You are on page 1of 16

ለ አእምሮ ልዩ እትም / ታህሳስ/ጥር 2006 / 01 / 2014 - አዲስ ዓመት

ቅጽ 2፣ ቁጥር 5 / Vol II-06/01-5

ለ ማሰብ ...

2014

... ለ ማወቅ

እንኳን አደረሳችሁ!
1

ይ ዘ ት / Content
2014
እንኳን አደረሳችሁ !
***
ኦ! ... አንቺ ኢትዮጵያ !
—————————ለ አእምሮ ልዩ እትም / ታህሳስ/ጥር 2006 / 01 / 2014 – አዲስ ዓመት/ ቅጽ 2፣ ቁጥር 5

2

2014

እንኳን
አደረሳችሁ …
ገና ! X-MAS
ልጆች ሲጫወቱ ጣታቸውን እያሳዩና እየቆጠሩ „…እኛ ቤት ሁል ጊዜ ሁለት ገናዎች… ሁለት
አዲስ ዓመቶች፣ሁለት ፋሲካና ሁለት… ይከበራል። ሁለቱንም ጊዜ ስጦታ ይቀርብልናል።
ይሰጣናል።“
ይህን ሲሰሙ ሌሎቹ „ይህማ ትክክል አይደለም ! …እኛ እኮ አንዴ ብቻ ነው የምናገኘው ይህ
ትክክለኛ ሥራ አ…“
„እንደ እናንተ!“-የበዓላችንን ብዛትና መደራረብ አይተው ነጮቹ- „ እንደ እናንተ የታደለ
ሕዝብ የለም!“ ይሉናል።
3

እንደምናውቀው እኛም እርስ በራሳችን
በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሁለቴና
ሦስት ጊዜ „…የደስታና የጤና የፍቅርና የሰላም
ዘመን…ለአንቺም ለአንተም ለእኛም ይሁንልን
ይሁንላችሁ!“ እንደ ደንቡና እንደ ቆየው
ልማዳችን በሥነ-ሥርዓቱ እንባባላለን።

ነጮቹ እንደሚሉት በእርግጥ „እሱ ረስቶን“
ይሆን?

በእርግጥም ይህን ምኞት ማቅረቡና ማሰማቱ
በደንብ ብናስብበት (እንደ እኛ) ዕውነቱን
ለመናገር – ምርቃቱ ቀላል አይደለም- የታደለ
ሕዝብ የለም።

ፍቅሩም ሰላሙም ጤንነቱም (በየአለበት ሰው
ሁሉ በነገር ተሳክሮ ዕብደት ብቻ ስለሆነ)
ይኸው የተባለው ምኞት ሳይደርስልን ከአርባ
አመት በላይ ስንቆጥረው አልፎታል።

አዲሱን ዓመት ቢያንስ ሁለት ጊዜ አብዛኛዎቻችን
ውጭ አገር ያለን ሰዎች እናከብራለን። የገና
በዓልን እንደዚሁ። ፋሲካንና ስቅለትን እነሱንም
እንደዚሁ አከታትለን ሁለት ጊዜ አንዱ
የእኛን ሌላ ጊዜ የአውሮፓን ከተለመደው
የከበረ ሰላምታና ምኞት ጋር አብረን እኩል
እናከብራለን።

„…ኤርትራ
ትገንጠል፣…ኤርትራ
ከአልተገነጠለች፣… ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል
አይደለችም። ስለዚህ ኤርትራ ይኸው በእናንተ
ፈቃድና ምኞት ትገንጠል ብላችሁ ጠይቃችሁ
ተገነጠለች። እኛም ይህ ከሆነ ከእንግዲህ ውጭ
የሚንከራተት የኤርትራ ስደተኛ አይኖርም።
ጦርነቱም ያቆማል። ወደፊትም አይኖርም ብለን
ገምተን ነበር። ግን አሁን እንደምናየውና እንደ
ምንሰማው ሰው በብዛት አገሩን እየጣለ እየወጣ
የስደተኛው ቁጥር በውጭ አገር ጨምሮአል።…
ይባስ ብለችሁ ኦሮሚያ ከአልተገነጠለች
ትላላችሁ። ኦጋዴን ከአልሄደች። አማራ
መንደሩን ለቆ ይውጣ ከማለት አልፋችሁ
ደግሞ የእራሳችሁን ትላልቅ ለም የእርሻ መሬት
ከነጫካውና ከነወንዙ ለባዕድ መንግሥታትና
ነጋዴዎች ለሰባና ዘጠና አመታት ቸብችባችሁ፣
በረሃብ አለቅን ልናልቅ ነው እረ እባካችሁ
ድረሱልን ትላላችሁ። …ምንድነው ለመሆኑ
እናንተ የምትፈልጉት? ለመሆኑ የምትፈልጉትን
በቅጡ ታውቃላችሁ….“ ነጮቹ እንደዚህ እያሉ
በየጊዜው ይጠይቃሉ።

ከሞስሊሙ ሓይማኖት ተከታዮችና ከአረቡ
ሕዝብም ጋር እኩል ትልቁን በዓላቸውን
አብረን „…እንኳን አደረሳችሁ…“ ብለን በጋራ
ተመኝተን በጋራ እናከብራለን።

ወይስ ሌሎቹ እንደሚሉት „ምኞቱ ከልብ
ስለአልሆነ …አልሰማ ብሎን ይሆን?“
ይህን የምንልበት በቂ ምክንያት አለን።

ግን አንድ ቅር የሚልና የሚገርምም ነገር አለ።
እሱም :በየጊዜው ለወዳጅ ለጓደኛ ለዘመድና ለጎረቤት
„…የደስታና የሰላም የፍቅርና የጤና…ዘመን
ይሁንልን“ ብለን የምንመኘው ምኞታችንን
እግዚአብሔር ሰምቶ ለምን እስከ አሁን ድረስ
ለዚያ „በመከራና በሥቃይ ለሚኖረው …ሰላምና
ፍቅር ደስታና ጤና ለጠማውና ለሚናፍቀው
ሕዝብና ለእኛም ጭምር መልስ የአልሰጠበት
መልስ የማይሰጥበት ምክንያት ? ማወቁ ዕርዳታ አቅራቢ ነጮቹ የፈለጉትን በየጊዜው
አስቸጋሪ ነው።
ቢሉ፣ይህን ሲሉ ዕውነት አላቸው።
4

ታሪክ ፍርዱዋን ያልሰጠች ይመስል- ታሪክ
ፍርዱን ብዙ ቦታ ሰጥቶአል- ንጉሡ ወርደው
በንጉሡ ፋንታ„…ሰበአዊና ዲሞክራሲያዊ
መብቶች የተከበሩበት ነጻ ምርጫ የሚካሄድበት
ነጻ-ሕብረተሰብ በኢትዮጵያ ይመሰረታል „
እንዳልተባለ በእሱ ቦታ የተረሣውን መድገም
ያስፈልጋል፣ደርግ የሚባል የወታደሩ አምባገነን
መንግሥት ኢትዮጵያ ላይ ተመሥርቶ ሁሉን
ጸጥ ለጥ አድረጎ ገዝቶአል።

መብቶችን ጉዳይ ዞር ብለው ያላዩ ሰዎች“ አንዱ
እንዳለው (እነ አቶ ታምራት ላይኔ እነ ዶ/ር
ነጋሶ ጊዳዳ አቶ ሰዬ አብረሃ፣አምባሳደር ካሣ
ከበደ፣ አንዳርጋቸው ጽጌ…)፣አሁን ሰውዬው
እንዳለው „ ለዲሞክራሲ መምጣት ግንባር
ቀደም ታጋይ ወጥቶአቸው እኛን ከገባንበት
ማጥ ነጻ ለማውጣት ተነስተዋል“
ከፊሉ አሥመራ ላይ መሽጎ! ሌላው ከአሜሪካ፣
የተቀረው ከአዲስ አበባ !

ለማስታወስ ያኔም በየዓመቱ ለአሥራ ሰባት
ዓመታት በተከታታይ„…ገና ሲመጣ ዘመን „ለመሆኑ ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ ?“ ብለው
አልፎ ዘመን ሲተካ…ፋሲካ ሲደርስ እንደ አንዳዶቹ እራሳቸውን ተገርመው ይጠይቃሉ።
ተለመደው „…የሰላም የፍቅር የ…“ ተባብለናል።
„የሞቀ ቤታቸው ውስጥ ተቀምጠው“ ነጻውን
በሁዋላስ?
የዲሞክራሲ አየር የሚተነፍሱ እንደፈለጉ
ማንንም ሳይፈሩ ገብተው የሚወጡ አንዳንድ
እነሱን -ደርግንና መንግሥቱ ኃይለማሪያምን ሰዎች ደግሞ -ይህ ነው ሌላው ጥያቄ „…ለምን
ጥለን- „ …እንደገና ነጻና ዲሞክራቲክ እና በምን ምክንያት ምንስ ነክቶአቸው ነው ?
መንግሥትን በኢትዮጵያ መስርተን የግለሰብ …ስለ ኪዩባና ስለ ፔኪንግ ስለዚያ አምባገነን
ነጻነትን አክብረንና አስከብረን ነጻ-ጋዜጣን ሥርዓት ስለ እነሱ መፍትሔና ጎዳና ለአገራቸው
ፈቅድን የፓርላማ ምርጫን አካሂደን …“ ለኢትዮጵያና ለሕዝቦቻቸው የሚመኙት?“
ያሉ ድርጅቶች ሥልጣኑን ሲጨብጡ ብለው ነጮቹ እዚህ በሚያወጡት ጽሑፍ ላይ
አገሪቱን ለሁለት ከፍለው መዳፋቸው ውስጥ እራሳቸውን ይጠይቃሉ እኛንም መልስ አምጡ
አስገብተው ትንሽ ቆይተው እነሱ እራሳቸው ብለው ይወተውታሉ።
ጦርነት ከፍተው ከአንድ መቶ ሺህ ወጣቶች
በላይ ባድሜ ላይ ወድቀዋል።
አልፈው ሄደው በነገሩ ተገርመው “ …ከአልጠፋ
የሰበአዊና ዲሞክራሲዊ መብቶች ጽንሰ-ሐሳብ
እንደገና ለማስታወስ ያኔም እንደተለመደው „… ኮንሴፕት (ዓለም አቀፉ የተባበሩት መንግሥታት
እንኳን አደረሳችሁ ተባብለን…የፍቅርና የሰላም አዋጅ አለ) ለምንድነው አንዳንድ ጸሓፊች፣
የደስታና የ…“ ምኞታችንን ተለዋውጠናል።
ከአልጠፋ ነገር ስለ `የገዳ – ዲሞክራሲ´ና
ስለ እሱ መምጣት የሚያስተምሩት?“ ብለው
አሁንስ?
እነዚህ ሰዎች እራሳቸውን ይጠይቃሉ።
በሥልጣን ዘመናቸው ቅንጣት ያህል እንኳን እንግዲህ
„አትድከሙ
እግዚአብሔር
አተኩሮ አድረገው „…የሰበአዊና ዲሞክራቲክ ረስቶአችሁዋል።„ የሚሉት ወገኖች ሆነ ወይም
5

„….ቅመሱት እኛም ቀምሰነው ወጥቶልናል
…..ይገባችሁዋል „ የሚሉት የቀድሞ ምሥራቅ
ጀርመን ወዳጆቻችን… ሁለቱም ሦስቱም
ወቃሾች ሁሉም በእኛ ላይ በሚሰጡት „ፍርድ“
ዕውነት ያዘለ ነገር የወረወሩ ይመስለናል።
ዕውነትም አላቸው።
„…የሰላምና የፍቅር፣የደስታና የጤና የብልጽግና
እና የጥጋብ የጸጋና የሐብት…“ ምኞቶችን
ከልብ ታስቦበት ለዘመድ ወይም ለወገን
ከአልተመኙላቸው፣ያ ነገር ዝም ብሎ ከተፍ
አይልም። መመኘት ብቻ ሳይሆን ያ የተመኙት
እንዲመጣም እንዲደርስም በፍቅርና በአንድነት
በጋራ አንድ ላይ ሁነው ተረዳድተው ተግተው
ጥረው ደክመው እንደገና በጋራ ያ ሁኔታ
እንዲመጣ ከአልሰሩበት እንዲያው ከሰማይ
ዱብ የሚል የመና ዳቦም አይደለም።

ተረግመን ለማኝ ሆነን እንድንቀር የተደረግን
ፍጡሮችም“ አይደለንም።
ቁም ነገሩ ያለው ሌላ ቦታ ላይ ነው።
እነሱ ፣- ይህ ነው የኑሮ ብልሃቱ- እነሱን
ከሚያጣላና ጥላቻን ብቻ ከሚያስተምር
አይዲዎሎጂ እና የፖለቲካ ቲዎሪ እረሳቸውን
አርቀው ተቻችለውና ተከባብረው -እኛ
ሁላችንም በየአመቱ አንዴ ወይም ሁለቴ
እንደምንለው „…የሰላምና የፍቅር የደስታና
የብልጽግ የጤናና የፈንጠዚያ …ምኞታቸውን“
በቃላትና በአፍ ብቻ ሳይሆን በተግባር በሥራ
ላይ አውለው በጋራ አንድ ላይ ቆመው
ተደጋግፈው በመሥራታቸው ብቻ ነው።
ተግባባን?

ይህ ደግሞ ፈጠራ ሳይሆን የፖለቲካ ቲዎሪ
ምናልባት „እግዚአብሔር የማይሰማን እሰከ መጽሓፍቶቻቸው ውስጥ ተጽፎ ይገኛል።
አሁን ያልሰማን „ ከልብ ስለአልሆነ ይሆን?
ይህን የጋራ ዓላማ የሚጥስ ሰው በመካከላቸው
ታሪክ ፍርዱዋን ሌላ ቦታ ሰጥታለች።
የለም ፈጽሞ አይገኝም ማለት አይቻልም።
ግን -ይህን ማወቅ ያስፈልጋል- ሕጉም
ዞር ብለን አካባቢአችንንከቃኘን ብዙ ቦታዎች ሞራሉም
ሕሊናውም
ነጻ-ፕሬሱም
ታሪክ ፍርዱዋን ሰጥታለች።
አስተዳደጉም ጓደኛውም፣ ዘመድም ወገንም
የሁዋላ ሁዋላ እንደዚህ ዓይነቱን ሰው
አካባቢአችንንከቃኘንና ትንሽ ቆም ብለን ደግሞ ይወቅሰዋል።ይገሥጸዋል። ተው እንዴ አበድክ
እሱን አንስተን ከአሰላሰልን አንድ የምንረዳው ወይ ይለዋል።
ነገር ቢኖር „… የበለጸጉ ሓብታም የእንዱስትሪ
አገሮች የሚባሉት መንግሥታት“ እዚህ የተረፈ በዚህ መንፈስ፥በዚህ አመለካከት እንኳን
ዳቦ የሚጣልበት ደረጃ ላይ የደረሱት፣ እነሱ ለአዲሱ አመት እንኳን ለብርሃነ ልደቱ፣
ከእኛ ይልቅ „…አማኝ ሃይማኖተኛ ሁነው ለሰላምና ለፍቅሩ … በደህና አደራሳችሁ
እግዚአብሔርን በመቅረባቸው ብቻ „ተባርከው እንላለን።
እዚህ የደረሱ ምርጥ ልጆቹ“ በመሆናቸው
አይደለም።
የሰላምና የፍቅር የደስታና የብልጽግና የጤናና
ወይም ደግሞ አንዳንዶቹ እንደሚገምቱት „እኛ እና የፈንጠዚያ ዘመንም እንመኝላችሁዋለን!
6

ምናልባት ፈጣሪያችን – ይህን ከልብ ስለአልን- አንድ ቀን ይሰማን ይሆን?
አዘጋጆቹ
ለአእምሮ
—————————ለ አእምሮ ልዩ እትም / ታህሳስ/ጥር 2006 / 01 / 2014 – አዲስ ዓመት/ ቅጽ 2፣ ቁጥር 5
***
ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4/
ለ አእምሮ / Le'Aimero የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !
( A New Book)
“Abyssinian Christianity: The First Christian Nation?”

7

የፖለቲካ ቲዎሪና ታሪክ የሰጠቺው ፍርድ

እኛ ማን ነን?
ኦ! … አንቺ ኢትዮጵያ !„ -በእነዚህ ቃላት ነው ትረካውን እሱ የጀመረው -„…
በዓለም ታሪክ ውስጥ ያለሽን ታሪክና ቦታ በደንብ ብታውቂ ኑሮ አንቺም እንደ ጃፓኖቹ በአካባቢሽ
ተፈርተሽና ተከብረሽ ትኖሪ ነበር። ግን ምን ይደረጋል ብልሃቱን በደንብ አላወቅሽበትም።
ባለማወቅሽም ልጆችሽ ዛሬ በባዕድ አገር መሣቂያና መቀለጃ ሁነዋል።
እንደ ታላቁዋ ብርታኒያን ወይም እንደ ሆላንድ አንቺም ንጉሥሺን ወይም ንግሥትሽን ይዘሽ
ኮርተሽ እንደ ሌሎቹ እኩል ተገቢውን ቦታሽን ይዘሽ በዓለም ላይ ልጆችሽ ሳይፈሩና ሳይዋረዱ
ፊታቸውን አስመትተው መድረኩ ላይ እንደ ጓደኞቻቸው በሆኑና መድረኩ ላይ ኮርተው እነሱ
በተውረገረጉልሽ ነበር።
ምን ይሆናል አይኖችሽ ሳይታወሩ ታውረው ጨልሞብሽ ይህን ነገር ነቅተሽ በጊዜው ሳታደርጊ
ቀርተሽ ሁሉ ነገር ሳታስቢው ከእጅሽ አፈትልኮ አምልጦአል።
እንደ ዴንማርክና እንደ ሰውዲን እንደ ቤልጅግና እንደ ስፔንና እንደ ኖርዌይ እንደ ሉክስምበርግና
…እንደ ሞሮኮ እንቺም – የለም ሳውዲና ሞሮኮን ትተሽ- እንደ የላይኖቹ ሕዝብና መንግሥታት
የአንቺም ስም በጥሩ ነገር በተነሳ ነበር።
እንደ ፈረንሣይ እና አንደ አሜሪካ ኮርተሽ ፕሬዚዳንቶችሽን አንቺም አንድ ሁለት ብለሽ ብለሽ
ልትመርጪ ትችይ ነበር።
ግን…ምን ይደረግ!
እንደ ጀርመንና እንደ አውስትራሊያ እንደ ኦስትሪየና እንደ ደቡብ አፍሪካ እንደ ጋና እና እንደ
ኬንያ እንደ ናይጄሪያና …ቦትስዋና አንችም በነጻ -ምርጫ በየአራትና በየአምስቱ አመታት
8

መሪዎችሽን በመረጠሽ እንደ ሸሚዝ እነሱን “ ጥፋቱ …የአስተማሪዎቹ? ወይስ …የወላጅ
አንቺም በለዋወጥሽም ነበር።
የአሳዳጊዋቹ ? ጥፋቱ …መካሪ ጓደኞቻቸው?
ወይስ ነጮቹ? …ወይስ ደግሞ እንደሚባለው
ግን እንደምናየው ለዚህ አልታደልሽም ።
የንጉሠ-ነገሥቱ? የእሳቸው ሥርዓት?…
መሣፍንቱና መኳንንቶቹ? ወይስ ጻሓፊ ትዕዛዝ
ወደፊትም የታደልሽ አይመስልም።
አክሊሉ ሐብተውልድ ብቻቸውን? ወይስ
የልጅ እንዳልካቸው መኮንን ካቢኔ? ጥፋተኛው
ሌላው ቀርቶ ነጻ -ጋዜጣ እና ነጻ -ፍርድ ቤት የ…ድንበር ጠባቂ ወታደሮች? ወይስ ምንም
እንደ ጎረቤት አገር እንደ ኬንያ እንኳን ማቋቋም የማያውቁ…ድንጋይ ወርዋሪ ተማሪዎች? እነሱ
አቅቶሽ አንድም ቦታ ለወሬ የሚሆን እንዲያው የለኮሱት እሳት? ለመሆኑ …ተራ ገበሬ ተጠያቂ
ለመከራከሪያ ምንም ነገር በእጅሽ የለም።
ነው? ወይስ የሠራተኛው መደብ? እነሱ ከሆኑ
-ለመሆኑ አገሪቱ ስንት ሺህ የፋብሪካ ሠራተኞች
ዜጎችሽ አለ ጸጥታ ፖሊስ ቁጥጥር አዳራሽ ያኔ ነበራት?“ እያለ ባህታዊው አፋቸውን
ተከራይተው መሰብሰብ እንኳን በገዛ ከፍተው የሚያዳምጡትን ሰዎች ይጠይቃል።
አገራቸው አይችሉም። መቃወም መደገፍ
መተቸት መውቀስ መደራጀት በመሬትሽ ላይ „ በአገሪቱ ውስጥ ለተካሄደው ጥፋት ተጠያቂው
አይቻልም።
ለመሆኑ የመንግሥት ሠራተኞች ናቸው? ወይስ
ለመሆኑ ኢትዮጵያ ከአለችበትና ከገባችበት
ለመሆኑ ወደሽ ነው ወይስ ተገደሽ ነው ? አንቺ ችግር ለመውጣት ተጠያቂው ያኔ ይንቀሳቀሱ
– እንደ ትልቅ ቁም ነገር የመረጥሽውመንገድ- የነበሩ ወንበዴዎች ? እነዚያ ነጻ-አውጪ ነን
የቼጉቬራና የካስትሮ፣ የሆቺሚንና የፖልፖት፣ ባዮች…. ጀበሃና ሻቢያ ናቸው?“
የማኦና የስታሊን የሌንን እና የማርክስ የሆነው?
„እረ ማነው? ኢትዮጵያንለመበተን የተነሳው?…
ይህ በመሆኑም ልጆችሽ ተበጣብጠው አረቦቹ ? ወይስ ሌላ የማናውቃቸው ውጭ
ተናንቀው ተጨራርሰው ሞተዋል። አልቀዋል። ኃይሎች?… ኮሚንስት ቻይና ወይስ ኮሚኒስት
ወይም ተበትነዋል። ወይም ደግሞ አገር ጥለው ሞስኮ…? ወይስ አሜሪካና አውሮፓ? ማነው
ተሰደዋል።
ለኢትዮጵያ እዚህ አሁን ያለችበት ደረጃ ላይ
ለመድረስ፥ ለማድረስ ተጠያቂው?
„ጥፋቱ የማነው ንገሪኝ? „ እያለ ይህን ነገር
በዓይኑ አይቶ ወረቀት ላይ አስፍሮ ያነበበ ሰው ደርግ ነው? ወይስ ….መኢሶንና ኢህአፓ?
„ ያ ! ገና በዕድሜው ወደ ሃምሳው አመት ወያኔና ኦነግ? ሰደድና …ወዝ? ወይስ ደግሞ
መጀመሪያ ላይ የሆነው ባህታዊ ከተረከዙ የከተማ ቀበሌ? የፍርድ ሽንጎና ችሎት?
ብድግ ብሎ እየተንጠራራ ንግረኝ ጥፋቱ የማን
ነው? የሚለው ጥያቄው ከአንጎሌ አልወጣ ወይስ ቀስ ብሎ ….ትንሽ ቆይቶ …. እነዚያ የአገሪቱ
አለኝ „ ብሎ አንድ አዳራሽ ውስጥ ብዙ ሰዎችን ካህናቱና ቀሳውስቱ?…“ ሲል አዳመጩ ሁሉ
ያጫውታል።
በአንድ ድምጽ „…እነሱማ ካህናቱና ቀሳውስቱ
9

እነሱማ ምን አደረጉ? እነሱ አይደሉም … ሌሎቹ “….በስደት ዘመናቸው ዮሴፍ ቅድስት
ናቸው።
ማሪያምና ክርስቶስ በመሬትሽ ላይ ተሰደው
ኑሮዋል።ለመሆኑ ይህን ታውቃላችሁ? ይህን
…. እነ እገሌን እነ እገሌን አባ ረስተዋል። እነሱን አስተማሪዎቻችሁ አስተምረዋችሁዋል? ….
እላይ እንደጀመሩት ይቁጠሩልን ? …ሰይጣኑ ከዚያ በፊት የሙሴ ጽላት ታቦቱ ወደ እንቺ
ኢትዮጵያን የለከፋት አጋንንት ያለው እዚያና ቤት – ወደ ውድ እናቴ ገብቶአል።….ለግሪክ
እዚህ ነው…እነ አገሌ መንደር ነው እንደጀመሩት ፍልስፍና ለሮም ሕግጋት ለፋርስ አኗኗር ዘይቤ
ይቁጠሩልን …እያሉ
አንቺ አዲስ አይደለሽም።
ሲጣሩ ባህታዊው „ ታሪኩን የሚያጫውተው
ጸሓፊ እንደተረከው“ … እነሱን እሳቸው በዚያ
ግርግር እንዳልሰሙ ሁነው እንደገና ብድግ
እያሉ ከተረከዛቸው እየተንጠራሩ -እሱ
እንደ ተረከው- እጆቻቹን ዘርግተው „ ….አይ
ኢትዮጵያ! አላወቅሽበትም እንጂ -የምዕራቡ
ዓለም ገና አሕዛብ በነበረበት ዘመን አውሮፓና
አሜሪካ ማለታቸው ነው- አንቺ በዓለም
ላይ የመጀመሪያው የክርስቲያን መንግሥት
የተመሠረተበት የተቀደሽ አገርና መንግሥት
ነበረሽ። …. ታሪክሽን ግን አንቺ በደንብ
አታውቂም። ለመሆኑ ታውቂ አለሽ? ከሜካና
ከመዲና ውጭ አንቺ የመጀመሪያው የነቢዩ
መሐመድ ተከታይ ስደተኞች አስተናጋጅ አገር
እንደ ነበርሽ? „

አባቶችሽ መርከብ ሠርተው ባህር አቋርጠው
በህንድ ውቂያኖስ ላይ ተንሳፈው ወደ ላይ ወደ
ታች ተዘዋውረው አካባቢውን ተቆጣጥረው
እንደ ፈለጉት ይወጡ እንደ ፈለጉት ይገቡ
ነበር።ያ ዛሬ አትላንቲክ ውቅያኖስ ተብሎ
የሚጠራው ባህር ስሙንታውቃላችሁ?ይህን
ስሙ፣የህንድ ውቅያኖስ እንደሚባለው
የኢትዮጵያ ውቅያኖስ ነበር“ እያለ ያ ባህታዊ
አረፋ እየደፈቀ እጁን እየመተረ – ሁኔታውን
የዘገበው ሰው እንደአለው- አዳማጮቹን
ይቆጣል።ዓይኑን ጎልጉሎ ያፈጣል። ቀስ
እያለም አየሩን እየሳበ የተቻለውን ከዕውቀቱ
እያካፈለ ለሚሰሙት ያስተምራል ።

ቀጥሎም ይህ በቢጫ ቀሚሱ ላይ ተመሣሣይ
ነጠላውንና የደረበው ባህታዊ „ …እናት
ከተቦጫጨቀው ወረቀት ላይ እዚያው ላይ አገራችሁ በዓለም ላይ ትልቁን ሰማይ ጠቀስ
ቀጥሎ እያነበበ:ሐውልት ሰርታላች። ምድር ወርደው መሬት
ቆፍረው ድንጋይ ፈልፍለው አባቶቻችሁ
አዲሱን ኢየሩሳሌም ቆርቁራዋል።
ያ ሁሉ ጥበብ ያ ሁሉ ዕውቀት ያ ሁሉ
የመኖር ብልሃት የአስተዳደር ዘይቤ አሁን
የት ገባ? ምን አደፈረሰው? አላወቅሽበትም
እንጅ አንቺም ኢትዮጵያ… „ ሰውዬው
እዚህ ላይ አቀራረቡን በየጊዜው አድማጩ
በአላሰበበትና በአልገመተበት ሰዓት
10

ይቀያይረዋል- „እንደሌሎቹ መንግሥታትና
ሕዝብ ልጆችሽ ከመራባቸው በፊት ብድግ ብለሽ
ሽንጡን ከደቡብ አሜሪካ ከአርጀንቲና ታላቅና
ታናሹን ከብራዚል ማንጎና አናናሱን የወይን
ፍሬውንና ጽጌረዳውንከቺሊ ከኮሎምቢያ
ከኬንያና ከደቡብ አፍሪካና ከካሜሩን እንቺም
ብታውቂበት ማምጣት ትችያለሽ።

ሲቆጥር „እኛም መኪና መሥራት እንችላለን
„ የሚለው መዝሙር የሰውዬውን ንግግር
ማጀብ፣ልጁ እንደጻፈው ማጀብ ይጀምራል።
„…ግን ምን ይደረግ አንዲት አጥንት“ – ይህ
ለሰሚው ሁሉ ኃይለኛ ቃል ነው -„…ሆን ተብሎ
ተጠንቶ እንዲጣልባቸው፣ እንደተጣለላቸው
የመንደር ውሾች ልጆቹዋ እንዲጣሉበት
ያን!… „ ባህታዊው እዚህ ላይ ነገር የገባው
ይመስላል-የሰውን ልጆች ሁሉ ከአላወቁበት
የሚያበጣብጠውን የዘር ጥያቄን፣የነገሮች ሁሉ
እምብርት አድረጎ የሚያየውን ትምህርት- „…
እናውቃልን ለሚሉት ወጣት የኢትዮጵያ ልጆች
አስጨብጠው በነገር አሳክረው ለቀቁአቸው …“
ልጁ እንደዘገበው ሰባኪው ባህታዊው ይላል።

ወረድ ብለሽ ወርቅና አልማዙን የዝሆን ጥርሱን
መዳቡን ከኮንጎ፣ ነዳጅ ዘይት ከሱዳን ከአንጎላና
ከጋና ….“ እያለ ሲቆጥር „ ተመልከት ተመልከት
ይህን ፊውዳል ርዝራዥ„ ምን አለ? ሰማኸው
ምን እንዳለ?… ከኮንጎ እና ከኬንያ ከ…ደቡብ
አፍሪካ …ከአርጀንቲና ሽንጥና አልማዝ
እናስገብር አለ…“ አያሉ አንዳንድ ወጣት ልጆች
ሲጮሁበት፣ሌሎቹ „….አባ ይቀጥሉ፣ዝም
ብለው ይቀጥሉ…“ የሚል ድምጽ ተሰማ።
በዚህቺ ደቂቃ ይህ ተሰምቶ ሳያልቅ ደወል
ተደውሎ ታቦቱ ወደ ጥምቀት ወንዝ ለመውረድ
„…ነዳጅ ዘይት ከሳውዲ ከኢራንና ሊቢያ …“ ከመቅደሱ ይወጣል።
የሚለው ቃል ሲሰማ ሰው ሁሉ ደስ ብሎት –
ጸሓፊው እንደ ዘገበው „…ቅልጥ ያለ ጭብጨባ ሁካታና ግርግር ጩኸትና እልልታ ቅጥር
በገዳሙ ውስጥ ተሰማ።“
ጊቢው ውስጥ ይሰማል። ገዳሙ ሁል ጊዜ ምን
እንደሆን አይታወቅም ታቦት ሲወጣ እንዳለ
ያለነው እሱ ጸሓፊው እንዳ አጫወተው ይንቀጠቀጣል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ከአሉት በሺህ ከሚቆጠሩት
አድባራትና ገዳማት ከአንዱ አጥር ግቢ ውስጥ ታቦቱን የተሸከሙ ቄስ ከነጃንጥላው ዞር ሲሉ
ነው። „… የወይን ጠጅ ከጣሊያን አገር „ ሲል ህዝቡ ሆ ብሎ መሬት ላይ ወድቆ አፈሩን ሣሩን
ደግሞ ልክ „ሳውዲ ብሎ እላይ ኢ… ኢራን „ ድንጋዩን ተሳልሞ …በበራ ዓይኑ ከወደቀበት
ሳይል እንደተቋረጠው እንደገና አሁንም ልጁ ይነሳል።…ያኔ እልልታው ይቀጣል።ከበሮው
እንደተረከው „ጣሊያን „ የሚባለው ቃል ይደቆሳል።ትናንሽ
ልጆች
ተደናግጠው
ሲሰማ በጭብጨባ „ የወይን ጠጅ ለኢትዮጵያ ይሁን ደስ ብሎቸው ይጮኻለሁ። ጽናጽሉ
ከፈረንሣይ ሳይባልና ሳይጨመርበት“ እዚያው አለ። እጣኑ። አልፎ አልፎ ጠበንጃ የያዙት
ላይ ይቋረጣል ።
ይተኩሳሉ።የባሩድ ሽታም አፍንጫ ይመታል።
„እኔን ሁለት የተለያዩ የከበሮው ድምጽ የሚሰጡ
ባህታዊው የወይራ ዘይት „…ከግሪክና ከቱኒዚያ ድምጾች ምን እንደሆን አይታወቅም ስሰማ ልቤ
መኪና ከጀርመን፣ ከአሜሪካና ከጃፓን…“ እያለ ደስ ይለዋል። እንቢልታውና መለከቱ ዋሽንቱና
11

ማሲንቆው…ዝማሬውና ሽብሸባው…ይህ ሁሉ ባልቴቶችንም አንድ ላይ ጨፍልቆ አድማጮቹን
ሌላ ዓለም ውስጥ „ ጸሓፊው እንዳለው „እምነት ሁሉ እያፈጠጠ ይጠይቃል።
እንኳን የሌለውን ሰው ጎትቶ ይከታል።“
„ቀላል ነው!…“ ብሎ እራሱ መልስ ለመስጠትም
እንደገና ከሌላ ቦታ ተንደርድሮ ይነሳል።

ከግቢው ወጥተው ትንሽ እንደተራመዱ ሁለት
ሦስት ታቦቶች አንድ መገናኛ መንገድ ላይ
ይገናኛሉ።
እንደገና ሁሉም ነገር በሦስት እጥፍ ቅድም
እንደታየው (አቤት! አቤት!)በበለጠ ይቀልጣል
። „ይህ ነው ኢትዮጵያን“ ልጁ እንደጻፈው“
ለብዙ መቶ አመታትና ዘመናት ለሺህና ሁለት
ሺህ አመታት አንድ አድረጎ -ይህን መቀበል
የማይፈልጉ አሉ- ያቆያት።“

„… በዘር ወንደሞቼና እህቶቼ!.. በቆዳ ቀልም
ሐብት በአለውና በሌለው በመደብ በሃይማኖት
በዕድሜ በጾታ ወንድና ሴት እያልክ፣ ጥቁርና
ነጭ ክልስና መጤ ኑዋሪውንና የቆየውን …
በተለይ የአሜሪካኑን ዜጋማ አንተማ ጣሊያን
ነህ።አንተ ደግሞ ዘርህ ጀርመን ነው። አንተ
እንግሊዝ… ፈረንሣይ ናይጄሪያ ስፔን ፖርቱጋል
አማራ ጉራጌ ትግሬ ሐማሴን ኦሮሞ ጋናዊ
አረብ አሜሪካዊ እያልክ…ሆላንድ እና ስውዲን
ግሪክንና አርመንን ዝም ብለህ ከፋፍለህ፣
ከቻልክ ሜክሲኮን ድንበርህን አስመልስ
ብራዚልን ተሰባሰብ እያልክ…“ ሰውዬው
የአሜሪካኖችን ታሪክ የሚያውቅ ይመስላል„ ልታበጣብጣቸው (የሚሰማህ የለም እንጅ)
እነሱን እኛ ከመሬት ተነስተን እንደተበጣበጥነው
በቀላሉ እነሱንም -የሚሰማህ የለም እንጅ –
ቀስ ብለህ ልትበትናቸው ትችላለህ…“

አዳማጮቹን ስለ አገኘ ባህታዊው በታየው
ግርግር ፈጽሞ ሳይረበሽ ቀጥሎበት ኑሮ፣ሌላ
አህጉር ጭልጥ ብሎ ገብቶአል። በመካከሉ
በጀመረበት ንግግሩ አንዳንድ አገሮችን ነካክቶ
አሜሪካንና ሕንድ ላይ ደርሶአል። ቻይናና „የሚሰማ „ ዕውነትም ሰውዬው እንዳለው
ሩሲያንም ዋዘኛ ሰው አይደለም በዚያች አጭር እንደዚህ ዓይነቱን ምክርና ዕብደት አሜሪካን
አገር ዱሮም ቢሆን አሁንም የለም፣የለም ።
ጊዜ ዳስሶአል።
እርግጥ አንድ ጊዜ ደቡቦቹ እንገንጠል ብለው
„…ሕንድን ከውስጥ ገብቶ ለመበተን፣ ቻይናና የእርስ በእርስ ጦርነት ተከፍቶ የአሜሪካ
ሩሲያን ለመገልበጥ አውሮፓን እንደ ዶሮ አንድነት በደም መፍሰስ ተመልሶአል።
ለመገነጣጠል ታላቁዋ ብሪታንንያንና ትልቁን
አሜሪካንን“ ባህታዊው እንዳለው „ እንደ መብቱ ተጠብቆለት እያለ ምን አቅብጦት ነው
ኢትዮጵያ እነሱ ውስጥ ገብቶ ለመበተን፣ ነጻ የሆነውን የጋራ ቤቱን ከመሬት ተነስቶ
ምን ማድረግ ያስፈልጋል ? እስቲ ንገሩኝ ቆዳዬ ዘሬ መልኬና ሐብቴ እያለ እንደ ዕብድ
?“ ብሎ ወጣቱንም አዛውንቱንም የደከሙ የሞቀ ቤቱን የሚያፈርሰው? እንነሳ የሚሉትን
12

ሕጉም አይለቀውም።
አይፈቅድለትም።

ይቀጠዋል

እንጂ ወታደሮች ብቅ ይሉበታል።

„ምንድነው የምታወራው? ምንድ ነው
„…አረቦቹንም
ከአወክበት“
ባህታዊው የምትቀሰቅሰው?…“ ይሉታል ።
እንደአለው „እነሱንም ብደግ ብለህ እንደ
ክርታስ ቤት ልትበትነው ትችላለህ። አረብና ሳይፈራ ጸሓፊው እንደ ዘገበው ባህታዊው
ጥቁር አፍሪካ እያልክ ቱርክና ኩርድ ሦሪያና „….እኔ የማወራው ስለ ሌላ ነገር ሳይሆን
ፋርስ፣ ሽኢትና ሱኒት ዋህቢና ታሊባን…እያልክ በዓይነህ ስለምታየው የኢትዮጵያ ሁኔታ ነው!“
እየከፋፈልክና እየሰነጣጠክ -ይህ ምን ያደርጋል ብሎ በጠያቂዎቹ ላይ አፍጦ ይጮኻል።
እግዚአብሔር አይቀበለውም – እነሱንም አንዳንድ አዳመጮች ፈርተው ዞር ይላሉ። እሱ
እርስ በእራሳቸው በቀላሉ አጋጭተህ… ግን እንዳፈጠጠ እዚያው ቆሞ ይቀራል።
ልታጋጫቸውም ትችላለህ፣ትበትናቸዋለህ።“
ታሪኩ በዚህ አያልቅም።
ለቻይና ለሕንድ እንደ ባህላቸውና እንደ
ሥርዓታቸው ባህታዊው እነዚህ አገሮች ባህታዊው ወታደሮቹ ላይ ይወርድባቸዋል።
ከአንድ እንጨት ተፈልጠው ስለአልወጡ በምድር ብቻ ሳይሆን በምትሰሩት ሥራ ሰማይ
እነሱንም የሚያበያብጥ ቲዎሪ የተከታተለው ቤትም ትጠየቁበታላችሁ። ለነፍሳችሁ ራሩ
ልጅ እንዳለው በኪሱ አለው። በተለይ ። ቶሎብላችሁ ንሰሓ ግቡ አለበለዚያ ሲኦል
ሕንድን ትልቁንና ትንሹን ሰው በአገሪቱ ያጠብቃችሁዋል። እናንተም ልጆቻችሁም
ውስጥ በሚለየው „በካስት የንቀትና የክብር ልጆች ከሌላችሁ ዘመዶቻችሁ ይቀሰፋሉ።
ሥርዓታቸው „ እሱ ጸሓፊው እንዳዳመጠው ወየው ለእናንተ ብሎ መስቀሉን ይዞ ወደ
በቀላሉ መበታተን – እዚያም የሚያዳምጥ ማስፈራራቱ ይዘልቃል።
ሰው ከተገኘ ግን እንደዚህ ዓይነት ሞኝ ሰው
በቀላሉ አይገኝም እንጂ- እነሱንም አባ እንዳሉት ከአንድ ሰዓት በላይ በፈጀው ሰበካው በሁዋላ
መበታተን ትችላለህ።
-ጸሓፊው የተቦጫጨቀ ደብተሩን እያገላበጠ
እንደ አተተው- ባህታዊው በላቡ ታጥቦ
ባህታዊው በዚህ የሰበካ ዘዴው ቆየት ብሎ „… የደከመ ይመስላል። ፈገግታ በፊቱ ላይ
ኢትዮጵያም ከአወቀችበት ዓለምን በታትና ስለሚታይ ይህ ግን አይታወቅበትም። ንጹሕ
እሱዋ እንደፈለገችው እነሱን ልትገዛቸው ልብ ያለው ይመስላል። ነጭ ጥርሱ፣ግራጫ
ትችላለች። ግን አንተ ሞኝ በመሆንህ፣እንኳን ጢሙ፣ረጅሙና የተጎነጎነ ጠጉሩ ሞላ ያለ
ይህን ለማድረግ ይህን ለማሰብ ቀርቶ የእራስህን ድምጹ ከቢጫ ቀሚሱ ጋር ራስ ተፈሪያንን
ነፍስ ለማዳን የማትችልበት ደረጃ ደርሰኻል። ያስመስለዋል።
…አስብበት“ እያለ ወጣቱን ትውልድ በንቀት
ዓይን ይቆጣል። በመሐከሉ ትንሽ ቆየት ብሎ„… „…መስቀል ኃይል ነው።መስቀል መድሓኒት
ለመሆኑ አንተ ማን ነህ?“ የሚሉ የመንግሥት ነው።…መስቀል ያድናል እያለ „ ልጁ እንደዘገበው
13

ባህታዊው ሲሰብክ „ ለእርድ የሚነዱ ምን
የመሰሉ ቀይና ነጭ ጥቁርና ቡራቡሬ ከብቶች
ጨርቅ ለብሰው ከአራጆቻቸው ጋር ወደ ታች
ወደ ጠበሉና ወደ ወንዙ ሕዝቡንና ታቦቱን
ተከትለው ይወርዳሉ። በዚያን ሰዓት ነው
ጎረምሶችም ቆነጃጅት ኮረዳዎችን ተከትለው
አየህ ጥርሱዋን አየህ ዓይኑዋን ተረከዙዋማ
…እያሉ እየሳቁና እየተሳሳቁ፣ልጃገረዶቹ

የተነሱት ነጥቦች እዚያ ገዳም ውስጥ ትክክለኛ
ናቸው። ግን ባህታዊው ያለነሱአቸውም አብይ
ነጥቦችም አሉ።
ቤተ ክርስቲያናችን እነ መንግሥቱ ኃይለ
ማሪያም „ሥር-ነቀል ለውጥ„ ብለው በቆየው
የኢትዮጵያ ባህልና ታሪክ በእራሱዋ በቤተ
ክርስቲያኑና በቤተ ክህነቱ ላይ ሲነሱ -ቅድስት
ቤተ ክርስቲያናችን ምንምነገር አልተናገረችም።
ግፍ ሲሰራ፣በደል በአገሪቱ ሲነግስ፣ድህነት
ሲስፋፋ ሕግ ሲጓደል ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን
በአለፉት ዘመናት ሆነ አሁንም ምንም ሆነምን
ነገር
ቢመጣ፣በይፋ
ተነስታድምጹዋን
አላሰማችም።

ቅድስት ቤክርስቲያናችን አልን እንጅ ሌሎች
እየተሽኮረመሙ -ሕይወት እንደዚህ ናት – ቅዱሳን የሃይማኖት ተቋማትና ዘርፎችም
ቁልቁል እነሱም ይወርዳሉ።
እነሱም ደፍረው ሁል ጊዜ ድምጻቸውን
ሲያሰሙ አልተሰሙም።
ለዕርድ የሚቀርቡት በጎቹና ፍየሎቹ ነገ
ይከተላሉ አዛውንቶቹ ሲሉ „…እንደ ነቀርሳ ምናልባት ጭቆናን ስደትን ግርፈትንና ክትትል
አገራችን ገብቶ ያቺን አገር የበተናት የዚያ ፈርተው ሊሆን ይችላል። እኛ ስለዚህ ምንም
የስታሊን ድርሰት የዚያ የሌኒን ሁለት ታክቲክ… የምናውቀው ነገር የለም።
እያለ ባህታዊው – ስለምን እንደሚያወራ የምናውቀው ነገር ቢኖር -ከታሪክ- ኮሚንስቶች
ያውቃል- እጁን ወደ ላይ ዘርግቶ የሚራገመው ተነስተው ሥልጣን በያዙበትና እነሱ እራሳቸው
ድምጹ እንደ ገደል ማሚቶ እዚያ ቅጥር ግቢ እንደሚሉት
„አምባገነን-ዲክታተርሽፕ
ውስጥ ያስተጋባ ነበር…“
ሥርዓት„ በመሠረቱበት ሕብረተስብ ውስጥ
አንደኛው በሩሲያና በምሥራቅ አውሮፓ ነው፣
በሁዋላ ስለ ሰውዬው ተጣርቶ ስሰማ ይህ ሁለተኛው በቻይና እና በሩቅ ምሥራቅ አገሮች፣
ሰው ባህታዊ ከመሆኑ በፊት በአሜሪካን አገር ሶስተኛው በአፍሪካ በተለይ የላይኞቹን ልምሰል
ቲዎሎጂና ፍልስፍና ተምሮ የዚህች ዓለም በአልችው በኢትዮጵያ በእነዚህ አገሮች
ነገር በቃኝ ብሎ መንኖ አገሩ የገባና በየገዳሙ „ሃይማኖትና የሃይማኖት አባቶች የእምነት
ተንከራቶ በመጨረሻው የመነኮሰ ግን ደግሞ ተቋሞች በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ውለው
ላስተምር ብሎ የተነሳ ሰው ነው ብለው ቀጭጭው እንዲጠፉ ወይም ሞት ይዞአቸው
አጫውተውኛል።
እንዲሄድ የሚደረጉ ኃይሎች ናቸው።“
14

ኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥትና ቤተ ክህነት ምን እሱ ብቻ !
-ልክ እንደ አውሮፓ ያኔ እንደ ነበረው
የኢንላይትመንት እንቅስቃሴ „ሁለቱ ይለያዩ“ „መሬት ለአራሹ“ የተባለው ጥያቄ ዛሬ
የሚል እንቅስቃሴና ጥያቄ ያኔ ተስፋፍቶ ነበር። እንደምናየው የገበሬው ሳይሆን በአሥመራም
በኢትዮጵያም „የገዢው ፓርቲ ሀብት „
እሱ ብቻ አይደለም።
ሁኖአል።
ኢትዮጵያ ውስጥ መሬት ለአራሹም ለገበሬው የከተማ ቤቶችና መናፈሻዎች እንደዚሁ
ተብሎም ነበር።
በሃያኛው ክፍለ-ዘመን እነ ሌኒን እንደ አደረጉት
አሁንም እንደገና „የገዢው ፓርቲ ንብረት
እሱ ብቻ አይደለም።
ሁነዋል።“
ከዚሁ ጋር ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው ሁሉ ሓሳቡን አነሱ ናቸው የፈለጉበት ቪላና ቤተ-መንግሥት
የሚገልጽበት ነጻ ፕሬስና የፕሬስ ነጻነት ሳንሱር ውስጥ የሚኖሩበት። የመሸጥ የመለወጥ መብት
ይነሳ ተብሎም ነበር።
የእነሱ ብቻ ነው።
የንጉሠ ነገሥቱ መሬት፣የራስ መሥፍን እና
ከዚሁ ጋር ቀጥሎም ተያይዞም „ነጻ የሽንጎ ወይም የነደጃች እከሌ የእርሻ ቦታዎች
ምርጫ፣ የተላያዩ የፖለቲካ ደርጅቶች ለየገበሬው ይሆናል እንደ ተባለው ሳይሆን …
ምሥረታ፣ የመናገር የመሰብሰብ የመተቸት ዛሬ ለገዦቹ፥ ለእነሱ ወይ የሼክ አላሙዲ ናቸው
የመቃወም የመደገፍ …መብት „ በምሁራኑ ወይም የሳውዲ ንጉሥ። ከገዢው ፓርቲ ጋር
ዘንድ ተጠይቆም ነበር።
ሆላነዶች ሕንዶች ቻያናዎች አዲሱ የአገሪቱ
….የምርምር ነጻነት በዩኒቨርስቲ፣ አለሳንሱርና መሬት ባላባቶች ናቸው።
ቁጥጥር ፊልም ና መጽሓፍ ቲያትርና ሙዚቃ፣ „….ሥር-ነቀሉአብዮት“ በኢትዮጵያ በአጭሩ
ግጥምና ዘፈን … እንድረስ የፈለግነውን ልብስ የሰዎች ለውጥ ነው።
እንልበስ ተብሎም ነበር።
ነጻ ፕሬስ ነጻ ፍርድ ቤት ነጻ ሕብረተሰብ
ነጻ ሰው የሕግ በላይነት ትችት ወቀሳ ክርክር
ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ይህን ያሉና ይህን ያላሉ ስብሰባ …የሚባል ነገር የለም።
እንድ ላይ ሁነው- ይህ ነው የአገራችን ትራጀዲ
ሳይታሰብ „ …የላብ አደሩን ወይም የወዝ አደሩን ፍራንሲስ ፉክያማ የበርሊን ግንብ አጥሩ እንደ
ወይም ደርግ እንዳለው የሠራተኛውን ወይም ፈረሰ የኮሚኒስቶቹም ሥርዓት ተራ በተራ
ይባስ ብለው እነ ኢሳያስ አፈወርቂማ የፍርድና እየተንኮታኮተ መውደቁን አይቶ ይህ ምሁር
የፍትህ ….አምባገነን ሥርዓት የሁዋላ ሁዋላ ተቻኩሎ በጻፈው መጽሓፉ -የጀርመኑን
በአገሪቱ ውስጥ ተክለው“ ሁሉም ከታሪክ ፈላስፋ ሔግልን ተከትሎ- „የዓለም ታሪክ በዚህ
ጨዋታ ውጭ፣ዛሬ በደረስንበት ዕውቀት ማለት መጨረሻውን አገኘ“ ብሎ ሐሳቡን ሸብ ያኔ
እንደምንችለው -ሁሉም ሁነዋል።
አድርጎአል።
በአንድ በኩል ምሁሩ ዕውነት አለው ።
15

በፖለቲካ ቲዎሪ አንጻር -የኢኮኖሚ ቲዎሪውን ለጊዜው ቦታው ስለ አልሆነ እንተው- የሰው
ልጆችን የመናገር የመጻፍ የመመራመር የመተቸት የመፈላሰፍና የመቃወም …. ሰበአዊ መብትን
የሚያውቅና የሚቀበል እንድ ሕብተረሰብ ቢኖር ይህ እኛ በዓይናችን የምናየው -ብዙዎቹ
ተሳስተው የሚሉት – የቡርጁዋ ! …የለም በትክክል ለመናገር የምዕራቡ የሊበራሉ ዲሞክራቲክ
ሕብረተሰብ ብቻ ነው።
ቻይና እንደ ሌኒንና የስታሊን ራሺያ ይህን ዛሬማድርግ አትፈልግም።
የምዕራቡሕብረተሰብከድንበሩ አልፎ ለእኔና ለአንተ / አንቺ መብት ይቁም አይቁም፣መቆም
አለበት የለበትም የሚለው፣ …ይህ መቼም አሁን ሌላ ጥያቄ ነው።
ጥያቄው!ዋናው ጥያቄ አንተ እራስህ ምንታስባለህ ነው? ምን ዓይነት የፖለቲካ ሥነ-ሥርዓት ነው
አንተ/አንቺ የምትፈልገው/ጊው? የሚለው ነው። ወሳኝ ጥያቄው!
ጨዋታው ያለው „እኛ ምን ዓይነት ሥርዓት እንፈልጋለን? „ የሚለው ግልጥ የሆነ ጥያቄ ላይ
ነው።
ታሪክ ደግሞ በበቂ ለጥያቄው መልስ ሰጥታበታለች።
——
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
—————————ለ አእምሮ ልዩ እትም / ታህሳስ/ጥር 2006 / 01 / 2014 – አዲስ ዓመት/ ቅጽ 2፣ ቁጥር 5

16