You are on page 1of 2

ምን መደረግ አለበት?

ከተስፋዬ መኮንን

ይህ ጥያቄ ዘመናዊ ተብሎ ሲጠራ በመጣ የፖለቲካ ዓለም ሲመላለስ የመጣ ነው።ጥያቄው የሚነሳው በፖለቲካ ሂደቱና በመሪ ድርጂት
ነኝ ባዩ መሀል አለመገናኘት ሲያጋጥም ነው።ተጨባጩ ሁኔታ ከመሪነኝ ባዩ ይቀድምና መሪውን የቁም ተመልካች ሲያደርገው “አረ ምን
ይበጃል” የሚያስብል ጊዜ ሲመጣ።ለዚህ መሰረታዊ የመሪ ያለህ ለሚያስብል ጥያቄም መልስ የሌለው መሪ ነኝ ባይም የባለህበት እርገጥ
ሕይወት ወስጥ ገብቶ ሲዳክር ታሪክ ደጋግሞ አስያቷል።

ለዚህ ታሪክ አነሳስ ርቆ ለታሪክ ማመሳከር የበዙ ሀገሮችን ተሞክሮ ታሪክ በማገላበጥ ጊዜ ከማጥፋት ይልቅ የራሳችንን ታሪክ መለስ
ብሎ መቃኘት ይበቃል።ይህ የባለህበት እርገጥ ታሪክ ደምቆ የታየው በኛው ታሪክ በመሆኑ የመማር ችሎታው ባለቤቶች ብንሆን እሱን
መለስ ብሎ መቃኘት ብቻ ይበቃል ። ያለፈው የ40 ዓመታት ታሪክ በሱ የተመላ ነውና።

ከጧት በትግሉ ውስጥ የነበሩት እንደሚያስታውሱት የጸረ-ፊውዳል ትግሉ ሲጀመር ከተነሱት አንኳር አንኳር ጥያቄውች ወስጥ አንዱና
ወሳኙ “ትግሉ ከየት ይጀመር”? የሚለው ነበር።ይህንን ወሳኝ ጥያቄ ለማስተናገድ ሁለት ፍጹም የማይገናኙ አቋሞች ብቅ አሉ።በዚያን
የፖለቲካ ጨቅላነት ዘመን ያልታየን ግና እስከዛሬ ድረስ ለሚያንገላታን ድክመታችን መቋጠሪያው የተበጀለት በዚያን ወቅት
በውሰድነው የተሳሳተ ምርጫ ሆነ።የቀረቡትም ምርጫዎች እነዚ ነበሩ።

በሀገር ውስጥ ይጀመር

1) እንደዛሬ ሁሉ ትግሉን ለማካሄድ የተመረጠው የትግል ስልት የሚያከራክር አልነበረም።በፈላጭ ቆራጭ ስራት ላይ ከማመጽ ያለፈ
ሌላ አማራጭ አልነበረም።ቁልጭ ፤ጥርት ብሎ የተቀመጠ አቋም አልነበረም። መንፈሱ ግን ይህንን ይመስል ነበር።ጥያቄው ታድያ
የፈላጭ ቆራጩን ስራት ለመጣል ትግሉን ከውስጥ ሁኖ፤የሕዝቡን ኑሮ እየኖሩ፡መከራና ስቃዩንም እየተካፈሉ፤መስዋእትነትንም
እየከፈሉና ቀጣይ አመራሩን ሕዝቡ በሂደት እንዲተካ ከማድረግ ሌላ አማራጭ የለም።የእለት ትግሉንም የህዝቡ እንዲሆን ለማድረግ
ክህዝቡ ጎን በመቆም ከማራመድ ሌላ ምርጫ የለም የሚለውን የደገፈው ወገን አንዱ ነበር።ከሕዝቡ ሳንነጠል ትግሉን ማራመድ
ለእውነተኛ ብሄራዊ ነጻነታችን ዋስትና ነው።ከውጪ ጥገኝነት የመዳኛው ይህ የግል ስልት ብቻ ነው የሚለው ነበር።

በውጪ ሀገር ይጀመር

2) ትግሉን በሀገር ውስጥ ለመጀመር ተጨባጩ ሁኔታ አይፈቅድም።የፈላጭ ቆራጩ የአመጽ በትር የጠነከረ ነው።ትግሉ እንደተጀመረ
በእንጭጩ ይመታል።ሕዝቡንም ማስመታትና ተስፋ እንዲቆርጥ ማድረግ ይሆናል። በተለይም በተሳሳተና በተጋነነ ሁኔታ የውጪውን
የተማሪ እንቅስቃሴን ሚና አግንኖ በማቅረብ ውጪ ወጥቶ ተደራጅቶና ታጥቆ ወደ ሀገር በመግባት የነጻነት ትግሉን መምራት
እንደሚቻል ተነበየ።ባጭሩ በሁለቱ አቋሞች መሀል የነበረ ልዩነት ትግሉን ሕዝባዊ እናድርገው ወይስ ፋኖዊ የሚለው እንደነበር በኋላ
በትግሉ ወስጥ ግልጽ እየሆነ መጣ። ሁለተኛው የኛው ምርጫ ፋኖዊ የሆነ የተግል ስልትን ከሕዝባዊ የትግል ስልት አልቆ የሚመለክት
የምሁር አቋሙን በሚገባ አስቀመጠ።ባያሌው ያን የመሰለ መከዳዳትነ መተላለቅ የወለደው ያየተሳሳተ ጎዳና ነበር።

ከዚህ የተሳሳተ ምርጫ ላይ ተመስርተን ውጪ በመውጣት ለፈጠርናቸው ድርጂቶቻችን እርዳታን ለማግኘት የብዙዎችን በር
አንኳኳን።የፈጥርናቸውን ድርጂቶች አላምዎችን ለሸአብያ፤ለሶማሊያ፤ለሱዳን፤ለፓሊስታይንና ለኩባ ዓለም አቀፍ ጥቅም ተደራቢ
በማድረግ የተነሳንለትን ብሄራዊ ጥቅም አሳልፈን ሸጥን።ይህ የኛው ያለፈ ታሪክ ነው።

የዛሬውስ የቀጠለው ትውልድ የኛን የጥፋት ታሪክ መርምሮ የሚበጀውን የአደረጃጀት ስልቱን ዘርግቷልን? ብሎ መጠየቅ ዋና ነገር
ነው።ታሪካችንን አሳዛኝ የሚያደርገው የቀጠለውም የዛሬው ትውልድ በዚያው የተሳሳተ ጎዳና ወስጥ ቁሞ ባለህበት እርገት ሲመታ
መታየቱ ነው።ይህንን የቀጠለውን የአደረጃጀት ጉድለት ለማየት ያለውን ሁኔታ ዘርዘር አርጎ ማየት ይጠቅማል።

ዛሬ የተገንጣይ የታሪክ ልቅላቂዎችን ትተን በሀገር ጉዳይ ከሞላ ጎደል በአንድ ሀገራዊ ጎራ የተማከሉትን በሁለት መክፈል ይቻላል።
አንደኛው በሀገር ወስጥ ወያኔ የቀደደላቸውን “የፓርላማ ፖለቲካን”ሸሚዝ አጥልቀው ላለፊት 19የወያኔ አገዛዝ ዘመን ወስጥ ላይ ታች
ሲሉ ቆይተው ከመድረኩ በአንድ ላይ የተጠረጉትን ይመለከታል። ሁለተኛው የኛ የተሳሳተ ከሕዝብ ተነጥሎ በውጭ የመደራጀቱ አባዜ
የተጠናወተው “ግንባር ፤ንቅናቄ ድርጂት፤ነጻ-ዓውጪ፤”ወዘተ.. በሚል የተመሰረቱን ይመለከታል።ይህ ወገን ባጠቃላይ የወያኔን የጸረ-
ኢትዮጵያን ዓላማ የተረዳ ነው።ይህንን የአመጽ ሀይል ያለአመጽ የሚሽረው ሌላ አማራጭ እንደሌለ በሚገባ የተቀበለ ነው። ግን ይህ
ብቻውን በቂ አይደለም።ይህንን የዘረኛ ሀይል እንዳልነበር አድርጎ ለማጥፋት ከጠባብ የፋኖ ድርጂት የላቀ የፖለቲካ ራእይ ባለቤት
መሆንን ይጠይቃል።የላቀ የሰፋ የፖለቲካና የጦር ድርጂት ባለቤት መሆንን የጠይቃል።እነዚህ ሁለት የማይነጣጠሉ የሀይል መሳሪያዎች
ደግሞ የሚገኙት ከማንም የውጪ ሀይል ቁጥጥር ዊጭ ሁነው ለመገንባት ሲችሉ ነው።ይህ ደግሞ እንደገና የሚወለደው ለትግሉ
ከመረጥነው የትግል ስልት ዘንድ ይሆናል።

ንቅናቄው ወይንም ግንባሩ የመረጠው የትግል አካሄድ የኛን የፋኖ የትግል ስልትን ከሆነ ድርጂቱ ሕዝብ የሚያውቀው፤ቁሞ
የሚዋደቅለት ስላይደል በተፈጠርበት የውጪው አለም “መጣሁ” እያለ እንደፎከረና እንዳቅራራ ሳይደርስ የጸረ- ኢትዮጵያ ሀይሎች
“የወያኔ ማስፈራሪያ”እንደሆነ ይቀራል።እነዚህ ሀይሎች በርዳታ ስም ባጠለቁለት ሉጋም እንደተሸበበ፤እንደጫጨ፤እድሜውን
ይቆጥራል። ከዚህ ከመረጠው የትግል ስልት ካልተላቀቀና መሰረታዊ የሆነውን ሕዝባዊ የትግል ስልትን ካልተቀበለ ከዚህ ህይወቱ
የሚያላቅቀው ተአምር አይኖርም።

ለነዚህ በመሰረቱ የሕዝብ ወገኖች ለሆኑ ግና መሄጃ መነግዱ ለጠፋባቸው ቀናው መንገድ ከዚህ የሚከተለው ነው እላለሁ። በተለያየ
ስም ዙሪያ የተሰባሰቡ ወገኖች አንድ ሊይዙት የሚገባ ነገር ቢኖር በተበጣጠሰና በጫጨ ድርጂት ሀገር ነጻ ሊሆን እንደማይችል መረዳት
ነው።ስለሆነም አንኳር አንኳር በሆኑ የሀገር ጥያቄ ላይ በመስማማት አስቸኳይ አንድነትን መፍጠር ዛሬ እንጂ ነገ የሚባል
አይደለም።ሌላው ይህ አንድነት ቢሰምር ሁለተኛው እርምጃ ባስቸኳይ አመራሩ ከሕዝቡ ጋር በአካል የሚቀላቀልበትን እርምጃ
መውሰድ የትግል ስልቱ ለውጥ ጉልላት ነው።በውስጥና በውጭ ያለውን ትግል የሚያቀናጅ አንድ የአመራር አካል ብቻ ከውጭ
በመተው ለትግሉ መስዋእት ለመሆን የቆረጠው ገብት እንዲታገል ከውስት ትግሉን ማፋፋም ወስኝ ነው።

ይህ ይትግል ለውጥ ታይቶ የማይታወቅ ጭካኔ የተመላውን መስዋእትነት እንደሚጠይቅ ግን ቀድሞ መረዳት ወሳኝ ነው።የምንታገለው
ለበቀል የመጣን የባንዳን ዘረኛ ሀይል ነው።ወያኔ የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ አይቶት የማያውቅው ጨካኝና አረመኔ ጠላቱ ነው።ከዚህ
ጠላት ጋር መግጠም ማለት በጦርነት ታሪክ ታይተው የማይታወቁ የጭካኔ በትሮች የሚሰነዘሩበት መሆኑን ለታጋዩ ግልጽ መሆን
አለበት።ትግሉ ሁሉ አቀፍ ይሆናል።ምህረት የለሽ።ለዚህ መሰሉ ትግል ልበሙሉና ቆራጥነት የተዋሀደው፤በእራሱ ሕዝብ ሀያልነት ላይ
የማያወላውል የጸና እምነት ያለው አመራር መኖር ወሳኝ ነው።ትግሉ ሲጎመዝዝና ብርህን ጨለማ ሲለብስ እንዳንድ ሰው ሆኖ ተባብሮ
የሚቆም አመራር የሚፈለግ ነው።ይህ መሰል አመራር ብቻ ነው የሕዝብን አለኝታ የሚጨብጥ።

ዛሬ በሀገራችን ወስጥ ያለው የባንዳ ይዞታ ነው።ይህንን ሀቅ ለመሸፈን ከወያኔ ዙሪያ ቁመው ብዙ የደከሙ ነበሩ።እስከ ቅርብ ጊዜ
ድረስም ከመሀከላችን የታገሉ መስለው ለማወናበድ የሞከሩ ባንዳን የልወጥ አጋር አድርገው ለማቅረብ ሞክረውም ነበር።ሕዝቡም
ለተወሰነ ጊዜ ለምን አናያቸውም ብሎ ቢሞክራቸው ወያኔ ከሰጣቸው የመድረክ ጫወታ ውጪ ለሚመጣ የቁርጥ ቀን እንደማይወሉ
ከ97ቱ ምርጫ በኋላ ወያኔ በሕዝባችን ላይ ለሰነዘረው ስይፍ ባሳዩት መፍረክረክ ሕዝቡና እነሱ ዳግም ላይገናኙ ተለያይተዋል።እንግዲህ
አሁን የቀሩት “ግንባሮችና ንቅናቄዎችም”እንደወንድሞቻቸው የታሪክን ፍርድ ሳይቀምሱ ሚናቸውን የመለያው ቀን አሁን ነው። ወይ
ግቡና ከሕባችሁ ተቀላቀሉና የትግሉን ቋያ አቀጣጠሉ ወደግሞ መንገዱን ለአዲሱ ትውልድ ልቀቁለትና የራሱን የታሪክ ድርሻ
ይወጣበት።

www.ethiomedia.com – A site of alternative news and views


July 31, 2010

You might also like