You are on page 1of 3

የኢትዮጵያ የኤሌክትሮኒክስ የአንድ መስኮት አገልግሎት ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለፁት የኢኮኖሚ ማሻሻያ

አንዱ አጀንዳ የንግድ ስራ አመቺነት (Ease of Doing Business) ነው ብለዋል፡፡

የተሳለጠ የንግድ አሰራር ባለመዘርጋቱ የንግድ ስራ ሃሳብ እያላቸው ወደ ስራ ለመግባት የሚቸገሩ ዜጎች
መኖራቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የአንድ መስኮት አገልግሎት የንግድ ሰራን ከማቀላጠፍ በተጨማሪ ሌብነትን ለመቀነስ ጠቀሜታ እንዳለው
ተናግረዋል፡፡

ንግድ እንዲስፋፋና ብልፅግና እውን እንዲሆን በንግድ ስራ አመቺነት ያለችበትን ደረጃ ማሻሻል ያስፈልጋል፡፡

የአንድ መስኮት አገልግሎት ዋናው ውጤት የሚለካው ነጋዴዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀደም ሲል ከነበረው
አሰራር የተሻለ ሲሆን ነው፡፡

ባለድርሻ አካላት በዚህ አገልግሎት የሚገለገሉ ደንበኞች ችግር እንዳይገጥማቸው አስፈላገውን ድጋፍ
እንዲያደርጉም ጠይቀዋል፡፡

ፕሮጀክቱ 16 የሚሆኑ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈና በሀገራችን የዓለም አቀፍ ንግድ ሂደትንና የሎጂስቲክስ
ሥርዓትን በማዘመን፣ ኢኮኖሚያዊ ተወዳዳሪነታችንን በማሳደግ በኩል ሊተካ የማይችል ከፍተኛ ሚና
ይጫወታል።

ፕሮጅክቱ አስመጪውች እና ላኪወች በየተቋማቱ መሄድ ሳያስፈልጋቸው በሚቀርብላቸው የኤሌክትሮኒክስ


አግልግሎት አማካኝነት ለማስመጣት ወይም ለመላክ የሚያስፈልጉ የንግድና ተያያዥ ሂደቶችን በቢሮ፣በቤት
ወይም በአመች ቦታ ሆኖ ለመፈጸም ያስችላል፤ በዚህም ይወጣ የነበረውን፣ ወጪ፣ ጊዜና ድካም ማዳን
ይቻላል።

የገቢና የወጪ ሂደት የሚወስደውን ጊዜ ከ 44 ቀናት በመጀመሪያ ምዕራፍ ወደ 13 ቀናት በሁለትኛ ምዕራፍ
ደግሞ ወደ 3 ቀናት ይቀንሳል፡፡

ፕሮጅክቱ የንግድ ሂደቱን የሚተነበይ ያደርገዋል፣የህግ ተገዥነትን ያሳድጋል ፤የሙስና ተግባራትን ለማስቀረት
ያስችላል፤ በዚህም ከፍተኛ ወጭ ማዳን ይቻላል።
የመረጃ እና የግንኙነት ቴክኖሎጂዎች (አይቲሲዎች) በዓለም ዙሪያ ላሉት የኤሌክትሮኒክስ መንግስታት የኤሌክትሮኒክስ
መንግስት አስፈላጊ መሣሪያዎች ናቸው ፡፡

የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን (ኢ-መንግስትን) ለማሳደግ ግቦችን ደረጃ በደረጃ እየሰራ ይገኛል ፡፡ ለዚህም
መንግስት ኢኮቴክን ለልማት አጀንዳዎች እንደ ዋና መሣሪያ አድርጎ ለመጠቀም የተለያዩ እርምጃዎችን ወስ has ል ፡፡
ከእነዚያ አነቃቂዎች ውስጥ አንዱ የግብይት ኢ-ሰር መሣሪያዎች ልማት ነው ፡፡

የ “eService” ስርዓቱ ለመስመር ላይ ግብይት አገልግሎቶች አንድ የጋራ መድረክ እና አጠቃላይ መሳሪያዎችን
ለማቅረብ የተቀየሰ ነው። ሥርዓቱን በመጠቀም የመንግሥት ድርጅቶች የኤሌክትሮኒክ ሕዝባዊ አገልግሎቶችን ለዜጎች ፣
ላልሆኑት ዜጎች ፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለመንግስት እና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ይሰጣሉ ፡፡

የአገልግሎት ጥያቄን ለማስገባት አንድ ዜጋ መለያውን በመጠቀም በመለያ መግባቱን ወይም የተጠቃሚውን መለያ
ለማግኘት እና በትግበራ ለመቀጠል ወደ ስርዓቱ መመዝገብ አለበት ፡፡ ለአንድ የተወሰነ የህዝብ አገልግሎት የኤሌክትሮኒክ
ፎርሙን ከጠቀሰ በኋላ ዜጋው ሁሉንም አስገዳጅ መስኮች ይሞላል ፣ ሰነዶችን ይሰቅላል እና የስህተት እርማት
ከተመለከተ በኋላ ጥያቄውን ያቀርባል።

ጥያቄው ከገባ በኋላ ስርዓቱ ዜጋ የትግበራ ሁኔታቸውን ለመከታተል አውቶማቲክ የማመልከቻ ማጣቀሻ ቁጥር ያወጣል
፡፡ የመከታተያ ቁጥሩ የተጠቃሚዎች ሁኔታን ለመከታተል ፣ ቀጠሮዎችን ለመያዝ ቀጠሮዎችን በመያዝ እንዲሁም
በአገልግሎት ሰጪው በኩል የጠየቀውን ማንኛውንም ተጨማሪ ደጋፊ ሰነዶችን እና መረጃዎችን ለማስገባት የሚያገለግል
ነው ፡፡ የአገልግሎት አቅርቦት ፡፡
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዶክተር አብርሀም በላይ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጀኒ ተርኪህን ጋር
ተወያይተዋል፡፡

ውይይታቸው በሩሲያ አቶሚክ ሀይል ኮርፖሬሽንና በኢኖቬሽናና ቴክኖሎጂ ሚንስትር መካከል ባለፈው ታህሳስ ወር
በተፈረመው መሠረት በኢትዮጵያ የኒውክለር ሀይልን መጠቀም የሚያስችል ተቋም ለማቋቋም እና ኒውክለርን ለሰላም
መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

የኒውክለር ሀይልን ከመጠቀም አንፃር በህዝብ ውስጥ ያለውን የተሳሳተ አመለካከት መቀየር የሚያስችሉ ስራ እና
በኢትዮጵያ የኒውክለር ሀይልን መጠቀም የሚያስችው ተቋም ለማቋቋም የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በአጭር ጊዜ
ለማጠናቀቅ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ የባዮሊጂካል ሴንተር አቋቁሞ የሩሲያና የኢትዮጵያ ምሁራን በጋራ ምርምር ለማድረግ
የሚያስችላቸውን ሰነድ የማዘጋጀት ሰራ ተጀሯል።

በስፔስ ሳይንስ እና በሌሎች የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ሁለቱ ሀገራት በስፋት መስራት በሚያስችላቸው
ጉዳዮች ዙርያ የተነጋገሩ ሲሆን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብረሀም በላይ ኢትዮጵያ ለጉዳዩ ልዩ
ትኩረት በመስጠት እንደምትሰራ ተናግረዋል፡፡

ከ 2013 ጀምሮ በሩሲያና በኢትዮጵያ መካከል ተግባራዊ የነበረ ስምምነት ቢኖርም ስምምነቱ ሌሎች ያልተካተቱ
ተግባራትን በማካተት በአዲስ ስምምነት እንዲተካ መግባባት ላይ ተደርሷል።

You might also like