Professional Documents
Culture Documents
2012 Up
2012 Up
ማውጫ ገፅ
1. መግቢያ...........................................................................................................................................3
2. አላማ…………………………………………………………………………………………..3
3. ተልዕኮ.............................................................................................................................................3
የተቋሙ ራዕይ.....................................................................................................................................3
የተቋሙ ተልዕኮ...................................................................................................................................3
የቡድኑ ተልዕኮ....................................................................................................................................4
7. ማጠቃለያ……………………………………………………………………………………….10
በተቋማዊ ደህንነት ዳይሬክቶሬት የቬቲንግ እና ስክሪኒንግ ቡድን ተልዕኮ የሆነውን የተቋሙን የሰው ሀይል
ደህንነት የማረጋገጥ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት እንዲችል ከዚህ በፊት የነበሩትን የስራ እንቅስቃሴዎች
ስኬቶችና ውስንነቶችን በመገምገም ለቀጣይ የስራ ዕቅድ እንደ ግብዓት መጠቀም በሚያስችል አኳኋን
አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ለ 2012 ዓ.ም በጀት አመት ለኤጀንሲያችን ተልዕኮ መሳካት የበኩላችንን ድርሻ
ለመወጣት አስፈላጊውን ትኩረት በመስጠት የምንሰራ ይሆናል፡፡ በዚህም መሰረት አጠቃላይ የተቋሙን የሰው
ሀይል የተጋላጭነት ስጋቶች ለመቀነስ እና ቀጣይነት ባለው መልኩ የተቋሙን ሁለንተናዊ ደህንነት ለማረጋገጥ
የሚያስችሉ ተግባራት ላይ በዋናነት ትኩረት በማድረግ የቡድኑን የመፈጸም አቅም የማሳደግ፣ ተቋማዊ
ትስስሮችን የማጠናከር፣ የሰው ሀይል የማወቅ ደረጃ የማሳደግ እና ሌሎች ተጓዳኝ ስራዎችን በመስራት
የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ የምንሰራ ሲሆን የባለድርሻና የሌሎች አጋር አካላትን ድጋፍ በመደመርና
በመጠቀም ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት በትጋት መስራት በዚህ ዓመት በስራ ክፍሉ ትኩረት የሚሰጠው
ጉዳይ ነው::
2. አላማ
የሰው ሀይል ደህንነትን ለማረጋገጥ ያለፉ ተሞክሮዎችን መነሻ በማድረግ ውስጣዊና ውጫዊ ከባቢዎችን
በመፈተሸ ክፍሉ በ 2012 ዓ.ም የሚያከናውናቸውን ተግባራት በመለየትና የአፈጻፀም ስልት በመንደፍ
ተልዕኮውን ለመወጣት ያለውን ዝግጁነት እና ተጣጣሚነት በዚህ ሪፖርት ማቅረብ ነው፡፡
3. ተልዕኮ
የተቋሙ ራዕይ
በ 2017 ዓ.ም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ብቃት ያለው እና በሃገሪቱ ህዳሴ ቁልፍ ሚና የሚጫወት ብሄራዊ
የሳይበር ሴኪውሪቲ ተቋም ዕውን ማድረግ ፡፡
የተቋሙ ተልዕኮ
ግብ 1፡- የተቋሙን የሰው ሀይል ደህንነት ማረጋገጥ (የሰው ኃይል የማወቅ ደረጃ ማሳደግ) የቀደምትነት
ዋና ዋና ተግባራት ደረጃ
ለተቋሙ ተልዕኮ የሚመጥን፣ ማንነቱ የታወቀ እና ደህንነቱ የተረጋገጠ የሰው ሀይል መለየት (የሰው ኃይል የማወቅ
ደረጃ ማሳደግ) 1
የቅድመ ቅጥር ምልመላ እና መረጣ ስራዎችን ማከናወን
የቅድመ ቅጥር ኢንተርቪው ማድረግ
በውስጥ ቅጥር፣ዝውውር እና እድገት የሚቀጠሩ አባላትን ኢንተርቪው ማድረግ
በማስታወቂያ ቅጥር የሚገቡ አዲስ አባላትን ኢንተርቪው ማድረግ
አዲስ የመረጃ(ቋንቋ) ባለሙያዎችን ምልመላና መረጣ ስራ ማከናወን
መረጃ መሰብሰብ፣ ክትትል ማድረግና መቀመር
ኘሮፋይል ዝግጅት
የማንነት ማጣራት (ቬትንግ) ስራዎች ማከናወን
1
በተቋሙ የተለያዩ የቅጥር አይነቶች ቅጥር የሚፈፅሙና የሚመደቡ አባላት
በልዩ ሁኔታ የተመረጡ በተቋሙ የስራ ክፍሎች ውስጥ የሚሰሩ አባላት
ከተቋሙ ውጭ ባሉ ቁልፍ የመንግስት ተቋማት የሚመጡ የቬቲንግ ጥያቄዎች
ዋና ዋና ተግባራት
ኢንተርቪው እና ኢንትሮጌሽን ማድረግ
ትንተና ማከናወን
የጥናት ውጤት ሪፖርት ማዘጋጀት
ፕሮፋይል ማዘጋጀት
ግብ 2፡- ከአጋር እና ባለድርሻ አካላት ጋር ጠንካራ እና ቀጣይነት ያለው ግንኙነት በመፍጠር ለተልዕኳችን ኃይል ማብዛት፤
በማንነት ማጣራት ስራ (ቬቲንግ) ከተቋሙ ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር ትስስር መፍጠር፤ በቀጣይነት አጠናክሮ መቀጠል
ባለድርሻ አካላት
ከተቋሙ የተለያዩ የስራ ክፍሎች ጋር ያለውን ትስስር ማጠናከር፤
1
በዳይሬክቶሬቱ ውስጥ ካሉ ሌሎች ቡድኖች ጋር ያለውን ትስስር ማጠናከር፤
አጋር አካላት
ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት
በየደረጃው ያሉ የመንግስት አስተዳደር መዋቅሮች (ክልል፣ ዞን፣ ወረዳ፣ቀበሌ)
ሌሎች የደህንነት መዋቅሮች (እንዳስፈላጊነቱ)
በቅድመ ቅጥር ምልመላ እና መረጣ ስራ ከባለድርሻ አካላት ጋር ግንኙነት መፍጠር
ከሰው ሀይል ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
ከቀጣሪ ክፍሎች
ምልመላው ከሚከናወንበት ተቋም (የት/ተቋም፣ ማሰልጠኛ ተቋማት፣በየደረጃው ያሉ የመንግስት አስተዳደር
መዋቅሮች)
የክፍሉን ስራዎች ትራንስፎርም ሊያደርጉ በሚችሉ እና አጠቃላይ ተቋማዊ ጥናቶችን ማከናወን በሚያስችሉ ስራዎች
ላይ ተሳትፎ ማድረግ
ግብ 3፡- የክፍሉን የመፈፀም አቅም ማሳደግ
ዋና ዋና ተግባራት
የክፍሉን የአሰራር ስርዓቶች ማሻሻል (የማንነት ማጣራት እና የቅድመ ቅጥር ምልመላና መረጣ)
የክፍሉን እስትራቴጂክ እቅዶች እና የአፈፃፀም መመሪያዎች ማዘጋጀት፣ ማፀደቅ፣ ተግባራዊ ማድረግ
የአባላትና የአመራር ፕሮፋይል በቀጣይነት ማደራጀት (እቅድ፣ ሪፖርቶች እና ግምገማዎች) 1
የተልዕኮ ግልፅነት የሚፈጥሩ ውይይቶችን ማድረግ (ሀገራዊ እና ተቋማዊ መመሪያዎች፣ ደንቦች፣ የአሰራር ስርዓቶች)
የተቋሙን የሰው ሀይል ልማት እስትራቴጂዎች መሰረት ያደረገ የአባላትን የስልጠና እና ትምህርት እድሎች ማመቻቸት
የአሰራር ስርዓቶችን ማዘመን (ሰው ለማወቅ የሚያግዙ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና ሳይንሳዊ የአሰራር ስርዓቶችን
ማጥናት)
መለኪያ
ግቦች
ቀዳማይ ዳህራይ
የማንነት ማጣራት (ቬቲንግ) ስራዎችን መፈፀም (100%) ትንተና የተሰጠበት የአባላት ፕሮፋይል
የቅድመ ቅጥር ምልመላና መረጣ ስራዎችን መፈፀም ትንተና የተሰጠበት የአባላት ፕሮፋይል
1
(100%)
የአባላትን ፕሮፋይል ማደራጀት (100%) ካታሎግ ስርዓት ውስጥ የገባ የአባላት ፕሮፋይል
አባላት ብዛት
የተደራጀ የአባላት ፕሮፋይል በ% 20 0% 100% 100% 100% 100% 100%
30
የደንበኛ እርካታ መጠን በ% 30 50% 90% 60% 70% 80% 90%
3 30 ስትራቴጂዎች
የተዘጋጁ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በቁጥር 30 0% 4 1 1 1 1
የፀደቀ መመሪያ በቁጥር 30 0 1 ዝግጅ ማፀደቅ 1 ትግበራ
ት
7. ማጠቃለያ
የቬቲንግና ስክሪኒንግ ቡድን የ 2012 ዓ.ም አመታዊ እቅድ የክፍሉ ተልዕኮ የሆነውን ከሰው ሀይል ሊመነጭ የሚችልን የደህንነት ስጋት
በመቀነስ ማንነቱ የታወቀ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የሰው ሀይል የመለየት ተግባራት ላይ ትኩረት በማድረግ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ
ከመቸውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ርብርብ የሚደረግ ይሆናል፡፡ በመሆኑም በቀጣይ ጊዜያት የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ
ስርዓቶችና የማሻሻል፣ የማዘመንና ሳይንሳዊ የማድረግ ስራዎች በስፋት የሚሰሩ ይሆናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ
ዘርፉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የጠላት እንቅስቃሴ እና ተለዋዋጭ የማጥቂያ ስልቶች ማወቅ
በተየያዘ የዘርፉ አስፈላጊነት ከተቋማችንም ባለፈ የሌሎች ተቋማትን ትኩረት የሚስብ በመሆኑ በዘርፉ ሀገራዊ
አቅም ለመፍጠር ለአቅም ግንባታ ስራዎች ከፍተኛ ትኩረት ተሰጦ የሚሰራ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ክፍሉ በ 2012
በጀት አመት በሁሉም የክፍሉ አባላት ዘንድ የተልዕኮ ግልፀኝነት በመፍጠር በከፍተኛ የስራ ተነሳሽነት እና የአመራር