You are on page 1of 2

#አስር_ምርጥ_የኮምፒዉተር_ሶፍትዌሮች_ማዉረጃ_ዌብሳይቶች_ልጠቁማችሁ

1) Download.Com
የኮምፒዉተር ሶፍትዌሮችን ከማዉረጃ ሳይቶች ቀደምት ሲሆን ከዛሬ 14 ዓመት በፊት የተመሰረተ ነዉ፡፡ የዚህ ሳይት ባለቤት
በቴክኖሎጂዉ ዘርፍ ገናና ስም ያለዉ CNet ነዉ፡፡ ለ Windows, Mac, and Linux የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን እንዲሁም
የሞባይል አፕሊኬሽኖችን እዚህ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከ 100,000 በላይ ፕሮዳከቶችን አካቷል፡፡ ሶፍትዌሮቹ በ ኤዲተሮች
ተገምግመዉ እና ደረጃ ተሰጥቷቸዉ ተቀምጠዋል፡፡ የተመዘገቡ ተጠቃሚዎች ግምገማዎችን መፃፍ እና ለ ሶፍትዌሮቹ ደረጃ
መስጠት ይችላሉ፡፡
2) FileHippo.Com
ይህ ሳይት በብዙ ሰዎች ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፈ ነዉ፡፡ FileHippo Update Checker የሚል ፕሮግራም ያካተተ
ሲሆን ይህም በኮምፒዉተራችን ላይ የጫንናቸዉን ሶፍትዌሮች scan በማድረግ አዲስ የተሻሻለ ምርት ካላቸዉ ይጠቁመናል፡፡
ይህም ኮምፒዉተርን ከሚያጠቁ ቫይረሶች ለመከላከል እጅጉን ይጠቅመናል፡፡
3) ZDNet Download
ይህ ሳይትም እንደሌሎቹ ብዙ የ ሶፍትዌር አማራጮችን የያዘ እና በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈ ሳይት ነዉ፡፡
4) Softpedia.Com
Softpedia የሮማኒያ ዌብሳይት ሲሆን ሶፍትዌሮችን ዳዉንሎድ ማድረግ እና ስለ ሶፍትዌሮቹ ማብራሪያ መረጃዎችን
ማግኘት ያስችለናል፡፡ ከ ሶፍትዌሮቹም በተጨማሪ የ ቴክኖሎጂ፣ ጤና፣ ሳይንስ እና መዝናኛ ዜናዎችን ያገኙበታል፡፡ ሶፍትዌሮችን
በ ካታጎሪ ተቀምጠዉ ማግኘት ስለምንችል ስራችንን ያቀልልናል፡፡ ተጠቃሚዎችም በሚፈልጉት መስፈርት መፈለግ ይችላሉ፡፡
ለምሳሌ በተሻሻሉበት ቀን፣ በተጠቃሚ ብዛት፣ ሬቲንግ እና በመሳሰሉት፡፡
5) Tucows.Com
ስሙ ምህጻረ ቃል ሲሆን ይህም The Ultimate Collection Of Winsock Software ማለት ነዉ፡፡ ለ
Windows, Linux እንዲሁም ለድሮዎቹ የ Windows ቨርዢኖች የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን ያገኙበታል፡፡
6) FreewareFiles.Com
ነፃ የሆኑ ሶፍትዌሮችን በብዛት የምናገኝበት ሳይት ሲሆን ከ 15,800 በላይ ነፃ ሶፍትዌሮችን አካቷል፡፡ እነዚህን
ሶፍትዌሮችንም በ ካታጎሪ ስለተቀመጡ በቀላሉ ማግኘት እንችላለን፡፡
7) MajorGeeks
ይህ ሳይት በፊት TweakFiles በመባል ይታወቅ ነበር፡፡ አብዛኞቹ ፋይሎች አሪፍ ኢንተርፌስ ያላቸዉ እና ለተጠቃሚዎች
በቀላሉ የተገለፁ ናቸዉ፡፡ ፋይሎቹ ዌብሳይቱ ላይ ከመለጠፉ በፊት ጥራታቸዉ ይረጋገጣል ይህም ብዙዎችን ከሚያሰለቸዉ
የዉሸት ሶፍትዎሮች እንዲሁም ቫይረሶች ይጠብቅዎታል፡፡ በተጨማሪም አሪፍ ዩሰር ኮሚዩኒቲ ያለዉ ሲሆን ስለ ኮምፒዉተር
ያሉንን ጥያቄዎች ይመልሱልናል፡፡
8) FileCluster
FileCluster አሁን ላይ ከተመሰረቱ አዳዲስ ዌብሳይቶች ዉስጥ አንዱ ነዉ፡፡ ተጠቃሚዎቹም አዲስ እና የተሻሻሉ
ሶፍትዌሮችን ያገኙበታል፡፡ የ WordPress Themes፣ ዜናዎችን እና ሶፍትዌር ካምፓኒዎችንም ማግኘት ይችላሉ፡፡
9) Soft32
በ 2003 የተመሰረተ ሲሆን የ ሶፍትዌር ዳይሬክተሪዉን ቶሎ ቶሎ update በማድረግ ይታወቃል፡፡ ለ Windows, Mac,
and Linux እንዲሁም ለ ሞባይል የሚሆኑ ሶፍትዌሮች ሲኖሩት ለ iPhone ተጠቃሚዎች ብቻ ራሱን የቻለ ክፍል
አዘጋጅቷል፡፡ ከ 85,000 በላይ ሶፍትዌሮች ሲይዝ ጥያቄዎቻችንን መጠየቅ የምንችልበት ፎረምም አለዉ፡፡
10) File Horse
እንደ ሌሎቹ ሳይቶች በቁጥር ብዙ ሶፍትዌሮችን ያካተተ ባይሆንም በጣም ታወቂ እና ጥራት ያላቸዉን ሶፍትዌሮችን ያገኙበታ
#ስለ_ነፃ_ስኮላርሺፖች ዝርዝር መረጃዎች የምታገኙባቸው 5 የፌስቡክ ገፆች ልጠቁማችሁ
በለስኮላርሺፕ ዙሪያ ዝርዝር መረጃዎችን የሚያሰራጩ ብዙ የፌስቡክ ገፆች አሉ።
ከነዚህ ገፆች መካከል ለናንተ ይጠቅማሉ ያልኳቸውን የፌስቡክ ገፆች ከነ ሊንካቸው መርጨላችኋለሁ።ከናንተ የሚጠበቀው
እነዚህን ገፆች ላይክ ማድረግ ነዉ።ከዚያ በኋላ ገፆቹ አዳዲስ ስኮላርሺፖች በተመለከተ መረጃ ሲለቁ በቀላሉ መረጃዎቹ
ይደርሳችኋል።
ዛሬ ስለ ስኮላርሺፕ መረጃ ላትፈልጉ ትችላላችሁ፤ነገ ከነገ ወዲያ ደሞ ልትፈልጉ ትችላላችሁ ወይም ጓደኞቻችሁ ወይም
ከቤተሰቦቻችሁ አንዳቸው ሊፈልጉ ይችላሉ።ስለዚህ ቀጥሎ የዘረዘርኳቸው የፌስቡክ ገፆች Like እና Follow ብታደርጓቸው
ጥቅም እንጂ ጉዳት ያለው አይመስለኝም።
#ሼር_ይደረግ
1 ኛ፦ Free Scholarships
https://www.facebook.com/freescholarships/
2 ኛ፦Scholarships for international students
https://www.facebook.com/ScholarshipsAds/
3 ኛ፦Scholarship corner
https://www.facebook.com/scholarcorner/
4 ኛ፦Allscholarships
https://www.facebook.com/ScholarshipPositions/
5 ኛ፦International Scholarships
https://www.facebook.com/International.scholarships.online/
#ሼር_ይደረግ
💐#ወደ 7044 OK ብለው ቴክስት ሲያደርጉ በየቀኑ #አጫጭር_ጠቃሚ_ቴክ_ነክ_መረጃዎች ይደርሳችኋል
የዩቲዩብ ቻነሌን እግረመንገዳችሁን ሰብስክራይብ አድርጉ 👇
https://m.youtube.com/channel/UCPeUyORyXZ9tLL7okpkmETQ
የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ 👇
https://t.me/dotcomtvshow

Comments
Write a comment...

Yordanos Bedilu
Thank you
https://bimaplus.org/applications-2021-2022/form-first-
call/#HgQnMZNQShNTN1O6NbzHI0Ggs1C0nsTOHBpnyW_sr54$*

You might also like