You are on page 1of 2

Thirteen Star Plc.

በአዋሽ ባንክ አክስዮን ማህበር / አበዳር/

እና

በሰርቲን ስታር ኃ/የተ/የግ/ማህበር ፣ አድራሻ የካ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 02፣ ስልክ ቁጥር 0911-35-42-

67 /ወካይ እና ተበዳር/ ፡፡ እንድሁም በተወካይ በኤልአውቶ አሴምብሊንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር አድራሻ

ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 07፣ ስልክ ቁጥር 0930-03-33-03 /ተወካይ/ መካከል የተደረገ በመኪና ላይ

የምለጠፍ የማስታወቂያ ስራ ስምምነት ነዉ፡፡

ይህ ስምምነት በመኪና ላይ የምለጠፍ የማስታወቂያ ስራ ስምምነት ነዉ ፡፡ ስምምነቱም የምከተሉትን

ሁኔታዎችን ያካተተ እንድሁም በሶስቱም አካላት ስምምነት ተፈጻም የምደረግ ይሆናል ፡፡

 ተበዳሪዉ በዋስትነና የሰጣቸዉን ንብረቶች ሁሉ ሁኔታ በማደስና በመንከባከብ የመጠበቅ ግዴታ

አለበት፡፡

ተበዳሪዉ ከባንኩ በወደሰደዉ የብድር ገንዘብ በገዛቸዉና በዚህ የብድር ዉል ላይ በዝርዝር በተገለጹት

46 (አርባ ስድስት) JAC J4 2020 ሞዴል ተሸከርካሪዎች ለይ ባንኩ ማሰታወቂያዎቹን አዘጋጅቶ

ከለጠፈበት ቀን ጀምሮ ለቀጣዮቹ ሁለት አመታት የባንኩን ምርቶች እና አገልግሎቶች

የሚያስተወዋዉቁ ማስታወቂያዎችን ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ በሚከተሉት ሁኔታዎች መሰረት

ተሰማምቷል፡፡

 ተበዳሪዉ በተሽከርካሪዎቹ ግራና ቀኝ ፣ከ ኃዋላ በር ቀጥሎ ባለዉ ክፍት ባታ ፣እንዲሁም ከ ጀርባ

ላይ የባንኩን ምርቶችና አገልግሎቶች የሚያሰተዋዉቁ የሰቲከር ማስታወቂያዎቹን ይለጥፍል

ባንኩ በራሱ ወጭ ወሩ ማስታወቂያቹን መለዋወጥ ይችላል፡፡


Thirteen Star Plc.
 የባንኩ መለያ (brand) ከመጠበቅ አኳያ ተበዳሪዉ ሁሉጊዜ የተሽከርሪዎቹን ንጽህና የመጠበቅና

ለዕይታ ሳቢ ሆነዉ እንዲታዩ ለማድረግ ተሰማምቷል፣ለዚህም ዋሰትና ይሰጣል፣ተበዳሪዉ ባንኩ

በየጊዜዉ የሚያቀርብለትንና የባንኩን ምርቶችና አገልግሎተቶች የሚያስተዋዉቁ በራሪ ጽሑፎችና

እና ብሮሽሮች ተሽከርካሪዋቹ ዉስጥ ለተሳፋሪ እይታ ቅርብና ምቹ በሆኑ ባታዎች ላይ እንዲቀመጡ

ይደረጋል፣በሚያልቅበት ጊዜም ባንኩ እንዲያቀርብለት ይጠይቃል፡፡

 የማስታወቂያዎቹ ዲዛይን በ ባንኩ የሚወሰን ሆኖ የህትመት ወጪ፣የማስታወቂያ ግብር (ካለ) እና

ሌሎች ከማስታወቂያዉ ጋር የሚገናኙ ተያያዥ ወጪዎች በባንኩ የሽፈኑ ይሆናል፡፡

 በተበዳሪዉ ወይም በሹፌሮቹ ጥፋት ምክንያት የመቀየሪያ ጊዜያቸዉ ሳይደርስ (ሶስት ወር

ሳይማላቸዉ) ማስታወቂያቹ ቢበላሹ ወይም ቢቀደዱ በተበዳሪዉ ወጪ የማስታወቂያዉ ሕትመት

በድጋሚ ተዘጋጅቶ ይለጠፋል፡፡

 የማስታወቂያ ሂደቱ በአግባቡ እየተከናወነ መሆኑን ባንኩ ይቆጣጠራል፣ለዚህም ይረዳዉ ዘንድ የ 24

ሰዓት የዝግጅት ጊዜ በፅሁፍ ለተበዳሪዉ በመሰጠት ተሽከርካሪዎቹ ለእይታ ምቹ በሆነ ቦታ በአንድ ላይ

እንዲገኙለት ለማድረግ ይችላል፡፡

 ይህ የሁለት ዓመት የማስታወቂያ አገልግሎት ጊዜ ገደብ ከዋናዉ የብድር ዉል ጊዜ ዘመን /ጊዜ ገደብ/

ጋር የማይያያዝ እና የጊዜ ገደቡ ከመጠናቀቁ 30 ቀናት አስቀድሞ የማስታወቂያ ጊዜ እንዲራዘመም

የሚፈልግ ወገን የስምምንት ነጥቦቹን በማስቀመጥ ለሌላኛዉ ተዋዋይ የዉል ጊዜዉ እንዲራዘም በፅሁፍ

ለመጠየቅ ይችላል፡፡

You might also like