You are on page 1of 32

ሲራ ክፍል 1 – የነብዩ የዘር ሐረጋቸው፣

አወላለዳቸው እና የልጅነት ዘመን

ሙሐመድ የዐብደላህ ልጅ፣ የአብዱል ሙጦሊብ ልጅ፣ የሃሽም ልጅ፣ የመናፍ ልጅ፣ የፈህር (ቁረይሽ) ልጅ፣
የማሊክ ልጅ፣ የነድር ልጅ፣ የኪናነህ ልጅ፣ የዐድናን ልጅ፣ የአላህ ነብይ እስማዒል ልጅ፣ የአላህ ወዳጅ
የኢብራሂም ልጅ። አላህ ከጥሩ ጎሳ መረጣቸው። የመሐይምነት ዘመን ቆሻሻ ወደ ዘር ግንዳቸው አልገባም።

ሙስሊም እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

“አላህ ከእስማዒል ልጆች ኪናናን፣ ከኪናናህ ልጆች ውስጥም ቁረይሽን፣ ከቁረይሽ ሃሽምን፣ ከበኒ ሃሽም በኩል
ደግሞ እኔን መርጧል።” (ሙስሊም ዘግበውታል)

አወላለዳቸው
የተወለዱት የዝሆን አመት (ዓመል ፊል) በመባል በሚታወው ዘመን ነው። ይህም ዓመት አብረሃ ካዕባን
ለማፍረስ የሞከረበት ኣመት ነበር። አላህም እጅግ በሚያስደንቅ ጥበብና ተአምር ሐሳቡን አምክኖታል። ይህ
በቁርአን ታሪክ ተወስቷል። ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በዚሁ አመት በወርሃ ረቢአል አወል 11ኛው ቀን
በእለተ ሰኞ እንደተወለዱ ዘገባዎች ያመለክታሉ።

አስገራሚ ጅምርና ግልጽ በረከት

አባት አልባ ሆነው ተወለዱ። እናታቸው እርሳቸውን የሁለት ወር እርጉዝ እያለች አባታቸው ሞቱ። አያታቸው
ዐብዱል ሙጦሊብም የማሳደግ ሐላፊነቱን ወሰዱ። በያኔዎቹ ዐረቦች ባህል መሠረትም ከበኒ ሰዕድ ጎሳ
የሆነችና ሐሊመት ቢንት አቢ ዙዓይብ የምትባል እንስት ታሳድጋቸው ዘንድ ተሰጣት።

የታሪክ ጸሐፊዎች እንደሚስማሙት ያኔ የበኒ ሰዕድ ቀዬ በድርቅ የተመታበት አመት ነበር። የእንስሳት ጋቶች
ነጥፈዋል። አዝርእቱ ደርቀዋል። ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በሐሊማ ቤት ካረፉበት እና ጡቷን መጥባት
ከጀመሩበት ቅጽበት አንስቶ ግን የሐሊማ ቤት በበረከት ተሞላ። ፍየሎቿ ጠግበውና ጋቶቻቸው በወተት
ተሞልቶ ይመለሱ ጀመር።

በበኒ ሰዕድ መስክ ላይ እያሉ የተከሰተው የደረታቸው መቀደድ አላህ ለትልቅ ሐላፊነት እንደመረጣቸው
የሚጠቁም የነብይነት ምልክት ነበር። አነስ ኢቢን ማሊክን (ረ.ዐ) ዋቢ በማድረግ ሙስሊም እንደዘገቡት
የአላህ መልእክተኛ በልጅነታቸው ዘመን ከሕጻናት ጋር በመጫወት ላይ እያሉ ጅብሪል (ዐ.ሰ) መጣና
ያዛቸው። አጋደማቸውም። ደረታቸውንም ሰነጠቀው። ልቦናቸውንም አወጣ። የረጋ ደም የሚመስል ነገርም
ከውስጡ አስወገደ። “ይህ የሰይጣን ድርሻ ነው” አለም። በወርቅ ሳህን ውስጥ አድርጎም በዘምዘም ውሃ
አጠበው። ከዚያም እንደነበር ጠገነውና ወደቦታው መለሰው። ልጆችም ወደ ሐሊማ ቤት እየሮጡ ሄደው
“ሙሐመድ ተገደለ” በማለት ተናገሩ። ሲመጡ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ፊት ገርጥቶ አገኙት። አነስ፡- “የዚህን
ክስተት ፋና ከነቢዩ ደረት ላይ አይቻለሁ” ሲሉ ተናግረዋል። ከልባቸው ውስጥ የረጋ ደም የሚመስል ነገር
መወገዱ እርሳቸውን ከልጅነት አጓጉል ባህሪያት አርቆ፣ ቁም ነገረኛ፣ ጽኑ፣ ሚዛናዊና ውብ ባህሪያት የተላበሱ
ለማድረግ ነው። አላህ በጣም እንደሚጠብቃቸው እና እንደሚንከባከባቸው፣ ሰይጣንም እርሳቸውን
የመተናኮል አቅም እንዳይኖረው መደረጉን ለማመልከትም ጭምር ነው። (ፊቅሁ ሲራ – ዶክተር ረመዷን
አል-ቡጢ)

ይህ ክስተት ሐሊማ ሕጻኑን ወደ ቤተሰቦቹ እንድትመልስ ምክንያት ሆነ። ያኔ የነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) እድሜ
አምስት አመት ነበር። ስድስት አመት ሲሞላቸው እናታቸው አሚና ሞተች። አያታቸው ሊያሳድጓቸው
ወሰዷቸው። ስምንት ዓመት ሲሞላቸው አያታቸው ሞቱ። የማሳደጉን ሐላፊነትም አጎታቸው አቡ ጧሊብ
ወሰዱ።
የላቀ እጣ ፈንታ

አስራ ሁለት አመት ሲሞላቸው አጎታቸው አቡ ጧሊብ ወደ ሻም ለንግድ እርሳቸውን አስከትለው ወጡ።
ቅፍለቱ በስራህ በተባለ ቦታ ላይ ሲያርፍ ቡሐይራ የተባለን አንድ መነኩሴ ለመጎብኘት ጎራ አለ። ሰውየው
የክርስትና ሐይማኖትና መጽሐፍት አዋቂ ነው። ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) በትኩረት አስተዋላቸው። በጥንቃቄ
አጠናቸው። አናገራቸውም። ከዚያም ወደ አቡ ጧሊብ በመዞር፡- “ይህ ልጅ ምንህ ነው?” አላቸው። “ልጄ
ነው” አሉት። (አቡ ጧሊብ በጣም ስለሚወዷቸው ልጄ በማለት ነበር የሚጠሯቸው።) ቡሐይራም፡- “ልጅህ
አይደለም። የዚህ ልጅ አባት በሕይወት ሊኖር አይችልም” ሲል ተናገረ። አቡ ጧሊብም “የወንድሜ ልጅ ነው”
አሉ። “አባቱ ምን ሆነ?” ሲል ጠየቃቸው። “ተረግዞ እያለ ሞተ” አሉ። “እውነት ብለሐል። በአስቸኳይ
ወደሀገሩ ይዘኸው ተመለስ። አይሁዶች እንዳያገኙት ተጠንቀቅ። በአላህ እምላለሁ ካገኙት ይተናኮሉታል።
ለታላቅ ደረጃ የሚበቃ ልጅ ነው” አላቸው። አቡ ጧሊብም ፈጥነው ወደ መካ መለሱት።

እንጀራ ፍለጋ

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ለወጣትነት እድሜ ሲደርሱ እንጀራ ፍለጋ መሮጥ ጀመሩ። ፍየል ጥበቃ
የጥረታቸው መጀመሪያ ነበር። በኋላ ላይ፡- “ለመካ ሰዎች በቀራሪጥ (መጠነ ትንሽ ክፍያ) ፍየል እጠብቅ
ነበር።” ሲሉ ተናግረዋል።

አላህ ያደረገላቸው ጥበቃ

ከወጣትነት አጓጉል ድርጊቶችና ጨዋታዎች ሁሉ አላህ ጠብቋቸዋል። ስለ ራሳቸው እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፡-

“በመሐይምነት ዘመን ወጣቶች ይፈጽሟቸው የነበሩ ድርጊቶችን ለመፈጸም ያሰብኩት ሁለት ጊዜ ብቻ


ነበር። በነዚህም ጊዜያት አላህ ያሰብኩትን እንዳላደርግ አቀበኝ። ከዚያ በኋላ በመልእክተኛነት እስኪልከኝ
ድረስ ተመሳሳይ ድርጊት አስቤ አላውቅም። ይኸውም አንድ ቀን ሌሊት በመካ ከፍታማ ቦታዎች ላይ ፍየል
አብሮኝ ይጠብቅ ለነበረ ልጅ፡- ‘ፍየሌን ጠብቅልኝ። ልክ እንደወጣቶች መካ ውስጥ ስጫወት ልደር’ አልኩት።
‘ይሁን’ አለኝ። ወደ መካ ወረድኩ። እዚያ እንደደረስኩ ከአንድ ቤት ውስጥ ዘፈን ሰማሁ። ምንድን ነው?
በማለት ስጠይቅ፣ የሰርግ ዘፈን እንደሆነ ተነገረኝ። ቁጭ ብዬ ማድመጥ ስጀምር አላህ ጆሮዬን ደፈነው።
ጥልቅ እንቅልፍም ወሰደኝ። ከእንቅልፍ ያነቃኝ የረፋዱ ጸሐይ ግለት ነበር። ወደ ባልንጀራየም ተመለስኩ። ስለ
አዳሩ ጠየቀኝ። የሆነውን ነገርኩት። በሌላ ሌሊትም ተመሳሳይ ሙከራ አደረግኩ። ልክ የመጀመሪያው ሌሊት
ዓይነት ሁኔታ አጋጠመኝ። ከዚያ በኋላ ያን ዓይነት ሐሳብ አስቤ አላውቅም።”

በአላህ ብቻ መመካት
የፍጡራን ፈርጥ ለየት ያለ የሕይወት ጅማሬ፣ አላህ ቀልባቸው ከርሱ ውጭ በሌላ አካል እንዳይንጠለጠል
እንደፈለገ ያመለክታል። በአባት፣ በእናት፣ በአያት ወይም በአጎት፣ በገንዘብ፣ በስልጣን ወይም በሌላ ነገር
እንዳይመኩ የፈለገ ይመስላል። ይህ ስሜት ለሙስሊም ባጠቃላይ እና ለዳዒ በተለይ ለስብእናው ስሪት
እጅግ አስፈላጊ ነው። ከሚንከባከባቸው ክንድ ወይም ድሎት ከሚለግሳቸው ሰው ገንዘብ አርቆ አላህ ብቻ
ሊጠብቃቸው እና ሊንከባከበው በመሻት ይህን አደረገ። ይህ ሲሆን፣ “አባቴ” በማለት ፋንታ “አምላኬ”
ይላል። ነፍሳቸውም ወደ ገንዘብ ወይም ክብር፣ ወደ አያት ቅድመ አያቶች ንግስናና ስልጣን ወደማስመለስ
ስሜት አትዘነበልም። ሰዎችም የዱንያ (ምድሯዊ) ክብር ከነብይነት የተቀደሰ ደረጃ ጋር አይቀላቀልባቸውም።

ይህም በመሆኑ መልእክተኛው ነብይ ነኝ ያሉት ዓለማዊ ክብርና ጥቅም ለማግኘት ወይም በዘመናችን
አገላለጽ “በሐይማኖት ለመነገድ” ነው የሚባሉ ክሶች ሁሉ የሚቆሙበት መሠረት አጡ። ዓለማዊያንና
አምላክ የለሾች በቅን የዳዕዋ ሰዎች ላይ ይህን ክስ በየዘመናቱ ሲሰነዘሩት ይደመጣል።

ጠቃሚ ትምህርቶች

ገና በለጋ እድሚያቸው እንጀራ ፍለጋ ያሳዩት ትጋት ሦስት ጠቃሚ ትምህርቶችን አካቷል።

1. አላህ ለነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ያላበሳቸውን ውብ ባህሪና ረቂቅ ስሜት ያሳያል። አጎታቸው የተሟላ
እንክብካቤ ያደርጉላቸው ነበር። ልክ እንደ አባት ያዝኑላቸውም ነበር። ይህም ሆኖ ግን መልእክተኛው
(ሰ.ዐ.ወ) ሰርተው ማደር እንደሚችሉ ሲሰማቸው ወደ ስራ ተሰማሩ። የአጎታቸውን የገንዘብ ቀዳዳዎች
ያቅማቸውን ያህል ለመሸፈን ጥረት አደረጉ። ከስራቸው የሚያገኙት ገቢ ምንም ያህል አነስተኛ ቢሆንም
እንኳ ኩሩ ስብእናቸው፣ ያቅሙን ያህል ከመጣር የማይሰስተው ባህሪያቸው ወደ ስራ መራቸው። የአጎታቸው
ውለታ ለመመለስና የተግባር ምስጋና ለማድረስ ይህን አደረጉ።

ስለዚህ አንተም ልክ እንደርሳቸው ጥንቁቅና ኩሩ ሁን። “ራስህን ባንገትህ ተሸከም።”

2. አላህ ለባሪያው በምድር ላይ የሚወድለትን የሕይወት ዓይነት የሚያብራራ አጋጣሚ ነው። ይኸውም
አላህ ቢፈልግ ኖሮ ለነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ገና ከሕይወታቸው መጀመሪያ ጀምሮ ኑሯቸውን ድሎታማ በማድረግ
እንጀራ ፍለጋ ከመኳተን መታደግ ይችል ነበር። ግና ለሰው ልጅ መልካሙ ገንዘብ ለሕብረተሰቡ በሚሰጠው
አገልግሎት ወይም በጥረቱ የሚያገኘው መሆኑን፣ ሳይሰራ እና ሳይለፋ፣ ለሚኖርበት ማሕበረሰብ ቅንጣት በጎ
ነገር ሳያደርግ፣ ስራ ፈትቶና እጁን አጣጥፎ ተቀምጦ የሚያገኘው ገንዘብ ደግሞ መጥፎ መሆኑን በጥበቡ
ሊያስተምረን ስለከጀለ ነው።
በመሆኑም ልክ እንደ ተወዳጁ ነብይ (ሰ.ዐ.ወ) ሐላል ስራዎችን ብቻ ሰርተህ ገንዘብ ለማግኘት ጉጉና ትጉ
ሁን።

3. ዳዒ የኑሮ መሠረቱ ዳዕዋ ሲሆን፣ ወይም በሰዎች ስጦታና ምጽዋት ላይ ሲመሠረት ዳእዋው ክብደትና
ግምት ያጣል።

َ ُ‫علَى الاذِي فَ َط َرنِي أَفَ ََل ت َ ْع ِقل‬


‫ون‬ َ ‫علَ ْي ِه أ َ ْج ًرا ِإ ْن أ َ ْج ِر‬
َ ‫ي ِإ اَل‬ َ ‫سأَلُ ُك ْم‬
ْ َ ‫يَا قَ ْو ِم ََل أ‬
“ሕዝቦቼ ሆይ! በእርሱ (በማድረሴ) ላይ ምንዳን አልጠይቃችሁም። ምንዳዬ በዚህ በፈጠረኝ ላይ እንጂ
በሌላ ላይ አይደለም። አታውቁምን?” (ሁድ 11፤51)

መልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) የሰዎች ውለታ በአንገታቸው ዙሪያ ተጠምጥሞ ሐቅን ይሉኝታ ሳይዛቸው በድፍረት
እንዳይናገሩ የሚያደርጋቸው አንድም አጋጣሚ በነብይነት ከመላካቸው በፊትም ሆነ በኋላ በሕይወታቸው
ውስጥ እንዲኖር አላህ አልፈቀደም። ስለዚህም ለራስህ እና ለዳዕዋው ክብር ቀናኢ ሁን። ለምትሰጠው የዳዕዋ
አገልግሎት ከሰዎች ምንዳም ሆነ ምስጋና አትሻ። የእስልምና ዳእዋ ልክ እንደ አንበሳ ኩሩና ቁጥብ፣ እንደ
ዳመና ውሃ ንጹህ መሆኑን እወቅ።

ፍጹም ሰዋዊ ስብእና

ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንደ ማንኛውም ሰው ሰዋዊ ባህሪን የተላበሱ፣ ሰዋዊ ስሜቶችና ፍላጎቶች
ያሏቸው መሆኑ ጥርጥር የለውም። በማንኛውም ወጣት ላይ የሚስተዋሉ ተፈጥሯዊ ዝንባሌዎች
ነበሩባቸውም። ይህም እውነት ከሌሎች ሰዎች የተለዩ እንዳልሆኑ ያመለከታል። ልክ እንደ ሌሎች ወጣቶች
በጨዋታ የሚያሳልፉት ጊዜ ቢኖራቸው ይፈልጋሉ። ይህ ተፈጥሯዊ ስሜት መጥፎ አይደለም። ይሁንና አላህ
ይህን ተከትሎ ከሚመጣና ከበጎ ስነ-ምግባሮች ተምሳሌ፣ የዘልዓለማዊው አምላካዊ ሸሪዓ መምህር
ከመሆናቸው ጋር ከማይጣጣሙ አጓጉል አጋጣሚዎች ጠበቃቸው።
ሲራ ክፍል 2 – የፉጅጃር ጦርነትና የፈዱል
ስምምነት

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እድሜያቸው 14 ሲሞላ “ሐርበል ፉጅጃር” በተባለው ጦርነት ላይ ተሳተፉ፡፡ የኪናናህና
የቁረይሽ ጎሳ በአንድ ወገን፣ የቀይስ ጎሳ በሌላ ወገን ተሰልፈው ያደረጉት ጦርነት ነው። ለዐረቦች እጅግ አስፈሪ
ጦርነት ነበር። የተቀደሰችውን የመካን ከተማ ክብር የገረሰሰ ስለነበር እለቱ “የውመል ፉጅጃር” (የአመጽ
ቀን) ተባለ። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፡- “በዚያ ጦርነት ላይ ለአጎቶቼ ቀስት
እየሰበሰብኩ አቀብል ነበር።”

ያኔ የአስራ አራት ወይም የአስራ አምስት አመት ልጅ እንደነበሩ ከፊል ዘገባዎች ያመለክታሉ። ሌሎቹ ደግሞ
የ20 አመት ልጅ መሆናቸውን ዘግበዋል። የመጀመሪያው ሐሳብ ሚዛን ይደፋል። ምክንያቱም በጦርነቱ
ወቅት የነበራቸው ሚና ቀስት እየሰበሰቡ ማቀበል መሆኑ ልጅ እግር እንደነበሩ ያመለክታል። ይህ ተሳትፎ
ከልጅነታቸው ጀግንነትን እንዲማሩና የውጊያ ልምድ እንዲቀስሙ አደረጋቸው። ይህ ጦርነት እንደሌሎች
የዐረብ ጦርነቶች ሁሉ በኢምንት ምክንያት የተነሳ ነው። ከዚያም የዘረኝነት እሳት አቀጣጠለው። የኢስላም
ብርሃን ልቦናዎቻቸውን አስማምቶ ይህን ጥመት እስኪያስወግድላቸው ድረስ እንደዚሁ ነበሩ።
ቁረይሾች ከፉጅጃር ጦርነት እንደተመለሱ “ፈዱል” ለተባለው ስምምነት ለማድረግ ተጠራሩ። ስምምነቱ
ከቁረይሽ ባላባቶች መካከል አንዱ በነበረው በጀድዓን ቢን ተይሚ ቤት ውስጥ ተፈጸመ። የስምምነቱ ይዘት
መካ ውስጥ ተበድሎ ያገኙትን ማንኛውም ሰው -የከተማዋ ነዋሪ ይሁንም አይሁን- ከጎኑ ቆመው በደሉን
ለማካካስ የተስማሙበት ነበር። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከአጎቶቻቸው ጋር በመሆን በስምምነቱ ላይ
ተሳትፈዋል። አላህ በመልእክተኝነት ከላካቸው በኋላ እንዲህ ሲሉ ተደምጠዋል፡-

‫ ولو دعيت به في اإلسَلم ألجبت‬،‫لقد شهدت مع عمومتي حلفًا في دار عبد هللا بن جدعان ما أحب أن لي به ُح ْمر الناعم‬

“በዐብደላህ ኢቢን ጀድዓን ቤት ውስጥ በተደረገው ስምምነት ላይ ተገኝቻለሁ። ከዚያ ሳልገኝ ቀርቼ በልዋጩ
ቀይ ግመል ቢሰጠኝ የምመርጥ አይደለሁ። በእስልምና ውስጥ ሆኜም ወደዚያ ስምምነት ብጋበዝ
ግብዣውን እቀበላለሁ።”

ምክንያቱም እርሳቸው የተላኩት መልካም ስነ ምግባራትን ለማሟላት ነው። የስምምነቱ ይዘትም የመልካም
ስነ ምግባር አካል ነው። ኢስላም የስምምነቱን አብይ ይዘት ያጸድቃል። ይህ ስምምነት በርካታ ሰዎችን
ከበደል ታድጓል።

ከ “ሒልፈል ፉዱል” ስምምነት ከምናገኛቸው ትምህርቶች መካከል ዋነኛው፡- “ከተበዳይ ጎን መቆምና


በደሉን ማካካስ” ነው። ውድ አንባቢያችን! በዚህ ረገድ የሚወሳ የግል ተሞክሮ አለህን?

ሲራ ክፍል 3 – እመት ኸዲጃን


ማግባታቸው
ኢብን ሂሻም እንደዘገቡት ኸዲጃ (ረ.ዐ) ማሕበራዊ ክብር እና ሃብት የነበራት ነጋዴ እንስት ናት። ወንዶችን
በሽርክና ታስነግዳለች። የአላህን መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሐቀኝነትና ታማኝነት እንዲሁም መልካም ስብእና
ስትሰማ ወደርሳቸው መልእክት በመላክ ገንዘቧን ይዘው ለንግደ ወደ ሻም እንዲሄዱ ጠየቀቻቸው። ለሌሎች
ከምትሰጠው በላይ ገንዘብም ልትሰጣቸውና መይሰራህ የተባለ አገልጋይዋን ከርሳቸው ጋር ልትልክ ቃል
ገባች።

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጥያቄዋን ተቀበሉ። ገንዘቧንም ይዘው ከአገልጋይዋ ከመይሰራህ ጋር ወደ ሻም ተጓዙ።


ጉዟቸው የተሳካ ነበር። እጥፍ ድርብ ትርፍ ይዘው ወደ ኸዲጃ ተመለሱ። ገንዘቡንም በታማኝነት አስረከቡ።
መይሰራህ የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) መልካም ስብእናና ውብ ባህሪ ሲያይ ልቦናው በአድናቆትና በክብር ተሞላ።
ያየውንም ለኸዲጃ አወጋት። እርሷም በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ታማኝነት ተደነቀኝ። በርሳቸው ሰበብ ያገኘችው
በረከትም ሳያስገርማት አልቀረም፡፡ ይህ ሁኔታ ለጋብቻ እንድትጠይቃቸው አነሳሳት። ሐሳቧን አቀረበችላቸው።
እርሳቸውም ተቀበሏት። አጎቷን ዐምር ኢቢን አሰድን በአጎታቸው በአቡ ጧሊብ በኩል አስጠየቁ። አቡ
ጧሊብ የጋብቻ ጥያቄውን ያቀረቡት በሚከተለው ንግግር ነበር፡-

‫ وجعلنا خدام الناس ثم إن ابن أخي هذا محمد بن عبد هللا َل يوزن به‬،‫ وجعلنا حضنة بيته‬،‫الحمد هلل الذي جعلنا من ذرية إبراهيم‬
ً ‫رجل (إَل رجح به) شرفًا ونبَلً وفضَلً (وعقَلً) وإن كان في المال قَلًّ (أي‬
،‫فقيرا) فإن المال ظل زائل وأمر حائل وعارية مسترجعة‬
،.…)‫وهو وهللا بعد هذا له نبأ عظيم وخطر جليل وقد خطب إليكم رغبة في كريمتكم خديجة وقد بذل لها من الصداق (كذا‬
“የኢብራሂም ዝርያ፣ የቤቱ ጠባቂ፣ የሐጃጆች አገልጋይ ላደረገን አምላክ ምስጋና ይድረሰው። ይህ የወንድሜ
ልጅ ሙሐመድ በገንዘብ በኩል ድሃ ቢሆንም በመልካም ስብእናና በአስተዋይነት ከየትኛውም ወንድ ሚዛን
ይደፋል። ገንዘብ ደግሞ አላፊና ጠፊ ነገር ነው። ከዚህ በተጨማሪም ሙሐመድ ታላቅ እድል ያለው ሰው
ነው። ልቅናችሁን በመሻትም ኸዲጃን ለጋብቻ ጠይቋታል። ይህን ያህል ጥሎሽም ይጥላል።”

የኸዲጃ ቤተሰቦች ተስማሙ። ጋበቻውም ተፈጸመ። ያኔ የርሳቸው እድሜ 25 ዓመት ሲሆን፣ የርሷ ደግሞ
40 ዓመት ነበር። ኸዲጃ እርሳቸውን ከማግባቷ በፊት ሁለት ባሎችን አግብታ ፈትታለች።

መሠረት-አልባ ሂስ

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከኸዲጃ (ረ.ዐ) ጋር ያደረጉት ጋብቻ ለስጋዊ ሐሴት ብዙም ትኩረት የማይሰጡ እንደነበሩ
ያመለክታል። እንደሌሎች የእድሜ እኩዮቻቸው ወጣቶች ስጋዊ ደስታን የሚሹ ቢሆን ኖሮ በእድሜ
ከርሳቸው የምታንስ፣ ቢያንስ ቢያንስ የእድሜ እኩያቻውን ያገቡ ነበር። እርሷን ለማግባት የወሰኑት
ክብሯንና መልካም ስብእናዋን ተመልክተው ነበር። በዘመነ መሐይምነት ንጹህና ከአጓጉል ድርጊት የተጠበቀች
እንደነበረች ተመስክሮላታል። (የአንተም የትዳር ጓደኛ ምርጫ የነብይህን አርአያነት የተከተለ ይሁን።)

ይህ ጋብቻ እመት ኸዲጃ (ረ.ዐ) በ56 ዓመት እድሜያቸው እስከሞቱበት እለት ድረስ ቀጥሏል። ነቢዩም
(ሰ.ዐ.ወ) ሌላ ሴት የማግባት ሐሳብ ሳይኖራቸው እድሚያቸው 50ዎቹን ተሻገረ። ወንድ ልጅ ብርቱ የወሲብ
ፍላጎቱን ለማርካት ሲል ብዙ ሚስቶችን ለማግባት የሚከጅለው ከ25-50 ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ
መሆኑ ይታወቃል።

ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በኸዲጃ (ረ.ዐ) ላይ ሌላ ሴት የመደረብ ሐሳብ ሳያድርባቸው ይህን የእድሜ
ክልል አለፉ። ቢፈልጉ ኖሮ በርካታ እንስቶችን ያገኙ ነበር። የሕብረተሰቡ ባህልም ይደግፋቸውዋል። ኸዲጃ
(ረ.ዐ) አግብታ የፈታች እና በእድሜም የርሳቸው እጥፍ ልትባል የምትችል ሆና እያለ ቢያገቧትም ከርሷ ጋር
ሌላ እንስት ሳያገቡ አብረዋት ኖረዋል። ይህ እውነታ ለእስልምና የበረታ ጥላቻ ያላቸው ሚሽነሪዎችና
ኦሪየነታሊስቶች፣ እንዲሁም የነርሱ አገልጋይ፣ የአስተሳሰባቸው አቀንቃኝ የሆኑ አምላክ የለሾችና ዓለማዊያን
የሚሰነዝሩትን ክስ ባዶ የሚያስቀር ነው። እነዚህ ወገኖች የአላህን መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጾታዊ ስሜት
ያጠቃቸው አድርገው ለመሳል ጥረዋል። ዓላማቸው እውነትን መፈለግ ሳይሆን እምነትን ማናጋት፣
የርሳቸውን አርአያነት ጥላሸት መቀባትና የወሲብ ስሜትን እሳት ማቀጣጠል በመሆኑ ሂሳቸው አያስገርምም።

ለስጋዊ ስሜቱ ተገዥ የሆነ ሰው እንደ ዐረቢያ ባለ በብክለት የተከበበ ክልል ውስጥ እየኖረ፣ በዙሪያው
በሚተራመሰው የብክለት ማእበል ሳይሳብ እስከ 25 ዓመት እድሜው ንጹህና ጥብቅ ሆኖ ሊኖር አይችልም።
ከዚያ በኋላም በእጥፍ እድሜ የምትበልጠውን ፈት ሴት ለማግባት፣ ብሎም በዙሪያው ወዳሉ በርካታ
እንስቶች አይኑን ሳይጥል፣ የፈለጋትን ሴት ለማግኘት ያለውን ሰፊ እድል ሳይጠቀም እድሜውን ሙሉ
ከአዛውንት ሚስቱ ጋር ለመኖር አይፈቅድም።

ከኸዲጃ (ረ.ዐ) ሕልፈት በኋላ ዓኢሻን (ረ.ዐ) እና ሌሎች እንስቶችን ማግባታቸው በነቢዩ ሙሐመድ
(ሰ.ዐ.ወ) ልቅናና በምሉእ ባህሪያቸው ላይ ያለንን እምነት የሚያጠናክሩ ሰበቦችንና ጥበቦችን ያዘሉ ናቸው።
የጋብቻዎች ምክንያቶች ምንም ይሁኑ ምን የእስልምና ጠላቶች እንደሚያናፍሱት ስጋዊ ስሜቱን
ለማስተናገድ ሊሆን ፈጽሞ አይችሉም። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይህ ፍላጎት ቢኖራቸው ኖሮ ሊያስተናግዱበት
በሚችሉበት ተፈጥሯዊ ጊዜ ባስተናገዱት ነበር። በዚያ ላይ ያኔ ከየትኛውም ሐሳብና ሐላፊነት ነጻ ስለነበሩ
ይህን ጥሪ ለማስተናገድ እንቅፋት የሚሆናቸው ነገር አልነበረም።

ሲራ ክፍል 4 –
በካዕባ ግንባታ መሳተፋቸው
ካዕባ በአላህ ስም፣ አላህን በብቸኝነት ለማምለክ የተገነባ የመጀመሪያው ቤት ነው። አባታችን ነብዩ
ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ከጣኦት አምልኮ ጋር ከፍተኛ ፍልሚያ ካደረጉ በኋላ ከአላህ በሆነ ትእዛዝ ካዕባን አነጹ።

َ‫س َما ِعي ُل َربانَا تَقَبا ْل ِمناا إِناكَ أَنت‬ ِ ‫َو ِإ ْذ َي ْرفَ ُع إِ ْب َرا ِهي ُم ا ْلقَ َوا ِع َد ِم َن ا ْلبَ ْي‬
ْ ‫ت َو ِإ‬
‫س ِمي ُع ا ْلعَ ِلي ُم‬
‫ال ا‬
“ኢብራሂምና ኢስማኢልም ‘ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል። አንተ ሰሚውና ዐዋቂው አንተ ነህና’ የሚሉ ሲኾኑ
ከቤቱ መሠረቶቹን ከፍ ባደረጉ ጊዜ (አስታውስ)።” (አል-በቀራህ 2፤ 127)

ካዕባ ከዚህ በኋላ ለብዙ አደጋዎች ተጋልጧል። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በነብይነት ከመላካቸው ከጥቂት አመታት
በፊት መካን ያጥለቀለቀው ሐይለኛ ጎርፍ ይጠቀሳል። የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በነብይነት ከመላካቸው
በፊት ካዕባን ለማደስ በተደረገው ጥረት ላይ በንቃት ተሳትፈዋል፤ በትከሻቸው ድንጋይ እየተሸከሙ ያቀብሉ
እንደነበር ተዘግቧል። ያኔ እድሜያቸው 35 ዓመት እንደነበር ዘገባዎች ያመለክታሉ። ቡኻሪ እንደዘገቡት
ጃቢር ኢቢን ዐብደላህ (ረ.ዐ) የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡-

‫ اجعل إزارك‬: ‫ فقال العباس للنبي صلى هللا عليه وسلم‬، ‫ ذهب النبي صلى هللا عليه وسلم والعباس ينقَلن الحجارة‬،‫لما بنيت الكعبة‬
‫ أرني إزاري فشده عليه‬: ‫فخر إلى األرض وطمحت عيناه إلى السماء فقال‬
ّ ، ‫على رقبتك‬

“ካዕባ በሚገነባ ጊዜ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እና አጎታቸው ዐብባስ (ረ.ዐ) ድንጋይ ያቀብሉ ነበር። ዐብባስም ለነቢዩ
‹‹ሽርጥህን ከአንገትህ ላይ ደልድለህ ተሸከም›› አሏቸው። ነቢዩም እንደተባሉት ሲያደርጉ ራሳቸውን ስተው
ወደቁ። ዓይናቸው ወደ ላይ ተንጋጠጠ። ‘ሽርጡን አቀብሉኝ’ አሉና ከወገባቸው ላይ ታጠቁት።”

አላህ ይህን ያደረገው ሐፍረተ ገላቸውን ሌላ ሰው እንዳያየው ለመከላከል ነው። ይህ ክስተት እኒህ ሰው
ለታላቅ ጉዳይ የታጩ መሆናቸውን አመላካች ነበር።

ጥቁሩን ድንጋይ ወደ ቦታው የመመለስን ክብር ለማግኘት በጎሳዎች መካከል የተነሳውን ውዝግብ በማፍታቱ
ሂደትም ነቢዩ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። ውዝግቡ ወደ ጦርነት ሊያመራ ተቃርቦ ነበር። የበኒ ዐብዱዳርና
የበኒ ዓድይ ጎሣዎች በደም የተሞላ ገበታ አቅርበው ለክብራቸው በጋራ ለመፋለም እጃቸውን ከገበታው
ውስጥ በማስገባት ቃል ተገባቡ። ቁረይሾች ውዝግቡን ለመፍታት ለአራት ወይም ለአምስት ቀናት
ቢቀመጡም አልተሳካላቸውም። በመጨረሻም አቡ ኡመየህ አል- መኽዙሚ የተባለ ሰው፡- “ወገኖቼ ሆይ!
አትወዛገቡ። ሁላችሁም የምትስማሙበትን ሰው ዳኛ አድርጉ” ሲል ሐሳብ አቀረበ። “በተቀደሰው ካእባ በር
መጀመሪያ ለሚገባው ሰው ዳኝነት እናድራለን” ሲሉም ተስማሙ። ያ ሰው ታማኙ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
ሆኑ። “ይህ ታማኝ የሚሰጠንን ብይንስ በደሰታ እንቀበላለን” አሉ። ጉዳዩን አጫወቷቸው። እርሳቸውም
ኩታቸውን ዘረጉ። ሁሉም ጎሳዎች የኩታውን ጫፍ እንዲይዙ አዘዙ። ድንጋዩን አነሱና ከኩታቸው ላይ
አስቀመጡት። እንዲያነሱትም አዘዟቸው። ከሚቀመጥበት ቦታ ላይ ሲደርስ እርሳቸው ድንጋዩን ያዙና
አስቀመጡት። ይህ ክስተት የነቢዩን አዎንታዊ ስብእና፣ ጥበባቸውንና የላቀ ደረጃቸውን ያሳያል። ታዲያ
ወገኖቻቸው መልእከታቸውን ላለመቀበል ለምን ያን ያህል አንገራገሩ?

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ተቀጣጥሎ የነበረውን የጦርነት እሳት ማጥፋታቸው አራት እውነታዎችን
ይከስትልናል፡-

አንደኛ፡- አዎንታዊነት የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ስብእና መሠረታዊ አካል ነው። በካዕባ ግንባታም ሆነ
በሌሎች የማሕበረሰባቸው ጉዳዮች ላይ ያሳዩት የነበረው የላቀ ተሳትፎ ከዚህ ባህሪያቸው የመነጨ ነው።

ሁለተኛ፡- ጉዳዮችን የሚያስኬዱበትን፣ ችግሮችን የሚፈቱበትን እጅግ አስደናቂ ጥበብ ያሳያል። በተለይም
ይህን በጥበብ የከበረ የሽምግልና ሂደት ያከናወኑት በመካከላቸው ውዝግብ በተነሱባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ
ብዙ ደም ከመፍሰሱ በፊት እርቅ በማያወርዱ ጎሳዎች መሐል መሆኑ ደግሞ ለድርጊታቸው የበለጠ ድምቀት
ይሰጠዋል።

ሦስተኛ፡- ከቁረይሾች ዘንድ የነበራቸውን የላቀ የክብር ደረጃ ያመለክታል። “ታማኙ” (አል-አሚን) በሚል
ማእረግ ይጠሯቸው ነበር። በሁሉም ዘንድ ተወዳጅ ነበሩ።

አራተኛ፡- ከአላህ ዘንድ መልእከት ወርዶላቸው እርሱን ማድረስ በጀመሩ ጊዜ የነዚህ ወገኖቻቸው ልቦች
በክህደት መሞላታቸው፣ በማስተባበልና በማወክ ጥሪያቸውን ማስተናገዳቸው በጣም ያስገርማል።
በየትኛውም ቦታና ዘመን የሚገኙ የእውነት ተጣሪዎችን የሚቀናቀኑ ወንጀለኞችን እኩይ ባህሪም በጉልህ
ያሳያል።

ሲራ ክፍል 5 – የነብያችን (ሰ.ዐ.ወ)


በሂራዕ ዋሻ መገለል /ኸልዋ/
የነብያችን (ሠ.ዐ.ወ) እድሜያቸው ወደ 40 እየተቃረበ ሲመጣ፤ ከወትሮው በተለየ ከሠው መነጠልን
በተለያዩ ጊዜያት እየወደዱት መጥተዋል። አላህም ለመገለያው ቦታ የሂራዕ ዋሻን እንዲወዱት አድርጓቸዋል።
ሂራዕ ማለት ከመካ በሰሜን ምዕራብ የሚገኝ ተራራ ሲሆን ነቢያችንም ዋሻው ውስጥ ለብዙ ሌሊቶች
አንዳንዴም አስር ሌላ ጊዜም ከዘያ ለሚዘልቁ ቀናት አላህን በመገዛት ያሳልፉ ነበር።

ወደ ቤታቸው ሲመለሱም ብዙም ሳይቆዩ ለሚቀጥለው ኸልዋ በአዲስ ስንቅ ይቋጥሩ ነበር። በእነዚህ
ኸልዋዎች (ብቸኝነት) በአንደኛው ላይ ወህይ እስከመጣላቸው ድረስ በዚህ ሁኔታ አሳልፈዋል።

ኸልዋ /አላህን ለመገዛት ብቸኝነትን በመምረጥ መገልል/

ያኔ የነብያችን ቀልብ እንዲህ በፍቅር የገዛው ኸልዋ፤ ለአጠቃላይ ሙስሊሞች በተለይ ደግሞ ወደ ኢስላም
ለሚጣሩ ዳዒዎች እጅግ ከፍተኛ የሆነ ጥቅም ያለበት ነው። ከዚህም ውስጥ፡-

1. በቀልብ ውስጥ የአላህን ሙሀባ /ውዴታ/ ማሳደግ

አእምሮን ብቻ በእውቀት ማጥገብ በቂ አይደለም። ይህማ ቢሆን ኖሮ ኦረይንታሊስቶች /ሙስሊም ያልሆኑ


ኢሰላምንና ሌሎች የምስራቅ ሀይማኖትን የሚያጠኑ/ ከሙስሊሞች የበለጠ አሏህና የነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ)
ወዳጅ ይሆኑ ነበር። ለመሆኑ ከምሁሮች አንድም እራሱን አሳልፎ ለአንድ ሂሳባዊ የስሌት ህግ አለያም
አልጀብራ ጥያቄ መስዋእትነት የሠጠ ሰምተሀልን?… ይልቁንም በአላህ ከማመን በኋላ ወደ እሱ ውዴታ
መዳረሻ መንገዶች በዋነኝነት፡-

1. የታላቅነቱ ማረጋገጫ የሆኑ ምልክቶችን፤ ውለታውና ፀጋዎቹን በሠፊው ማስተንተን


2. በምላስና በቀልብ በብዛት እሱን ማውሳት
3. ፈርድ የሆኑ ነገሮች በጥንቃቄ ተጠባብቆ መስራት ሡና /ነዋፊል/ የሆኑትንም ማባዛት

ይህ ሁሉ ሊገራ የሚችለው በተደጋጋሚ ከአላህ ጋር ብቸኝነትን /ኸልዋ/ በማዘውተር ነው።

2. ነፍስን መተሣሠብና በሽታዎቿን ማከም

የሰው ልጅ ነፍስ የብዙ በሽታዎች መናኸሪያ ናት። ታዲያ ከነዚህ በሽታዎች መካከል ከሰዎች ተነጥሎ ነፍስን
በመተሳሰብና ያለፈቻቸውን ድንበሮች እያሰታወሱ ጉድለቶቹዋን በማሰተዋል እንጂ የማይታከሙ አሉ።
ብቻውን ሆኖ ሲያስተነትን ግን የሰው ልጅ የነፍስያ እውነታ ይገለጽለታል። ምን ያህል ነፍስ አላህን ፈላጊና
ደሀ እንደሆነችና በእያንዳንዷ ቅጽበት የእሱን (አላህ) እርዳታ ፈላጊ መሆኗ፤ ሠዎች እሱን ለመጥቀምም ሆነ
ለመጉዳት የማይችሉ ደካሞች መሆናቸውን ይደርስበታል። ስለሆነም ሙገሳቸውም ሆነ ወቀሳቸው ውጤት
አልባ እንደሆነ ይገለጥለታል፤ ይህና ሌሎችም መሠል እውነታዎች ፍንትው ብለው ሲታዩት ስራውን ለአላህ
ብቻ አጥርቶ ይሰራል፤ ይተናነሳል… በተደጋጋሚ መገልልን /ኸልዋን/ በማብዛቱ የተነሳ ባገኘው ብርሃን
የነፍስን እውነታ ሲረዳ አብሮ የነፍስ ጣጣ /መዘዞች/ አብረው ይገረሰሳሉ /ይወገዳሉ/።

ተግባራዊ ልምምድ፡-

ይህ ሁሉ የሚሆነው ከዱንያ ጭንቅንቅ፣ ከጩኅቷ፣ ከከንቱ ብለጭልጯ በቀን፣ በለሊት፤ በወራትና፤


በዓመታት ለተወሰኑ ግን ተደጋጋሚ ለሆኑ ወቅቶች ገለል ብሎ ራስን መመልከት ሲቻል ነው። ለዚሁም
ለምሳሌ

1. እዕቲካፍ በረመዷን የመጨረሻው አስር ቀናት ወይም አንዲት ምሽት ከሁሉም ወራት በመስጂድ
ውስጥ ማሳለፍ
2. በሁሉም ሌሊቱ የመጨረሻው 1/3ኛ ክፍል ላይ የማገባደጃ ጥቂት የኢስቲግፋር ወቅት
3. በጠዋት እና በማታ ውዳሴ /አዝካር/ ወቅት
4. ከመኝታ በፊት ነፍስን በመተሳሰቢያና የመኝታ ዚክር በሚደረግበት ወቅት
5. መስጂድ ቀደም ብሎ ለሰላት መግባትና ሰላትን ቁጭ ብለው እየተጠባበቁ
6. ከሰላት በኋላ ቁጭ ብሎ ዱዓ በማድረግ ወቅት ላይ
7. ሌላው ቢቀር አዛን እየሰማ ከሙአዚኑ ተከትሎ ካለ በኋላም ሊሆን ይችላል

ከላይ የተጠቀሱት ጊዜያት ሁሉም ቀልብ ከዱንያ ጋ ያለውን መገናኛ በመቁረጥ ትኩረቱን ትልቅና አሸናፊ ወደ
ሆነው አላህ በአዲስ መልክ የሚያቆራኝበት ነው።

የወህይ መጀመር

ኢማሙል ቡኻሪ እንደዘገቡት እናታችን ዐዒሻ /ረ.ዐ./ የወህይ አጀማመር እንዴት እንደነበር ስትገልፅ እንዲህ
ትላለች።

‫ ثم حبب إليه الخَلء وكان يخلو‬،‫ فكان َل يرى رؤيا إَل جاءت مثل فلق الصبح‬،‫ الرؤيا الصالحة في النوم‬ ‫أول ما بدء به رسول هللا‬
‫ حتى جاءه الحق‬،‫بغار حراء فيتحنث فيه الليالي ذوات العدد قبل أن ينزع إلى أهله ويتزود لذلك ثم يرجع إلى خديجة فيتزود لمثلها‬
: ‫ اقرأ‬:‫ فقال ما أنا بقارئ قال فأخذني فغطني حتى بلغ منى الجهد ثم أرسلني فقال‬: ‫ فجاءه الملك فقال له اق رأ‬. ‫وهو في غار حراء‬
‫ ما أنا بقارئ فأخذني وغطني الثالثة ثم أرسلني فقال‬: ‫ فقلت‬:‫ فأخذني وغطني حتى بلغ منى الجهد فقال اقرأ‬،‫فقلت ما أنا بقارئ‬
.‫سانَ َما لَ ْم يَ ْعلَ ْم‬
َ ‫علا َم اإلن‬ َ ْ‫ ا ْق َرأ‬. ‫ق‬
َ ‫ الاذِي‬. ‫وربُّكَ األَك َْر ُم‬
َ . ‫علا َم بِا ْلقَلَ ِم‬ ٍ َ ‫عل‬ ْ ‫ ا ْقرأْ بِا‬:
َ ‫ َخلَقَ اإلن‬. َ‫س ِم َر ِبّكَ الاذِي َخلَق‬
َ ‫سانَ مِ ْن‬

“መጀመሪያ ጥሩ ጥሩ ህልሞች በእንቅልፋቸው ያዩ ነበር ታዲያ ያዩዋቸው ህልሞች ልክ እንደ ንጋት ጎህ


በእውን ይከሰቱ ነበር። ከዚያ በኋላ በሂራ ዋሻ ዉስጥ መገለልን ወደዱ በዚህም ዋሻ ዉስጥ ብቻቸውን ለዚህ
የሚሆን ስንቅን ለመሰነቅ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሳይመለሱ ብዙ ሌሊቶችን ያሳልፉ ጀመር። ከዚያም ወደ ኸዲጃ
(ረ.ዐ) ይመለሱና ስንቅ ይሰንቃሉ በእንዲህ አይነት ሁኔታ በሂራ ዋሻ ዉስጥ ከጌታቸው የሆነው ሃቅ
እስከመጣላቸው ድረስ ቀጠለው ነበር።

መላኢካው መጥቶ ‘አንብብ’ አላቸው ‘እኔ አንባቢ አይደለሁም’ በማለት መለሱ፤ ይዞኝ ነፍሴ እስክትወጣ
ድረስ ጭምቅ አደረገኝና ለቀቀኝ። እንደገና ‘አንብብ’ አለኝ ‘እኔ አንባቢ አይደለሁም’ ስል መለሰስኩኝ። ይዞኝ
በድጋሚ ነፍሴ እስክትወጣ ድረስ ጭምቅ አድርጎኝ ለቀቀኝና ‘አንብብ’ አለኝ እኔም ‘አንባቢ አይደለሁም’
አልኩት። ለሶስተኛ ጊዜ ነፍሴ ልትወጣ እስክትደርስ ጨምቆ ለቀቀኝና እንዲህ በማለት ተናገረኝ ‘አንብብ በዚያ
(ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም። ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)። አንብብ ጌታህ በጣም ቸር
ሲኾን፤ ያ በብዕር ያስተማረ፤ ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን።’”

አላህ በፍፁም የማያዋርዳቸው ሰዎች ባህሪ

ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ልባቸው በጣም እየመታና እየተርገፈገፉ ተመልሰው ወደ ባለቤታቸው ኸዲጃ ቢንቲ
ኹወይሊድ (ረ.ዐ) ዘንድ “አከናንቡኝ፤ አከናንቡኝ” /ዘሚሉኒ ዘሚሉኒ/ እያሉ ገቡ። የያዛቸው ፍርሀት
እስኪለቃቸው ድረስ አከናነቧቸውና ለኸዲጃ ክስተቱን ሁሉ ነገሯት። እኔ ለነፍሴ ፈራሁ! አሉ። ኸድጃም
(ረ.ዐ)፡-

‫ إنك لتصل الرحم وتحمل الكل وت ُكسب المعدوم وتقرى الضيف وتعين على نوائب الحق‬،ً‫كَل وهللا َل يخزيك هللا أبدا‬

“በፍፁም! ወላሂ አላህ በጭራሽ አያዋርድህም አንተኮ ዝምድናን የምትቀጥል፤ የተቸገረን የምትረዳ፤
እንግዳን የምታከብር፤ ለሌላቸው ሰጪና ሀቅ ላይ የምትተባበር ነህ።”

የአዋቂ ምስክርነትና የተዋረድ ፈለግ

እናታችን ኸዲጃ (ረ.ዐ) ነቢያችንን ወደ ወረቀት-ኢብኑ ነውፈል ዘንድ ወሰደቻቸው። ወረቀት ኢብኑ ነውፈል
የአጎቷ ልጅ ሲሆን በጃሂሊያው ዘመን ክርስትናን ከተቀበሉት መሃል ነበር። ከወንጌልም አላህ የፈለገለትን
በኢብራይስጥ ቋንቋ ይፅፍ ነበር። ከእርጅናም ብዛት ዓይኑ ታውሮ ነበር። ኸዲጃም የአጎቴ ልጅ ሆይ
የወንድምህ ልጅ የሚልህን እስቲ ስማ ስትለው ወረቀትም ለነቢያችን የወንድሜ ልጅ ሆይ ምንድነው
የሚታይህ በማለት ጠየቃቸው።

ነብያችንም (ሰ.ዐ.ወ) የታያቸውን ነገር ነገሩት ወረቀትም “ይህማ በሙሳ (ዐ.ሰ) ላይ የወረደው ናሙስ ነው
(ጂብሪል/ወህይ) ዋ! ጠንካራ ወጣት ሆኜ በነበር! ዋ! ያኔ ወገኖችህ ከሀገርህ ሲያስወጡህ በህይወት ሆኘ
በነበር!” አለ ነብያችንም “እውን ያስወጡኛልን” አዎ አንድም ሰው አንተ በመጣህበት ተመሳሳይ የመጣ
በጭራሽ የለም ጠላት የሚያፈራ ቢሆን እንጂ ቀኑን ካደረሰኝ ሁነኛ እገዛን ባገዝኩህ ነበር።” ወረቀት ግን
ብዙም ሣይቆይ ሞተ፣ ወህይም ለተወሰኑ ጊዜያት ተቋረጠ።

ቡኻሪ ከጃቢር ኢብኑ አብደላህ (ረ.ዐ) እንደዘገበው ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ስለወህይ መቋረጥ ሲናገሩ

‫ فإذا الملك الذي جاءني بحراء جالس على كرسي بين السماء واألرض‬،‫بينما أنا أمشى إذ سمعت صوتا ً من السماء فرفعت بصري‬
‫ فحمى الوحي وتتابع‬،‫ والرجز فاهجر‬: ‫ يا أيها المدثر قم فأنذر – إلى قوله‬: ‫ زملوني زملوني فأنزل هللا‬: ‫ فرجعت فقلت‬،‫فرعبت منه‬

“በመራመድ ላይ ሳለሁ ከሠማይ ድምጽ ሠማሁና አይኔን ቀና ሳደርግ ያ ሂራ ዋሻ ውስጥ የመጣብኝ


መላኢካ በምድርና ሰማይ መካከል በሆነ ዙፋን ላይ ተቀምጧል። በጣም ደነገጥኩኝ፤ በፍጥነትም ተመልሼ
‘አከናንቡኝ! አከናንቡኝ!’ አልኩ። አላህም ‘አንተ (ልብስህን) ደራቢው ሆይ። ተነስ አስጠንቅቅም። ጌታህንም
አክብር። ልብስህም አጥራ። ጣኦትንም ራቅ። ማብዛትንም የምትፈልግ ኾነህ (በረከትን) አትለግስ። ለጌታህም
ታገስ።’ የሚለውን አንቀድ አወረደ።”
ቀጥሎም ወሕይ ተቋረጠ፤ ወህይ የተቋረጠበትን የግዜ ቆይታ በተመለከተ የተለያዩ ንግግሮች የተሠነዘሩ
ሲሆን ትክክለኛው ለተወሰኑ ቀናት ነበር የሚለው ነው። ኢብኑ ሠዕድ ከኢብኑ ዐባስ ያወሩት ይህን የሚደግፍ
ነው (ረሂቀል መኽቱም፣ ሠፊዩ ረህማን ሙባረክ ፋሪ)።

ሲራ ክፍል 6 – ሚስጥራዊው የዳእዋ


ሂደት

ነብያችን (ሠ.ዐ.ወ) ለአላህ ትእዛዝ አዎንታዊ ምላሽ መስጠት ጀምረዋል፤ አላህን አንድ ብቻ አድርጎ
ማምለክና ጣኦታትን ወደ መተው መጣራትን ተያያዙት። ነገር ግን ቁረይሾች ለጣኦቶቻቸው እና ለሽርክ
አምልኮቶቻቸው ካላቸው ጭፍን ታማኝነትና ወገንተኝነት አንጻር ጥሪው ድንገተኛ እናዳይሆንባቸው
በመስጋት ዳዕዋውን በሚስጥር ያካሂዱ ነበር። በቁረይሾች መቀማመጫ አደባባዮች በግልፅ ዳዕዋ
አያደርጉምም ነበር። በጣም የሚቀርባቸው ዘመድ ወይም ከዚህ በፊት ለሚያውቁት ሰው ካልሆነ በስተቀር
ጥሪያቸውን አያደርጉለትም ነበር።

የመጀመሪያዎቹ መጀመሪያዎች
መጀመሪያ ወደ ኢስላም ከገቡት ውስጥ፤ ኸዲጃ (ረ.ዓ)፣ ዐሊይ ኢብኑ አቡጧሊብ የነብያችን (ሠ.ዐ.ወ)
ያሳደጉትና ኻዲማቸው (አገልጋይ) የነበረው ዘይድ ኢበኑ ሐሪሳ፣ አቡበክር ኢብኑ አቢቁሀፋ፣ እና አቡበክር
ሲዲቅ ወደ ኢስላም የጠሯቸው ዑስማን ኢብኑ ዐፋን፣ ዙበይር ኢብኑል ዐዋም፣ ዐብድረህማን ኢብኑ ዐውፍ፣
ሰእድ ኢብኑ አቢወቃስ … እንዲሁም ሌሎችም ይጠቀሱ ነበር።

የተርቢያ ስብስብ በአርቀም ቤት

እነዚህ ሰሀቦች ከነብያችን ጋ በሚስጢር ይገናኙ ነበር። አንድኛቸው መስገድ አልያም ኢባዳ ማድረግ ሲፈልግ
ከቁረይሾች እይታ ለመደበቅ መካ ውስጥ ከሚገኙ ገደላ ገደሎች ወደ አንዱ ይሄዱ ነበር። ወደ ኢስላም
የሚገቡት ወንድና ሴቶች ቁጥር ከሰላሳ መብለጡን የተመለከቱት ነቢይ ከእነርሱ መካከል የአርቀም ኢብኑ
አቢ አርቀምን ቤት በመምረጥ እዚያ እየተገናኙ የዳእዋውን ጉዳይ ያስተምሯቸውና ተርቢያን ይሰጧቸው
ገቡ። በዚህን ወቅት ዳዕዋው ደርሷቸው ወደ ኢስላም የገቡ ሰዎች ቁጥር አርባ አካባቢ ይደርስ ነበር። ታዲያ
አብዛኞቹ ድሆችና ባሪያዎች በቁረይሽም ዘንድ ቦታ የማይሰጣቸው ግልሰቦች ነበሩ።

የዳእዋው ድብቅነት ለዳዕዋው ችግርን ከመስጋት እንጂ ለነፍስ ከመፍራት የመነጨ አልነበረም። ነብያችን
(ሠ.ዐ.ወ) በመጀመሪያዎቹ ሶስት አመታት የድብቅ ዳዕዋን የመረጡበት ምክንያት ለነፍስ ጉዳትን ከመስጋት
የመነጨ አልነበረም። ዳእዋውን ከጅምሩ ለሁሉም አይነት ሰዎች ግልጽ እንዲያደርጉት ከጌታቸው ትእዛዝ
ቢመጣ ኖሮ ከፊታቸው ሞት ቢጠብቃቸው እንኳን ለመፈጸም ምንም ሰዓት አያባክኑም ነበር።

ነገር ግን የመጀመሪዎቹን የዳዕዋ ግዜያት ዳዕዋውን በድብቅና በሚስጥር ያምኑልኛል እንዲሁም ዳዕዋውን
ይቀበሉኛል ብለው ለጠረጠሯቸው ሰዎች ብቻ እንዲያደርጉ አላህ አሳወቃቸው። ይህም የሆነው በአላህ ላይ
የሚኖረን መሰረታዊ ኢማን እንዳይበረዝና ቀጥሎ የሚመጡ ዳዒዎች በአላህ ላይ ብቻ መተማመን እና
መታገዝ ላይ እንዲያተኩሩ ትምህርት እዲሆን ነው።

ከዚህ በመነሳት በየትኛውም ዘመን የሚኖሩ የኢስላማዊ ዳዕዋ ባለቤቶች ዳእዋቸውን የሚያደርጉበትን ስልት
(በሚስጢር ወይስ በግልፅ የሚለውን) ካሉበት ዘመን ሁኔታና ተጨባጭ አንፃር መወሰን ይችላሉ ማለት
ነው። ይህ የኢስላም ሸሪዐ ገር ከመሆኑ አንፃር የተቀመጠ ሲሆን ስልቱ የነብያችን (ሠ.ዐ.ወ) ሲራ ላይ
የተመረኮዘ እንዲሁም ከላይ የተጠቀሱትን አራት ሂደቶችን መሰረት ያደረገ በዋነኝነት የሙስሊሞችና
የዳእዋውን መስላሀ (ጥቅም) ከግምት ያስገባ መሆኑ ነው።

ለዚህም ነው አብዛኛዎቹ የፊቅህ ምሁራን፤ ሙስሊሞች በቁጥር ሲያንሱ ወይም በዝግጅት ደካማ ሲሆኑ፣
ጠላቶቻቸው ላይ ምንም አይነት ተፅእኖ መፍጠር ሳይችሉ እንሸነፋለን ወይም ጠላቶቻችን ይጎዱናል ብለው
ከጠረጠሩ ነፍስን የመጠበቅ ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ የተስማሙት። ምክንያቱም ዲንን ጠብቆ
ለማቆየት በየትኛውም መልኩ ህይወትን ጠብቆ ማቆየት የግድ ይለናልና።

እውነታው ላይ ላዩን ስንመለከተው ለነፍስ ቅድሚያ መስጠት ይመስላል። ነገር ግን ጉዳዩን በጥልቀት
ከተመለከትነው በተጨባጭ ዲንን ጠብቆ ማቆየት ሆኖ እናገኘዋለን። በዚህ እይነት የሙስሊሞችን ነፍስ
በሰላም ጠብቆ ማቆየት፤ ወደፊት እንዲጓዙና ሌሎች ክፍት የሆኑ ሜዳዎች (የዳእዋ ዘርፍና ስልቶች) በተገኙ
ጊዜ ትግል እንዲያደርጉ እድል ስለሚሰጣቸው ለዲኑ ቅድሚያ ተሰጥቷል እንላለን። ይህ ሳይሆን ቢቀርና
ሙስሊሞች ቢጠፉ በዲኑ ላይ የመጣ ጉዳት ተደርጎ ይወሰዳል።

ደካሞችና ድሃዎች ቀድመው ለምን ተቀበሉ?

የሲራ ድርሳናት እንደሚገልፁልን በመጀመሪያዎቹ የዳእዋ ወቅቶች ወደ ኢስላም የገቡት ሰዎች በአብዛኛው
ድሆች ደካሞችና ባሪያዎች የተቀላቀሉበት ነበር። ታዲያ ከዚህ ጀርባ ያለው ጥበብ ምንድን ነው? ኢስላማዊ
መንግስቱስ ሲመሰረት በነዚህ ሰዎች መሰረት ላይ የመገንባቱ ሚስጥርስ ምንድንነው?

መልሱ፡- ይህ የነቢያት ዳዕዋ የመጀመሪያው ሂደት የሚያሰተናግደው ተፈጥሮኣዊ ክስተት ነው። ሚስጥሩም፤
አላህ ሁሉንም መልእክተኞች ሲልካቸው ከሰው ልጅ አገዛዝና የስልጣን ተፅእኖ ወደ አላህ ብቸኛ አስተዳደርና
ስልጣን ነፃ ያወጡ ዘንድ ነው። ራሳቸውን አማልክትና ፈላጭ ቆራጭ አድርገው የበላይ ነን የሚሉትን
አምባገነኖች ምንነት የሚያዋርድና የሚያንኮታኩት ጥሪ ነው።

ይህም ከደካሞች፣ ከተዋረዱ እና ከባሪያዎች ሁኔታ ጋር ስለሚገጣጠም ለጥሪው አዎንታዊ ምላሽ ሲሰጡ
በአፀፋው እነዚያ አምለክ ነን አስተዳዳሪ ነን ባዮች ከመኩራራትና ከጥላቻ በዘለለ ለኢስላማዊው ጥሪ
መሰናክል ሆነው ይቆማሉ።

ይህ እውነታ የበለጠ ግልፅ እንዲሆንልህ በፋርሱ ጦር መሪ ሩስቱም እና በሰዕድ ኢብኑ አቢ ወቃስ ጦር ተራ


ወታደር ረቢዕ ኢብን ዓምር መካከል በቃዲሲያ ጦርነት ወቅት የተካሄደውን ንግግር ተመልከት። ሩስቱም
እንዲህ አለው “ምንድን ነው እኛን እንድትዋጉን እና ሀገራችንን ዘልቃችሁ እንደትመጡ ያደረጋችሁ?” ረቢዕ
ኢብኑ አሚርም “እኛ የመጣነው በፍላጎት ሰዎችን ከሰዎች ባርነት ወደ አላህን ብቻ ወደ ማምለክ ነፃነት
ለማምጣት ነው” አለው፤ ከዚያም ከቀኝ እና ከግራ ለሩስቱም ሩኩዕ ያደረጉ ሰዎችን ሰልፋ ተመለከተና
በመገረም “በእርግጥ ከዚህ በፊት ስለናንተ ህልሞች ይደርሱን ነበር፤ አሁን በተጨባጭ ሳያችሁ ግን ከናንተ
በታች ቂል የሆነን ህዝብ አልተመለከትኩም። እኛ ሙስሊሞች እኮ ከፊላችን ከፊሉን ባሪያ አደርጎ እኮ
አይገዛውም! እናንተም እንደኛ በመካከላችሁ በመልካም እንደምትውሉ ነበር የማስበው ምናልባትም በጣም
ጥሩ ከሰራችሁት ነገር አንዳችሁ የአንዳችሁ ጌታ (አምላክ) እንደሆናችሁ እየነገራችሁኝ መሆኑ ሊሆን ይችላል
……”

ይህኔ ደካሞቹ እርስበርሳቸው መጠቃቀስና ማጉረምረም ጀመሩ “ወላሂ ይህ አረብ እውነት ተናገረ” ነገር ግን
መሪዎቹ እና አስተዳዳሪዎቹ የረቢዕን ንግግር ውስጣዊ ማንነታቸውን ያፈራረሰ መብረቅ ሆነባቸው።
እርስበርስም “በእርግጥ ረቢዕ የወረወረው ንግግር ባሮቻችንን ወደ እርሱ ሳይጎትታቸው (ሳያዘናብላቸው)
የሚቀር አይደለም” አሉ።

ሲራ ክፍል 7 – ይፋዊ ጥሪ

ኢብኑ ሀሺም “ሰዎች በብዛት ከሴትም ከወንድም ወሬው በመካ ውስጥ እስኪሰራጭ ድረስ ወደ ኢስላም
ገቡ። ይህ ወቅት ረሱል ዳእዋውን በድብቅ ማድረግ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ በአላህ ትዕዛዝ ግልጽ
እስከወጣበት ጊዜ የነበሩት ሶስት አመታት ናቸው።”

ይህኔ ረሡል (ሠ.ዐ.ወ) “የታዘዝክበትን ነገር በይፋ ግለፅ። አጋሪዎችንም ተዋቸው።” ለሚለው የአላህ ትዕዛዝ
ምላሽ መስጠት እና መተግበር ጀመሩ። ሶፋ ተራራም ላይ ወጡና “የፈህር ጎሳዎች፤ የኡደይ ጎሳ ልጆች ….”
እያሉ መጣራትቱን ተያያዙት። በዙሪያቸው ሰዎች ይሰባሰቡ ጀመር፤ ራሳቸው መምጣት ያልቻሉትም ምን
እንደሆነ ለማወቅ መልክተኛ ላኩ።
ነብዩም (ሠ.ዐ.ወ) “በሸለቆው አቅጣጫ ወራሪ ሊወጋችሁ እየመጣ ነው ብላችሁ ታምኑኛላችሁን?” ብለው
ጠየቁ “ውሸት ከአንተ አይተን አናውቅም” ብለው መለሱላቸው ነቢዩም “እንግዲያውስ ብርቱ ቅጣት
እንዳያገኛችሁ አስጥንቃቂያችሁ ነኝ” በማለት ሲናገሩ አቡ ለሃብ በቁጣ ቀኑን ሙሉ የከሰርክ ሆነህ ዋል!
የሰበሰብከን ለዚሁ ነውን? አላህም “የአቡ ለሃብ እጆች ከሰሩ (ጠፉ)፤ እርሱም ከሰረ።” የሚለው የቁርአን
አንቀፅ አወረደ። ከዚያም ነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ) ወረዱ። “ቅርብ ዘመዶችህን አስጠንቅቅ” ለሚለው የአላህ
ቃልም እንዲሁ ምላሽ ሰጡ። በዙሪያቸው ያሉትን ዘመዶችና የቅርብ ቤተሰቦች ሰበሰቡና “እናንተ የካዕብ
ኢብኑ ሉአይ ልጆች ሆይ እራሳችሁን ከእሳት አድኑ። የሙረት ኢብኑ ካእብ ልጆች ሆይ እራሳችሁን ከእሳት
አድኑ፤ የዐብድ ሸምስ ልጆች ሆይ እራሳችሁን ከእሳት አድኑ፤ የአብድ መናፍ ልጆች ሆይ እራሳችሁን ከእሳት
አድኑ፤ የአብዱል ሙጦሊብ ልጆች ሆይ እራሳችሁን ከእሳት አድኑ አንቺ ፋጢማ ሆይ እራስሽን ከእሳት አድኚ፤
እኔ ከአላህ ዘንድ ምንም አልጠቅምሽም። ግና ዘመዶቼ ናችሁና ዝምድናችንን እንከባከባታለሁ።”

ደዕዋው በግልፅ መደረግ ሲጀምር የቁረይሽ ምላሽ ጀርባ መስጠትና ማውገዝ ሲሆን ለዚህም ከአባቶቻቸው
የወረሱትን እምነት ፈጽሞ መተው እንደማይችሉ ምክንያት በማቅረብ ነበር። አላህ ይህን እውነታ ሲናገር
ለእነርሱም

َ‫َّللاُ قَالُوا بَ ْل نَتَّبِ ُع َما أ َ ْلفَ ْينَا َعلَ ْي ِه آبَا َءنَا أ َ َولَ ْو َكان‬
َّ ‫َو ِإذَا قِي َل لَ ُه ُم ات َّ ِبعُوا َما أَنزَ َل‬
‫﴾ َو َمث َ ُل الَّذِينَ َكفَ ُروا َك َمث َ ِل الَّذِي‬١٧٠﴿ َ‫ش ْيئًا َو ََل َي ْهتَدُون‬ َ َ‫آ َبا ُؤ ُه ْم ََل َي ْع ِقلُون‬
َ‫ي فَ ُه ْم ََل يَ ْع ِقلُون‬ ُ ‫يَ ْن ِع ُق ِب َما ََل يَ ْس َم ُع إِ ََّل دُ َعا ًء َونِدَا ًء‬
ُ ‫ص ٌّم بُ ْك ٌم‬
ٌ ‫ع ْم‬
“ለእነርሱም ‘አላህ ያወረደውን ተከተሉ’ በተባሉ ጊዜ ‘አይደለም አባቶቻችንን በርሱ ላይ ያገኘንበትን ነገር
እንከተላለን’ ይላሉ። አባቶቻቸው ምንም የማያውቁና (ወደ እውነት) የማይመሩም ቢኾኑ
(ይከተሉዋቸዋልን?) የነዚያም የካዱት (እና ወደ ቅን መንገድ የሚጠራቸው ሰው) ምሳሌ እንደዚያ
ድምጽንና ጥሪን በስተቀር ሌላን በማይሰማ (እንስሳ) ላይ እንደሚጮህ ብጤ ነው። (እነርሱ) ደንቆሮዎች፣
ዲዳዎች፣ ዕውሮች ናቸው፤ ስለዚህ እነርሱ አያውቁም።” (አል-በቀራ 2፤ 170-171)

የአማልክቶቻቸውን ዋጋ ቢስነት ሲያሳውቋቸው፤ ህልሞቻቸውን ውድቅ ሲያደርጉባቸውና ጣኦት አምልኮት


ሙጥኝ ለማለታቸው ያቀረቡትን ምክንያት ውድቅ በማድረግ የአያቶቻቸውና አባቶቻቸው ፈለግ ስለሆነ ብቻ
መሆኑን ሲያጋልጧቸው፤ አባቶቻቸውን አቅል ሁሉ እንደሌላቸው ሲናገሩ፤ ከእነርሱ ውስጥ አላህ በኢስለም
ካዳናቸው እንዲሁም ከጎናቸው ቆመው ሲከላከሉላቸው ከነበሩት ከአጎታቸው አቡ ጧሊብ ውጭ ሁሉም
ነገሩን ትልቅ ቦታ ሰጥተውት አወገዙትም፤ ፍፁም በጠላትነት ፈርጀው ለመቃወም አደሙ።

ቅድሚያ ለዘመድና ቤተሰብ


ጥያቄ፡- አላህ ለነቢዩ ለምን ዳዕዋውን ለቤተሰቦቻቸውና ዘመዶቻቸው እንዲያደርሱ ነጥሎ አዘዛቸው?

መልስ፡- እዚህ ውስጥ ባጠቃላይ በሁሉም ሙስሊም በተለይ ደግሞ እንደ ደዕዋ ሰው የተለያዩ የተጠያቂነት
ደረጃዎች እንዳሉ እንመለከታለን።

ትንሹ የተጠያቂነት ደረጃ፡- ይህ አንድ ሰው ስለ ራሱ ተጠያቂ የሚሆንበት ደረጃ ነው። ወህይ ሲጀምር
እንደተመለከትነው ያን ያህል ረዘም ያለ ጊዜ የቆየው፤ ለዚህ እርከን ተገቢውን ጊዜ ከመስጠት አንፃር ነበር።
ይህም ሙሐመድ (ሠ.ዐ.ወ) ተረጋግተው ከአላህ ዘንድ የተላኩ ነብይና የሚወርድላቸውም ወህይ ከአላህ
(ሱ.ወ) መሆኑን ለራሳቸው አምነው ልባቸው እንዲረጋጋና ከዚያ በኋላ ለሚመጣላቸው ትእዛዝ መርህና
ድንጋጌዎች እንዲዘገጁ ነበር።

ለጥቆ የሚመጣው የተጠያቂነት ደረጃ፡- አንድ ሙስሊም ስለቤተሰቦቹ እና ስለዘመዶቹ የሚኖረው


ተጠያቂነት ነው። ይህን ሓላፊነት በአግባቡ መወጣትን ስንቃኝ አላህ ቤተሰብንና ዘመዶችን ማስጠንቀቅና
ዳእዋን ለእነርሱ የማድረስ ግዴታን በይፋ ለሁሉም የማድረስ ሃላፊነትን ካዘዘ በኋላ ሆኖ እናገኘዋለን፤ ይህም
የተሰጠውን ስፍራ በሚገባ ያመላክታል። ይህን የሀላፊነት ደረጃ የመሸከሙ ሂደት ማንኛውም ቤተሰብና
ቅርብ ዘመዶች ያሉትን በሙሉ የሚያካትት ሲሆን የጥሪውም ይዘት ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ለህዝቦቻቸው
የሚያደርጉት ጥሪ ለቤተሰብና ለዘመዶች ከሚደረግ ጥሪ እምብዛም የተለየ ሆኖ አናገኘውም። ምናልባት
የመጀመሪያው በአላህ ወህይ እየተመራ ወደ አዲስ እምነትና የህይወት ጎዳና ሲጣራ ሌላኛው ይህንን ጥሪ
አድራሽና የሱ ቃል አቀባይ ከመሆኑ በስተቀር።

ሶስተኛው ደረጃ፡- አንድ አሊም ወይም ዳኢ ስለ መንደሩ ወይም ስለሀገሩ እንዲሁም አንድ አስተዳደሪ
ስለሀገሩና ህዝቦቹ የሚኖርበት ኃላፊነት ነው።

ሲራ ክፍል 8 – ጥሪውን ለማኮላሸት


ቁረይሾች ሙሀመድን (ሠ.ዐ.ወ) ማስዋሸታቸው እና ችላ ማለታቸው ከዳዕዋው እንደማይነቀንቀው ሲያዩ
በድጋሚ ቆም ብለው ማሰብ ጀምሩ፤ ይህንን ደዕዋ ለማቆምና ለማኮላሸት የሚረዱ ዘዴዎችንም መረጡ።
ይህም እንደሚከተለው ይቀርባል።

1. ማፌዝ፣ ማናናቅ፣ ማላገጥና ማስተባበል

የዚህ ስልት ጠቀሜታ ሙስሊሞችን ማዋረድና ውስጣዊ ጥንካሬያቸውን ማዳከም ነበር። ነብያችንንም
(ሠ.ዐ.ወ) የዘቀጡ ቅጥፈቶችን እና የቂል ስድቦችን ሰደቧቸው። እብድ ብለውም ይጠሯቸው ነበር።

ٌ ُ‫َوقَالُوا يَا أَيُّ َها الَّذِي نُ ِ ِّز َل َعلَ ْي ِه ال ِذِّ ْك ُر ِإنَّ َك لَ َم ْجن‬
‫ون‬
“‘አንተ ያ በእርሱ ላይ ቁርኣን የተወረደለት ሆይ! አንተ በእርግጥ ዕብድ ነህ’ አሉም።” (አል-ሂጅር 15፤ 6)

ደጋሚና ቀጣፊ ይሏቸው ጀመር፡-

ٌ َّ‫اح ٌر َكذ‬
‫اب‬ ِ ‫س‬َ ‫َو َع ِجبُوا أَن َجا َء ُهم ُّمنذ ٌِر ِ ِّم ْن ُه ْم َوقَا َل ْال َكافِ ُرونَ َٰ َهذَا‬
“ከእነርሱ የሆነ አስፈራሪም ስለ መጣላቸው ተደነቁ። ከሓዲዎቹም ‘ይህ ድግምተኛ (ጠንቋይ) ውሸታም ነው’
አሉ።” (አሷድ 38፤ 4)
በጥላቻ እይታና ስሜት ይሸኟቸዋል፤ ይቀበሏቸዋል።

ُ‫س ِمعُوا ال ِذِّ ْك َر َويَقُولُونَ إِنَّه‬


َ ‫ار ِه ْم لَ َّما‬
ِ ‫ص‬َ ‫َوإِن يَ َكادُ الَّذِينَ َكفَ ُروا لَيُ ْز ِلقُون ََك بِأ َ ْب‬
ٌ ُ‫لَ َم ْجن‬
‫ون‬
“እነሆ እነዚያም የካዱት ሰዎች ቁርኣኑን በሰሙ ጊዜ በዓይኖቻቸው ሊጥሉህ (ሊያጠፉህ) ይቀርባሉ።
‘እርሱም በእርግጥ ዕብድ ነው’ ይላሉ።” (አል-ቀለም 68፤ 51)

ነቢዩ በደካማ ባልንጀሮቻቸው ተከበው በሚቀመጡ ጊዜ አቀማማጮቹ እነዚህ ናቸው እያሉ ያፌዙባቸው
እንደነበር ቁርአን ሲገልፅ

َّ ‫ض ِلِّيَقُولُوا أ َ َٰ َهؤ ََُل ِء َم َّن‬


‫َّللاُ َعلَ ْي ِهم ِ ِّمن بَ ْينِنَا‬ َ ‫َو َك َٰذَ ِل َك فَتَنَّا بَ ْع‬
ٍ ‫ض ُهم بِبَ ْع‬
“እንደዚሁም ‘ከመካከላችን አላህ የለገሰላቸው እነዚህ ናቸውን?’ ይሉ ዘንድ ከፊላቸውን በከፊሉ
ሞከርን።” (አል-አንዐም 6፤ 53)

አላህ እንዲህ በማለት ይመልሳል

َّ ‫َّللاُ ِبأ َ ْعلَ َم ِبال‬


َ‫شا ِك ِرين‬ َّ ‫ْس‬َ ‫أَلَي‬
“አላህ አመስጋኞቹን ዐዋቂ አይደለምን?” (አል-አንዐም 6፤ 53)

ሁኔታቸውን አላህ እንዲህ ሲል ተርኮልናል

‫﴾ َو ِإذَا َم ُّروا ِب ِه ْم‬٢٩﴿ َ‫ض َح ُكون‬ ْ ‫ِإ َّن الَّذِينَ أ َ ْج َر ُموا َكانُوا ِمنَ الَّذِينَ آ َمنُوا َي‬
‫﴾ َو ِإذَا َرأ َ ْو ُه ْم‬٣١﴿ َ‫﴾ َوإِذَا انقَلَبُوا ِإلَ َٰى أ َ ْه ِل ِه ُم انقَلَبُوا فَ ِك ِهين‬٣٠﴿ َ‫يَتَغَا َم ُزون‬
َ‫﴾ َو َما أ ُ ْر ِسلُوا َع َل ْي ِه ْم َحافِ ِظين‬٣٢﴿ َ‫ضالُّون‬ َ ‫قَالُوا ِإ َّن َٰ َهؤ ََُل ِء َل‬
“እነዚያ ያምመጹት በእነዚያ ባመኑት በእርግጥ ይስቁ ነበሩ። በእነርሱም ላይ ባለፉ ጊዜ ይጠቃቀሱ ነበር።
ወደ ቤተሰቦቻቸውም በተመለሱ ጊዜ (በመሳለቃቸው) ተደሳቾች ኾነው ይመለሱ ነበር። ባዩዋቸውም ጊዜ
‘እነዚህ በእርግጥ ተሳሳቾች ናቸው’ ይሉ ነበር። በነርሱ ላይ ተጠባባቂዎች ተደርገው ያልተላኩ ሲኾኑ።” (አል-
ሙጠፊፊን 83፤ 29-33)

2. አስተምህሯቸውን ጥላሸት መቀባት፣ ብዥታዎችን መፍጠር

በመልእክተኛውና በስብእናቸው ዙሪያ የሀሰት ወሬዎችን መንዛት፣ ጥርጣሬን ማንገስ ተራው ሰው ቆም ብሎ


ለማሰብና ለማስተንተን ፋታ በማያገኝበት አኳኋን የሀሰት ዘመቻውን በስፋትና በብዛት ማሰራጨት።
ቁርአንን አስመልክተው እንዲህ ብለዋል፡-

ِ َ ‫ي ت ُ ْملَ َٰى َعلَ ْي ِه بُ ْك َرة ً َوأ‬


ً ‫ص‬
‫يل‬ َ ‫ير ْاْل َ َّو ِلينَ ا ْكتَتَبَ َها فَ ِه‬
ُ ‫اط‬ َ َ ‫َوقَالُوا أ‬
ِ ‫س‬
“አሉም ‘የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናት። አስጻፋት። እርሷም በእርሱ ላይ ጧትና ማታ
ትነበብለታለች።’” (አል-ፉርቃን 25፤ 5)

‫َوقَا َل الَّذِينَ َكفَ ُروا إِ ْن َٰ َهذَا ِإ ََّل ِإ ْف ٌك ا ْفت َ َراهُ َوأ َ َعانَهُ َعلَ ْي ِه قَ ْو ٌم آخ َُرونَ فَقَ ْد‬
ً ‫ظ ْل ًما َو ُز‬
‫ورا‬ ُ ‫َجا ُءوا‬
“እነዚያም የካዱት ይህ (ቁርኣን ሙሐመድ) የቀጠፈው በእርሱም ላይ ሌሎች ሕዝቦች ያገዙት የኾነ ውሸት
እንጂ ሌላ አይደለም አሉ። በእርግጥም በደልንና እብለትን ሠሩ።” (አል- ፉርቃን 25፤ 4)

‫َولَقَ ْد نَ ْعلَ ُم أَنَّ ُه ْم َيقُولُونَ ِإنَّ َما يُ َع ِلِّ ُمهُ َبش ٌَر‬
“እነርሱም ‘እርሱን (ቁርኣንን) የሚያስተምረው ሰው ብቻ ነው’ ማለታቸውን በእርግጥ እናውቃለን።” (ነህል
16፤ 103) ይሉ ነበር።

መልእክተኛውን (ሠ.ዐ.ወ) አስመልክቶ

ِ ُ ‫ق لَ ْو ََل أ‬
‫نز َل ِإلَ ْي ِه‬ ِ ‫ام َو َي ْمشِي فِي ْاْل َ ْس َوا‬ َّ ‫سو ِل َيأ ْ ُك ُل‬
َ ‫الط َع‬ َّ ‫َوقَالُوا َما ِل َٰ َهذَا‬
ُ ‫الر‬
ً ‫َم َل ٌك َف َي ُكونَ َم َعهُ نَذ‬
‫ِيرا‬
“ለዚህም መልክተኛ ምግብን የሚበላ፣ በገበያዎችም የሚኼድ ሲኾን ምን (መልክተኛነት) አለው? ከርሱ ጋር
አስፈራሪ ይኾን ዘንድ ወደርሱ መልአክ (ገሃድ) አይወረድም ኖሯልን? አሉ።” (ፉርቃን 25፤ 7) ይሉ ነበር።
ለነዚህና መሰል እብለቶቻቸው የተሰጡ ምላሾችን ቁርአን ውስጥ በብዛት እናገኛለን።

3. ቁርአንን የጥንት አፈታሪክ ነው በማለት ማጣጣል

ይህን ስልት ሰዎች ቁርአንን እንዳይሰሙና ትኩረታቸው ወደ እሱ እንዳያደርጉ የሰዎን ህሊና ለመጥመድ
የተጠቀሙበት መንገድ ነበር። ነድር ቢን አል-ሐሪስ በአንድ ወቅት ለቁረይሾች እንዲህ አላቸው፡-

“እናንት የቁረይሽ ህዝቦች ሆይ፤ ወላሂ ዘዴው ያልተሰጣችሁ የሆነ ነገር ነው እናንተ ላይ የወረደው።
ሙሀመድ እኮ እናንተ ውስጥ የነበረ ያደገ የምትወዱት የነበረ ወጣት ነበር። ከሁላችሁም በላይ በንግግሩ
እውነተኛና በአደራ ታማኝ ነበር። ባመጣላችሁን ነገር ሲመጣላችሁ ግን ድግምተኛ አላችሁት በእርግጥ
የድግምተኞችን ንፍስታ እና ትብታብ አይተናል፤ ወላሂ! በፍጹም ድግምተኛ አይደለም። ጠንቋይ አላችሁት
በእርግጥ የጠንቋዮችን ማስፈራሪያ አይተናል ማጓራታቸውንም ሰምተናል፤ ወላሂ! በፍጹም ጠንቋይ
አይደለም። ገጣሚ አላችሁት በአላህ ይሁንብኝ ገጣሚም አይደለም፤ እብድ አላችሁት በእርግጥ እብዶችን
አይተናል ከመተናነቁም ሆነ ንግግሩም ከማምታታትና ነገር ከማደበላለቅ የጸዳ ነው እናንተ ቁረይሽ ጎሳዎች
ሆይ በሚገባ ወደራሳችሁ ተመልከቱ በእውነቱ ትልቅ ዱብዳ ነው የወረደባችሁ።”

ቀጥሎም ነድር ጉዞውን ወደ ሒይራህ (ኢራቅ) በማድረግ የፋርስን የጥንት ንጉሳን ወሬዎች፣ የሩስቱምንና
የአስፈንድሪያን ታሪክ ተምሯል። እናም ረሱል (ሠ.ዐ.ወ) ስለ አላህ ሊያስታውሱና ቅጣቱን ሊያስጠነቅቁ
ከሰዎች ጋር ቆይታ አድርገው ሲያጠናቅቁ ነድር ቢን አል ሀሪስ እርሳቸውን በመተካት እንዲህ ይላል፡- “በአላህ
እምላለሁ ሙሀመድ ከኔ ይበልጥ ያማረ ወግ የለውም።” ከዚያም ስለ ፋርስ ንጉሳን፣ ስለ ሩስቱምና
አስፈንደሪያስ ያወጋቸዋል። እንዲህም ሲል ይጠይቃቸዋል “ታዲያ ሙሀመድ በወግ ከኔ የሚበልጠው እንዴት
ሆን ነው?”

የኢብኑ አባስ ዘገባ እንደሚያመላክተው ነድር ዘማሪ እንስት ገዝቶ ነበር። አንድ ሰው ለመስለም እንደሚፈልግ
በሰማ ጊዜ ወደዚህች ዘፋኝ ይሄድና “አብይው፣ አጠጪው፣ ዝፈኝለት። ሙሀመድ ከሚጋብዝህ ነገር የተሻለ
ነውም በይው።” ይላታል። እርሱን በማስመልከት የቁርአን መልእክት ተላልፏል፡-

‫َّللاِ ِبغَي ِْر ِع ْل ٍم‬ َ ‫ض َّل َعن‬


َّ ‫س ِبي ِل‬ ِ ‫اس َمن َي ْشت َ ِري لَ ْه َو ْال َحدِي‬
ِ ُ‫ث ِلي‬ ِ َّ‫َو ِمنَ الن‬
ٌ َ‫َويَت َّ ِخذَهَا ُه ُز ًوا أُو َٰلَئِ َك لَ ُه ْم َعذ‬
ٌ ‫اب ُّم ِه‬
‫ين‬
“ከሰዎችም ያለ ዕውቀት ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስትና ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት አታላይ ወሬን የሚገዛ
አልለ። እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው።” (ሉቅማን 31፤ 6)
4. የድርድር ፖለቲካ

በሲራ ዑለማኦች ዘንድ እንደተዘገበው ዑትባ ኢብኑ ረቢዕ በህዝቦቹ ዘንድ የተከበረ ጥበብና ብልሀት ያለው
ሰው ነበር። በቁረይሾች ስብሰባ ላይ “እናንተ ቁረይሽች ሆይ፣ ሙሃመድ ጋር ሄጄ ባናግረውስ? አንዳንድ
ነገሮችንም በድርድር አቅርቤለት ከፊሉን ቢቀበለኝና ብቻ የፈለገውን ሰጥተነው ቢተወን?” አላቸው። እነሱም
እንዴታ አንተ የወሊድ አባት ሆይ ተነስ ሂድና አናግረው አሉት። ዑትባም ወደ ረሱል (ሠ.ዐ.ወ) ጋር መጥቶ
ቁጭ አለና፡-

“የወንድሜ ልጅ ሆይ እስከማውቀው ድረስ አንተ እኛ ውስጥ በዝምድናም ሆነ በጎሳ ትልቅ ቦታና ክብር ያለህ
ሰው ነህ በእርግጥ ወደ ህዝቦችህ ከባድ የሆነን ነገር ይዘህ መጥተሀል በእርሱም ሀብታቸውን በትነሀል፣
አስተሳሰባቸውን ቂላቂል አድርገሀል… አስኪ አንዳንድ ነገሮችን በድርድር አቀርብልሀለሁ ስማኝና አስበህበት
ምናልባት ከፊሉን ትቀበለኝ ይሆናል” አላቸው።

ረሡልም (ሠ.ዐ.ወ) ተናገር የወሊድ አባት ሆይ ተናገር እሰማሀለሁ አሉት። “የወንድሜ ልጅ ሆይ በዚህ
ይዘኸው በመጣኸው ጉዳይ ገንዘብ ከሆነ የፈለግከው ከኛ የበለጠ ሀብታም እስክትሆን ገንዘብ
እንሰበስብልሀለን፣ ክብር ከሆነ የምትፈልገው በማንኛውም ጉዳይ ከአንተ ላንወጣ ከኛ በላይ እንሾምሀለን፣
ንግስናም ከሆነ የምትፈልገው ከላያችን እናነግስሀለን፣ ይህ የሚመጣብህን ራዕይ ስትመለከተው መከላከል
የማትችለው ከሆነ ገንዘባችንን አውጥተን ሀኪም እንፈልግልህና ከእርሱ ነጻ እስክትሆን ድረስ ሁሉን
እናድርግልሀለን።” ረሡልም (ሠ.ዐ.ወ) “የወሊድ አባት ሆይ ጨረስክ” አሉት “አዎ” አላቸው እንግዲያውስ
ስማኝ አሉትና የሚከተሉትን የቁርአን አንቀጾች አነበቡለት፡-

َ ‫ت آ َياتُهُ قُ ْرآنًا‬
‫ع َر ِبيًّا‬ ْ َ‫صل‬
ِّ ِ ُ‫اب ف‬
ٌ َ ‫﴾ ِكت‬٢﴿ ‫الر ِح ِيم‬َّ ‫الر ْح َٰ َم ِن‬
َّ َ‫نزي ٌل ِ ِّمن‬
ِ َ ‫﴾ ت‬١﴿ ‫حم‬
﴾٤﴿ َ‫ض أ َ ْكث َ ُر ُه ْم فَ ُه ْم ََل يَ ْس َمعُون‬
َ ‫ِيرا فَأَع َْر‬
ً ‫ِيرا َونَذ‬ ً ‫﴾ بَش‬٣﴿ َ‫ِلِّقَ ْو ٍم يَ ْعلَ ُمون‬
‫عونَا ِإلَ ْي ِه َوفِي آذَانِنَا َو ْق ٌر َو ِمن َب ْينِنَا َو َب ْينِ َك‬ ُ ‫َوقَالُوا قُلُوبُنَا فِي أ َ ِكنَّ ٍة ِ ِّم َّما ت َ ْد‬
‫ي أَنَّ َما‬َّ ‫﴾ قُ ْل ِإنَّ َما أَنَا َبش ٌَر ِ ِّمثْلُ ُك ْم يُو َح َٰى ِإ َل‬٥﴿ َ‫املُون‬ ِ ‫اب َفا ْع َم ْل ِإنَّنَا َع‬ ٌ ‫ِح َج‬
َ‫احدٌ فَا ْست َ ِقي ُموا ِإلَ ْي ِه َوا ْست َ ْغ ِف ُروهُ َو َو ْي ٌل ِلِّ ْل ُم ْش ِر ِكين‬ ِ ‫ِإ َٰلَ ُه ُك ْم ِإ َٰلَهٌ َو‬
“ሐ.መ.(ሓ ሚም)። (ይህ ቁርኣን) እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ ከሆነው (አላህ) የተወረደ ነው።
አንቀጾቹ የተብራሩ የኾነ መጽሐፍ ነው። ዐረብኛ ቁርኣን ሲኾን ለሚያውቁ ሕዝቦች (የተብራራ) ነው።
አብሳሪና አስፈራሪ ሲኾን (ተወረደ)። አብዛኛዎቻቸውም ተዉት። እነርሱም አይሰሙም። አሉም ‘ልቦቻችን
ከእዚያ ወደእርሱ ከምትጠራን እምነት በመሸፈኛዎች ውስጥ ናቸው። በጆሮዎቻችንም ላይ ድንቁርና አልለ፤
በእኛና ባንተም መካከል ግርዶሽ አልለ። (በሃይማኖትህ) ሥስራም፤ እኛ ሠሪዎች ነንና።’ (እንዲህ) በላቸው
‘እኔ መሰላችሁ ሰው ብቻ ነኝ። አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ወደእርሱም ቀጥ በሉ ምሕረትንም
ለምኑት ማለት ወደእኔ ይወረድልኛል። ለአጋሪዎቹም ወዮላቸው።” (ፉሲለት 41፤ 1-6)

ከዚያም ረሱል (ሠ.ዐ.ወ) ሲያነቡ ዑትባም እያዳመጠ

َ ‫صا ِعقَةً ِ ِّمثْ َل‬


َ‫صا ِعقَ ِة َعا ٍد َوث َ ُمود‬ َ ‫ضوا فَقُ ْل أَنذَ ْرت ُ ُك ْم‬
ُ ‫فَإ ِ ْن أَع َْر‬
“(ከእምነት) እንቢ ‘ቢሉም እንደ ዓድና ሰሙድ መቅሰፍት ብጤ የኾነን መቅሰፍት አስጠነቅቃችኋለሁ’
በላቸው።” (ፉሲለት 41፤ 13) ሲደርሱ አፋቸውን ያዛቸውና ማንበብ እንዲያቆሙ ተማጸናቸው። ይህም
የሆነው ከአንቀጹ አስፈራሪነት የተነሳ ነው።

ከዛም ዑትባ ወደ ጓደኞቹ ተመልሶ በተቀመጠ ጊዜ “የወሊድ አባት ሆይ ከምን ደረስክ፣ ምን ነካህ” አሉት።
ዑትባም “የነካኝማ.. ሰምቼ የማላውቀውን ንግግር መስማቴ ነው፤ ወላሂ ግጥም አይደለም፤ ድግምትም
ጥንቆላም አይደለም፤ ወላሂ ጥፍጥና አለው ሰርጾም ይገባል፤ የሰው ልጅ ንግግርም አይደለም። የበላይ
ይሆናል እንጂ የበላይ አይኮንበትም። እናንት ቁረይሾች ሆይ እሽ በሉኝና ይህን ሰዉ ከነ ጉዳዩ ተውት፤
ልቀቁት። ወላሂ የሰማሁት ነገር ትልቅ ይሆናል አረቦች ጉዳት ካደረሱበት (ከገደሉት) ተገላገላችሁት። ከአረቦች
የበላይ ከሆነ ንግስናው ንግስናችሁ ነው ክብሩም ክብራችሁ ነው” አላቸው። “ወላሂ የወሊድ አባት ሆይ
በምላሱ ደግሞብሀል” አሉት ዑትባም “ይህ የኔ ሀሳብ ነው የፈለጋችሁትን አድርጉ” አላቸው።

ጦበርይ፣ ኢብኑ ከሲር እና ሌሎችም እንደዘገቡት ወሊድ ኢብኑል ሙጊራ፣ አስ ኢብኑ ዋኢል እና ጥቂት
ሙሽሪኮች ለረሱል የሚከተለውን የድርድር ሀሳብ አቀረቡ። ከነርሱ በላይ ሀብታም እስኪሆኑ ድረስ ብር
ሊሰጧቸው እና ቆንጆ ድንግል ሴት ሊያጋቧቸው በምላሹ አማልክቶቻቸውን መስደብና ባህሎቻቸውን ማቄል
እንዲተው ጠየቁ። ረሡል (ሠ.ዐ.ወ) የተላኩበትን ወደ ሀቅ ደዕዋ ማድረግ እንጂ አሻፈረኝ አሉ በዚህን ጊዜ
“እኛ አምላክህን አንድ ቀን እንገዛውና ሌላ ቀን የኛን አማልክት ተገዛ አሏቸው” ይህንንም አሻፈረኝ አሉ።
አላህም የሚከተለውን ቃል አወረደ፡-

ُ‫﴾ َو ََل أَنت ُ ْم َعا ِبدُونَ َما أ َ ْعبُد‬٢﴿ َ‫﴾ ََل أ َ ْعبُدُ َما ت َ ْعبُدُون‬١﴿ َ‫قُ ْل يَا أَيُّ َها ْال َكافِ ُرون‬
‫﴾ لَ ُك ْم دِينُ ُك ْم‬٥﴿ ُ‫﴾ َو ََل أَنت ُ ْم َعا ِبدُونَ َما أ َ ْعبُد‬٤﴿ ‫﴾ َو ََل أَنَا َعا ِبدٌ َّما َع َبدت ُّ ْم‬٣﴿
‫ِين‬
ِ ‫يد‬َ ‫َو ِل‬
“በላቸው ‘እናንተ ከሓዲዎች ሆይ! ‘ያንን የምትግገዙትን (ጣዖት አሁን) አልግገዛም። እናንተም እኔ
የምግገዛውን (አምላክም አሁን) ተገዢዎች አይደላችሁም። እኔም ያንን የተገዛችሁትን (ወደፊት) ተገዢ
አይደለሁም። እናንተም እኔ የምግገዛውን (ወደፊት) ተገዢዎች አይደላችሁም። ለእናንተ ሃይማኖታችሁ
አልላችሁ። ለእኔም ሃይማኖቴ አለኝ።’” (አል-ካፊሩን)

ከቁረይሾች ውስጥ የተከበሩት ሹማምንቶች ካወጡና ካወረዱ በኃላ ኡትባ ኢብኑን ወሊድ ያደረገውን ሙከራ
ደግመው ለመሞከር ተስማምተው ረሡል (ሠ.ዐ.ወ) ጋር ተሰባስበው በመሄድ ሹመት እና ገንዘብን
በድርድር አቀረቡላቸው እንዲሁም የሚመጣባቸው ነገር የጅን ራዕይ ከሆነ ሀኪም ሊያመጡ ቃል ገቡላቸው።
ረሡልም (ሠ.ዐ.ወ)፡- “እምትሉት ሁሉ እኔ ጋር የለም ወደናንተ የመጣሁበት ነገር ይዠ ስመጣ ገንዘብ፣
ክብርና ንግስና ፈልጌ አይደለም። ግና አላህ ወደናንተ መልክተኛ አድርጎ ላከኝ። መጽሀፉንም በኔ ላይ አወረደ።
አብሳሪና አስጠንቃቂ እንድሆን ስላዘዘኝ የጌታየን መልክት አደረስኩላችሁ መከርኳችሁም። ያመጣሁትን
ከተቀበላችሁኝ በዚህም በመጪው አለምም ድርሻችሁ ነው። እምቢ ካላችሁም አላህ በመካከላችን
እስኪፈርድ በእርሱ ትዕዛዝ ስር እታገሳለሁ።”

እነሱም “ካቀረብንልህ ነገሮች ምንም የማትቀበለን ከሆነ ይሀን ብቻ አድርግልን ከህዝቦች ሁሉ ከኛ በላይ
ጠባብ በሆነ ሀገር፣ ባነሰ ግብዓት እና በተጣበበ ኑሮ የሚኖር ማንም እንደሌለ ታውቃለህ፤ በላከህ
(መልእክት) የላከህን ጌታ ጠይቅልን፤ ይሄን ያጣበበንን ተራራ ያንቀሳቅስልን ልክ እንደ ሻም እና ኢራቅ
ወንዞች ወንዝ ያፍልቅልን ወይም ደግሞ ያለፉት አባቶቻችንን ከሞት ይቀስቅስልን። ታዲያ ከሚቀሰቀሱት
ውስጥ አንዱ ቁሰይ ኢብኑ ኪላብ ይሁን እና እውነተኛ ሽማግሌ ስለነበር የምትለው ነገር እውነት ይሁን
ውሸት እንጠይቀዋለን። ለአንተም የአትክልት ስፍራ፤ ያሸበረቀና ያማረ ቤት፣ ከምናይህ ሁኔታህ
የሚያብቃቃህ በወርቅና በብር የተሞላ ካዝና ይስጥህና ሀብታም ያድርግህ። የጠየቅንህን ካስደረግክ
እናምንልሀለን አላህ ዘንድም ያለህን ቦታ እንረዳለን እንደምትለውም መልክተኛ አድርጎ ልኮሀልም ማለት
ነው።” አሉ።

ረሡልም (ሠ.ዐ.ወ) “ይህን አላደርገውም ጌታውንም በንዲህ አይነት ጥያቄ የሚጠይቅ ሰውም አይደለሁም
አሏቸው።” ከብዙ ንግግር እና ክርክር በኃላ ቁረይሾችም “ይህን የሚያስተምርህ የማማ አካባቢ የሚገኝ
ረህማን የሚባል ሰው እንደሆነ ደርሰንበታል። ወላሂ በረህማን በፍጹም አናምንም። ሙሀመድ (ሆይ)
አማራጮችን ሁሉ ሰጥተንሀል ወላሂ ሳናጠፋህ ወይም ሳታጠፋን አንላቀቅም” ብለው ተነስተው ሄዱ።

5. ማሰቃየት

ቁረይረሾች ከዚህ በፊት የኢስላምን ደዕዋ ለማቆም የተጠቀሟቸው ስልቶች ምንም ጥቅም እንዳላስገኙላቸው
በመረዳት ነብያችንን (ሠ.ዐ.ወ) እና ሰሀቦችን ማሰቃየትና መቅጣት ጀመሩ። ቡኻሪ ከአብደላህ ኢብኑ
መስዑድ እንደዘገቡት ነብያችን (ሠ.ዐ.ወ) ካዕባ ጋር እየሰገዱ ሳለ አቡ ጃህልና ጓደኞቹ ተቀምጠው ባሉበት
“ሙሀመድ ሱጁድ ሲወርደ የእርድ ሆድ እቃ (አንጀት) አምጥቶ ጀርባው ላይ የሚጥል ማን ነው” ብለው
ተጠያየቁ። ከውስጣቸው እጅጉን የጠመመው ሰው (ኡቅባ ኢብኑ ሙዒጥ ይባላል) አምጥቶ ነብያችን
(ሠ.ዐ.ወ) ሱጁድ እስከሚያደርጉ ጠብቆ በትከሻቸው መሀል ከጀርባቸው ላይ አስቀመጠው። ይህ ሁሉ ሲሆን
ከመመልከት ውጭ ምንም ማድረግ አልችልም ነበር። ምን አለ አቅም ቢኖረኝ!! በኩራት በመምቦጣረር
አንዳቸው አንዱ ላይ እየተዘናበለ ሲሳሳቁ ፋጢማ (ረ.ዐ) መጥታ ከጀርባቸው ላይ እስክታነሳላቸው ድረስ
በሱጁድ ላይ ቆይተው ነበር። ከዛም እራሳቸውን ቀና አደረጉና ሶስት ግዜ ‘ያ አላህ ቁረይሾችን አንድ በላቸው’
ብለው ዱዕ ሲያደርጉ በዚያ ሀገር የተደረገ ዱዕ ተቀባይነት እንደሚኖረው ስለሚያውቁ በጣም ደነገጡ።

ከዚህም አልፈው ረሡል (ሠ.ዐ.ወ) በመካከላቸው፣ ባጠገባቸው አልያም በመንገድ ሲያልፉ እንዲሁም
በስብሰባዎቻቸው ላይ ያፌዙ ይቀልዱ እና ያላግጡባቸው ነበር።

ጦበሪ እና ኢብኑ ኢስሀቅ እንደዘገቡት ከቁረይሾች አንዱ ረሡል (ሠ.ዐ.ወ) ከመካ መንገዶች በአንዱ ላይ
ሲያልፉ አፈር ዘግኖ ጭንቅላታቸው ላይ በተነባቸው። በዚሁ ሁኔታ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ከልጆቻቸው
አንዷ እያለቀሰች አፈሩን ስታጥብላቸው “ልጄ አታሰልቅሽ አላህ አባትሽን ይከላከልለታል” ይሏት ነበር።
በአብዛሀኛው ህዝብም ሆነ በግለሰቦች ዘንድ ካላቸው ትልቅ ተምሳሌትነት እና ክብር እንዲሁም በአቡ
ጧሊብ ከሚደረግላቸው ከለላ አልፎ ወራዳ የሆኑ በደሎች ይደርሱባቸው ነበር።

ሰሀቦቻቸውማ (ረ.ዐ) ታጋሽ እንኳን ሊያወሳው የሚዘገንን የሆኑ የስቃይ አይነቶች ተፈራርቀውባቸዋል።
ከቅጣቱ ብዛት የሞተው ሞቶ የታወረው ታውሯል… ይህ ሁሉ ግን ከአላህ ዲን (ኢስላም) ቅንጣትን ታክል
ንቅንቅ አላደረጋቸውም። በያንዳንዳቸው ዙሪያ የተዘገበውን ብናነሳ ስለሚረዝም ከገጠማቸው ቅጣቶች
የተወሰኑ ምሳሌዎችን እንጥቅስ።

1. ኡሰማን ኢብኑ አፋንን (ረ.ዐ) አጎታቸው ከዘምባባ ቅጠል በተሰራ ሰሌን ያፍኑትና ከስር ጭስ
በማጨስ ይቀጡት ነበር።
2. ሙስዐብ ኢብኑ ኡመይር (ረ.ዐ) እናቱ መስለሙን ባወቀች ግዜ ከሰዎች ሁሉ የተሻለ ፀጋ
የሞላበት ኑሮ ከሚኖርበት ቤቱ አስወጥታው ቆዳው ልክ እንደ እባብ ቆዳ እየተቀረፈፈ
እስኪላላጥ ድረስ ለረሀብ ዳረገችው።
3. ቢላል (ረ.ዐ) የኡመያ ኢብኑ ኸለፍ አልጁመህይ ባሪያ ነበር። ኡመያ የፀሀይቷ ንዳድ ከፍ ሲል
በጋለው የመካ አሸዋ ላይ ቢላልን አስተኝቶ ትልቅ ቋጥኝ ደረቱ ላይ በማስቀመጥ “ወላሂ
በሙሃመድ ክደህ ኢዛና ላትን እስካላመለክ ድረስ ትሞታለህ እንጂ አለቅህም” ይለው ነበር።
ከዚህ ሁሉ ስቃይ ጋር የቢላል መልስ ግን “አሃዱን አሃድ” ነበር።
4. አማር ኢብኑ ያሲር (ረ.ዐ) የበኒ መህዙም አገልጋይ (ባሪያ) ነበር። ከነወላጆቹ ሰለመ።
ጣኦታዊያን -በዋናኝነት አቡጃህል ፀሀይ ስትበረታ ወደ ሜዳ ያወጧቸውና በግለቱ ይቀጣቸው
ነበር። በመቀጣት ላይ ሳሉ ነብያችን (ሠ.ዐ.ወ) ባጠገባቸው አለፉ። “የያሲር ቤተሰብ ሆይ
ታገሱ። ጀነት ቃል ተገብቶላችኋል” አሏቸው። ያሲር ከቅጣቱ ብዛት ሲሞት ሱመያን (የአማርን
እናት) አቡ ጃህል ብልቷ ላይ በስለት ወግቶ ገደላት። በዚህም በኢስላም ታሪክ የመጀመሪያዋ
እንስት ሸሂድ (መስዋእት) ለመሆን ታደለች። አማር ላይ ስቃዩን አበረቱበት። አንድ ግዜ በጸሐይ
ግለት፣ ሌላ ግዜ ደረቱ ላይ ቋጥኝ በማስቀመጥ፣ ቀጥሎም ውሃ ውስጥ በመድፈቅ ቅጣቶችን
እያፈራረቁ አሰቃዩት። “ሙሀመድን ሳትሰድብ ወይም ስለ ላትና ኡዛ በጎ ነገር ካልተናገርክ
አንተውህም” አሉት። ያሉትንም ለመፈፀም ተስማማ። ተገዶም ፍቃዳቸውን ፈፀመ። ከነቢዩ
(ሰ.ዐ.ወ) ዘንድም እያለቀሰ በመምጣት ይቅርታ ጠየቃቸው። አላህም ተከታዩን ቁርአናዊ
መልእክት አስተላለፈ “ከእምነቱ በኋላ በአላህ የካደ ሰው (ብርቱ ቅጣት አልለው)። ልቡ በእምነት
የረጋ ኾኖ (በክህደት ቃል በመናገር) የተገደደ ሰው ብቻ ሲቀር። ግን ልባቸውን በክሕደት የከፈቱ
ሰዎች በነሱ ላይ ከአላህ ቁጣ አለባቸው። ለእነሱም ታላቅ ቅጣት አልላቸው።” (ነህል 16፤ 106)

5. ስሙ አፍለህ (ረ.ዐ) የሚባል የበኒ ዐብደዳር ባሪያን፤ እግሩን በገመድ አጥብቀው አስረው መሬት
ለመሬት ይጎትቱት ነበር።
6. ኸባብ ኢብኑል ዐረት (ረ.ዐ) ጣኦታዊያን የበረታ ስቃይ ያደርሱበት ነበር። ብዙ ጊዜ በጠራራይቷ
ነዲድ ጸሃይ በጋለ አለት ራቁቱን አስተኙት። መንቀሳቀስ እንዳይችልመ ትልቅ አለትን ደረቱ ላይ
አስቀመጡበት። አለቱ ጀርባውን ሰርስሮ በመግባቱ ቀዝቅዞ ከላዩ ላይ ሲወድቅለት ሰውነቱ ላይ
ትልቅ ሽንቁርን ትቶ ነበር።

ለአላህ ሲሉ መከራን የተሸከሙ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረቦች (ሰሀቦች) ስም ዝርዝር ብዙ ነው። ጣኦታዊያን
አንድ ሰው መስለሙን በሰሙ ቁጥር እጅግ የሚያሳቅቅ ቅጣት ይቀጡት ነበር። እዚህ ጋር ኢማሙ አል-
ቡኻሪ የዘገቡትን አንድ ታሪክን እናውሳ። ኸባብ ኢብኑል ዐረት ሲናገር “አንድ ቀን ነብዩ (ሠ.ዐ.ወ) በካዕባ
ጥላ ስር ፎጣቸውን ተንተርሰው ሳሉ ወደርሳቸው መጣሁ። በወቅቱ ከጣኦታዊያን ይደርስብን የነበረው
መከራ ከባድ ስለነበር ነቢዩንም ‘አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አላህን አይለምኑልንምን?’ ስላቸው ፊታቸው
በንዴት ቀላ። ከተጋደሙበት ቀና ብለው ተቀምጠው:-

‫ وليتمنّ هللا هذا األمر حتى يسير‬،‫لقد كان من قبلكم ليمشط بمشاط الحديد ما دون عظامه من لحم أو عصب ما يصرفه ذلك عن دينه‬
‫الراكب من صنعاء إلى حضرموت َل يخاف إَل هللا والذئب على غنمه ولكنكم تستعجلون‬

‘ከናንተ በፊት የነበሩ ህዝቦች በብረት ሙሽጥ (መላጊያ) አጥንታቸው እስኪቀር ስጋቸው ሲቧጠጥ ከዲናቸው
ንቅንቅ አይሉም ነበር። አላህም ይህንን ጉዳይ (ኢስላምን) ሙሉዕ ያደርገዋል (እተፈለገበት ያደርሰዋል)።
አንድ ተጓዥ ከሰንዕ ተነስቶ ሀድረሞት እስኪደርስ አላህን ከዚያም ፍየሎቹን ተኩላ እንዳይበላበት እንጂ
ማንንም ሳይፈራ ይጓዛል። እናንተ ግን ትቸኩላላችሁ’ አሉኝ” ብሏል።

You might also like