You are on page 1of 12

የፌዯራሌ የከተሞች የስራ ዕዴሌ ፈጠራና ምግብ ዋስትና

ኤጀንሲ

ገበያ ጥናት ዲይሬክቶሬት

የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በሚወጡ ጨረታዎች ተሳታፊና


ተጠቃሚ እንዱሆኑ ግንዛቤ ሇመፍጠር የተዘጋጀ መጣጥፍ

ሰኔ/2011ዓ.ም

አዱስ አበባ

-0-
1. መግቢያ

መንግስት ሇጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ትኩረት በመስጠት የዘርፉን ሌማት ሇማስፋፋትና


ሇማጠናከር የተሇያዩ ዴጋፎች ሲሰጥ ቆይቷሌ፡፡ ከሚሰጡ ዴጋፎችም መካከሌ በጥቃቅንና አነስተኛ
ኢንተርፕራይዞች ሌማት ዘርፍ ሇተሰማሩ አንቀሳቃሾች የሚያመርቱትን ምርትና የሚሰጡትን
አገሌግልት በማስተዋወቅ የገበያ ትስስር እንዱፈጠርሊቸው በማዴረግ ገቢያቸው እንዱሻሻሌና
በውስጣቸው የስራ እዴሌ እንዱፈጥሩ ሇማዴረግ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራት ሊይ ይገኛሌ፡፡

ስሇሆነም በዘርፉ የተሰማሩ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ያሊቸው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ


ፋይዲ ከፍተኛ በመሆኑ ምክንያት የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር በ2002 ዓ.ም የፌዯራሌ መንግስት
የግዥ አፈጻጸም መመሪያ አሻሽል በማውጣት ሇኢንተርፕራይዞች ሌዩ አስተያየት በማዴረግ
ኢንተርፕራይዞችን በየዯረጃው ዴጋፍና ክትትሌ በማዴረግ በተሰራው ስራ ባሇፉት ዓመታት ቀሊሌ
የማይባለ ኢንተርፕራይዞች ተጠቃሚ መሆን ችሇዋሌ፡፡ ሆኖም ግን በሚወጡ ጨረታዎች ሊይ
ኢንተርፕራይዞችን ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዱሆኑ ሇማዴረግ በሚሰራው ስራ ኢንተርፕራይዞች የግንዛቤ
ክፍተት የሚታይባቸው በመሆኑ በሚፈሇገው ዯረጃ ያህሌ ተጠቃሚ እየሆኑ አይዯሇም፡፡ በመሆኑም
በጨረታ ሂዯት ያሇባቸውን የግንዛቤ ክፍተት በመሙሊት የኢንተርፕራይዞችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት
ሇማሳዯግ ይቻሌ ዘንዴ ይህ መጣጥፍ ተዘጋጅቷሌ፡፡

2. የጨረታ ምንነት

ጨረታ ማሇት የግዥ ወይም የንብረት ሽያጭ ማስታወቅያ ይፋ ከሆነበት ወይም ጥሪ ከተዯረገበት ጊዜ
ጀምሮ አሸናፋ ተሇይቶ ውሌ እስኪፈርም ዴረስ ያሇውን የግዥ አፈፃፀም ወይም የንብረት ሽያጭ ሂዯት
ነው፡፡

3. የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በጨረታ ሂዯት የሚታይባቸው ችግሮች


 በጨረታ የሚሳተፉ ኢንተርፕራይዞች ሇጨረታው ብቁ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ በወቅቱና
በተሟሊ ሁኔታ ማቅረብ ወይም የቅዴመ ብቃት መገምገሚያ መመዘኛዎችን አሟሌቶ አሇመገኘት፤
 የተጫረቱበትን ስራ ሇማከናወን የሚያስችሌ ሙያዊ፣ቴክኒካሌ ብቃትና ሌምዴ ማነስ፣
 አስተማማኝ የገንዘብ ምንጭና በቂ የሰው ሀይሌ ሳይኖር ወዯ ጨረታ በመግባት ስራውን በውለ
መሰረት በወቅቱና በጥራት ማዴረስ አሇመቻሌ፣
 በመንግስት ግዥ ሇመሳተፍ በፌዯራሌ የመንግስት የግዥ ንብረት አስተዲዯር ኤጀንሲ የተዘጋጀውን
የአቅራቢዎች ምዝገባ ዴረ-ገፅ አሇማወቅና አሇመመዝገብ፣

-1-
 በመንግስት ግዥ መመሪያ በኩሌ የሚዯረጉ የጨረታ ሌዩ አስተያየቶችን ሇላሊ 3ተኛ ወገን አሳሌፎ
መስጠት፣

 የጨረታ መረጃዎችን ከተሇያዩ ምንጮች በራሳቸው ተነሳሽነት አሇመፈሇግ ወይም ከመንግስት ብቻ


መረጃው እንዱሰጣቸው መጠበቅ፣
 ከጨረታ ተወዲዲሪዎች ጋር ዋጋ ተስማምቶ ወይም በራሱ ዝቅተኛ ዋጋ ሇማቅረብ መሞከር /ዋጋ
ሰብሮ መግባት/፣
 ወቅታዊ የገበያ መረጃን ያሊማከሇ የመጫረቻ ዋጋን ማቅረብ፣
 በጨረታ ሰነዴ አሞሊሌ ሊይ ያሊቸው ግንዛቤ አናሳ መሆኑ፣

4. የፌዯራሌ መንግስት የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ሊይ ተጫራች ኢንተርፕራይዞች


ማሟሊት የሚገባቸው ቅዴመ ሁኔታዎች

የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በመንግስት ግዥዎች ሇመሳተፍ የአፈጻጸም መመሪያው ሊይ


የተቀመጡ ቅዴመ ሁኔታዎችን ማሟሊት እንዱችለ ሇግንዛቤ እንዱሆን ከመመሪያው የተወሰደ ነጥቦች
እንዯሚከተሇው ቀርቧሌ፡፡

የተጫራቾች ብቃት
በመንግስት ግዥ ውስጥ ሇመሳተፍ ተጫራቾች(ኢንተርፕራይዞች) ብቁ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ
ማቅረብ አሇባቸው፡፡ የተጫራቾችን ብቃት የማጣራት ዓሊማ የሚከተለት ሁኔታዎች መሟሊታቸውን
ማረጋገጥ ነው፡፡
በመንግስት ግዥ ውስጥ የሚሳተፉ ተጫራቾች ኢንተርፕራይዞች በአዋጅና በመመሪያው ውስጥ
የሰፈሩትን የህጋዊነት የሙያ እና የስነ ምግባር መመዘኛዎች ወይም ዯረጃዎች ማሟሊት
ይኖርባቸዋሌ፡፡
ተጫራቾች የተወዲዯሩበትን ጨረታ ወይም አገሌግልቶች በአግባቡ ማከናወን የሚችለ መሆን
አሇባቸው፡፡

ተጫራቾች ሙያዊና ቴክኒካዊ ችልታ እንዲሊቸው ሇማሳየት የሚከተለትን ማስረጃዎችና ማረጋገጫዎች


ማቅረብ ይጠበቅባቸዋሌ፡፡
 የተጫረቱበትን የግንባታ ዘርፍ ስራ፣ አቅርቦትና አገሌግልት ሇማከናወን የሚያስችሌ
ሙያዊ፣ቴክኒካዊ ብቃት እና ከዚህ በፊት ያሊቸው የስራ ሌምዴ
 አስተማማኝ የገንዘብ ምንጭ

-2-
 ተስማሚ የስራ መሳሪያዎች ላልች አስፈሊጊ ነገሮችን ወይም እነኝህን መሳሪያዎችና አስፈሊጊ
ነገሮች እንዯአስፈሊጊነቱ ሇሚፈሇገው ጊዜ በኪራይ ሇማግኘት መቻሊቸው
 አስፈሊጊ ሆኖ ሲገኝ የማምረት ችልታ
 ተጫራቾች ከአሁን በፊት ካከናወኑት ተግባር ጋር ተያያዥነት ያሇው መሌካም የኮንትራት
አፈፃፀም እና ጥሩ ዝና ያሊቸው ሇመሆኑ የሶስተኛ ወገን ማረጋገጫ ማቅረብ
 በቅጥርም በችልታም ውለን ሇማከናወን የሚያስፈሌገውን የሰው ሀይሌ ሇማሟሊታቸው
ማረጋገጫ ማቅረብ

ተጫራቾች ውሌ ሇመፈፀም የሚያስችሌ ህጋዊ ችልታ እንዲሊቸው ማሳየት አሇባቸው፡፡ ይህ ማሇት


ምንም ዓይነት የፍርዴ ቤት ዕገዲ የላሇባቸው መሆኑን ሇመንግስት መስሪያ ቤቱ ማሳየት አሇባቸው፡፡

ሀገር በቀሌ ተጫራቾች በሀገሪቱ ህግና መመሪያ መሰረት ግብር የከፈለ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ
የግብር ምዝገባ ቁጥር ወይም የግብር ከፋዩን የመሇያ ቁጥር፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ
ቁጥር፣የገቢ ግብር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የተወሰነበት የመጨረሻ ዓመት፣ ግብር እና የተጨማሪ
እሴት ታክስ በወቅቱ የተከፈሇ መሆኑን የሚያሳይ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋሌ፡፡

ሁለም አመሌካቾች የቅዴመ ብቃት መገምገሚያ መመዘኛዎችን ማሟሊት ካሌቻለ የጨረታ ውዴዴሩ
ይሰረዛሌ፡፡

ማናቸውም ተጫራች ብቃት ያሇው መሆኑን ሇማረጋገጥ ያቀረበው መረጃ የተዛባ ወይም ያሌተሟሊ
ከሆነ ተጫራቹን በማንኛውም ጊዜ የመንግስት መስሪያ ቤቱ ከውዴዴር ውጪ ሉያዯርገው ይችሊሌ፡፡
ተጫራቹ ከውዴዴር ውጪ የተዯረገበት ምክንያት በቅዴመ ብቃት ወይም በጨረታ ግምገማው ሪፖርት
ውስጥ በግሌፅ ሉቀመጥ ይገባሌ፡፡ ተጫራቹ ተመሳሳይ ዴርጊት በተዯጋጋሚ ፈጽሞ ከተገኘ
በተወዲዲረበት ጨረታና ሇወዯፊቱ የመንግስት መስሪያ ቤቱ በሚያወጣው ጨረታ ተሳታፊ ሆኖ ሲገኝ
በዴርጊቱ ምክንያት ከውዴዴር ውጭ ሉያዯርግ ይችሊሌ፡፡

የቅዴመ ብቃት ሠነድች


ቅዴመ ብቃት ሰነዴ ማሇት ብቃትና አቅም ያሊቸው ተጫራቾች እንዱሳተፉ ሇመሳብ የሚጠቅም ዘዳ
ሲሆን የመንግስት መ/ቤቱ ሇወዯፊቱ ሇሚያካሂዯው ጨረታ የሚያሳትፉ ብቃት ያሊቸውን ተጫራቾች
ሇመሇየት የሚጠቀሙበት ሰነዴ ነው፡፡ የቅዴመ ብቃት ሰነዴ ቢያንስ የሚከተለትን ነጥቦች ያካትታሌ፡-
በግዥው ሂዯት ውጤት ምክንያት በውለ ውስጥ የሚካተቱ ዋና ዋና ሁኔታዎች ሇምሳላ
የሚጠቀሙበት መሰረታዊ የግዥ ሠነድች፣የጨረታ ሰነዴ መሇያ፣መጠንና የምርት መሇኪያ፣
የገንዘብ ምንጭ፣ህጋዊነት፣የብቃት መመዘኛ መስፈርት፣የተሇየ ዕቃ መሳሪያ አስፈሊጊነትና፣
የጨረታው ጥሪ የሚዯረግበት ጊዜ፣የማጠናቀቂያ ጊዜን በመንግስት መ/ቤቱ የተመረጠውን

-3-
ንዑስ ተቋራጭ አካቶ የስራውን ወሰን የሚገሌፅ ዝርዝር መግሇጫ ጨምሮ የመ/ቤቱን የተሇየ
የስራ ሁኔታ፣
የመንግስት መ/ቤቱ ጨረታዎችን በሙለ ወይም በከፊሌ የመሰረዝ ስሌጣን እንዲሇው የሚገሌፅ
ዓረፍተ ነገር፣
የመገበያያ ገንዘብና የአከፋፈለ ስሌት ወይም ዘዳ፣
የአቅራቢዎች ወይም የተቋራጮች ዜግነት ግምት ውስጥ ሳይገባ ሉሳተፉ እንዯሚችለ ወይም
ሉሳተፉ የሚችለት የተወሰኑ ሀገር ዜጎች ብቻ መሆናቸውን የሚገሌፅና የማይሇወጥ መግሇጫ፣
ቅዴመ ብቃት ማመሌከቻዎች አዘገጃጅትና አቀራረብ መመሪያዎች፣
ግዥውን ሇመፈፀም ብቃት ያሊቸው መሆኑን ሇማሳየት አመሌካቾች ማቅረብ ያሇባቸውን
በአዋጁና በመመሪያው ሊይ የተገሇፁ ማስረጃዎችና ላልች ዯጋፊ መረጃዎች፣
የቅዴመ ብቃት ማመሌከቻዎች የሚቀርቡበት ሁኔታ፣የማቅረቢያው ቦታና የማስረከቢያው
የመጨረሻ ቀን፤

ተወዲዲሪ ተጫራቾች ሇዕቃዎች ወይም የግንባታ ዘርፍ ስራዎች የጨረታ ማቅረቢያውን በአግባቡ
ማዘጋጀት እንዱችለ አስፈሊጊ የሆኑ መረጃዎች በሙለ በጨረታው ሰነዴ ውስጥ መገሇፅ አሇበት፡፡
የጨረታ ሰነዴ የሚከተለትን ነጥቦች ማካተት አሇበት፡፡

የጨረታ ሰነደን ሇማዘጋጀትና ሇማቅረብ አስፈሊጊ የሆኑ መመሪያዎችን፣


የጨረታ ሰነደ ማስረከቢያ ቀን፣ሰዓትና ቦታ እንዱሁም የተጫራቾች ወኪልች በጨረታው
የመክፈቻ ስነ ስርዓት ሊይ ሉገኙ የሚችለ መሆኑን የሚገሌፅ መረጃ፣
የሚያስፈሌግ ሆኖ ሲገኝ የጨረታ ማስከበሪያ፣የውሌ ማስከበሪያና የአምራቾች የውክሌና ስሌጣን
የሚያሳይ የጨረታ ማቅረቢያ የናሙና ቅጾች፣
ከዋናው የጨረታ ሰነዴ ጋር መቅረብ ያሇባቸውን ተጨማሪ ኮፒዎች(ቅጾች)፣
አጠቃሊይ ሌዩ የውሌ ሁኔታዎች፣
እንዯ አግባብነቱ ዕቃውን ሇማቅረብ ወይም ስራውን ሇማጠናቀቅ ይወስዲሌ ተብል የሚገመተውን
የጊዜ ገዯብ ጨምሮ ተፈሊጊውን የዕቃና የአገሌግልት ዝርዝር፣
ተጫራቹ በጨረታው ሇመሳተፍ ብቃት ያሇው መሆኑን ሇማረጋገጥ የሚያቀርባቸውን መረጃዎች
ዓይነት እንዱሁም የፋይናንስ አቋሙን እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ መሆኑን
ሇማረጋገጥ ማቅረብ ያሇበትን መረጃ፣
ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ፣
ጨረታውን ሇመገምገምና የጨረታውን አሸናፊ ሇማሳወቅ ታሳቢ ሉሆኑ የሚገቡ መስፈርቶች
የሚገመገሙበት ሁኔታ፣

-4-
ተጫራቹ ማጭበርበር፣ ሙስና ፣ማታሇሌና የማስገዯዴ ዴርጊት የማይፈፅም መሆኑን
ሇማረጋገጥ ግዳታ ሇመግባት ከጨረታ ሰነደ ጋር ተያይዞ የሚገኘውን ቅፅ መፈረም አሇበት፣
ግዥ የሚፈፅመው መ/ቤት የጨረታው አሸናፊ ይፋ ከመዯረጉ በፊት በማናቸውም ጊዜ
ጨረታውን የመሰረዝ መብት ያሇው መሆኑን፣
አግባብነት ሲኖረው የጨረታ ሰነደን ሁኔታ በሚመሇከት ማብራሪያ ሇመስጠት ከተወዲዲሪ
ተጫራቾች ጋር ቅዴመ ጨረታ ስብሰባ ማዴረግ፣
ተጫራቾች ቅሬታ ማቅረብ ከፈሇጉ ሉከተለት የሚገባውን የቅሬታ አቀራረብ ሂዯት በጨረታ
መረጃ ሰነደ ማሳወቅ፤

የጨረታ ሰነድች በሚዘጋጁበት ጊዜ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መመሪያዎች ማክበር አሇባቸው፡፡ የጨረታ
ሰነድች ነፃ ውዴዴርን እንዱፈቅደና እንዯሚያበረታቱ ከመጥቀስ በተጨማሪ የሚከተለትን በግሌፅ
ማሳወቅ አሇባቸው፡፡

 ሉሰራ የሚገባውን ስራ  ዝቅተኛው የአፈጻፀም


 ስራው የሚገኝበት ቦታ መስፈርቶች
 የሚቀርቡ ዕቃዎች  የዋስትና ማረጋገጫና የጥገና
 የማስረከቢያ ወይም መስፈርቶች
የመገጣጠሚያ ቦታ  ላልች ተገቢ ሁኔታዎች
 የማስረከቢያና የማጠናቀቂያ
መርሀ-ግብር
ተቀባይነት ባገኘ አቅራቢዎች ዝርዝር መጠቀም

የአቅራቢዎች ምዝገባ፡-

 በመንግስት ግዥ መሳተፍ የሚፈሌጉ ኢንተርፕራይዞች በፌዯራሌ የመንግስት የግዥ ንብረት


አስተዲዯር ኤጀንሲው ዴረ-ገፅ (www.ppa.gov.et) በተሇይ ሇአቅራቢዎች ምዝገባ በተዘጋጀው
ክፍሌ በቅዴሚያ ራሳቸውን መመዝገብ ይኖርባቸዋሌ፡፡

በአቅራቢነት ሇመመዝገብ መሟሊት ያሇባቸው ሁኔታዎች፡-

አቅራቢው የተሰማራበትን የስራ ዘርፍ የሚገሌፅ የታዯሰ ንግዴ ፈቃዴ.


በምክር አገሌግልት በመስጠት ስራ ሊይ የተሰማራ አቅራቢ ከሆነ ስሇተሰማራበት የሙያ ዘርፍ
በሚመሇከተው አካሌ የተሰጠ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ፣
በግንባታ ስራ ሊይ የተሰማራ ከሆነ የስራ ተቋራጭነት ስራ እንዱሰራ ከከተማ ሌማትና
ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተሰጠውን ዯረጃ የሚገሌፅ ማስረጃ፣

-5-
የተሽከርካሪ ጥገና አገሌግልት በመስጠት ስራ ሊይ የተሰማራ ከሆነ ከትራንስፖርት ሚኒስቴር
የተሰጠ ዯረጃን የሚገሌፅ ማስረጃ፣
መዴሀኒት እና የህክምና መገሌገያ መሳሪያዎችን በማቅረብ የተሰማራ ከሆነ ከምግብ፣መዴሀኒትና
ጤና እንክብካቤ አስተዲዯርና ቁጥጥር ባሇስሌጣን የተሰጠውን ማስረጃ፤

የጨረታ ዋጋ የሚከተለትን ማካተት አሇበት፡-

የጨረታው ጥሪ የጨረታው ዋጋ ተያያዥ የሆኑ በተጫራቹ ሉከናወኑ የሚገባውን ነገሮች


ሇምሳላ ትራንስፖርት፣ መዴን፣ ስሌጠና፣ የተሇዩ መሳሪያዎች፣ ማኑዋልች፣ ወ.ዘ.ተ ጨምሮ
ዕቃዎችን የማስረከቢያ ቦታው ሊይ ሇማዴረስ፣የግንባታ ዘርፍ ስራዎችን ሇማጠናቀቅ ወይም
ሇመገጣጠም የሚያስፈሌገውን ዋጋ በሙለ በሚያመሊክት ሁኔታ መውጣት አሇበት፡፡
የተጠቀሰው ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በስተቀር ክሶችና የጉምሩክ ቀረጥ ዕቃዎችን ነፃ
ሇማዴረግ የሚከፈሌ ክፍያን በሙለ ማካተት አሇበት፡፡ ነገር ግን የግዥ ፈፃሚው መ/ቤት የዚህ
ዓይነቱን ክስ በበጀቱ ውስጥ ታሳቢ እንዱያርገው ተጫራቹ በዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ
የተጨማሪ እሴት ታክስን እንዱያሳይ ይጠበቃሌ፡፡

*በሚዘጋጁ የጨረታ ሰነዴ ተጫራቾች ከጨረታ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ የማቅረብ ግዳታ


እንዲሇባቸው መግሇፅ አሇባቸው፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ዓሊማ በታሰበው ጨረታ ውስጥ ኃሊፊነት
በተሞሊበት ሁኔታ የማይሳተፉትን ተጫራቾች ሇማስቀረት ነው፡፡ ከአንዴ አቅራቢ ከሚፈጸም ግዥና
በዋጋ ማቅረቢያ መጠየቂያ ግዥ በስተቀር በግሌጽ ጨረታ፣ ሁሇት ዯረጃ ጨረታ፣ የመወዲዯሪያ ሀሳብ
በመጠየቅ የሚፈጸም ግዥ እና ውስን ጨረታዎች ሊይ የጨረታ ማስከበሪያ መጠየቅ አሇበት፡፡

*የጨረታ ማስከበሪያው ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበትን ጊዜ ካሇፈ በኋሊ ሇ28 ቀናት ፀንቶ መቆየት
አሇበት፡፡ ይህም መ/ቤቱ በተጫራቾች ሊይ ጥያቄ ሇማቅረብ ወይም የመጠየቅ መብቱን ሇመጠቀም በቂ
ጊዜ እንዱኖረው ያስችሇዋሌ፡፡ ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከተራዘመ የጨረታ ማስከበሪያው አዱሱ
ጨረታ ጸንቶ ከሚቆይበት ጊዜ በኋሊ ሇ28 ቀናት መቆየት አሇበት፡፡ የጨረታ ማስከበሪው ከተራዘመ
የጨረታ ማስከበሪው የሚሰጥበት ቀን በሚመሇከት መ/ቤቱ ሇተጫራቾቹ ማሳወቅ አሇበት፡፡

*የጨረታ ሰነዴ በፅሁፍ ተዘጋጅቶና ተፈርሞበት በታሸገ ኢንቨልፕ ውስጥ ሆኖ በጨረታ ማስታወቂያው
ወይም በማሻሻያው ሊይ ከተመሇከተው የጊዜ ገዯብ በፊት በተገሇፀው ቦታ ገቢ መዯረግ አሇበት፡፡
ተጫራቾች ጨረታውን በቴላክስ፣ በፋክሲሜይሌ ወይም ኤላክትሮኒክ ሜይሌ መሊክ አይችለም፡፡
የጨረታ አቀራረብና ስርዓትን አሟሌተው የተሊኩ ቢሆኑም እንኳን በቴላክስ፣ በፋክሲሜይሌና
በኤሌክትሮኒክ ሜይሌ የተሊከ ማንኛውም ጨረታ ግምት ውስጥ አይገባም፡፡ ጨረታዎች በእጅ ወይም
የማመሊሇሻ አገሌግልቶችን ጨምሮ በፖስታ ብቻ መቅረብ አሇባቸው፡፡

-7-
*የጨረታው ሳጥን በሚከፈትበት ወቅት ጨረታው የታሸገና የታተመ መሆኑን ሇማረጋጥ ብቻ ሳይሆን
አሇመከፈቱን ማረጋገጥ እንዱቻሌ ተጫራቾች ኢንቨልፖቹ በትክክሌ ማሸግና ምሌክት ማዴረግ
አሇባቸው፡፡ ኢንቨልፖቹ በትክክሌ ባሇመታሸጋቸው እና ምሌክት ሊሌተዯረገባቸው የጨረታው መረጃ
አስቀዴሞ ስሇመውጣቱ ተጫራቹ ሙለ በሙለ ሃሊፊ ይሆናሌ፡፡ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ እንዯዚህ
ዓይነት ሁኔታ ካጋጠመ ጨረታውን የከፈተው አካሌ በራሱ ጊዜ በጨረታ ማቅረቢያው የተቀመጠው
መረጃ መውጣቱ የጨረታ ሂዯቱን እማኝነት ያበሊሸዋሌ ወይም አያበሊሸውም እንዱሁም ጨረታው
ውዴቅ መሆን አሇበት ወይስ የሇበትም የሚሇውን በሚመሇከት ውሳኔ መስጠት አሇበት፡፡

*ተጫራቹ ጨረታውን ሲያስረክብ ዯረሰኝ መጠየቅ ይችሊሌ፡፡ በዚህ ጊዜ ጨረታውን የተረከበው ሰራተኛ
ወይም ሀሊፊ ጨረታውን የተረከበበትን ቀንና ሰዓት እንዱሁም የተጫራቹን ስምና አዴራሻ የሚገሌፅ
ማስረጃ መስጠት አሇበት፡፡ ጨረታው በፖስታ ወይም በማመሊሇሻ ሲሊክ ስሇመዴረሱ በተመሳሳይ
ማረጋገጫ መስጠት አሇበት፡፡

*የጨረታውን አሸናፊ ማሳወቅና ውሌ መፈረምን በተመሇከተ ጨረታውን ያወጣው መ/ቤት ጨረታው


ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከማሇፉ በፊትና ጨረታውን የሚያፀዴቀው ኮሚቴ የጨረታውን አሸናፊ
ካፀዯቀበት ቀን ጀምሮ በአንዴ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ጨረታውን ሊሸነፈው ተጫራች አሸናፊነቱን ማሳወቅ
አሇበት፡፡ የጨረታ አሸናፊነት ማስታወቂያው በጨረታው ሰነዴ አጠቃሊይ እና ሌዩ የውሌ ሁኔታዎች
በተሰጠው ናሙና መሰረት ውለን በማያያዝ የሚከተለትን መግሇፅ አሇበት፡፡

 ጨረታው በመ/ቤቱ ተቀባይነት ማግኘቱን


 አሸናፊው ተጫራች ያቀረበው ዋጋ
 የውሌ ማስከበሪያው መጠንና ቅፅ
 የውሌ ማስከበሪያው የሚሰጥበት ቀንና ሰዓት
 ውለ የሚፈረምበት ቀንና ሰዓት

*የጨረታው አሸናፊነት ማስታወቂያ ከተገሇጸበት ቀን ጀምሮ ሰባት የስራ ቀናት ከማሇፉ በፊት
የመንግስት መ/ቤቱ ውለን መፈረም የሇበትም፡፡

*የውሌ ማስከበሪያው የውለን ክንውን(አፈፃፀም) ሇማረጋጥ እንዱያስችሌ በቂ መሆን አሇበት፡፡ መጠኑም


የጠቅሊሊ ዋጋ ከ10% ማነስ የሇበትም፡፡

*የጨረታው አሸናፊ የውሌ ማስከበሪያ ካሌሰጠ ወይም በጨረታው ሰነዴ በተገሇጸው መሰረት ካሌፈረመ
በመንግስት መ/ቤቱ ውለን ሇሚቀጥሇው አነስተኛ ዋጋ ሊቀረበው ተጫራች መሰጠት ይቻሊሌ፡፡
ላልችንም በዯረጃቸው በቅዯም ተከተሌ መሰረት የሚከናወን ይሆናሌ፡፡ ነገር ግን ይህ ዓይነቱ እርምጃ
መውሰዴ ያሇበት መ/ቤቱ የተገመተውን የጨረታ ዋጋ ከተቀበሇው ነው፡፡ ሆኖም ቀሪዎቹ ተሟሌተው

-8-
የቀረቡት ጨረታዎች የተገመገመው ዋጋ ከታወቀው ግምት ወይም ከተፈቀዯው በጀት ወይም በገበያ
ሊይ ካሇው የገበያ ዋጋ ከበሇጠ መ/ቤቱ ጨረታዎች፣የሀሳብ ማቅረቢያዎችና የዋጋ ማቅረቢያዎች ውዴቅ
በሚሆኑበት ሁኔታ ተገቢውን እርምጃ ሉወስዴ ይችሊሌ፡፡ ሁለም ጨረታዎች ውዴቅ ከተዯረጉ
በመንግስት መ/ቤቱ የተሻሻሇውን የጨረታ ሰነዴ በመጠቀም እና በመመሪያው መሰረት በስፋት
በማስተዋወቅ በዴጋሚ ጨረታውን ማካሄዴ ይችሊሌ፡፡

ማስታወሻ፡- ከሊይ በግዥ መመሪያው ሊይ በጨረታ ማስከበሪያ እና በውሌ ማስከበሪያ በተመሇከተ


የተገሇጸው የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በሌዩ አስተያየቱ የሚስተናገደ ይሆናሌ፡፡

ሇጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተዯረገ ሌዩ አስተያየት

የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በሌዩ ሁኔታ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዱሆኑ በ2002 ዓ.ም
በወጣው የፌዯራሌ የመንግሰት ግዥ መመሪያ የተቀመጡ ሌዩ አስተያየቶች ከታች የተገሇጸ ሲሆን ሌዩ
አስተያየቱ እንዯየክሌለ ተጨባጭ ሁኔታ የሚሇያይ ነው፡፡

 ከሀገር ውስጥ አቅራቢዎች ጋር በሚያዯርጉት ውዴዴር 3% ሌዩ አስተያየት ይዯረግሊቸዋሌ፡፡


 በጨረታ ማስከበሪያ፣ በውሌ ማስከበሪያ እና በቅዴሚያ ክፍያ ዋስትና ምትክ ተቋማቱን
ካዯራጃቸው አካሌ የሚሰጥ የዋስትና ዯብዲቤ ተቀባይነት ይኖረዋሌ፡፡
 ሇጨረታው የተዘጋጀውን ሰነዴ በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋምነት የተቋቋመበትን የህጋዊነት ማስረጃ
በማሳየት ያሇክፍያ በነጻ ይሰጣቸዋሌ፡፡

ከመንግስት ግዥ አቅራቢነት የሚያሰርዙ ጥፋቶች

 በቂ ምክንያት ሳይኖር በውለ መሰረት ዕቃና አገሌግልት አሇማቅረብ፣


 ተፈሊጊውን የጥራት ዯረጃ ያሌጠበቀ ዕቃና አገሌግልት ማቅረብ፣
 በሌዩ አስተያየት ተጠቃሚ የሆኑ ኢንተርፕራይዞች በውሌ ያሌተካተቱ ተጨማሪ ሁኔታዎች
መጠየቅ፣
 በመንግስት በኩሌ የሚዯረጉ ዴጋፎችን ሇላሊ ሶስተኛ ወገን አሳሌፎ የሰጠ መሆኑ በበቂ መረጃ
ሲረጋገጥ፣
 ያሇ በቂ ምክንያት ጨረታውን ካሸነፈ በኋሊ ስራውን የተወ ወይም የስራውን ቅዴመ ክፍያ
ወስድ ስራውን ያቋረጠ ኢንተርፕራይዝ ሇተከታታይ ሶስት ጨረታዎች እንዲይሳተፉ
ይዯረጋሌ፤ሊስከተሇውም ኪሳራ በህግ ተጠያቂ ይሆናሌ፡፡
 ሆን ተብል የጨረታ ስርዓቱን ሇማዛባት እንዱሁም ተገቢ ያሌሆነ ጥቅም ሇማግኘት ከጨረታ
ተወዲዲሪዎች ጋር ዋጋ ተስማምቶ ዝቅተኛ ዋጋ ሇማቅረብ መሞከሩ

-9-
የግንኙነነት ስሌት
በመንግስት መስሪያ ቤቶች እና አቅራቢዎች፣ዕጩ ተወዲዲሪዎች ወይም ተጫራቾች መካከሌ የሚዯረጉ
ግንኙነቶች በፅሁፍ መሆን ይኖርባቸዋሌ፡፡ ግንኙነቶች በፅሁፍ እንዱሆን የተዯረገበት ዋና ዓሊማ ሇህግ
የአስገዲጅነት ባህሪ እንዱኖራቸው ታስቦ ነው፡፡
አቤቱታ የማቅረብ መብት
የአዋጁ ዴንጋጌዎች እንዯተጠበቁ ሆነው ማንኛውም ተጫራች የመንግስት መ/ቤቱ አዋጁንና የአፈጻጸም
መመሪያውን በመጣስ በፈጸመው ወይም ባሌፈጸመው ዴርጅት ሊይ የአስተዲዯር ምርመራ በነጻ ማግኘት
ይችሊሌ፡፡
ከዚህ በፊት በተዘረዘሩት ጉዲዮች ግን አቤቱታ ሉቀርብባቸው አይችለም

 በአዋጁ በተዯነገገው መሰረት የግዥ ዘዳ መረጣ፣


 በአዋጁ መሰረት ሁለንም ጨረታዎች፣ የመወዲዯሪያ ሃሳብ ማቅረቢያዎችንና የዋጋ
ማቅረቢያዎችን ውዴቅ እንዱዯረጉ በሰጠው ውሳኔ፣
 በአዋጁ መሰረት ሇአገር ውስጥ አቅራቢዎችና ሇጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት በሚሰጥ ሌዩ
አስተያየት፣

የመንግስት መ/ቤቱ በሰራቸው ወይም ሳይሰራ በተዋቸው ጉዲዮች ሊይ ተጫራቹ በቅዴሚያ አቤቱታ
የሚያቀርበው ሇመንግስት መ/ቤቱ የበሊይ ሀሊፊ መሆን አሇበት፡፡

ተጫራቹ ሇቅሬታው ምክንያት የሆኑ ነገሮች መኖራቸውን ባወቁ በአምስት የስራ ቀናት ውስጥ
አቤቱታውን ማቅረብ ይችሊሌ፡፡ አቤቱታው በስምምነት ካሌተፈታ በስተቀር የመንግስት መ/ቤቱ የበሊይ
ሀሊፊ የግዥውን ሂዯት ማዘግየት አሇበት፡፡ አቤቱታው ከቀረበ በኋሊ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ምክንያቱን
በመግሇጽ በጹሁፍ ውሳኔ መስጠት አሇበት፡፡ አቤቱታው ተቀባይነት ካሇው ሉወስደ የሚገባቸውን
የእርምት እርምጃዎች መግሇጽ አሇበት፡፡ የመ/ቤቱ የበሊይ ሀሊፊ ከሊይ በተገሇጸው ጊዜ ውስጥ ውሳኔ
ካሌሰጠ ወይም ተጫራቹ በውሳኔው ካሌረካ ተጫራቹ የተሰጠው ውሳኔ በመንግስት መ/ቤቱ ከተገሇጸው
ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በአምስት የስራ ቀናት ውስጥ አቤቱታውን ሇቦርዴ ማቅረብ ይችሊሌ፡፡

ቦርደ አምስት አባሊት ያለት ሲሆን እነሱም፡-ከነንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር የሚወከሌ በሰብሳቢነት፣
ከንግዴ ምክርቤት አንዴ አባሌ ፣ከመንግሰት መ/ቤቶች የሚመረጥ አንዴ አባሌ ፣ከመንግስት የሌማት
ዴርጅቶች የሚወከሌ አንዴ አባሌ እና ከመንግስት ግዥና ንብረት አስተዲዯር ኤጀንሲ የሚወከሌ አንዴ
አባሌ ይኖሩታሌ፡፡ ቦርደ የአቤቱታው ዯብዲቤ እንዯዯረሰው በ15 የስራ ቀናት ውስጥ ውሳኔውን
ምክንያትና የተሰጠውን መፍትሄዎች በመግሇጽ ውሳኔ መስጠት አሇበት፡፡ በመንግስት መ/ቤት ወይም
በቦርዴ ውሳኔ ቅር የተሰኘ ተጫራች አቤቱታውን ሇተገቢው ፍርዴ ቤት ማቅረብ ይችሊሌ፡፡

- 10 -
5. ከፌዯራሌ ግዥ መመሪያው በመነሳት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች
በጨረታ ሂዯት ሉገነዘቡ የሚገባቸው ነጥቦች
 የመንግስት ግዥ መመሪያውን በመረዲት ሇጨረታው ብቁ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ
በወቅቱና በተሟሊ ሁኔታ ማቅረብ፤
 የተጫረቱበትን ስራ ሇማከናወን የሚያስችሌ ሙያዊ፣ቴክኒካዊ ብቃትና ተዛማጅ የስራ ሌምዴ
በመያዝ የተሰጣቸውን ስራ በወቅቱ ማጠናቀቅ ይገባቸዋሌ፡፡ ይህም ሇቀጣይ ሇሚመቻችሊቸው
የቅዴሚያ እዴሌ ተጠቃሚ እንዱሆኑ ያስችሊቸዋሌ፡፡ በዚህም መሰረት እንዯየክሌለ ተጨባጭ
ሁኔታ የግዢ መመሪያ የሚሇያይ ቢሆንም ሇአብነት በኦሮሚያ ክሌሌ በግዥ መመሪያ ሊይ
የተገሇፀው ኢንተርፕራይዞች በእጃቸው ካሇው ሥራ 70% እና ከዚያ በሊይ ሳይጨርሱ በላሊ
ሥራ ሊይ መወዲዯር የማይችለ መሆኑ በግሌፅ አስቀምጧሌ፤
 የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን ከአቅራቢነት ሉያሰርዟቸው የሚችለ ሁኔታዎች ቀዯሞ
በመገንዘብ አስፈሊጊውን ጥንቃቄ ማዴረግይገባሌ፡፡ ሇአብነት በአማራ ክሌሌ ግዥ መመሪያ ሊይ
ከአቅራቢነት ሉያሰርዙ የሚችለ ሁኔታዎች በሚሌ የተዘረዘሩት በቂ ምክንያት ሳይኖር በውሌ
መሰረት ዕቃና አገሌግልት አሇማቅረብ፣ተፈሊጊውን የጥራት ዯረጃ ያሌጠበቀ ዕቃና አገሌግልት
ማቅረብ፣የወሰደትን የቅዴመ ክፍያ በውሊቸው መሰረት ስራ ሊይ አሇማዋሌ፣በመንግስት በኩሌ
የሚዯረጉ ዴጋፎችን ሇላሊ 3ተኛ ወገን አሳሌፎ መስጠት፣ በውሌ ያሌተካተቱ ተጨማሪ
ሁኔታዎች መጠየቅ፣የስራውን ቅዴመ ክፍያ ወስድ ስራውን ማቋረጥ እና ከጨረታ ተወዲዲሪዎች
ጋር ዋጋ ተስማምቶ ዝቅተኛ ዋጋ ሇማቅረብ መሞከር ከአቅራቢነት የሚያሰርዙ ዴርጊቶች ናቸው፤
 ተጫራች ኢንተርፕራይዞች ወዯ ጨረታው ሂዯት ከመግባታቸው አስቀዴሞ በቂ የአዋጭነት ጥናት
እንዱሁም ወቅታዊ የገበያ ዋጋ ጥናት በማካሄዴ አሳማኝ የጨረታ ዋጋ ትመና በማዴረግ
ሇስራው አስፈሊጊ የሆነ አስተማማኝ የገንዘብ ምንጭና በቂ የሰው ሀይሌ በማዘጋጀት በውለ
መሰረት በወቅቱና በጥራት ስራውን በማጠናቀቅ መሌካም የኮንትራት አፈጻፀምና ጥሩ ዝና
እንዱኖራቸውቸ ማዴረግ፤
 ኢንተርፕራይዞች በጨረታ ሰነዴ አሞሊሌ ሊይ ያሇባቸውን ክፍተት ሇመሙሊት ተከታታይነት
ያሇው የግንዛቤ መፍጠሪያ ሉኖር ይገባሌ፤

 በመንግስት ግዥ ሇመሳተፍ በፌዯራሌ የመንግስት የግዥ ንብረት አስተዲዯር ኤጀንሲ የተዘጋጀውን


የአቅራቢዎች ምዝገባ ዴረ-ገፅ www.ppa.gov.et በመጠቀም ሇአቅራቢነት በመመዝገብ እንዱሁም
የተሇያዩ የጨረታ ማስታወቂዎች በመከታተሌ ያለ የገበያ አማራጮችን መጠቀም፡፡

- 11 -
ሰነደ የተጠቀማቸው የመረጃ ምንጮች

 የፌዯራሌ መንግስት የግዥ አፈጻፀም መመሪያ (ሰኔ,2002)

 የፌዯራሌ መንግስት ግዥ አፈጻፀም ማኑዋሌ (ሀምላ,2002)

 የፌ/ከ/ስ/ዕ/ፈ/ም/ዋ/ኤጀንሲ የገበያ ሌማትና የግብይት ስርዓት ሞዳሌ መመሪያ ቁጥር

003/2010

 የፌ/ከ/ስ/ዕ/ፈ/ም/ዋ/ኤጀንሲ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የገበያ ትስስር

ሁኔታ፤ተግዲሮቶች እና መሌካም አጋጣሚዎች የጥናት ሰነዴ (መጋቢት,2010)

 የክሌልች የግዥ አፈጻፀም መመሪያ

- 12 -

You might also like