መድረክ በላስቬጋስ የተሳካ ስብሰባ አካሄደ

መድረክ በላስ ቬጋስ ረቡዕ ሚያዚያ 6 ቀን 2002 ዓ.ም በአካባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያን ጋር መጭውን ምርጫ፣
የወ/ሪት ብርቱካንን እስር፣ የሉአላዊነት ጉዳይ፣ በማንሳት የተሳካ ስብሰባ አካሄደ። ለመድረኩ ማጠናከሪያ የገንዘብ ድጋፍ
አሰባሰበ።
በላስ ቬጋስ የአንድነት የድጋፍ ቻፕተር በተጠራው በዚህ ስብሰባ ላይ የመድረኩ አመራር አባላት ኢንጂነር ግዛቸው
ሺፈራው፣ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ አቶ ገብሩ አስራት በየበኩላቸው ንግግር ያደረጉ ሲሆን ከተሰብሳቢዎቹ ለቀረቡ የተለያየ
ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
መሪያችሁ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በእስር እያለች እንዴት ምርጫ ውስጥ ትገባላችሁ፣? በምርጫውስ ታሸንፋላችሁ
የሚሉና ተያያዥ ጥያቄዎች ቀርበው አመራሩ

በሰጠው ምላሽ ወ/ሪት ብርቱካንን ለማስፈታት የሚደረገውን እንቅስቃሴ

እንደሚቀጥል ምርጫው ነፃና ፍትሀዊ ከሆነ መደረክ ሙሉ ለሙሉ እንደሚያሸንፍ ገልፀዋል።

መድረኩ እንደ ቅንጅት አይፈርስም ወይ? የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄ ከአንዳንድ ተሳታፊዎች ቀርቦ መድረኩ በመቻቻል
የሚያምን የቅንጅትን ተሞክሮዎች ግንዛቤ ያስገባ በመሆኑ እንደማይፈርስ ጠቅሰው የፖለቲካ ኢንሹራንስ ግን ማቋቋም
እንደማይቻል አመልክተዋል።
መድረክ ፍፁም ሰላማዊና ህጋዊ ሆኖ የሚንቀሳቀስ ድርጅት መሆኑን ደጋግመው የጠቀሱት አመራሮች ኢህአዴግ የሚፈራው
ሰላማዊ ትግልን መሆኑን ገልፀዋል።

በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የመድረኩን ተሞክሮ በማየት በልዩ ልዩ ምክንያቶች ተከፋፍለው ለአገር ጉዳይ በአንድ
ሊቆሙ አለመቻሉን መሪዎቹ አስታውሰው በመቻቻል በአንደድ ላይ በመቆም የዲፕሎማሲውን ጥረት እንዲያግዙና የገንዘብ
አስተዋጽኦቸውን ለማድረግ የዜግነት ግዴታ እንዳለባቸው ጠቁመዋል።የቬጋስ የአንድነት የድጋፍ ቻፕተር ሰብሳቢ አቶ ያሬድ
ታደሰ በእለቱ በከተማው መሬት እንሰጣለን የሚል ጥሪ በማድረግ በተመሳሳይ ሰዓት በመንግስት ተወካዮች ስብሰባ
መጠራቱን አስታውሰው

ያንን ትተው የአገር ጉዳይ ይቀድማል በማለት የመጡ ተሰብሳቢዎችን አመስግነው በአገር ጉዳይ

ከመለያየት በመቻቻል አብረን እንስራ ሲሉ ጠይቀዋል።

Sign up to vote on this title
UsefulNot useful