You are on page 1of 2

ቁጥር

Ref. No. ____________________


በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ
ቀን
FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA Date________________________
በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር
Ministry of Urban Development and Construction አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ
Addis Ababa/ Ethiopia
የፌዴራል መንግሥት ሕንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት
Federal Government Buildings Construction Project Office

ለክቡር ሚኒስቴር ዴኤቴ /ኮንስትራክሽን ዘርፍ/


ከ/ል/ኮ/ሚ
ጉዳዩ፡- አዲሱ ፕሮፌሽናል ቤተ-ተውኔት ግንባታን ይመለከታል
አፍሮ-ጽዮን ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግል ማህበር የብሔራዊ ቲአትር ፕሮፌሽናል ህንጻ ግንባታ ለማከናወን ከ ፕ/ጽቤታችን ጋር
በገባዉ ዉል መሰረትእጅግ ደካማ አፈጻጸም ስለነበረዉ ይህንንም ሁኔታ ለመቀየር በርካታ ጥረትና ድጋፍ ቢደረግለትም ሊያሻሻል
ባለመቻሉ እ.ኤ.አ 26 NOV. 2020 የቅድመ ውል ማቋረጫ ደብዳቤ (Notice to Termination) መስጠታችን ይታወሳል፡፡
ይሁንና ስራ ተቋራጩ ጉዳዩ በአስተዳደራዊ ውሳኔ እንዲታይለት በቁጥር አጽኮ/04223/05/13 በቀን 28/05/2013 ለሚ/ር
መ/ቤታችን ማመልከቱ ይታወሳል፡፡ ሚኒስቴር መ/ቤታችንም በአስተዳደራዊ ውሳኔ ማየት እንዲችል አራት መሰረታዊ ቅድመ
ሁኔታዎችን በማስቀመጥ በቁጥር ፕ-250/252/1 በቀን 27/04/2013 በተጻፈ ደብዳቤ ለተቋራጩ አሳውቋል፡፡ ነገር ግን ከአራቱ
መሰረታዊ ቅድመ ሁኔታዎች በተራ ቁጥር 2 ለፕሮጀክቱ በከፍተኛ ደረጃ መጓተት ምክንያት በቂ የሥራ ማስኬጃ ገንዘብ
ባለማቅረባችሁ ስለሆነ እስከ ብር 300,000.000.- /ሶስት መቶ ሚሊዮን ብር/ ወደ ጋራ አካወንት ማስገባት ስለመቻላችሁ
ባንካችሁም ይህን ገንዘብ ወደ ጋራ አካወንት ለማስገባት ፈቃደኛ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ እንዳለባቸው እንዲያውቁት
ቢደረግም አላስፈላጊ /መሠረታዊ ያልሆነ/ የቁጥር ልዩነት በመጥቀስ ማለትም ወደ ጋራ አካወንት መግባት ያለበት 176,000,000.-
/አንድ መቶ ሰባ ስድስት ሚሊየን ብር/ እንጂ 300,000,000.- /ሶስት መቶ ሚሊዮን ብር/ እንዳልሆነ አላስፈላጊ የሆነ እና እሴት
የማይጨምር መፃፃፍ እያደረገ ይገኛል፡፡
ይሁን እንጂ ይህ ደብዳቤ እስከተጻፈበት ጊዜ ድረስ በጋራ አካወንታችን ውስጥ ገንዘብ ያልገባ ከባንካቸውም ፍቃደኝነቱን
የሚገልጽ ማረጋገጫ ያልቀረበ መሆኑን እና ይህንንም ሀሳብ ቀደም ብለን በቁጥር ፌመህ/606/2161 በቀን 24 ጥር 2013 በተጻፈ
ደብዳቤ ለስራ ተቋራጩ አሳውቀናል፡፡ አሁንም እሴት በማይጨምር የደብዳቤ መጻጻፍ ዉስጥ ከገባ የቅድመ ውል ማቋረጫ
ደብዳቤ (Notice to Termination) ከተጻፈ አራት ወራት ተቆጥረዋል፡፡ ሥራ ተቋራጩ ፕሮጀክቱን ለመቀጠል በዚህ ጊዜ ዉስጥ
በርካታ የጋራ ዉይይቶች ተከናዉነዋል ፡፡አቅምና ፍላጎት ካለዉ አራቱን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት የግድ ስለመሆኑ ከበቂ በላይ
ጊዜ ተወስዶ ተነግሮታል፡፡በመሆኑም ይህን ፕሮጀክት በዚህ ሁኔታ ለተጨማሪ ጊዜ ማቆየት ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ተጠያቂ
ስለሚያደርግ ዉሳኔ እንዲሰጥበት በትህትና እንጠይቃለን፡፡

ስልክ/ TEL ፋክስ/ Fax


0115 58 12 20 0115 58 13 00
0115 58 12 28
0115 53 03 40
ቁጥር
Ref. No. ____________________
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ
ቀን
FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA Date________________________
በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር
Ministry of Urban Development and Construction አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ
Addis Ababa/ከሠላምታ
Ethiopiaጋር
የፌዴራል መንግሥት ሕንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት
Federal Government Buildings Construction Project Office
ግልባጭ፤
ለክብርት ሚኒስቴር /ከተማ ልማትና ኮንትራክሽን
ከ/ል/ኮ/ሚ
 ለአዲስ መብራቱ አማካሪ አርኪቴክቶች እና መሀንዲሶች
አዲስ አበባ
 ለፌዴራል መንግሥት ህንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት
 ለምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ
 ለፕሮጀክትና ኮንትራት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
ፌ/መ/ህ/ግ/ፕ/ጽ/ቤት

ስልክ/ TEL ፋክስ/ Fax


0115 58 12 20 0115 58 13 00
0115 58 12 28
0115 53 03 40

You might also like