You are on page 1of 5

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

የ Cross - cutting/ Standard/ ጥራት ቡድን ወይም አንድ ለአምስት ቡድኖች የሪፖርት ማቅረቢያ

የጥራት ቡድን መሪ ለፋሲሊቴተር ሪፖርት ማድረጊያ

የሪፖርት ማቅረቢያ ጊዜ በየ ሣምንት


የቡድን መሪ ስም የሪፖርት ጊዜ የጥራት ቡድኑ አባላት ብዛት
 ዳኛቸው ኮሬ  ከ 25/10/2008 –1/11/2008 ዓ.ም  10

በሳምንት ጊዜ ውስጥ የተከናወኑ ቁልፍ ስራዎች

ቁልፍ ተግባር 1 ፡ የዩኒት 1፤2፤3፡4 ፤5 ፤ 6 ፤7 እና የዩኒት 8 የኮሚሽኒንግ ስራ ተጠናቆ የኃይል ማመንጨት ሥራ ጀምረዋል፡፡
የዩኒት 9 እና የዩኒት 10 የጀነሬተር እና የተርባይን ተዛማጅ ዕቃዎች የመግጠም እና የተከላ ሥራ በመካሄድ ላይ ይገኟል፡፡
የሮተር ቁጥር 9 የመገጣጠም ሥራ አልቆ ወደጀነሬተሩ ፒት ገብቷል፡፡ ፤ የ 10 ቁጥር ሮተር ፖል የመገጣጠም ሥራ ተጠናቆ በፍተሻ ላይ ይገኛል፡፡
የ 9 ነኛውና የ 10 ውኛው የኤክዛይቴሽንና ጎቨርነር እንዲሁም ኤልሲዩና ጀነሬተር ፕሮቴክሽን ፓነሎች በየቦታቸው ተቀምጠው የኢንስታሌሽን ስራ እየተሠራ ይገኛል፡፡
የ 10 ኛዉ መጨረሻው ዩኒት እስቴተር ሁለቱም ሰክሻን በቦታው ፒት ውስጥ ተቀምጦ የማገጣጠም ሥራ ተጠናቆ የባር ኢንስታሌሻን ሥራ ተጠናቋል፡፡ ቀጣይ ተዛማጅ መገጣጠሚያዎች
ሥራ እየተሠራና ሮተር ለማስገባት በሂደት ላይ ይገኛል፡፡
የውሃ ፓምፕና የኬብል ሥራዎች በእስፓራል ኬዝ ፍሎር በ 10 ኛው ዩኒት ደርሷል፡፡

በዋናው መቆጣጠሪያ ክፍሎች የሚሠሩ የቬንትሌሽን ኢንስታሌሽን ሥራ ተጠናቆ በተግባር ላይ ይገኛል፡፡፤ የመብራትና ሶኬት እንዲሁም የአደጋ ሴንሰሮች መስመር ዝርጋታ ሥራዎችን
በመካሄድ ላይ ይገኟሉ፡፡ በመጨረሻም ሥራቸው ያለቁ የየዩኒቶቹ ተዛማጅ ዕቃዎች በየዕለቱ በሚደረጉ የኮንትራክተሩ ፕሮግራም መሠረት ለትክክለኛነታቸው የፍተሸ ሥራ በማድረግ
እና በማረጋገጥና እርምት በሚያስፈልጋቸው ላይ ትችት በመስጠት እንዲታረሙ የማድረግ ሥራ ያካሄዳል፡፡ ይህ በቀጣይነት የሚደረግ የዕለት በዕለት የሥራ አካሄድ ነው፡፡

የተወሰደ እርምጃ ፡ ዓለም ዓቀፍ የእስታንዳርድ መስፈርቶችን (IEC, IEEE እና ሌሎችም) በሚያዘውና መስፈርቱን በሚያሟላው መሠረት ሥራዎች መሠራታቸውን በማረጋገጥና በመፈተሸ ውጤቱን
ለሥራው በተዘጋጀው የጥራት መቆጣጠሪው ሰነድ በየሥራ ዓይነቱ መመዝገቡን የጥራት ቡድኑ አረጋግጧል፡፡
በኤሌክትሪካልና መካኒካልሥራ በፍተሸው የተገኙትን ግድፈቶችና ጉድለቶች በመልቀም እንዲታረሙና እንዲስተካከሉ እየተደረጉ ናቸው፡፡

ቁልፍ ተግባር 2 ፡ በኃይል ማመንጫዉ ከዋናው ትራንስፎርመር ወጪ የ 400 ኪ/ቮ የዲስኮነክተር፤ አሬስተርና የመስመር ማገናኘት ሥራ በወጪ መስመር 9 እና 10 እየተካሄደ
ይገኛል፡፡ በቀጣይነት የፍተሻ ሥራዉ እንደሥራዉ አካሄድ ይሠራል፡፡
የዋናዉ የ 400 ኪ/ቮልት ትራንስፎርመር የተጓዳኝ ዕቃዎች የመገጣጠምና የእሳት አደጋ መከላከያ መስመር መዘርጋት እንዲሁም የትራንስፎርመር 13፤ 14፤ እና 15 የዘይት የማጣራትና የ
መሙላት ሥራ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ከጀነሬተር መውጫ እስከ ጂሲቢ እና እንዲሁም ከጂሲቢ እስከ 400 ኪ/ቮልት ትራንስፎርመር መግቢያ የ 15 ኪ/ቮልት ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ቱቦ (IPB) የመዘርጋት ሥራ ከዩኒት 9 እስከ
ዩኒት 10 እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የ 400 ኬቪ ትራንስፎርመር ቡሺንግ ተከላ ሥራ ተጠናቆ የእልክትሪክ ፍተሸ ሥራ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የትራንስፎርመር የእሳት አደጋ መከላከያ የቧንቧ መዘርጋት ሥራ 13 ኛው
ትራንስፎርመር ላይ ደርሷል፡፡

የተወሰደ እርምጃ ፡ ጥራቱን የጠበቀና መስፈርቱን ያሟላ ሥራ መካሄዱን በማረጋገጥ የሥራውን ውጤት በዕለታዊ የሪፖርት መዝገብ ሰፍሯል፡፡
በኤሌክትሪካልና መካኒካልሥራ በፍተሸው የተገኙትን ግድፈቶችና ጉድለቶች በመልቀም እንዲታረሙና እንዲስተካከሉ እየተደረጉ ናቸው፡፡
ቁልፍ ተግባር 3 ፡ በድራፍት ትዩብና በተርባይን ወለል ከዩኒት 9 ጀምሮ የኬብል ማረፊያ አልጋ የማንጠፍና በተጓዳኝ የኬብል ዝርጋታ ሥራ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የተወሰደ እርምጃ ፡ ጥራቱን የጠበቀና መስፈርቱን ያሟላ ሥራ መካሄዱን በማረጋገጥ ዕለታዊ የሥራ ውጤቱን በዕለታዊ መመዝገቢያ ተመዝግቧል፡፡

ቁልፍ ተግባር 4 ፡ ከስዊች ያርድ እስከ ሠራተኞች ቋሚ መንደር የሚሄደው የ 15 ኪ/ቮልት የኤሌክትሪክ መስመር የፖል ተከላ ሥራ ተጠናቆ የኬብል ዝርጋታ ሥራ ተጀምሯል፡፡
በኮንትራክተሩ ሳሊኒ በሁለት አቅጣጫ የሚሠራው የአሳንሰር (elevator) ሥራ ተጀምሮ ከፊል ሥራው ተጠናቋል፡፡
የተወሰደ እርምጃ ፡ ጥራቱን የጠበቀና መስፈርቱን ያሟላ ሥራ መካሄዱን በማረጋገጥ የሥራውን ውጤት በዕለታዊ የሪፖርት መዝገብ ሰፍሯል፡፡
በኤሌክትሪካልና መካኒካልሥራ በፍተሸው የተገኙትን ግድፈቶችና ጉድለቶች በመልቀም እንዲታረሙና እንዲስተካከሉ እየተደረጉ ናቸው፡፡
ቁልፍ ተግባር 5 ፡ ከውጪ የሚገቡትን ቋሚና አላቂ ዕቃዎች የመፈተሸና የመመርመር ሥራ ፤ (ቀጣይነት ያለው ሥራ ነው፡፡)
የተወሰደ እርምጃ ፡ በኮንትራቱ መሠረት ዕቃዎቹ በዓይነት ፤ በመጠንና ጥራታቸውን በማየትና በጉዞ ጉዳት አለመድረሱን ተረጋግጧል፡፡ በገቢ ሰነድ ለትክክለኛነቱ ኢንስፔክተሩ አረጋግጧል፡፡
(ቀጣይነት ያለው ሥራ ነው፡፡)
ቁልፍ ተግባር 6 ፡ በሥራ ተቋራጩ በየሥራ ዘርፉ መሠራት የሚገባቸዉንና ሳይሠሩ ተዘንግተውም ሆነ ሆን ተብለው የተዘለሉ ጥቃቅን ሥራዎችን መልቀም (punch list ማዘጋጀት)፤ (ቀጣይነት ያለው
ሥራ ነው፡፡
የተወሰደ እርምጃ ፡ የጥራት ተቆጣጣሪ ቡድኑ ግድፈት ያለባቸውንና የተዘለሉትን ሥራዎች በየሥራ ዓይነቶቹ በመዘርዘር (punch list በማዘጋጀት) ለሥራ ተቋራጩ እንዲያስተካክል ሠጥቷል፡፡

በሳምንት ጊዜ ውስጥ የመጣ መሻሻል


1. የሥራ ተቋራጩ የሰው ኃይሉንና ባለሙያዎቹን እንዲሁም የመፈተሻ መሣሪያዎቹን በመጨመር ሥራዎቹን ለማጣደፍና ወደኋላ ዘግይቶ የሚገኘውን ሥራ ለማካካስ እየሞከረ
ይገኛል፡፡
2.
3.
4.

ያጋጠሙ ችግሮች

1 ፡ በጊዜ ሠንጠረዡ በተነደፈው የሥራ ፕሮግራም በ (June 11, 2014) በተከለሠው) መሠረት ሁሉም ሥራዎ ች እየተሠሩ አለመሆናቸውና ሥራዎች ዘገይቶ እንደሚገኝ፤ አሁን
እየተሠሩ የሚገኙት ሥራዎች ቀደም ሲል
ከሁለትና ሦስት ወራት በፊት መጠናቀቅ የሚገባቸው እንደነበረ ቡድኑ ይገልፃለል፡፡የሥራ ተቋራጩ የ ሰው ኃይልና ለፍተሸ የሚያገለግል የመፈተሸ ዕቃዎች
እንዲያቀርብና ሥራዎች በታቀደላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቅ
ተጠይቋል፡፡

2፡

ካለፈው ግብረ መልስ በመነሳት የተወሰዱ እርምጃዎች


1
2
3
በቀጣይ ሳምንት የሚከናወኑ ቁልፍ ተግባራት

ቁልፍ ተግባር 1 ከላይ በዚህ ሣምንት የተከናወኑት ሥራዎች በቀጣይነት የሚታዩ ሥራዎች ናቸው፡፡

የሚወሰድ እርምጃ ፡ ድሮዊንግና ዶክሜንቶች ለሥራው ዝግጁ መሆናቸዉን ማረጋገጥ፤ ሥራዎች መስፈርቱን (IEC) ሰታንዳርድ በተከተለ መልኩ በትክክል መሠራቱን መከታተል የተሠሩትን የሥራ ውጤት
በጥራት መከታተያ ሰነድ ማስፈር፤

ቁልፍ ተግባር 2 ፡ ከላይ በዚህ ሣምንት የተከናወኑት ሥራዎች በቀጣይነት የሚታዩ ሥራዎች ናቸው፡፡

የሚወሰድ እርምጃ ፡ ድሮዊንግና ዶክሜንቶች ለሥራው ዝግጁ መሆናቸዉን ማረጋገጥ፤ ሥራዎች ዲዛይኑን፤ ቴክኒካል እስስፊኬሽንና ዓለምዓቀፍ መስፈርቱን (IEC) ሰታንዳርድ በተከተለ መልኩ በትክክል
መሠራቱን መከታተል የተሠሩትን የሥራ ውጤት በጥራት መከታተያ ሰነድ ማስፈር፤

ቁልፍ ተግባር 3 ፡ ከላይ በዚህ ሣምንት የተከናወኑት ሥራዎች በቀጣይነት የሚታዩ ሥራዎች ናቸው፡፡

የሚወሰድ እርምጃ ፡ ድሮዊንግና ዶክሜንቶች ለሥራው ዝግጁ መሆናቸዉን ማረጋገጥ፤ ሥራዎች መስፈርቱን (IEC & IEEE) ሰታንዳርድ በተከተለ መልኩ በትክክል መሠራቱን መከታተል የተሠሩትን
የሥራ ውጤት በጥራት መከታተያ ሰነድ ማስፈር፤

ቁልፍ ተግባር 4 ፡ ቀጣይነት ያለውን ከውጪ የሚገቡትን ቋሚና አላቂ ዕቃዎች በትክክል መግባታቸውን መከታተልና በጉዞ ላይ ችግር አለመድረሱን ማረጋገጥ፤

የሚወሰድ እርምጃ ፡ በሰነዱ (Packing list) መሰረት የዕቃ ዝርዝሩን መፈተሸ፤ በዕቃዎቹ ላይ ጉዳት አለመድረሱን ማረጋገጥና ትክክለኛነታቸውን ማወቅ፤

ቁልፍ ተግባር 5 ፡ የተከላና የእንስታሌሽን ሥራ አልቆ ለፍተሸ በተዘጋጁ መሣሪያዎች የአፈፃፀም ችግርና እርማት የሚያስፈልግባቸዉን ዝርዝር (punch list) ማዘጋጀትና ለሥራ ተቋራጩ እንዲያስተካክል
መስጠት፤
የሚወሰድ እርምጃ ፡ የሥራ ተቋራጩ በጥራት ቡድኑ የተሠጠውን የእርምት ሥራ መሥራቱን የማረጋገጥና በተዘጋጀው የጥራት ሠነድ መስፈሩን በማረጋገጥ መፈረም፤

You might also like