Professional Documents
Culture Documents
የኮሌራ በሽታ
የመከላከል እና
የመቆጣጠር
ኣጠቃላይ እቅድ
የጤና ማበልፀግና በሽታ መከላከል
መምሪያ
የመከላከያ ጤና ዋና መምርያ ስለ ኮሌራ በሽታ የመከላከል እና መቆጣጠር ኣጠቃላይ እቅድ
Table of Contents
የመከላከያ ጤና ዋና መምርያ የኮሌራ የመከላከል ዕቅድ.................................................................................... 2
ለ- ስለ ኮሌራ ወርርሽኝ ጤና ትምህርት በመስጠት ማህበረሰቡ የመከላከል ስራ ኣጠናክሮ እንዲሰራ ማነቃነቅ ..... 5
መግብያ
የኮሌራ በሽታ ቫይብሮ ኮሌራ በተባለ ኣንጀትን የሚያጠቃ ባክተርያ ይከሰታል፡፡ ኮሌራ ልጅ ኣዋቂ ሳይል ለሁሉም
የሚያጠቃ በሽታ ነው፡፡ የኮሌራ በሽታ የኣንድ ማህበረሰብ እድገት መመዘኛ የሆነ በሽታ ከመሆኑም በላይ ንፁህ
ውሃ እና የተሟላ ንፅህና (ሃይጅን) የሌላቸው ኣገሮች ዋነኛ ተግዳሮት ነው፡፡
የኮሌራ በሽታ ሊያባብሱ ከሚችሉት ነገርች የህዝቦች መፈናቀል፡ ስደት እና የእውቀት ማነስ ናቸው፡፡ ስለሆነም
በኣገራችን የተለያዩ ክልሎች ኣዲስ ኣበባን ጨምሮ በትግራይ፡ በኣማራ፡ በኦሮምያ እና በሱማሌ ክልሎች በወረርሽኝ
መልክ ተከስተዋል፡፡ ኣሁን ያለው ከዝናብ ወቅት መሆኑ ተያይዞ በሽታው ሊስፋፋበት የሚችልበት እድል ከፍተኛ
ነው፡፡
በትግራይ (14 በበሽታው የተጠረጠሩ ሰዎች ) በክልተ ኣውላዕሎ ወረዳ፡ በተምቤን እንዳባ ሃደራ ጸበል፡
በመቀሌ እና በኣዲግራት
በኣማራ ክልል ( 198 በበሽታው የተጠረጠሩ ሰዎች) ኣምስት ወረዳዎች (በዋግ ህምራ ዞን ኣበርገለ ወረዳ፡
ሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት፡ በየዳ እና ቋራ ወረዳዎች፡ በኣዊ ዞን ጉዋንጓ ወረዳ)
በኦሮምያ ክልል (225 በበሽታው የተጠረጠሩ ሰዎች) በምዕራብ ሃረርጌ ዞን ኣራት ወረዳዎች (ጭሮ፡ በደሳ
ከተማ፡ ኦዳ ቡሉተመ፡ እና ሜኤሶ ወረዳ) እንዲሁም በወለታ ከተማ
በኣዲስ ኣበባ (35 በበሽታው የተጠረጠሩ ሰዎች)) ከቦሌ ክፍለ ከተማ ውጭ በሁልም ክፍለ ከተሞች
በሱማሌ ክልል 33 ውሃማ ተቅማጥ የታየባቸው በግንቦት 9/2011 ታይተው ነበር፡ ከዛ በኃላ የታየ በሽተኛ
የለም
ባለንበት ወቅት ሰራዊታችን የተረጋጋ ኑሮ ለመምራት የሚቸገርበት ወቅት ነው ያለው፡፡ በከፍተኛ ደረጃ ከቦታ ቦታ
የሚንቀሳቀስበት ሁኔታ ተፈጥረዋል፡፡ ስለዚህ ለኮሌራ በሽታ የመጋለጥ እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ የዚህ እቅድ ኣለማም
የተቋማችን ማህበረሰብ ከወረርሽኑ በመከላከል የተሰጠውን ግዳጅ በኣግባቡ እንዲወጣ ማደረግ እና ወረርሽኑ
ሲከሰትም በቀላሉ መቆጣጠር እንድንችል ማድረግ ነው፡፡
የእቅዱ ኣላማ
ሰራዊታችንና እና የተቋማችን የማህበረሰብ ኣባላት ከኮሌራ ወረርሽኝ በመከላከል ሰራዊታችን የተሰጠውን ግዳጅ
በብቃት እንዲፈፅም ማስቻል
ዋና ዋና የእቅዱ ተግባራት
ሀ- በየደረጃው የኮሌራ ወረርሽኝ የመከላከል እና የመቆጣጠር ግብረ ሃይል እና ኮሚቴዎች በማቋቋም ስራ እና
ሃላፊነታቸውን ማስቀመጥ
መ- የህክምና ኣገልግሎት
ተጨማሪ የኢመርጀንሲ ድጋፍ ከጤና ጥበቃ ወይም ከተለያዩ ኣጋር ድርጅቶች በመጠየቅ ማቅረብ
የእዙ ወረርሽኝ ኮሚቴ በማቋቋም ሰራዊቱ ስለ ኮሌራ ወረርሽኝ ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማንቀሳቀስ፡
የሚያስፈልጉ ማተርያሎች ከሚመለከተው ኣካል መጠየቅ፡
የእዙ ፈጣን ግበረ መልስ ቡድን (Rapide Response Team) በማቋቋም ኮሚቴው ዝግጁነትን
ማረጋገጥ፡ ወረርሽኝ ሲከሰት ወረርሽኑ ወደ ኣጋጠመበት በኣፋጣኝ በማሰማራት በኣፋጣኝ እንዲቆጠጠር
ማድረግ፡፡
የቅኝት ስራ በማጠናከር፡ መረጃዎች በግዜ ትንታኔ በመስጠት ውሳኔ መስጠት፡ ወደ ላይ መላካቸውን
ማረጋገጥ
ወርረሽኙ የተከሰተባቸው ኣሃዱዎች በቦታ መለየት፡ እንቅስቃሰያቸው የተወሰነ እንዲሆን በማድረግ
የሚያሰፈልግ ማተርያል እንዲቀርብ ማደረግ
ለኢመርጀንሲ የሚላኩ ማተርያሎች በኣግባቡ ማስተዳደር
ወርርሽኝ ሲያጋጥም ያለውን የሰው ሃይል ተጠቅሞ ምርመራ ማድረግ፡፡ ጉብኝት ማድረግ፡፡
ወረርሽኝ ሲያጋጥም በየቀኑ ለበላይ ኣካል፡ የተከናወኑ ተግባራት፡ ያጋጠሙ የበሽተኞች ቁጥር እና የሞት
ቁጥር ሪፖርት ማድረግ
በየገዜው የሚያሰፈልግ ማተርያል እና ኣቅረቦት እየገመገመ የጎደለውን ማሟላት
የኮሌራ የህክምና ማዕከል መለየት
ከክልሎች ተቆራኝቶ የመስራት ግንኙነት መፍጠር
የውሃ ማከምያ መድሃኒቶች ማለትም እንደ ሰራዊቱ በግሉ እና በቡድን ለውሃ ማከምያ የሚጠቀምባቸው
መድሃኒቶች በቀን በሳምንት፡ በወር እና በሰው ሃይል ተሰልቶ መጠየቅና ማሰራጨት
የማከምያ መድሃኒቶች እንደ ቴትራ ሳይክሊን፡ ዶክሲ ሳይክሊን ኦኣር ኤስ እና በደም ስራ የሚሰጡ ፈሳሾች
የኮሌራ ማንዋል በሚያዘው መሰረት ተሰልቶ መጠየቅ፡፡ ይህ ሰራዊቱ ባለበት ወርርሽኑ የገባባቸው
ወረዳዎች ያለውን የታማሚዎች ፕሪቫለንስ በመወሰድ ማስላት ይቻላል፡፡
የኮሌራ ማከምያ ማእከል ለማቋቋም ኣስገዳጅ በሚሆንባቸው ክፍሎች ማእከሉን ለማቋቋም
የሚያሰፍልግ ማተርያል እና የሰው ሃይል ማዘጋጀት፡፡
እንደ ፖስተሮች፡ በራሪ ጽሁፎች የመሳሰሉ የመከላከል ግብኣቶች በማዘጋጀት ወይም ከሚመለከታቸው
ኣካላት በመጠየቅ ማሰራጨት
የሪፖርት ፎረማቶች፡ መመርያዎች እና የህክምና ፕሮቶኮሎች ማሰባሰብ እና ማሰራጨት
ኣስቀድመው ማወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡ እስከ ኣሁን በኣዲስ ኣበባ በጦር ሓይሎች ኮምፕረሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ
ሆስፒታል ኣንድ የኮሌራ የህክምና ማእከል ለማቋቋም በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
እዞች እንደ በሽታው ስጋት ከክልሎች በመረዳዳት ኣስፋላጊ ሁኖ ሲገኝ በካምፖች የኮሌራ የህክምና ማእከል
ማቋቋም አለባቸው፡፡ ለዚህ የሚያስፍልግ የሰው ሃይል እና ማተርያል በማንዋል መሰረት ማዘጋጀት፡፡ ለቅደመ
ዝግጅት እና ጥንቃቄ የሚያስፈልግ የወትሮ ዝግጁነት ስለሚያስፈልግ ለዚህም የሚያስፈልግ ማተርያል እና
የህክምና መድሃኒቶች በኮሌራ ማንዋል መሰረት ማዘጋጀት፡፡ የኦኣርስ እና የሪንገር እንዴት መጠቀየቅ እና ማዘጋጀት
እንዳለባቸው በሰንጠረዥ ኣንድ በምሳሌ ተቀምጠዋል፡፡
ሊያጋጥሙ በከፍተኛ
የተገልጋይ የሚቸል የኮሌራ ደረጃ
ክፍል ብዛት በሽተኞች የተጠቁ ORS Ringer
A B C D E F
C*Sever
XX OOO B*AR Rate C*6.5 D*6
ማእበል 6000 12 2.4 78 14.4
ኣዋሽ 870 1.74 0.348 11.31 2.088
ደንበል 2500 5 1 32.5 6
ቁጥጥር እና ግምገማ
ሁሉም ክፍሎች ከታች ወደ ላይ በየቀኑ ሪፖርት ማድረግ ግዴታ ኣለባቸው፡፡ ሪፖርት በስልክ፡ በቴክስት
መልእክት፡ ወይም በሬድዪ ሁኖ የቀኑ የታዩ በሽተኞች ብዛት በሽተኛ ካልታየም ኮሌራ ዜሮ ብለው ሪፖርት
ማደረግ፡፡
ወረርሽኑ ለመከላከል የተከናወኑ ተግባራት፡ ያጋጠሙ ተግዳረቶች እና እንዴት እንደተፈቱ እንዲሁም
ያልተፈቱ ችግሮች በሳምንት ሪፖርት ይደረጋሉ፡፡
የጤና ዋና መምርያ የሚቋቋመው ግበረ ሃይል በወር ኣንድ ግዜ ይሰበሰባል፡፡ የተቀመጡ ኣቅጣጫዎች እና
ተፈፃሚነታቸው በዝርዝር በማየት ውሳኔ ያስተላልፋል
የዕዝ የኮሌራ መከላከል ግበረ ሃይል በየሁለት ሳምንት ይሰበሰባል፡፡ የተሰሩት ስራዎች ይገምግማል፡፡
ኣቅጣጫዎች ያስቀምጣል፡፡
እላይ የተጠቀሱ ዋና ዋና ተግባራት በዕዝና ተመጣጣኝ ክፍሎች በእቅድ እየተመሩ በተዋረድ እስከ ታች
ክፍሎች ተግባራዊ መሆናቸውን ማረጋገጥ