You are on page 1of 21

የመሰከረም 2006/September 2013 ልዩ እትም – ዕንቁጣጣሽ – II /06-09-1

ዕ ን ቁ ጣ ጣ ሽ (ርዕሰ አንቀጽ)

መስከረም ሲጠባ …. ሸ ን ጎ -

“አዲስ ትውልድና አዲስ ዘዴ :-ስውር ኮሚቴ! “ ይላል መጻጽፉ

ሰነዶችና መረጃዎች

„ዓለም /አፍሪካ እንዴት ሰነበተች“- DW

LALIBELA / ላ ሊ በ ላ -

የመስከረም 2006/September 2013 ልዩ እትም * ዕንቁጣጣሽ *

ዕ ን ቁ ጣ ጣ ሽ (ርዕሰ አንቀጽ)
Published September 9, 2013
← Previous

ዕ ን ቁ ጣ ጣ ሽ (ርዕሰ አንቀጽ)

*ዕ ን ቁ ጣ ጣ ሽ*
አንድ የሚያደርገንና አንድ ያደረጉን ነገሮች ብዙ ናቸው።
አንደኛው አለጥርጥር ዕንቁጣጣሽ ነው። ይህን የሚክድ ሰው ከአለ ኢትዮጵየዊ
እሱ/እሱዋ አይደሉም። ቀልዱ እዚህ ላይ ያቆማል።
ኢትዮጵያን በዚያውም እኛን አንድ የሚያደርግ ነገር ቢኖር ይህ ዛሬ ሁላችንም
የምናከብረው አዲሱ አመት ነው።
ሁለተኛው የሰዓት አቆጣጠራችን ነው። ሶስተኛው ልዩ የሆነው የምግብ
አሰራራችን ነው። አራተኛው የዘመን መቁጠሪያችን ነው። ቅርጫና በመሶብ
ዙሪያ አብሮ መብላትም አለ።
አምስተኛው ምርቃቱም ነው። ከሁሉም የምናምንበት አሃዱ አምላከችንም
አንደኛውና መዚጊያው ነው።
ስድሰተኛውና ሰባተኛው፣ ስምንተኛውና….ዘጠነኛው….

የቡሄና የገና ጫዋታ፣ …አበባዬ ሆይ፣ ሙዚቃው፣ ትዝታና ሰርጋችን፣ ዕድር
ዕቁባችን (…በአንዳንድ ነገር የተበሳጩ ልጆች፣ ሌላ ጊዜ ፈልገው በአገኙት ነገር
ተደስተው ያናደዱአቸውን ጓደኞቻቸውን መልስው በተራቸው ሲያበሽቁ „ኤቺ
ቤቺ…ይኸው እየው፣ ተመልከተው፣ … እኔም አለኝ…“ ልጆች ተንኮለኛ ናቸው
እዚህ ይላሉ) እነዚህ ሁሉ አንድ የሚያደርጉን ነገሮች ናቸው። በዚህ አያቆምም
ሌሎቹም አሉ።
የሆነው ሁኖ፣ እነዚህ ሁሉ ባህሎቻችን እኛን ከሌሎቹ እንደለ „ፍጹም ልዩ“
ያደርጉናል።
አዋቅረው አያይዘው አንድ አድርገው የያዙን ብዙ ናቸው። ይህ ደግሞ ቢሉት
ቢገፉት፣ ለመፋቅ ቢሞክሩት አይፈቅም። ይህ በቀላሉ አይሰረዝም። ይህ
ከአእምሮ አይጠፋም። ይህ ወደዱም ጠሉም ሕያው ሁኖ ለመጪው ትውልድም
የሚተላለፍ ባህል ነው።
አንድ ጊዜ ከጸሎት በሁዋላ አዲሱን አመት ለማክረበር ወደ አንድ አዳራሽ
ተያይዘን ስነገባ አንድ እንግዳ ፈረንጅ እኛን አይቶ የማያውቅ (ይመስለኛል ከሴት
ጓደኛው ጋር አብሮ የመጣ) ሲተዋወቀን የአንዱን ጓደኛችንን ስም መሓመድ
መሆኑን ሰምቶ ተገርሞ „…እንዴ እርሶም እዚህ ይመጣሉ እንዴ?“ ብሎ
ሲጠይቀው“ እኔ እኮ ጌታዬ ሞስሊም እንጂ አረብ አይደለሁም „ ያለው መልሱ
አይረሳም።
በሁዋላ በደመራ በመስቀል በዓል ላይ ይኸው ሰው፣ ሌላውን „ሐሰን“
የሚባለውን አንዱን ኢትዮጵያዊ ያገኘዋል። ምን እንደተባባሉ መገመት
ለአንባቢው መተው በቂ ነው።
ክርስቲያኑም እስላሙም፣ አይሁዱም ጭምር (እነሱ ቤተ-እሥራኤሎቹ አሁን
ወጥተው አልቀዋል ይባላል) አዲሱን አመት አብረው አንድ ላይ ያከብራሉ።
የዶሮ ወጡ አንድ ነው። የቡና አፈላል ሥርዓቱ ( ሌላ ሳይሆን ) አይለያይም

ያው አንድ ነው።

የጠላ አጠማመቁ፣ የጤፍ እንጀራው፣ ፍትፍቱ፣ አገልግሉ፣ (ልጆች ምን ይላሉ
እንደዚህ ዓይነቱን ነገር ብለናል…ኤች ቤች!) ድፎ ዳቦው፣ ሽሮው፣ በርበሬው፣ …
የሸማ-ልብሱ፣ ጥጡ(ቀለሙ ይለያይ እንጂ) ነጠላው፣ ጋቢው፣ ቡሉኮው፣
ፈትሉና ሸማኔው ያው አንድ ነው። ቅመሙም አንድ ነው። ኢትዮጵያም
የቀመመችበት ቅመም፣ ምሥጢሩም ይኸው ነው። ግን ደግሞ የአንድነታችን
ምሥጢሩ ከዚህም አልፎ ይሄዳል።
የቤተ-ክርስቲያኑን ቁልፍ እስላሙ በታመኝነት ተረክቦ ይጠብቃል። አጎቱና
አክስቱ እስላም ወይም ክርስቲያኑ የሆኑ ጥቂት አይደሉም። በጋራ የጉልበት ሥራ
በደቦ ድሮም አሁንም ኢትዮጵያኖች ይገናኛሉ። ይረዳዳሉ።
አብረው ያጭዳሉ። በጋራ መንገድ ይጠርጋሉ። በአማርኛ ቋንቋ ይነጋገራሉ።
ይገበያያሉ። እንቅፋት ሲመታቸው የማይተዋወቁ ሰዎች መንገድ ላይ
„ወንድሜን“ ይባባሉ። ሲያስነጥሰው „ይማርህ/ይማርሽ „መንገድ ላይ ሰላምታ
ይለዋወጣሉ። ይህ የት ቦታ አለ?
በዛሬው ዕለት ደግሞ ልጆች ተሰብስበው፣ ዘር ሳይቆጥሩ ፣ ሐብት
ሳያራርቃቸው፣ ሃይማኖት ሳይሉ፣ በአንድነት „አበባዬ ሆይ“ ይላሉ።
ጎረቤት ጎረቤቱን ያምናል። ጓደኛ በአብሮ አደጉ ይተማመናል። …በፍቅር ላይ
የተመሰረተ የተደበላለቀ ትዳር በብዛት አለ። ከእነሱም የወጡ ልጆች በያአለበት
በየመንደሩና በየአገሩ ተሰማርተዋል። ተበትነዋል።
እንግዲህ ኢትዮጵያና ልጆቹዋ ድሮም እነደዚህ ነበሩ። ዛሬም እንደዚህ ናቸው።
ይህ ነው እኛን ኢትዮጵያቾችን ከሌሎቹ ለይቶ „ልዩ“ የሚያደርገን ነገር። ቢያንስ
በዚህ በመስከረም ወር አዲሱን አመት (2006ዓ.ም)የሚያከብር ሕዝብ እኛ ነን።
ይህ የት ይገኛል?
ሌሎች እኛን አንድ የሚያደርጉን ነገሮችም አሉ።
እሱም ለሰበአዊ መብትና ለነጻነት ያለን፣ ወራሪ ነጮች ግን ሊረዱት
የማይችሉት፣ የቆየ ጥማታችን እንዳለ ነው። ለዚህ በማይሸጠውና
በማይለወጠው ቀናተኛ የተፈጥሮ ነጻነታችንና መብታችን፣ አገራችንን ኢትዮጵያን
ከጣሊያን ወረራ፣ ከቱርክና አረቦች ሴራ፣ ከፖርቱጋል ሙከራ፣ …አባቶቻችን
አድነዋል።
አሁን የሚቀረው ደግሞ (ደግመን ደጋግመን የምናነሳው) ዕውነተኛው የግለሰብ
መብቶች እንደገና፣ ለመናገር ያ! አምላክ የሰጠንን የተፈጥሮ ጸጋ ሙሉ ሰበአዊ
መብታችንና ነጻነታችንን አለአንዳች አምባገነን ፍርሃቻ እሱን ማስከበር ነው።

ይህ ደግሞ አንዱን ከሌላው ሳይል አንድ የሚደርገን የ21ኛው ክፍለ-ዘመን፣
ግዳጅም ኃላፊነትም፣ መድረሻናግብም፣ የጉዞ መንገድም፣ የጋራ እሴትም ነው።
ይህን አስመልክተን ስለ ፓርላማ ሥርዓት (ስለ ሸንጎ) አንድ ጽሑፍ
እንድትመለከቱት አቅርበናል። እዚያም ላይ ስለ ሶሰት ሥርዓቶች አንስተናል።
ስለ ሃይማኖት አክራሪዎች መንግሥት፣ ስለጠበንጃ አንጋቢዎች ሥርዓትና ስለ
ዲሞክራቲክ ሕብረተሰብ፣ ከብዙ በጥቂቱ ዘርዝረን አልፈናል።
„አንድ ሕልም አለን“ ያ የእኛ የዘንድሮው ምኞትና ሕልማችን (እሱን እንናገር
ከተባለ) እዚያ የሸንጎ አዳራሽ ውስጥ የተለያዩ ስምና ቀለም ያላቸው ድርጅት
ተወካዮች ወንበሮቹን በምርጫ በአገኙት ድምጽ ተከፋፍለው ቦታቸውን
ሲይዙና፣ ተዝናንተው አዳራሹ ውስጥ ሲገቡና ሲወጡ ማየት ነው።
የተለያዩ ድርጅት ተወካዮች ከተከራከሩ በሁዋላ ቢራቸውንና ቡናቸውን
አብረው ተገባብዘው ሲጠጡ ማየት ነው።
ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?
ወረድ ብላችሁ ደግሞ ሌላውን ጽሑፋችንን ተመልከቱት።
እንደምናውቀው ፣ ሃይማኖትና ባህል፣ ልማዶችና የኑሮ ዘይቤዎች፣ ታሪክና
ምሳሌዎች….አንድን ሕዝብ አንድ የሚያደርጉ ክስተቶች ናቸው። ከእነሱ ጋር
የጋራ እሴትም/እሴቶችም የሰውን ልጆች አንድ ያደርጋሉ። አለበለዚያ
የአውሮፓን አንድነት፣ የአሜሪካና የአውሮፓ ሕብረት፣ የሰሜን አትላንቲኩን
የጦር ቃል-ኪዳን…ወዘተ መረዳት አይቻልም።
ከዚያ ውስጥ አንዱ እሴት ፓርላማና የነጻ ሰው መብት የሚለው ፍልስፍና ነው።
እንግዲህ ይህን እሴት አንስተን መልካም አዲስ አመት እንመኝላችሁዋለን።
መልካም አዲስ አመት ለእናንተም 364 ቀናቱን በሙሉ በተከታታይ „እኛ“
ኢትዮጵያዊ አይደለንም ለምትሉትም ወገኖቻችን ሁሉ አብረን እንመኛለን።
ምክንያቱም ቢያንስ-ይህ ነው መነሻ ሐሳባችን- የዛሬው የኢትዮጵያ የዘመን
መለወጫ ቀን ሁላችንንም አንድ ያደርገናል።
አንድ ሕልም አለን ያ ሕልምም ለመድገም „ማንም…ፖለቲከኛ „ነን የሚለው
ሰው ሁሉ አደባባይ ወጥቶ ተወዳድሮ በአገኘው ውጤት ፓርላማ ገብቶ
ወንበሩን ሲይዝ ማየት ነው።

ጠበንጃ እና ድርጅት ግን ከሁሉ በፊት፣ በመጀመሪያ፣ ልክ እንደ መንግሥትና
ሃይማኖት፣ ሁለቱ መለያየት ይኖርባቸዋል። መለያየትም አለባቸው።
የሰላም የጤና እና የዲሞክራሲ ዓመት።
——

የመስከረም 2006/September 2013 ልዩ እትም * ዕንቁጣጣሽ *

መስከረም ሲጠባ – ሸ ን ጎ – !
Posted on September 10, 2013 | Leave a comment

መስከረም ሲጠባ …..
-ሸንጎ-

አንድ ቀን መስከረም ይጠባል

„ስምህን ንገረኝና ማን እንደሆንክ እነግረኻለሁ። “ይህ አረፍተ ነገር ቢያንስ
ቅንጣት ያህል ዕውነት አለው። ቤትህን አሳየኝና ማን እንደሆንክ እነግረሃለሁ
እንደ ማለትም ነው።
…ወንበርህን ፣ …መጻሕፍትህን፣ መኪናህን፣ ወይም ጠረጴዛህን እስቲ ደግሞ
ለጥቂት ደቂቃ እሱን አሳየኝና ማን እንደሆንክ እነግረኻለሁ ሊሆንም
ይችላል። ሸሚዝንም ልንጨምርበት እንችላለን። …የቤት ሳህንም፣ ካለሲና
ጫማም ልናክልበት እንችላለን።
የሸንጎ ሕንጻም፣ ፓርላማም አንደዚሁ፣ ብዙ ነገር ይናገራል። ሌላው ይቅር ስንት
ተቃዋሚ እዚያ ውስጥ አለ የሚለው ጥያቄ -ምን አደከመን ወሳኝ ነው። ስንት?
አንድ መንግሥት፣ ያ ሕዝብ፣ እነዚያ የተለያዩ የሚፎካከሩ ድርጅቶችና
ፓርቲዎች የሚቀመጡበት ወንበርና ጠረጴዛ፣ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየው፣
አገሪቱ ለዲሞክራሲና ለግለሰብ መብት ያላትን ቦታና ክብር ነው።
በተለይ የወንበሮቹ አቀማመጥ፣ የአዳራሹ አሸናሸን፣ ለተለያዩ ፓሪቲዎች
የተሰጠው የቢሮዎቹ ክፍሎቻቸውና የጽሕፈት ቤታቸው፣ የስልኩ ብዛትና
የመደወል ነጻነት እነዚህ ሁሉ ወሳኝ ናቸው። የአንዳንዱ የአንደኛ ክፍል

ትምህርት ቤት ይመስላል። የሌላው እኩል የሆኑ ሰዎች የሚቀመጡበት ክብ
አዳራሽ።
ለመሆኑ ስንት ተቃዋሚ ናቸው አዳራሹ ውስጥ በሕዝብ ተመርጠው
እንዲቀመጡ „የተፈቀደላቸው?“ ለዚህም ጥያቄ የምናገኘው መልስ (ብዙ ቦታ
መንከራተት አያስፈልግም) በቂ ነው። አንድ ሰው ብቻ ሊሆንም ይችላል።

ተዘዋውሮ ውስጡን እየተንጎራደዱ ማየቱ ደግሞ፣ አንድን ጎብኚ እንዴት ደስ
ያሰኘዋል።
ቪላዲሚር ኢሊች ሌኒን ግን በአንድ አረፍተ ነገር“…የቀባጣሪዎች የጫጫታ ቤት
ብሎ…“ ሁሉን ነገር ጨርሶታል። እሱም ያ ዲሞክራሲን አመጣላችሁዋለሁ ብሎ
ለዘመናት ቅስቀሳውን የለቀቀ ሰው፣ ብድግ ብሎ ሁሉንም አባሮአቸዋል።
ሒትለር መጥቶ ደግሞ ይህን „የአእምሮ መቅደስን“ እሳት ለኩሶበት፣
አቃጥሎት፣ ከእንግዲ ምን ትፈልጋላችሁ ሂዱ ከዚህ ብሎ የሕዝብ
እንደራሴዎቹን በትኖአቸዋል። ሌኒን ወደ ሳይቤሪያ ሲልካቸው፣ ሒትለር እሥር
ቤትና የጋዝ ምድጃም ውስጥ ነድቶአቸው አጋይቶአቸዋል።
እንዴት ደስ ይላል የታላቁዋን ብርታኒያ ምክር ቤት ውስጥ አንድ ተመልካች
ማንንም ሳይፈራ (…ሌላው እኮ ጠበንጃውን አቀባብሎ „ ወንድም ሳትበላሽ ዞር
በል ከዚህ“ ብሎ ከእሩቁ መንገድ ላይ አፍጥጦ ከዚያ አካባቢ ፎቶግራፍ
ለማንሳት የቆመውን ያባራል!) በዓይኑ የለንደኑን አዳራሽ ሲቃኝ።

ሲከራከሩ እዚያ ውስጥ ተቀምጦ ማየቱ አንጀት ያርሳል። የሕዝብ እንደራሴዎች
(የተለያዩ )“…እሰጥ አገባ „ ሲሉ፣ ቆይተው ሄ..ሄ… ብለው የተናጋሪውን ሐሳብ
አጥላልተው ውድቅ ሲያደርጉ፣ ተጋፍተው ወደ አዳራሹ ሲገቡ፣ እንደተማሪ
እየተሳሳቁ ተጋፍተው ሲወጡ ፣ እላይ ሠገነቱ ላይ ተቀምጦ መስማቱና መየቱ
በጣም ደስ ያሰኛል።

የዋሽንግተኑ ኮንግሬስ፣ የጀርመኑ ቡንደስ ታግ፣ የፈረንሣዩ ናሽናል አሴምብሊ፣
የቶኪዮው፣ የማድሪዱና የሊሳቦኑ፣ የሮማውና የሩሲያውን፣ የፔኪንግና
የዴሊውን፣ ከእነሱም ጋር የአዲስ አበባውንና የደቡብ አፍሪካውን፣ የቤላ
ሩሲያን እና የ… አወዳድሮ፣ አነጻጽሮ ማየቱ:-ቱርስት መሆን አያስፈልግም የቤት
ቴሌቪዥንም ይበቃል- ትምህርትም ይሰጣል። መንፈስንም የአንዳንዶቹ ሥራ
ደስ ያሰኛል።
እንዱ ተነስቶ ሌላውን በቡጢ የሚያጣድፍበት ቦታም አለ። ደፋሩ ገላጋይ
መሓል ገብቶ፣ አንተም ተው አንተም ተው እያለ ሲወራጭም፣ በአንድና
ከአንድም በላይ በሆኑ ሁለት፣ ሶሰት የሸንጎ አዳራሾች ውስጥ፣ በተለያዩ ቦታዎች
አይተናል። ተሳዳቢ „ጠቅላይ ሚኒስትርም“ አለ። ሲቀልድም ሲያሾፍም ብዙ
ጊዜ ተቀርጾ ለሕዝብ እንደ ትልቅ ቁም ነገር ተላልፎአል ። የሚጠይቀው ሰው
የለም። የሚቆጣው።

ጢፊውን ሲቀምስ ደግሞ ገላጋዩ፣ እሱም መልሶ አጠገቡ ያገኘውን
ሲያጠናግረው – የሆሊውድን የሰከሩ የካው ቦይ ፊልምን፣ የባለጌ ልጆችን
ግርግር በትንሹም ቢሆን ያ ሁኔታ ያስታውሳል።
አንዳንዱማ
ሸንጎ
ውስጥ
በየጊዜው
(ትኩስ
ደም
የአላቸው
ይመስላል) ይተናነቃሉ። አጸያፊ ቃላቶችን –እንደ የሰለጠነ የሕዝብ እንደራሴ
ሳይሆን- አሳዳጊ እንደ በደላቸው የባለጌ ልጆች አዳራሹ ውስጥ፣ የማይሆን ነገር
ይወረውራሉ።
ስፔን ውስጥ የጠገቡ ወታደሮች አንዴ አዳራሹን በጥሰው ገብተው የሸንጎ
አባሎቹን ካሜራው እየቀረጸ፣ „…ሁላችሁም ተንበርከኩ! „ ሲሉ አንዱ ደፋር
ተነስቶ“…እስቲ ተኩስ“ሲለው አይተናል።
ንጉሡም፣ ሁዋን ካርሎ፣ ለሕዝቡ ብቅ ብለው በአደረጉት ንግግር“
አልቀበላችሁም“ ብለው እነሱን አዋርደዋል። እስፔን ከአምባገነኖች መዳፍ
እንደገና አምልጣለች።
ሌሎቹ የቴለቪዥን መድረክ ላይ ወጥተው፣ ክርክሩና ክሱ ሲጠነክርባቸው
ከቃላት ጨዋታ ይልቅ፣ ቡጢና ትግል መርጠው ፣ አሰተናጋጅ ጋዜጠኛዋንም

ዞር በይ ብለው፣ ገላጋይ እሰከሚደርስ ድረስ በቦክስ ተቃዋሚያቸውን
ሲያጣድፉ ከአንዴም ሁለቴ ተመልክተናል።
በሌላ በኩል የሰለጠኑት፣ “ተቆንጥጠው ያደጉት“ ሳይፈሩ ከመቀመጫቸው
ብድግ ብለው ጠቅላይ ሚንስትራቸውን በጥያቄና በመልስ፣ በትንትናና በፌዝ
መልስ እየሰጡ ሲክከሩም እኛ እነሱን እዚህ ተከታትለናል።
የሸንጎ ታሪክ ብዙና እንደሚታወቀው ረዥም ነው።
ከሁሉም የሚደንቀውና የሚገርመው እንዲያውም ዜናውን ሲከታተሉት ደስ
የሚለው ከአንድ አመት በላይ የሚፈጀው የሰሜን አሜሪካኖቹ የፕሬዚዳንት
„የማጣሪያ ምርጫ“ ነው።
አለ
ጥርጥር፣
የእነሱ
ድካም፣
ከማራቶንን
እሩጫ
ጋር
ይመስላል። የኦለምፒኩንም በአለ አሥር፣ የፉክክር ሜዳ ውድድር …የአሎሎና
የጦር ውርወራ፣ የወሃ ዋና እና ዝላይ… ችሎታን የአሜሪካኑ ሥርዓት በደንብ
ለተከታተለው ሰው፣ እሱን ያስታውሰዋል።
የኦባማ አመጣጥ፣ የሒለሪ ክሊንተን ግትርነት (እኛ ጋ እኮ አንዱ ተነስቶ
ሌላውን ሻለቃው አንዴ እንዳሉት ቁርስ ያደረገዋል) የሁለቱ እጩዎች ከመንደር
ወደመንደር፣ ከእስቴት ወደ እስቴት ድጋፍ ፍለጋ መሯሯጥ፣ በሁዋላ እፎይ
ብለው አንድ ላይ ሁነው ተስማምተው ሪፓብሊካኖቹን መግጠም፣ … በጋራም
ቆመው እነሱን ማሽነፍ ፣ እሱ የፕሬዚዳንትነት ወንበሩን ፣ እሱዋ የውጭ
ጉዳይ ሚኒስትር ቦታን መያዝ

„ደም ሳይፈስ“ ይህን ሁሉ ማየት እጅግ ደስ አያሰኝም?
የተሸናፊው:- ይህ ነው ሁሌ የማይረሳ – የጆን ማኬን ግሩም ንግግር ( ኦባማ ያኔ
የመጀመሪያው የአሜሪካን ጥቁር ፕሬዚዳንት ሁኖ መድረኩ ላይ አሸንፎ

ከባለቤቱ ጋር ይደንሳል) “… ከዛሬ ጀምሮ ባራክ ሁሴን ኦባማ የእኔም
የእናንተም፣
የአሜሪካኖች
ሁሉ
ፕሬዚዳንት
ነው።
መሸነፌን
እቀበላለሁ። እናንተም ተቀበሉት …“ አዛውንቱ ማለታቸው (….አፍሪካ ቢሆኑ
እኝህ ሰው አለ ጥርጥር ቁርስ ናቸው) ልብ ይበላል። ለምን ይደማመጣሉ?
የጃፓኖቹ ፖለቲከኞች የአክብሮትና የዝቅታ ሰላምታ ሲመለከቱት የእኛን ባህል
ያስታውሳል። የታይላንዶቹ ሚኒስትሮች ግን ንጉሡን ሲያዩ መሬት ላይ ወድቆ
መንከባለል ያሳፍራል። የአንዳንድ ጠቅላይ ሚኒስትሮች የደፈረሰ ዓይን… በሌላ
በኩል እሱን ማየቱ እጅግ ይገርማል። አንዳንድ ጊዜማ ያስፈራል።
እንደባህሉ፣ እንደወጉ ነው። ያም ሆኖ ይህ መሆን አለበት?
የማይረሳውና መጨረሻ የሌለው የብረዢኔቭ እና የሆንከር ዲስኩርም አለ። …
የካስትሮና የፔኪንጉ ኮሚኒስቶች፣ … የስድስትና የሰባት፣ የስምንትና የዘጠኝ
ሰዓት አሰልቺ ንግግር፣ ከዚያም ጋር የተወካዮቹ ተሰላችቶ ወንበራቸው ውስጥ
ማንቀላፋት፣ …በየጊዜው ማዛጋት፣ አፍንጫና ጆሮ መጎርጎርና ጥርስና ከንፈር
መጥረግ፣ እነዚህ ሁሉ በጣም የሚገርሙ ትርዕይቶች ነበሩ።
አሁንም አሉ?
ነገሩም ተዛምቶ ኢትዮጵያ ገብቶ አራትና አምስት ሰዓት ድረስ ዲስኩሩ ገፍቶ
አንዴ እንደሄደ ይነገርለታል። ምን ለመሆን ? ብሎ የሚጠይቅም ሰው
የለም። „ቁርስ ለመሆን“ ያበደም ሰው የለም። ያኔ ደግሞ መንግሥቱ ኃይለ
ማሪያም፣ ይህን አይቶ፣ ገብቶት አንዱ እንዳለው „ያጓራ“ ነበር። ሲከቡት ግን
ብድግ ብሎ ጠፋ!
ነፍሱን ይማረውና ጋዜጠኛው ተፈራ አሥማረን „ …ለመሆኑ የአራቱንና
የአምስቱን ሰዓት የኮነሬሉን ንግግር እንዴት አድርጋችሁ ሰብሰብ አድርጋችሁ
(ኤዲት) ታደርጋላችሁ? ሰውዬው ያ ቀረ፣ ይህ ጎደለ ብሎ ተቆጥቶ
አይቀጣችሁም እንዴ?“ ሲባል፣
„….አብዮተኛው መሪ በአደረጉት ትልቁና ሰፊ፣ ትክክለኛው ሳይንሳዊ
ትንተናቸው፣ ብለን ስንቀባበውና አየር ላይ ስንለቀው….እራሱ ምን እንዳለ፣
እሱ እራሱና ተከታዮቹ ጭምር ምን እንደተባለም አያስታውሰውም …“ ብሎ
አጫውቶኛል።
ሥዩም ወልዴም በዘመኑ ግሩም ነገር ተመልክቶ ነበር።
የእሱንም ነፍሱን ይማረውና ጸሓፊው ሥዩም ወልዴም „…ግራ ጌታ አማረ፣
…የቀኝ ጌታ መላኩ „ በሚለው ግሩም ግጥሙ (ይህ ወረቀት የት እንዳለ

እግዚአብሔር ይወቀው) የአውሮፓ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማህበር ገና „
ሳይበታተኑ“አንድ ላይ በነበሩበት ዘመን፣ በበርሊኑ የኦለምቲክ ስታዲዮም
አዳራሽ ፣ ያኔ ሲከራከሩ ቢያንስ „የፓርላማ ሥነ-ሥርዓትን ቅደም ተከተል“
መሰረት አድርገው:- እነሱ ብቻ ሳይሆኑ ሌሎቹም፣ የአዳራሹን ግራና ቀኝ ይዘው
ይፋጩ ነበር።
አዲሱን ተመልካች „ግራም ያጋቡ“ ነበር።
በዚያን ዘመን አንዱ የደረሰበትን የሓሳብ „መዋዠቅም“ በአንዲት
ጀልባ፣ አስመስሎ እሱና ጓደኞቹ በዚያች ጀልባ ውስጥ የደረሰባቸውን ሁኔታ
እንደዚህ አድርጎ አጣፍጦ ያ ጎልማሳ አስቀምጦት ነበር። … ይባላል ያ ጎልማሳ?
አንዱ ተነስቶ ይላል ይኸው ሰው ሲያጫውተን“ …ግራ ጌታ አ… ተነስቶ…እኛ!
የምንለው፣ … እኛ! የምንፈልገው፣ ….እንደዚህና እንደዚያ አይነቱን ነገር
ነው። ከሁሉም በፊት ያ በመጀመሪያ መደረግ አለበት። ቅደም ተከተሉ
እንደዚህ ነው። …ይህ መሆን አለበት ብሎ ተንጠራርቶ ፣ ግራና ቀኙን
ረግጦ፣ ጀልባዋን እነደዚሁ ወደ ግራና ወደ ቀኝ ቀዝፎ ፣ እሱ እንዳለው ከአሁን
አሁን እዚያ ጣለን ስንል፣ ቀልበስ አድርጎ ወደ አንዱ ወገን ወርውሮን፣ እኛን
እዚያ ጥሎን ይሄዳል። እፎይ ብለን ዐየር ስበን ትንሽ አረፍን ብለን ስንዝናና
ደግሞ፣
ሌላው ፣ ቀኝ ጌታ መ… በተራው ተነስቶ፣ … ይህ አይቻልም። ያም ሊሆን
አይችልም።
ስለዚህ ይህ ነው ትክክለኛው መንገድ። ያኛው
አያዋጥም፣ እንደዚህ፣ እንደዚያ ነው! ብሎ ቀዝፎ ወዲያና ወዲህ
ረግጦ፣ አሳምኖ ጀልባዋን እንደገና ወደ ግራና ወደ ቀኝ ወደ ፊትና ሁዋላ ቀዝፎ
ወደ አንደኛው ወገና ዘንበል አድርጎን እሱም በተራው ሌላው አፋፍ ላይ
ወርውሮን ይሰወራል።
ገና ፋታ አግኛተን ሳናርፍ ሦስተኛው ይነሳና …ወደዚያና ወደዚህ በአነጋገር ስልቱ
በጨዋታ ቀልዱ፣ በፌዙና በምሳሌው አዋክቦንና አንገድግዶን መሓል መንገድ
ላይ ጥሎን ዞር ይላል። …አራተኛው ወደ ግራ ጎትቶን አውላላ ሜዳ ላይ በትኖን
ያመልጣል“ ብሎ (ለማሳጠር) ያ ወጣት (ዛሬ አዛውንት ሳይሆን ይቀራል!)
የደረሰበትን አጫውቶናል።
አካሄዱም ሳይበስል፣ ትምህርቱም ሳይገባደድ፣ በርካታ በቂ ዕውቀቶች
ሳይሰበሰቡ አብዮቱ ፈንድቶ፣ ወታደሩ ሥልጣኑ ላይ ጉብ ብሎ „…በመሪ ጌታ
ሌኒን የተነደፈውን ፣ አዲሲቱን ሶሻሊስት ኢትዮጵያን ለመመሥረት እሩጫው፣
በገጠሩም በከተማውም ይጀመራል። “

ይህ አነደኛው መንገድ ነው።
በሌላ በኩል „የብሔር ብሔረሰብ ትግል እሰከ መገንጠል“ የሚለውን ገመዱን፣
በመሪጌታ ስታሊን የተነደፈውን ዓላማ፣ (ይህ ግልጽና የታወቀ ነው) በሌላ
አቅጣጫ ብድግ ብሎ ይጎትታል። ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ
ትግርኛ፣ ኦጋዴን፣ በሁዋላም አማራ ይባላል። ይህ ሁለተኛው መንገድ ነው።
በዚህ የተጀመረውጉዞ፣ በዚሁ እንግዲህ አንዱ እንዳለው የኢትዮጵያ ነገር
አለቀላት። „አዲሱን ዳቦ ለመጋገር „ ይኸው ሰው አክሎ ያኔ እንዳለው
„ሊጡም፣ ተቦክቶ፣ ምጣዱ ላይ ተዘርግፎ (ኢትዮጵያ ላይ) ተጋገረ“።
ይህን ያዩ ፣ አሜሪካ በአንድ በኩል፣ ሩሲያ በሌላ በኩል፣ መንደሮቹን
ተከፋፍለው ነገሩ ውስጥ ዘለው ገቡበት። የሸንጎ፣ የፓርላማ- ሥርዓት
አንዳንዶቹ እነደ ተመኙት በዚሁ ተቀጭቶ፣ ሐሳቡ ተኖ ቀረ።

ሶስት ሥርዓቶች በ21ኘው ክፍለ-ዘመን፣ በሶስተኛው ዓለም፣

ገነው

ወጥተዋል።
አንደኛው የኢራኑን „የሃይማኖት አባቶች“ የሙላዎቹ የእነ አያቶላ አነሱ
እንደሚሉት „የአላህ መንግሥት“ ነው።
ይህንና ከአዚሁ በምንም የማይለየውን „የካሊፋት ሥርዓትና መንግሥት“
ከሞሮኮ እስከ ፓኪስታን፣ እስከ እንዶኔዢያ፣ እስከ ሞንጎሊያ ያሉ የሞስሊም
ሃይማኖት አክራሪ ተከታዮች ተመሥርቶ ማየት ይፈልጋሉ።

ሁለተኛው በጠበንጃ የበላይነት የሚያምኑወታደሮችና የጦር ኃይል
ባልደረባዎች፣ እነዚህ የፈለጉትን ስም ይያዙ፣ ነጻ-አውጪዎችም ሊሆኑ
ይችላሉ፣ በብዙ ቦታዎች በጠበንጃ ኃይል የመሰረቱት „ሥርዓትና መንግሥት“
ነው።
ይህም ብዙዎቹ እንደሚሉት „በነጻ-አውጪዎች“ ስም ተደራጅተው ሥልጣን
የያዙትንና ለመያዝ የሚፈልጉትን ድርጅቶች ሁሉ በተለይ በአፍሪካና በእሲያ
በመካከለኛው ምሥራቅም ያሉትን አካባቢዎች ያጠቃልላል።
ቻይና አንደኛዋ ናት። ኡጋንዳ፣
ኤርትራ…እያለም ዝርዝሩ ይሄዳል።

ዚምባቡዌ፣

ሩዋንዳ፣

ኢትዮጵያና

ሶስተኛው፣
„ምድራዊው“ ወይም „ሴኩላር“ ወይም የግለሰቦችን
መብትና ነጻነትን (ቀለማቸውን ሳያይ፣ ዘራቸውን ሳይቆጥር፣ ጾታቸውን ከቁጥር

ወስጥ ሳያስገባ…ሐብታቸውን ሳይገምት) የሚያከብረውና የእነሱንም መብት
የሚንከባከው፣ ነጻና ዲሞክራቲክ ሥርዓት ነው።
ይህም ሥርዓት„በመንፈሳዊው“ ወይም „በአላህ“ ወይም ደግሞ በጠበንጃ ኃይልና
በእሱ የበላይነት ተማምነው ሥልጣን ላይ ወጥተው ሕዝባቸውን ምርኮኛ
ያደረጉትን፣ የአምባገነኖች፣ የቶታሊቴሪያን ሥርዓትን ይጻረራል።
የላይኛው ሁለቱ፣ ልክ በቅርቡ፣ እዚህ አውሮፓ ተንኮታኩቶ እንደ ወደቀው
የኮሚኒስቶች ሥርዓት፣ የሰውን ልጆች ጭንቅላት፣ የፖለቲካ አመለካከታቸውንና
አስተሳሰባቸውን፣ አካሄዳቸውንና አእምሮአቸውን ለመቆጣጠር የሚፈልጉ፣
ልቆጣጠርም ብለው የሚነሱ፣ ተነስተውም እሥር ቤቶችንና የቅጣት ደንቦችን፣
የሚያወጡ፣ ያወጡም ሥርዓት ናቸው።
እንግዲህ ሁለቱን አንድ የሚያደርጋቸው ነገሮች ቢኖሩ እንደዚህ ዓይነቱ
የቶታሊቴሪያን አስተሳሰብ ነው።
የአክራሪዎቹ የካሊፋቱ ሥርዓት ደግሞ ከምናውቀው ከኮሚስቶቹ፣ በዚያውም
ከጠበንጃ አንጋቢዎቹን የቶታሊቴሪያን ሥርዓት፣ ከዚያም አልፎ በጥልቀቱና
ስፋቱ ይሄዳል።
የእስላም ሃይማኖት „ዲክታተሮች“ የአንድን ሰው አስተሳሰቡን ብቻ ሳይሆን
ጭንቅላቱንም ጭምር ማርኮ ለመያዝ ይፈልጋሉ። ከዚያም ተራምደው
ልቡንም፣ ፣ ነፍሱንም፣ ሰውነቱንም፣ አንዱ እንዳለው ጠቅላላ ሕይወቱንም እሰከ
መጨረሻው ፍጻሜ፣ እሰከ የሞት እስትንፋሹ ድረስ እንቆጣጠረው ብለው
ይነሳሉ።
አለጥርጥር ሁለቱም ሶስቱም ሥርዓቶች (የኮሚኒስቶቹ፣ የሃይማኖት
አክራሪዎቹ፣ የጠበንጃ አንጋቢዎቹ- የወታደሮች ሥርዓት) የአንድ ሰው የግለሰብ
ነጻነቱን፣ የሌላውን ሰው የሃይማኖት ነጻነቱን፣ … ፈጽሞ የማያውቁ፣
የማይቀበሉ እምቢ ከአለ አሳደው የሚገርፉ፣ የሚገድሉ፣ የሚያስሩ በግልጽ
እንናገር ከአልን የአንድን ሰው ሕይወት እንቆጣጠር የሚሉ ጸረ-ዲሞክራቲክ
ሥርዓት ናቸው።
እነሱ የሰውን ልጅ መሰረታዊ ነጻነት አይቀበሉም። ለምን ብለው። የሲቪል
ነጻነትና መብት፣ ማንም ሰው የፈለገውን እምነትና የፈለገውን ሐሳብ
መከተል፣ መደራጀት፣ መሰብሰብ፣ መናገርና መጻፍ፣ መቃወምና መደገፍ፣
መምረጥና መመረጥን ….በዙ ቦታዎች እንደምናየው ይከለክላሉ። መብቱን
ከአገኘ ያባ ርረናል ብለው።

ምድራዊ ነጻነትና ምድራዊ ሕይወትን በአሉታዊ ዓይን የሚያዩ ብቻ ሳይሆን
የሚያግዱም ናቸው። ይህ ደግሞ በየአለበት የታየ ነው። ግን እጃቸው አትግባ !

ይህን ማለት „ሃይማኖትን“ እንዳለ „መቃወም“ ማለት አይደለም። ይህ ማለት
በሃይማኖት ስምና በዚያ ዓላማ ሽፋን በሰው ልጆች ላይ ጠበንጃና ኃይል መከታ
አድርገው እሱን ተጠቅመው ሥልጣናቸውን ዘርግተው ሰበአዊ መብቶችን
የሚገፉ አምባገነኖች አሉ ብቻ ለማለት ነው።
እንግዲህ በየትኛው ሥርዓት ነው አንድ ሰው የፈለገውን እምነትና አመለካከት፣
ፍልስፍናና ጥበብ፣ የኑሮ ዘይቤና የእራሱን ሕይወት ማንንም ሰው ሳይፈራ
፣ መርቶ ሊኖር የሚችለው?
አለአንዳች ጥርጥር፣ በዚህች በምዕራቡ የዲምክራቲክ ሥርዓት ውስጥ ብቻ
ነው።
ቸርልችርል በጥሩ አረፍተ-ነገር ደህና አድርጎ አስቀምጦታል።
ሥርዓቶች ይህኛው፣ …ምንም ቢሆን የተሻለ ነው“ ብሎአል።

„…ከአሉት

ሽንጎህ ውስጥ ስንት ተቃዋሚ ሰው እንደተቀመጠ ንገርኛና ማን እንደሆንክ
እነግርኻለው የሚባለውም ለዚህ ነው።
እርግጠኛ ነን፣ …እስላምና ክርስቲያኑ፣ አቴእስቱና የተፈጥሮ አማኙ፣ አህዛቡም
ጭምር… ጎን ለጎን ለብዙ ሺህ አመታት በሰላም ተቻችለውና ተከባብረው
በኖሩበት በአገራችን በኢትዮጵያ፣ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችና አስተሳሰቦችም
ጎን ለጎን አብረው ተቻችለው ሊኖሩ ይችላሉ። „አይችሉም“ የሚባልበት
ምክንያት- እኔ ብቻዬን ከአልገዛሁ የሚል የአምባገነነንት በሽታና መንፈስ እስከ
ሌለ ድረስ – ለእኛ ፈጽሞ አይታየንም።
ይህ ከሆነ ደግሞ ፣ አንድ ቀን የፖለቲካ ድርጅቶች ሕዝብ ፊት ቀርበው
ተወዳድረው፣ እንደ የምርጫ ውጤታቸው፣ አባሎቻቸው፣ የሕዝብ
እንደራሴዎቹ፣ የሸንጎ አባል ሁነው፣ ተራ በተራ ከፈረሳቸው ወይም
ከመኪናቸው ወርደው አንድ ላይ ተጋፍተው ሲገቡና፣ … ሊበራሉ በዚህ
ወገን፣ ወግ አጥባቂው በዚያ፣ …ዲሞክራቶቹ በቀኝ፣ … ሪፓብሊካናቹ በግራ፣
ሶሻሊስቶቹ አገር ወዳዶቹ በመሓል፣ በክቡ የሸንጎ አዳራሽ ውስጥ፣ የፓርላማ

ፕሬዚዳንቱ ስብሰባውን በጭብጨባ ሲከፍት፣ ተመልካቹ ሰገነቱ ላይ ተቀምጦ
ሲንጠራራ፣ ካሜራው ሲወዛወዝ….አንድ ቀን፣ እርገጠኛ ነን ማየታችን
አይቀርም። እናያለን። አንድ ቀን እኛም ዘንድ መስከረም ይጣባል!

አዳራሽህን አሳየኝና ማን እንደሆንክ እነግረኻለሁ የሚባለውም ለዚህ ነው።
ከሁሉም በአለፉት አመታት ከታዩት ግርግርች ውስጥ በአንደኛው በር ሰልፈኞች
በሩን ሰብረውና በጥሰው ሲገቡ በጓሮ በርና በመስኮት በሕዝብ ያልተመረጡ
የሸንጎ አባሎች እግሬ አውጭኝ ብለው ፈትለክ ብለው ሲያመልጡ የታዩ
ፊልሞች ናቸው።
ሌላው የሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳንት ሲሞት አዳራሹ ውስጥ የታየው ግርግር
ነው። ሶስተኛው ግን ፍጹም ልዩ ነው።
በአንድ በኩል ጋዜጠኞች ተቀምጠው፣ በሌላ በኩል ፖለቲከኞች ቆመው፣ በብዙ
ሚሊዮን የሚቆጠሩ ተመልካቾች በሞቀ ቤታቸው ተቀምጠው፣ በተለያዩ ፓርቲ
መሪዎች መካከል የሚካሄደውን የቴሌቪዢን ፍልሚያውን ሲመለከተው፣
ተመልክተውም እነሱ ፍርድ ሲሰጡ፣ ይህን ማየቱ ደስ ያሰኛል። ይህ ነገር
ደግሞ እኛ ጋ መድረሱ የማይቀር ነገር ነው።
ይመሻል ይነጋል ደኅና ቀንም ይመጣል። በኢትዮጵያ መሰረት የተጣለበት የሸንጎ
ቤትና አዳራሽ እንደገና ነፍስ ይዘራል። ይህምእኛን ወደፊት አንድ የሚያደርገን
ሓሳብና እሴት ነው። እሴት!
ይልማ ኃይለ ሚካኤል

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ ዘዴ :Posted on September 10, 2013 | Leave a comment | Edit

“አዲስ ትውልድና አዲስ ዘዴ :-ስውር ኮሚቴ! “

ይላል መጻጽፉ (1

ስምና አርዕሰቱ የመጽሐፉ እራሱ ብዙ ይናገራል። ፕሮግራሙና ዓላማው ግቡም
ጭምር ምን እነደሆነ፣በአንድ ዓረፍተ ነገር ቁልጭ አድርጎ አስቀምጦታል።
መጽሓፉን ያነበበ ቀርቶ ገረፍ ያደረገ ሰው አንዳንድ በቅርቡ የተካሄዱ ነገሮች
ትዝ ይሉታል።
ለምን ቢባል:- የካይሮና የቲኒዚያ፣የብራዚልና የቱርክ ወጣቶች፣ የግሪክና
የፖርቱጋል፣ የስፔንና የሮም ጎልማሶች፣ የስውዲንና የፓሪሶቹን የውጭ አገር ዘር
ያላቸውን ልጆች …“በቃን!“ ብለው እንዴት፣ እንደተነሱ ምክንያቱንም ዘዴውንም
እዚያ ውስጥ፣የፈለገ ሰው በቀላሉ ያገኛል።
የመጽሐፉ ደራሲ ወይም ደራሲዎች እንማን እንደ ሆኑ ሰማቸውን እላዩ ላይ ስለ
አላሰፈሩ፣ እነ ማን እንደሆኑ አይታወቅም። እነሱም ሊታወቁ የፈለጉ
አይመስሉም። …ስውር ናቸው?
ግን መጽሐፉን ለጥቂት ደቂቃዎች ጨብጦ ፣እያንዳንዱን ገጽ ያገላበጠ ሰው
እንደሚረዳው ከእያንዳንዱ ምዕራፍ በስተጀርባ:-የአጻጻፍ ስልታቸው ፣የዓረፍተ
ነገር አሰካካቸው፣የነገር አጣጣላቸው፣ እንደ ቅሉ የተለያዩ ስለሆኑ-ከደርዘን በላይ

የሚሆኑ ሰዎች፣ ሐሳብ በማመንጨቱ ላይ ሰብሰብ ብለው እንደተሳተፉበት
በቀላሉ መረዳት ይችላል።
የፓሪሱን „ቃጠሎ“፣የስውዲኑን የወጣቶች ረብሻ፣የበርሊኑን „ከፖሊሶች ጋር
የወጣቶች የአይጥና ድመት ጨዋታ“ ድንጋይ ውርወራና የእሳት ልኮሳ
በመኪናዎች ላይ ጽሑፉ“አስክሮአቸው“ እንዲወጡ እነሱን እንደገፋፋቸው
መገመትም አይከብድም።
„…የቀሰቀሱት እነሱ ደራሲዎቹ ሳይሆን አይቀሩም“ ተብለው፣ጋዜጣዎች
ያኔ እንደጻፉት፣ አንዳንዶቹ በጥርጣሬ ተያዘው፣ ለአጭር ጊዜ የፖሊስ ምርመራ
ተጋብዘው አድረውም እንደ ወጡ አንዳንዶቹ በአምዶቻቸው ላይ አሥፍረዋል።
በአጠቃላይ እነ ዩሊያን አሳኝጅን፣እነ ኤርዋርድ ስኖድንን፣እነ …እነዚያ ጥሩ
ደመወዝ ይከፈላቸው የነበሩ ልጆች “… ምን አቅብጦአቸው ይህን ያህል
ምሥጢር ሊያወጡና መንግሥታቸውን ሊያጋልጡ ቻሉ ?“ ለሚለው ጥያቄ
ይህቺ ፓምፍሌት እንደ አቅምዋ መልስ ትሰጣለች።
ዱሮ (ይህ ነው አዲሱ ነገር) „የአንድ አመጽ“ አንቀሳቃሽ ቡድን መሪዎች፣የዚያ
አላማ ጭንቅላቶች፣በስውርም ሆነ በይፋ የሚንቀሳቀስ አንድ „የፖሊት ቢሮ
አባሎች፣ የማዕከላዊ ኮሚቴ እጩዎችና መሪዎች፣…ጠቅላላ ጉባዔና
ውሳኔዎች…“የሚባሉ የድርጅትና የአሰራር ዘዴዎች ነበሩ።
አሁን በእሱ ፋንታ „የማይታየው ሰውር ንፋስ“ (ይህ ነው እነሱ መርጠው
የሰጡት የመጽሓፋቸው አርዕስት) ጠቅላላውን አመራር፣ሁሉንም ሥራ ይህ
አካል እንዲይዝ፣እንዲጨብጥና እንዲወስድ እነሱ (ከጽሑፉ መረዳት
እንደሚቻለው) አድርገውታል።
ይህን ይበሉ እንጂ አዝማች አለቃ ይህ ኮሚቴ የለውም።ሰብሳቢ ሊቀመንበር
አያውቅም። የበላይና የበታች አካል፣የጦር አበጋዝና ሕዋስ፣አዛዥና ታዛዥ
የለውም ። አይኖረውም።አይኖራቸውም። ታዲያ ምንድነው?
ትንሽ ጊዜ ወስዶ ጽሑፉን ጠለቅ ብሎ የሚያገላብጠው ሰው እንደሚረዳው
ከሆነ „ሁሉም ሰው“ በመጨረሻ የእረሱ አለቃና አዛዥ፣ኮሚቴም ነው።
አላማቸው „ሥልጣን ላይ የተቀመጡትንና ሥልጣናቸውንና ጉልበታቸውን
መከታ አድርገው በሥልጣናቸው የሚባልጉትን አምባገነኖች ከትከሻቸው ላይ“
እነሱ ጸሓፊዎቹ እንደሚሉት“ …በሕዝብ አመጽ እነሱን አራግፎ መጣል „ ነው።
ከዚያስ?

በእነሱ እምነት “ …ምርጫ አካሂዶ አዲስ ነጻ መንግሥት መመስረት፣ ለእሱም
መምጣት መታገል ነው።“
„እሰከ አሁን“ ይላላሉ በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት „በቃኝ ብላችሁ
ተነሱእንጂ!“ የሚለውን ትንሽ ፓምፍሌት (መጽሐፍ) የጻፉት፣የፈረንሣዩ
ዲፕሎማት፣ ስቴፋን ሔስል እንዳሉት “… የሰው ልጆች ፍረሃቻ ለአረመኔዎች
አመችቶአል። …ብልሃቱ ግን ያለው እነሱን ደፍሮ መቃወሙ ላይ ነው…“ ብለው
የእራሳቸውን የሕይወት ታሪክ ከሒትለር እሥር ቤት እንዴት እንዳመለጡ፣
አምልጠውም የተቃውሞ ትግላቸውን እንዴት እንዳካሄዱ፣ አካሂደውም
ለዲሞክራሲ ሥርዓት መመሥረት እንደታገሉ፣ ታግለውም በሁዋላም…ዓለም
አቀፉን የሰበአዊ መብት አዋጅ አብረው ከሌሎቹ ጋር እንደነደፉ ከመሞታቸው
በፊት እኝህ ሰው አጫውተዋል።
እሳቸው በዚህ „የማይታየው ሰውር ንፋስ ኮሚቴ“ በሚባለው ድርሰት ላይ
ይሳተፉ አይሳተፉ ምንም የሚታወቅ ነገር የለም።
ግን „ኦኩፓይ:-ሜዳውንም መንገዱንም፣ሰገነቱንም ያዝ“ የሚባለውን ዓለም
አቀፉን እንቅስቃሴና የወጣት አረቦቹን ትግል፣በቱኒዚያና በግብጽ፣በየመንና
በሊቢያ፣…እንደሚደግፉት ደጋግመው፣ከመሞታቸው በፊት እኝህ ጠንካራ ሰው
ቀደም ሲል ገልጸዋል።
ለፖሊት ቢሮ ሰዎች፣ ለሴንትራል ኮሚቴ አምላኪዎች፣ ለፕሮፓጋንዳና ቅስቀሳ
አካሎች፣ ለመረጃ ሰብሳቢዎች፣ ለተዋጊ ጦር አባሎች…እረ ምኑ ቅጡ፣ ለሁሉም
ይህ“….ማንም ሰው ዛሬም ነገም በቤቱ ውስጥ ተቀምጦ ለእራሱ የሚፈጠረው
ስውር ኮሚቴ..“ አስደንጋጭ ዜና ነው።
ለመያዝም፣ ለመቆጣጠርም፣ ለማገድም፣ ውስጣቸው ገብቶ ለመከፋፈልም
አስቸጋሪም ነው። ይህ ያነጋግራል!
—————
1)
https://mitpress.mit.edu/books/coming-insurrection
http://libcom.org/library/coming-insurrection-invisible-committee

„ዓለም /አፍሪካ እንዴት ሰነበተች“- DW
Posted on September 9, 2013

LALIBELA / ላ ሊ በ ላ Posted on September 10, 2013 | Leave a comment | Edit

ላ ሊ በ ላ

LALIBELA / ላ ሊ በ ላ -