Accelerated School Transformation Strategy

You might also like

You are on page 1of 88

ትምህርት ቤቶችን በተፋጠነ መንገድ ወደ

ተፈላጊው ደረጃ (Accelerated School


Transformation) ለማሸጋገር የተዘጋጀ
ስትራቴጂ

ትምህርት ሚኒስቴር

ህዳር 2011 ዓ.ም


1
ማውጫ
በ2011 ዓ.ም የትምህርት ቤት ደረጃ ለማሻሻል የተዘጋጀ ስትራቴጂ ..................................................... 1
ክፍልአንድ .................................................................................................................................................... 3
አጠቃላይ ሁኔታ........................................................................................................................................... 3
1. መግቢያ ............................................................................................................................................ 3
2. የደረጃ ማሻሻያ ስትራቴጂ አስፈላጊነት፣ አበይትና ዝርዝር ዓላማ .............................................. 5
2.1. የደረጃ ማሻሻያ ስትራቴጂ አስፈላጊነት ................................................................................. 5
2.2. ዋና ዓላማ .................................................................................................................................. 5
2.3. ዝርዝር ዓላማዎች..................................................................................................................... 5
ክፍል ሁለት ................................................................................................................................................. 6
2. ነባራዊ ሁኔታ ዳሰሳ ................................................................................................................................ 6
2.1. የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ዳራ ................................................................................... 6
2.2. ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የተደረጉ ጥረቶች ............................................................... 7
2.3. ትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል ሂደት የተመዘገቡ ስኬቶች ......................................... 9
2.4. ትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል ሂደት የታዩ ተግዳሮቶች .......................................... 10
2.5. ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ..................................................................................................... 11
ክፍል ሦስት................................................................................................................................................ 12
3. የአጠቃላይ ትምህርት የውጭ ኢንስፔክሽን ውጤት የግብዓት፣የሂደት እና የውጤት
ስታንዳርዶች ትንተና ................................................................................................................................ 12
3.1. የግብዓት ስታንዳርዶች ትንተና................................................................................................... 12
3.2. የሂደት ስታንዳርድ ....................................................................................................................... 32
ክፍል አራት ............................................................................................................................................... 78
4. የድርጊት መርሃ ግብር እና የክትትልና ድጋፍ ስርዓት ............................................................ 78
4.1. የድርጊት መርሃ ግብር .......................................................................................................... 78
4.2. የክትትልና ድጋፍ ስርዓት .................................................................................................... 80

4.3. የክትትልና ድጋፍ መዋቅራዊ አካሄ ......................................................................................... 82


4.4. የሚያስፈልግ በጀት................................................................................................................ 83

2
ክፍልአንድ

አጠቃላይ ሁኔታ

1. መግቢያ

የሀገራት ማህበራዊ፣ ኦኮኖሚዊና ፖለቲካዊ የእድገት ደረጃን ከሚወስኑ መሰረታዊ አበይት


ጉዳዮች አንዱና ዋንኛው ትምህርት መሆኑን አያጠያይቅም፡፡ የበለጸጉ ሀገራት ከእድገታቸው
ጀርባ ያለው ሚስጥር የተፈጥሮ ሀብታቸው ሳይሆን በዋንኛነት የሰለጠነና ብቁ የሰው ሃይላቸው
ነው፡፡ ለዚህም ነው ሀገራት ለትምህርት ዘርፍ ልማት ትኩረት በመስጠት ሰፊ ኢንቨስትመንት
በማካሄድ ላይ የሚገኙት፡፡ ነገር ግን መዋለንዋይ ለትምህርት ዘርፍ ልማት ማዋላቸው
ብቻውን በቂ ነው ተብሎ አይወሰድም፡፡ በተለይም ድሃ ሀገራት ከሚያመነጩት ኢኮኖሚ
አንጻር ቀላል የማይባል ሀብት የሚመድቡ ቢሆንም በመደቡት መዋለ ንዋይ ልክ ግን
የትምህርቱ ዘርፍ ለሀገራቸው ሁለንተናዊ ልማት አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ እንዳልሆነ
የተለያዩ ዓለም አቀፍ ጥናት ያሳያል፡፡ በተለይም በ2016/17 በዓለም አቀፍ የትምህርት
ኮሚሽን (Global Education Commission) አማካይነት በሰባ ሀገራት የተጠኑ በርካታ
ጥናቶች የሚያሳዩት ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ላቸው ሀገራት ለትምህርት ዘርፍ ልማታቸው
ከሚመድቡት በጀት ውስጥ ከ50% በላይ አንድም ውጤት በማመጡ ጉዳዮች ላይ የሚመድቡ
ሲሆን በሌላም መልኩ በጀቱ በተለያየ ምክንያት ለታለመለት ዓላማ የማይውልና ለከፍተኛ
ብክነት የተጋለጠ ነው፡፡

ሀገራችንም ለትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ከምታመነጨው ጥቅል ሀገራዊ


ምርት ከ5% ያላነሰና ከመንግስት ዓመታዊ ወጪ ከ23% ያላነሰ በጀት የምትመድብ ቢሆንም
በዚሁ ልክ ጥራት ያለው ትምህርት በፍትሃዊነት የመስጠት አቅሟ ግን እንብዛም አይደለም፡፡
ለዚህ ዝቅተኛ አፈፃፀም የተለያዩ ምክንያቶች የሚጠቀሱ ቢሆንም በዋንኛነት የትምህርት
ቤቶቻችን ውጤታማ አገልግሎት በብቃት የመስጠት አቅምና ትኩረት ሰጥተው
አለመንቀሳቀስ መሆኑን አሌ አይባልም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከተቀመጠው ስታንዳርድ አንጻር
ከ90% ያላነሱ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ከ83% ያላነሱ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት
ቤቶች ከስታንዳርዱ በታች መሆናቸው የአገልግሎት አሰጣጣቸውን ለማሻሻል የሚያደርጉት
ርምጃን የሚያደናቅፍ መሆኑን በርካቶች ይስማሙበታል። ከዚህ አንፃር ባለፉት
ሰባት/ስምንት ዓመታት የትምህርት ቤቶችን አገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻልና ትምህርት
ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቀ እንዲሆኑ የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ተዘጋጅቶ
መተግበሩ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ትምህርት ቤቶች ከግብአት፣ ከሂደትና ከውጤት አንጻር

3
ትምህርት ቤቶች በራሳቸው የውስጥ አሰራራቸውን በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት
ፈትሸውና በውጫዊ አካል በሚደረግላቸው የኢንስፔክሽን ውጤት መሰረት የትምህርት ቤት
ማሻሻያ እቅድ እንዲያዘጋጁ ይጠበቃል። ከዚህ አንጻር ከ2006 ዓ/ም ጀምሮ ሁሉም ትምህርት
ቤቶች ቢያንስ አንድ ጊዜ በውጭ አካል ኢንስፔክሽን ተደርጎላቸዋል። ነገር ግን በዚሁ ልክ
የተቀመጡ ስታንዳርዶችን በአግባቡ በመተንተንና ውጤት በሚያመጡ አበይት ጉዳዮች ላይ
አተኩሮ ከመስራት አንጻር በርካታ ትምህርት ቤቶች አሁንም ደረጀቸውን ለማሻሻል ሙከራ
ቢያደርጉም ውጤታቸው ግን ቀድሞ ከተገመገሙበት ደረጃ አንፃር ፈቀቅ የማላቸው ሁኔታ
ግን እንብዛም አይደለም፡፡

ይህን ሁኔታ ለመቀልበስ በተለያዩ አካላት የተለያዩ ሙከራዎች ባለፉት ሁለት ዓመት
በሙከራ ደረጃ በመተግበር ላይ ይገኛል። በዚህ የሙከራ ፕሮጀክት ትግበራ ከተወሰዱ
ትምህርቶች መካከል አንዱና ዋንኛው ትምህርት ቤቶችን ወደ ተፈላጊው ስታንዳርድ
ለማድረስ በዋንኛነት የትምህርት ቤት አመራሮች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ነው፡፡ በተለይም
የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማውጣት ከተቀመጡ 26 ስታንዳርዶች ውስጥ 85%ቱ ሰፊ
ካፒታል የማይጠይቁና በርዕሰ መምህሩ መሪ ተዋንያንነት መተግበር የሚችሉ መሆናቸው
ታይቷል።

በዚህም መሰረት ትምህርት ሚኒስቴር ከተለያዩ መንግስታዊ አካላት አማካይነት የትምህርት


ቤቶችን ደረጃ ከማሻሻልና የተማሪዎችን ውጤት በከፍተኛ ደረጃ ከማሳደግ አንፃር የተገኘውን
ተሞክሮ መነሻ በማድረግ ትምህርት ቤቶችን በፍጥነት ወደ ተቀመጠላቸው ስታንዳርድ
እንዲደርሱ ለማድረግ የተፋጠነ የትምህርት ቤቶች ሽግግር ስትራቴጂ በማዘጋጀት በርካታ
ትምህርት ቤቶችን ወደ ስታንዳርዱ ለማስጠጋት የሚያስችል ሰነድ እንደሚከተለው የተዘጋጀ
ሲሆን ሰነዱ በክፍል አንድ አጠቃላይ ነበራዊ ሁኔታ፣ ትምህርት ቤቶችን ወደ ስታንዳርዱ
ለማስጠጋት ያለውን አስፈላጊነት፣ ዓላማ፣ በቀጣይ የሚጠበቅ ውጤትና መሰል ጉዳዮችን
ይዟል። በክፍል ሁለት የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ታሪካዊ ዳራን የያዘ ሲሆን
በዚህም ትምህርት ቤቶችን ከማሻሻል አንጻር ባለፉት ዓመታት የተሄደበት ርቀት፣ በጥንካሬና
በእጥረት የተለዩ ጉዳዮችና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን ይዟል። በክፍል ሶስት
የትምህርት ቤት መሻሻል ስትራቴጂ ማእቀፍ፣ የትምህርት ቤት ደረጃ ስታንዳርድን
በግብአትና በሂደት በመተንተን ትምህርት ቤቶችን ወደ ስታንዳርዱ ለማስጠጋት የሚከናወኑ
ተግባራትን ይዟል። በክፍል አራት ትምህርት ቤቶችን ወደ ስታንዳርዱ ከማስጠጋት አንፃር
የትምህርት ስርዓቱ በቀጣይ ባሉት ወራት የሚያከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራትና የክትትልና
ድጋፍ ስርዓትን በማስቀመጥ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።

4
2. የደረጃ ማሻሻያ ስትራቴጂ አስፈላጊነት፣ አበይትና ዝርዝር ዓላማ

2.1. የደረጃ ማሻሻያ ስትራቴጂ አስፈላጊነት

ትምህርት ቤቶችን ወደ ተፈላጊው ስታንዳርድ በማስጠጋት የተማሪዎችን ውጤትና


የመማር ውጤትን ማሳደግ ለትምህርት ዘርፉ የተሰጠው ከፍተኛ ተልእኮ መሆኑ
አያጠያይቅም። በተለይም ሀገራችን አሁን ካለችበት የለውጥ እንቅስቃሴና ህብረተሰቡ
በፍጥነት ሊመለስለት ከሚገቡ ጥያቄዎች ውስጥ ተደጋግሞ ከሚነሱ ጉዳዮች አንዱ ጥራት
ያለው ትምህርት ተጠቃሽ ነው፡፡ በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር በአዲሱ አደረጃጀት
ለህብረተሰቡ ምላሽ ለመስጠት ካስቀመጣቸው አበይት የትኩረት መስኮች አንዱ ትምህርት
ቤቶችን ወደ ስታንዳርዱ በማስጠጋት የተማሪዎችን ውጤት በከፍተኛ ደረጃ ማሻሻል አንዱ
ነው፡፡ ስለሆነም በያዝነው የትምህርት ዘመን ቢያንስ ከ10%-20% ትምህርት ቤቶችን በልዩ
ትኩረት

2.2. ዋና ዓላማ

የትምህርት ቤት አመራሩን አቅም በማሳደግና የተጠናከረ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ


ትምህርት ቤቶችን ወደ ስታንዳርዱ ማስጠጋት የዚህ ስትራቴጂ ዋና ኣላማ ተደርጎ
ይወሰዳል።

2.3. ዝርዝር ዓላማዎች

• የትምህርት ቤቶችን አመራር አቅም ማሳደግ


• መምህራን በክፍል ውስጥ ህይወት ያለው የመማር ማስተማር ሂደት ማካሄድ
እንዲችሉ ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ እንዲያገኙ ማድረግ
• የትምህርት ቤቶችና ህብረተሰቡን ግንኙነት ማጠናከር
• በቀጣይ የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ማእቀፍን በማሻሻል የሀገራችን
ትምህርት ቤቶች ተልእኳቸውን በብቃት ለመወጣት የሚያስችለውን አቅም መፍጠር

5
ክፍል ሁለት

2. ነባራዊ ሁኔታ ዳሰሳ

2.1. የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ዳራ

በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ታቅደው በሁሉም የመጀመሪያ


ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ ትም/ቤቶችና አማራጭ መሠረታዊ ትምህርት ጣቢያዎች
በመከናወን ላይ ካሉ ተግባራት መካከል የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ
ዋነኛው ነው። ፓኬጁ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ሲሆን በፓኬጁ
ከተካተቱት ዋና ዋና መርሀ-ግብሮች/ፕሮግራሞች መካከል ሁሉን አቀፍ በሆነ መልኩ በሁሉም
ትምህርት ቤቶች በመተግበር በተማሪዎች የትምህርት ውጤትና ስነ-ምግባር ላይ መሻሻልን
ለማምጣት ታወዶ በመተግበር ላይ ያለው የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ነው፡፡

ምንም እንኳን ፕሮግራሙ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ በሀሉም ሀገሪቱ በሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ
እና የሁለተኛ ደረጃ ትም/ቤቶችና አማራጭ መሠረታዊ ትምህርት ጣቢያዎች እየተተገበረ
ሲሆን ፕሮግራሙ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን በባለቤትነት ይዞ የሚመራና የሚያስተባብር
አካል በማስፈለጉ የትምህርት ሚኒስቴር በመስከረም 2007 ዓ.ም በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ
ስር የሚመራ የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ዳይሬከቶሬትን አቋቁማል።

በመሆኑም የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም በዋናነት በሁሉም ትምህርት ቤቶች


በትምህርት ቤት መሻሻል ዕቅድ ዝግጅት፣ አተገባበር እና ተያያዥነት ያላቸው ተግባራትን
እንዲሁም በትምህርት ቤት ድጎማ በጀት ምደባ፣ ስርጭትና አጠቃቀም ላይ አተኩሮ
በመስራት ላይ ይገኛል።

6
2.2. ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የተደረጉ ጥረቶች

የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ዋነኛ ትኩረት የተማሪዎች መማር እና የመማር ውጤት


ላይ ሲሆን ለዚህም ስኬት ትምህርት ቤቶች በቅድሚያ ደካማ እና ጠንካራ ጐናቸውን
በመለየት፣ በእያንዳንዱ የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም አበይት ርዕሰ ጉዳይ አንፃር
ቅድሚያ ትኩረት በማውጣት እና ግብ በማስቀመጥ ሁሉም የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ
አባላትና ሌሎች ባለድርሻዎች ለተማሪዎቹ መማርና የመማር ውጤቶች ከፍተኛ መሆን
የሚንቀሳቀሱበት የማያቋርጥ ሂደት ነው።

• ይህንን ሂደት ለማገዝ እንዲቻል የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት


ለፕሮግራሙ ተፋጻሚነት አጋዥ የሆኑና የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ላይ የታቀዱ
ዓላማዎችን በሚያሳካ መልኩ እንዲከናወን ሀገር አቀፍ ማዕቀፎችን፤ ሰታንዳርዶችንና
መመሪያዎችን ወዘተ… የሚመለከታቸው ባላድርሻዎች ባሳተፈ መልክ አዘጋጅቶ
በአገሪቷ የሚገኙ ተቋማቱ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ናቸው።
• በየተቋማቱ ወቅታዊ የሆኑ ግምገማ ስራዎችን ማከናወን፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን
መቀመርና ማስፋፋት፣ በየደረጃው የክትትልና ድጋፍ ሥራዎችን ማከናወን፤
• በትምህርት ቤት ደረጃ ለመምህራን፣ ለተማሪዎች፣ ለወላጆችና ለህብረተሰቡ፣
እንዲሁም ለአስተዳደር ሠራተኞች ስለፕሮግራሙ ምንነት፣ ዓላማና ጠቀሜታ
አስቀድሞ ሥልጠና በመስጠት የሁሉንም የጋራ ተሳትፎ በማስተባበር በጋራ
መንቀሳቀስ፣
• በትምህርት ሚኒስቴር ደረጃ ፤ ከክልሎችና ከባለድርሻ አካለት በተለያዩ ጊዜያት
ከተካሄዱ ከመስክ ምልከታና ሪፖርት የተገኙ መረጃዎችን መሰብሰብ፣ ማደራጀት፣
ማጠናቀርና መተንተን፣ በሚገኝ ግብረመልስ አሰራሮችን ማሻሻልና መረጃዎች
በመሰብሰብ ስራ ላይ ማዋል፤
• በሥራ ሂደት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ከዚሁ ጋር በተያያዘም ዓመታዊ ሪፖርቶችንና
ስታስቲካዊ መረጃዎችን ማዘጋጀት፤
• የምክከር መድረክ በማዘጋጃት ውይይት በማካሄድ ከመግባባት የተደረሰባቸውን
ሰምምነቶች ስልት ቀይሶ ሥራ ላይ እንዲውል ለሚመለከታቸው ተቋማት እንዲሰራጩ
ማድረግ፤

7
• አጋዥ የሆኑ የሥልጠና ሞጁሎች ማዘጋጀት፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን
ማዳበር፤ በየደረጃው ላሉ ባለሙያዎች፣ ለሱፐርቫይዘሮች፣ ለርዕሰ መምህራንና
ለመምህራን ሥልጠናና ሙያዊ ድጋፍ መስጠት፤
• አለም አቀፍና ሀገር አቀፍ መልካም ተሞክሮዎችን በመቀመር ማሰራጨት፤
ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር ዐውደ ጥናት ማዘጋጀት፤ የተገኙ
ውጤቶችን ከክልሎች ጋር በመሆን መተግበር፤

• ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በሁሉም ደረጃዎች የትምህርት አስተዳደሩንና


አመራሩን ብቃትና የሥራ ቅልጥፍና ለማሳደግ የሚያስችሉ ስልቶችን በመንደፍ
ተግባራዊ ማድረግ፤

• ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ምቹ የትምህርት ሁኔታና አካባቢ እንዲኖር እንዲሁም


የተማሪዎችን የትምህርት ፍላጎትና የፈጠረና ችሎታን የሚያበረታቱ ስልቶችን
በመንደፍ ተግባራዊ ማድረግ፤

• ወላጆችና ኅብረተሰቡ ለትምህርት ያላቸውን ግንዛቤ በተለያዩ ዘዴዎች በማሳደግ


ተሳትፎአቸውን ማጐልበትና ለትምህርቱ ሥራ የባለቤትነት መንፈስ እንዲኖራቸው
የሚያስችሉ ስልቶችን በመንደፍ ተግባራዊ ማድረግ፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የተገኙ
ውጤቶችን በተመለከተ መረጃ መያዝ፤ ማጠናቀርና ለሚመለከታቸው ማቅረብ፤

• ለትምህርት ቤቶች ደረጃ ለማሳደግ አስፋላጊ የሆኑ ሀብቶችን ማለትም የት/ቤቶች


ድጎማ በጀት፤የውስጥ ገቢ ጥቅል በጀት ወዘተ… አመዳደብን፣ ስርጭትና አጠቃቀምን
በፋይናንስ ደንብ በትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ቅድሚያ ለተሰጣቸው ተግባራት
ተግባራዊ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ፤

• የትምህርት ተሳትፎን ለማሳደግ የሚያስችሉ የህዝብ ንቅናቄ መድረኮችን


በማዘጋጀንና መድረኮቹ በየደረጃው እስከ ቀበሌና ትምህርት ቤቶች ድረሰ እንዲካሄዱ
የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን በማከናወን፤
• የትምህርት ተሳትፎን ለማሳደግ የሚያስችሉ የህዝብ ንቅናቄ መድረኮችን
በማዘጋጀንና መድረኮቹ በየደረጃው እስከ ቀበሌና ትምህርት ቤቶች ድረሰ እንዲካሄዱ
የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን በማከናወን፤

8
• በየክልሎች በሚገኙ በናሙና የትምህርት ተቋማት በመገኘት ስለፕሮግራሙ አፈፃፀም
ደረጃቸውን ያሳደጉ ትምህርት ቤቶች የተጓዙበትን ሂደት የሚገልጽ ሪፖርት
በማዘጋጀት ሌሎች እንደአካባቢያቸው ሁኔታ አንዲጠቀሙ በማሠራጨትና ድጋፍና
ክትትል ተደርጓል። ለሌሎች አርአያ እንዲሆኑና ሥራቸውም ቀጣይነት እንዲኖረው
ለማስቻል ደረጃቸውን ለሳደጉ ተቋማት ማበረታቻ እንዲሰጣቸው በማድረግ

• በአምስተኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት ለመርሀ ግብሩ የተቀመጠውን ዕቅድ


ከመፈጸም አንጻር ከዳይሬክቶሬቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ባለ-ብዙ ዘርፍ ጉዳዮች
/cross cutting issues/ ማለትም የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራምና በአደጋ ጊዜ
ትምህርት ማስቀልንና ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል።

2.3. ትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል ሂደት የተመዘገቡ ስኬቶች

መ/ቤታችን የትምህርት ጥራቱን በይበልጥ አጠናክሮ ለማቀጠል እንዲቻል ከ1999 ዓ.ም


ጀምሮ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ ተቀርፆ እየተተገበረ ይገኛል።

በዚህም በርካታ የትምህርት ተቋማት ለትምህርት ጥራት አስፈላጊ የሆነ መደላደል


በማመቻቸት ባደረጉት ጥረት እያስመዘገቡ ያለው ውጤት በተለመደው አሰራር ሲያከናወኑ
ከነበረበት ወቅት ጋር ሲነፃፀር የተማሪዎችን ውጤትና ስነ ምግባርን በማሻሻል ረገድ የተሻለ
መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ። በመሆኑም

1. በ2010 ዓ.ም በትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም አፈጻጸምና በትምህርት ቤት


ድጎማ በጀት አጠቃቀም ላይ የተካሄደው ጥናት እንደተመለከተው ቀደም ሲል የተሟላ
የ3 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ እና አመታዊ ዕቅድ ያላዘጋጁ ትምህርት ቤቶች ባላድርሻዎችን
አሳትፈውና ግለ-ግምገማ አድርገው ያዘጋጁ ት/ቤቶች የ2ኛ ደረጃ (9-10) ት/ቤቶች 93.3
በመቶ፣ የ2ኛ ደረጃ መሰናዶ (11-12) ት/ቤቶች 100 በመቶ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች 95
በመቶ እና የአማራጭ መሰረታዊ ትምህርት ጣቢያዎች 52.2 በመቶ ደርሰዋል።
2. መረጃን መሰረት ያደረገ የት/ቤት መሻሻል ዕቅድ ያዘጋጁ ት/ቤቶች የ2ኛ ደረጃ (9-10)
ት/ቤቶች 100 በመቶ፣ የ2ኛ ደረጃ መሰናዶ (11-12) ት/ቤቶች 100 በመቶ፣ የመጀመሪያ ደረጃ
ት/ቤቶች 90.6 በመቶ እና የአማራጭ መሰረታዊ ትምህርት ጣቢያዎች 41.3 በመቶ
ደርሰዋል።

9
3. በጥናቱ እንደተጠቀሰው የተሻሻለ የት/ቤቶች ድጎማ በጀት መመሪያን በክልላቸው ቋንቋ
ተርጉመው የሚተገብሩ ት/ቤቶች የ2ኛ ደረጃ (9-10) ት/ቤቶች 83.3 በመቶ፣ የ2ኛ ደረጃ
መሰናዶ (11-12) ት/ቤቶች 83.3 በመቶ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች 65.9 በመቶ እና
የአማራጭ መሰረታዊ ትምህርት ጣቢያዎች 56.5 በመቶ እንደደረሱ ለማወቅ ተችሏል።
4. በተሻሻለው የትምህርት ቤት ድጎማ በጀት መመሪያ መሠረት የበጀት አጠቃቀም የቅድሚያ
ተግባራት ዕቅድ አዘጋጅተው የሚተገብሩ ት/ቤቶች የ2ኛ ደረጃ (9-10) ት/ቤቶች 96.7 በመቶ፣
የ2ኛ ደረጃ መሰናዶ (11-12) ት/ቤቶች 100 በመቶ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች 93.3 በመቶ
እና የአማራጭ መሰረታዊ ትምህርት ጣቢያዎች 78.3 በመቶ ደርሰዋል። ይህም የሚያሳየው
ትምህርት ቤቶች የተመደበላቸውን በጀት በአግባቡ ስለሚጠቀሙ ይህም የትምህርቱን ሥራ
ለማሳከት ድርሻ ያለው መሆኑን ነው።
5. በሌላ በኩል በት/ቤት መሻሻል ፕሮግራም ዕቅድ ዝግጅትና የት/ቤቶች ድጎማ በጀት አጠቃቀም
ላይ ወተመህን በማሳተፍ የሚሰሩ ት/ቤቶች የ2ኛ ደረጃ (9-10) ት/ቤቶች 96.7 በመቶ፣ የ2ኛ
ደረጃ መሰናዶ (11-12) ት/ቤቶች 100 በመቶ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች 94.6 በመቶ እና
የአማራጭ መሰረታዊ ትምህርት ጣቢያዎች 80.4 በመቶ ደርሰዋል።ይህም የሚያሳየው
ማህበረሰቡ ከተቋማቱ ጋር በቅርበት የሚሰራ መሆኑን ነው።
6. በተሻሻለው የትምህርት ቤት ድጎማ በጀት እንደተመለከተው የት/ቤቶች ድጎማ በጀትን 50
በመቶ ለመማር ማስተማር ርዕሰ ጉዳይ ያዋሉ ት/ቤቶች የ2ኛ ደረጃ (9-10) ት/ቤቶች 96.7
በመቶ፣ የ2ኛ ደረጃ መሰናዶ (11-12) ት/ቤቶች 100 በመቶ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች
86.3 በመቶ እና የአማራጭ መሰረታዊ ትምህርት ጣቢያዎች 73.9 በመቶ ደርሰዋል።ከዚህ
መረዳት የሚቻለው ትምህርት ቤቶች ለመማር- ማሰተማር ሥራ ትኩረት ሰጥተው የሚሰሩ
መሆናቸውን መረዳት ይቻላል።
7. የት/ቤቶች ድጎማ በጀት መጠን፣ የአጠቃቀም ዕቅድና የህብረተሰብ ተሳትፎ በተመለከተ
በማስታወቂያ ሰሌዳ በግልጽ ለሁሉም በሚታይ ቦታ የለጠፉ ት/ቤቶች የ2ኛ ደረጃ (9-10)
ት/ቤቶች 50 በመቶ፣ የ2ኛ ደረጃ መሰናዶ (11-12) ት/ቤቶች 50 በመቶ፣ የመጀመሪያ ደረጃ
ት/ቤቶች 48.8 በመቶ እና የአማራጭ መሰረታዊ ትምህርት ጣቢያዎች 8.7 በመቶ
ደርሰዋል።ከዚህ መረዳት የሚቻለው ተቋማት ያላቸውን ሀብት የማህበረሰቡ ዕውቅና ባላቸውና
ግልጽ በሆነ መንገድ ሥራ ላይ የሚያውሉ መሆናቸውን ነው።

2.4. ትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል ሂደት የታዩ ተግዳሮቶች

የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም በዳይሬክቶሬት ደረጃ ተቋቁሞ መስራት ከጀመረበት


ጊዜ ጀምሮ በርካታ ተግዳሮቶች ያጋጠሙት ሲሆን በዋናነት ከሚጠቀሱት መካከል አደረጃጀቱ

10
በተመሳሳይ መልኩ በክልሎች ሳይቋቋም በመቆየቱ ለክትትልና ድጋፍ ስራዎችን ለማከናወን
አመቺ ሁኔታ ያልነበረ መሆኑ፣ በትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ዕቅድ አፈጻጸም ላይ
ከክልሎች መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ መሆኑ፣ በት/ቤት መሻሻል ፕሮግራም የሚሰጡ የአቅም
ግንባታ የአሰልጣኞች ስልጠናዎች በተዋረድ ለወረዳና ለት/ቤቶች በተፈለገው መጠን
አለመውረዳቸው፣ በዳይሬክቶሬቱ የታቀዱ በርካታ ተግባራትን ለማከናወንና በክልሎች በመገኘት
ተገቢውን ድጋፍ፣ ክትትልና ግምገማ ለማድረግ የዳይሬክቶሬቱ የሰው ሀይል ቁጥር አናሳ መሆኑ
የሚጠቀሱ ናቸው።

2.5. ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ

የትምሀርት ቤቶችን ደረጃ ለማሳደግ በየደረጃው ባሉ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት


የተጀመረው ጥረት የሁሉንም አስተዋዕጾ የሚጠይቅ ስለሆነ ተቋማቱ ያሉበትን ሁኔታ
በአግባቡ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉ በማሳተፍ ያለባቸውን ዕጥረት በመለየት በየደረጃው
በአቅም ደረጃ ማደረግ ያለበትን በብቃት ማከናወን ትልቁ ተግባር መሆን አለበት። በዘህ
መሰረት

• በተቋማቱ የተከናወኑ ተግባራትን በየጊዜው ድጋፍና ክትትል በማድረግ የተጀመሩ


ተግባራት ተጠናክረው እንዲከናወኑ ማድረግ እንዲሁም ግብረ-መልስ
ለሚያሰፈልጋቸው ጉዳዮች ወቅታዊ ምላሽ በመስጠት ሂደቱ ተጠናክሮ እንዲካሄድ
ማድረግ።
• በየደረጃው ያለውን የአቅም ክፍተት በመለየትና ለሂደቱ ማሳካት አሰተዋዕጾ ሊያደርግ
የሚችል ሥልጠናና የምክክር አውደ ጥናት በማካሄድና ስልት በመቀየስ ይህንኑ
ተግባራዊ እንዲያደርጉ በየደረጃው ያሉ የትምህርት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የቅርብ
ድጋፍና ክትትል ማደረግ ይገባቸዋል።
• ለሂደቱ አስተዋዕጾ ሊያደርጉ የሚችሉ መልካም ተሞክሮዎችን የተሻለ አፈጻጸም
ካላቸው ተቋማት መረጃዎች በማሳበሰብን በመጠናቀር ሪፖርቱን ለትምህርት ቤቶች
እንደአካባቢያቸው ተጨባጭ ሁኔታ አንዲጠቀሙ ማሰረጨት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች
ናቸው።

11
ክፍል ሦስት

3. የአጠቃላይ ትምህርት የውጭ ኢንስፔክሽን ውጤት የግብዓት፣የሂደት


እና የውጤት ስታንዳርዶች ትንተና

3.1. የግብዓት ስታንዳርዶች ትንተና

ስታንዳርድ1: - ትምህርት ቤቱ ለደረጃው በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት የመማሪያ እና


የመገልገያ ህንፃዎች፣ ፋሲሊቲዎች ፣ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች እና
የማስፈጸሚያ ሰነዶች አሟልቷል፡፡

ይህ ስታንዳርድ የትምህርት ቤቱ ምድረ ግቢና በትም/በቱ የሚገኙ የተለያዩ የአገልግሎት


መስጫ ክፍሎች በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት መገንባታቸውን እንዲሁም የስፖርት ሜዳ፣
ቁሳቁሶች፣ የመማሪያና ማስተማሪያ መጻህፍቶች መሟላታቸውን የሚመለከት ነው።

12
ሰንጠረዠ 1፡ ከ2009-2010 ዓ.ም በተካሄደው የዳግም ኢንስፔክሽን ትም/ቤቶች
በስታንዳርድ 1 ያስመዘገቡት ውጤት ትንታኔ

የ2009 እና የ2010 ዓ.ም የዳግም ኢንስፔክሽን ውጤት ትንተና


ደረጃ 3 ደረጃውን
እና 4 ያሟሉ
ደረጃ ደረጃ ደረጃ %( ደረጃ % (ደረጃ
ደረጃ 1 ድምር ትምህርት ትምህርት
2 33 4 1) 2)
ቤቶች ቤቶች
ክልል ቁጥር በመቶኛ
ሃገር አቀፍ 13906 8434 778 23 23141 60.09 36.45 801 3.46
አዲስ አበባ 217 479 110 2 808 26.86 59.28 112 13.86
አፋር 260 67 3 330 78.79 20.30 3 0.91
አማራ 3505 3136 302 12 6955 50.40 45.09 314 4.51
ቤኒሻንጉል
ጉሙዝ 295 112 16 0 423 69.74 26.48 16 3.78
ድሬዳዋ 36 36 14 86 41.86 41.86 14 16.28
ሶማሌ 213 22 3 238 89.50 9.24 3 1.26
ጋምቤላ 8 7 1 16 50.00 43.75 1 6.25
ሀረሪ 9 14 1 24 37.50 58.33 1 4.17
ኦሮሚያ 7340 3524 231 5 11100 66.13 31.75 236 2.13
ደቡብ 1613 724 76 2 2415 66.79 29.98 78 3.23
ትግራይ 410 314 21 745 55.03 42.15 21 2.82
ሀ/ በሀገርአቀፍ ደረጃ

ከላይ በሠንጠረዡ እንደተመለከተው ከ2009-2010 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ድጋሜ


ኢንስፔክሽን ከተካሄደባቸው 23141 ትምህርት ቤቶች ውስጥ በስታንዳርድ 1 ደረጃቸውን
ያሟሉት ማለትም ደረጃ 3 እና ደረጃ 4 ላይ የተፈረጁት (3.46%) ወይም 801 ትም/ቤቶች
ብቻ መሆናቸውን መረዳት ይቻላል፡፡ ይህ ማለት እጂግ በርካታ ትም/ቤቶች ከስታንዳርዱ
አኳያ ከደረጃ በታች መሆናቸውንና በቀጣይ ቤደረጃው ያለ አካል ጠንካራ ስራ በመስራት
ትምህርት ቤቶች በዚህ ስታንዳርድ የተሸለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ መደረግ አለበት፡፡

ለ/ በክልል ደረጃ

በዚህ ስታንዳርድ የክልሎችን አፈጻጸም ስንመለከት ምንም እንኳን በሁሉም ክሎልሎች


የሚገኙ ትም/ቤቶች በስታንዳርድ 1 ላይ ያስመዘገቡት ውጤት እጂግ ዝቅተኛ ቢሆንም
በአንጻራዊነት በተሻለ መልኩ ስታንዳርዱን ያሟሉ (ደረጃ 3 እና 4) የገቡ ትም/ቤቶች ከሃገር
አቀፉ ማለትም ከ(3.46%) በላይ አፈጻጸም ያላቸው ድሬዳዋ (16.28%)፣ አዲስ አበባ

13
(13.86%) ሲሆኑ ከሃገር አቀፉ በታች አፈጻጸም ያላቸው አፋር (0.91%)፣ ሶማሌ (1.26%)፣
ኦሮሚያ (2.13%) እና ትግራይ (2.82%) ትም/ቤቶች ብቻ ስታንዳርድ አንድን ያሟሉ ሲሆኑ
የሌሎች ክልሎች አፈጻጸም በመካከል የሚፈረጂ እንደሆነ መረጃው ያመለክታል።

ሐ/ ተጠቃሽ የሆኑ ችግሮች (ገላጭና አመላካች)

በሃገር አቀፍ ደረጃ (96.54%) ትምህርት ቤቶች በስታንዳርድ 1 ከደረጃ በታች ሲሆኑ በክልል
ደረጃ በተለይም በአፋር (99.09%) ፣ ሶማሌ (98.74%)፣ ኦሮሚያ (97.87%) እና በትግራይ
(97.18%) ትምህርት ቤቶች በስታንዳርድ 1 ከደረጃ በታች ሆነዋል ለዚህም እንደችግር
ሊጠቀሱ የሚችሉት፡-

• አዳዲስ ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ እውቅና ሲሰጣቸው የወረዳ፣ የዞን እንዲሁም


የክልል አመራሮች የህዝብ ጥያቄን ለመመለስ ብቻ እንጂ ስታንዳርዱ እንዲጠበቅ
አለማድረጋቸው፡
• የትም/ቤት ር/መምህራን እና የት/ቤቱ ማህበረሰብ መማሪያ ክፈሎችና ልዩ ልዩ
አገልግሎት ሰጭ ክፍሎች ወደ ስታንዳርዱ እንዲመጡ ችግሩን እየለዩ መፍተሄ
አለመስጠት
• የትም/ቤት ር/መምህራን ፋይናንስ አመንጭቶ ለመስራተ ሃብት አለማፈላለግና
ለተገቢው ተግባር አለመጠቀም
• የትም/ቤት ር/መምህራን ከቀትሰቦ፣ ወመህ እንዲሁም ከወረዳ ትም/ጽቤቶች ጋር ጥብቅ
ቁርኝት አለመፍጠር
• የትም/ቤት ር/መምህራን የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችንና ቁሳቁሶች ፍላጎትን ቀድሞ
ለይተው ለሚመለከተው አካል ያለማሳወቅና ተከታትሎ ያለማስፈጸም ያሉትንም
ህብቶች በአግባቡ ያለመጠቀም
• በትም/ቤት ውስጥ መገኘት የሚገባቸው ልዩ ልዩ ሰነዶች (የትም/ት ፖሊሲ፣ ገዥ
መመሪያዎች፣ አገራዊና ክልላዊ ፕሮግራሞችና ማእቀፎች፣ ህገ መንግስት ወዘተ )
የትም/ቤት ር/መምህራን ሠነዶች ይጠቅማሉ ብሎ አለማመን፣ ያሉ ሰነዶችንም
በአግባቡ አስቀምጦ ያለመጠቀም፣ የተጓደሉ ሰነዶችን ተከታተሎ አለማሟላት ፣ እነዚህ
ልዩ ልዩ ሠነዶች በህጋዊ ሞዴል ገቢ ተደርገው አለመያዛቸው ዋና ዋና ችግሮች
ናቸው

14
• የትም/ቤት ር/መምህራን የኢንስፔክሽንና የግለ ግምገማ ውጤትን ግብረ መልስን
መሰረት አድርገው እቅድ አቅደው ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው አለመስራታቸው
• የትም/ቤት ር/መምህራን የትም/ቤት ችግሮችን በየጊዜው ለቀበሌ ም/ቤት ማቅረብና
በአግባቡ በማስረዳት አለማስፈታታቸው
• የወረዳ ትም/ጽቤት የትም/ቤቶችን የኢንስፔክሽን ውጤትና ችግሮችን ተንትኖና
ለይቶ ለወረዳ ም/ቤት በተደጋጋሚ በማቅረብ የችግሩን አሳሳቢነት በበቂ ሁኔታ
ያለማሳየት

መ/ የሚከናወኑ ተግባራት

✓ አመልካች 1፡ የትም/ቤቱ የመማሪያና አገልግሎት መስጫ ህንፃዎች በተቀመጠላቸው


ስታንዳርድ መሰረት ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ባካተተ መልኩ (በቂ ብርሃን፣ስፋት፣ወለል
ወዘተ) የታነፁና የተሟሉ ናቸው፣

• ትም/ቤቶች ሲገነቡ በስታንዳርዱ መሠረት ደረጃቸው ተጠብቆ እንዲገነቡ


ግንዛቤ መፍጠርና መተግበር

• ቀድሞ በተሰሩ ትም/ቤቶች ላይ ስታንዳርዱን በጠበቀ መልኩ መሰረታዊ ጥገና


ማካሄድ (ምሳሌ ጠባብ ክፍሎች ካሉ አፍርሶ ማስፋት ፣ብርሃን መስጫ ቆርቆሮ
ጣራ ላይ ማድረግ)

• ሃብት ማፈላለግ/ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል ሰርቶ በጎ አድራጊ አካላትን እርዳታ


መጠየቅ፣ ህ/ሰቡን ማነቃነቅ ፣ የቀድሞ የተም/ቤቱን ተማሪዎች (ዲያስፖራው
እንድ ዶላር ለትም/ቤት የሚያውልበትን አሰራር ማካሄድ)

• አስፈላጊ የትምህርት ቁሳቁሶች (ወንበር፣ጥቁር ሰሌዳ፣ ጠረጴዛ) የመሳሰሉትን


በስታንዳርዱ ለማሟላት ሃብት ማፈላለግ/ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል ሰርቶ በጎ
አድራጊ አካላትን እርዳታ መጠየቅ፣ ህ/ሰቡን ማነቃነቅ ፣ የቀድሞ የተም/ቤቱን
ተማሪዎች (ዲያስፖራው እንድ ዶላር ለትም/ቤት የሚያውልበትን አሰራር
ማካሄድ)

አመልካች 2. ትምህርት ቤቱ በስታንዳርዱ መሰረት የተማሪ መጽሐፍ ፣ የተማሪ-ክፍል


ጥምርታ የመምህሩ/ሯ መምሪያ እና አጋዥ/ ማጣቀሻ መጽሐፍትን፣ ብሬይል አሟልቷል፣

15
• የትም/ቤት ር/መምህራን የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችንና ቁሳቁሶች ፍላጎትን
ቀድሞ በመለየትና ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ ተከታትሎ በማስፈጸም እንዲሁም
ያሉትን ህብቶች በአግባቡ ለመጠቀም ተኩረት ሰጥቶ ስታንዳርዱን ለማሻሻል
መስራት

አመልካች 3፡ ትምህርት ቤቱ በስታንዳርዱ መሠረት ቤተ-መጽሃፍት፣ቤተ-ሙከራ፣


የትምህርት ማበልጸጊያ ማዕከል፣ የስፖርት ሜዳ እና ሌሎች ፋሲሊቲዎችን አሟልቷል፡

• መማሪያ ክፍሎች ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ምቹ እንዲሆኑ ፣ መጸዳጃ ቤቶች


፣ቤተ ሙከራ ፣ቤተ መጻህፍት ክፍሎች ወዘተ… በስታንዳርዱ መሠረት
እንዲገነቡ በየደረጃው ያለ አካል እንዲያውቅ ማድረግ ፣አዲስ ለሆኑት በግንባታ
ወቅት ክትትል እንዲኖር ማድረግ

አመልካች 4 በትምህርት ቤቱ ሀገር አቀፍ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ፣ ገዥ መመሪያዎች፣


አገራዊና ክልላዊ ፕሮግራሞችና ማእቀፎች፣ ህገ መንግስት ወዘተ እንዲሁም ተያያዥነት
ያላቸው መመሪያዎችና የት/ቤቱ መተዳደሪያ ደንብ ተሟልተዋል፣

• በትም/ቤት ውስጥ መገኘት የሚገባቸው ልዩ ልዩ ሰነዶች (የትም/ት ፖሊሲ፣ ገዥ


መመሪያዎች፣ አገራዊና ክልላዊ ፕሮግራሞችና ማእቀፎች፣ ህገ መንግስት ወዘተ )
የትም/ቤት ር/መምህራን አነዚህ ሠነዶች ጠቃሚ መሆናቸውን ተገንዝበው ሰነዶችንም
በአግባቡ ግልጽ ሆኖ በሚታይ ቦታ አስቀምጦ ጥቅም ላይ ማዋል፣ የተጓደሉ ሰነዶችን
ከሌሎች ትም/ቤቶች በመዋስ ፣እና በግዥ ወይም ኮፒ በማድረግ ማሟላት ፣ ሠነዶችን
በህጋዊ ሞዴል ገቢ በማድረግ ኮድ ቁጥር ተሰጥቷቸው ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ

ስታንዳርድ 2፡- ትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማሻሻል ላቀዳቸው ቅድሚያ


ለሚሰጣቸው ተግባራት ማስፈፀሚያ የሚያገለግል የፋይናንስ ሃብት አሟልቷል፡፡

ይህ ስታንዳርድ ትምህርት ቤቱ የገቢ ምንጭን በመለየት፣ በማመንጨትና በማሰባሰብ


እንዲሁም ሃብቱን በአግባቡ ህጋዊ በሆነ በተደራጀ የሂሳብ አያያዝና አሰራርን ተከትሎ
ለመጠቀም የሚያስችል ነው

ሰንጠረዠ 2፡ ከ2009-2010 ዓ.ም በተካሄደው የዳግም ኢንስፔክሽን ትም/ቤቶች በስታንዳርድ


2 ያስመዘገቡት ውጤት ትንታኔ

16
የ2009 ዓ.ም እና የ2010 ዓ.ም የትምህርት ቤቶች የዳግም ኢንስፔክሽነ ውጤት ትንተና
ደረጃ 3 ደረጃ 3
እና ደረጃ እና ደረጃ
4 ላይ 4 ለይ
ደረጃ ደረጃ ደረጃ ደረጃ % (ደረጃ % (ደረጃ
ድምር ያሉ ያሉ
1 2 3 4 1) 2)
ትምህርት ትምህርት
ቤቶች ቤቶች
ክልል ቁጥር በ%
ሃገር አቀፍ 8861 12747 1411 50 23069 38.41 55.26 1461 6.33
አዲስ አበባ 129 443 175 5 752 17.15 58.91 180 23.94
አፋር 235 88 9 0 332 70.78 26.51 9 2.71
አማራ 2166 4333 435 20 6954 31.15 62.31 455 6.54
ቤኒሻንጉል
ጉሙዝ 185 207 18 4 414 44.69 50.00 22 5.31
ድሬዳዋ 33 42 3 0 78 42.31 53.85 3 3.85
ሶማሌ 208 26 4 0 238 87.39 10.92 4 1.68
ጋምቤላ 8 5 3 0 16 50.00 31.25 3 18.75
ሀረሪ 16 7 1 0 24 66.67 29.17 1 4.17
ኦሮሚያ 4678 5880 528 15 11101 42.14 52.97 543 4.89
ደቡብ 982 1274 155 5 2416 40.65 52.73 160 6.62
ትግራይ 221 442 80 1 744 29.70 59.41 81 10.89

ሀ/ በሀገርአቀፍ ደረጃ

ከሰንጠረዡ መረዳት መረዳት እንደሚቻለዉ በአገር አቀፍ ደረጃ በስታንደርድ 2 መሰረት


ደረጃቸዉን ያሟሉ ት/ቤቶች 1461 (6.33%) ብቻ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣፣
በሌላ መልኩ (96.7% ) የሚሆኑ ት/ቤቶች ከደረጃ በታች መሆናቸዉን
ያመልክታል፣፣
ለ/ በክልል ደረጃ

ሰንጠረዥ- 2 ክልሎች በስታንዳርድ 2 አብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶች የተቀመጠውን ዝቅተኛ


መመዘኛ ያላማሉ መሆኑን ያሳያል። ከሰንጠረዡ ማየትእነደሚቻለው አዲስ አበባ (23.94%)
እና በጋምቤላ (18.75%) የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች የተቀመጠውን ዝቅተኛ መመዘኛ ያሟሉ
በሶማሌ (1.68%) ፣በአፋር (2.71%) እና ድሬዳዋ (3.85%) የሚሆኑት ትምህርት ቤቶች
ብቻ ናቸው ለደረጃው የተቀመጠውን ዝቅተና መዘኛ ማሟላት የቻሉት።

17
ሐ/ ተጠቃሽ የሆኑ ችግሮች (ገላጭና አመላካች)

• ትምህርት ቤቱ በብሎክ ግራንትና ስኩል ግራት የተገኘውን ሃብት በአግባቡ


ለትምህርት ጥራት ማሻሻያ አለማዋል
• ህብት ከማመንጨት አኳያ የህብረተሰቡን ተሳትፎ አለማጎልበት
• ትምህርት ቤቱ ፕሮጀክት በመቅረጽ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት፣ታዋቂ
ግለሰቦችና የቀድሞ ተማሪዎች ጋር ግኙነት ወይም ትስስር በመፍጠር ሃብት
አለማሰባሰብ
• ትምህርት ቤቱ ከሃብት አጠቃም አኳያ ህጋዊ የሂሳብ አሰራር ባለመከተል ሃብቱን
ለብክነት መጋለጡ፣

መ/ የሚከናወኑ ተግባራት

አመልካች 1 እና 2 ፡- ትምህርት ቤቱ በስታንዳርዱ መሰረት የትምህርት ቤት ጥቅል በጀት


/Block grant/ ተቀብሎ በአግባቡ ሥራ ላይ አውሏል፤

• ትምህርት ቤቱ በብሎክ ግራንትና ስኩል ግራት ያገኘውን ህብት የቅድሚያ ቅድሚያ


የትኩረት ነጥቦችን በማቀድ ለትምህርት ጥራት ማሻሻያ በማዋል የትምህርት ቤቱን
ችግር በመፍታት የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል ማድረግ አለበት
• ህበቱን በወቅቱ ተከታትሎ በመቀበል ለሥራ ማዋል ይገባዋል

አመልካች 3 እና 4፡- ትምህርት ቤቱ ከወላጆችና ከአካባቢው ማህበረሰብ (በገንዘብ በዓይነትና


በጉልበት) ሃብት አሰባስቧል፣

• ህብት ለማሰባሰብ ትምህርት ቤቱ ያለበትን ተጨባጭ ደረጃ ለህብረተሰቡ በተደጋጋሚ


በግልጽ ማሳየትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ማዘጋጀት
• እንደአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ከህብረተሰቡ ሊገኝ የሚችለውን ድጋፍ በገንዘብ
፣በቁስና በጉልበት ለይቶ ማስቀመጥና ህበቱን ለማሰባሰብ ውሳኔ ላይ መድረስና
ማሰባሰብ
• ትምህርት ቤቱ እንደአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ የሃብት ማመንጫ ስልቶችን በመቀየስ
የተሻለ ሃብት ማሰባሰብ

አመልካች 5፡- ትምህርት ቤቱ በአካባቢው ከሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ግለሰቦች


/ከቀድሞ ተማሪዎች ፣ አካባቢ ተወላጆች…ወዘተ/ ሃብት አሰባስቧል፡፡

18
• ትምህርት ቤቱ ፕሮጀክት በመቅረጽ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት፣ታዋቂ
ግለሰቦች፣ በሃገር ውስጥና በሃገር ውጭ ካሉት የቀድሞ ተማሪዎች ጋር ግኙነት ወይም
ትስስር በመፍጠር ሃብት በማሰባሰብ ጥቅም ላይ ማዋል፤

አመልካች 6- ትምህርት ቤቱ በአግባቡ የተደራጀ የፋይናንስ ዶክመንቶች አሉት፣

• ትምህርት ቤቱ ለሚያወጣቸው ወጭዎችና ለሚፈጽማቸው ግዥዎች የፋይናንስ


አሰራርን ተከትሎ ( ለምሳሌ በግልጽ ጨረታ) እንዲሠራ ማድረግ
• ትምህርት ቤቱ ከሃብት አጠቃም አኳያ ህጋዊ የሂሳብ አሰራር መከተል (ገቢ ወጭና
ከወጭ ቀሪ ) የሚያመለክት የሂሳብ ሰነድ በመጠቀም ሃብቱን ለብክነት እነዳይጋለጥ
ማድረግ ይገባል
• ትምህርት ቤቱ የሂሳብ ሠራተኛ ከሌለው የሚመለከተውን አካል በአግባቡ ወክሎ
ማሠራት እንዲሁም ሂሳብ በየወሩ እየተዘጋ እንዲሄድ ማድረግ

ስታንዳርድ 3፡- ትምህርት ቤቱ ለደረጃው የሚመጥኑ ርእሳነ መምህራን፣ መምህራን እና


ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በስታንዳርዱ መሰረት አሟልቷል፡፡

ይህ ስታንዳርድ ትምህርት ቤቱ በቅጥር ወይም በምደባ የሚያገኘው የሠው ሃይል በትምህርት


ደረጃውና በሙያ ፈቃድ አሟልቶ እንዲገኝ የሚጠይቅ ነው፡፡

ሰንጠረዠ 3፡ ከ2009-2010 ዓ.ም በተካሄደው የዳግም ኢንስፔክሽን ትም/ቤቶች በስታንዳርድ


3 ያስመዘገቡት ውጤት ትንታኔ

የ2009 እና 2010 ዓ.ም የትምህርተ ቤት የዳምግም ኢንስፔክሽን ውጤት ትንተና ስታንዳርድ 3


ደረጃ 3 ደረጃ 3
ደረጃ ደረጃ ደረጃ ደረጃl % ( % (ደረጃ እና 4 እና 4
ድምር
1 2 3 4 ደረጃ 1) 2) ላይ ያሉ ላይ ያሉ
ክልል ትምህርት ትምህርት

19
ቤቶች ቤቶች
በቁትር በ%

ሃገር አቀፍ 17204 5061 741 64 23070 74.57 21.94 805 3.49
አዲስ አበባ 336 312 101 3 752 44.68 41.49 104 13.83
አፋር 259 65 8 0 332 78.01 19.58 8 2.41
አማራ 4685 1964 276 30 6955 67.36 28.24 306 4.40
ቤኒሻንጉል
378 30 6 414 91.30 7.25 6 1.45
ጉሙዝ
ድሬዳዋ 38 33 7 78 48.72 42.31 7 8.97
ሶማሌ 214 19 5 238 89.92 7.98 5 2.10
ጋምቤላ 11 4 1 16 68.75 25.00 1 6.25
ሀረሪ 8 15 1 24 33.33 62.50 1 4.17
ኦሮሚያ 8754 2101 233 13 11101 78.86 18.93 246 2.22
ደቡብ 1999 333 67 17 2416 82.74 13.78 84 3.48
ትግራይ 522 185 36 1 744 70.16 24.87 37 4.97

ሀ/ በሀገር አቀፍ ደረጃ

ከሰንጠረዡ መረዳት እንደሚቻለዉ በአገር አቀፍ ደረጃ ድጋሜ ኢንስፔክሽን ከተካሄደባቸው


23070 ትምህርት ቤቶች በስታንደርድ 3 ደረጃቸዉን ያሟሉ ት/ቤቶች 805 (3.49%)
ብቻ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣፣ በሌላ መልኩ (96.51%) የሚሆኑ ት/ቤቶች ከደረጃ በታች
መሆናቸዉን ያመልክታል፣፣
ለ/ በክልል ደረጃ

ስታንዳርድ ሦስትን በተመለከተ የክልሎች አፈጻጸም ሲታይ አዲስ አበባ (13.83%) ፣አማራ
(4.4 %) ፣ድሬዳዋ(8.97%)፣ ጋምቤላ (6.25%)፣ ሃራሪ (4.17%) እና ትግራይ (4.97% ) ከሃገር
አቀፉ አፈጻጸም በላይ ያላቸው ሲሆን ቀሪዎች ግን በተለይም ቤንሻንል ጉምዝ (1.45%)
ዝቅተኛ አፈጻጸም ያላቸው መሆኑን ለመረዳት ይቻላል፡፡

ሐ/ ተጠቃሽ የሆኑ ችግሮች (ገላጭና አመላካች)

• ለትምህርት ቤቶች የሚመደቡት መምሃራን እና ር/መምህራን ትምህርት ቤቱ


የሚጠይቀውን ደረጃ የሚያሟሉ አለመሆን
• መምህራን ባልሰለጠኑበት ትምህርት እንዲያስተምሩ ማደረግ
• ለትምህርት ቤቶች ድጋፍ ሰጭ ሠራተኞች ያለመኖር

20
• መምህራንና ርእሰ መምህራን ለሙያ ፈቃድ ምዘና ፍላጎት ያለመኖርና ራሳቸውን
ያለማዘጋጀታቸው
• በጋይዳንስና ካውንሰሊንግ የሰለጠኑ መምህራን እጥረት ያሉትም ቢሆን በቦታው
ያለመቆየት
• በልዩ ፍላጎት የሰለጠኑ መምህራንን በሚፈለገው መልኩ በገበያው ያለመገኘት

መ/ የሚከናወኑ ተግባራት

አመልካች 1፡ ሁሉም የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህራንና መምህራን የሙያ ፈቃድና


ለደረጃው የሚመጥን የትምህርት ማስረጃ የምስክር ወረቀት አላቸው፣
• የትምህርት ቤቱ ር/መምህር ከወረዳ ትም/ጽቤት ጋር በመነጋገር ደረጃውን
የጠበቁ መምህራን እንዲመደቡለት ጥረት ማደረግ
• የሙያ ፈቃድና እድሳትን በተመለከተ ር//መምህሩ ከወረዳ ትም/ጽ/ቤት ጋር
በመነጋገር ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ማዘጋጀት፣ አስፈላጊ
ማቴሪያሎችን ማሟላት
አመልካች 2- ትምህርት ቤቱ ለደረጃው የሚመጥን የስራ ልምድና የትምህርት ማስረጃ
ያላቸው ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች አሉት፣
• የትምህርት ቤቱ ር/መምህር ለወረዳ ትም/ጽ/ቤት ችግሮችን አጎልቶ በማሳየት
ለደረጃው የሚመጥን የስራ ማስረጃና የትምህርት ዝግጂት ያላቸው ድጋፍ ሰጭ
ሠራተኞች እንዲቀጠሩለት ማደረግ
• የትም/ቤት ር/መምህራን ከወመህና ቀትስቦ ጋር በመነጋገገር የውስጥ ገቢን
በመጠቀም ወይም ደግሞ የፈቃደኛ አገልግሎት ሰጭዎችን በማፈላለግ ድጋፍ
ሰጭ ሰራተኛ መቅጠር
አመልካች 3፡ ትምህርት ቤቱ የምክርና ድጋፍ /Guidance and Counselling/ አገልግሎት
የሚሰጥ ባለሙያ አለው፣
• የትም/ቤቱ ር/መምህር የጋይዳንስና ካውንስሊንግ ባለሙያ እንዲቀጠርለት
የባለሙያው መኖር ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል የሚናረውን ሚና አጉልቶ
በማሳየት ለወረዳ ትም/ጽ/ቤቱን ችግሩን ማቅረብና ተከታተሎ ማስመደብ
• ዘላቂ መፍትሄ ባይሆንም ችግሩን በተወሰነ መልኩ ለመቅረፍ ከመምህራን
መካከል ለሙያው ተቀራራቢ የትምህርት ዝግጂት ያላቸውን በተገቢው መንገድ
በመምረጥ ተግባሩ እንዲሠራ ማድረግ

21
አመልካች 4፡- ት/ቤቱ በልዩ ፍላጎት ትምህርት የሰለጠኑ መምህራን አሉት፡
የትም/ቤቱ ር/መምህር ለልዩ ፍላጎት ትምህርት ትኩረት በመስጠት የጉዳት አይነቱን
በመለየት በሙያው የሰለጠነ መምህር እንዲመደብለት የወረደ ትም/ጽቤቱን ደጋግሞ
በደብዳቤ መጠየቅ
ስታንዳርድ 4 ፡- ትምህርት ቤቱ ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ምቹ፣ የማያሰጋ እና
ደህንነታቸውን የሚያረጋግጥ የመማር - ማስተማር አካባቢ ፈጥሯል፡፡

ምቹ የመማሪያ አካባቢ ማለት ተገቢ የትምህርት ቁሳቁሶችን፣ በአግባቡ የተገነቡ መማሪያ


ክፍሎችን ፣ለተማሪዎች ደህንነት የማያሰጋ አካባቢና ጥሩ የዲሲፕሊን ደንቦችና አሰራሮች
ያሉት፣ በአጥር የተከለለ ትም/ቤት ከሚያውኩ ድምጾች የጸዳ እንዲሁም ንጹህ የመጠጥ ውሃና
ጽዱ መተዳጃ ያሉት ማለት ነው ፡፡

ሰንጠረዠ 4፡ ከ2009-2010 ዓ.ም በተካሄደው የዳግም ኢንስፔክሽን ትም/ቤቶች በስታንዳርድ


4 ያስመዘገቡት ውጤት ትንታኔ

የ2009 እና 2010 ዓ.ም የትምህርት ቤቶች የድግም ኢንስፔክሽን ውጤት ትንተና ስታንዳርድ 4
ደረጃ 3 ደረጃ 3
እና 4 እና 4
ደረጃ ደረጃ ደረጃ % (ደረጃ % (ደረጃ ላይ ያሉ ላይ ያሉ
ደረጃ 2 ድምር
1 3 4 1) 2) ትምህርት ትምህርት
ቤቶች ቤቶች
ክልል በቁትር በ%
ሃገር አቀፍ 6312 13554 3090 114 23070 27.36 58.75 3204 13.89
አዲስ አበባ 36 493 216 7 752 4.79 65.56 223 29.65
አፋር 216 91 24 1 332 65.06 27.41 25 7.53
አማራ 1734 4227 961 33 6955 24.93 60.78 994 14.29
ቤኒሻንጉል
414 31.16 57.25 48 11.59
ጉሙዝ 129 237 42 6
ድሬዳዋ 18 47 11 2 78 23.08 60.26 13 16.67
ሶማሌ 171 58 8 1 238 71.85 24.37 9 3.78
ጋምቤላ 11 5 16 0.00 68.75 5 31.25
ሀረሪ 2 20 2 24 8.33 83.33 2 8.33
ኦሮሚያ 3094 6552 1406 49 11101 27.87 59.02 1455 13.11

22
ደቡብ 691 1395 320 10 2416 28.60 57.74 330 13.66
ትግራይ 221 423 95 5 744 29.70 56.85 100 13.44

ሀ/ በሀገርአቀፍ ደረጃ

ከሰንጠረዡ መረዳት መረዳት እንደሚቻለዉ ከ2009-2010 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ በ 23070
ትምህርት ቤቶች ላይ ድጋሜ ኢንስፔክሽን ተካሂዶ በስታንደርድ አራት 3204 (13.89%)
ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን ያሟሉ ሲሆን በሌላ በኩል (86.11%) ደግሞ ከደረጃ በታች
መሆናቸውን ያመለክታል ፡፡

ለ/ በክልል ደረጃ

በክልል ደረጃ ሲታይ ከሀገር አቀፉ አፈጻጸም በላይ ያላቸው ጋንቤላ (31.25%)፣ አዲስ አበባ
(29.65%)እና ድሬዳዋ (16.67%) በአንጻዊነት የተሸለ አፈጻጸም ሲኖራቸው በዝቅተኛ
አፈጻጸም የተፈረጁት ደግሞ ሶማሌ (3.78%) ፣አፋር (7.53%) እና ሀረሪ (8.33%) ናቸው፡፡

ሐ/ ተጠቃሽ የሆኑ ችግሮች (ገላጭና አመላካች)

• ትምህርት ቤቶች በስታንዳርዱ መሠረት በቂ የቦታ ስፋት የሌላቸው መሆኑ


• የትምህርት ተቋማቱ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር የሌላቸው መሆኑ
• ከዚህ በፊት የተገነቡትም ሆነ አሁን በመገንባት ላይ ያሉት ትምህርት ቤቶች የልዩ
ፍላጎትን ችግርን ግምት ውስጥ በማስገባት ለአካቶ ትምህርት ምቹ አለመሆን
• በስታንዳርዱ መሠረት በሚገባ የትምህርት ቤቶች ምደረ ግቢ አለመታጠር
• የትምህርት ተቋማት ሲገነቡ ከአዋኪ ድምጽ የጸዱ አለመሆን እንዲሁም ለትራፊክ
አደጋ የተጋለጡ መሆን
• ትምህርት ቤቶችና ሌሎች አካላት የውስጥ ገቢን ለማሳደግ በሚል ኮንቴነሮችን
በተቋማቱ ዙሪያ በማስቀመጥና በማከራየት ለተማሪዎች ምቹ ሁኔታ አለመፍጠር
• የትምህርት ቤቱን ማሃበረሰብ ብዛት መሠረት ያላደረገ መጸዳጃ ቤት መገንባትና
ያሉትም መጸዳጃ ቤቶች ንጽህናቸውን የማይጠብቁና በቂ የውሃና የሳሙና አገልግሎት
የሌላቸው መሆን

23
• በአብዛኛው ተቋማት የንጹህ ውሃ አገልግሎት የሌለ መሆኑ፣ ያሉትም የተማሪዎችን
ቁጥር መሠረት ያደረገ እንዲሁም ንጽህናውን ያልጠበቀ መሆኑ

መ/ የሚከናወኑ ተግባራት
አመልካች 1፡- ትምህርት ቤቱ በስታንድርዱ መሠረት ተፈላጊውን የቦታ ስፋት አሟልቷል፣
• ነባር ትምህርት ቤቶች የቦታ ስፋት ይዞታቸው በስታንዳርዱ መሰረት
እንዲሆን ከሚመለከተው አካል ጋር በተከታታይ በመነጋገር ስታንዳርዱን
ማሟላት
• አዲስ የሚገነቡ ትምህርት ቤቶች ስታንዳርዱን መሰረት ባደረገ የቦታ ስፋት
ላይ እንዲገነቡ የሚመለከተው አካል በበቂ የቦታ ስፋት ላይ እንዲገነቡ
ክትትል ማድረግ

አመልካች 2፡- ትምህርት ቤቱ የይዞታ ማረጋገጫ ህጋዊ ሰነድ አለው፣


• ትምህርት ቤቱ የይዞታ ማረጋገጫ ሠነድ እንዲኖረው ር/መምህሩ
ለሚመለከታቸው አካላት ጉዳዩን በማቀረብና ያላሰለሠ ጥረት በማድረግ
ትም/ቤቱ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነዱን እንዲያገኝ ማድረግ

አመልካች 3፡- በትምህርት ቤቱ የሚገኙ ህንፃዎች ልዩ ፍላጎት ያላቸውን አካቶ ለመማር


ማስተማር ምቹ ነው፣
• አዲስ መማሪያ ክፍሎች ሲገነቡ ወደ ክፍል መግቢያ መንገድና በራቸው ልዩ
ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች ግምት ውስጥ እንዲያስገባ በግንባታ እቅዱ ውስጥ
ማካተትና ክትትል ማድረግ
• የትምህርት ቤቱ ር/መምህር ነባር መማሪያ ክፍሎች ለአካቶ ትምህርት ምቹ
እንዲሆኑ የማሻሻያ እና ማስተካከያ ስራ እንዲሠራ ማድረግ

አመልካች 4፡- የትምህርት ቤቱ ግቢ በአጥር ተከብሯል፣


• የትም/ቤቱ ር/መምህር አካቢውን ህብረተሰብ በማሳተፍ እንደአካባቢው
ተጨባጭ ሁኔታ በስታንዳርዱ መሰረት ደረጃውን የትምህርት ቤቱን ምደረ
ግቢ በአጥር ማስከበር ተገቢ ነው

አመልካች 5 ፡- ትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማር ሂደትን ከሚያውኩ ሁኔታዎች የፀዳ ነው፣


• አዲስ የሚገነቡ ትምህርት ቤቶች የቦታ መረጣ ሲደረግ ከአዋኪ ድምጽ
፣ከትራፊክ ፍሰት ፣ከገደላማ ቦታ ፣ከወንዞች ወዘተ የራቀና ምቹ እንዲሆን
ማድረግ

24
• የትም/ቤቱ ር/መምህር ነባር ተቋማት በተቻለ መጠን የትምህርት ቤቱን
ምቹነት የሚያውኩ ማለትም የገቢ ምንጭ ለማሳደግ ኮንቴይነር ሲያከራዩ
ተማሪዎችን ለመጥፎ ተግባር በማያጋልጥ ስራ ለሚሰሩ ተመርጦ ቢሰጥ
• የትምህርት ቤቱ ር/መምህር በተቋሙ ዙሪያ መማር ማስተማሩን የሚያውኩ
ተግባራት ካሉህግን መሠረት በማድረግ የመከላከል ስራ ከሚመለከታቸው
አካላት ጋር መስራት አለበት

አመልካች 6፤ በትምህርት ቤቱ ደረጃቸውን የጠበቁ፣ በየጊዜው የሚፀዱና በፆታ የተለዩ


የተማሪዎች፣ የመምህራንና ሰራተኞች መፀዳጃ ቤቶች ከውሃ እና ሳሙና ጋር ተሟልቷል፡፡
• አዲስ የሚገነቡ ተቋማት ከመገንባታቸው በፊት የመጸዳጃ ቤት በግንባታ እቅዱ
ውስጥ በስታንዳርዱ መሠረት መሆኑን ማረጋገጥ
• የትም/ቤቱ ር/መምህር ፕሮጀክት በመቅረጽ ከረጂ ድርጂቶች እንዲሁም
ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር በስታንዳርዱ መሰረት መጸዳጃ ቤት እንዲኖር
ማድረግ
• ለተማሪዎች የጽዳት መርሃ ግብር በማውጣትና ግንዛቤ እንዲኖራቸው በማድረግ
በእኔነት ስሜት በተራ እንዲያጸዱ ማድረግ
• የትም/ቤቱ ር/መምህር ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ የውስጥ ገቢን በመጠቀም
የጽዳት ሠራተኛ መቅጠር
• ለመጸዳጃ አገልግሎት ንጽህና የሚውል ውሃና ሳሙና ችግርን ለመቅረፍ
የትም/ቤቱ ር/መምህር ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ .ረጂ ድርጂቶችን በማፈላለግ፣
የውስጥ ገቢንና ህብረተሰቡን በማንቀሳቀስ የጉድጓድ ውሃ እንዲወጣ ማድረግ፣
የውሃ ማከማቻ በመጠቀም እንዲሁም ሳሙና ማቅረብ

አመልካች 7፤- ትምህርት ቤቱ ንፁህና የታከመ ለመጠጥ የሚያገለግል የውሃ አቅርቦት


አለው፡፡
• ለመጠጥ አገልግሎት የሚውል ውሃ ችግርን ለመቅረፍ የትም/ቤቱ ር/መምህር
ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ .ረጂ ድርጂቶችን በማፈላለግ፣ የውስጥ ገቢንና
ህብረተሰቡን በማንቀሳቀስ የጉድጓድ ውሃ እንዲወጣ ማድረግ፣ ምንጭ
በማጎልበትና ከባለሙያ ጋር በመነጋገር እንዲታከም ማድረግ
• ለመጠጥ አገልግሎት የሚውል የቧንቧ ውሃ ያላቸው ተቋማት ውሃው በአግባቡ
አገልግሎት እንዲሰጥ አስፈላጊው እንክብካቤ እየተደረገ ተማሪዎች
እንዲጠቀሙበት ማድረግ.

ስታንዳርድ 5 ትምህርት ቤቱ የተደራጀ የትምህርት ልማት ሰራዊት ፈጥሯል፡፡

25
ይህ ሥታንዳርድ ትምህርት ቤቶችን ውጠየታማ ለማድረግ የግባትና የአሰራር ስርኣታቸውን
በመዘርጋት በትምህርት ልማት ሠራዊት አካሄድ ሥራዎችን ለመስራት የሚያስችል ሙያዊ
ክህሎትና የአመራር ብቃት ለመፍጠር የሚያስችል ነው፡፡

ሰንጠረዠ 5፡ ከ2009-2010 ዓ.ም በተካሄደው የዳግም ኢንስፔክሽን ትም/ቤቶች በስታንዳርድ


4 ያስመዘገቡት ውጤት ትንታኔ

ደረጃ 3 ደረጃ 3
እና 4 እና 4
ደረጃ ደረጃ ደረጃ % (ደረጃ % (ደረጃ ላይ ያሉ ላይ ያሉ
ደረጃ 2 ድምር
1 3 4 1) 2) ትምህርት ትምህርት
ቤቶች ቤቶች
ክልል በቁትር በ%
ሃገር
23070 28.95 51.71 4462 19.34
አቀፍ 6679 11929 4169 293
አዲስ
134 338 267 13 752 17.82 44.95 280 37.23
አበባ
አፋር 167 124 33 8 332 50.30 37.35 41 12.35
አማራ 1274 3926 1671 84 6955 18.32 56.45 1755 25.23
ቤኒሻንጉል
135 216 52 11 414 32.61 52.17 63 15.22
ጉሙዝ
ድሬዳዋ 43 27 6 2 78 55.13 34.62 8 10.26
ሶማሌ 150 69 14 5 238 63.03 28.99 19 7.98
ጋምቤላ 4 9 3 16 25.00 56.25 3 18.75
ሀረሪ 5 15 4 24 20.83 62.50 4 16.67
ኦሮሚያ 4056 5457 1490 98 11101 36.54 49.16 1588 14.31
ደቡብ 599 1323 437 57 2416 24.79 54.76 494 20.45
ትግራይ 112 425 192 15 744 15.05 57.12 207 27.82

ሀ/ በሀገርአቀፍ ደረጃ

ከሰንጠረዡ መረዳት መረዳት እንደሚቻለዉ ከ2009-2010 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ በ 23070
ትምህርት ቤቶች ላይ ድጋሜ ኢንስፔክሽን ተካሂዶ በስታንደርድ አምሰት 3204 (19.34%)
ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን ያሟሉ ሲሆን በሌላ በኩል (80.66%) ደግሞ ከደረጃ በታች
መሆናቸውን ያመለክታል ፡፡

ለ/ በክልል ደረጃ

26
በክልል ደረጃ ሲታይ ከሀገር አቀፉ አፈጻጸም በላይ ያላቸው አዲስ አበባ (37.23%)፣ ትግራይ
(27.87%) እና አማራ (25.23.%) በአንጻራዊነት የተሸለ አፈጻጸም ሲኖራቸው በዝቅተኛ
አፈጻጸም የተፈረጁት ደግሞ ሶማሌ (7.98%) እና ድሬዳዋ (10.26%) ናቸው፡፡
ሐ/ ተጠቃሽ የሆኑ ችግሮች (ገላጭና አመላካች)

• ከፖሊቲካ አስተሳሰብ ጋር ማዛመድና አሉታዊ ገጽታ ማላበስ


• ተግባራቱ ያላቸውን ፋይዳ በማሳነስ ትኩረት ሰጥቶ አለመንቀሳቀስ
• የማስፈጸም አቅም እጥረት መኖሩ
መ/ የሚከናወኑ ተግባራት

አመልካች 1 በትምህርት ቤቱ ዓላማዎችና ተልዕኮዎችን ለመተግበር የሚያስችል ፣


አደረጃጀት፣ ተግብዐትና የአሰራር ስርዐት መዘርጋትን በተመለከተ

• የአደረጃጀቱን ስያሜ በማሻሻል ያለውን አደረጃጀት አጠናክሮ መቀጠል


• የመማማሪያ እንዲሁም ልምድ ልውውጥ መድረኮችን መፍጠር፤
አመልካች 2 ፡ በትምህርት ቤቱ ሁለቱን የልማት አቅሞች (የመንግስትና የህዝብ)
በማቀናጀት ት/ቤቱ ያስቀመጣቸውን ዓላማዎችና ግቦችን የተገነዘበና ለመፈፀም ዝግጁ የሆነ
የትምህርት ልማት ሰራዊት መፈጠሩን በተመለከተ

• በትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ላይ የነበረውን አሉታዊ አመለካከት መቀልበስ


የሚያስችል የግንዛቤ መድረኮችን መፍጠር
• የልምድ ልውውጦችን ማድረግ፤የተለዩ ልምዶችን ቀምሮ ማስፋት
አመልካች 5.3 በትምህርት ቤቱ ሁለቱን የልማት አቅሞች (የመንግስትና የህዝብ)
አቀናጅቶ ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት የሚያስችል ሙያዊ ክህሎትና የአመራር ብቃት
መፈጠሩን በተመለከተ

• በእያንዳንዱ አደረጃጀት ሙያዊ ክህሎትና ብቃት ለመፍጠር የሚችሉ አቅም


ያላቸውን መሪዎች መርጦ በየአደረጃጀቱ ማሳተፍ

ስታንዳርድ 6: ትምህርት ቤቱ የጋራ ራዕይ ፣ተልዕኮና እሴቶች አሉት፡፡

ይህ ስታንዳርድ በትምህርት ቤቱ አመራርና በባለድርሻ አካላት ተሳትፎ የተዘጋጀ ራዕይ፣


ተልዕኮና እሴቶች እንዳሉት የሚያመላከት ነው።

27
ሰንጠረዠ 6. በዳግም ኢንስፔክሽን ውጤት

የ2009 እና 2010 ዓ.ም የትምህርት ቤቶች የዳግም ኢንስፔክሽብ ውጤት ትንታነ


ስታንዳርደ 6
%(ደረጃ 3
እና ደረጃ
ደረጃ ደረጃ ደረጃ ደረጃ %(ደረጃ % (ደረጃ 4)
ክልል 1 2 3 4 ድምር 3) 4)
53 425 269 5 752 35.77 0.66 36.44
አዲስ አበባ
105 128 83 16 332 25.00 4.82 29.82
አፋር
1208 3450 2169 128 6955 31.19 1.84 33.03
አማራ
ቤኒሻንጉል 61 175 149 29 414 35.99 7.00 43.00
ጉሙዝ
8 27 34 9 78 43.59 11.54 55.13
ድሬዳዋ
153 65 17 3 238 7.14 1.26 8.40
ሶማሌ
2 8 6 16 37.50 0.00 37.50
ጋምቤላ
5 4 15 24 62.50 0.00 62.50
ሀረሪ
3253 4309 3236 303 11101 29.15 2.73 31.88
ኦሮሚያ
552 946 841 77 2416 34.81 3.19 38.00
ደቡብ
85 313 318 28 744 42.74 3.76 46.51
ትግራይ
5485 9850 7137 598 23070 30.94 2.59 33.53
ሃገር አቀፍ

ሀ/ በሀገርአቀፍ ደረጃ

በሀገርአቀፍ ደረጃ 23070 ት/ቤቶች ሲኖሩ በስታንዳርዱ በደረጃ 3 (30.94%) እና 4 (2.59%)


ላይ ያሉ ወይም ደረጃቸውን ያሟሉ 33.53 በመቶ ብቻ ናቸው። በመሆኑም በሀገርአቀፍ ደረጃ
የኢንስፔክሽን ትንተና እንደሚያሳየው ትምህርት ቤቱ ህብረተሰቡን ያሳተፈ የጋራ ራዕይ
፣ተልዕኮና እሴቶች ከማዘጋጀትና ከባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ከመፍጠር አንጻር ብዙ መስራት
እንዳለበት ያመለክታል።

28
Implication ይቀመጥ

ለ/ በክልል ደረጃ

በክልል ደረጃ ከስታንዳርዱ አንጻር ሲታይ የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው ማለትም ሀረሪ
(62.50%) እና ድሬዳዋ (55.13%) ደረጃቸውን ያሟሉ ት/ቤቶች አሏቸው። ዝቅተኛ አፈጻጸም
ያሏቸው ክልሎች ደግሞ ኢትዮ-ሶማሊ (91.60%)፣ አፋር (70.18%) ደረጃውን ያላሟሉ
ትምህርት ቤቶች ያሏቸው መሆናቸውን መረጃው ያመለክታል።

ተጠቃሽ የሆኑ ችግሮች (ገላጭና አመላካች)

ከላይ እንደሚታየው ከደረጃ በታች የሆኑ ት/ቤቶች ያሏቸው አብዛኛው ክልሎች ሲሆኑ ለዚህም
ከሚጠቀሱ ችግሮች መካከል፡

• ትምህርት ቤቱ የተዘጋጀውን ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች ግልጽና በሚታይ ቦታ


ማስቀመጥ አለመቻላቸው፣
• የትምህርት ቤቱ ራዕይ፣ ተልዕኮና ዕሴቶች ማህበረሰቡን በማሳተፍ ያልተዘጋጁና በቂ
ግንዛቤ ያልተፈጠረላቸው መሆናቸው፣

የሚከናወኑ ተግባራት

አመላካች 6.1 የትምህርት ቤቱ አመራር ባለለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የተቀረጸ ራዕይ፣


ተልእኮና እሴቶች ያሉት ስለመሆኑ፡፡
• የትምህርት ቤቱ ራዕይ፣ተልዕኮና ዕሴቶች ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ እንዲዘጋጅ
ማድረግ
• የትምህርት ቤቱ ራዕይ፣ ተልእኮና እሴቶች ለትምህርት ቤቱ እንደሚያስፈልጉ
ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መፍጠርና በቂ መረጃ መያዝ፣
• የትምህርት ቤቱ ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች ማህበረሰቡ በሚያየውና ጉልህ ሆኖ ሊነበብ
በሚችል ቦታ ሊቀመጥ ይገባዋል ፣

29
ስታንዳርድ 7: ትምህርት ቤቱ አሳታፊ የት/ቤት መሻሻል ዕቅድ አዘጋጅቷል፡፡

ይህ ስታንዳርድ ትምህርት ቤቱ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት ባሳተፈ መልኩ


ትምህርት ቤቱ ያለበትን ሁኔታ በመለየት ችግር ፈች ዕቅድ ማዘጋጀት እንዳለበት
የሚመለከት ነው።

ሰንጠረዠ 7 በዳግም ኢንስፔክሽን ውጤት

2009 እና 2010 ዓ.ም የትምህርት ቤቶች የዳግም ኢንስፔክሽብ ውጤት ትንታነ


ስታንዳርደ 7
%(ደረጃ 3
እና ደረጃ
ደረጃ ደረጃ ደረጃ ደረጃ %(ደረጃ % (ደረጃ 4)
ክልል 1 2 3 4 ድምር 3) 4)
139 371 231 11 752 30.72 1.46 32.18
አዲስ አበባ

120 154 49 10 333 14.71 3.00 17.72


አፋር
1121 3830 1885 119 6955 27.10 1.71 28.81
አማራ
ቤኒሻንጉል 74 193 123 24 414 29.71 5.80 35.51
ጉሙዝ
12 31 29 6 78 37.18 7.69 44.87
ድሬዳዋ
155 62 18 4 239 7.53 1.67 9.21
ሶማሌ
3 10 3 16 18.75 0.00 18.75
ጋምቤላ
5 12 8 3 28 28.57 10.71 39.29
ሀረሪ
2605 5496 2689 311 11101 24.22 2.80 27.02
ኦሮሚያ
503 1105 700 108 2416 28.97 4.47 33.44
ደቡብ
83 382 251 28 744 33.74 3.76 37.50
ትግራይ
4820 11646 5986 624 23076 25.94 2.70 28.64
ሃገር አቀፍ

30
ሀ/ በሀገርአቀፍ ደረጃ

በሀገርአቀፍ ደረጃ 23076 ት/ቤቶች ሲኖሩ በስታንዳርዱ በደረጃ 3 (25.94%) እና 4 (2.70%)


ላይ ያሉ ወይም ደረጃቸውን ያሟሉ 28.64 በመቶ ብቻ ናቸው። በመሆኑም በሀገርአቀፍ ደረጃ
የኢንስፔክሽን ትንተና እንደሚያሳየው ትምህርት ቤቱ አሳታፊ የት/ቤት መሻሻል ዕቅድ
ከማቀድ አንጻር ብዙ መስራት እንዳለበት ያመለክታል።

Implication ይቀመጥ

ለ/ በክልል ደረጃ

በክልል ደረጃ ከስታንዳርዱ አንጻር ሲታይ የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው ማለትም ድሬዳዋ
(44.87%) እና ሀረሪ (39.29%) ደረጃቸውን ያሟሉ ት/ቤቶች አሏቸው። ዝቅተኛ አፈጻጸም
ያሏቸው ክልሎች ደግሞ ኢትዮ-ሶማሊ (90.79%)፣ አፋር (82.28%) እና ጋምቤላ (81.25%)
መሆናቸውን መረጃው ያመለክታል።

ተጠቃሽ የሆኑ ችግሮች (ገላጭና አመላካች)

ከላይ እንደሚታየው ከደረጃ በታች የሆኑ ት/ቤቶች ያሏቸው ክልሎች ታዳጊ ክልሎች ሲሆኑ
ለዚህም ከሚጠቀሱ ችግሮች መካከል

• ትምህርት ቤቱ ቅድሚያ ትኩረት የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ


መለየት አለመቻሉ፣
• ትምህርት ቤቱ የ3ዓመት ስልታዊ እና አመታዊ ዕቅዶች የሚመለከታቸው ባለድርሻ
አካላት በማሳተፍ አለማዘጋጀቱ፣
• የትምህርት ቤቱ አመራር የዕቅድ አስተቃቀድ ግንዛቤ አናሳ መሆኑ፣
• ትምህርት ቤቱን የሚደግፉ አካላት የትምህርት ቤቱ አመራር የሚጎድሉትን ክፍተቶች
ለይቶ መደገፍ አለመቻል
• ስልታዊ ዕቅዱ ከትምህርት ቤቱ ራዕይና ተልዕ ጋር የተገናዘበ (የተናበበ) አለመሆኑ

31
• አመታዊ ዕቅዱ ከሶስት አመት ስልታዊ ዕቅድ የተቀዳ አለመሆኑ

የሚከናወኑ ተግባራት

አመላካች 7.1 ትምህርት ቤቱ የቅድሚያ ትኩረት የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ከባለድርሻ አካላት


ጋር በመሆን መረጃ ላይ በመመስረት መለየትና ማቀድ ይጠበቅበታል፡፡
• ለትምህርት ቤት አመራርና ለሚመለከታቸው አካላት የዕቅድ አስተቃቀድ ግንዛቤ
በሚመለከታቸው አካላት መፈጠር ይኖርበታል፣
7.2. ትምህርት ቤቱ የሶስት ዓመት ስልታዊና አመታዊ እቅዶችን የሚመለከታቸውን
ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ ስለማዘጋጀቱ
• ትምህርት ቤቱ ከውጭ ኢንስፔክሽን የተሰጡ አስተያየቶችን በዕቅድ ውስጥ አካቶ
ማቀድ ይጠበቅበታል
• ትምህርት ቤቱ የዕቅድ ፎርማቱን ተከትሎ ማቀዱን የቅርብ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
ያስፈልጋል፡፡
• ስልታዊ ዕቅዱ ከትምህርት ቤቱ ራዕይና ተልዕ ጋር የተገናዘበ (የተናበበ) መሆን
ይገባዋል፡፡
• አመታዊ ዕቅዱ ከሶስት አመት ስልታዊ ዕቅድ የተቀዳና የዘመኑን የትምህርት ውጤት
በመተንነተን ጠንካራና ደካማ ጎኑን በመለየት መሰራት ይኖርበታል፡፡

3.2. የሂደት ስታንዳርድ

ስታንዳርድ 8: የተማሪዎች መማርና ተሳትፎ ጎልብቷል፡፡

ይህ ስታንዳርድ ተማሪዎች መምህራኖቻቸው የሚሰጧቸውን ስራዎች በትጋት መፈጸም፣


በክፍል ውስጥ ጥያቄ መጠይቅና መሳተፍ፣ በአደረጃጀት መተጋገዝ፣ በተጓዳኝ ክበብ
ተደራጅተውና ንቁ ተሳታፊ ሆነው የውሳኔ ሰጭነት ልምድ እንዲኖራቸው መደረግ
እንዳለበት የሚያመላከት ነው።

32
ሰንጠረዠ 8. በዳግም ኢንስፔክሽን ውጤት

2009 እና 2010 ዓ.ም የትምህርት ቤቶች የዳግም ኢንስፔክሽብ ውጤት ትንታነ


ስታንዳርደ 8
%(ደረጃ 3
እና ደረጃ
ደረጃ ደረጃ ደረጃ ደረጃ %(ደረጃ % (ደረጃ 4)
ክልል 1 2 3 4 ድምር 3) 4)
አዲስ አበባ 61 425 258 8 752 34.31 1.06 35.37
አፋር 179 128 22 3 332 6.63 0.90 7.53
አማራ 1479 4627 826 23 6955 11.88 0.33 12.21
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 150 229 31 4 414 7.49 0.97 8.45
ድሬዳዋ 8 44 23 3 78 29.49 3.85 33.33
ሶማሌ 159 65 12 2 238 5.04 0.84 5.88
ጋምቤላ 7 8 1 16 6.25 0.00 6.25
ሀረሪ 2 20 2 24 8.33 0.00 8.33
ኦሮሚያ 2348 7041 1666 46 11101 15.01 0.41 15.42
ደቡብ 661 1429 309 17 2416 12.79 0.70 13.49
ትግራይ 141 443 154 6 744 20.70 0.81 21.51
ሃገር አቀፍ 5195 14459 3304 112 23070 14.32 0.49 14.81

ሀ/ በሀገርአቀፍ ደረጃ

በሀገርአቀፍ ደረጃ 23070 ት/ቤቶች ሲኖሩ በስታንዳርዱ በደረጃ 3 (14.32%) እና 4 (0.49%)


ላይ ያሉ ወይም ደረጃቸውን ያሟሉ 14.81 በመቶ ብቻ ናቸው። በመሆኑም በሀገርአቀፍ ደረጃ
የኢንስፔክሽን ትንተና እንደሚያሳየው ትምህርት ቤቱ የተማሪዎች መማርና ተሳትፎ
እንዲጎለብት ከማድረግ አንጻር ብዙ መስራት እንዳለበት ያመለክታል።

Implication ይቀመጥ

33
ለ/ በክልል ደረጃ

በክልል ደረጃ ከስታንዳርዱ አንጻር ሲታይ የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው ማለትም አዲስ አበባ
(35.37%) እና ድሬዳዋ (33.33%) ደረጃቸውን ያሟሉ ት/ቤቶች አሏቸው። ዝቅተኛ አፈጻጸም
ያሏቸው ክልሎች ደግሞ ሶማሌ (94.12%)፣ ጋምቤላ (93.75%) እና አፋር (92.42%)
ደረጃቸውን ያላሟሉ ትምህርት ቤቶች ያሏቸው መሆኑን መረጃው ያመለክታል።

ተጠቃሽ የሆኑ ችግሮች (ገላጭና አመላካች)

ከላይ እንደሚታየው ከደረጃ በታች የሆኑ ት/ቤቶች ያሏቸው አብዛኛው ክልሎች ሲሆኑ ለዚህም
ከሚጠቀሱ ችግሮች መካከል፡

• ተማሪዎች በክፍል ፣ በቤት ስራና በፕሮጀክት የተሰጣቸውን ተግባራት በግልና


በቡድን የመስራት ችግር ያለባቸው መሆኑ፣
• ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ጥያቄ በመጠየቅም ሆነ መልስ በመመለስ የነቃ ተሳትፎ
የማያደርጉ መሆናቸው፣
• ተማሪዎች ለትምህርት በሚመች አደረጃጀት ተደራጅተው የማይተጋገዙ መሆናቸው፤
• ተማሪዎች በቡድን ለመደራጀት ፍላጎት የሌላቸው መሆኑ፣
• ትምህርት ቤቱ የተጓዳኝ ክበባት ለመማር ማስተማሩ ያለውን ጠቀሜታ በሚገባ
አለማስገንዘቡ፣
• ተማሪዎች የተጓዳኝ ክበባት ጠቀሜታን ተረድተው የመሳተፍ ፍላጎታቸው ዝቅተኛ
መሆን ፣
• ህጻናት በፓርላማ በመደራጀት በመማር ማስተማሩ ሂደት ስኬታማነት የውሳኔ
ሰጭነት ሚናቸው ዝቅተኛ መሆን፣

የሚከናወኑ ተግባራት

አመልካች 8.1 ተማሪዎች የተሰጧቸውን ስራዎች በትጋት ስለመስራታቸው፡፡


• ተማሪዎች በክፍል፣ በቤት ስራና በፕሮጀክት የተሰጣቸውን ተግባራት በግልና በቡድን
የመስራት ልምድ እንዲኖራቸው የትምህርት ቤቱ አመራር ከመምህራን ጋር በመሆን
ግንዛቤ መፍጠር ይገባል፤

34
አመልካች 8.2.ተማሪዎች ጥያቄዎችን ለመጠየቅና መልሶችን ለመመለስ የነቃ ተሳትፎ
ስለማድረጋቸው፤

• ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ጥያቄ በመጠየቅም ሆነ መልስ በመመለስ የነቃ ተሳትፎ


እንዲያደርጉ መምህራን ማበረታት ይጠበቅባቸዋል፣
• መምህራን ወንድና ሴት ተማሪዎችን በእኩልነት በማሳተፍ ለመማር ማስተማሩ ምቹ
ሁኔታ መፍጠር ይገባቸዋል፡፡
አመልካች8.3. ተማሪዎች በአንድ ለአምስትና መሰል አደረጃጀቶች ተደራጅተው
ስለመረዳዳታቸው
• የትምህርት ቤቱ አመራር ተማሪዎችን ለትምህርት በሚመች አደረጃጀት እንዲደራጁ
በማድረግ በትምህርታቸው የሚተጋገዙበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር ይገባል፤
• የትምህርት ቤቱ አመራር ለተማሪዎች በቡድን የመደራጀትን ጠቀሜታ በማስገንዘብ
እንዲደራጁ ማድረግ ይገባዋል፣
• ትምህርተ ቤቱ የክፍል ውስጥ አደረጃጀት ለተማሪ ተኮር የማስተማር ስነ ዘዴ
ተግባራዊ ለማድረግ በሚያመች መንገድ ማደራጀት አለበት፤

አመልካች 8.4. ተማሪዎች በተለያዩ ተጓዳኝ ክበባት በመደራጀት ንቁ ተሳትፎ


ስለማድረጋቸው፤

• ትምህርት ቤቱ ተማሪዎች የተጓዳኝ ክበባት ለመማር ማስተማሩ ያለውን ጠቀሜታ


ተረድተው እንዲሳተፉ ግንዛቤ መፍጠር ይጠበቅበታል፣
• ክበባት ሲቋቋሙ ዕቅዳቸው ከትምህርት ቤት መሻሻል መርሃ ግብር እቅድ ጋር
የተናበበ መሆን አለበት

አመልካች 8.5. ተማሪዎች በህጻናት ፓርላማ ተደራጅተው በመማር ማሰተማር የውሳኔ


አሰጣጥ ሂደት ተሳትፎ ስለማድረጋቸው፤

• ትምህርት ቤቱ ህጻናትን በፓርላማ በማደራጀት በመማር ማስተማሩ ሂደት


ስኬታማነት የውሳኔ ሰጭነት ሚናቸው ከፍ እንዲል መስራት አለባት፣

ስታንዳርድ 9፡- ተማሪዎች በትምህርት አቀባበላቸው መሻሻል አሳይተዋል ፡፡

35
ይህ ስታንዳርድ ተማሪዎች ሳያረፍዱ፣ ሳይቀሩ፣ሳያቋርጡና ክፍል ሳይደግሙ የትምህርት
ጊዜያቸውን በአግባቡ በመጠቀም በራስ ተነሳሽነት የፈጠራ ስራን በማከናወንና ለሁሉም
የትምህርት አይነቶች እኩል ክብደት በመስጠት፤ የኩረጃን ጸያፍነት ባህል በማድረግና
በራሳቸው ብቃት የሚተማመኑ እንዲሁም ለትምህርታቸው ትኩረት የሚሰጡ መሆናቸውን
የሚያረጋግጥ ነው፡፡

ሰንጠረዥ 9.

2009 እና 2010 ዓ.ም የትምህርት ቤቶች የዳግም ኢንስፔክሽብ ውጤት


ትንታኔ ስታንዳርደ 9
% % % (ደረጃ 3 እና
ደረጃ ደረጃ ደረጃ ደረጃ ድም (ደረጃ (ደረጃ ደረጃ 4)
ክልል 1 2 3 4 ር 3) 4)
53 472 221 6 752 29.39 0.80 30.19
አዲስ አበባ
203 113 15 1 332 4.52 0.30 4.82
አፋር
195 455 695
7 9 424 15 5 6.10 0.22 6.31
አማራ
ቤኒሻንጉል 174 222 18 414 4.35 0.00 4.35
ጉሙዝ
13 47 17 1 78 21.79 1.28 23.08
ድሬዳዋ
153 72 10 3 238 4.20 1.26 5.46
ሶማሌ
4 13 922 939 98.19 0.00 98.19
ጋምቤላ
8 16 24 0.00 0.00 0.00
ሀረሪ
309 705 111
3 9 922 27 01 8.31 0.24 8.55
ኦሮሚያ
136 241
882 0 165 8 5 6.83 0.33 7.16
ደቡብ

36
168 511 64 1 744 8.60 0.13 8.74
ትግራይ
670 144 239
8 44 2778 62 92 11.58 0.26 11.84
ሃገር አቀፍ

ሀ/ በሀገርአቀፍ ደረጃ

በሀገርአቀፍ ደረጃ 23992 ት/ቤቶች ሲኖሩ በስታንዳርዱ በደረጃ 3 (11.58%) እና 4 (0.26%)


ላይ ያሉ ወይም ደረጃቸውን ያሟሉ 11.84 በመቶ ብቻ ናቸው። በመሆኑም በሀገርአቀፍ ደረጃ
የኢንስፔክሽን ትንተና እንደሚያሳየው ተማሪዎች በትምህርት አቀባበላቸው መሻሻል ማሳየት
እንዳለባቸው ያመለክታል።

Implication ይቀመጥ

ለ/ በክልል ደረጃ

በክልል ደረጃ ከስታንዳርዱ አንጻር ሲታይ የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው ማለትም ጋምቤላ
(98.19%) ደረጃቸውን ያሟሉ ት/ቤቶች አሉት። ዝቅተኛ አፈጻጸም ያሏቸው ክልሎች ደግሞ
ሀረሪ (100%)፣ ቤንሻንጉል (85.65%) ፣ አፋር (95.18%)፣ ሶማሌ (94.54%) እና አማራ (93.4
%) ያህሉ ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች መሆናቸውን መረጃው ያመለክታል።

ተጠቃሽ የሆኑ ችግሮች (ገላጭና አመላካች)

ከላይ ለማየት እንደተሞከረው ዝቅተኛ አፈጻጸም ያላቸው በአብዛኛው ክልሎች መሆኑን


ሲያሳይ በተለይ የሀረሪ ክልል ምንም ትምህርት ቤት ደረጃውን አለማሟላቱን ያመለክታል፡፡
ለዚህም እንደምክንያትነት የሚወሰዱት፡

• የተማሪዎች ማርፈድ፣ መቅረት፣ ማቋረጥና መድገም ከፍተኛ መሆን


• በትምህርት ቤቱ ምቹ ሁኔታ ባለመፈጠሩ ተማሪዎች በራሳቸው ተነሳሽነት የፈጠራ ስራ
የሚሰሩ አለመሆናቸው
• ተማሪዎች ለሁሉም የትምህርት ዓይነቶች እኩል ክብደት ሰጥተው አለመከታተላቸው

37
• ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ ባለመከታተላቸው፣ ማርፈድና መቅረት
በማዘውተራቸው በራሳቸው ጥረት ምዝናዎችን ከመስራት ይልቅ ኩረጃ ላይ የሚያተኩሩ
መሆናቸው
• ተማሪዎች የክፍል ስራ ፣ የቤት ስራ እና የቡድን ስራዎችን ተከታትለው አለመስራታቸው
• የትምህርት ቤቱ አመራር በማርፈድ ፣በመቅረትና በኩረጃ ላይ ለተማሪዎች ግንዛቤ
አለመፍጠራቸው
• የትምህርት ቤት አመራሩና መምህራን የተማሪዎችን ማርፈድ፣ መቅረትና ማቋረጥ
አስመልክቶ በቂ ክትትል ማድረግ አለባቸው፤
• መምህራን ተማሪዎች ሳያረፍዱና ሳይቀሩ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ሳቢና ማራኪ
የሆነ አቀራረብ ተዘጋጅተው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤
• ወላጆች ልጆቻቸው ትምህርታቸውን ሳያረፍዱና ሳይቀሩ እየተከታተሉ ለመሆናቸው
የቅርብ ክትትል አለማድረጋቸው፣

የሚከናወኑ ተግባራት

9.1. ተማሪዎች የትምህርት ጊዜያቸውን ሳያባክኑ በአግባቡ ስለመጠቀማቸው

• ተማሪዎች እንዳያረፍዱ፣ እንዳይቀሩ እና ትምህርትቸውን በአግባቡ እነዲከታተሉ


በትምህርት ቤት አመራሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በተከታታይ መፍጠር
• የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ለወላጆች ተከታታይነት ባለው መንገድ ልጆቻቸውን ወደ
ትምህርት ቤት እንዲልኩ ማስገንዘብ፣

9.2. ተማሪዎች በራሳቸው ተነሳሽነት አዲስ ነገርን መፍጠር፣ መመራመር እና የራሳቸውንና


የአካባቢያቸውን ችግሮች መፍታት ስለመቻላቸው

• ትምህርት ቤቱ ምቹ ሁኔታ በመፈጠር ተማሪዎች በራሳቸው ተነሳሽነት የፈጠራ ስራና


ምርምር በማድረግ የአካባቢያቸውን ችግሮች የሚፈቱበትን ስልት መቀየስ
• ተማሪዎች በፈጠራ ስራዎች እንዲበረታቱ ትምህርታዊ ጉብኝቶችን ማዘጋጀት
• ትምህርት ቤቱ በተማሪዎች የተሰሩ የፈጠራ ስረዎችን ለወላጆች በማሰተዋወቅ ተማሪዎቹ
የሚበረታቱበትን መንገድ ማመቻቸት

9.3. ተማሪዎች ለሚማሩት ትምህርት ሁሉ ተመጣጣኝ ክብደት ስለመስጠታቸው

38
• ተማሪዎች ለሁሉም የትምህርት ዓይነቶች እኩል ክብደት ሰጥተው እንዲከታተሉ
ግንዛቤ በመፍጠር ስልት ቀይሶ መንቀሳቀስ
• በተለያየ ሙያ የተመረቁ ውጤታማ ሰዎችን ትምህርት ቤት ድረስ በመጋበዝና
ተሞክሯቸውን እንዲያቀርቡ በማድረግ ተማሪዎችን ማነቃቃት

9.4. ተማሪዎች በፈተና/ምዘና የሚፈጠር ኩረጃ ጸያፍ መሆኑን ስለመገንዘባቸው

• ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ፣ ማርፈድና መቅረት


እንዳያዘወትሩና በራሳቸው ጥረት ምዝናዎችን እንዲሰሩ በማድረግ ከኩረጃ ነጻ
የሚሆኑበትን አሰራር በመዘርጋት ተግባራዊ ማድረግ
• ተማሪዎች የሚሰጧቸውን የክፍል ስራዎች፣ የቤት ስራዎችና የቡድን ስራዎችን በራሳቸው
ጥረት እንዲሰሩ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
• በራሳቸው ጥረት የቤት ስራዎችን፣ የክፍል ስራዎችንና የቡድን ስራዎችን በታታሪነት
የሚሰሩ ተማሪዎች ተለይተው የሚበረታቱበትን ስርዓት መዘርጋትና ተግባራዊ ማድረግ
• የሚኩረጁ ተማሪዎች ተለይተው ኩረጃ ወንጀል መሆኑን ሊያስተምር የኒችል እርምጃ
መውሰድ

ስታንዳርድ10. ተማሪዎች ለትምህርት ቤታቸው በጎ አመለካከት አላቸው

ይህ ስታንዳርድ ተማሪዎች በትምህርት ቤቱ አገልግሎት መርካታቸውን፣ ለትምህርት ቤቱ


ስራ ድጋፍ ስለማድረጋቸው፣ የሚያስተምሯቸውን መምህራኖች በቅርበት አውቀው መገምገም
መቻላቸውን እንዲሁም ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ተገቢውን አክብሮት በመስጠት
የትምህርት ቤቱን ህግና ደንብ የሚያከብሩ መሆናቸውን የሚያመለክት ነው፡፡

ሰንጠረዥ 10

2009 እና 2010 ዓ.ም የትምህርት ቤቶች የዳግም ኢንስፔክሽብ ውጤት ትንታነ


ስታንዳርደ 10
% (ደረጃ 3
ደረጃ ደረጃ % (ደረጃ % (ደረጃ እና ደረጃ
ክልል ደረጃ 1 ደረጃ 2 3 4 ድምር 3) 4) 4)
45 342 348 21 756 46.03 2.78 48.81
አዲስ አበባ
161 135 36 4 336 10.71 1.19 11.90
አፋር

39
871 4425 1587 76 6959 22.81 1.09 23.90
አማራ
ቤኒሻንጉል 70 280 61 7 418 14.59 1.67 16.27
ጉሙዝ
6 41 33 1 81 40.74 1.23 41.98
ድሬዳዋ
126 82 29 5 242 11.98 2.07 14.05
ሶማሌ
3 8 5 16 31.25 0.00 31.25
ጋምቤላ
8 13 3 24 12.50 0.00 12.50
ሀረሪ
1320 6980 2665 137 11102 24.00 1.23 25.24
ኦሮሚያ
362 1402 550 102 2416 22.76 4.22 26.99
ደቡብ
89 422 212 20 743 28.53 2.69 31.22
ትግራይ
3061 14130 5529 373 23093 23.94 1.62 25.56
ሃገር አቀፍ

ሀ/ በሀገርአቀፍ ደረጃ

በሀገርአቀፍ ደረጃ 23093 ት/ቤቶች ሲኖሩ በስታንዳርዱ በደረጃ 3 (23.94%) እና 4 (1.62%)


ላይ ያሉ ወይም ደረጃቸውን ያሟሉ 25.56 በመቶ ብቻ ናቸው። በመሆኑም በሀገርአቀፍ ደረጃ
የኢንስፔክሽን ትንተና እንደሚያሳየው ተማሪዎች ለትምህርት ቤታቸው በጎ አመለካከት
እንደሌላቸው ያመለክታል፡፡

ለ/ በክልል ደረጃ

በክልል ደረጃ ከስታንዳርዱ አንጻር ሲታይ የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው ማለትም አዲስ አበባ
(48..81%) ፣ ድሬዳዋ (41.98%)ደረጃቸውን ያሟሉ ት/ቤቶች አሏቸው። ዝቅተኛ አፈጻጸም
ያሏቸው ክልሎች ደግሞ አፋር (88.1%)፣ ሀረሪ (87.5%) ፣ ሶማሌ (85.95%)፣ ያህሉ ትምህርት
ቤቶች ከደረጃ በታች መሆናቸውን መረጃው ያመለክታል።

ተጠቃሽ የሆኑ ችግሮች (ገላጭና አመላካች)

40
ከላይ ለማየት እንደተሞከረው ዝቅተኛ አፈጻጸም ያላቸው በአብዛኛው ክልሎች መሆኑን
ሲያሳይ በተለይ አፋር ፣ ሀረሪ እና ሶማሌ ክልሎች በርካታ ትምህርት ቤቶች ደረጃውን
አለማሟላታቸው ያመላክታል፡፡ ለዚህም እንደምክንያትነት የሚወሰዱት፡

• መምህራን የሚያስተምሩትን ትምህርት ተዘጋጅተውና ተማሪዎችን በሚያረካ መልኩ


አለማስተማራቸው
• የትምህርት ቤቱ አመራር የተማሪዎች አያያዝና ግንኙነት አወንታዊነት የጎደለው
መሆኑ
• የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ተማሪዎችን ባሳተፈና የትምህርት ቤቱን ንብረት
እንዲንከባከቡ፣ በአግባቡ እንዲጠብቁና እንዲጠቀሙ አለማድረጉ
• ተማሪዎች ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ተገቢውን ክብር መስጠት አለመቻላቸው
• ትምህርት ቤቱ ለተማሪዎች የትምህርት ቤቱን ህግና ደንብ አለማስገንዘቡ
• ተማሪዎች የትምህርት ቤቱን ህግና ደንብ አለማክበራቸው

የሚከናወኑ ተግባራት

10.1. ተማሪዎች ትምህርት ቤቱ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ስለመርካታቸው

• መምህራን የሚያስተምሩትን ትምህርት በአግባቡ ተዘጋጅተውና ተማሪዎችን በሚያረካ


መልኩ ማስተማር አለባቸው
• መምህራን የሚያስተምሩትን ትምህርት በአግባቡ ተዘጋጅተው እንዲገቡና
እንዲያስተምሩ የትምህርት ቤቱ አመራር ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
ይጠበቅበታል

10.2. ተማሪዎች ትምህርት ቤቱ ለሚያከናውናቸው ስራዎች ድጋፍ ስለማድረጋቸው

• የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ተማሪዎችን በማሳተፍ የትምህርት ቤቱን ንብረት


እንዲንከባከቡ፣ በአግባቡ እንዲጠብቁና እንዲጠቀሙ ግንዛቤ መፍጠር ይጠበቅበታል

10.3. ተማሪዎች መምህራኖቻቸውን በአግባቡ መገምገም ስለመቻላቸው

• የትምህርት ቤቱ አመራር ተማሪዎች መምህራኖቻቸውን በየጊዜው መገምገም


የሚችሉበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይጠበቅበታል

41
• ተማሪዎች በክፍል ውስጥ በአግባቡ የሚያስተምሩና የማያስተምሩ መምህራንን
በመለየት ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር በሪፖርት ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል

10.4. ተማሪዎች ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ተገቢውን አክብሮት ስለመስጠታቸው

• ተማሪዎች ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በክፍል ውስጥና ከክፍል ውጭ ተገቢውን


ክብር መስጠት እንዲችሉ የትምህርት ቤቱ አመራር ግንዛቤ መፍጠር ይጠበቅበታል

10.5. ተማሪዎች የትምህርት ቤቱን ህግና ደንቦች ተቀብለው ተግባራዊ ስለማድረጋቸው

• ትምህርት ቤቱ ለተማሪዎች የትምህርት ቤቱን ህግና ደንብ ከተማሪዎች ጋር በጋራ


ማውጣት ይኖርበታል፡፡
• በትምህርት ቤቱና በታማሪዎች የወጡ ህግና ደንቦች ሁሉም ተማሪዎችና የትምህርት
ቤቱ ማህበረሰብ ሊያዩት በሚችሉ ቦታ መገኘት ይጠበቅበታል፤
• ተማሪዎች ከትምህርት ቤቱ ህግና ደንብ የተቀዳ የከፍል ውስጥ መተዳደሪያ ደንብ
እንዲያዘጋጁ መምህራን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል
• ተማሪዎች የትምህርት ቤቱንና የራሳቸውን ህግና ደንብ ማክበር ይጠበቅባቸዋል

ስታንዳርድ 11. መምህራን የሚያስተምሩት ትምህርት በአግባቡ የታቀደ፣ በአመቺ


የትምህርት መርጃዎች የተደገፈ እና ከፍተኛ የትምህርት ውጤትን ለማስገኘት አልሞ
የተዘጋጀ ነው

ይህ ስታንደርድ መምህራን የትምህርት ዕቅድ ዝግጅት ፎርማቱን ተከትለው መርጃ መሳሪያና


ዘመናዊ ቴክኖሎጅን በመጠቀም ትምህርቱን በተግባር በማስደገፍ እና ተማሪዎች
ከአካባቢያቸው በሚገኙ ቁሳቁሶች የትምህርት መርጃ መሳሪያ ማዘጋጀት እንደሚችሉ
በማሳወቅ ተማሪዎቻቸው ውጤታማ እንዲሆኑ በማጠናከሪያ ትምህርት መደገፍ እንዳለባቸው
ያመላክታል፡፡

ሰንጠረዥ 11.

2009 እና 2010 ዓ.ም የትምህርት ቤቶች የዳግም ኢንስፔክሽብ ውጤት ትንታነ


ስታንዳርደ 11
% (ደረጃ 3
ደረጃ ደረጃ % (ደረጃ % (ደረጃ እና ደረጃ
ክልል ደረጃ 1 ደረጃ 2 3 4 ድምር 3) 4) 4)
42
125 454 171 2 752 22.74 0.27 23.01
አዲስ አበባ
233 90 8 1 332 2.41 0.30 2.71
አፋር
2816 3754 369 16 6955 5.31 0.23 5.54
አማራ
ቤኒሻንጉል 259 148 7 0 414 1.69 0.00 1.69
ጉሙዝ
20 50 8 0 78 10.26 0.00 10.26
ድሬዳዋ
190 40 7 237 2.95 0.00 2.95
ሶማሌ
15 1 16 6.25 0.00 6.25
ጋምቤላ
6 17 1 24 4.17 0.00 4.17
ሀረሪ
4805 5594 680 22 11101 6.13 0.20 6.32
ኦሮሚያ
1220 1048 139 9 2416 5.75 0.37 6.13
ደቡብ
234 441 68 743 9.15 0.00 9.15
ትግራይ
9923 11636 1459 50 23068 6.32 0.22 6.54
ሃገር አቀፍ

ሀ/ በሀገርአቀፍ ደረጃ

በሀገርአቀፍ ደረጃ 23068 ት/ቤቶች ሲኖሩ በስታንዳርዱ በደረጃ 3 (6.32%) እና 4 (0.22%)


ላይ ያሉ ወይም ደረጃቸውን ያሟሉ 6.54 በመቶ ብቻ ናቸው። በመሆኑም በሀገርአቀፍ ደረጃ
የኢንስፔክሽን ትንተና እንደሚያሳየው በአብዛኛው መምህራን የሚያስተምሩት ትምህርት
በአግባቡ የታቀደ፣ በአመቺ የትምህርት መርጃዎች የተደገፈ እና ከፍተኛ የትምህርት
ውጤትን ለማስገኘት አልሞ የተዘጋጀ አለመሆኑን ያመለክታል፡፡

ለ/ በክልል ደረጃ

43
በክልል ደረጃ ከስታንዳርዱ አንጻር ሲታይ የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው ማለትም አዲስ አበባ
(23.01%) ፣ ድሬዳዋ (10.26%) እና ትግራይ (9.15%) ደረጃቸውን ያሟሉ ት/ቤቶች
አሏቸው። ዝቅተኛ አፈጻጸም ያሏቸው ክልሎች ደግሞ ቤኒሻንጉል (98.31%)፣ አፋር
(97.29%) እና ሶማሌ (97.05%) ያህሉ ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች መሆናቸውን መረጃው
ያመለክታል።

ተጠቃሽ የሆኑ ችግሮች (ገላጭና አመላካች)

ከላይ ለማየት እንደተሞከረው ዝቅተኛ አፈጻጸም ያላቸው በአብዛኛው ክልሎች መሆኑን


ሲያሳይ በተለይ ቤኒሻንጉል ፣ አፋር እና ሶማሌ ክልሎች በርካታ ትምህርት ቤቶች ደረጃውን
አለማሟላታቸው ያመላክታል፡፡ ለዚህም እንደምክንያትነት የሚወሰዱት፡

• መምህራን የትምህርት ዕቅድ ዝግጅታቸውን በሚፈለገው የዕቅድ ፎርማት መሰረት


ማቀድ አለመቻላቸው
• መምህራን ከትምህርት ይዘቱ ጋር ተስማሚ የሆነ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን
አዘጋጅተው መተግበር አለመቻላቸው
• የትምህርት ቤቱ አመራር ለዘመናዊ ቴክኖሎጅ ትኩረት ሰጥቶ መምህራን
እንዲጠቀሙበት ማድረግ አለመቻሉ
• መምህራን የንደፈ ሃሳብ ትምህርቱን በተግባር አስደግፈው ትምህርቱ ህይወት
እንዲኖረው ማድረግ አለመቻላቸው
• መምህራን ተማሪዎቻቸው በፈጠራ ስራዎች እንዲሳተፉ የሚያስችሉ አሰራሮችን
ዘርግተው ተግባራዊ አለማድረጋቸው
• ትምህርት ቤቱ የማጠናከሪያ ትምህርት ፕሮግራም አዘጋጅቶ ድጋፍና ክትትል
በማድረግ የማጠናከሪያ ትምህርት እንዲሰጥ አለማድረጉ
የሚከናወኑ ተግባራት

11.1. የመምህራን የትምህርት ዕቅድ የሚያስተምሩት ትምህርት ዓላማ፣ ይዘት የመምህሩ


ተግባር፣ የተማሪው ተግባርና የምዘና አፈጻጸም ስለማከተቱ

• መምህራን የትምህርት ዕቅድ ዝግጅታቸውን በሚፈለገው የዕቅድ ፎርማት መሰረት


አቅደው ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው

44
✓ መምህራን ዕለታዊ፣ ሳምንታዊ፣ ወርሃዊና ዓመታዊ የትምህርት ዕቅድ
ማዘጋጀታቸው ተረጋግጦ ተግባራዊ መሆን አለበት

11.2. መምህራን የመማሪያ ማስተማሪያ መርጃ መሳሪያዎች በማዘጋጀት ጥቅም ላያ


ስለማዋላቸው

• መምህራን በራሳቸው የተዘጋጁና ትምህርት ቤቱ በግዥ የሚያቀርብላቸውን


የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች ከትምህርት ይዘቱ ጋር በማገናዘብ መጠቀም
አለባቸው
• መምህራን የሚጠቀሙት የትምህርት መርጃ መሳሪያ በዕለታዊ የትምህርት ዕቅድ
ውስጥ አካተው መተግበር ይጠበቅባቸዋል

11.3. መምህራን የሚያስተምሩትን ትምህርት በዘመናዊ ቴክኖሎጅ (ሬዲዮ፣ቴሌቪዥን፣


ኮምፒዩተር ወዘተ) ስለመደገፋቸው

• የትምህርት ቤቱ አመራር ለዘመናዊ ቴክኖሎጅ ትኩረት ሰጥቶ መምህራን


እንዲጠቀሙበት ምቹ ሁኔታ መፍጠር አለበት

11.4. መምህራን የሚያስተምሩትን ትምህርት በሳይንስ ኪት፣ በቤተሙከራና በመስክ ምልከታ


አስደግፈው ስለመስጠታቸው

• የትምህርት ቤቱ አመራር መምህራን የንድፈ ሀሳቡን ትምህርት በተግባር


እንዲያስደግፉ ተፈላጊ ግብዓቶችን ማሟላት፣ ምቹ ሁኔታ መፍጠርና ድጋፍና
ክትትል ማድረግ ይጠበቅበታል
• መምህራን የንደፈ ሃሳብ ትምህርቱን በተግባር አስደግፈው ትምህርቱ ህይወት
እንዲኖረው ማድረግ አለባቸው

11.5. መምህራን የሳይንስና ቴክኖሎጅ ትምህርትን ውጤታማ ለማድረግ ተማሪዎቻቸው


የአካባቢ ቁሳቁስ ተጠቅመው የፈጠራ ስራ እንዲሰሩ ስለማበረታታቸው

• መምህራን ከሳይንስና ቴክኖሎጅ ትምህረቶች ጋር የሚገናኙ የፈጠራ ስራዎችን ሰርቶ


በማሳየት ለተማሪዎቻቸው ሞዴል(አርአያ) መሆን ይገባቸዋል

45
• መምህራን ተማሪዎቻቸው በፈጠራ ስራዎች እንዲሳተፉ የሚያስችሉ አሰራሮችን
ዘርግተው ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል

11.6. መምህራን ተማሪዎቻቸው በትምህርታቸውና በውጤታቸው እንዲሻሻሉ የማጠናከሪያ


ትምህርት ስለመስጠታቸው

• ትምህርት ቤቱ የማጠናከሪያ ትምህርት ፕሮግራም አዘጋጅቶ ስለ አተገባበሩ


ከመምህራን ጋር በመወያየት ድጋፍና ክትትል በማድረግ የማጠናከሪያ ትምህርት
እንዲሰጥ ማድረግ አለበት

ስታንዳርድ 12: መምህራን የሚስተምሩትን የትምህርት ይዘት ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡

የስታንዳርዱ ትንተና

ይህ ስታንዳርድ መምህራን በሚያስተምሩት የትምህርት ይዘት ላይ በቂ ዕውቀትና


ክህሎት ኖሯቸው ቁልፍ ጽንሰ-ሀሳቦችን ትኩረት በመስጠት ለተማሪዎች በሚመጥን
አቀራረብ ትምህርት መስጠታቸውን የሚመለከት ነው።

ሰንጠረዠ 12 በዳግም ኢንስፔክሽን ውጤት ከስታንዳርድ 12 አንጻር

የስታንዳርድ 12 የዳግም ኢንስፔክሽን ውጤት ትንተና


ደረጃ ደረጃ ደረጃ
ደረጃ
ክልል 2 3 4 ደረጃ 1 ደረጃ 2
1
ድምር በመቶኛ በመቶኛ ደረጃቸውን

46
ያሟሉ
በመቶኛ
አዲስ አበባ 36 258 442 16 752 4.79 34.31 68.9
አፋር 100 163 60 9 332 30.12 49.10 20.8
አማራ 300 3308 3227 121 6956 4.31 47.56 48.1
ቤንሻንጉል-
ጉሙዝ 22 285 102 5 414 5.31 68.84 25.9
ድሬዳዋ 1 35 36 6 78 1.28 44.87 53.9
ኢትዮ-ሶማሌ 102 100 34 2 238 42.86 42.02 15.1
ጋምቤላ 5 7 4 16 31.25 43.75 25
ሀረሪ 6 18 24 0.00 25.00 75
ኦሮሚያ 684 5018 5005 394 11101 6.16 45.20 48.6
ደ/ብ/ብ/ህ 189 1240 919 68 2416 7.82 51.32 40.9
ትግራይ 26 341 350 27 744 3.49 45.83 50.7
ሀገር አቀፍ 1465 10761 10197 648 23071 6.35 46.64 47

ሀ/ በሀገርአቀፍ ደረጃ

በሀገርአቀፍ ደረጃ 23071 ት/ቤቶች ሲኖሩ በስታንዳርዱ በመሆኑ ደረጃቸውን ያሟሉ 47


በመቶ ሲሆኑ በደረጃ 1 (6.35%) እና 2 (46.6%) ላይ ደረጃቸውን ያላሟሉ ናቸው። በመሆኑም
በሀገርአቀፍ ደረጃ የኢንስፔክሽን ትንተና እንደሚያሳየው መምህራን የሚስተምሩትን
የትምህርት ይዘት ጠንቅቀው ከማወቃቸው አንጻር ብዙ መስራት እንዳለበት ያመለክታል።

የዚህ ስታንዳርድ ባግባቡ መከናወኑ መምህራን የተማሪዎቻቸው የትምህርት አቀባበል ባገናዘ


መልኩ ስለሚያስተምሩ ተማሪዎች የትምህርቱን ይዘት በተገቢው መንገድ እንዲያውቁ
ያግዛል።

ለ/ በክልል ደረጃ

በክልል ደረጃ ከስታንዳርዱ አንጻር ሲታይ የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው ማለትም ሀረሪ (75%)
እና አዲስ አበባ (61%) ደረጃቸውን ያሟሉ ት/ቤቶች አሏቸው። ዝቅተኛ አፈጻጸም ያሏቸው
ክልሎች ደግሞ ኢትዮ-ሶማሊ 15% ፣ አፋር 21%፣ ጋምቤላ 25% እና ቤንሻንጉል-ጉሙዝ
26% ት/ቤቶች መሆናቸውን መረጃው ያመለክታል።

ተጠቃሽ የሆኑ ችግሮች

47
ከላይ እንደሚታየው ከደረጃ በታች የሆኑ ት/ቤቶች ያሏቸው ክልሎች ታዳጊ ክልሎች ሲሆኑ
ለዚህም ከሚጠቀሱ ችግሮች መካከል

• በክልሎቹ ለደረጃው የሚመጥኑ መምህራን ባለመመደባቸው የሚያስተምሩትን


ትምህርት ይዘት በማወቅና በማቅረብ በኩል ችግሮች አሉ
• የመምህራን የዕርስ በርስ መደጋገፍና የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ባግባቡ አለመተግበር
• በማስተማር ስነ-ዘዴ ላይ በቂ ስልጠና አለማግኘት
• በቂ የማጣቀሻ መጻህፍት አለመኖርና አለመጠቀም
• የመምህራን የትምህርት ዕቅድ ባግባቡ አለመዘጋጀት

አመላካች 12 1 መምህራን በሚያስተምሩት ትምህርት ይዘት በቂ እውቀትና ክህሎት አላቸው፣


የሚከናወኑ ተግባራት

• በየትምህርት አይነቱ ለደረጃው የሚመጥኑ የመምህራን ፍላጎትን ለይቶ እንዲመደቡ


ማድረግ
• የመምህራን የዕርስ በርስ መደጋገፍና የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ተግባራትን አጠናክሮ
መተግበር
• በተለያዩ ዘዴዎች (በግዢ፣ ከአጋር ድርጅቶች እና ከአካባቢው ተወላጆች) በመጠቀም
መምህራንን የሚያግዙ በቂ የማጣቀሻ መጻህፍት እንዲኖሩ ማድረግ

አመላካች 12.2 መምህራን ለተማሪዎች በሚመጥን ቋንቋ እና አቀራረብ ይዘቱን ቀለል


አድርገው ያቀርባሉ፡
የሚከናወኑ ተግባራት

• መምህራን የሚያቀርቡትን የትምህርት ይዘት ተማሪውን ማዕከል ያደረገ የትምህርት


አቀራረብ በተገቢው መንገድ ተግባራዊ እንዲያረጉ የመማሪያ-ማስተማሪያ ቁሳቁሶችን
በማሟላትና ተገቢውን ስልጠና መስጠት
• የትምህርት ማበልፀጊያ ማዕከላትን ማጠናከርና ለይዘቱ የሚመጥን የትምህርት መርጃ
መሳሪያ በማዘጋጀት ስለመጠቀማቸው ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
• የትምህርት ዕቅድ ዝግጅትንና ተግባራዊነትን የተጠናከረ ክትትልና ድጋፍ ስርዓት
ዘርግቶ ተግባራዊ ማድረግ

48
አመልካች 12.3 መምህራን በትምህርቱ ውስጥ ያሉ ቁልፍ ጽንሰ ሃሳቦችን ለተማሪዎች
በግልጽ ቋንቋ አብራርተው ስለማቅረባቸው

የሚከናወኑ ተግባራት

• መምህራን የሚያቀርቡትን የትምህርት ይዘት ቁልፍ ጽንሰ-ሀሳቦችን ተማሪዎች


እንዲጨብጡ አካባቢን ባገናዘበና ተማሪዎች በቀላሉ ሊረዱት በሚችል መልኩ
ተግባራዊ እንዲያደርጉ ስርዓት ዘርግቶ መከታተል
• መምህሩ የተለያዩ የማጠቀሻ መፃህፍትን እንዲጠቀም ቤተ-መፃህፍትን ማጠናከርና
ክትትል ማድረግ
• በትምህርት ዕቅድ ዝግጅት የይዘት ቁልፍ ፅንሰ-ሀሳቦች መካተታቸውን ማረጋገጥ

ስታንዳርድ 13፦የት/ቤቱ አመራርና መምህራን ለሁሉም ተማሪዎች ተስማሚና ዘመናዊ


የማስተማር ስነ-ዘዴዎችን በመጠቀማቸው የሁሉም ተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎ
ጎልብቷል፡፡

ይህ ስታንዳርድ የትምህርት ቤቱ አመራርና መምህራን ዘመናዊና አሳታፊ የማስተማር ዘዴ


መጠቀማቸውንና የተግባር ምርምር ማድረጋቸውን፣ ተማሪዎች በጥንድና በቡድን
መማማራቸውንና ሴት ተማሪዎችና ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች በቂ ድጋፍ
ማግኘታቸውንና የሁሉም ተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎ መጎልበትን የሚመለከት ነው።

49
ሰንጠረዠ 13 በዳግም ኢንስፔክሽን ውጤት ከስታንዳርድ 13 አንጻር

የዳግም ኢንስፔክሽን የስታንዳርድ 13 ውጤት ትንተና


ደረጃ ደረጃ ደረጃ ደረጃቸውን
ደረጃ ደረጃ 1 ደረጃ 2
ክልል 2 3 4 ድምር ያሟሉ
1 በመቶኛ በመቶኛ
በመቶኛ
አዲስ አበባ 208 410 131 3 752 27.66 54.52 17.9
አፋር 232 92 5 329 70.52 27.96 1.6
አማራ 2322 4080 536 17 6955 33.39 58.66 8
ቤንሻንጉል-
ጉሙዝ 175 214 24 1 414 42.27 51.69 6.1
ድሬዳዋ 11 39 11 61 18.03 63.93 18.1
ኢትዮ-
ሶማሌ 172 55 10 1 238 72.27 23.11 4.7
ጋምቤላ 11 5 16 68.75 31.25 0
ሀረሪ 3 20 1 24 12.50 83.33 4.2
ኦሮሚያ 3158 6749 1168 26 11101 28.45 60.80 10.8
ደ/ብ/ብ/ህ 820 1341 244 9 2414 33.97 55.55 10.5
ትግራይ 160 467 116 1 744 21.51 62.77 15.8
ሀገር አቀፍ 7272 13472 2246 58 23048 31.55 58.45 10

ሀ/ በሀገርአቀፍ ደረጃ

በሀገርአቀፍ ደረጃ በስታንዳርዱ በደረጃ 1 (31.55%) እና 2 (58.45%) ላይ ያሉ በመሆኑ


ደረጃቸውን ያሟሉ 10 በመቶ ናቸው። በመሆኑም በሀገርአቀፍ ደረጃ የኢንስፔክሽን ትንተና
እንደሚያሳየው የት/ቤቱ አመራርና መምህራን ለሁሉም ተማሪዎች ተስማሚና ዘመናዊ
የማስተማር ስነ-ዘዴዎችን መጠቀምን በተመለከተ በጣም ዝቅተኛ መሆኑንና የተማሪዎች
የትምህርት ተሳትፎ በጣም አነስተኛ መሆኑን ያመለክታል ፡፡

የዚህ ስታንዳርድ ባግባቡ መከናወኑ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራር ዘመናዊና አሳታፊ


የማስተማር ዘዴ እንዲጠቀሙ በማስቻል የሁሉም ተማሪዎች ተሳትፎ እንዲጎለብት ያግዛል።

ለ/ በክልል ደረጃ

በክልል ደረጃ ከስታንዳርዱ አንጻር ሲታይ የሁሉም ክልሎች አፈጻጸም ከ20 በመቶ በታች
እና አተገባበሩም በጣም ዝቅተኛ ደረጃ መሆኑ ይታያል። በተለይም ጋምቤላ ደረጃውን ያሟሉ
(0%)፣ ሀረሪ (4.2 %) እና ኢትዮ-ሶማሌ (4.7%) መሆናቸውን መረጃው ያመለክታል።

50
ተጠቃሽ የሆኑ ችግሮች

ከላይ እንደሚታየው ከደረጃ በታች የሆኑ ት/ቤቶች ያሏቸው ክልሎች ታዳጊ ክልሎች ሲሆኑ
ለዚህም ከሚጠቀሱ ችግሮች መካከል

• መምህራን በዘመናዊና አሳታፊ የማስተማር ስነ-ዘዴ ላይ በቂ ስልጠና አለማግኘታቸው


• መምህራን ከተለምዷዊው የመምህር ተኮር የማስተማር ዘዴ ወጥተው ተማሪ-ተኮር
የማስተማር ዘዴን ለመተግበር ቁርጠኛ አለመሆናቸው
• የትምህርት ቤቱ አመራር ተስማሚና ዘመናዊ የማስተማር ስነ-ዘዴ እንዲተገበር ምቹ
ሁኔታ አለመፍጠርና አለመከታተል
• መምህራን በአንድ ክፍል ውስጥ የተማሪ ብዛትን እንደምክንያት በመውሰድ ዘመናዊ
የማስተማር ስነ-ዘዴ ለመጠቀም ፍቃደኛ አለመሆን
• ለትምህርቱ ይዘትና ለተማሪዎች ተስማሚ የሆነ የማስተማሪያ ስነ-ዘዴዎችን ለይቶ
አለመጠቀም
• ልዩ ፍላጎት ያላቸው እና ሴት ተማሪዎች በትምህርቱ ሂደት የሚያጋጥሟቸውን
ችግሮች በመለየት ተስማሚ የማስተማር ዘዴ በመጠቀም ድጋፍ አለመስጠት
• መምህራን የመማር ማስተማሩን ችግር ለመፍታት የተግባር ምርምር
አለማድረጋቸው፡፡

አመላካች 13.1 መምህራን ተማሪዎች በትምህርታቸው ተመራማሪ፣ ፈጣሪ፣ ችግር ፈቺ እና


ራሳቸውን የሚመሩ እንዲሆኑ ልዩ ልዩ አሳታፊ ዘዴዎችን ተጠቅመዋል፣
የሚከናወኑ ተግባራት
• መምህራን ልዩ ልዩ አሳታፊ የማስተማር ስነዘዴዎችን ለይተው በክፍል ውስጥ
መተግበራቸውን በራሳቸው የሚያረጋግጡበትን ስርዓት ዘርግቶ ተግባራዊ ማድረግ
• በልዩ ልዩ የማስተማር ስነ-ዘዴዎች ላይ ለመምህራን ስልጠና መስጠት
• በትምህርታቸው ተመራማሪ፣ ፈጣሪ፣ ችግር ፈቺ እና ራሳቸውን የሚመሩ ተማሪዎችን
ማበረታታት
• በትምህርታቸው አቀባበላቸው የተሻሉ ሆነው ተመራማሪ የሆኑ ተማሪዎችን መሰረት
ያደረገ ልዩ ዕገዛ ማድረግ

51
አመላካች 13.2 የትምህርት ቤቱ አመራር ዘመናዊና አሳታፊ የመማር-ማስተማር ስነ ዘዴ
በት/ቤቱ እንዲተገበር ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሯል፣
የሚከናወኑ ተግባራት
• የትምህርት ቤቱ አመራር መምህራን አሳታፊ የማስተማር ስነዘዴዎችን ለይተው በክፍል
ውስጥ እንዲጠቀሙ ምቹ ሁኔታ (እርስ በርስ የልምድ ልውውጥ በማድረግ፣ ለተማሪ
ተኮር የማስተማር ዘዴ የሚያግዙ የማጠቃሻ መጻህፍትን በማቅረብ) በመፍጠር
የመምህራንን ተሳሽነት ማሳደግ
• የመማሪያ ክፍሎችን አሳታፊ የማስተማር ስነዘዴዎችን ለመተግበር ምቹ ማድረግ
• መምህራን አሳታፊ የማስተማር ስነ-ዘዴዎችን ለይተው በክፍል ውስጥ መጠቀማቸውን
በድጋፍ፣ በክትትል እና በግብረ-መልስ ማረጋገጥ

አመላካች 13.3 መምህራን ተማሪዎችን እንደ አስፈላጊነቱ በጥንድ፣ በቡድን እና በግል


ትምህርታቸውን እንዲማሩ አድርገዋል፣
የሚከናወኑ ተግባራት
• የክፍሉ አደረጃጀት ተማሪዎች በጥንድና በቡድን እንዲማሩ አመቺ መሆኑን
ማረጋገጥ
• መምህራን የትምህርቱን ይዘትና የተማሪዎቹን ሁኔታ ማዕከል ያደረገ የማስተማር
ስነ-ዘዴ በመጠቀም ተማሪዎች የሚማሩበትን ስልት መቀየስ

አመላካች 13.4 መምህራን ለሴት ተማሪዎች ልዩ ድጋፍ ሰጥተዋል፣


የሚከናወኑ ተግባራት
• መምህራን ለሴት ተማሪዎች ልዩ ዕገዛ ማድረግ
• መምህራን በትምህርት አቀባበላቸው ፈጣን ያልሆኑ ሴት ተማሪዎችን ለይተው
ተከታታይነት ያለው ድጋፍ ማድረግ
• በትምህርት አቀባበላቸው የተሻሉ ሴት ተማሪዎች በትምህርት አቀባበላቸው ፈጣን
ያልሆኑ ሴት ተማሪዎችን ድጋፍ እንዲያረጉ ምቹ ሁኔታ ፈጥሮ ተግባራዊ ማድረግ
• የሴት ተማሪዎች ቤተሰቦች ከትምህርት ቤቱ አመራርና ከመምህራን ጋር በመተባበር
ሴት ተማሪዎች በቤታቸውም ሆነ በት/ቤት ልዩ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ
አመላካች 13.5 መምህራን ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ልዩ ድጋፍ ሰጥተዋል፣
የሚከናወኑ ተግባራት

52
• የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ቤተሰቦች ከትምህርት ቤቱ አመራርና ከመምህራን ጋር
በመተባበር ተማሪዎቹ በቤታቸውም ሆነ በት/ቤት ልዩ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ
• መምህራን ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች በመለየት ተስማሚ የሆነ የትምህርት
አቀራረብ በመጠቀም ማገዝ
• የትምህርት ቤቱ አመራር ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች በመለየት
እንደየፍላጎታቸው በቂ ድጋፍ የሚያገኙበትን ስልት በመቀየስ ተግባራዊ ማድረግ

አመላካች 13.6 መምህራን የመማር ማስተማሩን ችግር ለመፍታት የተግባር ምርምር


አካሂደዋል፡፡

የሚከናወኑ ተግባራት

• የተግባር ምርምር አሰራር ላይ ስልጠና መስጠት፣ አስፈላጊ ቅፆችን ማቅረብ


• የትምህርት ቤት አመራር መምህራን የተማሪዎች የትምህርት ውጤት ላይ
በመመስረት ችግር-ፈቺ የተግባር ምርምር ስራዎችን እንዲያከናውኑ ምቹ ሁኔታ
መፍጠር
• መምህራን በመማር ማስተማር ሂደት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመለየት በተግባራዊ
ምርምር በመታገዝ መፍትሄ ማፈላለግና ተግባራዊ ማድረግ
• በተግባር ምርምር ዙርያ ልምዳቸውን ሊያካፍሉ ከሚችሉ ተቋማት ጋር ግንኙነት
በመፍጠር መምህራኑ በቂ ልምድ እንዲወስዱ ማድረግ

ስታንዳርድ 14
ትምህርት ቤቱ ለሴቶችና እና ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች አስፈላጊውን መረጃ
ይይዛል፣ ልዩድጋፍ ያደርጋል፡፡
ስታንዳርድ 14 ትምህርት ቤቱ የልዩ ፍላጎት እና የሴት ተማሪዎችን መረጃ ባግባቡ መያዙንና
የትምህርት ውጤታቸውን ለማሻሻል ልዩ ድጋፍ ማድረጉን የሚመለከት ነው።

53
ሰንጠረዠ 14 በዳግም ኢንስፔክሽን ውጤት ከስታንዳርድ 14 አንጻር

የዳግም ኢንስፔክሽን የስታንዳርድ 14 ውጤት ትንታና


ደረጃ ደረጃ
ደረጃ ደረጃ ደረጃ ደረጃቸው
ደረጃ 1 2
ክልል 2 3 4 ድምር ን ያሟሉ
1 በመቶ በመቶ
በመቶኛ
ኛ ኛ
አዲስ 750.0
አበባ 202 351 197 0 750.00 26.93 46.80 26.3
አፋር 248 76 8 0 332 74.70 22.89 2.4
አማራ 3695 2735 489 36 6955 53.13 39.32 7.5
ቤንሻንጉ
ል-ጉሙዝ 108 245 59 2 414 26.09 59.18 14.7
ድሬዳዋ 21 47 10 78 26.92 60.26 12.8
ኢትዮ-
ሶማሌ 167 59 10 2 238 70.17 24.79 5
ጋምቤላ 6 9 1 16 37.50 56.25 6.3
ሀረሪ 4 14 6 24 16.67 58.33 25
ኦሮሚያ 5317 4785 944 55 11101 47.90 43.10 9
ደ/ብ/ብ/ህ 803 1260 302 51 2416 33.24 52.15 14.6
ትግራይ 224 402 114 4 744 30.11 54.03 15.9
ሀገር 23068.0
አቀፍ 10795 9983 2139 901 0 46.80 43.28 10

ሀ/ በሀገርአቀፍ ደረጃ

በሀገርአቀፍ ደረጃ በስታንዳርዱ በደረጃ 1 (46.8%) እና 2 (43.28%) ላይ ያሉ በመሆኑ


ደረጃቸውን ያሟሉ 10 በመቶ ናቸው። በመሆኑም በሀገርአቀፍ ደረጃ የኢንስፔክሽን ትንተና
እንደሚያሳየው የልዩ ፍላጎት እና የሴት ተማሪዎችን መረጃ ባግባቡ በመያዝና የትምህርት
ውጤታቸው እንዲሻሻል ልዩ ድጋፍ ከማድረግ አንጻር በጣም ዝቅተኛ አፈጻጸም መኖሩን
ያመለክታል ፡፡

54
የዚህ ስታንዳርድ ባግባቡ መከናወኑ የልዩ ፍላጎት እና የሴት ተማሪዎችን መረጃ ባግባቡ
ተይዞ ልዩ ድጋፍ እንዲያገኙና ውጤታቸው እንዲሻሻል ያስችላል።

ለ/ በክልል ደረጃ

በክልል ደረጃ ከስታንዳርዱ አንጻር ሲታይ የሁሉም ክልሎች አፈጻጸም ከ27 በመቶ በታች
እና አተገባበሩም በጣም ዝቅተኛ ደረጃ መሆኑ ይታያል። በተለይም አፋር (2.4%)፣ ኢትዮ-
ሶማሌ (5%)፣ ጋምቤላ (6.3%) ፣ አማራ (7.5%) እና ኦሮሚያ (9%) መሆናቸውን መረጃው
ያመለክታል።

ተጠቃሽ የሆኑ ችግሮች

ከላይ እንደሚታየው ከደረጃ በታች የሆኑ ት/ቤቶች ያሏቸው ክልሎች በርካታ ሲሆኑ ለዚህም
ከሚጠቀሱ ችግሮች መካከል

• ስለ ልዩ ፍላጎት ትምህርት ግንዛቤ ማነስና ትኩረት አለመስጠት


• የሴቶች እና የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች መረጃ ባግባቡ ያለመያዝ
• ፍላጎታቸውን መሰረት በማድረግ ተገቢውን ድጋፍ አለማድረግ
• በልዩ ፍላጎት ትምህርት የሰለጠኑ መምህራን ያለመኖር (በተለይ ከ4ኛ በላይ)
• ለሴት ተማሪዎችና ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ምቹ ሁኔታ አለመፈጠሩ
• ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች የሚያስፈልጉ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችና የመማሪያና
ማጣቀሻ መጻህፍት አለመኖር
• ከአካባቢው ህብረተሰብና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ልዩ ፍላጎት ያላቸው
ተማሪዎች ድጋፍ እንዲያገኙ አለመደረጉ
• የልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ቤተሰቦች ከትምህርት ቤቱ አመራርና ከመምህራን
ጋር በመተባበር በቤታቸውም ሆነ በት/ቤት ልዩ ድጋፍ አለማግኘታቸው

አመላካች 14.1 ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎችን የተመለከቱ መረጃዎች ትምህርት ቤቱ


መዝግቦ ይዟል፤
የሚከናወኑ ተግባራት

55
• ስለ ልዩ ፍላጎት ትምህርት መምህራንና የት/ቤቱ ማህበረሰብ በቂ ግንዛቤ
እንዲኖራቸው ማድረግ
• የልዩ ፍላጎት ተማሪዎችን በተመለከተ መረጃ ባግባቡ የሚያዝበትን ስልት ቀይሶ
ተግባራዊ ማድረግ
• የልዩ ፍላጎት ተማሪዎችን በተመለከተ የአካባቢውን ህብረተሰብ ግንዛቤ ማሳደግ

አመላካች 14.2 ትምህርት ቤቱ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎችን የትምህርት ውጤት


ለማሻሻል እና ለማሳደግ ልዩ ድጋፍ አድርጓል፣
የሚከናወኑ ተግባራት
• በልዩ ፍላጎት ትምህርት የሰለጠኑ መምህራን እንዲመደቡ ማድረግ (በተለይ ከ4ኛ በላይ)
• ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች የሚያስፈልጉ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችና የመማሪያና
ማጣቀሻ መጻህፍት እንዲሟሉ ማድረግ
• ከአካባቢው ህብረተሰብና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ልዩ ፍላጎት ያላቸው
ተማሪዎች ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ
• የልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ቤተሰቦች ከትምህርት ቤቱ አመራርና ከመምህራን
ጋር በመተባበር በቤታቸውም ሆነ በት/ቤት ልዩ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ

አመላካች 14.3 ትምህርት ቤቱ የሴት ተማሪዎችን የትምህርት ውጤት ለማሻሻል እና


ለማሳደግ ልዩ ድጋፍ አድርጓል፣
የሚከናወኑ ተግባራት
• ለሴት ተማሪዎች ምቹ ሁኔታ መፍጠር
• የሴት ተማሪዎች ቤተሰቦች ከትምህርት ቤቱ አመራርና ከመምህራን ጋር በመተባበር
ሴት ተማሪዎች በቤታቸውም ሆነ በት/ቤት ልዩ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ
• የትምህርት ቤቱ አመራርና መምህራን ለሴት ተማሪዎች ተጨማሪ የትምህርት ድጋፍ
ማግኘታቸውን ማረጋገጥ
• ከአካባቢው ህብረተሰብና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ሴት ተማሪዎች ድጋፍ
እንዲያገኙ ማድረግ

ስታንዳርድ 15

56
መምህራን፣ ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ መርሃ-ግብር /CPD/
ተግባራዊ አድርገዋል፡፡
ስታንዳርድ 15 በት/ቤቱ ሁሉም መምህራን፣ ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ተከታታይ
የሙያ ማሻሻያ መርሃ-ግብር /CPD/ በመመሪያው መሰረት ተግባራዊ በማድረጋቸውን
የሚያመለክት ነው።

ሰንጠረዠ 15 በዳግም ኢንስፔክሽን ውጤት ከስታንዳርድ 15 አንጻር

ክልል የስታንዳርድ 15 ውጤት


ደረጃ ደረጃ
ደረጃ ደረጃ ደረጃ ደረጃቸው
ደረጃ 1 2
2 3 4 ድምር ን ያሟሉ
1 በመቶ በመቶ
በመቶኛ
ኛ ኛ
አዲስ
አበባ 359 236 150 6 751.00 47.80 31.42 20.8
አፋር 187 129 15 1 332 56.33 38.86 4.8
አማራ 1913 3718 1272 26 6929 27.61 53.66 18.7
ቤንሻንጉ
ል-ጉሙዝ 215 153 43 3 414 51.93 36.96 11.1
ድሬዳዋ 13 39 26 78 16.67 50.00 33.3
ኢትዮ-
ሶማሌ 182 50 6 238 76.47 21.01 2.5
ጋምቤላ 4 11 1 16 25.00 68.75 6.2
ሀረሪ 9 14 1 24 37.50 58.33 4.1
ኦሮሚያ 2830 5687 2420 164 11101 25.49 51.23 23.3
ደ/ብ/ብ/ህ 736 1071 540 68 2415 30.48 44.35 25.2
ትግራይ 167 363 202 12 744 22.45 48.79 28.8
ሀገር 23042.0
አቀፍ 6615 11471 4676 280 0 28.71 49.78 21.5

ሀ/ በሀገርአቀፍ ደረጃ

57
ከላይ ከሰንጠረዡ እንደሚታየው በሀገርአቀፍ ደረጃ በስታንዳርዱ በደረጃ 1 (28.71%) እና 2
(49.8%) ላይ ያሉ በመሆኑና ደረጃቸውን ያሟሉ 21.5 በመቶ መሆናቸውን ነው። በመሆኑም
በሀገርአቀፍ ደረጃ ያለው አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆኑን ያመለክታል።

የዚህ ስታንዳርድ ባግባቡ መከናወኑ መምህራን፣ ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ሙያቸውን


በማሳደግ የተማሪዎችን የመማር ውጤት እንዲሻሻል ያግዛል።

ለ/ በክልል ደረጃ

በክልል ደረጃ ከስታንዳርዱ አንጻር ሲታይ የሁሉም ክልሎች አፈጻጸም ከ34 በመቶ በታች
እና አተገባበሩም ዝቅተኛ ደረጃ መሆኑ ይታያል። በተለይም ኢትዮ-ሶማሌ (2.5%)፣ ሀረሪ
(4.1%)፣ አፋር፣ (4.8%) እና ጋምቤላ (6.2%) መሆናቸውን መረጃው ያመለክታል።

ተጠቃሽ የሆኑ ችግሮች

ከላይ እንደሚታየው ከደረጃ በታች የሆኑ ት/ቤቶች ያሏቸው ክልሎች በርካታ ሲሆኑ ለዚህም
ከሚጠቀሱ ችግሮች መካከል

• በተከታታይ ሙያ ማሻሻያ መርሃ ግብር ላይ ያለው ግንዛቤ ማነስና ትኩረት ሰጥቶ


በተገቢው መንገድ ተግባራዊ አለማድረግ
• የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ መርሃ ግብር አተገባበር ሂደት ተደጋጋሚ በመሆኑ
ተግባራዊነቱ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ
• የትምህርት ቤቱ አመራር የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ መርሃ ግብርን ትኩረት ሰጥቶ
በቂ ድጋፍና ክትትል አለማድረጉ
• የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ኮሚቴ የመርሀ-ግብሩን አፈጻጸም በተገቢው መንገድ
ትኩረት ሰጥቶ በቂ ድጋፍ፣ ክትትልና ግብረመልስ አለማድረጉ
• በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች አዲስ ለሚመደቡ መምህራን የተሻሉ አማካሪ መምህራን
አለመኖር
• የአማካሪ መምህራን ድጋፍና የመረጃ አያያዝ ስልት የተጠናከረ አለመሆን

58
አመላካች 15.1 ነባር መምህራን፣ ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የትምህርት ቤቱን የመማር
ማስተማር ችግር ለመፍታት የሚያስችል ችግሮችን በቅደም ተከተል ለይተው
ሞጁል አዘጋጅተው ቢያንስ በዓመት ለ6ዐ ሰዓት በተከታታይ ሙያ ማሻሻያ መርሃ
ግብር ላይ ተሳትፈዋል፣

የሚከናወኑ ተግባራት
• በተከታታይ ሙያ ማሻሻያ መርሃ ግብር ላይ ያለው ግንዛቤ ማሳደግና ትኩረት ሰጥቶ
በተገቢው መንገድ ተግባራዊ ማድረግ
• የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ መርሃ ግብር አተገባበር የተለዩ ችግሮች በወቅቱ እንዲፈቱ
ማድረግ
• የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ኮሚቴ የመርሀ-ግብሩን አፈጻጸም በተገቢው መንገድ ትኩረት
ሰጥቶ በቂ ድጋፍ፣ ክትትልና ግብረመልስ ማድረግ
• መርሀ-ግብሩ በተቀመጠለት ሰዓት መሰረት መጠናቀቁን ማረጋገጥ

አመላካች 15.2 አዲስ ጀማሪ መምህራን አማካሪ መምህራን ተመድበውላቸው የሙያ ትውውቅ
መርሃ ግብር /Induction Course/ አጠናቀዋል፣
የሚከናወኑ ተግባራት
• አዲስ ለሚመደቡ መምህራን ተገቢው የሙያ ትውውቅ በማድረግ ወደ ስራ ማሰማራት
• አዲስ ለሚመደቡ መምህራን ተገቢውን አማካሪ በመመደብ ድጋፍና ክትትል ማድረግ
• የአማካሪ መምህራን ድጋፍና የመረጃ አያያዝ ስልት ማጠናከር

ስታንዳርድ 16
የትምህርት ቤቱ አመራር፣ መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በልማት ሠራዊት
በመደራጀት በቡድን ስሜት እየሰሩ ነው፡፡
ስታንዳርድ 16 የትምህርት ቤቱ አመራር፣ መምህራን፣ ተማሪዎች እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች
በልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ተደራጅተው እና በጥሩ ስነ ምግባር የታነጸው፣ለሙያቸው ተገቢ
ክብር በመስጠት በልማት ሰራዊት አግባብ ትምህርት ቤቱን ማገልገል መቻላቸውን
የሚያመለክት ነው።

59
ሰንጠረዠ 16 በዳግም ኢንስፔክሽን ውጤት ከስታንዳርድ 16 አንጻር

የዳግም ኢንስፔክሽን የስታንዳርድ 16 ውጤት


ደረጃ ደረጃ ደረጃ ደረጃ 1 ደረጃ 2 ደረጃቸው
ደረጃ
ክልል 2 3 4 ድምር በመቶ በመቶ ን ያሟሉ
1
ኛ ኛ በመቶኛ
አዲስ
አበባ 73 679 256 3 1011 7.22 67.16 25.6
አፋር 115 187 26 5 333 34.53 56.16 9.3
አማራ 1077 4406 1424 48 6955 15.49 63.35 21.1
ቤንሻንጉል
-ጉሙዝ 156 209 48 1 414 37.68 50.48 11.9
ድሬዳዋ 37 53 15 2 107 34.58 49.53 15.9
ኢትዮ-
ሶማሌ 170 55 10 3 238 71.43 23.11 5.5
ጋምቤላ 5 10 1 16 31.25 62.50 6.2
ሀረሪ 1 21 22 4.55 95.45 0
ኦሮሚያ 1738 6609 2644 110 11101 15.66 59.54 24.8
ደ/ብ/ብ/ህ 547 1419 422 28 2416 22.64 58.73 18.6
ትግራይ 94 443 190 16 22613 0.42 1.96 97.6
ሀገር
አቀፍ 4013 14091 5036 216 22613 17.75 62.31 20

ሀ/ በሀገርአቀፍ ደረጃ

60
ከላይ ከሰንጠረዡ እንደሚታየው በሀገርአቀፍ ደረጃ በስታንዳርዱ በደረጃ 1 (17.75%) እና 2
(62.31%) ላይ ያሉ በመሆኑና ደረጃቸውን ያሟሉ 20 በመቶ መሆናቸውን ነው። በመሆኑም
በሀገርአቀፍ ደረጃ ያለው አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆኑን ያመለክታል።

የዚህ ስታንዳርድ ባግባቡ መከናወኑ አደረጃጀቶቹ ተጠናክረው በመደጋገፍና ችግሮችን በጋራ


በመፍታት የትምህርት ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግ ያግዛል።

ለ/ በክልል ደረጃ

በክልል ደረጃ በዚህ ስታንዳርድ ከፍተኛ አፈጻጸም ያለው የትግራይ ክልል ብቻ ሲሆን
አፈጻጸሙም 97.6 በመቶ ት/ቤቶች ደረጃቸውን ያሟሉ ናቸው። ሆኖም የአብዛኛዎቹ ክልሎች
አፈጻጸም ሲታይ ከሀገርአቀፉ አማካይ (20 በመቶ) በታች በመሆኑ አተገባበሩም ዝቅተኛ
ደረጃ ላይ ያለ መሆኑን ያመለክታል። በተለይም ሀረሪ (0%)፣ ኢትዮ-ሶማሌ (5.5%)፣ ጋምቤላ
(6.2%) እና አፋር(9.3%) በመሆናቸው ልዩ ትኩረት የሚሹ ናቸው።

ተጠቃሽ የሆኑ ችግሮች

ከላይ እንደሚታየው ከደረጃ በታች የሆኑ ት/ቤቶች ያሏቸው ክልሎች በርካታ ሲሆኑ ለዚህም
ከሚጠቀሱ ችግሮች መካከል

• የአደረጃጀቶቹን ጠቀሜታ አሳንሶ በማየት ለተግባራዊነቱ ተገቢውን ትኩረት


አለመስጠት
• ከዕቅድ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ተግባራዊነቱ ድረስ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት
ማከናወን አለመቻል
• የልማት ሰራዊት አደረጃጀትን ከትምህርት ልማት አንጻር ሳይሆን ከፖለቲካ ድርጅት
ጋር በማያያዝ በመተርጎም ለተግባራዊነቱ ተነሳሽነት መጓደል
• የት/ቤቱ አመራር ትኩረት ሰጥቶ በተገቢው መንገድ የተጠናከረ ክትትል፣ ድጋፍ እና
ግብረ-መልስ አለመስጠት
• አደረጃጀቶችን በተመለከተ የተጣራ መረጃ አደራጅቶ አለመያዝ
• የት/ቤቱ ማህበረሰብ ለመምህርነት ሙያ ተገቢውን ክብር በመስጠት ት/ቤቱን
ለማገልገል ቁርጠኛ አለመሆን

61
• ለተማሪዎች በአርአያነት የሚጠቀሱ የት/ቤቱ አመራርና መምህራን በበቂ መጠን
አለመኖራቸው

አመልካቾች 16.1፡-
የትምህርት ቤቱ አመራር፣መምህራን፣ ተማሪዎችና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በልዩ ልዩ
አደረጃጀቶች ተደራጅተው የትምህርት ልማት ሰራዊት በመገንባት ስራቸውን ውጤታማ በሆነ
መልክ ተወጥተዋል፣ በውሳኔ አሰጣጥ ላይ እንዲሳተፉ ተደርጓል፣ እርስ በእርስም በውስጥ
ሱፐርቪዥን አማካኝነት ተገነባብተዋል፡፡
የሚከናወኑ ተግባራት
• ሁሉም የትም/ቤቱ ማህበረሰብ አደረጃጀቶቹ የስራ ማሳለጫ መሳሪያ መሆናቸውን
በዕምነት እንዲይዝ ማድረግ
• የት/ቤቱ አመራር በአደረጃጀቶች ላይ የጋራ ግንዛቤ እንዲያዝ ማድረግ
• ሁሉም አጀረጃጀቶች ከዕቅድ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ሪፖርትና ግብረ-መልስ በተሟላ
ሁኔታ እንዲከናወን ማድረግ
• የት/ቤቱ አመራር ሁሉም አደረጃጀቶች የተቀመጠውን አሰራር ተከትለው
መፈጸማቸውን ትኩረት ሰጥቶ የተጠናከረ ክትትል፣ ድጋፍ እና ግብረ-መልስ መስጠት
• ት/ቤቱ አደረጃጀቶችን የተመለከተ መረጃ አደራጅቶ በመያዝና በመተንተን ወቅታዊ
ግብረ-መልስ መስጠት

አመልካቾች 16.2፡-
የትምህርት ቤቱ አመራር፣ መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በጥሩ ስነ ምግባር የታነፁ፣
ለሙያቸው ተገቢ ክብር ያላቸው፣ትምህርት ቤቱን ለማገልገል ቁርጠኛ የሆኑ ናቸው፣
የሚከናወኑ ተግባራት
• የት/ቤቱ ማህበረሰብ ለመምህርነት ሙያ ተገቢውን ክብር እንዲሰጡ ምቹ ሁኔታ
መፍጠር
• የመምህራንን ማህበራዊ ግንኙነትና መተባበር የሚያጎለብቱ የተለያዩ ኮሚቴዎችን
ማጠናከር
• አርአያነት ያላቸውን የትምህርት ቤቱ አመራር፣ መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች
የሚያበረታታ ስርዓት ዘርግቶ ተግባራዊ ማድረግ

62
ስታንዳርድ 17፡-

ሥርዓተ ትምህርቱ ትርጉም ያለው፣ አሳታፊ እና የተማሪዎቹን የእድገት ደረጃና ፍላጎቶች


ያገናዘበ መሆኑን መምህራን ይገመግማሉ፣ ግብረ መልስ ይሰጣሉ፣ ያሻሽላሉ፡፡

ይህ ስታንዳርድ ስርዓተ ትምህርቱ የተማሪዎችን የዕውቀት፣የክህሎትና የአመለካከት


እንዲሁም የሀገሪቱን ባህል፣አሳታፊ የማስተምር ስነ-ዘዴን ማካተቱን ወዘተ… መሰረት
በማድረግ ስለመዘጋጀቱ መምህራን አስፈላጊውን የስርዓተ ትምህርት ግምገማና አስተያየት
መስጠት መቻልን የሚያመላክት ነው፡፡

ሰንጠረዥ17. 1 የ2009 እና 2010 ዓ.ም የዳግም ኢንስፔክሽን መረጃ

የዳግም ኢንስፔክሽን የስታንዳርድ 17 ውጤት ትንተና


ደረጃ ደረጃ ደረጃ (ደረጃ ደረጃ3 & 4
ክልል 1 ደረጃ2 3 4 ድምር (ደረጃ 3%) 4%) በ %
አዲስ አበባ 122 475 145 10 752 19.28% 1.33% 20.61%
አፋር 155 155 16 6 332 4.82% 1.81% 6.63%
አማራ 1240 4649 1007 58 6954 14.48% 0.83% 15.31%
ቤንሻንጉል 96 267 47 4 414 11.35% 0.97% 12.32%
ድሬ ዳዋ 6 50 22 78 28.21% 0.00% 28.21%
ሶማሌ 131 79 26 2 238 10.92% 0.84% 11.76%
ጋምቤላ 3 10 3 16 18.75% 0.00% 18.75%
ሃረሪ 6 18 24 0.00% 0.00% 0.00%
ኦሮሚያ 2029 7158 1823 91 11101 16.42% 0.82% 17.24%
ደቡብ 442 1478 419 77 2416 17.34% 3.19% 20.53%
ትግራይ 68 418 245 5 736 33.29% 0.68% 33.97%
ሀገር አቀፍ 4298 14757 3753 253 23061 16.27% 1.10% 17.37%

ሀ/ በሀገርአቀፍ ደረጃ

63
በዚህ ስታንዳርድ እንደ ሀገር ከ23071 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 17.3 በመቶው ትምሀርት
ቤቶች ብቻ በደረጃ 3 እና 4 ላይ ሲገኙ የተቀሩት 82.7 በመቶዎቹ ከደረጃ በታች መሆናቸውን
መረጃው ያሳያል፡፡ ይህም ማለት እነዚህ ትምህርት ቤቶች በቀጣይ ጠንክረውና አቅደው
በማስራት ወደ ቀጣዩ ደረዳ መሸጋገር አለባቸው፡፡

የዚህ ስታንዳርድ በተገቢው ሁኔታ መከናወን የተዘጋጀው ስርዓተ ትምህርት የተማሪዎቹን


የእድገት ደረጃ ያገናዘበ እንዲሆን ያስችለዋል

ለ/ በክልል ደረጃ

በክልሎች ደረጃ በዚህ ስታንዳርድ በጣም ዝቅተኛ አፈጻጸም ያሳዩ ክልሎችን ስንመለከት
ሀረሬ (0%) አፋር (6.6%) ሲሆኑ በአንጻራዊነት የተሻለ አፈጻጸም ካላቸው ክልሎች ውስጥ
ትግራይ (33.9%) ድሬ ዳዋ (28.2%) ያስመዘገቡ ሲሆን የተቀሩት ክልሎች ደግሞ ከሀገራዊ
አማካኝ ውጤት ጋር ተቀራራቢ አፈጻጸም አላቸው፡፡

ተጠቃሽ የሆኑ ችግሮች

ከላይ እንደሚታየው ከደረጃ በታች የሆኑ ት/ቤቶች ያሏቸው ክልሎች ታዳጊ ክልሎች ሲሆኑ
ለዚህም ከሚጠቀሱ ችግሮች መካከል

➢ ለደረጃው ብቁ የሆኑ የሰው ሀይል ያለመሟላት


➢ የመምህራንና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተነሳሽነትና የቁርጠኝነት ችግር መኖር
➢ መምህራን ስርዓተ ትምህርቱን ለመገምገም የክህሎት ችግር መኖር
➢ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ያሉ የስርዓተ ትምህርት ኮሚቴዎች ትኩረት ሰጥቶ
ያለመስራትና ከዕቅድ ያለፈ ወደ ተግባር ያለመሸጋገር ችግር መኖር
➢ ትምህርት አመራሩ ይህንን ስራ ተግባራዊ እንደሆን ለመምህራን ምቹ ሁኔታን
ያለመፍጠር ችግር መኖር
➢ የተገመገሙ የስርዓተ ትምህርት ጉዳዮችን ከላይ እስከታች ድረስ ግብረ መልስን
በቅብብሎሽ ያለመስራት ችግረሮች መኖር

የሚከናወኑ ተግባራት

አመልካች 17-1 መምህራን በሥራ ላይ ያለውን ስርዓተ ትምህርት ጠንቅቀው ስለማወቃቸው፣

➢ የትምህርት ቤቱ አመራር በስርዓተ ትምህርት ግምገማ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ


መስራት
64
➢ ለአዳዲስ መ/ራን በሙያ ትውውቅ ለነባር መ/ራን ደግሞ በተሙማ ስልጠና ላይ
የልምድ ልውውጥና የሙያ ማሻሻያ ስራዎችን መስራት
➢ የስርዓተ ትምህርት መሳሪያዎችንና አስፈላጊ ግብዓቶችን ማሟላት

አመልካች 17.2 መምህራን የሚያስተምሩት ትምህርት በአገር አቀፍና በክልል የተዘጋጁ


ሥርዓተ ትምህርቶችን ያገናዘበ ስለመሆኑ፣

➢ የትምህርት ክፍል ሀላፊዎች የየሳምንቱን የትምህርት ዕቅድ በጥልቀት በመገምገም


ተገቢውን ግብረ-መልስ፣ድጋፍና ክትትል ማድረግ
➢ በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ በክፍል ውስጥ በመገኘት አስፈላጊውን የክፍል
ውስጥ ምልከታ ማካሄድ፡፡
➢ መምህራን የተዘጋጀውን ስርዓተ ትምህርት በአገር አቀፍና በክልል የተዘጋጁ ሥርዓተ
ትምህርቶችን ያገናዘበ ስለመሆኑ መገምገም አለባቸው

አመልካች 17.3 መርሃ-ትምህርቶቹና ሌሎች የስርአተ ትምህርት መሳሪያዎች


ከተማሪዎቹ እድገት ደረጃ ጋር የተገናዘቡ ስለመሆናቸው ገምግመው ግብረመልስ
ስለመስጠታቸው፣

➢ በመርሃ-ትምህርቶቹና ሌሎች የስርአተ ትምህርት መሳሪያዎች ላይ ግንዛቤና


የትውውቅ ስራ መስራት
➢ የትምህርት ቤቱ መምህራን ተዘጋጅተው ትምህርት ቤት የደረሱ የስርዓተ
ትምህርት መርሀ ትምህርቶችን መገምገምና ግበረ- መልስ መስጠት
➢ መምህራን በልዩ ልዩ ጥናቶች ስለ ስርዓተ ትምህርቱ ተገቢነት ችግሮችን
በመለየት የጥናት ውጤቱን ይፋ ማድረግና መተግበር አለባቸው፡፡

ስታንዳርድ 18 ተማሪዎች በትክክል ተመዝነዋል፣ አስፈላጊው ግብረመልስ ተሰጥቷቸዋል፡፡


ይህ ስታንዳርድ ተማሪዎች በተዘጋጀው ስርዓተ ትምህረት መሰረት በተዘጋጁ የመመዘኛ
መሳሪያዎች መመዘኛቸውን፣ ወቅታዊ እና ተገቢ የሆነ ግብረመለስ መስጠታቸውን
የሚያመላክት ነው።

ሰንጠረዥ18. 1 የ2009 እና 2010 ዓ.ም የዳግም ኢንስፔክሽን መረጃ

የዳግም ኢንስፔክሽን ስታንዳርድ 18 ውጤት ትንተና


ደረጃ ደረጃ ደረጃ ደረጃ (ደረጃ ደረጃበ ደረጃ 3 & 4
ክልል 1 2 3 4 ድምር 3በ%) % (4) በ %
28.19
አዲስ አበባ 64 473 212 3 752 % 0.40% 28.59%
አፋር 210 107 14 1 332 4.22% 0.30% 4.52%
148 10.21
አማራ 5 4734 710 26 6955 % 0.37% 10.58%

65
ቤንሻንጉል 145 227 41 1 414 9.90% 0.24% 10.14%
32.05
ድሬ ዳዋ 7 46 25 78 % 0.00% 32.05%
ሶማሌ 147 79 12 238 5.04% 0.00% 5.04%
ጋምቤላ 6 9 1 16 6.25% 0.00% 6.25%
ሃረሪ 1 21 2 24 8.33% 0.00% 8.33%
258 138 1110 12.46
ኦሮሚያ 7 7095 3 36 1 % 0.32% 12.78%
15.40
ደቡብ 577 1447 372 20 2416 % 0.83% 16.23%
21.10
ትግራይ 106 474 157 7 744 % 0.94% 22.04%
533 1471 292 2307 12.70
ሀገር አቀፍ 5 2 9 94 0 % 0.41% 13.10%

በሃገር ደረጃ

ይህ ስታንዳርድ እንደ ሀገር ሲታይ አፈጻጸሙ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ያመላክታል፡፡


አፈጻጸሙም 13.1% ነው፡፡ የተቀሩት 86.9% ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች መሆናቸውን
ያሳያል።

የዚህ ስታንዳርድ በአግባቡ መከናወኑ ተማሪዎች በተገቢው ሁኔታ ተመዝነው ግብረ-መልስ


እንዲሰጣቸው ያስችላል፡፡

በክልል ደረጃ

ከላይ ከመረጃው መረዳት እንደሚቻለው አጠቃላይ ካሉት ክልሎችና የከተማ አስታዳደሮች


ውስጥ ድሬዳዋ 32.05%፣ አዲስ አበባ 28.59% ውጤት በማግኘት በአንጻራዊነት የተሻለ
አፈፃፀም ያላቸው ሲሆን አፋር 4.52%፣ ሶማሌ 5.04% እና ጋምቤላ 6.25% ዝቅተኛ
አፈፃፀም ያላቸው ናቸው።

ተጠቃሽ የሆኑ ችግሮች

ከላይ በሰንጠረዡ እንደሚታየው ከደረጃ በታች ለሆኑ ት/ቤቶች በምክንያትነት ከሚጠቀሱ


ችግሮች መካከል

✓ መምህራን በፈተና አዘገጃጀት ላይ በቂ ግንዛቤ ያላቸው አለመሆን፣


✓ መምህራን እና ር/መምህራን በምዘና ምንነት እና አተገባባር ላይ ያላቸው ግንዛቤ
ዝቅተኛ መሆኑ፣
✓ ትምህርት ቤቶች በራሳቸው ደረጃ የፈተና ቋት አለማደራጀት፣
✓ በትምህርት ቤት ደረጃ የሚዘጋጁ ፈተናዎች የፈተና ቢጋርን የተከተለ አለመሆን፣

66
✓ በትምህርት ቤት የሚዘጋጁ ምዘናዎች ሶስቱን የእውቀት ዘርፎች /Domain) የያዘ
አለመሆን፣
✓ ወጥ የሆነ የፈተና አስተዳደር ስርዓት በትምህርት ቤት አለመኖር፣
✓ አመራሩ የምዘና ስርዓቱን በትክክል ስለመተግበሩ አስፈላጊውን ድጋፍ፣ ክትትልና
ግብረ መልስ ያለማድረግ ችግር

የሚከናወኑ ተግባራት

አመልካች 18.1. በትምህርት ቤቱ የሚዘጋጅ ምዘና ስርአተ ትምህርቱን መሰረት ያደረገ


በቢጋር /Table of Specifications/ የተዘጋጀ ነው፣
✓ ስለ ፈተና ቢጋር ምንነት፣ አስፈላጊነት እና አዘገጃጀት ላይ በቂ ስልጠና መስጠት፣
✓ የሚዘገጁ ፈተናዎች በፈተናና ምዘና ኮሚቴዎች እየተገመገሙና እየተረጋገጡ
ግብረመልስ እየተሰጠባቸው እንዲሄዱ ማድርግ፣
✓ የፈተና አሰጣጥ ስርዓቱ በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲፈፀም ማድረግ፣
✓ የፈተና ጥያቄዎች አዘገጃጀት ፈተና ህግና ስርዓትን የተከተለ መሆኑንን እየፈተሹ
እና ግብረመልስ እየሰጡ መሄድ

አመልካች 18.2. ተማሪዎች በክልል/ከተማ አስተዳደር፣ በዞን/ክፍለ ከተማ በወረዳና


በጉድኝት ማዕከል በሚዘጋጁ ፈተናዎች ይመዘናሉ፣
➢ በየደረጃው ያሉ አካላት በየትምህርት እርከኑ እና ትምህርት ዓይነቶች
ደረጃቸውን የጠበቁ ፈተናዎችን በማዘጋጀት ተማሪዎችን መመዘን፣
➢ በየደረጃው ባሉ አካላት በሚዘጋጁ ፈተናዎች ተማሪዎች ከተመዘኑ በኋላ
የውጤትን ትንተና መስራት በየደረጃው ግብረመልስ መስጠት፣
➢ የትምህርት አመራሩ ተማሪዎች በየደረጃው ባሉ የትምህርት መዋቅሮችን
ተማሪዎችን ለመመዘን የተዘጋጁ ፈተናዎች በአግባቡ ተግባራዊ መሆናቸውን
መከታተልና መደገፍ
➢ የተማሪዎችን የምዘና ውጤት በተገቢው ደረጃ መረጃውን አደራጅቶና ተንትኖ
መጠቀም

አመልካች 18.3. መምህራን የተማሪዎችን ውጤት ለመለካት በተቀመጠው ዝቅተኛ


የመማር ብቃት /MLC/ መሠረት የንድፈ ሃሳብና የተግባር ሁኔታን ባገናዘበ መልኩ
ተከታታይ ምዘናን ይጠቀማሉ፣
➢ ለመምህራን ስለተካታታይ ምዘና ምንነት እና አስፈላጊነት ላይ ያላቸውን ግንዛቤ
ማሳደግ፣
➢ የተከታታይ ምዘና አተገባበር የአሰራር መመሪያ ማዘጋጀት እና ተግባራዊ
ማድረግ፣

67
➢ ስለ እያንዳንዱ ተማሪ የትምህርት አቀባበል፣ የባህሪ መለወጥ እና ያመጡትን
መሻሸል በሚያሳይ መልኩ ማህደረ ተግባር ማዘጋጀት ፣
➢ የትምህርት ቤቱ አመራር መምህራን በትክክል የክፍል ውስጥ ተከታታይ ምዘናን
ተግባራዊ ማድረጋቸውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣

ስታንዳርድ 18.4. መምህራን የተማሪዎችን ውጤት በመተንተን ድጋፍ ሰጥተዋል፣


➢ መምህራን በየደረጃው በየትምህርት ኣይቱ የሚዘጋጁ የፈተና ውጤቶችን
በየክፍል ደረጃ፣በትምህርት ዓይነት፣ እና በፆታ መተንተን፣
➢ የፈተና ውጤት ትንተና መሰረት በማድረግ ዝቅተኛ ውጤት ለማጡ ተማሪዎች
የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት መደገፍ፣
➢ የፈተና ውጤት ትንተና መሰረት በማድረግ ለሁሉም ተማሪዎች ተገቢውን
ድጋፍ ማድረግ
➢ የትምህርት ቤቱ አመራር መምህራን ተግባራቸውን በአግባቡ ስለመተግበራቸው
ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ

ስታንዳርድ 18.5. መምህራን ተማሪዎች ውጤታቸውን እንዲያሻሽሉ ግብረ-መልስ


በመስጠት ድጋፍ ያደርጋሉ፣
➢ የትምህርት ቤት አመራር አካላት በትምህርት ቤት ውስጥ ምዘና ከተከናወነ
በኃላ አስፈላገውና ወቅታዊ የሆነ ግብረ መልስ የሚሰጥበትን ስርዓት መዘርጋት
➢ ዝቅተኛ ውጤት ላላቸው ተማሪዎች ተከታታይ ድጋፍ ከፍተኛ ውጤት
ላስመዘገቡ ተማሪዎች ደግሞ የማበረታቻ ስርዓት መዘርጋት

ስታንዳርድ 18.6. ትምህርት ቤቱ የተማሪዎችን ውጤት ለወላጆች በማሳወቅ ግብረ መልስ


ይቀበላል፡፡
➢ በትምህርት ቤት ውስጥ የተማሪ ወላጆችንና የትምህርት ቤት ግንኙነትን
ማጠናከር
➢ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪና የተማሪ ወላጆች የእውቅና መድረክ መፍጠር

ስታንዳርድ 19 የትምህርት ቤቱ አመራር የልዩ ልዩ አደረጃጀት ተጠሪዎች ያቀዷቸው


እቅዶች በተያዘላቸው ጊዜ፣ ጥራትና መጠን መሰረት መፈጸማቸውን ይከታተላሉ፡፡
ይህ ስታንዳርድ የትምህርት ቤቱ አመራር በትምህርት ቤቱ የሚታቀዱ አጠቃላይ እቅዶችን
በወጣላቸው የጊዜ መርሃ ግብር ስለመፈጸማቸው አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ
የሚያደርጉበትን ስርዓትን የሚገልጽ ነው፡፡
ሰንጠረዥ19. 1 የ2009 እና 2010 ዓ.ም የዳግም ኢንስፔክሽን መረጃ
68
የዳግም ኢንስፔክሽን የስታንዳርድ 19 ውጤት ትንተና
ደረጃ ደረጃ ደረጃ
ደረጃ 2 3 4 (ደረጃ ደረጃበ ደረጃ 3 &
ክልል 1 ድምር 3በ%) % (4) 4 በ %
18.09
አዲስ አበባ 233 379 136 4 752 % 0.53% 18.62%
አፋር 211 101 16 1 329 4.86% 0.30% 5.17%
229 10.45
አማራ 3 3910 727 25 6955 % 0.36% 10.81%
ቤንሻንጉል 197 177 38 2 414 9.18% 0.48% 9.66%
24.36
ድሬ ዳዋ 13 45 19 1 78 % 1.28% 25.64%
ሶማሌ 147 79 12 238 5.04% 0.00% 5.04%
ጋምቤላ 6 8 1 1 16 6.25% 6.25% 12.50%
ሃረሪ 9 14 23 0.00% 0.00% 0.00%
333 133 1110 12.03
ኦሮሚያ 2 6365 6 68 1 % 0.61% 12.65%
13.22
ደቡብ 743 1321 324 62 2450 % 2.53% 15.76%
15.44
ትግራይ 201 423 115 6 745 % 0.81% 16.24%
738 1282 272 2310 11.79
ሀገር አቀፍ 5 2 4 170 1 % 0.74% 12.53%

በሃገር ደረጃ፡-

እንደ ሀገር 12.5% የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ብቻ ይህንን ስታንዳርድ በማሳካት ደረጃቸውን
ያሟሉ ሲሆን የተቀሩት 87.5% የሚሆኑት ትምህርት ቤቶች የተቀመጠውን ዝቅተኛ መመዘኛ
መስፍርት አላሟሉም።

በክልል ደረጃ

በዚህ ስታንዳርድ በየክልሉ ያሉ ትምህርት ቤቶችን አፈፃፀም ስንመለከተ ድሬዳዋ እና አዲስ


አበባ በአንፃራዊነት የተሻለ አፈፃፀም ያለቸው ትምህርት ቤቶች ሲኖራቸው ከዚህ ውጭ ባሉ
ክልሎች ያሉ ትምህርት ቤቶች በጣም ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸው መሆኑን መረጃው
ያመላክታል።

ተጠቃሽ የሆኑ ችግሮች

69
ከላይ በሰንጠረዡ እንደሚታየው ከደረጃ በታች ለሆኑ ት/ቤቶች በምክንያትነት ከሚጠቀሱ
ችግሮች መካከል

➢ ለተለያዩ አደረጃጀቶችና በኮሚቴ የሚከናወኑ ስራዎች የመማር ማስተማሩ ተግባር


አንድ አካል ናቸው ብሎ በእምነት ይዞ አለመተግበር
➢ የትምህርት ቤቱ አመራር በትምህርት ቤት የሚደራጁ ልዩ ልዩ አደራጃጀቶች
ያቀዷቸውን እቅዶች በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት መስራታቸውን፣ በተገቢው
መልኩ የመከታተል የመደገፍና የማብቃት ስራ እየሰራ አለመሆኑ፣
➢ የተለያዩ አደረጃጀቶች ዕቅድን በየወቅቱ መገምገም፣ መክለስ እና በተዋረድ ዕቅድ
አፈፃፀም ሪፖርት አዘጋጅቶ እንዲያቀርቡ ማድረግ ላይ ውስንነት መኖሩ፣
➢ ተመሳሳይ አላማና ተግባር ያላቸውን አደረጃጀቶች የማዋሃድ ስራ አለመስራት
ማለትም አሁን በትምህርት ቤት ደረጃ የተደራጁ አደራጃጀቶች ቁጥር መብዛት
ለክተትልና ድጋፍ አስቻጋሪ መሆናቸው
➢ በተከታታይ ሙያ ማሻሻ ፕሮግራም ላይ የአመለካከት ችግር መኖሩ
➢ እነዚህን አደረጃጀቶች ከተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶች ጋር አያይዞ የማየት ችግር

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

አመላካች 19.1 የትምህርት ቤቱ አመራር በትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ የተደራጁ የትምህርት


ልማት ሰራዊት እቅዶች በአግባቡ መታቀዳቸውንና መከናወናቸውን ስለመከታተሉና
ለችግሮች መፍትሄ ስለመስጠቱ፣

➢ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በት/ቤት አደረጃጀቶች የተያዙ እቅዶችን ተግባር


ማስፈጸሚያ መሳሪያ ናቸው ብሎ በእምነት ይዞ ተግባራዊ ማድረግ
➢ የትምህርት ልማት ሰራዊት ምንነት እና አደረጃጀት ዙሪያ ለትምህርት ቤት
ማህበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠር
➢ በዕቅድ አዘጋጀጃት፣ አተገባበር እና ግምገማ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ
ማዘጋጀት የትምህርት ቤቱን ማህበረሰብ ግንዛቤ ማሳደግ፣
➢ የትምህርት አመራሩ የአደረጀጃቶችን ግምገማ መሰረት በማድረግ ግልጽ እና
ከችግሮች ሊያወጣ የሚችል የመፍትሄ ሃሳብ በማስቀመጥ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣

አመልካች 19.2 በትምህርት ቤቱ የተቋቋመው የትምህርት ቤት መሻሻል ኮሚቴ


የፕሮግራሙን አተገባበር ስለመከታተሉ እና ድጋፍ ስለመስጠቱ፣

➢ ለትምህርት ቤት መሻሸል ከሚቴው በትምህርት መሻሻል ፕሮግራም ዙሪያ ያላቸውን


ግንዛቤ ማሳደግ፣

70
➢ የትምህርት ቤት መሻሻል ኮሚቴ የትምህርት ቤት መሻሸል ፕሮግራም ዕቅድ
አፈፃፀምን መከታተል፣መገምገምና ግብረመልስ መስጠት፣
➢ የትምህርት ቤት መሻሻል አፈፃፀም መነሻ በማድረግ የእውቅና ፕሮግራም ማዘጋጀት
እና እውቅና መስጠት፣

አመልካች 19.3 በትምህርት ቤቱ የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ኮሚቴ የመርሃ ግብሩን አፈፃፀም


ስለመከታተሉ እና ድጋፍ ስለማድረጉ፣

➢ በተከታታይ ሙያ ማሻሸያ መርሃ ግብር ዙሪያ ለትምህርት ቤቱ መምህራን እና


አመራር ስልጠና መስጠት፣
➢ የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ መርሃ ግብር ኮሚቴን ዕቅድ አዘጋጅቶ የክትትልና ድጋፍ
ስራ እንዲሰራ ማድረግ፣
➢ የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ፕሮግራም ፕ መምህራን ክህሎቴን የሚያሳድግ እና ብቁ
መምህራን ሊያደርገኝ የሚችል ነው ብለው በእምነት ይዘው ተግባራዊ እንዲያደርጉ
ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣

አመልካች 19.4 የትምህርት ቤቱ አመራር በትምህርት ቤቱ የሚካሄደውን የመማር


ማስተማር ሂደትና የተጓዳኝ ክበባት ዕቅድ በት/ቤቱ ዓመታዊ እቅድ ስለመካተቱ፣
አፈፃፀሙን ስለመከታተሉና ድጋፍ ስለመስጠቱ፣

➢ የት/ም አመራሩ አጠቃላይ የአደረጃጀት ዕቅዶችን ባለድርሻ አካላትን በመያዝ


የእቅድ ክለሳ ማድረግ፣
➢ ለክበባትና ለልዩ ልዩ አደረጃጀቶች አስፈጊውን የበጀት ምደባ ማድረግ፣ የቁሳቁስ
ሌሎች መሰል ድጋፎችን ማድረግ
➢ በዕቅዱ መሰረት ተግባራት መከናወናቸውን መገምገና ድጋፍ ማድረግ ወዘተ ናቸው

አመልካች 19.5. ት/ቤቱ የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ አካላትን ስለማበረታቱ እና


ዕውቅና ስለመስጠቱ፣

➢ የተሻለ አፈጻጸም ላለቸው ተማሪዎች፣ መ/ራንና የትምህርት አመራሮች


የማነቃቃትና እውቅና የመስጠት ስርዓት መዘርጋት፡፡
➢ በሴሚስተርና በአመቱ መጨረሻ የላቀ አስታውጾ ላበረከቱ የትምህርት ቤቱ
ማህበረሰብ የሽልማትና የማበረታቻ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት እውቅና
መስጠት፡፡

ስታንዳርድ 20፡- ትምህርት ቤቱ የሰው ፣ የገንዘብ እና የንብረት ሃብት አጠቃቀም ስርአት


ዘርግቶ ተግባራዊ አድርጓል፡፡

71
ይህ ስታንዳርድ ትምህርት ቤቱ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ሃብቶችን በመንግስት ህግና መመሪያ
ስራ ላይ ስለማዋሉ የሚመለከት ነው።

ሰንጠረዥ20. 1 የ2009 እና 2010 ዓ.ም የዳግም ኢንስፔክሽን መረጃ

የዳግም ኢንስፔክሽን የስታንዳርድ 20 ውጤት ትንተና


ደረጃ ደረጃ ደረጃ
ደረጃ 2 3 4 (ደረጃ ደረጃበ% ደረጃ 3 & 4
ክልል 1 ድምር 3በ%) (4) በ %
አዲስ አበባ 84 403 253 12 752 33.644% 1.596% 35.24%
አፋር 173 122 32 5 332 9.639% 1.506% 11.14%
አማራ 1114 4538 1241 62 6955 17.843% 0.891% 18.73%
ቤኒሻንጉል 107 236 65 6 414 15.700% 1.449% 17.15%
ድሬ ዳዋ 11 41 24 3 79 30.380% 3.797% 34.18%
ሶማሌ 144 75 18 1 238 7.563% 0.420% 7.98%
ጋምቤላ 4 13 17 0.000% 0.000% 0.00%
ሃረሪ 4 19 1 24 4.167% 0.000% 4.17%
ኦሮሚያ 2975 6845 1206 75 11101 10.864% 0.676% 11.54%
ደቡብ 485 1487 397 55 2424 16.378% 2.269% 18.65%
ትግራይ 117 406 212 10 745 28.456% 1.342% 29.80%
ሀገር አቀፍ 5218 14185 3449 229 23081 14.943% 0.992% 15.94%

በሃገር ደረጃ

ከላይ በሰንጠረዡ እንደተገለፀው በስታንዳርደ 20 ላይ ትምህርት ቤቶች ያላቸው አፈፃፀም


እንደ ሀገር ዝቅተኛ መሆኑን የሚያመልክትነው። በዚህም መሰረት ካሉን አጠቃላይ
ትምህርት ቤቶች 15.94% የሚሆኑት ብቻ ለደረጃው የተቀመጠውን ዝቅተኛ የመመዘኛ
መስፍርት ያሟሉ ሲሆን 84.06% የሚሆኑት ደግሞ ከደረጃ በታች ናቸው።

በክልል ደረጃ

በስታንዳርድ 20 ላይ ክልሎች ያላቸውን አፈፃፀም ስንመለከት አዲስ አበባ


35.24%፣ድሬዳዋ 34.18%፣ ትግራይ 29.8%፣ አማራ 18.73% ፣ ደቡብ 18.65% እና
ቤኒሻንጉል ከሃገር አቀፉ አማካይ አፈፃፅም በላይ ሲሆኑ ከዚህ ውጭ ባሉ ክልሎች የሚገኙ
ትምህርት ቤቶች ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸው ናቸው።

ተጠቃሽ የሆኑ ችግሮች

ከላይ በሰንጠረዡ እንደሚታየው ከደረጃ በታች ለሆኑ ት/ቤቶች በምክንያትነት ከሚጠቀሱ


ችግሮች መካከል

72
➢ በትምህርት ቤት ደረጃ የሚመደቡ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በተቀመጠው ስታንዳርድ
መሰረት የተሟሉ አለመሆኑ፣
➢ ትምህርተ ቤት ውስጥ የሚከናወኑ የፋይንናስ አሰራር፣ የንብረት አስተዳደር እና
የሰው ሃብት አደረጀጃት በተቀመጠው የመንግስት ደንብ እና መመሪያ መሰረት
አለመከናወን፣
➢ በትምህርት ቤት ደረጃ የሚፈፀም ግዥዎች የምንግስት ደንብ እና መመሪያ
የተከተለ አለመሆኑ
➢ በመንግስት የግዥ ስርኣት፣ የንብረት እና የሰው ኃይል አስተዳደር ላይ ር/ምህራን
ያላቸው ግንዛቤ አናሳ መሆን፣

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

አመልካች 20.1 ት/ቤቱ የመረጃ አሰባሰብ፣አያያዝ እና አጠቃቀም ሥርዓት ዘርግቶ ተግባራዊ


ስለማድረጉ፣

➢ የመረጃ አያያዝና አጠቃቀም ስርዓት መዘርጋት


➢ በመረጃ አሰባሰብ፣ አያያዝ፣ አደረጃጀት እና አጠቃቀም ዙሪያ ለትምህርት ቤት
ማህቨረሰቡ ስልጠና መስጠት
➢ መረጃዎችን ለትምህርት ቤቱና ለባለድርሻ አካላት ግልጽእና ተደራሽ እንዲሆኑ
ማድረግ፣

አመልካች 20.2 መምህራን በሰለጠኑበት የትምህርት አይነት ተመድበው


ስለማስተማራቸው፣

➢ ሁሉም መምህራን በሰለጠኑበት የትምህርት ዓይነት ተመድበው እንዲያስተምሩ


ማድረግ፣

አመልካች 20.3 ርዕሰ መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በሰለጠኑበት የሙያ መስክ


ተመድበው ስለመስራታቸው፣

➢ ር/መምህራን እና ም/ር/መምህራን በሰለጠኑበት የትምህርት አይነት እነዲሰሩ


ማድረግ
➢ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በሰለጠኑበት የትምህርት መስክ መመደብ ወደ ስራ
ማስገባት፣

አመልካች 20.4 በት/ቤቱ ያሉ ህንፃዎች፣ ፋሲሊቲዎች እና ተጨማሪ ግብዓቶች በአግባቡ


ጥቅም ላይ ስለመዋላቸው፣

➢ በትምህርት ቤቱ ያሉ የመማሪያ ና አገልግሎት መስጫ ህንፃዎችና ፋሲሊቲዎች


ሁሉም ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ፣
➢ የግብዓት አጠቃቀም ስርዓት በመዘርጋት ተግባራዊ ማድረግ፣

73
አመልካች 20.5 የት/ቤቱ በጀት ቅድሚያ ለተሰጣቸው የትምህርት ቤት መሻሻል እቅድ ላይ
በተቀመጡና አግባብነት ያላቸው አካላት በወሰኑት መሠረት በተገቢ መንገድ ሥራ ላይ
ስለመዋሉ፣

➢ ለትምህርት ቤቱ የተመደበ በጀት የትምህርት ቤት መሻሻል ዕቅድ መሰረት በማድረግ


እና በተለይ ድግሞ የቅድሚያ ቅድሚያ የትኩረት አቅጣጫዎችን መሰረት ባደረገ
መልኩ ጥቅም ላይ እነዲውል ማድረግ፣
➢ በትምህርት ቤቱ በጀት አጠቃቀም እና አስተዳደር ዙረያ የሚለከታቸው ባለድርሻ
አካላት በማሳተፍ ተግባራዊ ማድረግ፣

ስታንዳርድ 21፡- ትምህርት ቤቱ ከተማሪ ወላጆችና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ጠንካራ


ግንኙነት አለው፡፡

የትምህርት ቤቱና የተማሪ ወላጆች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ በትምህርት ቤቱ


ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ተግባራትን በባለቤትነት መፈጸም መቻልና የመደጋገፍ ስሜትን
ያመለክታል፡፡

ሰንጠረዥ21. 1 የ2009 እና 2010 ዓ.ም የዳግም ኢንስፔክሽን መረጃ

ስታንዳርድ 21
ደረጃ ደረጃ ደረጃ
ደረጃ 2 3 4 (ደረጃ ደረጃበ ደረጃ 3 & 4
ክልል 1 ድምር 3በ%) % (4) በ %
74
20.88
አዲስ አበባ 87 494 157 14 752 % 1.86% 22.74%
አፋር 173 122 32 5 332 9.64% 1.51% 11.14%
217
አማራ 4 4115 623 42 6954 8.96% 0.60% 9.56%
ቤኒሻንጉል 144 251 18 1 414 4.35% 0.24% 4.59%
20.51
ድሬ ዳዋ 9 52 16 1 78 % 1.28% 21.79%
ሶማሌ 142 72 21 3 238 8.82% 1.26% 10.08%
ጋምቤላ 4 11 1 16 0.00% 6.25% 6.25%
12.50
ሃረሪ 3 18 3 24 % 0.00% 12.50%
210 167 1110 15.12
ኦሮሚያ 0 7254 9 68 1 % 0.61% 15.74%
11.84
ደቡብ 563 1485 286 82 2416 % 3.39% 15.23%
11.42
ትግራይ 187 463 85 9 744 % 1.21% 12.63%
558 1433 292 2306 12.66
ሀገር አቀፍ 6 7 0 226 9 % 0.98% 13.64%

በሀገር አቀፍ ደረጃ

ከላይ መረጃው እንደሚያሳየው ስታንዳርድ 21 ላይ እንደሀገር ትምህርት ቤቶች ያላቸው


አፈጻጸም 13.64% የሚሆኑት ብቻ ለደረጃው የተቀመጠውን ዝቅተኛ መመዘኛ መስፈርት
ያሙሉ ሲሆን የተቀሩት 86.36% ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች የሆነ አፈጻጸም ላይ
ናቸው፡፡

በክልል ደረጃ

ከላይ በሰንጠረዡ እንደተገለጸው ስታንዳርድ 21 ትምህርት ቤቶች ከህብረተሰቡ ጋር የተሻለ


ግንኙነት ያደረጉ የክልል ትም/ት ቤቶችን ስንመለከት አዲስ አበባና ድሬ ዳዋ በአንጻራዊነት
ጥሩ አፈጻጸም ያላቸው ሲሆን ቤኒሻንጉልና ጋምቤላ ክልሎች ላይ ያሉ ትምህርት ቤቶች
ዝቅተኛ አፈጻጸም ያላቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡

ተጠቃሽ የሆኑ ችግሮች (ገላጭና አመላካች)

75
ከላይ በሰንጠረዡ እንደሚታየው ከደረጃ በታች ለሆኑ ት/ቤቶች በምክንያትነት ከሚጠቀሱ
ችግሮች መካከል

➢ ወላጆች በትምህርት ቤት አመራሮች ላይ ያላቸው አመኔታ ዝቅተኛ መሆን፡፡


➢ ወላጆች የትምህርት የቤቶችን አጠቃላይ ጉዳይ ለመንግስት ብቻ የተተወ አድርጎ
ማሰብ፡፡
➢ የትምህርት ቤት አመራሮች ከወላጆች ጋር ያላቸው ግንኙነት በተቀመጠው የጊዜ
ሰሌዳ መሰረት መከናወን አለመቻሉ፡፡
➢ አብዛኛዎቹ የተማሪ ወላጆች የወላጆችና የትምህርት ቤት ግንኙት ገንዘብ ለማሰባሰብ
ብቻ መሰረት ያደረገ ነው ብሎ ማሰብ፡፡
➢ የተማሪዎች ውጤትና ስነ-ምግባር እንዲሁም የትምህርት ቤቱ አጠቃላይ አፈጻጸም
በችግር የሚታይ ሆኖ መገኘት፡፡

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

ስታንዳርድ 21.1 ትምህርት ቤቱ ወላጆች በመማር ማስተማሩ ስራ ላይ ንቁ ተሳትፎ


እንዲያደርጉ ያበረታታል፤ በትምህርት ቤትና በክፍል ደረጃ ወላጆች ትርጉም ያለው ተሳትፎ
በተደራጀ መልኩ እንዲያደርጉ ያደርጋል፡፡

➢ የተማሪ ወላጆችና የትምህርት ቤቶች ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግ


➢ የክፍል ውስጥ ወተመህን ማደራጀትና ወደ ተግባር እንዲገባ ማድረግ

ስታንዳርድ 21.2 ትምህርት ቤቱ በየወቅቱ ለወላጆችና ለአካባቢው ማህበረሰብ በተማሪዎች


የትምህርት አቀባበልና ውጤት፣ ባህርይ፣ የፋይናንስ አጠቃቀም እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች
ላይ መረጃ ይሰጣል፣ ግብረ መልስም ይቀበላል፣

➢ የትምህርት ቤቶች የሀብት አጠቃቀምንና ሌሎች አሰራሮችን ለተማሪዎላጆችና


ለባለድር አካላት ግልጽ ማድርግ
➢ ወላጆች በተማሪዎች ውጤትና ስነ- ምግባር መሻሻል ላይ ጉልህ አስታወጽኦ
እንዳላቸው ግንዛቤ መፍጠር
➢ ትምህርት ቤቱ ከወላጆች የሚሰጡ ግብረ መልሶችን ፣ አስተያየቶችንና ሌሎች
ግብዓቶችን በመሰብሰብና በመተንተን የእቅዱ አካል ማድረግ፡፡

ስታንዳርድ 21.3 ወላጆች ልጆቻቸው በቤት ውስጥ በትምህርታቸው እንዲበረታቱ ያግዛሉ፣

76
➢ የተማሪ ወላጆች ልጆቻቸው የክፍል ፣የቤት ስራና የግል ስራዎችን
ስለመስራታቸው መከታተል
➢ ወላጆች ለልጆቻቸው የጥናት ጊዜ በመመደብ ድጋፍና ክትትል ማድረግ
➢ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ሲያስመዘግቡ ማበረታቻ መስጠት

ስታንዳርድ 21.4 ወላጆች በወላጅ፣ተማሪ፣ መምህር ህብረት(ወመህ/ወተመህ) እንቅስቃሴ ላይ


ንቁ ተሳትፎ ያደርጋሉ፣

➢ ትምህርት ቤቶች በወመህ/ወተመህ አደረጃጀት ላይ የወላጆች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ


ግንዛቤ መፍጠር
➢ ትምህርት ቤት ውስጥ ባሉ የተለያዩ አደረጃጀቶች ላይ የወላጆች ተሳትፎ እንዲኖር
ትምህርት ቤቶች በእቅዳቸው ውስጥ አካተው መስራት

ስታንዳርድ 21.5 ትምህርት ቤቱ ለአካባቢው ማህበረሰብ በአንጻራዊነት የልህቀት ማዕከል


በመሆን ያገለግላል፣
➢ ትምህርት ቤቶች በፈጠራ፣በጤና፣በግብርናና ወዘተ… ተግባራት ላይ ግምባር
ቀደም/ሰርቶ ማሳያ እንዲሆኑ ማድረግ፡፡

ስታንዳርድ 21.6 ወላጆች በትምህርት ቤቱ የሥራ አፈፃፀም መርካታቸውን መረጃዎች


ያመላክታሉ፣

➢ በትምህርት ቤት ውስጥ የወላጆችን አስተያየት መስጫ ሳጥን በማዘጋጀት ተግባራዊ


እንዲሆን ማድረግ
➢ በወላጆች የተሰጡ አስተያየቶችን በመተንተን የርካታ ደረጃቸውን መለካትና
መግለጽ

77
ክፍል አራት

4. የድርጊት መርሃ ግብር እና የክትትልና ድጋፍ ስርዓት

4.1. የድርጊት መርሃ ግብር

የድርጊት መርሃ ግብር ፈፃሚ አካል


ተ/ቁ የሚከናወኑ ተግባራት
ህዳ ታህ ጥር የካ መጋ ሚያ ግን ሰኔ
የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን የአቅም
1 ግንባታ ማሰልጠኛ መነሻ ሰነድ ማዘጋጀት x
የተዘጋጀውን ሰነድ ከክልል ትምህርት ቢሮና
2 ባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር ማበልጸግ x
የተዘጋጀውን ሰነድ ለሁሉም ትምህርት ቤቶች
የሚደርስበትን ሁኔታ ማመቻቸት (በማእከል
ደረጃ ለተወሰኑ ትምህርት ቤቶች አሳትሞ
ማሰራጨት፣ ክልሎች በራሳቸው በጀት
3 አስተርጉመው ማሰራጨት x x x x
የትምህርት ቤት ድጎማ በጀት ከትምህርት ቤት
ደረጃ መሻሻል ጋር በማቆራኘት የበጀት
አጠቃቀም ስርኣት መዘርጋት (የትምህርት ቤት
ሪፖርት ካርድ፣ ትምህርት ቤቱ ያለበትን ደረጃ
4 የሚያሳይ ባነርና መሰል ዝግጅት) x
የትምህርት ቤት አመራር አቅም ለመገንባት
በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ክልላዊ የ አሰልጣኞች
5 ስልጠና መስጠት x

78
የድርጊት መርሃ ግብር ፈፃሚ አካል
ተ/ቁ የሚከናወኑ ተግባራት
ህዳ ታህ ጥር የካ መጋ ሚያ ግን ሰኔ
በተመረጡ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ
ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ የትምህርት ቤት
ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘር የትምህርት
ቤት ደረጃን ለማሻሻል በተዘጋጀው ሰነድ ላይ
የአምስት ቀን ስልጠና መስጠት (በተግባር
6 የተደገፈ) x
Conducting Re Inspection
ስልጠናውን ከወሰዱ የትምህርት ቤት ርዕሰ
መምህራን የሚመሯቸው ትምህርት ቤቶች
በስልጠናው መሰረት ከትምህርት ማህበረሰቡ
ጋር የጋራ መግባባት ፈጥረው ወደ ስራ የገቡ
ትምህርት ቤቶችን ሪፖርት መሰብሰብና ግብረ
7 መልስ መስጠት X x
ትምህርት ቤቶቻቸውን ለማሻሻል በትምህርት
ቤት ማህበረሰብ አማካነት እየተከናወኑ ያሉ
ጅምር ስራዎችን የመስክ ምልከታ በማካሄድ
ግብረ መልስ ለክልል፣ ለወረዳ፣ ክላስተርና
8 ትምህርት ቤት አመራር መስጠት x x x x x x
የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል
ለትምህርት ቤት አመራሮች 2ኛ ዙር የአቅም
ግንባታ ስልጠናና በመስክ የታዩ የጋራ ችግሮች
9 ላይ ግምገማዊ ስልጠና መስጠት x
የመጀመሪያ ሴሚስተር የተማሪዎች ውጤት
ትንተና በትምህርት ቤት ደረጃ እንዲዘጋጅ
ማድረግ፣ ለትምህርት ማህበረሰቡ ውጤቱን
ማሳወቅና የቀጣይ ስልቶችን አዘጋጅቶ
10 እንዲሄድ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ x

79
የድርጊት መርሃ ግብር ፈፃሚ አካል
ተ/ቁ የሚከናወኑ ተግባራት
ህዳ ታህ ጥር የካ መጋ ሚያ ግን ሰኔ
ትምህርት ቤቶቻቸውን ለማሻሻል በትምህርት
ቤት ማህበረሰብ አማካነት እየተከናወኑ ያሉ
ስራዎችን ሁለተኛ ዙር የመስክ ምልከታ
በማካሄድ ግብረ መልስ ለክልል፣ ለወረዳ፣
11 ክላስተርና ትምህርት ቤት አመራር መስጠት x
የትምህርት ቤቶችን አፈፃፀም የሚያሳይ
ሪፖርትና ግብረ መልስ ማዘጋጀትና
12 ለሚመለከታቸው አካላት ማስተዋወቅ x X x x x x x x
ትምህርት ቤቶች የኢንስፔክሽን አገልግሎት
13 እንዲያገኙ ማድረግ x x
የትምህርት ቤቶች መሻሻል ለመገምገም እና
የልምድ ልውውወጥ መድረክ ሆኖ
እንዲያገለግል የምክክር መድረክ ማዘጋጀት x x x

የልምድ ልውውጥ መድረክ ማዘጋጀት x


የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ትምህርት ቤቶች
ምርጥ ተሞክሮ መቀመር x x

4.2. የክትትልና ድጋፍ ስርዓት

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሻሻል አንጻር የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ሚናው ቀላል ባይሆንም በየደረጃው ያለው
የትምህርት መዋቅር ያለልተቋረጠ ክትትልና ድጋፍ አስተዋፅኦው ቀላል አይደለም፡፡ በመሆኑም ከትምህርተ ሚኒስቴር እስከ
ትምህርት ቤት ድረስ ባለው የትምህርት መዋቅር የሚገኙ አካላት የተፋጠነ የትምህርት ቤቶች ሽግግር ፕሮግራምን
ማስተባበር፣ መደገፍ፣ መከታተልና መገምገም ይጠበቅባቸዋል።

80
በዚህም መሰረት በክትትልና ድጋፍ ስርዓት ውስጥ ድርሻ የሚኖራቸው አካላት

• ትምህርት ሚኒስቴር
o ክቡር ሚኒስቴር፣ ሚኒስቴር ዴኤታ፣ የተለያዩ ዳሬክቶሬት ዳይሬክተርና ባለሙያዎች
• ክልል ትምህርት ቢሮ
o ቢሮ ሃላፊ፣ የተለያዩ ዳይሬክቶሬት ዳሬክተርና ባለሙያዎች
• ዞን ትምህርት መምሪያ
o የመምሪያው ሃላፊዎች፣ የስራ ክፍል ሃላፊዎችና ባለሙያዎች
• ወረዳ ትምህርት ጽኅፈት ቤት
o የጽህፈት ቤቱ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ የክላስተር ሱፐርቫይዘሮችና ሌሎች ውጫዊ አካላትም ይሳተፋሉ።

81
4.3. የክትትልና ድጋፍ መዋቅራዊ አካሄድ

የመስክ ምልከታ ድጋፍ መዋቅር


ግብረ መልስና ሪፖርት

ከ…
ትምህርት ሚኒስቴር ለ…

ወርሃዊ
በየ40 ቀን
በየ2 ወር ግብረ መልስ ወርሃዊ
ትምህርት ቢሮ ሪፖርት

በየ2 ሳምንት በየወሩ ግብረ


መልስ
በየወር
ዞን ትምህርት
በየሁለት
መምሪያ/ፎካል
ሳምንት
በየ15 ቀን
ግብረ መልስ
ወረዳ ትምህርት ጽህፈት
ቤት
በየሳምንት
በሳምንት
ሳምንታዊ
ግብረ መልስ
ትምህርት ቤት ሪፖርት

82
4.4. የሚያስፈልግ በጀት

4.4.1 ለአቅም ግንባታ ስልጠና

የበጀት መግለጫ
ተ/ቁ የሚከናወኑ ተግባራት
ፈፃሚ አካል
ከአማራ፣ ደቡብ ብ/ብ/ህ/ክልሎች የተሻለ ተሞክሮ
ያላቸውን የትምህርት ቤት ርእሰ መምህራን፣ 254310.00
ኢንስፔክተሮችና የክልል ባለሙያዎች እንደሁም ብር
ከትምህርት ሚኒስቴር የተለያዩ ስራ ክፍሎች
የተውጣጡ አጠቃላይ 30 ተሳታፊዎች ለ7 ቀናት
የሚሳተፉ ሲሆን አጠቃላይ ከመድረኩ የሚጠበቀው
ትምህርት ቤቶችን ለማሻሻል የሚያስችል
ስትራተጂካዊ ሰነድ ይዘጋጃል። ለመርሃ ግብሩ
የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን የአቅም አጠቃላይ ወጪ = የውሎ አበል፣ ትራንስፖርት፣
1 ግንባታ ማሰልጠኛ መነሻ ሰነድ ማዘጋጀት መስተንግዶና የፅሃፈት መሳሪያ ወጪ
ከየክልሉ ከትምህርት ቤት መሻሻልና 397500
ከኢንስፔክሽን የስራ ክፍሎች የተውጣጡ የስራ ብር
ሃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ከትምህርት
ሚኒስቴር የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራምና
ኢንስፔክሽን ዲፓርትመንት የተውጣጡ
ባለሙያዎች በጥቅሉ 50 ተሳታፊዎች በተዘጋጀው
መነሻ ሰነድ ላይ ለ 5 ቀናት የሚወያዩ ሲሆን
ከውይይቱም የአሰልጣኞች ስልጠና ለመስጠት
የሚስችል የማሰልጠኛ ሰነድ ይዘጋጃል። የክልል
ትምህርት ቢሮና ትምህርት ሚኒስቴር የጋራ
የተዘጋጀውን ሰነድ ከክልል ትምህርት ቢሮና እቅድ፣ የክትትልና ድጋፍ ስርዓት ተዘጋጅቶ
2 ባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር ማበልጸግ መግባባት ይደረስበታል። አጠቃላይ ወጪው=
የበጀት መግለጫ
ተ/ቁ የሚከናወኑ ተግባራት
ፈፃሚ አካል
ለውሎ አበል፣ የትራንስፖርት፣ የመስተንግዶና
የጽኅፈት መሳሪያ
የተዘጋጀውን ሰነድ ለሁሉም ትምህርት ትምህርት በቤቶችን በፍጥነት ወደ ስታንዳርድ 160000
ቤቶች የሚደርስበትን ሁኔታ ማመቻቸት ለማስጠጋት የሚስችል ስትራቴጂክ ሰነድ ብር
(በማእከል ደረጃ ለተወሰኑ ትምህርት ቤቶች የመጨረሻ ቅርፁን ኬዘና አመራሩ ውሳኔ ከሰጠበት
አሳትሞ ማሰራጨት፣ ክልሎች በራሳቸው በኋላ በትምህርት መሳሪዎች ማምረቻ ድርጅት
3 በጀት አስተርጉመው ማሰራጨት አልያም በሌላ ወደ ህትመት የሚገባ ይሆናል።
የትምህርት ቤት ድጎማ በጀት ከትምህርት ሁሉም ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቤት ድጎማ
ቤት ደረጃ መሻሻል ጋር በማቆራኘት የበጀት በጀትን በመጠቀም የትምህርት ቤት ሪፖርት
አጠቃቀም ስርኣት መዘርጋት (የትምህርት ካርድ እንዲጠቀሙ ማድረግ
ቤት ሪፖርት ካርድ፣ ትምህርት ቤቱ
ያለበትን ደረጃ የሚያሳይ ባነርና መሰል
4 ዝግጅት)
ለ120 የትምህርት ቤት አመረሮች (ር/መምህራን 1037800
እና ሱፐርቫይዘሮች) የአሰልጣኘች ስልጠና ብር
ለአምስት ለ7 ቀናት መስጠት። አጠቃላይ ወጪ
የትምህርት ቤት አመራር አቅም ለመገንባት ለአሰልጣኞች የሙያ ክፍያ፣ ለውሎ
በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ክልላዊ የ አሰልጣኞች አበል፣ለትራንስፖርት፣ ለሪፍሬሽመንት እና
5 ስልጠና መስጠት ለአዳራሽ ክፍያ፣ለስቴሽነሪ
በተመረጡ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ 2000 የትምህርት ቤት አመራሮች የ5 ቀናት 12745000
ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ የትምህርት ቤት ስልጠና መስጠት ብር
ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘር የትምህርት ወጪ ለአሰልጣኞች የሙያ ክፍያ፣ ለውሎ
ቤት ደረጃን ለማሻሻል በተዘጋጀው ሰነድ ላይ አበል፣ለትራንስፖርት፣ ለሪፍሬሽመንት እና
የአምስት ቀን ስልጠና መስጠት (በተግባር ለአዳራሽ ክፍያ፣ለስቴሽነሪ
6 የተደገፈ)
ለ2000 ትምህርት ቤቶች የኢንስፔክሽን
ለትምህርት ቤቶች የዳግም ኢንስፔክሽን አገልግሎት መስጠት።ለኢንስፔክሽን አገልግሎት
7 አገልግሎት መስጠት ለመስጥ ቢያንስ ሁለት ኢንስፔክተር ለአንድ

84
የበጀት መግለጫ
ተ/ቁ የሚከናወኑ ተግባራት
ፈፃሚ አካል
ትምህርት ቤት፣ ለ4 የኢንስፔክሽን ቀናት 2 ቀን
የሪፖረት ዝግጅት ሆኖ ለውሎ አበል እና
ለትራንስፖርት
ስልጠናውን ከወሰዱ የትምህርት ቤት ርዕሰ የመረጃ ማሰባሰብ ስራ የተሻለ አፈፃፀም ያላቸው 192000
መምህራን የሚመሯቸው ትምህርት ቤቶች ትምህርት ቤቶች 6 ቡድን አባላት በእያንዳንዱ ብር
በስልጠናው መሰረት ከትምህርት ማህበረሰቡ ቡድን ውስጥ 4 አባላት እንዲኖሩት ተድረጎ ለ20
ጋር የጋራ መግባባት ፈጥረው ወደ ስራ የገቡ ቀናት ይሆናል።
ትምህርት ቤቶችን ሪፖርት መሰብሰብና ወጪ ለነዳጅ እና ለውሎ አበል
8 ግብረ መልስ መስጠት
ትምህርት ቤቶቻቸውን ለማሻሻል የምስክ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እና ግብረመልስ 192000
በትምህርት ቤት ማህበረሰብ አማካነት መስጠት ብር
እየተከናወኑ ያሉ ጅምር ስራዎችን የመስክ ወጪ ለነዳጅ ለትራንስፖርት
ምልከታ በማካሄድ ግብረ መልስ ለክልል፣
ለወረዳ፣ ክላስተርና ትምህርት ቤት አመራር
9 መስጠት
የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል በመስክ የተገኘውን ተሞክሮ መሰረት በማድረግ 1037800
ለትምህርት ቤት አመራሮች 2ኛ ዙር ለ120 የትምህርት ቤት አመራሮች ለ5 ቀናት ብር
የአቅም ግንባታ ስልጠናና በመስክ የታዩ መስጠት አጠቃላይ ወጪው= ለውሎ አበል፣
የጋራ ችግሮች ላይ ግምገማዊ ስልጠና የትራንስፖርት፣ የመስተንግዶና የጽኅፈት መሳሪያ
10 መስጠት
የመጀመሪያ ሴሚስተር የተማሪዎች ውጤት
ትንተና በትምህርት ቤት ደረጃ እንዲዘጋጅ
ማድረግ፣ ለትምህርት ማህበረሰቡ ውጤቱን
ማሳወቅና የቀጣይ ስልቶችን አዘጋጅቶ
11 እንዲሄድ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
ትምህርት ቤቶቻቸውን ለማሻሻል የምስክ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እና ግብረመልስ 192000
በትምህርት ቤት ማህበረሰብ አማካነት መስጠት ብር
12 እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ሁለተኛ ዙር ወጪ ለነዳጅ ለትራንስፖርት

85
የበጀት መግለጫ
ተ/ቁ የሚከናወኑ ተግባራት
ፈፃሚ አካል
የመስክ ምልከታ በማካሄድ ግብረ መልስ
ለክልል፣ ለወረዳ፣ ክላስተርና ትምህርት ቤት
አመራር መስጠት
የትምህርት ቤቶችን አፈፃፀም የሚያሳይ
ሪፖርትና ግብረ መልስ ማዘጋጀትና
13 ለሚመለከታቸው አካላት ማስተዋወቅ
በተመረጡ ትምህርት ቤቶች ላይ በመገኘት 183600.00 ብር
የልምድ ልውውጥ መድረክ ማዘጋጀት
የተሻለ አፈፃፀም ካስመዘገቡ ትምህርት ለ5 ቀናት የጎዞን ጨመር 20 የትምህርት ቤት
ቤቶች መካከል የተወሰኑት ለሌሎች አመራሮች በተገኙበት
ትምህርት በቤቶች ልምድ እንዲሰጡ ወጪ ውሎ አበል እና ትራንስፖርት፣
16 ማድረግ አዳራሽ፣ሪፍሬሽመንት እና የጽህፍት መሳሪያዎች
የተሻለ አፈጻፀም ካሳዩ ትምህርት ቤቶች የተመረጡ 21 ትምህርት ቤቶች ላይ የልምድ 266000
መልካም ተሞክሮ መቀመር፣ ማሳተምና ልውውጥ ማድረግ፣ 7 ቡድን ለ25 ቀናት፣ ለውሎ ብር
17 ማሰራጨት አበል እና ትራንስፖርት
16658010.00ብር

4.4.2 ለትምህርት ቤቶች መሰረተ ልማትና ግብአት

በ2009 ዓ/ም እና በ2010 ዓ/ም የትምህርት ቤቶች ዳግም ኢንስፔክሽን በደረጃ አንድ እና በደረጃ ሁለት ላይ ካሉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ
ከስታንዳርድ 1 አንፃር 96%ቱ ትምህርት ቤቶች በዚሁ ስታንዳርድ ያስመዘገቡት ውጤት ከደረጃ በታች መሆኑን ያሳያል፡፡ ይህም በአጭሩ
እነዚህ ትምህርት ቤቶች ግንባታቸው የተሟላ አለመሆኑ፣ በቂ የትምህርት ቤት የውስጥ ቁሳቁስ (የተማሪ ዴስክና መሰል) ያልተሟላላቸው
(ተማሪዎች በእንጨትና መሬት ላይ የሚቀመጡ፣ በቂ የማጣቀሻ መፅሃፍት የሌላቸው እንዲሁም የላብራቶሪ ቁሳቁስ ጨርሶ የሌላቸው
እንደሆነ ከስታንዳርዱ ዝርዝር አመልካች መረዳት ይቻላል። በመሆኑም ትምህርት ቤቶቹን ወደ ስታንዳርዱ ለማስጠጋት ከሚሰራው የአቅም
ግንባታ ስራ በተጨማሪ እነዚህን ትምህርት ቤቶች በግብአት ማጠናከር አስፈላጊ ይሆናል። በዚህም መሰረት ትምህርት ቤቶቹን በፍጥነት

86
ወደ ስታንዳርዱ ለማስጠጋት በየክልሉ የተለያዩ ፍላጎትና የትምህርት ቤቶች ብዛት ያለ በመሆኑ ይህን ታሳቢ ያደረገ የወጪ ዝርዝር
እንደሚከተለው ቀርቧል።

4.4.2.1 አራቱ ታዳጊ ክልሎች (የሚሻሻል)

የማጣቀሻ መፅሃፍ የሳይንስ ኪት ቆርቆሮ አጠቃላይ


ዳግም የግብአት በአንድ ድምር
ኢንስፔክሽን ድጋፍ የማጣቀሻ የሳይንስ ትምህርት
የተካሄደባቸ ደረጃ የሚደረግላቸ መፅሃፍ (100 ዋጋ (መቶ ኪት ቤት 100
ው ትምህርት ደረጃ ደረጃ 1 እና ው ትምህርት ማጣቀሻ ብር (90% ዋጋ (5000 ቆርቆሮ ዋጋ (280
ክልል ቤቶች 1% 2% 2 ቤቶች በት/ት ቤት) በመፅሃፍ) ት/ቤቶች) ብር/በኪት) ለ2 ክፍል ብር/)
አፋር 330 78.8 20.3 99.1 164 16,350 1,635,000 441 2,207,250 16350 4,578,000 8,420,250
ሶማሌ 423 69.7 26.5 96.2 204 20,350 2,035,000 549 2,747,250 20350 5,698,000 10,480,250
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 238 89.5 9.2 98.7 118 11,750 1,175,000 317 1,586,250 11750 3,290,000 6,051,250
ጋምቤላ 16 50.0 43.8 93.8 15 1,500 150,000 40.5 202,500 1500 420,000 772,500
ድምር 500 49,950 4,995,000 1349 6,743,250 49950 13,986,000 25,724,250

4.4.2.2 ሀረሪና ድሬደዋ ከተማ መስተዳድር (የሚሻሻል)

የማጣቀሻ መፅሃፍ የሳይንስ ኪት ቆርቆሮ አጠቃላይ


ዳግም የግብአት በአንድ ድምር
ኢንስፔክሽን ድጋፍ የማጣቀሻ የሳይንስ ትምህርት
የተካሄደባቸ ደረጃ የሚደረግላቸ መፅሃፍ (100 ዋጋ (መቶ ኪት ቤት 100
ው ትምህርት ደረጃ ደረጃ 1 እና ው ትምህርት ማጣቀሻ ብር (90% ዋጋ (5000 ቆርቆሮ ዋጋ (280
ክልል ቤቶች 1% 2% 2 ቤቶች በት/ት ቤት) በመፅሃፍ) ት/ቤቶች) ብር/በኪት) ለ2 ክፍል ብር/)
ድሬደዋ 86 41.9 41.9 83.7 18 1,800 180,000 16.2 81,000 1800 504,000 765,000
ሀረሪ 24 37.5 58.3 95.8 6 600 60,000 6 30,000 575 161,000 251,000
ድምር 110 24 2,400 240,000 22.2 111,000 2375 665,000 1,016,000

87
4.4.2.3 ትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ደቡብ ብ/ብ/ህ/ እና አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር (የሚሻሻል)

የማጣቀሻ መፅሃፍ የሳይንስ ኪት ቆርቆሮ አጠቃላይ


ዳግም የግብአት በአንድ ድምር
ኢንስፔክሽን ድጋፍ የማጣቀሻ የሳይንስ ትምህርት
የተካሄደባቸው የሚደረግላቸ መፅሃፍ (100 ኪት ቤት 100
ትምህርት ደረጃ 1 ደረጃ ደረጃ 1 ው ትምህርት ማጣቀሻ በት/ት ዋጋ (መቶ ብር (90% ዋጋ (5000 ቆርቆሮ ዋጋ (280
ክልል ቤቶች % 2% እና 2 ቤቶች ቤት) በመፅሃፍ) ት/ቤቶች) ብር/በኪት) ለ2 ክፍል ብር/)
Addis Ababa 808 26.9 59.3 86.1 35 3,500 350,000 32 157,500 3500 980,000 1,487,500
Amhara 6955 50.4 45.1 95.5 332 33,200 3,320,000 299 1,494,000 33200 9,296,000 14,110,000
Oromiya 11100 66.1 31.7 97.9 543 54,300 5,430,000 489 2,443,500 54300 15,204,000 23,077,500
SNNPR 2415 66.8 30 96.8 117 11,700 1,170,000 105 526,500 11700 3,276,000 4,972,500
Tigray 745 55 42.1 97.2 36 3,600 360,000 32 162,000 3600 1,013,600 1,535,600
Total 22023 1063 106,300 10,630,000 957 4,783,500 106300 29,769,600 45,183,100

አጠቃላይ ለግብአት ወጪ 71923350.00

• ለታዳጊ ክልሎች 25,724,250


• ለሀረሪና ድሬደዋ ከተማ መስተዳድር 1,016,000
• አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድርን ጨምሮ ቀሪዎቹ ክልሎች 45,183,100

88

You might also like