Professional Documents
Culture Documents
Essential English Amharic Episode 13
Essential English Amharic Episode 13
Emily
When did you get married?
Gary
I got married in 2002.
Emily
What’s your wife’s name?
Gary
Her name’s Sarah.
ከዚያ ጋሪ ‘በ2002 ነው ያገባሁት’ ‘I got married in 2002.’ ብሎ መለሰ። ‘I got married in…’ ካላችሁ በኋላ
ዓመተ ምህረቱን በማስከተል መቼ እንዳገባችሁ መናገር ትችላላችሁ። ዓመቱን ስንናገር የመጀመሪያዎቹን ሁለት ቁጥሮች
አንድ ላይ አያይዘን አንጠራና ከዚያ ቀጣዮቹን ሁለት ቁጥሮች እናስከትላለን። ቀጣዮቹን ምሳሌዎች ያዳምጡ።
1998
2012
ነገር ግን ከ2000 እስከ 2009 ያለውን ጊዜ ስንገልፅ ሙሉውን ቁጥር አንድ ላይ ነው የምንጠራው። ቀጣዩን ምሳሌ
ያዳምጡ።
2004
2008
ኤምሊ ከዚያ ‘የሚስትህ ስም ማን ነው?’ ‘What’s your wife’s name?’ ስትል ጋሪን ጠይቃዋለች። ‘Wife’ ሚስት
ማለት ሲሆን ባል ለማለት ደግሞ ‘husband’ን እንጠቀማለን። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
በመጨረሻ ጋሪ ለኤምሊ ‘ስሟ ሣራ ነው’ በማለት የሚስቱን ስም ነግሯታል። ያዳምጡና ደግመው ይበሉ።
በጣም ጥሩ፥ አሁን የተለያዩ ሰዎች መቼ እንደተጋቡ ሲጠያየቁ ያዳምጡና እርስዎ ካሉት ጋር ያመሳክሩ።
እሺ፥ ያንን እንደገና እንሞክረው። የእንግሊዝኛ አረፍተ ነገሮቹን ያዳምጡና ደግመው ይበሉ። እያንዳንዳቸውን እንዳንድ
ጊዜ ይሰሟቸዋል።
በጣም ጥሩ! አሁን እንግሊዝኛውን ምን ያህል እንደሚያስታውሱት እንይ። አረፍተ ነገሮቹን በአማርኛ ያዳምጡና
የእንግሊዝኛ አቻቸውን ይናገሩ።
መቼ ነበር ያገባኸው?
When did you get married?
የሚስትህ ስም ማን ይባላል?
What’s your wife’s name?
ስሟ ሣራ ነው።
Her name’s Sarah.
በጣም ግሩም፥ አሁን መቼ እንዳገቡ በእንግሊዝኛ መናገር ይችላሉ። ለኤምሊ ምላሽ በመስጠት ልምምድ ያድርጉ።
በ2008 ነው ያገባኹት ይበሉና ስም ፈጥራችሁ ተጠቀሙ።
Emily
When did you get married?
Gary
I got married in 2002.
Emily
What’s your wife’s name?
Gary
Her name’s Sarah.
በጣም ጥሩ! አሁን በእንግሊዝኛ መቼ እንዳገቡ መናገር ይችላሉ። የተማሩትን ነገር መለማመድን አይዘንጉ። ጓደኛ
ይፈለጉና ልምምድ ያድርጉ። ለተጨማሪ የEssential English Conversation ዝግጅቶች በሚቀጥለው ክፍል
ይጠብቁን። ደህና ይሁኑ!