You are on page 1of 1

እራስክን ከማንም ጋር አታወዳድርው

↩ የሁሉም መክሊቱ የተለያየ ነው እና


✔በሰው ሳይሆን በፈጣሪ ተደገፍ
↩ እሱ አይጥልህምና
✔ውሻ 3 ቀን ብታበላው 3 አመት ያስታውስሀል
↩ሰው ግን 3 አመት ብታበላው በ3 ቀን ይርሳሀል
#ወዳጀ
♨እራስክን ከማንማ ጋር አታወዳድር፡፡ ይህን ባደረክ ጊዜ እራስክን በራስህ እንደሰደብክ ቁጠረው፡፡
♨ቁልፍን ያለመክፈቻ ማንም እንደማይሰራ ሁሉ ፈጣሪም መፍትሄ የሌለው ችግር እንዲገጥምን አይፈቅድም፡፡
♨ደስታህን ከራስህ ባራቅህ ጊዜ ሕይዎት በአንተ ላይ ትስቃለች፡፡ ደስተኛ በሆንክ ጊዜ ሕይዎት ፈገግታዋን ትለግስሃለች፡፡
ሌሎች እንዲደሰቱ ምክንያት በሆንክ ጊዜ ግን ሕይዎት የከበረ ሠላምታዋን ታቀርብልሃለች፡፡
♨ማንኛውም ስኬታማ ሰው ከበስተጀርባው አስቸጋሪ ታሪኮች እንዳሉት ሁሉ ማንኛውም የችግር(አስቸጋሪ) ታሪክ
መጠናቀቂያው ስኬት ይሆናል፡፡ ስለሆነም ችግሩን ተቀበልና ለስኬት ተዘጋጅ፡፡
♨የሌሎችን ስህተት ለመተቸት በጣም ቀላል ነው፡፡ ከባዱ ነገር የእራስን ስህተት መረዳቱ ላይ ነው፡፡
♨የተፈጠረልህ መልካም አጋጣሚ ባመለጠህ ጊዜ እዛው ባለህበት ቁመህ አይንህን በእንባ አትሙላ፡፡ ቀጣዩንና የተሻለውን
መልካም አጋጣሚ እንዳታይ ይከልልሃልና፡፡
♨ለችግር ፊትን ማዞር ችግሩን አይቀይረውም ችግሩን መጋፈጥ እንጅ፡፡ በሌሎች ቅሬታን ከማሰማት እራስን ለውጦ
ሠላምን መግዛት፡፡
♨ስህተት ስህተቱ በተፈጠረበት ወቅት ስሜትን ይጎዳል፡፡ ከዓመታት በኋላ የስህተቶች ድምር የሚፈጥረውና ወደ ስኬት
የሚያመራው ከስህተት መማር ተሞክሮ(ልምድ) እንለዋለን፡፡
♨የቀለጠ ወርቅ ጌጣጌጥ እንደሚሆነው፣
አንተም በብዙ ችግር ባለፍክ ቁጥር አንተነትህ እያደገ መሆኑን አትርሳ፡፡ በመሆኑም ስትሸነፍ ጠንካራ ስታሸንፍ የተረጋጋ
ሁን፡፡
ከደራሲያን ዓለም Art of firaw//78

You might also like