You are on page 1of 12

የተከላካይ ጠበቆች ስነምግባርና ከተከሳሾች ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት

Solomon Engda Alemu


LL.B, LL.M, Judge Trainer and program
coordinator at Federal Justice Professionals
Training Center, e mail
Solomonengda@mail.com,s.e.alemu@warwick.
ac.uk,

1. መሠረታዊ ነጥቦች

1.1 የተከላካይ ጠበቃዎች በአገራችን የወንጀል የፍትህ ሥርዓት በግል ጠበቃ ቀጥረው
ለማቆም አቅም የሌላቸውን ወገኖች በመደገፍ ሚዛናዊና ትክክለኛ ፍትህ እንዲሠጥ
ለማድረግ በሚደረገው እንቅሥቃሴ የሚያበረክቱት አሥተዋጽኦ ቀላል የሚባል
አይደለም፡፡
1.2 የኢፌድሪ ህገ መንግስትም በወንጀል የተከሠሱ ሠዎች በመረጡት ጠበቃ የመወከል
መብት እንዳላቸው እና ጠበቃ ባይቆምላቸው ፍትህ የሚጓደል መሆኑን ፍርድ ቤት
ካመነበት በመንግሥት ወጪ ጠበቃ እንደሚመደብላቸው ይገልጻል፡፡
1.3 ህገ መንግስታችን አንድ ዜጋ ጠበቃ የማቆም አቅም ሥለሌለው የፍትህ መጓደል
እንዳይደርሥበት በመንግስት ወጪ ጠበቃ በመመደብ ለዜጋው ጥበቃ የሚያደርግ
ቢሆንም የተከላካይ ጠበቃነት የሥራ ድርሻ እሥከአሁንም ድረስ ትኩረት ተሠጥቶት
እንቅሥቃሴ ሲደረግበት የሚታይ የሥራ ክፍል አይደለም፡፡
1.4 በፅ/ቤት
በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚሰሩ ተከላካይ ጠበቆች አንድ ቢሉም በፅ/
ደረጃ ተቋቁመው ያሉ አሊያም ባለሙያዎቹ በአብዛኛው የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው
ነገር ግን በውክልና የተከላካይ ጥብቅናውን ሥራ የሚሠሩ ናቸው፡፡
1.5 የተከላካይ ጥብቅና የሥራ ድርሻ ትኩረት የተሠጠው አይደለም ሥንል የሥራ
ክፍሎቹ በማቴሪያልም ሆነ በሠው ኃይል ከሚሠጡት አገልግሎት አንፃር የተደራጁ
አይደሉም፡፡ የባለሙያዎቹን አቅም ባጭር፣ በመካከለኛና በረዥም ጊዜ ለማሣደግ
የሚደረገው ጥረት ብዙም ክብደት የተሠጠው አይደለም ለማለት ነው፡፡

Solomon Engda Alemu


የተከላካይ ጠበቆች ስነምግባርና ከተከሳሾች ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት

1.6 የወንጀል የፍትህ ሥርዓታችን ቀልጣፋና ውጤታማ ሊሆን የሚችለው የዳኞችን


ወይንም የዓቃብያነ ህግን አቅም በማጐልበት ወይም የእነዚህን የሥራ ክፍሎች
በቁሳቁስና በሠው ኃይል እንዲሁም በአዲስ አሠራሮች በማደራጀት ብቻ ሊሆን
አይችልም፡፡ በወንጀል የፍትህ ሥርዓቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አሥተዋጽኦ
የሚያደርጉ የሥራ ክፍሎች እና ባለሙያዎች ሁሉ እንደሌሎቹ የሥራ ክፍሎች ትኩረት
ተሠጥቷቸው አሠራራቸውን ዘመናዊ ቀልጣፋና ውጤታማ ማድረግ መቻል አለባቸው፡፡

1. የጠበቆች ብቁ ሆኖ መገኘት
2.1 የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቆች ፈቃድ አሠጣጥና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር
199/1992 በመግቢያው (Preamble) ላይ የጥብቅና አገልግሎት ማለት “በህግ
ሙያ የሠለጠነና ሠፊ ልምድ ያለው፣ የፍርድ ቤት አሠራርን ጠንቅቆ የሚያውቅ፣
የታማኝነት፣ የቅንነትና የእውነተኝነት መንፈሥን የተላበሠ ሠው ለህግ የበላይነትና
ለፍትህ መሥፈን ከፍትህ አካላት ጐን በአጋዥነት የሚሠለፍበት ሙያ ነው” በሚል
ትርጉም ሰጥቶታል
2.2 በአዋጁ መግቢያ ላይ ለጥብቅና አገልግሎት ከተሠጠው ትርጉም አንድ የህግ
ባለሙያ የጥብቅና አገልግሎት ለመሥጠት ሌሎች መመዘኛዎቹን ጨምሮ
• በህግ ሙያ የሠለጠነ
• ሠፊ ልምድ ያለው
• የፍርድ ቤት አሠራርን ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆን ይኖርበታል፡፡
2.3 ጠበቃው የህግ ባለሙያ መሆኑና በሙያው ሠፊ ልምድ ያለው መሆኑ ደግሞ
የጥብቅና አገልግሎቱን በሙያዊ ችሎታና ብቃት እንዲያከናውን ያሥችሉታል ማለት
ነው፡፡
2.4 በእርግጥ አንድ ጠበቃ በሚሠጠው የጥብቅና አገልግሎት ከፍተኛ የሙያ ችሎታና
ብቃት ማሳየት ይጠበቅበታል ሲባል ብቃቱን ለመለካት ምን አይነት መመዘኛ መጠቀም
እንዳለብን የተቀመጠ መለኪያ መስፈርት የለም፡፡
2.5 በግል የጥብቅና አገልግሎት የሚሠጡ ባለሙያዎች ወደ ሥራው ከመግባታቸው
በፊት አገልግሎቱን ለመሥጠት ፈቃድ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡ ፈቃዱን ለማግኘት
ደግሞ በአብዛኛው ጠበቆቹ የሙያ ፈተና የሚሠጣቸው ሲሆን ፈተናውን ማለፋቸው
ፈቃዱን እንዲያገኙ ከማሥቻል አልፎ በእርግጠኝነት ብቃታቸውን ያሳያል ብሎ
መደምደም ግን የሚቻል አይደለም ምክንያቱም በአንድ ወቅት ላይ በሚሠጥ እና

Solomon Engda Alemu


የተከላካይ ጠበቆች ስነምግባርና ከተከሳሾች ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት

የተወሠኑ የህግ አርዕስቶችን ብቻ በሚወክል ፈተና የባለሙያዎቹን ችሎታና ብቃት


መመዘን አሥቸጋሪ ስለሚሆን ነው፡፡
2.6 የሆነው ሆኖ ፈቃድ ሰጪው አካል የጥብቅና ፈቃድ ለባለሙያው ሲሰጥ ባለሙያው
አገልግሎቱን ለመስጠት የተፈቀደለት እንደሆነ የሚያሳይ እንጅ የጠበቃውን በሙያውና
በሚሰጠው አገልግሎት ብቁ ሆኖ መገኘት የሚያመለክት ሊሆን አይችልም፡፡ ታዲያ
የደንበኛው ብቃት የሚለካው እንዴት ነው ?
2.7 የደንበኛው ብቃት በመሰረታዊነት መለካት ያለበት ጠበቃው ህግ በሚፈቅድለት
መሰረት የደንበኛውን መብትና ጥቅም ለማስከበር እውቀቱን፤ክህሎቱን እና የሥራ
ልምዱን በሥራ ላይ አውሎ ለደንበኛው የሚጠቅም ውጤት ለማስገኘት በሚያደርገው
ጥረት ነው ይህም ማለት ጠበቃው ለደንበኛው ህግ የሚፈቅድለትን መብትና ጥቅም
እንዲያገኝ ማድረግ መቻል አለበት ማለት ነው፡፡
2.8 በሌላ አገላለጽ ደንበኛው ህግ የፈቀደለትን መብትና ጥቅም ጠበቃው ተገቢውን
የሙያ ችሎታና ልምድ ተጠቅሞ ባለመከራከሩ ሳያገኘው የቀረ እንደሆነ ጠበቃው
ብቃት የለውም ሊባል ይችላል ማለት ነው፡፡
2. አጠቃላይ መርሆዎች
3.1 የህግ ባለሙያዎች ሥነ ምግባር በሙያው የተሰማሩ ሰዎችን ሙያዊ የሥነ ምግባር
እሴቶች የሚመለከት ነው፡፡ እነዚህም የመልካም ሙያዊ ሥነ ምግባር እሴቶችና
መርሆዎች በአለም አቀፍ ደረጃ በአብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል ተቀባይነት ያላቸውና
ዋጋ የሚሰጣቸው ናቸው፡፡
3.2 በብዙዎቹ የሕብረተሰብ ክፍሎች እንደመልካም ሙያዊ ሥነ-
ሥነ-ምግባር ከሚቆጠሩት
እሴቶች መካከል ታማኝነት፣ ኃላፊነት፣ ምክንያታዊነት፣ አመዛዛኝነትና የመሳሰሉት
ጥቂቶቹ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
3.3 የአሜሪካን የባር አሶስየሽን ያወጣቸው ሞዴል መመሪያዎች የአሜሪካን ጠበቆች
ላይ ብቻ ሳይሆን በአለም ዙሪያ በዚህ የሥራ መሥክ የተሰማሩ ባለሙያዎች ላይ ሁሉ
ተጽዕኖ ማሳደር የቻሉ ናቸው ለዚህም ምክንያቱ እነዚህ ሞዴል መመሪያዎች
የጠበቆችን ሙያዊ ሥነ ምግባር ያካተቱ መሆናቸው ነው፡፡
3.4 ሞዴል መመሪያዎቹም የደንበኛንና የጠበቃን ግንኙነት፣ በፍትህ ሥርዓቱ
የጠበቃውን ተግባር፣ ጠበቃው ከደንበኞች ውጪ ካሉ ሌሎች ሰዎች ጋር ሥለሚኖረው
ግንኙነት፣ ከህግ ማህበራት፣ ከሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ጋር ጠበቃው
ሥለሚኖረው ግንኙነት እንዲሁም ሥለ ጥብቅና ሙያ ክብርና የመሳሰሉትን የሚያካትት
ነው፡፡
Solomon Engda Alemu
የተከላካይ ጠበቆች ስነምግባርና ከተከሳሾች ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት

3.5 የጠበቆች ሥነ ምግባር መለያ ባህሪያት ከሆኑት ውስጥ ምስጢር መጠበቅ፣


ችሎቶቹንና የፍርድ ሂደቱን ማክበርና ማስከበር፣ ከሌሎች ጋር በሚኖር ግንኙነት
እውነተኛና ሀቀኛ መሆን፣ ሙያዊ ነጻነትና የመሳሰሉት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
3.6 ጠበቆች ወክለዋቸው የሚከራከሩላቸውን ደንበኞች ጥቅምና መብት ለማስከበር
ማንኛውንም ህጋዊ የሆነ ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህም ማለት ጠበቆች
ደንበኛቸው ጉዳዩን እንዲያሸንፍ ለማድረግ ከሆነ ይሁን በማለት መፈፀም ሳይሆን
መሆን ያለበት መሆኑን ሊረዱት ይገባል፡፡
3.7 እንግዲህ እነዚህ ከፍተኛ የማሸነፍ ፍላጐቶች ናቸው ጠበቆች ላይ የሙያዊ ሥነ
ምግባር ሥጋት እንዲፈጠር የሚያስገድዱት፡፡
3.8 እንደጠበቃ የምናቀርባቸው ሐሳቦችና የመከራከሪያ ነጥቦች ደንበኞቻችንን ነጻ
ሊያደርጉ የሚችሉ መሆናቸውን ብቻ ሳይሆን የተጐጂዎችንና የቤተሰቦቻቸውን
እንዲሁም የመላውን ሕብረተሰብ ሥብዕና የሚነኩ አለመሆናቸውን ማረጋገጥ አለብን፡፡
ለምሳሌ፡- አንድ የሰባት ዓመት ህጻንን ለገደለ ሰው በጥብቅና የሚከራከር ባለሙያ
የሟች ቤተሰቦች የአኗኗር ሁኔታ ከጤናማ ቤተሰብ የኑሮ ሁኔታ ጋር የሚጣጣም
አይደለም በተለይም የሟች ቤተሰቦች የአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚ መሆናቸው የዕጽ
ነጋዴው ልጃቸውን እንዲገድለው ምክንያት ሆኗል በሚል ደንበኛው ከጥፋተኛነት ነፃ
እንዲሆን ተከራክሯል፡፡ ይህ የመከራከሪያ ሃሳብም ልጃቸውን ላጡ ቤተሰቦች በልጃቸው
ሞት ተጐጂ ከመሆናቸው ባሻገር ከፍተኛ የሆነ የህሊናና ማህበራዊ ጉዳት
እንዲደርስባቸው ያደርጋል፡፡ ስለሆነም ጠበቆች የሚያቀርቧቸው መከራከሪያዎች
በበሰሉና ቅንነት በተሞላባቸው ሁኔታዎች የሚቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡

4.የጠበቆች ስነምግባር መለያ ባህሪያት


4.1 ነጻነት
4.1.1 ጠበቆች የሙያ ተግባራቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ ከማንኛውም ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ
ተጽዕኖ ነጻ መሆን አለባቸው፡፡ ይህ ነጻነት ከጠበቃው ከራሱ የግል ፍላጐት (Personal interest)
ጭምር መሆን አለበት፡፡

Solomon Engda Alemu


የተከላካይ ጠበቆች ስነምግባርና ከተከሳሾች ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት

4.1.2 ጠበቆች ደንበኞቻቸውን ወይም ዳኞችን ወይም ሌሎች ሶስተኛ ወገኖችን ለማስደሰት ሲሉ
ሙያዊ ኃላፊነታቸውንና በሙያው የተጣለባቸውን ግዴታ የሚጐዳ ተግባር በፍፁም ከመፈፀም
መቆጠብ አለባቸው፡፡
4.1.3 የጠበቆች ነጻነትም በችሎት ላይ በሚቆሙበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ከያዙት
ጉዳይ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሌሎች ተግባራትን ከችሎት ውጪ
በሚያከናውኑበት ጊዜም ጭምር ሊሆን ይገባል፡፡
4.1.4 ጠበቃው አንድን ደንበኛ ወክሎ በሚከራከርበት ጊዜ ነጻነቱን፣ አላማውንና
ችሎታውን በሚፈታተን ደረጃ ከደንበኛው ጋር ቅርርብ መፍጠር የለበትም፡፡ የዘወትር
ተግባሩና ኃላፊነቱ የሆኑትን መልካም ሙያዊ ሥነ ምግባር፣ ሞራላዊ እሴቶችና ሙያዊ
መርሆዎች ማክበርና መከተል አለበት፡፡
4.1.5 የጥብቅና ሙያ ተግባር ደንበኞችን ከጥፋተኝነትና ከቅጣት ነጻ ማድረግ ነው ይህ ተግባር
በሚፈፀምበት ጊዜ ህግንና ደንብን በተከተለ መልክ በጥንቃቄ ካልሆነ ደንበኛን ከችግር
ለማውጣት እራሥን ችግር ውስጥ መክተት ሊከሰት ይችላል ሥለሆነም የጥብቅና ሙያ
አገልግሎት በምንሰጥበት ጊዜ ህግንና ደንብን በተከተለ መልክ መሆን ይኖርበታል (Your
Job is to get your client out of trouble, not to get your self into it.)
4.2 ምሥጢርን መጠበቅ (Confidentiality)
4.2.1 ደንበኛ ለሌሎች ሶስተኛ ወገኖች ግልጽ የማያደርገውን ምስጢር ለጠበቃው ይናገራል፡፡
ጠበቃው በስራ ግንኙነታቸው ምክንያት ደንበኛው የነገረውን ወይም በዚሁ ሥራ አጋጣሚ
ያወቀውን ምስጢር የመጠበቅ ወይም ለሌላ የሶስተኛ ወገን አሳልፎ ያለመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
4.2.2 ጠበቃው ምስጢሩን እንደሚጠብቅለት እርግጠኛ እስካልሆነ ድረስ በደንበኛና በጠበቃው
መካከል መተማመን የሚባል ነገር ሊኖር አይችልም ሥለዚህ ምስጢር መጠበቅ ዋነኛና መሰረታዊ
የጠበቆች ግዴታ ነው ማለት ነው፡፡
4.2.3 ምስጢርን መጠበቅ ጠቀሜታው ለደንበኛውና ደንበኛው ከጠበቃው ጋር ለሚኖረው
የወደፊት ግንኙነት ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ለፍትህ አስተዳደሩም ጭምር ነው፡፡
4.2.4 በፍርድ ቤቶች የሚሰጠው ውሳኔ ፍትሐዊና ተመዛዛኝ እንዲሆን የህግ እውቀት የሌላቸው
ተከሳሾች በጠበቃ መወከል እንዳለባቸው የሚታወቅ ሲሆን ጠበቃው የደንበኛውን ምስጢር
የማይጠብቅ ከሆነ በሁለቱ መካከል መተማመን አይኖርም መተማመን ከሌለ ደግሞ ጠበቃው
ደንበኛውን ወክሎ ሊከራከር አይችልም ስለዚህም ከላይ እንዳየነው ፍትሃዊና ተመዛዛኝ ውሳኔ
ለመስጠት ያስቸግራል በዚህም የፍትህ አስተዳደሩ ፍትሃዊነት ይጐድለዋል ማለት ነው፡፡
4.2.5 ምስጢርን የመጠበቅ ግዴታ በጠበቃው ላይ ብቻ ሳይሆን እርሱ በቀጠራቸው ረዳቶችና
ሌሎች ሰራተኞች ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ የተጣለ ግዴታ ነው፡፡
Solomon Engda Alemu
የተከላካይ ጠበቆች ስነምግባርና ከተከሳሾች ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት

ጥያቄ፡-1
ጥያቄ፡
ወይ? ምስጢሩ እስከመቼ ነው የሚጠበቀው?
ምስጢርን መጠበቅ በጊዜ ገደብ ሊወሰን ይችላል ወይ? የሚጠበቀው?
ደንበኛው በፍርድ ቤት ያለውን ክርክር ጨርሶ ሲሰናበት ምስጢሩ ይፋ ቢሆን ልዩነት ያመጣል
ወይ? ደንበኛው በወንጀል ጥፋተኛ ቢሆንና ምስጢር የተባለውም ነገር ቢሆን በጉዳዩ ውጤት
ወይ?
ቢሆን? ምስጢር የተባለው ነገር ከተከሰሰበት ጉዳይ ጋር ምንም ግንኙነት
ላይ ልዩነት የማያመጣ ቢሆን?
ቢሆን? በህግ የማያስቀጣው
የሌለው ሆና ነገር ግን ጠበቃው የሙያ ተግባሩን ሲወጣ ያወቀው ቢሆን?
ቢሆን?
ሆኖ በግላዊና ማህበራዊ ህይወቱ ተጽዕኖ የሚፈጥር ቢሆን?

ጥያቄ 2
ተከሳሹ የተከሰሰው በመድፈር ወንጀል ሆኖ ነገር ግን ጠበቃው የሙያ ተግባሩን በሚወጣበት ጊዜ
ደንበኛው የተሰለበና የመድፈር ወንጀል መፈፀም የማይችል መሆኑን ቢረዳ ነገር ግን ደንበኛው
ይህንን ጉዳይ ለፍርድ ቤትም ሆነ ለሌላ ለማንኛውም ሰው ግልጽ እንዳያደርገው ለጠበቃው
ቢነግረው በሌላ በኩል ተከሳሹ አሁን ምስጢር ነው ከተባለው ጉዳይ ውጪ ሌላ ከጥፋተኝነትና
አለበት?
ከቅጣት የሚያድነው ማስረጃ ባይኖር ጠበቃው ምን ማድረግ አለበት?

ጥያቄ 3
አንድ ጠበቃ ደንበኛው የነገረውን ወይም በስራ አጋጣሚ ስለደንበኛው ያወቀውን ምስጢር
ለሌላ ለማንኛውም ሰው አሳልፎ መስጠት እንደሌለበት ቀደም ሲል ያየን ሲሆን ይህ ምስጢርን
ወይ? የሚጣስ ከሆነስ ጠበቃው የደንበኛውን
አሳልፎ ያለመስጠት ግዴታ ሊጣስ ይችላል ወይ?
ነው?
ምስጢር ለሌላ ሶስተኛ ወገን ግልጽ ሊያደርግ የሚችለው መቼ ነው?

4.3 የደንበኛን ምስጢር ስለመግለጽ


4.3.1 የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን ጠበቆች ሥነ ምግባር ለመወሰን በሚኒስትሮች ምክር ቤት
የወጣው ደንብ ቁጥር 57/92 አንቀጽ 11 ላይ ተደንግጐ እንደሚገኘው ጠበቃው ተገቢ ነው ብሎ
ሲያምን በሙያ ሥራው አጋጣሚ በእጁ የገባውን መረጃ በሚከተሉት ምክንያቶች እንደአስፈላጊነቱ
መጠን ሊገልጽ ይችላል፡፡
i ከደንበኛው ያገኘው መረጃ ለተወከለበት ሥራ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ
ii. ከደንበኛው ጋር ክርክር በሚፈጠርበት ጊዜ ራሱን ለመከላከል ወይም መብቱን
ለማስከበር
iii. የውክልና ሥልጣኑን የተመለከተ ክርክር ሲነሳ
iv. ህግ በሌላ ሁኔታ በግልጽ የጣለበትን ግዴታ ለመወጣት
v.ደንበኛው ለጠበቃው ሲፈቅድለት

Solomon Engda Alemu


የተከላካይ ጠበቆች ስነምግባርና ከተከሳሾች ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት

4.3.2 ጠበቃው መረጃዎቹን ግልፅ ሊያደርግ የሚችለው ከተራ ቁጥር 1-5 የተዘረዘሩት ምክንያቶች
ሲከሰቱና የመረጃው ግልፅ መሆን አስፈላጊ ሲሆን ግልፅ መሆን ባለበት አስፈላጊነት መጠን ብቻ
መሆኑን ለመረዳት ይቻላል፡፡

ጥያቄ 4
ለአንድ ተከሳሽ በደንበኛነት የሚከራከር ጠበቃ ከደንበኛው ጋር በተፈጠረው ግንኙነት ደንበኛው አሁን
በወንጀል ከተከሰሰበት ወንጀል በተጨማሪ ብዙሃኑን ህዝብ ሊጐዳ የሚችል የባዬሎጂካል የጦር መሳሪያ
ለምሳሌ አንትራክስ በቤቱ ውስጥ ያለው መሆኑን ቢያውቅ ይህንን መረጃ ግልፅ ማድረግ የለበትም
ወይ?
ወይ?

4.3.3 ማንኛውም ጠበቃ በራሱና በደንበኛው ወይም በዘመዶቹና በደንበኛው ወይም በሸሪኮቹና
በደንበኛው ወይም በሁለት ደንበኞቹ መካከል የጥቅም ግጭት መኖሩን እያወቀ የሙያ አገልግሎት
ለመስጠት መዋዋል አይችልም የጥቅም ግጭቱ መኖሩ የታወቀው አገልግሎት ከተጀመረ በኋላ ከሆነ
ይህንኑ ለደንበኛው አስረድቶ አገልግሎቱን ማቋረጥ አለበት፡፡

4.4. ለተቃራኒ ወገን ቅን ስለመሆን


4.4.1 ቅን ባለሙያ ማን ነው?
ነው? የሚለውን ስንመለከት እርሱ ሊታመን የሚችል ባለሙያ ነው ይህም
ሲባል የጠበቃው አገላለፅና ባህሪ ትክክለኛ እና ትክክለኛነቱም የሚረጋገጥ መሆን አለበት ለማለት
ነው፡፡ (Accurate and authentic መሆን አለበት)
አለበት)
4.4.2 እርግጠኛ (Accurate )መሆን አለበት ሲባል ደግሞ ጠበቃው የሚሰጠው መረጃ ወይም
የሚያቀርበው ክርክር እውነትነት ያለው እና ሌሎችን ሆን ተብሎ የሚያሳስት ወይም
የሚያታልል መሆን አይኖርበትም ማለት ነው፡፡
4.4.3 እርግጠኛነት(Accuracy) እውነትነት ያላቸውን መረጃዎች የሚመለከት ሆኖ መረጃዎቹ
እርግጠኛነት(Accuracy)
እንዲሁ ሲታዩ እውነት ሆነው ነገር ግን ቴክኒካዊ ሁኔታቸው ሲታይ የሚያሳስቱ ወይም
ጠቀሜታ ኑሮአቸው መገለፅ ሲገባቸው በሚታለፉበት ጊዜ እነዚህን መረጃዎች ለመመዘን
የምንጠቀምበት ዘዴ ነው፡፡

4.4.4 የሚያሳስት መረጃ እርግጠኛነት የሌለው ስለሆነ የሚታመን መረጃ ተብሎ አይወሰድም፣
መረጃ(Authentic expression or Evidence) ግን ፍትሃዊ በሆነ ሁኔታ
የተረጋገጠ መረጃ(Authentic
የጠበቃውን ሃሳብ የሚያረጋግጥ መረጃ ነው፡፡

Solomon Engda Alemu


የተከላካይ ጠበቆች ስነምግባርና ከተከሳሾች ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት

4.4.5 በዓቃቤ ህግና በወንጀል ጠበቆች መካከል የሚኖረው ግንኙነት የመተማመንና የመተባበር
መንፈስ የሚታይበት መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህም በችሎት በሚከራከሩበት ጊዜ የተለያዩ ወገኖችን
ለህ/ሰቡ ደህንነት የሚሰሩ በመሆናቸው
ወክለው የሚከራከሩ በሆኑም ሁሉም ለፍትህ፣ ለእውነትና ለህ/
ቅንነት በተሞላበት ሁኔታ ክራክራቸውን ማከናወን እንደአለባቸው የሚያመለክት ነው ፡፡
4.4.6 ሁለቱም ወገኖች ሙያዊ ክርክርን የሚያንዛዛና የፍትህ ሥርዓቱን የሚጐዳ ውጤት
ሊያስገኝ የሚችል ተግባር መፈፀም የለባቸውም ይህም ሲባል በሁለቱም ባለሙያዎች መካከል
በክርክር ሂደት የመከባበርና የሙያ አጋርነት መንፈስ ሊንፀባረቅ ይገባል፡፡ ጠበቃው ቅንነት ይጎድለዋል
የሚባለው መቼ ነው ?
4.4.7 ጠበቃው ቅንነት ተቃራኒ ወገን ማስረጃ እንዳያገኝ ማንኛውም አይነት እንቅፋት
አለመፍጠርን ፣ ማስረጃን አለማሳሳትን ፣ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት የሌለው ወይም በማስረጃ
ሊደገፍ የማይችል ነገር አለማቅረብን፣ በምስክርነት ካልቀረበ በስተቀር በግሉ የሚያውቀን
የጭብጥ ፍሬ ነገሮች ያለመሰንዘርን፣ ለደንበኛው በሚሰጠው የጥብቅና አገልግሎት ሶስተኛ
ወገኖችን ያለማጉላላትን እና የመሳሰሉትን ሊያጠቃልል ይችላል፡፡
4.4.8 ጠበቃው ከደንበኛው፣ ከሌላኛው ተከራካሪ ወገን ወይም ከሌላ ሶስተኛ ወገን ጋር የሚኖረው
ግንኙነት በቅንነት፣ በመከባበርና በመግባባት ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ይህም ሲባል
ጠበቃው በክርክር ወቅት ማንኛውንም ሰው በማንኛውም መንገድ ማንቋሸሽ ወይም ክብሩን
ለመቀነስ መሞከር እንደሌለበት የሚያስገነዝብ ነው፡፡

4.5 የሚከራከሩበትን ጉዳይ በሚገባ መረዳት


4.5.1 ተከላካይ ጠበቆች ለሚከራከሩላቸው ደንበኞች ጉዳይ አስፈላጊውን እና ተገቢውን ዝግጅት
ማድረግ እንዳለባቸው ሁሉም የሚስማማበት ነጥብ ነው ሆኖም አንዳንድ ጊዜ ጠበቆቹ የወከሏቸውን
ደንበኞች መዝገብ ሳይመረምሩና ሳያጤኑ ወደ ችሎት የሚቀርቡበት ሁኔታ ይታያል፡፡
4.5.2 አሜሪካ ሀገር የኦሃዩ ሥቴት የወንጀል ጠበቆች ማህበር ኘሬዚዳንት ካርሜን ሄርናንዴስ ስለዚህ
ጉዳይ ሲናገር ትክክለኛና ሚዛናዊ ውሳኔ መስጠት እንዲቻል ዓቃቤ ህጉም ሆነ የወንጀል ጉዳይ
ጠበቃው የሚከራከርበትን ጉዳይ አጥንተውና ተዘጋጅተው ችሎት መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የሚከራከርበትን ጉዳይ ሳያጠናና ሳያዘጋጅ ወደ ችሎት የሚቀርብ ባለሙያ በሽተኛን
ሳይመረምር የቀዶ ጥገና ለማድረግ ስራው ወደሚሰራበት ክፍል የሚገባ ሃኪም ማለት ነው
ስለሆነም መዝገቡን ሳያጤኑ ወደ ችሎት መቅረብና የበሽተኛውን ታሪክና ሁኔታ ሳይመረምሩ
ባለጉዳዬችንም/ ደንበኞችን/
የቀዶ ጥገና ማድረግ ውጤቱ አደገኛና ባለጉዳዬችንም/ ደንበኞችን/ ለጉዳትና ለሽንፈት
የሚዳርግ ነው ብለዋል፡፡

Solomon Engda Alemu


የተከላካይ ጠበቆች ስነምግባርና ከተከሳሾች ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት

5- በጠበቆች ላይ የሚጣሉ የህግና የሞራል ግዴታዎች

5.1 ቀደም ሲል በዝርዝር ያየናቸውና በጠበቆች ላይ የሚጣሉ ግዴታዎችና ገደቦች በዋናነት


በሁለት ከፍለን ልናያቸው እንችላለን፡፡
1. የህግ ግዴታዎች(
ግዴታዎች(ገደቦች)
ገደቦች)
2. የሞራል ግዴታዎች(
ግዴታዎች(ገደቦች)
ገደቦች)
5.2 እነዚህ የህግና የሞራል ገዶቦች ጠበቆች ደንበኞቻቸውን በተመለከተ፣ ፍ/
ፍ/ቤቶችንና የፍትህ
ሙያ(Profession)
አካላትን በተመለከተ፣ የተሰማሩበትን ሙያ(Profession) በተመለከተ፣ ማህበረሰቡን
በተመለከተ በሚያከናውኗቸው ተግባራትና ከላይ ከጠቀስናቸው ነገሮች ጋር በሚኖራቸው
ግንኙነት ተፈፃሚ የሚሆኑ ናቸው፡፡
5.3 የዚህ ፅሁፍ ዓላማ በሞራልና በህግ ገደቦች ዝርዝር ሁኔታ ላይ ገብቶ ማብራራት ባይሆንም
እነዚህ ገደቦች ጠበቆቹ የስራ ተግባራቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ እርስ በእርሳቸው የሚጋጩበት
ሁኔታ የሚከሰትበት ጊዜ እንዳለ ግን መጠቀስ አለበት፡፡ ህጉ ጠበቃውን አንድ ነገር እንዲፈፅም
እያስገደደው ሞራሉ ደግሞ የህግን ግዴታ ለመፈፀም የሚያደርውን ጥረት ይፈታተነዋል፡፡

ጥያቄ 5 ፡-
በሞራልና በስነ ምግባር (Moral VS Ethics) መካከል ያለው ልዩነት ምንድ ነው?
ነው?
5.4 ሞራልና ሥነ ምግባር በአብዛኛው አንዱ ሌላውን ተክቶ ስንገለግልበት ይታያል ሆኖም
በሁለቱ መካከል ልዩነት እንዳለ መረዳት ያስፈልጋል፡፡
5.5 ሞራል የምንላቸው በአብዛኛው ከግላዊ የእስቴቶች (Value) አመለካከት ጋር የተያያዙ
ሲሆኑ ሥለ ጾታዊ ግንኙነት፣ ስለ መብላትና መጠጣት ያሉንን እንዲሁም ሀይማኖት፣ ባህል፣
ቤተሰብ ፣ ጓደኛ የማያሳድሩብንን ተፅዕኖዎች ሞራል በሚል ልመድባቸው እንችላለን በሌላ
በኩል ሥነ ምግባር ደግሞ ከላይ የዘረዘርናቸውን የሞራል እሴቶች ተግባራዊ በማድረግ ረገድ
አንድ ሰው የሚያሳየው ባህሪ ነው፡፡

Solomon Engda Alemu


የተከላካይ ጠበቆች ስነምግባርና ከተከሳሾች ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት

5.6 ሥነ ምግባራዊ እሴቶች የምንላቸው በሞራል ረገድ ትክክልና አግባብ የሆኑ እሴቶችን
ለምሳሌ፡- አንድ ሰው አልኮሆል መጠጣት ከሞራል
የምንለይበት እምነታችንን ነው ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ፡-
ውጪ እንደሆነ በግሉ ሊያምን ይችላል ሆኖም ግን አልኮል መጠጣት በራሱ ከመልካም የስነ
ምግባር መርሆዎች ውጪ ነው ሊባል አይችልም፡፡
5.7 ሲጠቃለልም ሞራላዊ እሴቶችን የራሱ ያላደረገ ጠበቃ በሙያ ስነ ምግባሩ ከፍትሃዊነት
ወደ ኢፍትሃዊነት፣ ከእውነተኛነት ወደ ሀሰተኛነት የሚያደላ ሲሆን ይህ ደግሞ የጥብቅና ሙያ
መመዘኛ( minimum Standard) የወረደ ስለሆነ
ከሚጠይቀው ዝቅተኛ ደረጃ ወይም መመዘኛ(
የጠበቃውን ደረጃ ዝቅ እንዲል ያደረገዋል፡፡

6- ጠበቆች ከደንበኞች ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት


6.1 የሙያ ግዴታ በሚፈቅደው መጠን ጠበቆች ሁልጊዜም የደንበኞችን ፍላጐት መሰረት
ያደረገ እንቅስቃሴ መከተል ያለባቸው ሲሆን የደንበኞች ፍላጐት ከራሳቸውም ሆነ
ከሌሎች በዚህ ሙያ ከተሰማሩ ሰዎች ፍላጐት በላይ መሆኑን ማረጋገጥ
ይጠበቅባቸዋል፡፡
6.2 ጠበቃው ስለ እያንዳንዱ የጉዳዩ ዝርዝርም ሆነ የችሎት ውሎ፣ በችሎት ስለተረዳው
ሁኔታ ለደንበኛው በዝርዝር የማስረዳትና የማሳወቅ ኃላፊነት አለበት፡፡
6.3 ደንበኛው ሌላ ጠበቃ ማግኘት በማይችልበት ሁኔታና ጊዜ የጥብቅና ውክልና
እንዲነሳለት ደንበኛውን ለመጠየቅ የሙያው ስነ ምግባር አይፈቅድለትም፡፡
6.4 ጠበቃው ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ደንበኞችን ወክሎ በሚከራከርበት ጊዜ
የፍላጐት ግጭት ቢፈጠር ወይም የሚፈጠርበት ስጋት ካለ ሁሉንም ደንበኞች
የመምከርና የመወከል ተግባሩን መፈፀም የለበትም፡፡

Solomon Engda Alemu


የተከላካይ ጠበቆች ስነምግባርና ከተከሳሾች ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት

ጥያቄ 6፡-

ነው?
ለሁሉም ደንበኞች የሚሰጠውን አገልግሎት ማቆም ያለበት ለምንድን ነው?
6.5 ከቀድሞ ደንበኞቹ መካከል የተወሰኑትን መምከርም ሆነ ወክሎ የመከራከር ተግባሩን
ቢፈፀም ቀደም ሲል ከሌሎቹ ደንበኞች በስራ አጋጣሚ ያወቀውን ወይም ደንበኛው
የነገሩትን ምስጢር መጠበቅ የማይችል በመሆኑና ይህም ሙያዊ ነጻነቱቱን የሚፈታተን
በመሆኑ ነው፡፡
6.6 አዲስ ደንበኛ በሚወክልበት ጊዜም ቀደም ሲል ከነበሩት ደንበኞች ያገኘው እውቀት
/መረጃ/
መረጃ/ አሁን ለሚወክለው ደንበኛ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ሊያስገኝለት የሚችል
መሆኑን ከተረዳው ጠበቃው አዲሱን ደንበኛ ወክሎ መከራከር የለበትም፡፡
6.7 የአውሮፓ ህብረት ጠበቆችን ሥነ ምግባር የሚወስነው ደንብ በአንቀጽ 3.3 ላይ
ጠበቆች የ “Pactum de Quota Litis” መብት ሊሰጣቸው እንደማይገባ
ደንግጓል፡፡
6.8 “Pactum de Quota Litis” ማለት ጠበቆችና ደንበኞች የሚገቡት ውል ሆኖ
ደንበኛ አባል የሆነበትን ጉዳይ ወክሎ የሚከራከረው ጠበቃ ጉዳዩን ካሸነፈ የአሸነፈውን
ሃብት መጠን በጋራ እኩል ለመከፋፈል የሚደረግ ውል ነው፡፡

ጥያቄ 7፡-
በኢትዮጵያ የፍትህ ሥርዓት ጠበቆች የ “Pactum de Quota Litis” ውል ሊዋዋሉ
ወይ?
ይችላሉ ወይ?

7 .ጠበቆች ከፍርድ ቤት ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት

7.1 ጠበቆች የችሎት ስራ ሥርዓት ይዞ እንዲሄድ በሚደረግው ጥረት በከፍተኛ ደረጃ መሳተፍ
አለባቸው፡፡ ይህም ማለት ማንኛውም ችሎት ውስጥ የሚፈጽሙት ተግባር የችሎቱን አካሄድ
ሥርዓት የተከተለ መሆን አለበት ለማለት ነው፡፡
7.2 ጠበቆች በችሎት በሚከራከሩበት ጊዜ ያለምንም ፍርሃትና መሸማቀቅ የደንበኞቻቸውን
ፍላጐት ለማስጠበቅ ከፍተኛውን ድርሻ መወጣት አለባቸው፡፡

Solomon Engda Alemu


የተከላካይ ጠበቆች ስነምግባርና ከተከሳሾች ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት

7.3 ጠበቆች በምንም አይነት መንገድ ወይም ምክንያት ሀሰትነት ያላቸውን ወይም
የሚያሳስቱ መረጃዎችን እያወቁ ለፍርድ ቤት መስጠት የለባቸውም፡፡
7.4 የደንበኛና የጠበቃን ግንኙነት ስንመለከት አንድ ተከላካይ ጠበቃ ወክሎ ከሚከራከርለት
ተከሳሽ /ደንበኛ/
ደንበኛ/ ገንዘብ ሊበደርም ሆነ ለእርሱ ለማበደር እንደማይችል በደንብ ቁጥር 57/92
ላይ ተደንግጐ ይገኛል ለዚህም ምክንያቱ ጠበቃው ከደንበኛው ጋር እንዲህ አይነት ግንኙነት
ቢመሰርት ነጻነቱን፣ ዓላማውንና ሙያዊ ኃላፊነቱም ሊጐዳው የሚችል መሆኑን ነው፡፡

8 ማጠቃለያ

• ጠበቃ ህግን ለማስከበርና ፍትህ ለማስገኘት የፍትህ አስተዳደሩን የማገዝ ኃላፊት እንዳለበት
የሚታወቅ ሲሆን ይህንንም ተግባሩን ሲወጣ ሙያዎ ነፃነቱን፣ የደንበኛን ምስጢር
መጠበቅን ፣ ለደንበኛውና ለፍትህ አስተዳደሩ ያለውን ታማኝነት በማይሸረሽር መልኩ
መሆን አለበት፡፡
• የጥብቅና የሥራ ድርሻ በሀገራችን የፍትህ አስተዳደር ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲያድግ
እንዲሁም የዳኝነት አካሄዳችንነ የተፋጠነ ፣ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ
የሚያበረክተው አስዋፅኦ ቀላል የሚባል አይደለም ስለሆነም በሀገንችን ውስጥ የሚገኙ
ፍ/ቤቶች ይህንን የስራ ክፍል በማቴሪያልም ሆነ በሰው ኃይል እንዲደራጅ ቢደረግ ጥቅሙ
ከፍ ያለ ይሆናል፡፡
• ተከላካይ ጠበቆችም ተከሳሽን ወክለው ሲከራከሩ ትክክለኛና ሚዛናዊ ፍርድ እንዲሰጥ
ጥረት ከማድረግ በተጨማሪ ዲሞክራሲና የፍትህ ስርዓቱ እንዲጐለብቱ
የራሳቸውንድርሻመወጣትይኖርባቸል ::

Solomon Engda Alemu

You might also like