You are on page 1of 4

አጭር ማስታወሻ ለእስክንድር

ፍሥሓ ታደሰ ፈለቀ

ውድ እስክንድር፦ በቅድሚያ እንኳን ለዘመነ ማቴዎስ አደረሰኽ። በመቀጠልም ስለኑሮኽ
ልጠይቅኽ፦ (ኑሮ ካሉት ቃሊቲም... ነውና) እንዴት አለኽ? ውድ ባለቤትኽስ? ልጅኽስ?
እኔ አምላከ-ኢትዮጵያ ይመስገን ከመላ ቤተሰቤ ጋራ ደኅና ነኝ። ከዚህ የሚቀጥለውን
እንዳንድ ታናሽ ወንድም ማስታወሻ ውሰድልኝ።

ስላንተ ላንተ ማውሳት ከንቱ ድካም ይኾናል። ስለዚህ አልሞክረውም። ይልቅ የማውቅኽ
በዝና ብቻ ሳይኾን አንድ ቀን ተያይተን እንደነበረ ልጠቁምኽ እወዳለኹ። ሥድስት ኪሎ
ከየካቲት 12 ሆስፒታል በስተጀርባ አካባቢ። ይኸውም ላንድ ዐቢይ ቁም ነገር ልትከራየው
ያሰብኸውን ቤት ለማየት ስትመጣ ጓደኞቼ እና እኔ ያንኑ ቤት ለተመሳሳይ ዐቢይ ጉዳይ
ጽ/ቤት ለማድረግ ውል ቆርጠን ሒሳብ ስንከፍል ደረስኽና በመቀደምኽ ቆጨኽ። ወዲያው
ለምን እንደምትከራዩት ብትነግሩኝ ብለኽ ፈቃዳችንን ጠየቅኽ (“እናንተ ይቅርባችኹ ለኔ
ልቀቁልኝ”

ልትለን

ዐስበኽ

ነበር

ይኾን?)።

እኛም

አላቅማማንም

“ለትንሣኤ-ግእዝ”

አልንኽ። ጥቂት ማብራሪያም አከልንልኽ። አንተም ቤቱን ለምን ፈልገኸው እንደነበር
ገለጥኽልን (ምስጢር አፈሳ/የባቄላ ወፍጮ ስላልኾነ፤ እዚህ አልገልጠውም)። ከዚያማ
ባላማችን መቀራረብ ደሥ አለኽና፤ እንዲያ ከኾነስ አይቆጨኝም፤ እንዲያውም ሥራችኹን
ስትጀምሩ አስታውሱኝና የዜና ሽፋን እሰጣችዃለኹ ብለኽ ቃል ገባኽልን። ኾኖም ያገራችን
ፍዳ አላለቀም ኖሯል አንተ ያለውድ በግድ ቃሊቲ ወረድኽ፤ እኛም ያለግድ በውድ
ያዘጋጀነውን ድግስ ሳናጋፍረው ተበታተንን። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በልቤ ውስጥ ተከብረኽ
ትኖራለኽ። ይህንኑ ከዚህ ቀደም ባልገልጥልኽም ቅሉ።

“ታዲያ ዛሬ ምን ተፈጠረና ብዕርኽን አነሣኽ?” ብትለኝ፦ ብዕሬንማ (ያውም በሌሊቱ)
ያነሣኹት... እንዳትሰበርብኝ ነዋ! ነገሩ እንዲህ ነው፦

“በልቤ ውስጥ ትኖራለኽ” አልኩኽ አይደል? ምን በእኔ ልብ ብቻ በመላ ኢትዮጵያውያን ልብ
ውስጥ እንጂ! እንዲህም ስለኾነ ባሜሪካ የሚኖሩ እውነተኞች ኢትዮጵያውያን በድጋሚ ወደ
ቃሊቲ የተወረወርኽበትን አንደኛ ዓመት ለማስታወስ ለ“ብርዕ” ተሸላሚው ላንተ ክብር
የሥነ-ጽሑፍ

ውድድር

እንዳዘጋጁ

ሰማኹ።

ሰማኹልኽና

“አበጃችኹ”

ብሎ

እንደማለት እንዲህ ብየ ርግማኔን ግጥም፦ “ለእስክንድር ያልኾነ ብዕር ይሰባበር።”

ዝም
እኔ

እንዲያ ከማለቴ ቀኑ ከች ማለቱ።

ችግሩ ግን በተለያየ ነገር ተወጠርኹና ለውድድር የሚበቃ ነገር አላዘጋጀኹም። እናሳ ዝም
ልበል? እንዴ! በገዛ ራሴ ርግማን ብዕሬ ብተሰበርብኝሳ? ስለዚህ ብዕሬን ለመታደግ ብዕሬን
አነሣኹ። ታነሣዃትም ዘንድ “ብዕርኽ ተምን?” እንደምባል ዐውቀዋለኹ። መልሴም “ብዕሬ
ተማስታወሻ” ነው። ከላይ ከጀመርኹት ማስታወሻ፣ ከሚቀጥለውም። ወደቅኔና ግጥም
መጠጋቷም አይቀርም።
እየውልኽ የዛሬ አራት ዓመት ገደማ “Radicalism and Cultural Dislocation in Ethiopia,
1960-1974” የተሰኘውን የፕሮፌሰር መሳይን መጽሐፍ አንብቤ ስጨርስ ስለ “ያ ትውልድ”
እንዲሁም

“ተራራውንም

ስላንቀጠቀጠው”

ያለኝን

አመለካከት

ባንዲት

ጉባኤ

ቃና

እንደሚከተለው ጠቅልየ ጎረስኹት።
ለኤርምያስ አብ ትውልደ-ሥሳ ጸዋሬ-ትንቢት ተጽዕቆ
መንፈቆ ርኢነ ወኢርኢነ መንፈቆ
ፍችውም፦
“ትንቢትን/ጭንቅን የተሸከመ (ያረገዘ) የአባት ኤርምያስ/የሥሳዎቹን ትውልድ
ከፊሉን አየን ከፊሉን አላየንም” ማለት ነው።
(ትርጉሙን ማራቀቁን ለሌላ ጊዜ። የለም ጥቂት ላራቅቀው መሰል፦ ኤርምያስ እስራኤልን
ይነቅል ይተክል ዘንድ እንደተሾመ ብትንቢቱ መጀመሪያ ነግሮናል። ምናልባት የኛም “ያ
ትውልድ” ተራራ አንቀጥቃጩም፣ ምን ባዩም አነሣሡ ይነቅል ይተክል ዘንድ እንደነበረ
ብንገምትም፤ እስካኹን ግን ነቀላውን እንጂ ተከላውን እንዳላየን ተመስጥሯል)

ይችንም ቅኔ፤ ምንም ብታንስ ብቻዬን በልቼ ብቻየን እንዳልሞት አልኹና ቢያንስ ለፕሮፌሰሩ
ላጋራቸው ፈለግኹ። ኾኖም ጉባኤ ቃናዋን እንዳለች ብልካት ላትዋጣቸው ትችል ይኾናል
በማለት፤ እሷኑ በዘይቤ ሳይኾን በምስጢር የሚፈታ አጭር ያማርኛ ግጥም ላክኹላቸው።
እንዲህ ብየ፦
ተወለድኹና፦
እግዜር ሲነቅላት (አገሬን) ሊተክላት
ሲያፈርሳት ሊሠራት
ባውቅም ቅሉ፦
እንዲመጣ ትፍሥሕት አንድ ቀን
እንዳለኹ አለኹ በሠቀቀን።
ርሳቸውም “You said it all” ብለው መለሱሉኝ። ለነገሩማ ቢያከብሩኝ እንጂ እንዲያ
ማለታቸው

ነገሩን

ሌላ

ገጣሚ

ጨርሶት

እንደነበረ’ኮ

ራሳቸው

በዚያው

መጽሐፍ

ገልጸውታል። እንዲህ ብለው፦
“The rise of destroyers consequent to the cutting of the umbilical cord finds a
poignant expression in the following poem of the Ethiopian Student:
Gone are those days when we were innocently playful
Gone too with them is the vigor of life;
Cold is the heart that once was warm with love,
And the hot and lively blood,
Has given way to coldness,
The coldness that heralds

The nearing of the end.”
ታሪካችንን የሞላውን ክብርና ዝና፤ እስከ “ሥር-ነቀሉ” ትውልድ ዘመን የዘለቁትንም
መንፈሳዊ እሴቶቻችንን ማወቃችን፤ ዛሬ ያጣነውን ነገር ከተራ የማጣት ስሜት ወደ
“አግኝቶ-የማጣት” ስሜት ከፍ ስለሚያደርገው፤ ዐዘናችን ተራ ዐዘን ሳይኾን “ሠቀቀን”
ኾኖብናል። ረ እግዚኦኦኦ! አግኝቶ-አጣ ኾነን እስከመቼ?
ይህ አንዲህ ነው፤ ቀሪውን ሆድ ይፍጀውና ለጊዜው አንተን ባለቤት ያደረገች አንዲት አጭር
ቅኔ ጀባ ብዬ ልሰናበትኽ--“ሚ በዝኁ” ቅኔ። “ሚበዝኁ” ባለሦስት ቤት ቅኔ ነው። ርእሱ
የተገኘው “እግዚኦ ሚ በዝኁ እለ ይሣቅዩኒ” (አቤቱ የሚያሠቃዩኝ ምንኛ በዙ) ከሚለው
የዳዊት መዝሙር ነው። እነሆ፦

ስፍሐ-ሕዝብ ሰላመ ምስለ-ፋእመ-መንግሥት ጽድቅ ትእንም እስክንድር
ወምእናመ-ግዕዛን ትኩን ኢትዮጵያ ሀገር
ጊዜሁ ቅሩብ። ወይትመየጡ ዉሉድ ትሩፋኒሃ ለምድር።

እስክንድር

ሆይ፦

ድር/የሕዝብ

ሰላምን

ከማግ/የመንግሥት

እውነት

ጋራ

(ትጽፈው፣ ታስተምረው) ዘንድ፣
አገራችን ኢትዮጵያም [የሸማኔ]/የነጻነት ጕድጓድ ትኾን ዘንድ
ጊዜው ቀርቧል። የምድር ፍጹማን ልጆቿም ይመለሱ ዘንድ(ይመለሱ(ይመለሳሉ)።

ያንተንም ያገራችንንም ነጻነት ያሳየን። ቶሎ ብሎ።
አሜን ወአሜን፤ ለይኩን፣ ለይኩን።

ትሸምነው