You are on page 1of 8

ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ይባላሉ። ከሚኖሩበት ስዊዲን አገር ቤት በመምጣት "አዲስ ካርዲያ" የተባለ የልብ ህክምና ማእከል

ከሌሎች ጋር ይመስርታሉ። ከ6 አመት በፊት 32 የህክምና መሳሪያዎች ቀረጥ ሳይከፍሉ አስገብተዋል በሚል ከነመላኩ
ፈንታና ገ/ዋህድ (ከፍተኛ ሌባ ዘራፊዎች) ጋር አብረው ይከሰሳሉ። እንዲከላከሉ ሲጠየቁ "ፍረዱብኝ" አሉ ተስፋ
ቆርጠው። ባለፈው ሳምንት 4 አመትና 60ሺህ ብር ተፈረደባቸው። ዳኞች ይህን ከመወሰናቸው በፊት ጥቁር አንበሳ
ሆ/ል በመሄድ አልጋ የያዙትን ዶ/ር ፍቅሩን ተመልክተዋል። ዶ/ር ፍቅሩ ስኳርና ደም ግፊት እንዲሁም ግራ ሳንባቸው
ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። ይህን የተመለከቱት ዳኞች ስለሰውየው መልካም ተግባራት አድምጠውም
አሳፋሪ ፍርድ ተብዬ ከማሳለፍ አልተመለሱም። በአገሪቱ የመጀመሪያውን የልብ ህክምና ማእከል በመክፈት፣ በርካታ
ህሙማን በመርዳት፣ በርካታ ሀኪሞች ውጭ አገር በመላክና እንዲሰለጥኑ ከማድረጋቸው ባሻገር በመቶ ሚሊዮኖች
ገቢ ሰብስበው ለታላቁ የአባይ ግድብ ግንባታ አስረክበዋል። እኚህ ግለሰብ ለግል ጥቅም ያልቆሙና ከውጭ
የሰበሰቡትን በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ያሰረከቡ መሆናቸው በመንግስትና ፍ/ቤት ተረጋግጦ እያለ፣ 77
ቢሊዮን የዘረፉት አባይ ፀሀዬና ሌሎች ዘራፊዎች እያሉ በዶክተሩ ላይ አሳፋሪ ውሳኔ አስተላለፉ። አባዱላ ለህፃን ልጃቸው
ዲቦራ 2 ሚሊዮን ዶላር ለህክምና አውጥተው (በተዘረፈ ገንዘብ) ውጭ ሲያሳክሙ፣ ዶ/ር ፍቅሬ መታከም ያልቻሉ
የልብ ህሙማንን ለመርዳት በመምጣታቸው እንደወንጀል ተቆጠረ። ዶ/ር ፍቅሩ ቀረጥ ባለመክፈል ሲባሉ፣ አዜብ
መስፍን 500 ሳተላይት ዲሾች ያለቀረጥ አስገብተው ቴሌ እያደሙ በየወሩ 20 ሚሊዮን ለሰባት አመት ሲመዘብሩ
የጠየቀ የለም። እጅግ አሳዛኝ ነው!
(በፎቶው ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ )

ዶክተር ፍቅሩ ማሩ የሞቱት ታካሚዎች ቁጥር 20 ደርሷል


አሉ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 30/2010)

በከፍተኛ ጥበቃ ስር ሆኜ የልብ ሕሙማንን እንዳክም ጠይቄ ስላልተፈቀደልኝ የሞቱት ታካሚዎች ቁጥር 20 ደርሷል ሲሉ
በእስር ላይ የሚገኙት ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ለፍርድ ቤት ገለጹ።
ከእስር ቤት ወደ ፍርድ ቤት በአቃቢ ሕግ ምስክር አለማቅረብ ምክንያት መመላለስ እንደመረራቸውም ታዋቂው የልብ
ሃኪም ዶክተር ፍቅሩ ማሩ በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በእስር ቤት እየደረሰባቸው ያለውን እንግልት
ተናግረዋል።
አቃቢ ሕግ ምስክር ማቅረብ ሲያቅተው በችሎት ውስጥ በሞባይል ጌም ይጫወታል።
እኔ ግን ከእስር ቤት ተመልሼ የምጫወተው ከትኋንና ከአይጥ ጋር ነው ይላሉ ከስውዲን መጥተው ኢትዮጵያውያንን
በማከም ላይ እያሉ ለእስር የተዳረጉት ዶክተር ፍቅሩ ማሩ።
በእስር ቤት ውስጥ ሰብአዊነት የሚባል ነገር የለም፣አቃቢ ሕግም እንደከብት እያስጎተተ ፍርድ ቤት በካቴና አስሮን
ከመጣን በኋላ ምስክር አላመጣልኝም እያለ እያጉላላን ነው ሲሉም የልብ ሃኪሙ ይናገራሉ።
ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ለፍርድ ቤቱ እንደገለጹት በከፍተኛ ጥበቃ ስር ሆነው የልብ ሕሙማንን ለማከም ጥያቄ አቅርበው
አልተፈቀደላቸውም።
በዚሁም ሳቢያ መዳን እየቻሉ ሃኪም አጥተው የሞቱት ታካሚዎ ቁጥር 20 ደርሷል ነው ያሉት።
ዶክተር ፍቅሩ እንደሚሉት አንድ ቀን ብቻ በ15ኛ ወንጀል ችሎት ዳኛ ተፈቅዶላቸው አንድ ሰው ብቻ ከፍተኛ ጥበቃ ስር
ሆነው ለማከም ችለዋል።
ከዚያ በኋላ ግን ሕሙማንን ለመርዳት እንዳልቻሉ ነው የተናገሩት።
ከታሰርኩ 4 አመት ከ8 ወር ሆኖኛል ያሉት ዶክተር ፍቅሩ አሁንስ መረረኝ ማርም ሲበዛ ይመራል ሲሉ ተናግረዋል።
አቃቢ ሕግ ምስክሮች አቀርባለሁ እያለ ባለማቅረቡ ከፍተኛ መጉላላት እንደደረሰባቸውም ነው የተናገሩት ።
እናም የምክክር ሂደቱ ታልፎ ብይን ይሰጥልኝ በሚል ለፍርድ ቤቱ በምሬት አቤቱታ አቅርበዋል።
ፍርድ ቤቱም ቀጠሮው የተያዘው ለጥር 3/2010 በመሆኑ በዚህ የመጨረሻ ቀጠሮ ብይን እሰጣለሁ ብሏል።

ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ለጠ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ


የላኩት ደብዳቤ

ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ለጠ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ የላኩት ደብዳቤ

~በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነ ሆስፒታል በአዲስ አበባ እንዲከፈት አድርጌያለሁ

~ሕክምናው እና መሳሪያው በኢትዮጵያ ውስጥ ባለመኖሩ ለዘመናት ለህልፈተ ሕይወት ይዳረጉ የነበሩ
ኢትዮጵያዊያን ዜጎች እድሉን በሃገራቸው እንዲያገኙ ሕይወታቸውን ለመታደግ ችያለሁ
~ በኢትዮጵያ ውስጥ በሙያው የሰለጠኑ አንድም ኢትዮጵያዊያን የልብ ሃኪሞች ስላልነበሩ ባለፉት 10 ዓመታት
ስድሰት ሐኪሞች ወደ ሲዊዲን በመላክ ልዩና ዘመናዊ የልብ ስፔሻላይዜሽን ሰልጥነው ወደ አገራቸው በመመለስ
ፈር ቀዳጅ የሆነውን ሕክምና በሃገራችን ውስጥ እንዲያከናውኑ ረድቻለሁ፡፡ እንዲሁም ቁጥራቸው ትንሽ የማይባል
ነገርሶችም ወደ ስዊድን ሄደው ልዩ ትምህርት አግኝተው በመምጣት እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
~ይህንኑ ልዩ የልብ ሕክምና ለማግኘት ወደ ውጭ የሚሄዱትን ኢትዮጵያውያን እዚሁ ሕክምናውን እንዲያገኙ
በማድረግ ሀገሪቱ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሪ ለማሰቀረት ተችሏል፡፡
~ በመታሰሬ በእኔ ተማምነው በየ 7 ዓመቱ የሚቀየር የልብ ማንቀሳቀሻ ባትሪ ሕክምና የወሰዱ ዜጎች ይህንን
የሚሰራ ሌላ ሃኪም በኢትዮጵያ ባለመኖሩ ብዙ ህሙማን ለሕልፈተ ህይወት ተዳርገዋል፤ እየተዳረጉም ነው፡፡
~በእኔ ሙያ ሊታከሙ የሚችሉ ኢትዮጵያውያን ተጎድተዋል፡፡
~ፈር ቀዳጅ የሆነው የልብ ሆስፒታል በብዙ ሚሊዮን ዶላር ሊስፋፋ የነበረው ባለበት ቆሟል፡፡
~ ከስዊድን በመምጣት የልብ ቀዶ ጥገና የሚያደርጉ ሀኪሞች እኔ በመታሰሬ መምጣት አቁመዋል፡፡

(ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች ደብዳቤው ላይ የሰፈሩ ናቸው። ሙሉ ደብዳቤውን ከስር ይመልከቱ)

ለክቡር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ

የ.ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር

አዲስ አበባ

ሀ. ጉዳዩ፡- ምን በድዬ ይሆን?

ክቡር ጠቅላይ ሚ/ር እኔ ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ የተባልኩትን ግለሰብ ከስሜ እና ከአንዳንድ ነገሮች ውጪ ብዙም ስለ
እኔ ያውቃሉ ብዬ ስለማልገምት ስለ ራሴ አጭር ገለፃ ሳደርግ በድፍረት ሳይሆን አክብሮት በተሞላበት ሁኔታ
መሆኑን በቅድሚያ ለመግለፅ አወዳለሁ፡፡

አመልካች በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ስዊድናዊ ስሆን በደርግ ጊዜ የነበረው የቀይ ሽብር ዘመቻ ሁለት
ወንድሞቼን አጥቼ እኔም ተሰድጄ በስዊድን ሃገር 43 አመታትን አስቆጥሬያለሁ፡፡

ክቡር ጠ/ሚኒስቴር ከ25 አመታት የስደት ኑሮ በኋላ ባለን የልብ ህክምና ሙያ ሃገሬን እና ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼን
ለማገልገል በመወሰን ከስዊድን መንግስት እና ስዊድናውያን ባለሃብቶች እንዲሁም ጥቂት ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ
ጋር በመሆን በአይነቱ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነ ሆስፒታል በአዲስ አበባ
እንዲከፈት በማድረግ ያከናወንኳቸው፡-

1ኛ. ሕክምናው እና መሳሪያው በኢትዮጵያ ውስጥ ባለመኖሩ ለዘመናት ለህልፈተ ሕይወት ይዳረጉ የነበሩ
ኢትዮጵያዊያን ዜጎች እድሉን በሃገራቸው እንዲያገኙ ሕይወታቸውን ለመታደግ ችያለሁ፡፡

2ኛ. በኢትዮጵያ ውስጥ በሙያው የሰለጠኑ አንድም ኢትዮጵያዊያን የልብ ሃኪሞች ስላልነበሩ ባለፉት 10 ዓመታት
ስድሰት ሐኪሞች ወደ ሲዊዲን በመላክ ልዩና ዘመናዊ የልብ ስፔሻላይዜሽን ሰልጥነው ወደ አገራቸው በመመለስ
ፈር ቀዳጅ የሆነውን ሕክምና በሃገራችን ውስጥ እንዲያከናውኑ ረድቻለሁ፡፡ እንዲሁም ቁጥራቸው ትንሽ የማይባል
ነገርሶችም ወደ ስዊድን ሄደው ልዩ ትምህርት አግኝተው በመምጣት እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

3ኛ፡ ይህንኑ ልዩ የልብ ሕክምና ለማግኘት ወደ ውጭ የሚሄዱትን ኢትዮጵያውያን እዚሁ ሕክምናውን እንዲያገኙ
በማድረግ ሀገሪቱ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሪ ለማሰቀረት ተችሏል፡፡
4ኛ፡ ወቅታዊ ለሆነው እና ታላቅ ሃገራዊ ፋይዳ ያለው የሕዳሴው ግድብ መሰረት ከተጣለ በኋላ በተከናወነው
የቦንድ ግዥ መሰባሰብ ሥራ የግሉን የጤና ዘርፍ ወክዬ ከዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ጋር በመሆን የብዙ ሚሊኒዬች
የቦንድ ግዥና እርዳታ እንዲፈፀም በማድረግና በተጨማሪም የግሌና በህክምና ሆስፒታሉም ስም ቦንድ በመግዛት
ሀገራዊ ግዴታዬን ተወጥቻለሁ፡፡

ወደ ጉዳዬ ስገባ :_

ለ. ባለፈው የፍርድ ሂደት፡

1. በግንቦት ወር 2005 ዓ.ም. ከቀድሞው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣኖች ጋር የጥቅም ግንኙነት


በማድረግ ክስ እንዲቋረጥ አድርገሃል ተብሎ ክስ ተመሰረተብኝ፤
2. ከ 3ዓመት የተጓተተ የፍርድ ሂደት በኋላ ምንም አይነት የሰነድም ሆነ የሰው ማስረጃ ሳይቀርብብኝ
በስሚ ስመሚ ብቻ ክሱን እንከላከል ተበየነ፤
3. ክረምቱ ካለፈ በኋላ በሚኖረው የፍርድ ቤት ሂደት በኋላ ክሴን ለመከላከል ስዘጋጅ በድንገት ነሀሴ 27
ቀን 2008ዓ.ም. ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተልኬ በዕለቱ የግራ ሳንባ መበላሸት (ኮላፕስ)
ስለደረሰብኝ የመጀመሪያውን የሳምባ ህክምና ተደረገልኝ፡፡
4• በተከታታይ የግራ ሳምባዬ እየተበላሸ በማስቸገረ ወደ ውጭ ሀገር ብቻ ሄጄ የቀዶ ጥገና ማድረግ እንዳለብኝ
አምስት የጥቁር አንበሳ ቦርድ ስፔሻሊስቶች በውሳኔ አረጋገጡ

5. በነበርኩበት ሁኔታ የፍ/ቤት ሂደቴን ልከታተል ባለመቻሌ ለለመከላል ስወስን፤ አፋጣኝ ፍትህ በማግኘት
ወደ ውጭ ሃገር ሄጄ ለመታከም በማሰብ ሲሆን በእርስዎ ድጋፍ እና ትብብር አፋጣኝ ፍርድ እንዳገኝ ተደርጎ፤
ችሎቱ በተኛሁበት ሆስፒታል ድርስ በመምጣት የ4 አመት ከ8 ወር እስራት ፍርድ መሰወኑ ተገልፀልኝ፡፡ ይህ ወሳኔ
ከታሰርኩበት ጊዜ ጀምሮ ስለሚቆጠር እንደምታ ተስፋ አድርጌ ስጠብቅ፤ ባልነበርኩበት እና ስብእናዬም ሆነ ሙያዬ
የማይመጥን በፈጠራ ላይ የተመሰረተ ሌላ ክስ ቀረበብኝ፡፡
6• በሽታዬ መታከም አለበለዚያ መሞት መርጫ ስለነበረ የስዊድን ሐኪሞች በመምጣት ከኢትዮጵያዊያን
ሐኪሞች ጋር በመሆነን ኦፕራሲዬን አድርገውልኝ ለጊዜው ሕይወቴ ሊድን ችሏል፡፡

7. የግራ ሳምባዬ ላይ የተከሰተው በሽታ ሳምባዬ ላይ ሊከሰት ስለሚችል የሚፈነዳ ቦምብ በሰውነቴ ይዤ
ህክምና በማላገኝበት ሁኔታ ላይ እገኛለሁ፡፡
8• የተፈረደብኝን ፍርድ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማለት ችሎቱም በተፋጠነ ሁኔታ መርምሮ ክሴን እና
ፍርዱን ውድቅ በማድረግ በነፃ አሰናብቶኛል፡፡

ሐ. የአሁኑስ ክስ የፍርድ ሂደት

በጥቅሉ ክሱ በሚለው በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በተሳው እረብሻ ቃጠሎ የ23 ታራሚ ህይወት እና ንብረት
ለመውደሙ ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ የገንዘብና የማስተባበር እርዳታ ግንቦት 7 ለተባለ “ሽብርተኛ” ቡድን በማድረግ
ተሳትፈዋል፤ አንቀፁ ቢያንስ 15 አመት ፅኑ እስራት አለበለዚያም ሞት ያስፈርዳል ይላል፡፡
1ኛ ምስክር ም/ሳጅን ———– የማረሚያ ቤቱ የዞን ሁለት ቤት ደልዳይና ተቆጣጣሪ ሲሆን፡

‹ዶ/ር ፍቅሩ በነገሩኝ መሰረት ለድሆች ልብስ መግዣ እና ለዋሰትና የሚሆን አራት ጊዜ በጠቅላላው ብር
176000.00 የምሳ ሳህን ስለማይፈተሸ (በሃሰት) አስገብቼ በቢሮ ውስጥ ሰጥቻለሁ፡፡ ገንዘቡም የተቀበልኩት
ከማላወቀው ሰው ነው ብሏል፡፡

የሚደንቀው ነገር ግን ይህ ማረሚያ ቤት አባል ሀገሩንና ህገ መንግስቱን ለማክበር ምሎ ሊያገለግል የነበረ፤ ይህንን
ይቅር የማይባል አንዴም ሳይሆን ለ4 ጊዜ እና (ለሌላም ተከሳሽ አስገብቻለሁ) ብሎ መስክሮአል፡፡ ሆኖም ይህን
እምነት አጉድሎ አሁንም ተመልሶ በማረሚያ ቤት ውስጥ ስራውን ቀጥሎ መገኘቱ ነው፡፡

2ኛ ምስክርም የማ/ቤቱ የሚገኝ በከባድ ነፍስ ማጥፋት ወንጀል የተከሰሰና ማስረጃ የተሰማበት የህግ ታራሚ
ሲሆን፡-

‹ ዶ/ርን አንድ ቀን የሆነ ሰው ሲያስተዋውቀኝ ደርሻህ ነው ብለው ገንዘብ ሰጡኝ፡ ከዚያ ቀጥሎ ነሀሴ 28 ቀን
2008ዓ.ም. የቃጠሎው ቀን ጠዋት ሌላ ገንዘብ ሰጡኝ› በገንዘቡ ግን ምንም ሳላደርግበት ተቃጠለ ብሏል፡፡ (እኔ
ነሀሴ 28 ቀን 2008ዓ.ም. በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተኝቼ በህክምና ላይ ነበርኩ፡፡)

3ኛ ምስክር፡-ከፍተኛ የክልል መንግስት የደህነነት ክፍላ ሃላፊና የገቢዎችም ዳይሬክተር የነበረ፤ አሁን በከፍተኛ
የሙስና ወንጀል የተከሰሰ ነው፡፡ በሰጠው ምስክርነት ‹ እኔና ዶ/ር ፍቅሩ አንተዋወቅም ታስረን የነበርነውም
በተለያየ ዞን ነው ። ነገር ግን እሳቸው የግንቦት ሰባት አባለትን በገንዘብ ይረዳሉ ሲባል ሰዎች ሲያወሩ ሰምቻለሁ፡፡”
ብሎ ነው የመሰከረው፡፡

4ኛ ምስክር፡- የፌዴራል ፖሊስ የነበረ በከፍተኛ ውንብድና የተከሰሰ ነው፡፡ በሰጠውም ምሰክርነት “አንድም ቀን
የኦነግ አባል በመሆን የተጠረጠሩና፤ የኦነግ አባል ነኝ ብሎ ያናገረኝ ታራሚ በማረሚያ ቤቱ ሜዳ ላይ በግልጽ
‹ታይኳንዶ› ሰሰለጥኑ ‹አይዞአችሁ› በርቱ ጊዜው ደርሷል ብከው ሲያበረታቱ ሰምቻለሁ፤ እንዲሁም አንድ
የአዕምሮ በሽተኛ ዱላ ይዞ ራቁቱን በመሆን ከ 1000 በላይ ለሚሆኑ ታራሚዎች እያባረረ በየክፍላቸው
ሲያስገባቸው እሳቸው ብቻ አጠገቡ ሄደው ‹ አይዞህ ንዳቸው› ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡ “ብሎ መስክሯል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር የሚገርመው እና የሚደንቀው አቃቤ ህግ በቃጠሎው ለምን እንዳልነበርኩ ሲያብራራ ‹
መድሃኒት ወስጄ አሞኛል ብዬ ወደ ሃኪም ቤት እሄዳለሁ እናንተ ቀጥሉ› ብሎአል ይላል፡ ሌላው አስገራሚ ነገር
ደግሞ በሁሉም ደረጃ ሲወራ የነበረው ‹ ዶ/ር ፍቅሩ የስኳር በሽተኛ ስለሆኑ ብዙ ቼኮሌት በመብላት ሳምባቸውን
አፍንድተው ነው ሆስፒታል የገቡት ተብሏል፡፡›ቢሆን እንኳ የቼኮሌት መድረሻ ጨጓራ እንጂ ሳምባ መሆኑን ሳይንስ
አላረጋገጠም፡፡ ምን አልባት መለኮታዊ ኃይል ይሆን?

መ. እኔ በመታሰሬ የደረሰ ጉዳት

1ኛ፡ በእኔ ተማምነው በየ 7 ዓመቱ የሚቀየር የልብ ማንቀሳቀሻ ባትሪ ሕክምና የወሰዱ ዜጎች ይህንን የሚሰራ ሌላ
ሃኪም በኢትዮጵያ ባለመኖሩ ብዙ ህሙማን ለሕልፈተ ህይወት ተዳርገዋል፤ እየተዳረጉም ነው፡፡
2ኛ. በእኔ ሙያ ሊታከሙ የሚችሉ ኢትዮጵያውያን ተጎድተዋል፡፡

3ኛ. ፈር ቀዳጅ የሆነው የልብ ሆስፒታል በብዙ ሚሊዮን ዶላር ሊስፋፋ የነበረው ባለበት ቆሟል፡፡

4ኛ. ከስዊድን በመምጣት የልብ ቀዶ ጥገና የሚያደርጉ ሀኪሞች እኔ በመታሰሬ መምጣት አቁመዋል፡፡

5ኛ. በመጀመሪያው የፈጠረራ ክስ ከ 4 ኣመት እስር እና እንግልት በኋላ ነፃ መሆኔ የእኔን፤ የቤተሰቤን እና የወዳጅ
ዘመዶቼን ቅስም በከባድ ሁኔታ የሰበረ እና ለከፍተኛ ጉዳትና እንግል የዳረገ ነው፡፡

6ኛ. እኔ በሐሰት እና ማስረጃ በሌለው ጉዳይ በተደጋጋሚ ክስ ሲቀርብብኝ እኔን ያዩ ዲያስፖራ ኢትዮጵያዊያን ወደ
ሃገራቸው ለመመለስ ከመጠራጠራቸውም አልፎ ለለመምጣት እስከመወሰን ይደርሳሉ፡፡

7ኛ. ሰዊድን እንደ ነጻ ሃገር ና የአውሮፓ ማህበር አባል በመሆኗ በስዊዲን ሲቀጥልም በአውሮፓ እና በኢትዮጵያ
ግንኙነት ላይ ተፅእኖ ሊያደርስ ይችላል፡፡

8ኛ. በየጊዜው በሐሰት ተከስሼ ከብዙ አመታት አስርና እንግልት በኋላ ነፃ መውጣት የፍትህ ስራአቱ በህዝብ ዘንድ
ያለውን ተአማኒነት በከፍተኛ ደረጃ ያሳጣል፡፡

ሠ. እኔ በመታሰሬ የተገኘ ወይም የሚገኝ ጥቅም ስላለመኖሩ፡

ኢትዮጵያ እንደ ሃገር፤ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ መንግስት በእኔ መታሰር ጉዳት እንጂ ምንም ጥቅም አላገኘም፡፡
ወደፊትም አይገኝም፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር፡- ማንም ሰው ከህግ በላይ እንዳልሆነና ካጠፋ በህግ ሂደቱ አፋጣኝ ፍትህ በማግኘት
ተመጣጣኝ እና አስተማሪ የሆነ ቅጣት መቀበል እንዳለበት ጠንቅቄ የማውቅ ነኝ፡፡ እርስዎም በፍትህ ስርአቱ ውስጥ
ጣልቃ ገብተው የእኔን ጉዳይ እንዲመለከቱም አይደለም፡፡ የኔ ዋና ጥያቄና ለብዙ አመታት አእምሮዬን በማስጨነቅ፤
ዘመድ ወዳጅን በማወያትና በመጠየቅ ለዚህ ሁሉ መከራና ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ምን ጥፋት አጥፍቼ እንደሆነ
ብፈልግ ምንም ነገር ባለማግኘቴ ለህሊናዬ ምላሽ ያጣ ጥያቄ በመሆኑ ምናልባት ባልዎት ሥልጣን እና ሃላፊነት
ለአንድ ሰው መቆርቆር ለሞላው ህዝብ መቆርቆር ነውና ለጥያቄዬ ምላሽ ያገኙልኛል በሚል ከፍተኛ እምነት ላይ
በመመስረት ነው፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር፡- ትናንት የሰራነው የዛሬ ታሪክ ነው፤ ዛሬ የምንሰራው የነገ ታሪክ ነውና የለብዎትን የጊዜ
መጣበብ ከግምት በማስገባት በሚያመችዎ መንገድ ምላሽ እንዲሰጡኝ በትህትና እና በአከብሮት አጠይቃለሁ፡፡

ከከበረ ሰላምታ ጋር

ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ
ከአ/አ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት

አሁንስ ፍትህ አገኝ ይሆን?

(ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ የላኩት ደብዳቤ)

~"ዐቃቤ ህግ ባቀረበው አቤቱታ ጉዳዩን የማየት እንኳን ምክንያት ሳይኖረው የሰበር ሰሚ ችሎት ያለምንም ክርክር “አብረው የተከሰሱት
ፍርድ ሳያገኙ ነፃ ማለት የማይቻል ነው” በማለት የከፍተኛው ፍርድ ቤትን ውሳኔ አፀናው፡፡ ይህ ለእኔ አሳዛኝ እና አስገራሚ ለህግ
ባለሙያዎች እፁብ ድንቅ በሚያሰኝ የሰበር ሰሚ ችሎትን ውሳኔ ለህሊና ፍርድና ለታሪክ እተወዋለሁ፡፡"

~"38 ተከሳሾች በፖሊስ ምርመራ ጊዜ ጥፍራቸው እየተነቃቀለ ጣታቸው እየተሰበረ በሚስማር እየተወገ በካቴና የተሰቀሉበት ጠባሳ
እንዳገኘ አረጋግጦ የኢፌድሪ የሰብአዊ መብት ኮሚቴ አጣርቶ መልስ ሰጥቷል።"

~ለምስክርነት የቀረቡት እስረኞችም በሃሰት እንዲመሰክሩ ከተከሳሾቹ በማያንስ የጭካኔ ቶርቸር እንዲሁም የማታለያ የትፈታላችሁ ቃል
ተገብቶላቸው እንደሆነ ምስክሮችን ጠይቆ መረዳት ይቻላል።" ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ

አሁንስ ፍትህ አገኝ ይሆን?

ለክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስተር

ከብዙ ወራቶች በፊት ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ ኃይላሪያም ደሳለኝ አፋጣኝ ፍትህ እንዲሰጡኝ የአቤቱታ ደብዳቤ አቅርቤ
እስካሁን መልስ ባለማግኘቴ ምናልባትም ከእርስዎ ላገኝ እችላለሁ የሚል ተስፋ አንግቤ ሌላ የማደርስበት አማራጭ መንገድ በማጣቴ
በዚህ አይነት መልክ ለማሳወቅ ተገድጃለሁ፡፡
ሀ. ስለ እኔ የክስ ጉዳዮች ዝርዝርና ጠለቅ ያለ ግንዛቤ እንዲያገኙ ለአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ያስተላለፍኩትን ደብዳቤ አባሪ አድርጌያለሁ፡፡
ለ. የጠቅላይ ሚኒስቴርነት ማእረግና ኃላፊነት ከወሰዱ ጥቂት ቀኖች መቆጠራቸው ግልፅ ነው፡፡ የተረከቡት የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ
ውስብስብ እና ከባድ፣ አንገብጋቢ እና አስቸኳይ መፍትሄ ማግኘት ያለባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ጠንቅቄ እገነዘባለሁ፡፡
ሐ. የእኔ የአንድ ግለሰብ ከሌሎች በሚሊዮን ከሚቆጠሩ ሰዎች ለእኔ ቅድሚያ እንዲሰጡኝ ሳይሆን የእኔ ጉዳይ የሚሊዮኖች የሚሊዮኖችም
ጉዳይ የእኔ ጉዳይባጭሩ የፍትህ ጉዳይ መሆኑን በማመን
መ. ላለፉት አምስት አመታት እኔ በእስር ቤት በማቆየት ከሃያ በላይ እኔን ተማምነው ሕክምና ያደረኩላቸው ኢትዮጵያውያን የልብ
ህሙማን ለህልፈተ ህይወት ተዳርገዋል፡፡ አሁንም መታማቸውና መሰቃየታቸው እየቀጠለ በመሆኑ የአንድ ኢትዮጵያዊ ህይወት ዋጋ
የማይወጣለት ክቡር ነገርና መዳን ከስቃይ መታደግ ቢቻልም አለማድረጉ ሰብአዊነት የጎደለው እንደሆነ አምናለሁ፡፡ እርስዎም ቢሆኑ
የእኔን አቋም እንደሚካፈሉ ጥርጣሬ የለኝም፡፡ ለመሪነትዎ ለተሸከሙት ኃላፊነት ድምር እሴት እና መርህ እንደሆነ ፅኑ እምነት አለኝ፡፡
ሠ. ባጭሩ ከላይ የጠቀስኳቸው ግብአቶች አፋጣኝ ፍትህ እና መፍትሄ ለመስጠት እንደሚስችሎት ተስፋ አለኝ፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር

የቤተሰቦቼ የጓደኞቼ እና የአያሌ የሚያውቁኝም የማያውቁኝም ሰዎች የእንቆቅልሽ መልስ ያልተገኘላቸው ጥያቄዎች እርስዎንም ለደቂቃም
ቢሆን እንዲያስቡ፣ እንዲጠይቁ ያደርግዎታል ብዬ ስላሰብኩ አጠር እና ጠቅለል ያለ ገለፃ ሳደርግ እንደድፍረት እንዳይቆጥሩብኝ አስቀድሜ
ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡
ከአምስት አመት በፊት በነ አቶ መላኩ ፈንታ መዝገብ ላይ በሙስና ወንጅ ተከስሼ የፍርድ ቤት ሂደቱ እየተጓተተ ከሶስት አመት በላይ
ካስቆጠረ በኋላ በደረሰብኝ አደገኛ በሽታ በህይወት መኖር ያለመኖሬ ከፍተኛ ጥያቄ በሆነበት ወቅት የከፍተኛው ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል
ችሎት በተኛሁበት ሆስፒታል ክፍል ድረስ መጥተው በመሰየም ያለምንም ማስረጃ በሰሚ ሰሚ እንደምስክርነት በመመርኮዝ የአራት
አመት ከስምንት ወር ፍርድ ተሰጠኝ፡፡
ከህመሜ አገግሜ ይግባኝ ጠይቄ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ክሱን የቀረበውን የምስክርነት “ማስረጃ” ከመረመረ በኋላ እንኳንስ ጥፋተኛ ብሎ
ሊያስፈርድ ይቅርና ለማስከሰስ እንኳን የማይችል በሚመስል መልክ ሙሉ በሙሉ ነፃ አደረገኝ፡፡
አቃቤ ህግ ባቀረበው አቤቱታ ጉዳዩን የማየት እንኳን ምክንያት ሳይኖረው የሰበር ሰሚ ችሎት ያለምንም ክርክር “አብረው የተከሰሱት
ፍርድ ሳያገኙ ነፃ ማለት የማይቻል ነው” በማለት የከፍተኛው ፍርድ ቤትን ውሳኔ አፀናው፡፡ ይህ ለእኔ አሳዛኝ እና አስገራሚ ለህግ
ባለሙያዎች እፁብ ድንቅ በሚያሰኝ የሰበር ሰሚ ችሎትን ውሳኔ ለህሊና ፍርድና ለታሪክ እተወዋለሁ፡፡
አሁን ደግሞ በሌለሁበት ማመን በማያስችል ሁኔታ “ገንዘብ ሰጥቶ የግንቦት 7 አባሎች በማደራጀት ማረሚያ ቤት አቃጥሏል” በሚል ክስ
ቀርቦብኝ የአቃቤ ህግ የምስክር ብይን በመጠባበቅ ላይ ነኝ፡፡
ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በጠየቀው መሰረት ቢያንስ ከ38 ተከሳሾች በፖሊስ ምርመራ ጊዜ ጥፍራቸው እየተነቃቀለ ጣታቸው
እየተሰበረ በሚስማር እየተወገ በካቴና የተሰቀሉበት ጠባሳ እንዳገኘ አረጋግጦ የኢፌድሪ የሰብአዊ መብት ኮሚቴ አጣርቶ መልስ ሰጥቷል፡፡
ለምስክርነት የቀረቡት እስረኞችም በሃሰት እንዲመሰክሩ ከተከሳሾቹ በማያንስ የጭካኔ ቶርቸር እንዲሁም የማታለያ የትፈታላችሁ ቃል
ተገብቶላቸው እንደሆነ ምስክሮችን ጠይቆ መረዳት ይቻላል፡፡
የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ያቀረበው ማረጋገጫ ግዙፍ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና የተዛባ የፍርድ ሂደት እንደሆነ ለትክክለኛ ፍትህ ክሱ
ተቋርጦ ተከሳሾች በነፃ መለቀቅ ይገባቸው ነበር፡፡ሆኖም….
ከላይ ያስቀመጥኩትን ካልኩ በኋላ ወደ እንቆቅልሽ ጥያቄዎች ስገባ እንዲህ አይነት በሃሰት በተቀነባበረ የውሸት ክስ ታስረው ዶ/ር ፍቅሩ
የሚሰቃዩት “እነኚህ ሰዎች ምን ፈልገው ነው? መሆኑ ምን አደረኳቸው? ከሳቸውስ የሚፈልጉት ነገር ይኖር ይሆን ወይ?”በሚል
ያብሰለስሉታል፡፡
በእኔ በኩል ግልፅ ላደርገው የምፈልገው የቀረኝን እድሜ በእስር ቤት ባሳልፍም ባለሁበት ሁኔታ ህይወቴ እዚሁ ቢያልፍም ስብእናዬን
የማይገልፅ የኑሮ መርህዬን የማይፈቅደውን ከእስር ቤት ለመውጣት ስል እንደማላደርገው ነው፡፡
እርስዎም ሆኑ ሌሎች በአፅኖት እንዲገነዘቡልኝ የምፈልገው በንግግርዎ እንደገለፁት እስካሁን የኖርኩትን ወደፊትም የምኖረው እንደ
ኢትዮጵያዊ ስሞትም እንደ ኢትዮጵያን ከገነቧት ወደፊትም ከሚያቆዩዋት እንደምደባለቅ ነው፡፡

ፍትህ ብልፅግናና ነፃነት

ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት

ከከበረ ሰላምታ ጋር

ፍቅሩ ማሩ

ከቂሊንጦ እስር ቤት

ግልባጭ:_

ሀ) ለስውይድን ጠቅላይ ሚኒስቴር


ለ) ለስውይድን ኤምባሲ
ሐ) ለኢፌዲሪ ፍትህ ሚኒስቴር
መ) ለፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
ሠ)ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን

You might also like