በቂ ነው።

የሩዋንዳው ፍጅት ሌላው የ20ኛው ክፍለ ዘመን ከላይኞቹ ጋር እንዳይደገም ጥሎልን የሄደው አሳዛኝ ትምህርት ነው። በመደብ ትግልና በዘር ጥያቄ አሁን ደግሞ በሃይማኖት ሳቢያ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት እንዴት እንደጠፋ- ገና በቂ ምርምር አልተደረገበትም- እንዴት እንደነበር መገመት ቀላል ነው።

ምንድነው እላይ ከቀረቡት ተማሪዎች ልብና እታች ከተጠቀሱት የመደብና የዘር ልዩነት ቲዎሪ አራማጆች መካከል ያለው „ልዩነትና አንድነት“?

በሁለቱም በሦስቱም መካከል ያለው „አንድነት“ አንድ አመቺ ሁኔታ ቁጥጥር የማይደረግበት ቦታና ሥፍራ… እራሱ ሕግ አውጪ እራሱ ሕግ አስፈጻሚ እራሱን በእራሱ ከሕግ በላይ ያደረገ ሰው የፈለገውን ከማድረግ እንደማይመለስ የሚያሳይ ነው። ይህም ማለት አመች ሁኔታ

አንድን ሰው እዚህ እንደሚባለው „ሌባ“ እንደሚያደርገው ሁሉ፣ አመች ሁኔታ:- የሚቆጣና የሚቆጣጠር ሕግና ሥርዓት በሌለበት ቦታና አካባቢ በዚያች አገር አንድ ሰው ሥልጣኑን በእጁ እስከ እሰከ አስገባ ድረስ የፈለገውን ከማድረግ የሚመልሰው ምንም ነገር የለም። በቅርቡ እዚህ ጀርመን አገር በፕሮፌሰር ቶማስ ኤበርት የኮንስታንት ዩኒቨርስቲ የኖይሮ-ሳይኮሎጂ አስተማሪ „የኮንጎና የሌሎች አፍሪካ አገር ነጻ-አውጪ ተዋጊዎች ታሪክን“ ተከታትሎ ተመራምሮ ያወጣው ጥናት ይህንኑ እላይ የተተረከውን „የተማሪዎች ታሪክ“ በሌላ መልኩ አቅርቦአል። ሰውዬው ተዋጊ ወጣት ጦረኞቹን አነጋግሮና ጠይቆ ወደ ምርመራ ጣቢያውም ተመልሶ የብዙ ወንጀለኞችን አንጎል መርምሮ እንደደረሰበት ሰውን ማሰቃየት ሆነ አንድን ሰው ለመግደል (-ብዙ ምክንያቶች ከጀርባው አለ… ቅናት አለ እራስን ከጠላት መከላከል አለ… አለጥርጥር በአይዲኦሎጂ መሳከርም አለበት…) „አውሬን አድኖ ከመግደል ደስታ

ጋር

ይህቺን „ደስታ“ ለማግኘት አንድ ጂን MAOA-GEN. ተጠያቂ

~ 30 ~

እንደተያያዘ“

ምሁሩ

ይገልጻል።

እንደሆነም ይኸው ጠበብት ያነሳል። ይህ ጂን ግን ተጠያቂ ቢሆንም

ይህ ጂን ግን ተጠያቂ ቢሆንም ፈንድቶ እንዳበጠብጥ እሱን የሚያግድ

ፈንድቶ እንዳበጠብጥ እሱን የሚያግድ ሜካኒዝም አለ።

ማንም ሰው ዕድሉን ከአገኘ „ገዳይ“ ለመሆን እንደሚችል ጥናቱ ይጠቁማል። … ለምድነው አንድ ሰው „ጨካኝ“ የሚሆነው? ሌላውስ ለምንድነው ፍዳ ተቀባይ የሚሆነው?

ይህ እንዳይሆን ይህን ለማገድና ለመቆጣጠር ምን ዓይነትና ብልሃትና ሕግ በእጃችን አለ?

በእጃችን የሚገኘው የጽላተ- ሙሴ ሕግጋት አንደኛው ነው። „…አትስረቅ አትግደል አትመኝ…“የሚለው የኢትዮጵያ ቤተ-ክርስትያን የያዘቺው ታቦት እንደ ምስክርነት ሊጠቀስ ይገባል። ይህ በታሪካችን የመጀመሪያው አመታት ላይ ብቅ ብሎ „አብሮ የመኖርን ሥርዓትና ደንብ“ መልክ ሊሰጠውም ችሎአል ። እሱ -ሕግጋቱ ብቻውን ግን “በቂ መተዳደሪያ አይደለም።”

የአዶልፍ ሒትለር ፖለቲካና የናሺናል ሶሻሊዝም ፍልስፋና የናዚዎቹ ርዕዮተ-ዓለም ወረድ ብለን እንደምንመለከተው ይህንኑ „…አትግደል“ የሚለውን ሕግ እንደአለ -„ይህ የአይሁዶች ፍልስፍና ነው“ ብሎ አዶልፍ ሒትለር „ሰርዝቶት „ ፍጅት በእነሱ በአይሁዶችና በሌሎች ሕዝቦች ላይ ሊከፍት ችሎአል።

አተይስት- ኮሚኒስቶቹም እነ ስታሊንና እነ ማኦ እነ…ከዚህ ያልተለ እርምጃም እነሱ በዘመናቸው ወስደዋል።“…አትግደልና ጠላትህን እንደራስህ አድርገህ ወደደው…“ ከሚለው ሕግ እራሳቸውን አርቀው እንደዚሁ በተራቸው እነሱም በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት – በሩሲያ በቻይና በካምቦጂያ በኮሪያ በኢትዮጵያ በቬትናም አሁን በኮንጎ በናይጄሪያ በሱማሌ…ፈጅተዋል። ሒትለርና ስታሊን

~ 31 ~

ከመፈጠረቸው በፊት የጀርመኑ ስመ ጥሩ ጸሓፊ ቮልፍጋን ጉተ ስለ አንድ „ኃይለኛ አጋንንት“ ያ ሰውን ሁሉ አታሎ ስቦና ማርኮ እሱ ባሪያው አድርጎ ስለሚገዛቸው ፍጡር ፣…ጽፎአል። ይህ ሰውም እሱ ማን እንደሆነ? ምን ማድረግ እንደሚችል?…ቆይቶም ሊያመጣ የሚችለውን መዓት ጠቅሶ እሱም እንዴት በአንድ ዓለም አቀፋዊ ኃይል ሊባረር እንደሚችል አንስቶ ከእሱ ጋር ጉተ በጽሁፉ እኛን አስተዋውቆአል። የጀርመኑ ደራሲ ጉተ ናፖሊዮንን አይቶ ስለ “ዴሞን” ሲጽፍ E.T.A. ሆፍማን የተባለው ሌላው የአገሩ ደራሲ በ19ኛው ክፍለ-ዘመን „ሥልጣን ስለጠማውና ሥልጣን ከመያዝ ስለማይመለሰው አንድ ሰው“ እሱም በድርሰቱ ላይ አንስቶ ቸክችኮአል። ይህም ፈላስፋው ፍሬደሪክ ኔቼ “ …ስለ ሥልጣን ጥማት“ ከመጻፉ በፊት የተነደፈ ሓሳብ ነበር።

„…ሕይወት ተንቀሳቃሽ ሕይወት ሁሉ ከትግል ጋር የተያያዘ ነው። ሕይወትም የትግል ውጤት ነው።ድል ሁሌ የጎበዙ እንጂ የደካማው ፍጡር አይደለም። ሌላውን ድል በማድረግም ጠንካራው ፍጡር ሥልጣኑንም ኃይሉንም ሐብቱንም ንብረቱንም ያበዛል። በዚህ መንገድ…ይበዛለታል። ይበረክትለታል።“

ኔቼ „…አስፈላጊ ያልሆኑትን ፍጡሮች በማጥፋትና በመደምሰስ አዲሱን ልዩ ሰው እሱን መፍጠር ይቻላል…“ ያለውን የፍልስፍና ፋንታዚ ሒትለር ብቅ ብሎ የኦሽዊትዝን ወህኒ ቤቶች መስርቶ „መኖር አይገባቸውም“ የሚላቸውን የሰውን ልጆች… አይሁዶችን ሲንቲና ሮማዎችን ጥቁርና ክልሶችን ደካማና በሽተኞችን እያጋዘ በእሳት ምድጃ - አዲስ „…አሪየን“ የተባለው „የጀርመኖች የነጭ ዘር ብቻውን ዓለምን

የነጭ ዘር ብቻውን ዓለምን እንዲገዛ „ እነሱን አጋይቶአቸዋል።

እንዲገዛ „ እነሱን አጋይቶአቸዋል።

~ 32 ~

ለዚህም ድርጊቱ „ እግዚአብሔር የፈለገው ቅዱስ ሥራ ነው“ የሚለውን መጠሪያ ስምና አላማ ሰጥቶት በቅስቀሳ የሰውን ልብና አእምሮ አስክሮ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ጭካኔውን አካሄዶአል።

ቢያንስ ከሦስት ሺህ የተለያዩ መጽሓፍት በላይ ስለ ተጻፈለት ሒትለር (አሁንም እየተጻፈለት ነው) ብዙ አዲስ ያልተሰሙ ነገሮችን ፈልጎ ጨምሮ ለአንባቢው ማቅረብ ቀላል ባይሆንም የሒትለር የፖለቲካ ቲዎሪ የተገነባው በ18ተኛውና በ19ኛው ክፍለ-ዘመን በተስፋፋው በኢቮሊሽን ቲዎሪ በዚያ ትምህርት ላይ መሆኑን መጥቀሱ እዚህ ላይ አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም ! ይህን የመሰለ „ዕብድ“ የተማሩና ያልተማሩ „ሰዎች“ እንዴት ታውረው እሱን በቀላሉ ተታለው ተከተሉት? ለሚለው ጥያቄ መልስ የሚሰጥ በመሆኑ ነው።

„ተፈጥሮ ርህራሄ የማታውቅ ጨካኝና መራራ ፍርድዋን ቁርጥ አድርጋ የምትሰጥ“- ትግሌ- በሚለው የዘረኛ ፖለቲካ ድርሰቱ ላይ ሒትለር እንደጻፈው „ …ኃይለኛ ፍጡር ናት።…የቻለውና ጠንካራው – ጥረቱ ለመኖር ነውና- አሽንፎ ወጥቶ እራሱንና ልጆቹን ከጥፋት ያድናል። ደካማው ደግሞ ወድቆ ቦታውን ጊዜው ለወለዳቸው ጠንካራ ዘሮች ይለቃል።…ሰበአዊ ርህራሄ የሚባል ነገር በተፈጥሮ ትግል ውስጥ የለም። …ይህን የሚሉት ፈሪዎቹ ደካማዎቹ አጉል እናውቃለን ባይ ጥረዝ ነጠቆች ናቸው። የሰው ልጅ በማያቋርጠው ዘላለማዊ ትግል ውስጥ ገብቶ እዚህ አሁን ያለንበት ደረጃ ላይ ደርሶአል። ዘለዓለማዊ ሰላም በሚባለው ነገር መታለል የለበትም። በዚህ ሓሳብ ከተታለለ ደግሞ ነገ ተንኮታኩቶ ይወድቃል።“ …ይህ ግን መሆን የለበትም ብሎ በዚህ ዘለዓለማዊ ትግል አሪየር የተባለው የጀርመኖች ነጭ ዘር ከሌላው ደካማ ደምና ቀለም ጋር ሳይካለስና ሳይበረዝ ሳይነካካ አሽናፊ ሁኖ ወጥቶ ሌሎችን ደምስሶ -ኢቮሉሽን ላይ እንደምናየው- ዓለምን -ሒትለር መግዛት አለበት“ ይላል።

በዚህም ጠቅላላውን የአይሁድና የክርስቲያን ሃይማኖት፣ የግሪክንና

~ 33 ~

የሮምን ሥልጣኔ እነሱ የመጡትን ኤቲክና ሞራል ፍልስፍንና አስተሳሰብ ሽሮ ሰርዞ አዲስ „የዘር“ ቲዎሪ ይገነባል።

ከዚያ በሁዋላ „ለመኖር ለመግዛት ለመስፋፋት …ያገኘኸውን ፍጀው „ ወደ የሚለው ፍልስፍናው ሒትለር ይሸጋገራል። የሩሲያ መሬት ለመስፈር ይገባናል ይላል።

አሥርቱ ቃላት ላይ የሰፈረው „አትግደል“ የሚለው ሕግና ደንብ „…እኛ ዓለምን እንዳንገዛ አውቆ በአይሁዶች የተላከብን አፍዝ አደንግዝ ትዕዛዝ ነው።… እሰከ ዛሬ ድረስ ያገለገሉት የሞራል ደንቦች ቦታ የላቸውም። የሲና ተራራ ላይ ሙሴ ከእግዚአብሔር ተቀበልኩት ያለው ጽላት በአሁኑ ዘመን ቦታ የለውም…“ ሒትለር ሲል ሒምለር የተባለው ጋሻ ጃግሬው የታጠቁትን የኤስ ኤስ የዘር የጽዳት ዘመቻ ጠራጊዎችን „ሂዱና

የጽዳት ዘመቻ ጠራጊዎችን „ሂዱና ግደሉ“ ከማለቱ በፊት እንደዚህ ብሎ

ግደሉ“ ከማለቱ በፊት እንደዚህ ብሎ ሸኝቶአቸል። „…ከፊታችሁ ወድቀው ተሰብስበው ከተከመሩት ከመቶ አስከሬን ፊት ብዙዎቻችሁ ስትቆሙ የሚሰማችሁን መገመት እችላለሁ። ወይም አምስት መቶው ተትረፍርፎ እዚያው ወድቆ ስታያዩት። ወይም ደግሞ አንድ ሺህ የሚጠጋው እዚያ እፊታችሁ ተጋድመው ስትቃኙአቸው። ነቅነቅ ሳትሉ ይህን እያያችሁ ኮርታችሁ ስትቆሙ -ይህ በማንም ታሪክ ላይ ያልተጻፈውን ጀግንነት ማንም ሰው በቃላት ገልጾ ሊያስቀምጠው የማይችለው ታሪካችሁና ታሪካችን ነው። በሉ ሂዱ …“ ብሎ ያሳናብታቸዋል።

በሉ ሂዱ …“ ብሎ ያሳናብታቸዋል። ከዚሁ ጋር የውሽት ፕሮፓጋንዳው

ከዚሁ ጋር የውሽት ፕሮፓጋንዳው አብሮ ይለቀቃል። ጠበንጃውና ቦንቡ ታንክና አይሮፕላኑ ይከተላል። ሁለተኛ ዓለም ጦርነት ይከፈታል። በዚሁ በተከፈተው ጦርነት ሳቢያ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት ጠፍቶአል።

~ 34 ~

ጥያቄው ትልቁ ጥያቄ ያ! ሒትለር የሚባል አንድ የሥዕል ትምህርት ቤት ለመግባት ዕድል ያላገኘ ሰው፣ ያ በሁዋላ ተራ ወታደር ሁኖ የአንደኛ ዓለም ጦርነት ውስጥ የተሳተፈ የፈላስፋዎችና የደራሲዎች አገር በሚባለው በጀርመን እንዴት በቀላሉ ሁሉንም ቡድኖች አሸንፎ ተከታዮቹን ሰብስቦ ሥልጣን ላይ እንዴት እሱና ፓርቲው ሊወጣ/ሊወጡ ቻሉ?ለዚህ ጥያቄ ደግሞ መልስ ለመስጠት ሌላ ጊዜ የሚጠይቅ አርዕስት ነው።

ያም ሆኖ አንደኛውን መልስ ብቻ ለመጥቀስ„… የፖለቲካ መደቡ በዚያን ዘመን አለመስማማት „ ለእሱ ለሒትለር ምን ጊዜም የማይገኝ ዕድልና በር ከፍቶለታል።

ኮሚኒስቶቹ በዚያን ዘመን -በየዓይነቱ ነበሩ- እርስ በእራሳቸው ያኔ ይጣሉ ነበር።እነሱ አንድ ላይ ሁነው ሶሻል ዲሞክራቶችን፣ ሶሻል ዲሞክራቶች-እነሱም ለጉድ ብዙ የተለያዩ ነበሩ- እርስ በራሳቸው… ሊበራሎቹ ከአናርኪስቶቹ ሞናርኪስቱ ከኮንሰርቫቲቡ እነሱ ደግሞ በተራቸው ከንጉሡ፣ ንጉሡ ከሩሲያና ከእንግሊዝ ጋር…ሁሉም ተሰብስበው አንዱ ላይ እንደገና እነሱ እርስ በራሳቸው…በዚህ ትርምስ (ኢትዮጵያን ይመስላል) ሒትለር መጥቶ ሁሉንም ጭጭ አድርጎ ቤተ-

መንግሥቱ

መፍትሔውን ያገኙት መራራውን የናሺናል ሶሻሊዝምን የፋሽሽት የግፍ አገዛዝ ከቀመሱና የብዙ ሰው ሕይወት ከጠፋ በሁዋላ ነው። ፓርላማ እና የፖለቲካ ነጻነት ሰበአዊ መብትና ነጻ-ጋዜጣ መቻቻልና መከባበር ጣምራ መንግሥት ማበጀትና ሕግን ማክበር…ይህ ሁሉ የመጣው ከ1945 ዓ .ም በሁዋላ ነው።

ሊገባ

ችሎአል።

„ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጋችሁ ጥላችሁ ለእንደዚህ ዓይነቱ ሥርዓት ብቻ ተነስታችሁ ታገሉ…“ያሉ የጀርመን ጭንቅላቶች ቀደም ሲል በብዛት ተነስተዋል። ስለእነሱም ወደፊት እናነሳለን።

~ 35 ~

ለአፍሪካም ያላትና የቀራት ምርጫ ይኸው የነጻ- ሕብረተሰብ መንገድ ነው።

የነጻ - ሕብረተሰብ መንገድ ነው። ይልማ ኃይለ ሚካኤል — - ለ አእምሮ

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

-

~ 36 ~

የዓለም ማጣፈጫው ማር…

የዓለም ማጣፈጫው ማር… ከስምንት ወር በፊት አንድ መጽሓፍ ሳገላብጥ እግረ -

ከስምንት ወር በፊት አንድ መጽሓፍ ሳገላብጥ እግረ-መንገዴን ያነበብኩት አንድ ምዕራፍ ከዚያን ቀን ጀምሮ እንደ አንዳች ነገር እንደ ጥላ እየተከታተለ እኔን ሲያጅበኝና ሲያሳድደኝ እረፍት ነስቶኝም እንደ አውሬ ሲያድነኝ ከርሞ ነበር።…“ ይህን የመሰለ ዓረፍተ ነገር የያዘ አሜሪካን አገር እየታተመ የሚወጣውን ዕለታዊ ጋዜጣ ያነበብኩት ከጀርመን ተነስቼ በሮም አቋርጬ ሌሊቱን ቀይ ወይኔን እየጠጣሁ ወደ አዲስ አበባ በምበርበት ሰዓት ነው። በዳዊት ብሩክ የተጻፈውን በኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ላይ„የፍቅር- ጨዋታ“ የሚለውን አርዕስት ይዞ የወጣውን ገጽ ገና ስጀምረው እኔን እራሴን ለወራት ሳይሆን ለአመታት እንደ ጓደኛ ሁኖ የሚከታተለኝን እና የሚያሳድደኝን አንድ የቆየ ጉዳይ አጻጻፉና አተራረኩ ጠቅላላ አቀራረቡ አስታወሰኝ። ብሩክ ያነበበው መጽሓፍና ከነከነኝ የሚለው ምዕራፍና አረፍተ-ነገር በሚካኤል ኢግናቴፍ የተጻፈውን የኢሳያ በርሊንን የሕይወት ታሪክ ባዮግራፊውን ነው። ኢሳያ በርሊን የዛሬውን ቅዱስ ጴጥሮስ ከተማ የቀድሞውን ሌኒን ግራድን በ1945 ዓ .ም. ሲጎበኝ አንድ ቀን ምሽት ሳያስበው ያጋጠመውን ሁኔታ ምዕራፉ ማለት ታሪኩ መለስ ብሎ ያስታውሳል።

~ 37 ~

በርሊን በዚያን የጉብኝት ሳምንቱ በአንዱ ቀን ምሽት ምንም የሚያደርገው ነገርና ልዩ ቀጠሮ አልነበረውም። አንድ ጓደኛው እሱ ጋ መጥቶ „ምን ይመስልኻል?…ጊዜና ምንም የምትሰራው ሥራ ከሌለህ እስቲ ወይዘሮ አና አህማቶቫን እንጎብኛት።…ከአየሁዋት እሱዋን ብዙ ጊዜዬ ነው…“ ይለዋል። በርሊን አህማቶቫ የምትባለውን ሴትዮ ማን መሆኑዋን ሳያውቅ እሽ ብሎ ተነስቶ አብሮ እሱዋ ቤት ለመሄድ ፈቃደኛነቱን ይገልጽለታል። በሁለቱ መካከል ቢያንስ የሃያ አመት ልዩነት አለ። ከዚያም በላይ አና አህማቶቫ ከሩሲያ አብዮት በፊት የታወቀች ትልቅ ደራሲና የቅኔ ሰው ናት። ከ1925 ዓ. ም. በሁዋላ ጠርጣሪዎቹ የሶቪየት ባለሥልጣኖች ምን ነገር እሱዋ ጽፋና አሳትማ እንዳታወጣም ከልክለዋታል። የመጀመሪያ ባሉዋ መሠረተ-በሌለው የሓሰት ወንጀል ተከሶ የሞት ፍርድ በ1921 ተበይኖበት በጥይት ተገድሎአል። ቆይቶ በ1938 ልጅዋ እንደዚሁ በጸረ-አብዮተኛነት ተይዞ ታስሮአል። ለአሥራ ሰባት ወራት በተከታታይ ልጅዋ ታስሮባት እሱ የት እንደደረሰ ለመጠየቅ በምን ሁኔታ እንደሚገኝ ለማወቅ የእሥር ቤቱ በራፍ ላይ ከሌሎች እናቶች ጋር አብራ ቆማ አሳልፋለች። በርሊን እንግዲህ በእንግድነት ጓደኛውን አጅቦ የሄደው እዚህች በበሰለ ዕድሜዋ ላይ የምትገኝ ቁንጅናዋ ግን ገና ያልከዳት በፈገግታ የተሞላ ፊቱዋን ሲያዩት ደስ የምትል መልከ-መልካም እና ከዚያም በላይ ጠንካራ መንፈስ ያላት አምባገነኖች ደግሞ እሱዋን የሚፈሩዋት ግን በአንድ በኩል በዓለም ጦርነቱ በሌላ በኩል በደርስባት በደል ልቡዋ የተሰበረ ጸሓፊ ቤት ነው። ጨዋታቸውን የከፈቱት በባጥ በቆጡ አርዕስቶች ግን መልክ በአላቸው አርዕስቶች ላይ ነው። …ስለ የብርትሽ አገር ዩኑቨርሲቲና ስለ ትምህርት አሰጣጥ ስለ ጦርነት ዘመንና ስለወጣቶች ሞት ያ ጦርነትም በሰው ልጆችና እናቶችና አባቶች ላይ ስለአመጣው ስለሚያመጣው መከራና ችግር ስለ እሱ በማዉራት ሐሳባቸውን በመለዋወጥ ጊዜአቸውን አሳለፈዋል። አንዳንድ እንግዶች በዚያን ምሽት አርፍደው ይመጣሉ። አንዳንዶቹ የመሸባቸው ተሰናብተው ይሄዳሉ። ወደ እኩለ ሌሊቱ ላይ ሁለቱ ብቻ የእንግዳ መቀበያው ክፍል ቀርተዋል። እሰዋ በጠረጴዛው አንደኛው ጠርዝ ላይ ተቀምጣለች። እሱ ራቅ ብሎ በሌላው ጫፍ ወንበሩ ላይ ደገፍ ብሎ ከደራሲዋ አፍ የሚወጡትን ቃላቶች በጥሞና እና በትካዜ ያዳምጣል። ስለ የልጅነት ዘመኑዋ ተወራለታለች። ስለ ኮረዳ ዘመነዋ…ታነሳለች።

~ 38 ~

እንዴት ቀለበት እንደአሰረች ትዳር እንደያዘች ስለ የመጀመሪያ ፍቅሩዋ …ስለባለዋ ታስሮ መገደል ስለዚሁ ሁሉ በግሩም ቃላቶች አጫውታው ወደ ሥነ-ጽሑፍ ዓለሙ ሰለዚያ ስለመተወዳቸው-ደራሲዎችና ጸሓፊዎች፣. ፈላፋዎችና… መጽሓፍቶች ትሸጋገራለች። በቃሉዋ በደራሲው በባይረን የተጸፈውን „የዶን ሑዋን“ ድርሰት በሚጥሙ ቅላጼዎቹዋ ስታንቆረቁረው በርሊን አላስችል ብሎት ዓይኑ ይረጥብበታል። ጆሮውን ሰጥቶአት እንዳይታወቅበት ደግሞ ፊቱን ቀስ ብሎ ወደ መስኮቱ አዙሮ በስንት መከራ የገነፈለበትን ውስጣዊ ስሜት ሁሉንም ነገር ቀስ ብሎ ይውጠዋል።ሊናገር ፈልጎአል።ግን ትቀድመዋላች።

ከእራሱዋ የቅኔ ድርሰት በቃሉዋ ጠቅሳ እንደዚሁ ከውበቱ በለሰለሰ ድምጽዋ ታካፍለዋለች። ስንት ግሩም ጻሓፊዎች በጸረ-አብዮት ስም እሥር-ቤት እንደተወረወሩ በጥይት በሶቪየቶች እነደተደበደቡና በሲባጎ እንደተንጠለጠሉ ስማቸውንና ሥራቸውን እየጠቀሰች ታጫውተዋለች። ከንጋቱ አሥር ሰዓት ላይ ወፎቹ መንጫጫት ሲጀምሩ እነሱ አውርተው ትላልቆቹ ደራሲና ጸሓፊዎች ላይ ደርሰዋል። አለጥርጥር ፑሺኪን እና ቼኮቭን ሁለቱም በጋራ አድንቀዋል። በርሊን ቀለል በአለ አቀራረቡ ብዕሩን እንደ ሙዚቃ ቅኝት ደበላልቆ የሚያንሸራትተውን ቱርጊኔቭን አደንቀዋለሁ ሲል አህማቶቫ ስውር የሰው ልጆችን ምሥጢር እየፈለቀቀ የሚያወጣውን ዶስትዬቪስኪን ከሁሉም ደራሲ እሱንአስቀድማለሁ ትለዋለች። የቶሊስቶይና የሼክሽፒር የዳንቴና የሆሜር የሲስሮና …ስሞች አንስተው ብዙ ቦታ ደርሰዋል። ብዙ በተነጋገሩ ቁጥር ወደ ውስጥ እየጠለቁ ሄደው ለረጅም አመታት እንደሚተዋወቁ ሰዎች ልባቸውን ከፍተው መጫወት ጀመሩ። እሱዋ ስለብቸኝነት ኑሮ ታነሳለች። ለኪነትና ለሥነ-ጽሑፍ ያላትን ፍቅርና ከዚያ የምታገኘውን ደስታ አንስታ ታሰረዳዋለች። ሚካኤል አንጂሎ ራፋኤል ሊዎራንዶ ዳቬንዥ …በርሊን ይህን እየሰማ ተመስጦ መታጠቢያ ቤት ለመሄድ እንዃን ያለበትን ደቂቃ በአንድ በኩል ጨዋታውን ላለማቋረጥ በሌላ በኩል የንግግሩዋ „እሥረኛ“ በመሆን አፉን ከፍቶ ማዳመጡን ይመርጣል። ሁለቱም አንድ ዓይነት መጽሓፍቶችን አንብበዋል።

~ 39 ~

ሁለቱም በሰበሰቡት ዕውቀት አንድ ደረጃ ላይ አብረው ቆመዋል። ሁለቱም ስለምን እንደሚነጋገሩ በደንብ ያውቃሉ። ዓለምንም የሚያዩበት ነጻ-ዓይናቸው አንድ ነው። በዚያን ምሽት ኢግንቴፍ እንደ ጻፈው „የበርሊን ሕይወት/…ነፍሱ ሥነ ጥበብና ሥነ -ጽሑፍ አንድ ላይ ሁነው የተገጣጠሙበት ሌሊት ነበር።“ ይለናል። በዚህ ስሜት በርሊን የአህማቶቫን ቤት ለቆ ከእሱዋ ተሰናብቶ ወደ ሆቴሉ ይመለሳል። ከጥዋቱ አምስት ሰዓት ላይ አልጋው ላይ ወዲያና ወዲህ እየተንከባለለ „…ፍቅር ይዞኛል።…ፍቅር ያዘኝ…“ ብሎ ጮኸ።

ምን ዓይነት ፍቅር? „…ዛሬ የምንኖርበት ዘመን ከጥቅም ጋር ብቻ የተያያዘና ምን አገኝበታለሁ? ከሚለው ጥያቄና አስተሳሰብ ጋር የተዛመደ ነው። ዙሪያ ጥምጥሙ ሁሉ ይህ ነው በማይባል የዜና እና የኢንፎርሜሽን ዳታ የተተበተበ ነው። ችግሮችን እንኳን ለመፍታት የምንሰጣቸው ማብራሪያዎች -ሊዎን ቪስልቲር እንደ አለው- ከዚሁ ከጥቅም ጋር የተያያዘ ነው። “ወይዘሮ አህማቶቫና ኢሳያ በርሊን አብረው ሁለቱ በግሩም ጨዋታ ሐሳብ በመለዋወጥ ያሳለፉት ምሽት ከላይኛው ከጥቅም አንጻር ከሚደረገው „ንግግርና መዘባረቅ ጋር“ ፈጽሞ የማይገናኝ ነው። ይህኛው የእነሱ ዓለምና አመለካከት ፍጹም የተለየ ነው። የእነዚህኞቹ የአዋቂዎች ጨዋታ ከዚያና ከዚህ ከሚቦጨቀው ተባራሪ ዜናዎችና የትም ከተቀመጠ „ዳታ“ ከሚባለው ኮሮጆ ተቀድቶ ታፍሶ በአራቱም ማዕዘን የሚረጭ ሰበካ አይደለም። የልጆችም ዕብደት- ዛሬ ይህንን ነገ ያንን ሥርኣትና ኑሮ ከአልመጣም የሚልም አይደለም።

ታላላቅ የሰው ልጆች ለዘመናት ከሰበሰቡትና ከአጠራቀሙት ኮትኩተውም ጠብቀውም ለትውልዱ ከአሳለፉት ባህልና ተመክሮ ሞራልና እሴቶች …የተስተካከለ ኑሮ ለመኖር አውጥተው አውረደው ከአሰቀመጡልን ጎተረ የተገኘ ነው።

በርሊንና አህማቶቫ እነዚህ በድንገትና በአጋጣሚ የተገናኙት ሁለት ጭንቅላቶች ከዚህ „…እንዴት የተስተካከለ መልክ ያለው ኑሮ እንኑር?“ ብለው ከሚያስቡ ሰዎች ዓለም የመጡና ያንንም ባህል የጨበጡ አእምሮአቸውም በዚያ የተገነባ ኢንቴሌክቹዋል ካፓሲትአቸውም

~ 40 ~

በዚያም የታነጸ ሰዎች ናቸው። አንድ ሰው ከትላልቅ አስተሳሰቦችና አመለካከቶች ከትላልቅ ጽሑፎችና ድርሰቶች የፋላስፋ ትምህርቶች ጋር እራሱን ከአላስተዋወቀና ከእነሱም ጋር በጥያቄና መልስ እራሱን ከአልፈተነ የዚህቺን ዓለም ኑሮ እንዴት እንደሆነች ፈጽሞ ሊረዳ አይችልም። እዚያ ውስጥ ገብቶ ከዋኘ ደግሞ ምን ያህል ብሩህ የሆነ ዕውቀትና ጥበብ አግኝቶ እሱ በሚሰጠው ፍርድና ሥራው ለሌላውም ሰው በሚያካፍለው ትምህርቱ ሕያው ሁኖ ይኖራል። ሕይወትም የሰው ልጆች ሕይወትም የተንኮለኞች መቀለጃ ሳትሆን ወርቅማ መሆኑዋን ይረዳል። የሞራል እና የሒሊና ፍርድም ማንኛቸውም እርምጃችን የፖለቲካ ይሁን የኢኮኖሚ የማህበራዊ ኑሮ ይሁን… የትዳር እራሱ የመልካም ጉርብትና አብሮ የመኖር ብልሃት ከዚሁ እላይ ከተባለው ዕውቀት ይመነጫል። አህማቶባና በርሊን ሊግባቡ ዓለምን በአንድ ዓይን ሊያዩ የቻሉት ከመጽሓፍት-ከተለያዩ መጻሕፍት ለቅመው ሰብስበው ከአገኙት ዕውቀት ነው። ለዚህ ነው መንፈሳቸው አንድ የሆነው። አመለካከታቸው አንድና ኩታ ገጠም የሚመስለው። ቋንቋቸውም አንድ ሆኖ በቀላሉ ሊግባቡ ችለዋል። ይህም እነሱን አንድ አድርጎአቸዋል። የጋራ ቋንቋቸው ይህቺን ዓለምና -ለብዙዎቹ ስውር የሆነውን የእኛን የሰው ልጆች ባህሪን – ጥሩ አድረገው ያቀረቡት የጸሓፊዎች የተጠቀሙበት„የሥነ-ጽሑፍ ቋንቋ ነው። “ያ ምሽት ሕያው ሁኖ የሚቆይ የሁለት ሰዎች „ትስስር“ ነበር። እንደዚህ ዓይነቱ ትስስርና ፍቅር ደግሞ በአንድ ሰው ሕይወት ውስጥ አንዴ ወይም ሁለቴ የሚመጣ ነው። በርሊንና አህማቶቫ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርገው ጥለው በአንዴ ተግባቡ። በብዙ መንገዶች ሁለቱም አንድ ሆኑ። በመካከላቸው በቅጽበት የበቀለው አንድነት ሁሉንም ነገር ረስተው ልብ ከልብ እንዲገናኙ አድርጎአቸዋል። ስለዚያ ምሽት ያቺ መልከ መልካሙዋ አህማቶቫ የጻፈቺውን ግጥም ዛሬ የሚያነብ ሰው ሁለቱ ተዋደው አንድ አልጋ ተቃቅፈው ጊዜውን ያሳለፉ ሊመስለው ይችላል። ግን ኢግናቴፍ እንደጻፈው ሲሰነባበቱ እንኳን ተቃቅፈው ከመሳሳም አላለፉም ነበር ይላል።

የፍቅር ቁርባናቸው ኢንተሌክቹዋሊ- በአእምሮ ጥበብና በዕወቀት ላይ

~ 41 ~

ብቻ ነበር። ይህም ጥሩ መንፈስና መልካም አመለካከትን በሁለቱ መካከል ፈጥሮአል። “ፍቅር” ወንድማዊና እህትማዊ ፍቅር ማለት ይህ ነው። ጓደኛሞች እጅ ለእጅ ተያይዘው ይህቺን መከራ የምታሳየንን ዓለም ለመቀየር አብረው የሚቆሙት በዚህ መንፈስ ነው። በርሊንና አህማቶቫም ያደረጉት ይህንኑ ነው። ለበርሊን ያ ከአህማቶቫ ጋር ያሳለፈው ምሽት የማይረሳው ነው።

እሱዋ እዚያው ሶቪየት ኅብረት እዚያ ውሸትና ፍራቻ በነገሰበት አምባገነን ሥርዓት ውስጥ ቀርታለች። ወደ ነጻው ማህበረሰብ ተመልሶአል።

ትንሽ ቆይቶ ሥርዓቱ እሱን በርሊንን እቤቱዋ ተቀብላ በማነጋገሩዋ- ከብርቲሽ ሰላይ ጋር ተንኮል ትጠነስሳለች ተብላ ከደራሲዎች ማህበር እንድትባረር ተደርጎአል።

ልጅዋ ወህኒ ቤት ይወርዳል። በርሊንን በመገናኘቱዋና ከእሱ ጋር ወርቅማ አስተሳሰቦችን በመለዋወጡዋ እሱን አንድ ጊዜም ተጸጽታ በጽሑፎቹ ላይ ግን ይህቺ ትልቅ ደራሲ ቀኑን አልወቀሰችውም።” …የሚለውን አስሰተሳሰብ ዳዊት ብሩክስ አስፍሮ በሚከተሉት ቃላት ሐሳቡን ይዘጋል።

„…እግዚአብሔር በሰጠኝ የዕድሜ ጸጋ በእንደዚህ ዓይነት ቁርባንና ወዳጅነት ትላልቅ ጽሑፎችንና /ትላልቅ አስተሳሰቦችን አብሮ እያጠኑና እኩል እየተከፋፈሉ ለመኖር የወሰኑ ሰዎችን ስም ለማስታወስና ለመቁጠር እችላለሁ።

ግን አሁን በዚህ በያዝነው ክፍለ ዘመን እኔ እርግጠኛ አይደለሁም ስንት ሰዎች ለእንደዚህ ዓይነቱ ቅዱስ ሥራ ዝግጁ እንደሆኑ አላውቅም።… ለእንደዚህ ዓይነቱ የመጽሓፍት ፍቅር ምን ያህል ትምህርት ቤቶችም (አስተማሪዎች)ተማሪዎቻቸውን አበረታትተውና ኮትክተው ያዘጋጁ/አያዘጋጁ እኔ የማውቀው ምንም ዓይነት ነገር የለም።“ ይህን ጽሑፍ እያነበብኩ ስጓዝ እኔን እንደ ጥላ ይከተለኝ የነበረው ነገር የዚያን ምሽት እንደገና በአእምሮዬ ብቅ አለ።

~ 42 ~

እሱም አንደኛው ዳዊት ብሩክ እንደአለው በመጽሓፍትና በዕውቀት ላይ የተመሰረተ የሰዎች ወዳጅነት በእኛ በኢትዮጵያኖች መካከል „…የኢንተለኬችዋል ኢሞሽናል ስፕሪሽዋል…ማለት የአእምሮ የመንፈስና የልብ ጓደኝነት…“ በመካከላችን መጥፋትና ማጣት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ „…ለነጻ-አስተሳሰብና ለነጻ- ሕብረተሰብ…ለዜጋ ነጻነት ያለን ፍቅር በቶታሊቴሪያን አስተሳሰቦች ተጨፍልቆ መደማመጥ በመካከላችን በመጥፋቱና ጫጫታ በአገራችን በመንገሡ ምን እናድርግ?መድሃኒቱስ ምንድነው የሚለውን የቆየ ጥያቄዬን እንደገና ቀስቅሶብኛል። ከጥበብ ውጭ ሌላ መፍትሔ የለም።

1) በነገራችን ኢሳያ በርሊን ስለ ሁለት ዓይነት „ነጻነት“ በጽሑፉ ላይ ደግሞ ደጋግሞ ያነሳል። አዎንታዊና አሉታዊ ነጻነት።

2) በሠለጠኑ የአውሮፓ አገሮች አዋቂዎች የጥናት ክበብና የጥናት ማህበራት አላቸው። ይህም ሙዚቃንና እስፖርትን ሥዕልና… ያካትታል።

~ 43 ~

.. . “የመጨረሻው የአፍሪቃ ንጉሠ-ነገሥት

የአፍሪቃ ንጉሠ - ነገሥት ” ቀ . ኃ . ሥ . “ የመጨረሻው የአፍሪቃ

. . .

የመጨረሻው የአፍሪቃ ንጉሠ-ነገሥት

ወደ ማምሻው ላይ በአይሮፕላን ጣቢያው አካባቢ ግርግር ይታይ ነበር። ሁሉም እዚያ ቦታ የካኪ ኮትና የቡሽ ባርኔጣ ስለደፉ ማን ምን እንደሆነ ለማወቅና ለመለየት ያስቸግራል። ሦስት አራት ሰዎች ከወታደር መኪና ላይ ዘለው ወርደው ታጅበው ወደ እንግዳ ማረፊያው ክፍል ዘልቀው

~ 44 ~

ይገባሉ። ከጥቂት ደቂቃ በፊት መኪናው ኬላውን ሲያቋርጥ ሚስተር ስሚዝ የሚባል መታወቂያ ወረቀት አንድ ወታደር አገላብጦ አይቶ መልሶላቸዋል። ስሚዝ በእንግሊዝ አገር ጥቂት አመታት ያሳለፈ አንድ ትልቅ ሰው ነው። ከእንግሊዝ አገር ከአንዱ የአየር ኃይል አይሮፕላን ጣቢያ ማምሻውን ተነስቶ ሌሊቱን በፈረንሣይ አገር ላይ በሮ ማልታ የምትባለው ደሴት ላይ ያረፈው የጦር አይሮፕላን ሚሰተር ስሚዝን ይዞአል።

ስሚዝን አጅበው ሦስት ኢትዮጵያኖች አብረው ከእንግሊዝ አገር ተነስተዋል። የሐረሩ መሥፍን ልዑል መኮንን አንደኛው ናቸው። ጸሓፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስ እና እንዲሁም አማካሪአቸው ብላታ ሎሬንሶ ከአጃቢዎቹ መካከል ይገኙበታል።

ባሕር ላይ ማረፍ በምትችለው አይሮፕላን ከንፈው አራቱም ካይሮ በተከታዩ ቀን ይገባሉ።ከካይሮ ወደ ሱዳን ከሱዳን ወደ ጎጃም ወደ ኦሜድላ ሜዳ ከዚያም ዘልቀው ቀስ እያሉ ወደ መሓል አገር ይደርሳሉ። መንገድ ላይ ብዙ ነገር ያጋጥማቸዋል። …ይህንና ይህን የመሰሉ ማስረጃዎችን ሰብስቦ እዚህ የሚተርክልን ጀርመን አገር በቅርቡ ታትሞ የወጣው የዶክተር ልጅ አስፋ ወሰን አሥራተ መጽሓፍ ነው። ሚስተር ስሚዝ የአጼ ኃይለ ሥላሴ የሽፋን ስም መሆኑን- መቼም ይህን ስሚዝ የሚባለው ነገር ያመጡት እነቸርችርል መሆን አለባቸው- አንባቢው የሚረዳው ቢያንስ አንድ መቶ ሰማንያ ገጽ ከአገላበጠ በሁዋላ ነው።

ከዚያ በፊትና ከዚያ በሁዋላ ያለው የንጉሠ ነገሥቱ ታሪክ እሳቸው ያሳለፉት ውጣ ውረድ የተቀበሉት ፈተናና መከራ -ሌሎቹም ጽፈውታል- ቀላል አይደለም።

የልጅ አሥራተን መጽሓፍ ልዩ የሚያደርገው ወደ መጨረሻው ላይ አንስተው የሚተርኩልን ጉዳዮች ናቸው። „…ባዶ ነበር !“ የሚለውን ቃል ጸሓፊው ወርውረዋል።

~ 45 ~

ምኑ ነበር ባዶ?

ልጅ አስፋ ወስን „የመጨረሻው የአፍሪካ ንጉሠ ነገሥት „ ብለው ሰይመው ያወጡት መጽሓፍ የንጉሠ-ነገሥቱን እርምጃ በተለይ ከእነ መንግሥቱና ከእነ ገርማሜ ነዋይ የመንግሥት ግልበጣ ሙከራ በሁዋላ ሥርዓቱን ለማሻሻል ምንም ዓይነት የለውጥ እርምጃ በአለመውሰዳቸው እሳቸውን ይተቻቸዋል። ግን ደግሞ እንደ እሳቸው እንደ አጼ ኃይለ ሥላሴ “በፎርቱና” -በአልታሰቡ ግሩም ዕድሎች የታደሉ መሪ በአገራችን በቅለው እነዳልነበሩ-አለጥርጥር ንጉሡ ዕድለኛ ነበሩ- ከሕይወት ታሪካቸው በደንብ ማንበብ ይቻላል። ፎርቱና! ትቀርባቸዋለች። ይህቺም ዕድል ትወዳቸዋለች። ይህቺም ዕድል ትሸሻቸዋለች።… ከጥይት በተአምር አምልጠዋል። ወሃ ሊበላቸው ሲል ሌሎቹ ነፍሳቸውን ሰውተውላቸው እሳቸው ተረፈዋል። ዘጠኝ ወይም አሥር የሚደርሱ ወንድሞቻቸው/ እህቶቻቸው ሲሞቱ እሳቸው ብቻቸውን ተርፈው ዙፋኑን ጨብጠዋል።

…ከልጅ ወደ ደጃዠማችነት ከዚያ ወደ ራስና ልዑል ራስ ከዚያም የጎንደር ንጉሥ አልጋ ወራሽና ትንሽ ቆይተው በሁዋላ ንጉሠ-ነገሥትም ሁነዋል። ይህቺ ፎርቱና ስትከዳቸው „ቀልባቸው ተገፎ ትከሻቸው ወድቆ አንገታቸውን ደፍተው ምስኪን መስለው ለመሄድም ተገደዋል።“

በስደት ላይ ገንዘብ አጥተው ንብረታቸውንና የምግብ ማቅረቢያ ሳህናቸውንና ሹካቸውን ሳይቀር ለመሸጥ ተገደዋል። መቸገራቸውን ያየ አንድ ኩባንያ „ …ፊልም በአንድ መቶ ሺህ ዶላር እንዲጫወቱም „ ጠይቆአቸዋል።

እሳቸውም (የቻይናው “የመጨረሻ ንጉሠ-ነገሥት” መቀለጃ ሁኖ ፊልም ሲጫወት በየመዝናኛ መሸታ ቤት ለጃፓኖች ሲዘፍን …) አላደርገውም ብለው እምቢ ብለዋል። ይህቺ ለጥቂት አመታት የተደበቀችባቸው ፎርቱና -እሳቸው ይህን የሰማይ መላዕክት የምድር ሠራዊት በአላወቀበትና በአልገመተበት ሰዓት ብለው ይተረጉሙታል- እንደገና ብቅ ብላ ፈልጋ ትክሳቸዋለች። የሁለተኛ ዓለም ጦርነት በአፍሪካ ሌላ መልክ ይይዛል ። ረስቶአቸው የነበረው ጎበዙ ዊኒስተን ቸርችርልም ያኔ -

~ 46 ~

ይህ

ኃይለሥላሴን ሚና መምጣቱን ይረዳል። ብድግ ብለው “ስሚዝ” ተብለው ይመለሳሉ።

አገሪቱን ከውጭ ኃይል መንጋጋም ያወጣሉ።

ከዚያ በፊት በስንት ተአምር አልጋ ወራሽ እንደሆኑና ሌሎችን “ተቀናቃኞቻቸውን” በፖለቲካ ጥበብና ብልሃት ከጨዋታ ውጭ እንደ አደረጉ መጽሓፉን ማገላበጥ ይጠቅማል።

ከስደት ተመልሰው ትምህርትን አስፋፍተዋል። ለጥበብና ዕውቀት ቅድሚያ ሰጥተዋል። የጦር ሠራዊቱን ገንብተዋል። ይኸው ሠራዊት/ሠራዊታቸው ከድቶአቸው ተነስቶባቸዋል።

አጼ ኃይለ ሥላሴ ግን „… አባቴ እግራቸው ላይ ወድቀው ሥልጣኑን ለአልጋ ወራሹ ይስጡ ቢሉአቸው እምቢ…አሉ“ የሚለውንም ሁኔታ ልጅ አስፋ ወሰን አንሰተዋል። በዚህ ጥያቄ ላይም በርካታ ባይባል አንዳንድ ሰዎች ጽፈዋል።

እንደ ታላቁዋ ብርታኒያ እንደ ስዊዲንና እንደ ዴንማርክ ስፔን እነደ …ልንሆን እንችል ነበር? ለምን አይቻልም?

የአጼ

የአውሮፓ

ሊበርቲና

የጸረ-

አምባገነኖች

አርቺቴክት-

በአርግጥ ፓርላማውን አሻሽለውና ሥልጣኑን አሳልፈው ሰጥተው (

በ1924 እ.አ.እ. የተመሰረተ በአፍሪካ የመጀመሪያው ፓርላማ ነው) ከእሱ ጋር ሳንሱርን አንስተው የፕሬስ ነጻነትን ንጉሡ አብረው ቢያውጁልን

ማርክሲዝም… ደርግና ሶሻሊዝም …የጠበንጃ

ትግልና…መገንጠል…. ነጻ አወጪ ወይም ….የላብ አደሩ አምባገነን መንግሥት…“ ከሚባለው / ከሚባሉት ቅዠቶች አምልጣ አሁን ያለችበት ሁኔታ ውስጥ በአልገባችም ነበር።

ኑሮ ያቺ አገር „:

ኮሚኒዝም

ምን ይደረጋል- እንደ ገና ፎርቱና ንጉሡን ትክዳለች። ወይስ „…ደርግ የሚባለው ፍጡር የሚሽከረክርበት አድማና አላማ ሌላ ዕድል ያመጣልኛል… „ ብለው ንጉሱ አስበው ይሆን? …ወይስ እንደ ሚባለው ዕድሜ ተጫጭኖአቸው ደክመው ?

~ 47 ~

ወይስ ብልሃቱ ጠፍቶአቸው? ወይስ ከእኔ በሁዋላ ሰርዶ አይብቀል ብለው? ወይም ደግሞ እስቲ ቅመሱአትና ተቀጡ! ይህ አይታወቅም። ግን ጊዜው የእሳቸው አልነበረም።ይመስላል እንጂ ጊዜው አሁንም ድሮም የተማሪዎችም የወታደሮችም አልነበረም። እንዲያው ሙከራ ተደረገ እንጂ ጊዜው የሶሻሊዝምና የኮሚኒቶቹም አልነበረም።

ጊዜው አሁንም ሆነ ዱሮም „የነጻ- አውጪዎችም „ አይደለም።

የልጅ አስፋ ወስን መጽሓፍ ከሦስት ሺህ አመት በላይ የኖረው የአገሪቱ ምልክት „ዘውዱ“ በንጉሠ ነገሥቱ „ግትርነት ወደቀ „ በተዘዋዋሪ ይላሉ።

ለምን ግን መሣፍንቱና መኳንንቱ ተሰብስቦ መላ- አንድ ሁለት ሦስት አራት አማረጮች… ብሎ እንዳልመታ? ለመረዳት ያስቸግራል። “ታማኝነትና …ባዶ ነበር” የሚሉ አረፍተ ነገሮች ገጹ ላይ ተወርውረዋል። ማለት የሚቻለው ሁሉም ተያይዞ ቦታውን ለአዲስ ተወናዋኒያኖች አስረክቦ ተሰናብቶአል። ማነው አዲሱ ተወናዋይ?

መጽሓፉን የታሪክ ምሁሩ „…መጪው ትውልድ የንጉሡን ሥራ ከአሁኑ (ትውልድ) በተሻለ ዓይን አይቶ ፍርዱን ይሰጣል።“ ብለው ትረካቸውን በዚህቺ አረፍተ ነገር ይዘጋሉ። „…እረኛውን-ማለት መሪውን አናቱን ብለህ ጣለው ከዚያ በሁዋላ በጎቹ ይበተናሉ።“ የተባለው አነጋገር በኢትዮጵያ ደርሶአል።

ለአገሪቱ ጥፋት ተጠያቂው ግን በእኔ ግምት አንድ ሰው ብቻ አይደለም። ተጠያቂዎቹ ብዙ ናቸው። እሱ ደግሞ ሌላ ቦታ ይወስደናል።

ማለት የሚቻለው ነገር ንጉሠ -ነገሥቱ ይህቺን አገር እኛን ጭምር ከብዙ መንጋጋዎች አውጥተውናል። ትምህርት ሰጥተውን “ከጨለማ

ኑሮ”…ከፋሽሽትና ከቅኝ ገዢዎች ቀንበር አላቀውናል።

ከዘመናዊ ሕይወት ጋር በትንሹም ከግለሰብ ከዜጋ ነጻነትና ፍርድና ፍትሕ ጋርም አለ ጥርጥር በደንብ አስተዋዉቀውናል። ነጻ-ሓሳብ እና የሕግ በላይነት የምንለውም ከዚያ ዘመን የመጣ አመለካከት ነው።

ከሥልጣኔና

~ 48 ~

ያምሆኖ ሊበራል ጭንቅላትና ሪፓብሊካን ዲሞክራቶች በዚያች ምድር በገፍ መወለድ ሲገባቸው በእነሱ ፋንታ “ቶታሊቴሪያን አስተሳሰብ ያላቸው አምባገነን ሥርዓት” የሚሉ ወታደሮቸም ነጻ አውጪ ተማሪዎችም ብቅ ብለው ሜዳውን መያዙ በጣም ያሳዝናል።

ታሪክ ጸሓፊው ልጅ አስፋ ወስን አሥራተ” መጪው ትውልድለየት ያለ ፍርድ ይሰጥ ይሆናል…” ብለው ለመድገም ትረካቸውን ዘግተዋል። ጸሓፊው ሞናርኪስት ሳይሆኑ ሪፓብሊካን መሆናቸውን በተዘዋዋሪ ገልጸዋል። ወይስ ?

….

መጽሓፉ በእንግሊዘኛ ና በአማርኛ እንደሚተረጎም ጸሓፊው ለደቸ ቬለ ሰሞኑን በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ አንስተዋል። መልካም ነው። በተለይም ሰፋ ያለው ወጣቱ ትውልድ አንብቦት ከትውልድ ሀገሩ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ጋር በሚያመዛዝን አእምሮ ቢተዋወቅና፣ ቢነጋገርበት ደግ ነው። ብዙ የአውሬ መንጋጋ አድፍጦና አሰፍስፎ ሊቦጫጭቀን በዝግጅት ላይ የሚገኝበት ዘመን ነው። በየት እንደሚመጡብን መገመት እንጂ ምኑም አይታወቅም። በፎርቱና- በዕድል ላይ ብቻ የተገነባ ፖለቲካ መጨረሻው አያምርም።

ፖለቲካ ሌላ ዕውቀቶችን ያጠቃልላል።

*

እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 10 Studies for Reference * Internationa Journal of Ethiopian and Eritrean Studies

~ 49 ~

~ 50 ~