You are on page 1of 1

።።።የልጅነት መጫወቻ ኳሶች የፍብረካ ትዝታ!

።።።

ሠላም ወገኖቼ! በማህበራዊ መገናኛ መድረክ ፅንሰ ሃሳብ ላይ ያተኮሩ ለጠፎቼ ወደ ትዝታ እንድመለከት ያስገደደኝ
የወዳጄ የእፁብ አለማየሁ የሶስት ተከታታይ ክፍል የራስዘስላሴ ት/ቤት የትዝታ ለጠፍ ነው።ምስጋና ለወንድሜ እፁብና
ለንባብ ቤተሰቡ። የልጅነት የትዝታ ዶሴ የበዛ ቀለምና ይዘት ያዘሉ ደማቅ ትውስታዎች ቢያስመለክተኝም በልጅነታችን
እንደ ልብ ያለገደብ ኳስ የተጫወትንባቸው ሜዳዎች ትዝታን ለወዳጄ እፁብ በመተው በሜዳዎቹ የነገሱ የመጫወቻ
ኳሶቻችን እዳስሳለሁ። ተከተሉኝ።

ያኔ በደጉ ዘመን ጫማ ለመጫማት አቅም የነበራቸው ወላጆችን ያገለገሉ ካልሲዎች ለእኛ ለልጆች በኳስ መስሪያነት
የማገልገል ክፍል ሁለት የግልጋሎት ምእራፍ ነበራቸው። ከዘመነ ግዢያቸው በግልጋሎት የሰፉ፣ ረጃጅምና ጠንካራ
ካልሲዎች ሆዳቸውን በጨርቅ፣ በፀጉርና መሰል ቁስ ሞልቶ በክብ የኳስ ቅርስ ማበጃጀት ገራሚ ትውስታ ነው። ሆዱ
የታጨቀ ካልሲን አጣጥፎ በክር መስፋት እንዴት ይዘነጋል። ይበልጥ ለማስዋብ የኮርኪ ልጣጭ በተፈበረከው የካልሲ ኳስ
አራርቆ የሰፋ ውበቷን ማስታወስ መች ይሳነዋል? በእነዚ ኳሶች የኳስ ኩኩ፣ ጥምጣም፣ ዲሞር፣ ምት ምትና መደበኛ
ግጥሚያ የተጫወተ ደስታው ቢከተለው አያስገርምም። አቤት ጨዋታ! አቤት ደስታ!። ያኔ በልጅነት ተንኮል የተለማመዱ
ታዳጊዎች በካልሲው ውስጥ ክብ ድንጋይ ከተው ለመንገደኛ ምታው አቀብለኝ በማለት በንረታ አውራ ጣቱን አንድደው
የሚስቁና የሚደሰቱ ታዳጊያን ሲያስታውስ ፈገግ ለማለት ማን ይቸገራል?።

ከኳስ ፍብረካ ጥበባችን የፌስታል ኳስ ሌላኛው ነበር። ፌስታል እንደዛሬ ቆሻሻ ብቻ አልነበረም ኳስ መፈብረኪያና
መጫወቻም ጭምር እንጂ። በመመሳሰል መንትያው የነበረው በወፍቾ (ኮባ) በጥልፍልፍ የሚፈበረከውን ኳስ መዘንጋት
እንዴት ይቻላል?።

እነኚህ የኳስ ፍብረካዎች ሇላቀር ያደረገች ከአፉፋ ወፈር ብላ በኳስነት ገብያውን በተቀላቀለች ጊዜ ሳንቲም አዋጥቶ የገዛ
ስንቱ ነው። ይህች ኳስ ከፊፍ በመሆኗ እርካታ አጠር ነበረች። እሷን ተከትሎ በውፍረት ተሻሽሎ ከመነዳሪ አልባ ሆኖ
በተከሰተው የፕላስቲክ ኳስ ተራግጠን ያጠራቀምነው ደስታ ዛሬም ይከተለናል። ከዛስ ባለካርታው ኳስ ስፌቱ ሲለቅ በጎማ
ክር ጠግኖ፣ ከመነዳሪው ሲቀደድ በቀዶ ጥገና ለጥፎ ያለገደብ ተጫውቶ ላለፈ ትዝታው እድሜ ዘመኑን ቢከተለው ማን
ይፈርድበታል? ማንም። አበቃሁ።

#መ.ጀማል (ለመኖር ትግሉ)

ዕለተ:—ዕሁድ፣ ጥቅምት:—22/2012 E.C

You might also like