You are on page 1of 5

አረቦናዊ ማንነት፦ ፍና-ህላዌ በ“ንብረት” እና በ“ቁመት” መካከል

{በኻች ዓምናው የዘመን መለወጫ “ያውዳመት ራስ” የሚል ጽሑፍ ለንባብ አብቅቼ ነበር። ዓምናን
በስንፍና እንዲሁ ዘለልኹት። ዘንድሮ ግን ለምን አንድ ጽሑፍ አላቀርብም አልኹና--ከላይ በመንፈስ
ቅዱስ የተገለጠላቸውን በነገሩን ነቢያት፣ ከታችም በአእምሮ ጠባይዕ የተመራመሩትን ባስረዱን
ፈላስሞች፣ ትክሻ ተንጠላጥየ--ይችን ስለጊዜ እና ስለህላዌ የምታወሳ ክታብ ከተሰቀለችበት የኅሊ
ግድግዳ አወረድዃት። እነዃትላችኹ።}
በዚህ ጽሑፍ የማቀርበው ዐተታ በዋናነት ፍልስፍናዊ ነው። ከቋንቋ ሥራት ጋራ የተያያዘ
ንባበ-ህላዌኣዊ ምርመራ

(ontological

inquiry)

ኾኖ፤ ህልውኣዊ ውጤት

(ontic

import)

አለው። ባተታየ ኢትዮጵያዊም ኤዎሮጳዊም ምንጮችን እጠቀማለኹ። ምንም ስንኳ ፖለቲከኛ
ባይደለኹም፤ ወደፊትም እንድኾን ባልሻ ቅሉ፤ ከተሳካልኝ፤ ያተታየ ድርስ ለአገራዊ ምክክር
ዐይነተኛ ፋይዳ ይኖረዋል ብየ አምናለኹ። ያውም በቅርብ ከተለያየ አግጣጫ ተነሥተው ለነበሩ
ውይይቶች። ይኹን እንጂ ዝርዝር ፋይዳውን አኹን አላትትም። ለጊዜው ስለኢትዮጵያ የሚገደው
ምሁር፣ ፖለቲከኛ፣ ማናቸውም ዜጋ እንዲያነብበኝ እየተመኘኹ ልቀጥል።
በጽሑፉ ገለጥዃቸውም አልገለጥዃቸው የማጠነጥንባቸው ዕሳቤዎች፦
ቅድምና (apriori perfect/apriorisches perfekt)
ጠቢብ ርባታ (philosophical conjugation)
always already/immer schon (ኹለዬ እኮ/ኹለግዜ ቢያ)
essence/ τό τί ήν είναι (ንብረት)
existence (ቁመት)
social ontology (ኅብረተ-ህላዌ)

1. በቅድሚያ በቅኔ ቤት የአእመረን ጓዝ ስናጠና ከቀሰምኹት ትምርት ልጀምር

“አእመረ” የሚለው የግእዝ ግሥ (ሊቃውንቱ በየዋሁ በዳዊት ግንብ በሚመስሉት) በየዋህ ርባታ
መንገድ ባማርኛ ሲፈታ “ዐወቀ” ይባላል። ይኸው ግሥ (በጠቢቡ በሰሎሞን ቤት በሚመሰለው)
ጽንዕ፣ መሠሪ ወይም ጠቢብ በሚባለው የርባታ መንገድ ደግሞ እንደሚከተለው ይፈታል፦

ግእዝ

ዐማርኛ

አእመረ
(ዐወቀ)

ዐውቆ አለ

ዐውቆ ኖረ

ዐውቆ ነበረ

ዐወቆ ኾነ

ዐውቆኣል/ዐውቋል

አንዱ ሌላውን ሲያውቀው፤ በየዋህ ርባታ “አእመሮ = ዐወቀው” ይላል። በጠቢብ ግን እንዲህ
ነው፦

ግእዝ

ዐማርኛ

አእመሮ
(ዐወቀው)

ዐውቆት አለ

ዐውቆት ኖረ

ዐውቆት ነበረ

ዐወቆት ኾነ

ዐውቆትኣል/ዐውቆታል

በቦቱ (በ“በ፟ት”) እና በሎቱ (በ“ለ፟ት”) የሚረባውን ጨምረን ብናየው የሚከተለውን እናገኛለን፦

ግእዝ

ዐማርኛ

አእመሮ

ዐውቆት አለ

ዐውቆት ኖረ

ዐውቆት ነበረ

ዐውቆት ኾነ

ዐውቆታል

(ዐወቀው)

ዐውቆበት አለ

ዐውቆበት ኖረ

ዐውቆበት ነበረ

ዐውቆበት ኾነ

ዐውቆበታል

ዐውቆለት አለ

ዐውቆለት ኖረ

ዐውቆለት ነበረ

ዐውቆለት ኾነ

ዐውቆለታል

እዚህ ላይ ልብ እንበል፦ እነ “አለ፣ ኖረ፣ ነበረ፣ ኾነ፣ ኣል” በዚህ አገባባቸው ረዳት ግሦች
ናቸው። እነሱን ራሳቸውን በመጀመሪያ እንደዋና ግሥ በዚህ መልኩ ብናረባቸው እና ከዚያ በዃላ
ረዳትነታቸውን ብንጠቀም ደግሞ፤ የባሰ እየረቀቅን እንኼዳለን። ምሳሌ፦ “ዐውቆት ኖሮአለ/ዐውቆት ኖሯል” ወይም “ዐውቆት ኾኖ አለ/ዐውቆት ኾኗል”። ይልቁንም እሊህን ግሦች
ካረባናቸው በዃላ ረዳትነታቸውን ለገዛ ራሳቸው ርባታ ብንጠቀመው (በዋና ግሥነታቸው መደብ
ማለት ነው) እንዴት እንደምንጠልቅ ተመልከቱት፦ ኖሮ ኖሮ አለ/ኖሮ ኖሯል፣ ነብ፟ሮ ነብ፟ሮ
አለ/ነብ፟ሮ ነብ፟ሯል፣ ኾኖ ኾኖ አለ/ኾኖ ኾኗል!
2. ወደተነሣኹለት ዐተታ ልግባ
የጊዜ እና የህላዌን ነገር በቀጥታ እንድንዳስስ የ“ሀለወ”ን ፍች “አእመረ = ዐውቆ አለ (ዐውቆኣል)”
በሚለው የጠቢብ ርባታ አካኼድ ብቻ እንውሰድና ምርምራችንን እንቀጥል።

ሀለወ = ኖሮ አለ (ኖሮኣል)። ለዘመናውያን ተመራማሮች የበለጠ ለማቅረብ፤ የዚህን አካኼድ
ተመጣጣኝ

(equivalent)

አገባባቸው

(ሰዋስዋቸው)

ባመዛኙ

ጊዜ-ተኮር

(tensal)

በኾነው1

በአልማንኛ አና በእንግልጣርኛ ምን እንደሚመስል እንይ፦
German: “ist gewesen” = English: “has been”
ይኸንንም ይዘን፦
3. አኹን ወደ ዐይነተኛው ነገር ጠልቀን እንግባ

In German language, an adjective can be derived from the infinitive “Sein” (to be), it
is: das Gewesene (that which has been)
When we derive abstract noun from these, we get: Gewesenheit = Having-been-ness
Hence:
Sein ist gewesen Gewesenheit = to be that which has been having-been-ness
በተመሳሳይ ኹናቴ ከ“ሀለወ” ቅጥል (adjective) እና ረቂቅ ስም (abstract noun) ስናወጣ ባማርኛም
ስንፈታቸው የሚከተሉትን እናገኛለን፦
ሀለወ  ህልው  ህልውና/ህሉና = ዐማርኛው በየዋህ ርባታ መንገድ ከኼድን፦ ኖረ  የኖረ 
የኖረ-እነት ወይም አለ  ያለ  ያለ-እነት ነው። በጠቢብ ርባታ መንገድ ከኼድን ደግሞ፦ ኖሮ
አለ  ኖሮ ያለ  ኖሮ-ያለ-እነት ወይም አል(ቶ?) አለ  አልቶ ያለ  አልቶ-ያለ-እነት ነው።
በሰንጠረዥ ብናስቀምጠው፦

ግሥ  ቅጥል  ስም
ግእዝ

ሀለወ  ህልው  ህልውና/ህሉና

ዐማርኛ (የዋህ)

ኖረ  የኖረ  የኖረ-እነት
አለ  ያለ  ያለ-እነት

ዐማርኛ (ጠቢብ)

ኖሮ አለ  ኖሮ ያለ  ኖሮ-ያለ-እነት
አልቶ አለ  አልቶ ያለ  አልቶ-ያለ-እነት

1

የ ኛ ባ መዛ ኙ አ ካ ል -ተኮ ር (personal) ነ ው።

ረቂቅ ስም አወጣጡ ላይ ባማርኛ የተለመደው ግን ያው ግእዙን እንዳለ መውረስ ነው። ህልውና
እንጂ የኖረነት/ያለነት ወይም ኖሮያለነት/አልቶያለነት ሲባል አይሰማም። ኾኖም በየዋህ መንገድ
ላገኘነው ረቂቅ ስም የጀርመንኛ እና የእንግሊዝኛ አቻዎቹ Seindheit እና Beingness እንጂ
Gewesenheit እና having-been-ness ሊኾኑ አይችሉም። ስለዚህ ከህልውና ይልቅ በግልጥ
ፍጽምናን-ከቅድምና-አጣምሮ-የሚያሳየን (apriori perfect) በመሠሪ ርባታ ያገኘነው “ኖሮ-ያለእነት” የሚለው ዐማርኛ ነው። ይኽንን ቃል ላንደበታችን ለማመቻቸት ስሞክር ወደሚከተለው
ደርሻለኹ፦ ሸመነ ብሎ ሸማኔ፣ መጨነ ብሎ መጨኔ እንደሚለው ኖሮ-አለ ብሎ ኖሮኣሌ
ቢልስ፤ እናም “እነት” ሲጨመርበት “ኖሯሌነት” ቢባልስ፤ አያስኼድም ይኾን? በርግጥ የተሻለ
ስልት ሊገኝ ይችል ይኾናል (ይችል-ይኾን-አለ)፤ ኾኖም ለጊዜው የኽንኑ ብንወስድ፤ እንግዲህ
ለጀርመንኛው

“Gewesenheit”

ወይም

ለእንግሊዝኛው

“having-been-ness”

ያማርኛው

“ኖሮኣሌነት” አቻው ነው ማለት ነው። ወይም የግእዙን “ህልውና/ህሉና” ይኽንን ስሜት ጭኖ መያዝ
ነው።
ዋናው ቊልፍ ነገር፦ “እነት”ን (ህላዌን) በጊዜ አድማስነት ማየት ነው። ወደማይለወጥ “ምን”እነት
(“what-ness”) ከሚያመራ የ“ንብረት” ስሜት (essentialism) ለመራቅ። ለዚህ ግንዛቤ የሃይዲገር
ዕዳ አለብኝ። ኾኖም ግን ሃይዲገር ወደደም ጠላም ዕሳቤው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነውና ለኢትዮጵያዊ
ትውፊታችን ፍጹም ባዕድ ኾኖ እንዳላገኘኹት ለመጠቆም እወዳለኹ።

ምስክር፦ አረቦን።

የሃይዲገር አረቦናዊ የጊዜ ግንዛቤ (kairological concept of time) ከቅዱሳት መጻሕፍት የተወረሰ
መኾኑን ብዙ ምሁራን አረጋግጠውልናል። “kairos” በሐዲስ ኪዳን ለአረቦን እኩያነት የተወሰደ
የጽርእ

(የግሪክ)

ቃል

ነው።

አረቦንም

(arrhavon)

ዕብራዊ

ትውፊት

መኾኑን

ማሳያዎች

ሞልተዋል። ነገር ግን ዛሬ ወደዚያ ለመግባት ዐሳብ የለኝም። ወደርእሰ ነገራችን እንመለስ።
በጊዜ እየተፈጸመ የመጣ ድልብ፤ ምናልባት ትርጕሙን በተለየ መልኩ ማየት እንጂ መነበ፟ሩን
በምንም በምን ሊያስቀሩት የማይቻል የማይለቅ ባሕርይ ነው። ኀላፊውን ትተን መጻኢውን ብቻ
ለመመልከት ብንሻም፤ ያለግድ በውድ ተቀብለን ኾነን ነውወነው በውስጣችን ልናሳልፈው ወይ
ያለውድ በግድ ተጭኖብን ሳንኾን ነውወነው በላያችን ሊያልፍ ኖሯሌነት ቅሉ በመጻኢው ውስጥ “ርስ”
(ርእስ) ኾኖ ይጠብቀናል። ፍጹም ልናመልጠው አንችልም። እንዲህ ስለኾነ ግን፤ አንዳችም ለውጥ
እንደማያገኘው “ጕል፟ት ንብረት” (reified essence) አናየውም። ኹሌ መንገድ ላይ ነንና። ጊዜ
ይቀጥላላ። የዚያ ባሕርይ ተሸካሚም ለነገ ክፍት ነዋ። ይኽም ብቻ ሳይኾን፤ ኖሯሌነትን ገንዘብ
የምናደርግበት ውሳኔም እየጊዜው እየቅሉ እየ“ርሱ” ነውና። በተለይም ግእዛን (ነጻነት) ላለው “ነየ
በሀሊ” (እነሆኝ ባይ) ፍጥረት (fürs Dasein)። እንዲህ ያለ ፍጥረት፦ ባለቤት በጉን አርዶ እና
አወራርዶ እንደሚበላ ሳይኾን፤ እረኛ በግን እንደሚያስወጣ እንደሚያስገባ፣ እንደሚጠብቅ፤ ኑሮን
የሚያስወጣ የሚያስገባ፣ ኑሮን የሚጠብቅ ስለኾነ፤ ሃይዲገር “Herr des Seins”/“Lord of Being”
(እግዚአ

ህላዌ/የኑሮ

ጌታ)

ሳይኾን

“Hirte

des

Seins”/“Shepherd

of

Being”

(“ኀላዌ-

ህላዌ”/የኑሮ እረኛ) ብሎታል። የበግ እረኛ የበጎቹን ድምፅ ለይቶ ማወቅ እንዳለበት፤ የኑሮ እረኛም
የኑሮን ድምፅ ለይቶ ማወቅ አሀልዎ/“መ-አሀለው”/ማስኖር (to let be) ይጠበቅበታል።
ይችን ጨምሬ ላብቃ፦
ህላዌ/ኑሮ (Being) በብቻ ዘርፋጣ ንብረት (Essence) አይወሰንም። በብቻ2 ልቅ ቁመተ-ሥጋም
(Existence)

አይወሰንም።

ተረክቦው

“ኹሌ’ኮ”/“ኹለዬ

እኮ”/“ኹለጊዜ

ቢያ”

(immer

schon/always already) ቅድምና-ያለው-ፍጹም (apriori perfect) ኖሮ፤ ገና ይኖር ዘንድ
ያለውም (zusein hat/to have to be) ነው። በዚህ መኻል እኛን የሚያገባን ነገር ምንድር ነው
ቢባል፤ የህላዌን ገናኛ ክሂል (possibility) ተገንዝቦ በየጊዜው በየበኵላችን እናኾን ዘንድ ያለንን
ነቅቶ ተግቶ የማኾን ድርሻችን ወይም ተኝቶ ሰንፎ ያለማኾን ቸልታችን ነው። አኹንን የማኾን ወይ
ያለማኾን። ይህ እንዲህ ነው፤ ይኹንና፦
ወውእቱ ይዌልጥ ዓመታተ ወመዋዕለ።
ሌሊቱን በመዐልት፣ መዐልቱን በሌሊት፤ ሰኞን በማግሰኞ፣ ማግሰኞን በረቡዕ፤ በጋውን
በክረምት፣ ክረምቱን በበጋ፤ ሉቃስን በዮሐንስ፣ የሐንስን በማቴዎስ፤ የሚለውጥ…
ፄዋዌን በሚጠት፤ ዓመተ ደዌን በዓመተ ጥዒና፣ ዓመተ ጥዒናን በዓመተ ደዌ፤ መዋዕለ
ኀዘንን በመዋዕለ ፍሥሓ፣ መዋዕለ ፍሥሓን በመዋዕለ ኀዘን፤ የሚለውጥ እሱ ነው።
እግዜር።
ትንቢተ ዳንኤል ፪፡፳፩
ክብር ምስጋና ለርሱ ለባለቤቱ ይኹን።

እንኳን ለዘመነ ማቴዎስ አደረሰን።
ፍሥሓ ታደሰ ፈለቀ
ድ.ክ.፦ “ነያ ትሄሉ ኢትዮጵያ” የሚለውን መዝሙር ጋብዣችዃለኹ።

“ብቻ” የ ምትባ ለ ውን ቅ ጽል “ይኽም ስ ም [ክ ር ስ ቶስ ] ብቻ የ መለ ኮ ት ብቻ የ ትስ ብእ ት አ ይደ ለ ም…” እ ን ደ ሚለ ው ባ ለ የ ጥን ት
ዐ ማር ኛ አ ነ ጋ ገ ር የ ተጠቀ ምኹት “እ ን ዲህ ብቻ/እ ን ዲያ ብቻ” በ ማለ ት እ ና “ብቻ እ ን ዲህ /ብቻ እ ን ዲያ ” በ ማለ ት መካ ከ ል ስ ስ ም
ቢኾን የ ምስ ጢር ልዩ ነ ት ያ ለ ስ ለ መሰ ለ ኝ ነ ው። የ ፊ ተኛ ው “only” እ ን ደ ማለ ት የ ዃለ ኛ ው ደ ግ ሞ “alone” እ ን ደ ማለ ት
ይኾን ?
2