You are on page 1of 3

ፍትሕ ርትዕ

ፍሥሓ ታዯሰ ፈሇቀ
ፍትሕ ወርትዕ ተዴሊ መንበርከ።
ፍት ርት የጌትነትኽ ጌጥ/ምቹ ዙፋንኽ ናቸው
(መዝ 88፥14)

ፍት ርት (ፍትሕ ርትዕ) ከግእዝ የተወረሰ ቃሌ ሲኾን ፍችውም ቅን ፍርዴ ማሇት ነው። መብትንም ያመሇክታሌ።
ዕሳቤው የሚጠቁመው ክሥተት ህሊዌ፥ ጥናቱም፥ በሕግ ተግባርና ምርምር ብቻ የተወሰነ አይዯሇም። በሚቀጥለት
መሥመሮች እንዯምናየው በቅደሳት መጻሕፍት ትምርት ከጥንት ከመሠረቱ የነበረና የዃሊ ዃሊም በሥነ ምግባር
ፍሌስፍና ውስጥ ገብቶ የተሇያዩ ታኦርያዎች (ቲዎሪዎች) የተተወሩሇት ዏይነተኛ ቁም ነገር ነው። በዚች አጭር
ጽሐፍ እቅደሳት መጻሕፍቱ ትምርትም ኾነ እፍሌስፍናው ታኦርያ ጠሌቆ መግባት ባይቻሌም፤ ክብር ይግባውና
ቸሩ መዴኀኔ ዓሇም “መምህረ ሕግ” ወ“ፍኖተ ጽዴቅ” (ሕግን የወሰነ፥ የሠራ፥ ያስተማረ ጌታ፤ የትሩፋተ ሥጋ
የትሩፋተ ነፍስ ጀማሪ)1 እንዯኾነ በተዘዋዋሪም ቢኾን ሇመጠቆም ያኽሌ የተወሰኑ ነጥቦችን ሇመዲሰስ እንሞክር።
በቅዴሚያ ስሇኦሪትና ስሇወንጌሌ። አይሁዴ ወንጌሌን እንዯማይቀበለ የታወቀ ነገር ነው። ከክርስቲያን ወገንም
ኦሪትን የሚያጣጥለ እንዲለ ስውር አይዯሇም። ምናሌባት ብዙዎች የማይገነዘቡት ኦሪትን የማጣጣለ ተግባር እምን
ዯረጃ እንዯዯረሰ ነው። ጥቂት የማይባለ ዘመናውያን ነባብያነ መሇኮት (modern theologians) “ኦሪት ተሽራሇች”
ከሚሇው የተሇመዯ አስተሳሰብ ዏሌፈው በነቢያት ዏዴሮ ይናገር የነበረው እግዚአብሔር እና በሌጁ በክርስቶስ
ህሌው ኾኖ ወንጌሌን ያስተማረው እግዚአብሔር እየራሳቸው የተሇያዩ እንዯኾኑ፤ ስሇዚህም በብለይና በሏዱስ
የቀጣይነት ትይይዝ (continuity) እንዯላሇ እስከማስተማር ይዯርሳለ።2 በነሱ ቤት የኦሪት በቀሇኝነት ከወንጌሌ
ርኅራኄ ጋራ ፈጽሞ አይጣጣምምና። እንዱያ ባይኾንም ስንኳ የብለዩን ፍት ርት ሏዱስ ኪዲን በፍቅር ተክቶታሌና
እንግዱህ ወዱያ አስፈሊጊ አይዯሇም የሚሌ ሇፍት ርት ዕውር የኾነ ፍቅርን (justice-blind love) ይሰብካለ።
እንዱህ ያሇው ነገር “አጋፒዝም” (agapism) ከሚባሇው ያስተሳሰብ ፈሇማ ይመነጫሌ።
“አጋፒስቶች” ሇአስተሳሰባቸው ዴጋፍ ይኾኗቸው ዘንዴ ከሏዱሱ እያዲነቁ የሚጠቅሷቸውን ጥቅሶች ከኦሪቱ
እያጣጣለ ከሚያነቧቸው ጋራ እያነጻጸርን በዝርዝር ሌንመረምራቸው በተቻሇ መሌካም ነበር። ነገር ግን ቦታውንም
ጊዜውንም ሇማብቃቃት በዚሁ እንሇፈውና፤ ከሉቃውንት ዯግሞ ጥቂት እንቅመስ።
የፍትሏ ነገሥት መቅዴም። ሉቃውንት በተሇያዩ መጻሕፍት ያብራሯቸውን ሳንጨምር እስኪ ሠሇስቱ ምእት
(በጉባኤ ኒቂያ የተሰበሰቡት ሦስት መቶ ዓሥራ ስምንት ሉቃውንት) ፍትሏ ነገሥትን እንዱያዘጋጁ ያነሣሣቸውን
ምክንያት ከሚገሌጠው መቅዴም ብቻ፤ የኦሪትና የወንጌሌን ሌዩነት እና አንዴነት የሚጠቁመውን ክፍሌ በመጠኑ
እንመሌከት። በፍትሏ ነገሥቱ መቅዴም ከተገሇጡት ቁም ነገሮች አንደ፤ የንጉሡ የቆስጠንጢኖስ ጥያቄ ነው።
እንዱህ የሚሇው፦
እስመ ፍኖተ ክርስቶስ ወፍኖተ ዓሇም ካሌእ ውእቱ። ወፍኖቱሰ ሇክርስቶስ ወትእዛዙ ጥይቅት ትቤ
አፍቅሩ ጸሊእተክሙ።… እስመ ዛቲ ትእዛዝ ሕገ ትሩፋት ይእቲ።…ዲግመ ትኤዝዝ ከመ ይትዏገሡ ወከመ
ይፁሩ። ይስረዩ ወያናኅሥዩ።… እፎ ይትከሀሇኒ ከመ አጽርዕ ዘንተ ትእዛዘ ወከመ አአዝዝ ኵነኔ።
የክርስቶስ ሕጉ ወንጌሌና የሙሴ ሕጉ ኦሪት ሌዩና ሌዩ ናቸውና። ይኸውም ኦሪት እጅ እግርን በስሇት
ዓይንን በፍሊት ቅጡ ስትሌ፤ የክርስቶስ ሕጉ ወንጌሌ ግን ጠሊቶቻችኹን ውዯደ ትሊሇችና።… ይህች
ወንጌሌ የትሩፋት ሕግ ናት።… ዲግመኛ በውስጥ በአፍኣ መከራን ታግሠው ይቀበለ ዘንዴ በሥጋ
1

“እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ…” (መዝ 83፥6) “አነ ውእቱ ፍኖተ ጽዴቅ ወሕይወት ዘበአማን” (ዮሏ
14፥6)
2

ሇምሳላ ያኽሌ በሴብቴምበር ዓሥራ አንደ አዯጋ ምክንያት 4 የአሜሪካ ወንጌሊውያን ያቀረቡትን ሙግት ማየት
ይቻሊሌ፦ Cowels, C.S., et al: Show Them No Mercy: 4 Views on God and Canaanite Genocide,
Sondervan, Grand Rapids, Michigan, 2003.

ወባሕቱ አላ ሇክሙ አብዕሌት” (ዴኾች ብፁዓን ናችኍ፤… እናንተ ባሌጸጎች ወዮሊችኍ) የሚሇውን የጌታን ቃሌ ሌብ ይሎሌ ..... መቅዴሙ ከዚህ አያይዞ እንዯሚያብራራው ንጉሡ፦ የወንጌሌ ሰው ከኾኑ ዘንዴ ፍት ርት መፈጸምና ማስፈፈጸም የማይቻሌ ስሇመሰሇው፤ ከዙፋኑ ወርድ ሥሌጣኑን ሉያስረክብ ተዘጋጅቶ ነበር። ነገር ግን ሉቃውንቱ ያቺ የመንግሥት ዕርሻ የፍትሕ ፍሬ እንዴታፈራ እንጂ ባድዋን እንዲትቀር ወዯፈጣሪኣቸው በጸሇዩ ጊዜ፤ ከጌታ የተሰጣቸው መሌስ፤ ንጉሡ ቅን ፍርዴ የሚፈርዴበትን፥ የሰውን መብት የሚያስከብርበትን ሕግ ከብለይ ከሏዱስ አውጣጥተው እንዱሰጡት በመኾኑ፤ እነሱም በታዘዙት መሠረት ከብለይ ከሏዱስ አውጣጥተው ፍትሏ ነገሥትን ጽፈዋሌ። ይኽም የሚያሳየው ጌታ በወንጌሌ ያስተማረው፤ በመሠረቱ በብለይ ከተነገረው የማይጻረር፤ ፍት ርትን ያገናዘበ ፍቅር (justice-alert love) እንጂ እንዱያው ዝም ብል በጭፍኑ ፍቅር ፍቅር ማሇትን (agapism) እንዲይዯሇ ነው። ርግጥ በዚሁ በፍትሏ ነገሥቱ መቅዴም የኦሪትና የወንጌሌን ሌዩነት የሚያመሇክቱ ኀይሇ ቃልች እንዲለ አይተናሌ። ይሌቁንም ኦሪት አካታ ያሇፈች አስመስል የሚገሌጥ ገጸ ንባብ አሇ፦ እስመ ኵለ ዘፍጹም ይዯለ በግብር ከመ ይሥዏሮ ሇዘየሏጽጽ። ወበእንተዝ ሠዏረቶ ሕገ እግዚእነ ሇዘይቀዴሞ እምኔሃ። ሇዛቲሰ ኢይዯለ ተሥዕሮታ። እስመ አሌቦ ዘይከብር እምኔሃ። ሇሉሃ ሕገ ፍጻሜ ወማኅሇቅት። ይኽም ማሇት፦ ፍጹሙ ሕጹጹን በግዴ ያሳሌፈው ዘንዴ ይገባሌና። ስሇዚህ ነገር የጌታችን ሕጉ ወንጌሌ ከሷ አስቀዴሞ የነበረ የኦሪትን ሕግ አሳሇፍችው። በሷ ግን ኅሌፈት የሇባትም። ከሷ የሚበሌጥ ስሇላሇ። የፍጻሜ የመጨረሻ ሕግ ናት እንጂ። ይህ እንዱህ ነው፤ ይኹን እንጂ፤ “ሕገ ፍጻሜ” (የፍጻሜ ሕግ) ማሇት’ኮ ያጸጸውን መሌቶ፥ የጠበበውን አስፍቶ ከሌዕሌና ወዯሌዕሌና ከፍ እያለ ፍጹም እየኾኑ መኼዴ እንጂ የቀዯመውን ማጥፋት እንዲሌኾነ ራሱ ጌታ አተስምሮናሌ። ኢይምሰሌክሙ ዘመጻእኩ እሥዏሮሙ ሇኦሪት ወሇነቢያት። ዘእንበሇ ዲእሙ ከመ እፈጽሞሙ። ኦሪትን ነቢያትን ሊሳሌፋቸው የመጣኹ አይምሰሊችኍ፤ ሊሳሌፋቸው አሌመጣኹም። ፍጹማን ሊዯርጋቸው ነው እንጂ። (ማቴ 5፡17) ይኽም “ንጉሥ በዘውደ ዴኻ ባመደ” እንዱለ፤ ኹለም ባሇው ብቻ (status quo) ይጽና ብል መተው ሳይኾን፤ ዴኾችን የሚገፉ ኀያሊን ከዙፋናቸው የሚወርደበት ስሇጽዴቅ የተዋረደ ትሐታን የሚከብሩበት፤3 አፍኣዊው ሥራትና ወግ ብቻ ያይዯሇ ውሳጣዊው የበጎ ምግባርና የትሩፋት ሕግ የሚከበርበት፤ የመዲን ተስፋም በጠባቡ ሇእስራኤሌ ብቻ ሳይኾን በሰፊው ሇአሕዛብ ኹለ የሚናኝበት ሕገ ትሩፋት፤ ፍጹም ኾኖ መሠራቱንና፤ ሏጋጌ ሕግ፥ መምህረ ሕግ (የሕግ ዏጋጊ፥ የሕግ አስተማሪ) በኾነው በራሱ በባሇቤቱ መፈጸሙን ያስረዲሌ። እንዳ! ጌታ መሰቀለም’ኮ፦ “የገዯሌክ ገዯሌክ፤ የበዯሌክ በዯሌክ፤ በቃኽ” ሳይኾን “በካሳ” በማሇቱ ነው። መዴኀኔ ዓሇም ያሰኘው ቅለ የኸ አይዯሇም እንዳ? ይኽን የሚያሰረዲ ነገር በመቅዴመ ወንጌሌ እንዱህ የሚሌ እናገኛሇን፦ ምሕሮሙ በዕበየ ሣህለ ወምሕረቱ ወኂሩተ ሠናይቱ…በዘይሤኒ ጽዴቁ ወርትዐ። በይቅርታው በቸርነቱ ብዛት ዏዘነሊቸው… ባማረ በተወዯዯ ፍርደ አዲናቸው። 3 ሇምሳላ “ወነሠቶሙ ሇኀያሊን እመናብርቲሆሙ። አዕበዮሙ ሇትሐታን። ወአጽገቦሙ እምበረከቱ ሇርኁባን። ወፈነዎሙ ዕራቆሙ ሇብዐሊን” (ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርድአሌ፤ ትሐታንንም ከፍ አዴርጎአሌ። የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአሌ፤ ባሇ ጠጎችንም ባድአቸውን ሰድአቸዋሌ።) የሚሇውን የእመቤታችን የማርያምን ጸልት፤ እንዱሁም “ብፁዓን አንትሙ ነዲያን.በነፍስም ያስተሰርዩ ዘንዴ። “ኢይብሇከ እስከ ስብዕ አሊ እስከ ሰብዓ በበስብዕ” (እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ አሌሌህም) ብሊ ታዝዛሇችና፤… ይኽን የወንጌሌን ትቼ የኦሪትን ፍርዴ መፍረደ እንዯምን ይቻሇኛሌ እንዯምን ይገባኛሌ?.

pp. 208. 212.“ኀሢሠ ትፍግዕት” ማሇትም ተዴሊ ዯስታን መሻት (pursuit of happiness—eudaimonia) ነበር። በኾነው መንገዴ ኹለ ትፍግዕትን (ተዴሊ ዯስታን) መሻት ዏሊማው ባዯረገ ማናቸውም ያስተሳሰብ ፈሇማ ዯግሞ፦ ርኅራኄ፥ ባሌንጀራን እንዯራስ መውዯዴ፥ የላሊውን ሰው መብት ማክበር የሚባለ ነገሮች ፍጹም ባዕዴ ናቸው። ባዕዴ ናቸውና፤ የምዕራቡ ዓሇም ፍሌስፍና እንዱህ ከባሕርዩ ውጭ የኾነውን ፍት ርትን በመዝገበ ታኦርያው ሉያካትት የቻሇው፤ እንዯነ አውጉስጢኑስ ባለ የቤተ ክርስቲያን ሉቃውንት አማካይነት ከቅደሳት መጻሕፍት ወርሶ ነው።4 ፍሌስፍናው ከቅደሳት መጻሕፍት የወርሰውን ትምርት በገዛ ባሕርዩ ሲተውር (በቲዎሪ መሌክ ሲያቀርብ) የተሇያየ አግጣጫ ተክትል ኼዶሌ። ጥቃቅን ሌዩነቶችን ወዯጎን ትተን በፍት ርት ዏይነተኛ ባሕርይ ሊይ ብናተኩር፤ ኹሇት ታኦርያዎችን እናገኛሇን። አንዯኛው፦ ፍት ርት ተፈጥሮኣዊ መብትን ማክበርና ማስከበር እንዯኾነ አዴርጎ ሲመሇከተው (justice as inherent rights)፤ ኹሇተኛው፦ የሇም ፍት ርት ቀና (የኅብረተሰብ) ሥርዏት/ያገር ዕዴር የማምጣት ጕዲይ ነው ይሊሌ (justice as right order)። እኩሌነትን ማረጋገጥም (equal regard) የፍት ርት ዏይነተኛ ባሕርዩ እንዯኾነ የሚናገሩ አለ። የኾነው ኾኖ፤ በውርስ ባሇጸጋ የኾነው ዓሇማዊ ፍሌስፍና፤ ፍት ርትን በሃይማኖት አጽንቶ እስከጠበቀ ዴረስ እንጂ፤ “ዘመናዊነት ኼድ ኼድ ዓሇማዊነትን በመሊው ዓሇም ያሰፍነዋሌና፤ ሃይማኖት ብል ብል ከምዴረ ገጽ ይጠፋሌ” የሚሇውን የቆየ ዘፈን አኹንም አሊዝናሇኍ ካሇ፤ ሕግና ሥራት ከመሠረቱ ይናዴና “ትፍግዕት” (eudaemonism) የምግባር መርሕ ኾኖ ቀኑን ይገዛሌ። የእንዱህ ያሇው ትምርት ዲፋ ሃይማኖተኞችን ብቻ ሳይኾን ዓሇሙን ኹለ እንዳት እንዯሚያዲፋ በተግባር እያየነው ቢኾንም ቅለ፤ እዚህም ጥቂት ባተትነው እንዳት ባማረ። ነገር ግን አኹን ጊዜውም ቦታውም ስሇገዯበን አንደም አንዶ አንባቢ እየራሱ እየራሷ እንዯተገሇጠሊቸው መጠን እንዱመረምሩት በዚሁ እንተወዋሇን። ወስብሏት ሇመዴኀኔ ኵለ ዓሇም። ይቆየን 4 “The ancients conducted all their ethical theorizing within the framework of eudaimonism. Nicholas. Princeton and Oxford. 2008. . “[T]he grip of eudaimonism had to be broken for a theory of rights to become possible… Augustine broke the grip (along perhaps with others) and that it was especially the influence of Scripture on Augustine that led to the break”. Princeton University Press.” Wolterstorff. Justice: Rights and Wrongs. 136.“ወበዴሌወት ኮነ ኵነኔ እግዚአብሔር ወአዴኀነነ በፍትሏ ጽዴቅ ወርትዕ” [በሚገባ ተፈርድብን ነበር፤ በእውነተኛ ፍት ርት አዲነን] እንዱሌ፤ ጌታ፦ የገዯሌክ ገዯሌክ፤ የበዯሌክ በዯሌክ፤ በቃኽ አሊሇም። በካሳ ብሎሌ እንጂ። በመጨረሻም ጥቂት ስሇፍት ርት ፍሌስፍና። ገና በመግቢያው እንዯተጠቆመው የፍት ርት ነገር እፍሌስፍና ቤት ውስጥ የገባው የዃሊ ዃሊ እንጂ ከጥንት ከጧቱ አሌነበረም። ይህን ስንሌ ግን በጥንቱ የአሕዛብ ፍሌስፍና የሥነ ምግባር ታኦርያ አሌነበረም ማሇታችን አይዯሇም። ዝርዝር ውስጥ ሳንገባ በዘመናችን ካለ ዓይናማ ፈሊስፎች አንደ ሊይ ተመርጉዘን ጠቅሊሊ አስተያየት ብንሰጥ፤ ሇጥንቱ የአሕዛብ የሥነ ምግባር ፍሌስፍና ዏይነተኛ ራግዙ (framework):. “No version of eudaimonism has room for compassion. A theory of rights… cannot be developed within that framework”.