You are on page 1of 2

ቁጥር 162749

ቀን
ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት
የካምድብ ሥራክርክር ችሎት
አዲስ አበባ
ከሳሽ መ/ር ጌታቸዉ አሸናፊ አድራሻ የካ ክ/ከ/ወረዳ 11
ተከሳሽ የኮተቤ ደብረ ገነት ቅ/ዑራኤል ቤ/ክ/ሰ/ጉ/አስ/ጽ/ቤት አድራሻ የካ
ክ/ከ/ወረዳ 11
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 256 መሠረት ተጨማሪ ማስረጃ እንዲያያዝ የቀረበ አቤቱታ
ነው
1. ከሳሽ ቀደም ሲል ባቀረብኩት አቤቱታ መሠረት ፍ/ቤቱ በዚሁ መ/ ቁ በቀን
27/6/2012 የሰጠው የእግድ ትእዛዝ ለተከሳሽ ደርሶት ፈርሞ ከተቀበለ በኋላ
የፍ/ቤቱን የዕግድ ትእዛዝ ጥሶ
2. 1 ኛ የከሳሽን ቢሮ ተከሳሽ በተንጠልጣይ ቁልፍ ደርቦ በመቆለፍ
3. ተከሳሽ ተቀማጭ የሆኑ መዝገቦችን ከመዝገብ ቤት በማስወጣት ሥራ
ያስጀመረ መሆኑን ሥልጣኑን ያለአግባብ በመጠቀም የከሳሽን ቢሮ
በተንጠልጣይ ቁልፍ ደርቦ በመቆለፍ መዝገቦችን ከመዝገብ ቤት በማስወጣት
በህገወጥ አሠራር ቼክ ፔይመንት (የወጭ መመዝገቢያ ሞዴል) ወደኋላ
ተመልሶ እንዲሠራበት በመፍቀድ በከሳሽሥራ ላይ ሌላ ሠራተኛ መድቦ
እያሠራ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም በደብሩ ሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ጽ/ቤት
ባወጣው የፈተና መርሐ ግብር ተፈትኜ በውጤት ያገኘሁትን እድገት
ያለአግባብ ስልጣኑን በመጠቀም ወደቀድሞ ሥራየ እንድመለስ ለማድረግ
በመ/ቁ.789/861/2012 በቀን መጋቢት 1 ቀን 2012 ዓ.ም የተፃፈን ደብዳቤ
የካቲት 1/2012 ዓ.ም የተፃፈ አስመስሎ ስርዝ ድልዝ በመሆኑ የደብሩ
የፕሮቶኮል መዝገብ ቀርቦ እንዲመረመርልኝ አመለክለሁ፡፡
ስለዚህ ደብሩ ባወጣው የፈተና መርሀ ግብር መሠረት በውጤት ያገኘሁትን
የሥራ እድገት ወደኋላ እንድመለስ የተደረገበት ደብዳቤ የእጅ ጽሁፍ 1 ገጽ
ፎቶኮፒ አያይዤ ሳቀርብ የተከበረው ፍ/ቤት ይህን መርምሮ በሥራየ ላይ
እየተደረገብኝ ያለውን የአስተዳደር ጫና መርምሮ እንዲወስንልኝ በትህትና
አመለክታለሁ፡፡
የቀረበው አቤቱታ እውነት ነው፡፡

You might also like