You are on page 1of 6

ዘመናዊ ትምህርት በIትዮጵያ

ውልደት Eና Eድገት

በበፍቃዱ ኃይሉ
መንደርደሪያ

“Aዋጅ፡፡
ሞኣ Aንበሳ ዘ Eምነገደ ይሁዳ፡፡
ዳግማዊ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘIትዮጵያ፡፡
Eስካሁን ማንም የEጅ ሥራ Aዋቂ የነበረ ሰው በውርደት ስም ይጠራ ነበር፡፡ ስለዚህም ማንም ሰው ለመማርና
ለመሰልጠን የሚደክም Aልነበረም፡፡ በዚህ ጎጂ በሆነ ሁኔታ ብንኖር ቤተ ክርስቲያኖች ይዘጋሉ፡፡ ይልቁንም ክርስቲያን
Aይገኝም፡፡
“በሌሎች Aገሮች Eያንዳንዱን ነገር ብቻ መማር ሳይሆን፥ Aዲስ ነገሮችም ይሰራሉ፡፡ ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ ለወደፊት ወንድ
ልጆችና ሴት ልጆች ሁሉ ከስድስት ዓመታቸው በኋላ ወደ ትምህርት ቤት Eንዲገቡ ይሁን፡፡
“ልጆቻቸውን ለማስተማር ለማይተጉ ቤተሰቦች፥ ወላጆቻቸው ሲሞቱ ንብረታቸው ለልጆቻቸው መሆኑ ቀርቶ ለመንግስት
ይተላለፋል፡፡ ተማሪ ቤቶችንና Aስተማሪዎችን የሚያዘጋጀው መንግስቴ ነው፡፡”
በ18ኛው ክፍለ ዘመን ማገባደጃ Eና በ19ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ላይ የተነገረው ይህ Aዋጅ በጥቅሉ
ለዘመናዊ ትምህርት በIትዮጵያ ፋና ወጊ Eንደሆነ ይቆጠራል፡፡ በወቅቱ ዘመናዊ ትምህርት ትውፊታዊ
የOርቶዶክስ ትምህርትን ያጠፋል የሚል ስጋት በቀሳውስቱ Eና በምEመኑ ዘንድ ስለነበር፥ ዳግማዊ ምኒልክ
‘ክርስትና Eንዳይጠፋ’ የሚል ማግባቢያ በAዋጃቸው ውስጥ የግድ ማካተት ነበረባቸው፡፡
ስለዘመናዊ ትምህርት በIትዮጵያ Eንዴት ተወልዶ ዛሬ ላይ Eንደደረሰ ስናወጋ፥ Eግረ መንገዳችንን
የጥንታዊውንና መካከለኛውን ዘመን ትምህርት ምን Eንደሚመስል ማውራታችን Aይቀርም፡፡ ከዚያው
Eንጀምር፡፡
ትውፊታዊ ትምህርት በIትዮጵያ
ሪቻርድ ፓንክረስት “የቤተክርስቲያን ትውፊታዊ ትምህርት (traditional education) የሚጀምረው በድምጽ
በተፈጠሩ፣ Eያንዳንዳቸው ሰባት ርቢ ባላቸው 26 ፊደላት ቆጠራ ሲሆን ‘መልEክተ ዮሃንስ’ በመባል
የሚታወቀውን ጽሁፍ ማንበብ ከፊደል ቆጠራ ተከታዩ Eና የመጀመሪያው ደረጃ ነው፡፡” ሲሉ ፅፈዋል፡፡ ከዚያ
ጽህፈት ይከተላል፣ በሦስተኛ ደረጃ የሐዋርያት ሥራ ጥናት፣ ጸሎት Eና የሒሳብ ስሌቱ ይቀጥላል፡፡ ይህ
ዓይነቱ ትውፊታዊ ትምህርት የተወለደው ከ3,000ዓመት በፊት Eንደሆነ ይነገራል - የዳበረው ደግሞ
ክርስትና ወደIትዮጵያ መግባቱን ተከትሎ ነው፡፡

የግEዝ ፊደላት የጥንታዊ ሳባ ግዛት ከነበረችው ደቡብ Aረቢያ ስልጣኔ የተወረሰ /Eያደገ የመጣ/ Eንደሆነ
Aንዳንድ ታሪካዊ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ፊደላቱ ከክርስቶስ ልደት በፊት 2,000 ዓመታት ቀደም ብለው
የተፈጠሩ Eንደሆነ ቢነገርም፥ በIትዮጵያ የግEዝ ትምህርት በሰፊው የተጀመረው ግን በንጉሥ Iዛና በኩል
Iትዮጵያ ክርስትናን ከተቀበለችበት ከAራተኛው ክፍለ ዘመን በኋላ ነበር፡፡
በIትዮጵያ የቤተክርስቲያን ትውፊታዊ ትምህርት ውስጥ የሒሳብ ስሌቶች Eንደነበሩ የሚገምቱ ወይም
የሚያውቁ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ሆኖም የቀን Aቆጣጠርን በተመለከተ ብቻ Eጅግ ውስብስብ የሆኑ ትውፊታዊ
ስሌቶች Eስካሁንም ድረስ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ውስጥ Aሉ፡፡
በዘመናዊ የሒሳብ ቀመሮች የምናውቃቸው ስሌቶችን (በተለይም ማባዛትን Eና ማካፈልን) በተመለከተ ፖውል
ሬኒ የተባሉ ተመራማሪ “Ancient Numerals and Arithmetic” በሚል ርEስ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፋቸው
የጥንታዊ ግብፃውያን፣ Iትዮጵያውያንና ባቢሎናውያን የሒሳብ ስሌቶችን ተንትነዋል፡፡ በዚህ ጥናት ውስጥ
Iትዮጵያውያን ይጠቀሙበት የነበረው ስሌት ቀዳሚውን ስፍራ የያዘ ሲሆን ለዘመናዊው የሒሳብ ስሌት ፈር
ቀዳጅ Eንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ የጥንታዊ Iትዮጵያውያን የሒሳብ ስሌቶች ዜሮን ስለማያካትቱ፥ Eንደ ፖውል
ሬኒ “ምንም Eንኳን የግብፃውያኑ የማባዛት ስሌት የተሻሻለ ቢሆንም፥ የIትዮጵያውያኑ ቀለም ላይ ተመስርቶ
ያደገ ሳይሆን Aይቀርም፡፡”
ይሁንና Eነዚህ ለዘመናዊ ትምህርት መሠረት ሊሆኑ የሚችሉ ትውፊቶች ከትውልድ ትውልድ ሊሸጋግሩ
Aልቻሉም፡፡ Eንዲያውም ዘመናዊ ትምህርት በIትዮጵያ ያቆጠቆጠው በ19ኛው ክፍለዘመን ማገባደጃ ላይ
Eንደነበር የታሪክ ድርሳናት ይመሰክራሉ፡፡ ለዚህ EንደAቢይ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ የዚህ ጽሁፍ
Aቅራቢ የሚገምታቸው መንስኤዎች የሚከተሉትን ይጨምራሉ፡ƒ

ዘላቂ Aደረጃጀት የነበራቸው የትምህርት ተቋማት Aለመኖራቸው፣ (ይህም በተለይ E.ኤ.A. በ969ዓ.ም
የተመሰረተው የግብፁ Aላዛር ዩንቨርስቲንና በ1026ዓ.ም. ተመስርቶ Eስከዛሬ መዝለቅ የቻለውን
የOክስፎርድ ዩንቨርስቲን ስንመለከት ጥንታዊ Eውቀትን ለዘመናዊው ትውልድ ለማስተላለፍ
የሚኖራቸውን ድርሻ መረዳት Eንችላለን፡፡)

ƒ

ተደጋጋሚ ጦርነቶች መበራከታቸው፣ (ጥንታዊት Iትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ንግሥናን በማስከበር፣
ግዛትን በማስፋፋት Eና Aንዳንዴም በሃይማኖታዊ ምክንያቶች ሳቢያ የEርስ በEርስ ጦርነቶችን
Eንዲሁም ከውጭ ወራሪዎች ጋር ጦርነቶችን Aካሒዳለች፡፡ Eነዚህ ጦርነቶች ትውፊታዊ
ትምህርቶችን Eንዳይስፋፉ፤ ብሶም Eንዲወድሙ ምክንያት ሆነዋል፡፡)

ዘመነ Aስኳላ
የ19ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ Iትዮጵያ ከትውፊታዊው የቤተክርስቲያን ትምህርት፣ በወቅቱ Aስኳላ የሚል
ስያሜ ወደተሰጠው ዘመናዊ ትምህርት ለመሸጋገር ዳዴ ማለት የጀመረችበት ወቅት ነው፡፡ Aፄ ቴዎድሮስ
(ዳግማዊ) ጋፋት ላይ Aሁን በተደራጀና በዘመናዊ መልኩ የቀረቡትንና የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና

የምንላቸውን የመሰለ፥ የወጣቶች ማሰልጠኛ የመክፈት ሕልም ነበራቸው፡፡ ምንም Eንኳን ዋነኛው የንጉሡ
ዓላማ የጦር መሳሪያ ማምረት ቢሆንም፥ በዘመናዊ መልኩ የተደራጀ ማሰልጠኛ ለመክፈት በማሰብ ግን ታሪክ
በIትዮጵያ የመጀመሪያው ሲል ይዘክራቸዋል፡፡ ያም ሆኖ በወቅቱ ከነበረው የተዛባ ባሕላዊ Aስተሳሳበ የተነሳ፥
ማሰልጠኛ ይቋቋምበታል ተብሎ በታለመው ጋፋት በጦር መሳሪያ ምርት Eንዲሳተፉ የተደረጉት የተገለሉት
Eና ‹ቀጥቃጭ/ሞረቴ/ቡዳ› በሚል ቅጽል ስም ተለይተው የሚታወቁት Iትዮጵያውያን ብቻ ነበሩ፡፡
ከዚያ በኋላ ባሕሩ ዘውዴ “የIትዮጵያ ታሪክ” በሚለው መፅሃፋቸው ላይ Eንዳስቀመጡት “የመደበኛ
ትምህርት በIትዮጵያ መስፋፋትን በተመለከተ በምኒልክ ዘመነ መንግሥት ፍጻሜ Aካባቢ Aንድ Aቢይ
ድርጊት ተከናውኗል፡፡ ይህም በንጉሠ ነገሥቱ ስም የሚታወቀው ትምህርት ቤት በ1900ዓ.ም. መከፈቱ ነው፡፡”
ዳግማዊ ምኒልክ ይህንን ያድርጉ Eንጂ መንገዱ ሁሉ ጨርቅ ሆኖላቸው ነበር ማለት Aይቻልም፡፡ በወቅቱ
ዘመናዊ ትምህርት ሃይማኖትን ያጠፋል የሚል ስጋት ስለነበር፥ Iትዮጵያን በሃይማኖት ትመስላት ከነበረችው
ከግብፅ መምህራንን ማስመጣት የግድ ነበር፡፡
ከግብፅ የመጡት መምህራን ከIትዮጵያውያኑ ተማሪዎች ጋር የቋንቋ መግባባት ችግር ነበረባቸው፡፡ ይህንኑ
ተከትሎ

መምህራኑ

ተጋራፊዎች

በመሆናቸው

ብዙዎቹ

ተማሪዎች

(የተቀማጠሉ

የመኳንንት

ልጆች

Eንደመሆናቸው) ትምህርታቸውን Eየጠሉ Eቤታቸው መቅረት ጀምረው ነበር፡፡ ይህንን የታዘቡት ዳግማዊ
ምኒልክ ለያንዳንዱ የመሳፍንት ቤተሰብ የተማሪዎቹን ስም ዝርዝር Eያሰፈሩ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ
Eስከመጻፍ ደርሰው ነበር፤ ያውም በEድሜያቸው ማክተሚያ ሰሞን ደብረሊባኖስ ለፀበል በተቀመጡበት
ወቅት፡፡ መኳንንቱም በበኩላቸው የንጉሡን ትEዛዝ ለማክበር ሲሉ ብቻ ከጠሏቸው Aሽከሮች መካከል
Eየመረጡ ወደ ትምህርት ቤት መላካቸው፥ Aስደማሚ ታሪካዊ ትዝታ ነው፡፡
“A History of Ethiopia in Pictures: from ancient to modern times” በሚለው መጽሃፋቸው ጂOፍሪ ላስት፣
ሪቻርድ ፓንክረስት Eና ኤሪክ ሮብሰን “[በ1917ዓ.ም.] Eሳቸው [ንጉሡ] ተፈሪ መኮንን የተባለውን ትምህርት ቤት
ከፈቱ፡፡ ከዚያም ‘ማንም Iትዮጵያን የሚወድ ትምህርት ቤቶችን ለማቋቋም ሊገድደው ይገባል’ የሚል ዜና
Aስነግረዋል፡፡ በ1923ዓ.ም ደግሞ ንግሥቲቱ ‘Eቴጌ መነን’ የተሰኘውን የልጃገረዶች ትምህርት ቤት Aቋቋሙ፡፡
Eንዲህ፣ Eንዲህ Eያለም የዘመናዊ ትምህርት ቤቶች መስፋፋት ከቀድሞው በተሻለ ነገር ግን በAዝጋሚ
ፍጥነት መጓዙን ቀጠለ፡፡
በዚያን ወቅት የትምህርት መስጪያው ቋንቋ (በ1933ዓ.ም. በEንግሊዝኛ ከመተካቱ በፊት) በፈረንሳይኛ ነበር፡፡
ከ1904ዓ.ም. በኋላ በድሬዳዋና በAዲስ Aበባ የAልያንስ ፍራንሴዝ ትምህርት ቤቶች መቋቋም፥ ይህን የፈረንሳይ
ባሕላዊ የበላይነት ይበልጥ Aጠናክሮታል፡፡ የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤትም ከ1923ዓ.ም. በፊት ለተማሪዎቹ
የሚሰጠው የፈረንሳይ መንግስት ሠርቲፊኬት ፈተናዎችን ነበር፡፡ ከተጠቀሰው ጊዜ ወዲህ ግን ትምህርት
ሚኒስቴር ራሱን የቻለ መሥሪያ ቤት ሆኖ በመቋቋሙ፥ በመጠኑም ቢሆን Iትዮጵያዊ ቀለም ላላቸው
ትምህርት ቤቶች መመስረት Eና ትምህርት Aሠጣጡንም ለIትዮጵያውያን ተስማሚ Eንዲሆን AስተዋፅO
ማድረግ ጀመረ፡፡

ድኅረ ጣልያን
ጣልያን ከIትዮጵያ በሽንፈት ከተሰናበተችበት ከ1933ዓ.ም. በኋላ፥ ምንም Eንኳን ሙሉ ለሙሉ የAገሪቱ
የትምህርት ፍላጎት ሊረካ ባይችልም፥ በIትዮጵያ የትምህርት ተቋሞች መጠነኛ Eድገት ማሳየት ችለዋል፡፡
ባሕሩ

ዘውዴ

በጠቀስነው

መጽሃፋቸው

Eንዳሰፈሩት

በወቅቱ

700,000

የሚደርሱ

ተማሪዎችን

የሚያስተናግዱት “ትምህርት ቤቶች በሙሉ በመንግስት የተቋቋሙ Aልነበሩም፡፡ Aያሌ የሚሲዮንና የግል
ትምህርት ቤቶች ከመከፈታቸውም በላይ Eያደር በሕዝቡ መዋጮ የሚሠሩት ትምህርት ቤቶች ቁጥርም
Eየተበራከተ” መጥቷል፡፡
Eንዲያም ሆኖ በጉልህ የሚስተዋሉ ፈተናዎች በትምህርቱ Eድገት ላይ ተጋርጠው ነበር፡፡ የሴት ተማሪዎች
ቁጥር ከወንዶቹ Aንፃር Eጅግ ማነሱ Eና የትምህርት ተቋሞች ስርጭት በተወሰኑ ቦታዎች ብቻ መገደቡ ዋነኛ
ፈተናዎች ነበሩ፡፡ Aብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶች የተከፈቱት በኤርትራና መሃል Aገር (ሸዋ Aካባቢ) ነበር፡፡
ከዚያ በኋላ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችም በAገሪቱ ይከፈቱ ጀመር፡፡ በወቅቱ ዝና ያተረፉት ሁለተኛ
ደረጃ ትምህርት ቤቶች የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት Eና ጄኔራል ዊንጌት ናቸው፡፡
ከፍተኛ ትምህርት በIትዮጵያ የተጀመረው ደግሞ በ1943ዓ.ም. የAዲስ Aበባ ዩንቨርስቲ ኮሌጅ ሲመሰረት
ነበር፡፡ ይህንን ተከትሎ በAምስት Aመታት ውስጥ የመሃንዲስ ኮሌጅና የሕንፃ ኮሌጅ በAዲስ Aበባ፣ የEርሻ
ኮሌጅ በዓለማያ፣ የጤና ጥበቃ ኮሌጅ በጎንደር ተከፈቱ፡፡ በመጨረሻም Eነዚህን ሁሉ በAንድ ጠቅልሎ
Eንዲያስተዳድር የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩንቨርስቲ (የAሁኑ Aዲስ Aበባ ዩንቨርስቲ) ተመሰረተ፡፡
Eንደዚያም ሆኖ Eስከ “Aብዮቱ ፍንዳታ” ድረስ ፊደል የቆጠሩ ሰዎች ቁጥር Eጅግ Aነስተኛ ነበር፡፡
ከ1971ዓ.ም. ጀምሮ ለAራት ዓመታት የተካሔደው የመሠረተ ትምህርት ዘመቻ ግን ፊደል የቆጠሩ
Iትዮጵያውያንን ቁጥር ከ8.8 በመቶ ወደ 50 በመቶ Aሳድጎታል፡፡
በ2001ዓ.ም. የትምህርት ሚንስቴር መረጃ መሠረት በIትዮጵያ ውስጥ 23 የመንግስትና ከAርባ በላይ የግል
ከፍተኛ ተቋማት የዲግሪ መርሓ-ግብር ትምህርቶችን Eየሰጡ ይገኛሉ፡፡ በ2001ዓ.ም. 25,212 የመጀመሪያ
ደረጃ (ከ1-8ኛ ክፍል የሚያስተምሩ)፣ 1,197 ሁለተኛ ደረጃ (ከ9-12ኛ ክፍል የሚያስተምሩ) ትምህርት ቤቶች
Eና 458 የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ማሰልጠኛ (TVET) ተቋማት

በመላው Aገሪቱ Eንደሚገኙ የትምህርት

ሚኒስቴሩ ዓመታዊ ስታትስቲክ Aስፍሯል፡፡ በዚሁ ዓመት፥ በተማሪዎች ምዝገባ የግል ከፍተኛ ተቋማት ድርሻ
17.3% ነበር፡፡ በጥቅሉ በትምህርት ሽፋን ጥሩ Eድገት Eየተመዘገበ Eንደሆነ ቁጥሩ ይናገራል፡፡
የምርምር ተቋማት በIትዮጵያ
በIትዮጵያ የመጀመሪያው የምርምር ተቋም፥ Aሁንም ድረስ የሰው Eና የቁስ ሃብት Eጥረት ችግሩ
Eንዳልተቀረፈ የሚነገርለት፣ በAዲስ Aበባ ዩንቨርስቲ ስር በ1956ዓ.ም. የተመሰረተው የIትዮጵያ ጥናት

ተቋም /Institute of Ethiopian Studies (IES)/ በመባል የሚታወቀው ተቋም ነው፡፡ ከዚያ በተሻገረ
በምርምር ረገድ Iትዮጵያ ዝናን ያተረፉ የምርምር (think-tank) ተቋማት Aላፈራችም ለማለት ያስደፍራል፡፡
በርግጥ Aንዳንድ መንግስታዊ ከሆኑ የምርምር ተቋማት ቀጥሎ፥ Aሁን፣ Aሁን ብቅ ጥልቅ የሚሉ
መንግስታዊ ያልሆኑ የምርምር ተቋማትም Aሉ፤ ከነዚህም መካከል በተለያዩ ማሕበራዊ ጉዳዮች ላይ
የምርምር Aውደ ጥናቶችን በማሰናዳት የሚታወቀው የማሕበራዊ ጥናት መድረክ/Forum for Social
Studies (ማጥመ/FSS) ይገኝበታል፡፡
በሌላ በኩል ሳይጠቀሱ የማይታለፉት፥ ጥቂት የመንግስት

(Aዲስ Aበባ፣ ጅማ፣ ሃሮማያ፣ መቀሌ Eና

ባሕርዳርን የመሳሰሉት) ዩንቨርስቲዎች ጎልቶ የወጣ ባይሆንም፥ ተስፋ ሰጪ ሊባል የሚችል የምርምር
ስራዎችን Eንደሚያካሒዱ ይታወቃል፡፡ ከግል ከፍተኛ ተቋማት መካከል ደግሞ በተለይ ዩኒቲ ዩንቨርስቲ Eና
ቅድስት ማርያም ዩንቨርስቲ ኮሌጅ ዘጠኝ Eና ስምንት (Eንደቅደም ተከተላቸው) ዓመታዊ፣ ብሔራዊ የምርምር
ሥራዎችን በመደጎም Eና Aውደ ጥናቶችን በማካሔድ የግሉ የትምህርት ዘርፍም ለIትዮጵያ ትምህርት Eና
ለምርምር Eድገት ጉልህ Eገዛ Eያደረጉ Eንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ (ቅድስት ማርያም ዩንቨርስቲ ኮሌጅ
በየዓመቱ የሚያዘጋጃቸው Aውደ ጥናቶች በግል የከፍተኛ ትምህርት Eድገት ላይ ያነጣጠሩ ናቸው፤
በተጨማሪም የተማሪዎች ምርምር መድረክን በማመቻቸት የመጀመሪያው ነው፡፡)
ማሳረጊያ
ዘመናዊ ትምህርት በIትዮጵያ Aሁንም ድረስ የሚያኮራ ደረጃ Eንዳልደረሰ የሚስማሙ ብዙዎች ናቸው፡፡
በመሠረቱ በIትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የተገኘ ዲግሪ በተለይም በምEራቡ ዓለም ውስጥ
በትምህርት ለመቀጠል ለሚፈልጉ ካልሆነ በቀር ለሥራ Eምብዛም ተፈላጊነት የለውም፡፡ ይህም ማለት
የከፍተኛ ትምህርት ተቋሞቻችን ዓለምAቀፍ ተወዳዳሪነት ያንሳቸዋል ማለት ነው፡፡
ለጠቅላላው የትምህርት Eድገት በIትዮጵያ፥ ትምህርት ሚኒስቴር Eና በስሩ ያሉት የከፍተኛ ትምህርት
Aግባብነት Eና ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ (HERQA - በAዲሱ መዋቅር ‘የትምህርትና ሥልጠና ጥራት
ማረጋገጫ ኤጀንሲ /ETQAA/’)፣ የሃገር Aቀፍ ፈተናዎች ድርጅት Eና ሌሎቹም ገንቢ ሚና Eንዲጫወቱ
በመታሰብ ተፈጥረዋል፡፡ የትምህርት ሽፋን በመላው ሃገሪቱ ይበል የሚያሰኝ Eድገት Eያሳየ ቢሆንም፥
የከፍተኛ ትምህርት በተለይም ከጥራት ጋር በተያያዘ ፈተናዎች ተጋርጠውበታል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ
የሚወጡ ምሩቃን ብቁ ተወዳዳሪ Eንዳልሆኑ በብቃት ማረጋገጫ ፈተናዎች ሳይቀር Eየተስተዋለ ነው፡፡ ችግሩ
የመንግስት ተቋማት ምሩቃንንም የሚመለከት ሆኖ ሳለ የትምህርት ሚኒስቴር Eርምጃዎች ግን የግል ከፍተኛ
ተቋማት ላይ ጣታቸውን የሚቀስሩበት ጊዜ Eንደሚበዛ የዚህ ጽሁፍ Aዘጋጅ ታዝቧል፡፡
የግል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሃገር Aቀፍ ፈተናዎች ላይ የሚያስመዘግቡት ውጤት
ከመንግስት ተማሪዎች ውጤት Eጅግ የላቀ ነው፡፡ ጎልተው Eየወጡ ያሉት የግል ከፍተኛ ተቋማትም ይህንኑ
Eውነታ በመንግስት ዩንቨርስቲዎች ላይ ወደሚደግሙበት Aቅም Eየገሰገሱ መሆኑን መካድ Aይቻልም፡፡ Aሁን
Eንደተጓደለ ለታመነበት የጥራት ችግር መፍትሄው በIትዮጵያ ትምህርት ጥራት Eና Eድገት ላይ የምርምር

ሥራዎችን Eየሰሩ የማጎልበቻ ብልሐት የሚጠቁሙ Aካላትን መፍጠር ወይም የተፈጠሩትን ማበረታታት ብቻ
ነው፡፡
ዋቢ ንባቦች፡ƒ
ƒ
ƒ
ƒ
ƒ
ƒ
ƒ
ƒ

ጳውሎስ ኞኞ፡፡ 1981ዓ.ም. Aጤ ምኒልክ፡፡
ባሕሩ ዘውዴ፡፡ 2002ዓ.ም. የIትዮጵያ ታሪክ፡- ከ1847 Eስከ 1983ዓ.ም.
ተክለፃዴቅ መኩሪያ:: 1981ዓ.ም. Aጤ ቴዎድሮስ Eና የIትዮጵያ Aንድነት፡፡
Geoffrey Last, Richard Pankhrust and Eric Robson. 2010. A History of Ethiopia in Pictures: from ancient
to modern times
FDRE, MoE. March 2010. Educational Statistic Annual Abstract 2001E.C.
Accessed on January 30, 2011. http://www.chatham.edu/pti/curriculum/units/2004/Renne.pdf
Accessed on January 30, 2011. http://www.higher.edu.et
Accessed on November 20, 2010. http://www.fssethiopia.org.et