CJJB

WTF

አተቤ


ወነአምን በአሓቲ ቅድስትቤተክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባዔ
ዘሐዋርያት

World Tewahedo family

የአለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

በኢትዮጵያና በመላው አለም የምንገኝ
የአለም የተዋሕዶ ቤተሰብ
ጥቅምት ፫ ŧ ƃƈ ዓ.ም. (3, 2004)
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
አዲስ አባባ፣ ኢትዮጵያ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
“ለቅዱሳን አንድጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠች ሃይማኖት እንድትጋደሉ እመክራለሁ” ይሁዳ ፩ ፥ ፳
ይድረስ ለቅዱስ ሲኖዶስ
የከበረ ሰላምታችንን በእግዚአብሔር ስም በትህትና ስናቀርብ በያላችሁበት እንዲደርሳችሁ ከልባዊ
ምኞት ጋር ነው።
አስቀድመን እስከዛሬ ድረስ የቤተክርስቲንን እምነት ሥርዓትና ትውፊት ለማስጠበቅ በበዙ
ለተጋችሁ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፥ አባቶች ካህናት፥ ወንድሞች ዲያቆናት፥ መምህራን ወሰባክያን፥ ዘማሪያን
ወዘማሪያት፥ ውድ የሰ/ት/ቤት አባላት፥ እና ምርጥ የተዋህዶ ልጆች በሙሉ ታላቅ አክብሮትና ምስጋና
ልናቀርብ እንወዳን።

የአለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

| kurtegnalejoch@gmail.com |

ገጽ 1

የተከበራችሁ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት
እኛ በመላው ዓለም የምንገኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን
ከማንኛውም ተፅዕኖ ነጻ ሆነን ስለ ቤተክርስቲያን ፍቅር በራሳችን ተነሳስተን የቤተክርስቲያን የቁርጥ ቀን
ልጅ ለመሆን በኅብረት ተዘጋጅተናል። የቤተክርስቲያን ጉዳይ እንደሚያሳስበን እንደሚያስቆጨን ብሎም
ለቤተክርስቲያን ታማኝ ልጆች መሆናችንን ለማረጋገጥ ጊዜው አሁን መሆኑ እሙን ነው። አሁን ባለው
የቤተ ክርስቲያን ሁኔታም አንዳንዶች አድህነነ እመዓትከ ወይም አበስኩ ገበርኩ ማለትን መርጠው
በጸሎት ሲተጉ ሌሎቹ ደግሞ ጎመን በጤና ሲሉ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚል አማራጭ የወሰዱ
እንዳሉ ልብ ይሏል። እስመ ለዓለም ምህረቱ ነውና ነገሩ አሁን ግን ሁሉንም ወደጎን በመተው በአፍአም
በውስጥ ያለነው ሁላችን በጋራ አብረን የድርሻችንን ለማድረግ መነሳታችን ስንገልጽ ሰበብ የማንፈጥርለት
አማራጭ ሆኖ አግኝተነዋል።
ቤተክርስቲያን በመስቀል የተመሰረተች ስለሆነ ያለ ፈተና የኖረችበት ጊዜ እንደሌለ በሁላችን
ዘንድ የታወቀ ነው። በጽኑ ዓለትም ላይ ስለተገነባች የገሃነም ደጆች አይችሏትም ሲል ጌታችን እራሱ
በወንጌል መስክሮላታል። ይህ ማለት ግን እኛ ዝም ብለን እንቀመጣለን ማለት እንዳልሆነ አንድምታ
አያሻውም። በዚህ እንጽናናለን እንበረታለን እንጂ ለድክመታችን መሸፈኛ አንድምታ ሆኖ መቅረብ
የሌለበት መሆኑ ለሁላችን ግልጽ ነው። የመስቀሉን ጉዞ ቀራንዮ ለማድረስና ለማሸነፍ ጽናት እና ተጋድሎ
ማስፈለጉ አይቀሬ ነውና። ይህም በመሆኑ ለዘመናት ታማኝ አገልጋዮቿ በከፈሉት መስዋዕትነት እምነቷ፥
ሥርዓቷ እና ትውፊቷ ተጠብቆ በመቆየቱ እስከዛሬ ድረስ ሰማያዊ አገልግሎቷን መስጠት ችላለች።
ስለዚህ እኛም ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ በጎ ፈቃደኝነት ፥ ተጋድሎ፥ የጸና አቋምና ቁርጠኝነት
እንደሚያስፈልገን የሁላችንን ስምምነት ያገኘ ወቅታዊ ዐቢይ ጉዳይ ነው።
ቀድሞ ከዓለማውያንና ከዓላውያን እንዲሁም ከአረማውያንና ከመናፍቃን ይደርስ የነበረውን ፈተና
አባቶቻችን በሰይፍ የመጣባቸውን በደም በኑፋቄ የመጣባቸውን በረቀቀ ትምህርታቸው ድል አድርገዋል።
ዛሬ ዛሬ ግን ይህን መሰል ተጋድሎ ጠፍቷልማለት ባያስደፍርም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ስለመሆኑ
ለአብዛኞቻችን ምዕመናን የማይታበል ሐቅ ሆኗል ።
በዘመናችን ቤተክርስቲያን የገጠማት ፈተናና ችግር ዘርፈ ብዙ ከመሆኑም በላይ በዓየነቱም ልዩ
የሚያደርገው መገለጫ አለው። ለምናስተውል ሁሉ ዝርዝሩን ለቤተክርስቲያን በሚያስቡ የተለያዩ
ወገኖችና መምህራን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ተገልጿል ። እንደ አስፈላጊነቱ በሌላ ጊዜ ደግመን
ልንገልፅ እንችላለን።
የችግሮቹን መንስዔ ለመግለፅ ብዙ ቢነገርም ትንቢታዊ መሰረቱን ማሰብ ግን ሊታለፍ የማይገባው
እውነታ መሆኑን እናምናለን። ቅዱስ መጽሐፍ ስለ መጻኢ ዘመን ክስተቶች በስፋት አትቷል። ስለሆነም

የአለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

| kurtegnalejoch@gmail.com |

ገጽ 2

የችግሮች ምንጭ ድንገተኛ እና ከተለያዩ ተፅዕኖዎች የመጣ ብቻ እንደሆነ ማሰብ ግን ወደማያዛልቅ
መፍትሔ ፍለጋ እንድናመራ ያደርገናል። በኋለኛው ዘመን እንደ ግል ሀሳባቸው የሚሄዱ ዘባቾች፤
ለመንጋው የማይጨነቁ ምንደኛ እረኞች፤ ሃሳባቸው ምድራዊ፥ ክብራቸው በነውራቸው፥ እና ሆዳቸው
አምላካቸው የሆነ አገልጋዮች እና አማኞች እንደሚነሱ ቅዱሳት መጻሕፍት በተደጋጋሚ ገልጸውታል ።
እኛም ይህን ሳንዘነጋ በሚሆነው ነገር ሁሉ መረበሽና መደንገጥን ወደ ኋላ መተው ፈለግን። ይልቁንም
“የጥፋት ርኩሰትን በተቀደሰ ስፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢ ያስተውል” እንዲል በዘመናች ጆሮን ጭው
የሚያደርጉ ነገሮችን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መስማት ከጀመርን ብዙ ክረምት አልፏል። ስለዚህ
ማስተዋልን ገንዘብ በማድረግ በፈተና እስከ መጨረሻው በመጽናት ከተጠሩት ሳይሆን ከተመረጡት ወገን
ለመሆን ተስማምተን ኅብረት ፈጥረናል።
ከዚህ የተነሳ ይህን ኅብረት አሁን የሚያሳስቡ ያሉት የወቅቱ ችግሮች ብዛታቸውና ዓይነታቸው
ወይንም ክብደታቸው ብቻ ሳይሆን የራስችን ስንፍናና የውስጥ ድክመት መሆኑን አምነንበታል።
በመሆኑም ለችግሮቹ መባባስ አይነተኛና ቀጥተኛ ድርሻ ወስደዋል የምንላቸውን ነጥቦች በአጭሩ
ለመግለጽ እንወዳለን፦

የሃይማኖት መጉደልና የእምነት ማነስ

የሥነ ምግባር ብልሹነት

ፍቅረ ንዋይ

ዝና፥ ክብርና ከንቱ ውዳሴ ላይ ያተኮረ አገልግሎት መስፋፋት

መልካም መንፈሳዊ አስተዳደር አለመስፈን

አገልግሎት መንፈሳዊ ሳይሆን ሙያዊ መሆኑ

ከክርስቲያናዊ አንድነት ይልቅ ዝምድና እና ወገንተኛነት መሰልጠኑ

ዘመኑን የዋጀ አሰራርና መዋቅር አለመኖር

ሕገ ቤተክርስያንን ያልጠበቀ ብቃት የጎደለው ሥልጣነ ክህነት ሹመት

ቤተ ክርስቲያን የተለያየ ዓላማ ላላቸው አካላት መጋለጧ

Ŧƅ

ግድየለሽነትና አለማዊነት

ŦƆ

የእርስበርስ መወነጃጀል

ŦƇ

የቤተክርስቲያን መጥፎ ታሪካዊ ክፍፍል

የአለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

| kurtegnalejoch@gmail.com |

ገጽ 3

በእነዚህና በሌላም በመሳሰሉት ችግሮች ምክንያትም በቤተክርስቲያን አገልግሎትና ታሪካዊ ጉዞ
ላይ ታላቅ አሉታዊ ጥላ ማጥላቱን የብዙኃን እምነት ነው።በጥቂቱ ከላይ የተጠቀሱ ችግሮች ዛሬ
ከአማኞች አልፎ በአለማውያንና በሌሎች ዘንድ ወሬ ማድመቂያን እና ርዕሰ ዜና መሆኑ አለም ያወቀው
ፀሓይ የሞቀው ጉዳይ ነው። ይህም በዙ መእመናንን ያስለቀሰና አንገት ያስደፋ ሲሆን ለሌሎች ግን
መፈንደቂያ ሆኗል። ችግሩን በተወሰነ ወገን ላይ ብቻ ማሳበብ ሽሽት እንጅ መፍትሔ እንደማይሆን
እናምናለን። በመደበኛ አገልግሎት ላይ ካሉት ከዓቃቤ ኆኅት እስከ ከፍተኛው ማዕረግ ያሉትን ሲያካትት፤
በምዕመናን በኩል ደግሞ ትንሹም ትልቁም፥ የተማረወም ያልተማረውም፥ ህፃኑም ሆነ አረጋዊው፥
ወጣቱም ሆነ ጎልማሳው የችግሩ ተጠቃሽ አካል መሆናቸው ትኩረት የሚያሻው ዐብይ ጉዳይ ነው።
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፦
ችግርን ብቻ መዘርዘር የመፍትሔ መነሻ እንጅ በራሱ መፍትሔ አይደለም ።በሽታውን ያልተናገረ
መድሃኒት አይገኝለትም እንዲሉ። የመፍትሔ ሀሳቦች በተለያዩ ሊቃውንት ፥ ምሁራን፥ እንዲሁም
በተቆርቋሪ ወገኖች እየተገለጠ ይገኛል። እኛም ከእውነተኛ ምንጭ የተገኙትን የመፍትሄ ሃሳቦችን
እንደምንጋራ ስንገልጽ ነገር ግን ወሳኝ የሆኑ እርምጃዎች እንዲወሰዱ በማስቀደም ነው። ይህን ስንል ግን
እኛ ለቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝና መመሪያ እየሰጠን አይደለም። አንድነታችን ለመግለጽና ችግሮች ከአቅም
በላይ እየሄዱ መሆናቸውን ከማሰብ የተነሳ ነው። በዚህ አጋጣሚ ይህ ኅብረት የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎችን
ሙሉ በመሉ እንደሚያከብርና ለተፈጻሚነታቸውም ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀታችን
ከወዲሁ እንገልጻለን። ከቆራጥ የሲኖዶስ አባላትና ከእውነተኛ አገልጋዮች ጋር በመተባበርም አንዲት፥
ሐዋርያዊትና ቅድስት የሆነችውን እናት ቤተክርስቲያን እምነት፥ ሥርዓቷንና ክብሯን ለማስጠበቅ
ከምንጊዜውም በበለጠ ዝግጁ ነን። ቤተክርስቲያን ዕውቅና በሰጠችው ሕጋዊ አካል መፍትሄዎች
በዘላቂነት ተግባራዊ እስከሚሆኑ ድረስ ግን ቅዱሱ ሲኖዶስ የሚቀጥሉትን አፋጣኝ ፥ ወሳኝ እና ሥር
ነቀል እርምጃዎችን እንዲውስድ በታላቅ ትህትናና አክብሮት እንጠይቃለን።
፩ ፡ ያለአግባብ ብቃት በሌለው ሁኔታ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ሳይጠብቅ የሚደረገው የሥልጣነ ክህነት
ሹመት ጊዜ ሳይሰጠው መቆም አለበት። በመንፈሳዊነት በትምህርት ሳይሆን በዝምድናና በዕውቅና
የተሾሙ አገልጋዮች ለተሃድሶ መናፍቃንና ለሌሎች ተዛማጅ ፈተናዎች እንድንጋለጥ አድርጎናል።

የአለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

| kurtegnalejoch@gmail.com |

ገጽ 4

ባሉን መረጃዎችም መሰረት በተለያዩ ሃገራት ቀኖና ያፈረሱ፥ ህዝብ ያሳዘኑ፥ህግ የጣሱ ግለሰቦች
ሹመት አግኝተው መደበቅ እንደሚፈልጉ አረጋግጠናል። ስለዚህ ቤተክርስቲያን እውነተኛ
አገልጋዮቿን እስክትለይ ድረስ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ እንጠይቃለን።
፪ ፡ በሃይማኖት ሕፀፅና በሥርዓት ግድፈት የሚጠቀሱ አገልጋዮችን በቀኖና የመመለስ ወይንም የመለየት
ፈጣን ውሳኔ እንዲሰጥ እንጠይቃለን። ይህንም በማድረግ በምእመናን መካከል የሚታየው መለያየት
ግጭት ውዥንብርና ሁከት በቀላሉ በማቆም ማረጋጋት ይገባል።
፫ ፡ የተሃድሶ መናፍቃንን ዓላማ ለማምከን ቅዱስ ሲኖዶስ አንድ ወጥ የሆነ የአቋም መግለጫ እንዲሰጥበት
እንጠይቃለን። በመቀጠልም ሕዝብን የማንቃትና የማሳወቅ ሥራ ለሚሰሩ እውቅናና መብት
ከተጠያቂነት ጋር እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን
፬ ፡ ያለ ቤተክርስቲያን ሕጋዊ እውቅና የሚያስተምሩና የሚያጠምቁ አገልጋዮችን ያለ ምንም ቅድመ
ሁኔታና ድርድር እንዲያቆሙ ። ማንነታቸውም ተለይቶ አግባብነት ያለው እርምጃ እንዲወሰድ
እንጠይቃለ።
፭ ፡ ከዝምድናና ከወገንተኛነት የፀዳ መልካም መንፈሳዊ አስተዳደር ከአጥቢያ ሰበካ ጉባኤ አንስቶ እስከ
ጠቅላይ ቤተክህነት ድረስ እንዲሰፍን እንጠይቃለን።
፮ ፡ ሙስና ብክነትን ፈጽሞ ማስወገድ ለነገ የማይባል አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን አምነንበታል። የአለማዊው
አስተዳደር እንኳን ሙስናንና ብክለትን ለማጥፋት በትጋት ሲሰራበት የመልካም ሥነ ምግባር አርዓያ
መሆን የነበረባት ቤተክርስቲያን ግን በዚህ ችግር ተዘፍቃ መታየቷ አሳዛኝ ብሎም አሳፋሪ ነው።
ስለዚህም ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ጉዳይ ላይ ቁርጥ ውሳኔ እንዲሰጥበትና በአጥፊዎችም ላይ አስተማሪ
የሆነ እርምጃ እንዲወሰድ እንጠይቃለን።
፯ ፡ ያለ ሥርዓት የሚሄዱትን እና በእነርሱ ምክንያትም የእውነት መንገድ የሚያስነቅፉ አገልጋዮች
(ካህናት፥ባህታውያን፥ሰባክያን፥ ዘማርያን) ላይ የእርምት እርምጃ እንዲደረግ። ወጥ የሆነ የአሠራር
ሂደት እንዲኖር እንጠይቃል።
፰ ፡ በየአብነት ትምህርት ቤቶች፣ ተማሪዎች፣ እና ውድ የቤተክስቲያን ሊቃውንት ተገቢው ክብርና
እንክብካቤ

እንዲገረግላቸው።

፱ ፡ በአባቶችና በምዕመናን መካከል የነበረው መልካም ግንኙነት ወደ ቀደመ ይዞታው በመመለስ
በመከባበርና በፍቅር የመሠረተው ግንኙነት እንዲቀጥል ሁሉም አባቶች የበኩላቸውን እንዲወጡ
እናመለክታለን።

የአለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

| kurtegnalejoch@gmail.com |

ገጽ 5

፲ ፡ በበዓላትና በተለያዩ የመንፈሳዊ አገልግሎት መስጫ ሥፍራዎች በምእመናን ላይ የሚደረገው
ሥርዓት የለሽ መስተንግዶና እንግልት እንዲቆም እንጠይቃለን። ሥርዓት አስከባሪና ከዘበኛ እንዲሁም
የበላይ አለቆች ሁሉ ምእመናንን በትህትናና በፍቅር ሊያስተግዷቸው ይገባል። ምእመናን
የቤተክርስቲያን ውድ ጌጦች ናቸውና። ዛሬ ያልተንከባከብናቸውን ነገ በብዙ ድካም አናገኛቸውምና።
በዚህ አጋጣሚ አንዳንድ ሰ/ት/ቤቶች በበዓላት ወቅት በትህትናና በሥርዓት በማስተናገድ ግፊያና
ግርግርን ለመቀነስ የሚደክሙትን ሳናመሰግን አናልፍም።
Ŧƅ፡ ከሐዋርያት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን የቅዱስ ሲኖዶስ ሥልጣንና ክብር እንዲጠበቅ
አጥብቀን እንጠይቃለን። ሲኖዶስ መንፈስ ቅዱስ መራሽ መሆኑን በጽኑዕ እናምናለን። ስለሆነም
የቅዱስ ሲኖዶስ የበላይ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ ማንኛውንም
የበላይነትና ጣልቃ ገብነት አበክረን እንቃወማለን።
ŦƆ ፡ በቤተ ክርስቲያን ላይ ከተለያዩ ወገኖች የሚሰነዘሩት ነቀፋዎች አሉታዊ አንድምታዎች እንዲሁም
የመብት ጥሰቶችን በህገ ቤተክርስቲያንም ሆነ በሀገሪቱ ሕገ መንግስት አንፃር የማስቆም እርምጃ
እንዲወሰድ እንጠይቃለን
ŦƇ ፡ ታሪክን ለማጥፋትና ሃብት ለመሰብሰብ የቤተክርስቲያንም ሆነ የሀገሪቱን የታሪክ አሻራ በያዙ
ገዳማትና አድባራት ላይ የሚደረገው የብርቅ ቅርሶች ዘረፋ እንዲገታ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ።
ጉዳዩ ለሚመለከታቸው መንግታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች በማሳወቅ ሕጋዊና ሰፊ ጥበቃ
እንዲደረግላቸው እንጠይቃለን።
ŦƈŁ በተለያዩ አድባራት እና ከተሞች ሆን ተብሎ በንፁሃን ምእመናን ላይ እየተደረገ ያለውን
ማወናበድ፥ ግፍ እና እንግልት በአስቸኳይ የሚቆምበት መንገድ እንዲፈለግ እንጠይቃለን። በዚህ
የተነሣ ብዙ ምዕመናን ተስፋ እየቆረጡ እና በቤተ ክርስቲያን ላይ ያላቸው እምነት እየተናደ ስለሆነ
ትልቅ ትኩረት ያሻዋል እንላለን።
ከላይ የተዘረዘሩ ጉዳዮች ሁሉ እኛ እንደ አዲስ ያቀረብነ እንዳልሆና ብዙ የተባለባቸውና የተነገሩ
ሊሆኑ እንደሚችሉ እንገምታለን። ነገርግን ከግለሰብ ሃሳብ ወደ ጥቂቶች ከዚያም ወደ ኅብረት ከኅብረትም
ወደ አንድነት በመምጣት አባቶችና አገልጋዮች እንዲሁም ምእመናን አንድ ላይ ሆነን የጋራ ችግሮቻችንን
በጋራ ለመፍታት ይቻለን ዘንድ በማሰብ ነው። እንግዲህ ቅዱስ ሲኖዶስ እኒህንና ሌሎች መሰል
እርምጃዎችን በመወሰን የበለጠ አገልግሎት የሚሰጥበትን መንገድ እንደሚያመቻች ሙሉ እምነት አለን።

የአለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

| kurtegnalejoch@gmail.com |

ገጽ 6

ይህን ስናቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ከመንፈስ ቅዱስ በታች የቤተክርስቲያን የመጨረሻ ወሳኝ አካል መሆኑን
በማመን ነው።
በመጨረሻም ቤተክርስቲያን ለዘመናት ላዘኑ መጽናኛ ለድሆች መጠጊያ ለደከሙት ብርታት
ለታመሙት መዳኛ በመሆን ቆይታለች። ዛሬ በተቀደሰውሥፍራ የሚታየው ሁከት፥ ጭቅጭቅ፥
መለያየትና ሥርዓትኧልበኝነት ይህንን መንፈሰዊ አገልግሎት እንዳያደክም እንሰጋለን።
“ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምስያጥ፤ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ ወአንትሙሰ ረሰይክምዎ በአተ
ፈያት ወሰረቅት”። ማቴ ŧ ƅ ፥ ŦƆ
በወንጌል እንደተገለጸው “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ ተጽፎአል፥ እናንተ ግን የወንበዶች
ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው” በማለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ቤቱ ቀንቶ ሥርዓት
አስከብሯል። ዛሬ ጌታችን እራሱ ዳግመኛ ጂራፍ አንስቶ ለማጽዳት እንደማይመጣ ግልጽ ነው።
ምሳሌውን ከእኔ ተማሩ ብሏልና ፍለጋውን ተከትለን ሁላችንም የድርሻችንን ለማድረግ የምንተጋበት
ጊዜው አሁን ስንል በክርስቲያናዊ ቁርጠኝነት ነው። ይህ በተዋህዶ ልጆች ልብ ውስጥ የተቀጣጠለው
ቅናተ ቤተክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ግፊት ነውና ምንም ነገር ለያዳፍነው እንደማይችል እየተንፀባረቀ
ያለ ሐቅ ነው። ኅብረታችን ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ የሚደረገውን የትኅድግና ርብርቦሽ አበክሮ
ይደግፋል። የቤተ ክርስቲያን ህልውና ተከብሮ ሥርዓቷ ተጠብቆ እስክናይ ድረስ ግን ማንኛውንም
መስዋእትነት ለመክፈል ተዘጋጅተናል። በዚህም መሰረት ደቂቀ ናቡቴ ለመሆን በተዋህዶ የታተምንበት
ቅዱሱ መንፈስ ክርስቲያናዊ ግዴታችን እንደሆነ ያሳስበናል። ነገር ግን አሁን የተያዘው አካሔድ
ካልታረመና የሚፈለገው ለውጥ እንደ አግባቡ ካልተፈጸመ በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎት፥
በሀገሪቱ የእድገትና የልማት ጎዳና ብሎም በሕዝቦችም ሰላምና አንድነት ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ
ተፀዕኖ ከባድ እንደሚሆን የሚመለከተው አካል ሁሉ እንዲያስተልበት ብሎም እርምት እንዲወስድበት
ልናሳስብ እንወዳለን። እግዚአብሔር ለሁላችንም አንዳች ጥቂት መልካም ሥራ የምንሰራበት ብርታትና
ሃይል ሰጥቶን ታሪክ ሰርተን መልካም ዘመን ለማየት ያበቃን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን !
የአለም የተዋሕዶ ቤተሰብ
ከልባዊ አክብሮትና መንፈሳዊ ሰላምታ ጋር !

የአለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

| kurtegnalejoch@gmail.com |

ገጽ 7

ግልባጭ:
፩/ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
፪/ ለብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
፫/ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
፬/ ለብጹዓን አባቶች በየአህጉረ ስብከቶቻቸው
፭/ ለአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
፮/ ለሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኀበረ ቅዱሳን
፯/ ለሰሜን አሜሪካ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ

የአለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

| kurtegnalejoch@gmail.com |

ገጽ 8

Sign up to vote on this title
UsefulNot useful