You are on page 1of 4

የወገብ ህመምየወልቃይት ስትራቴጅክ ጠቀሜታና የውጭ ኃይሎች የፖለቲካ ሴራ!

(ክፍል አንድ) ስትራቴጅካዊ

ጠቀሜታ! በዚህ ትንታኔ ለአንባቢን መሰረታዊ ግንዛቤ ያመች ዘንድ ‹ወልቃይት› እያልን የምንጠራው አካባቢ ሰቲት

ሁመራን፤ ጠገዴንና ጠለምትን ያካትታል፡፡ በዚህ ቀጠና እንደአማራ ቀዳሚ ፍላጎታችን የተነጠቀ ማንነታችንን

ማስመለስ ሲሆን፤ አማራ በመሆናቸው ብቻ በትህነግ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈጸምባቸው የኖሩ ወገኖቻችን

ከቀጥተኛ የህልውና አደጋ ተጋላጭነት ነጻ ማድረግ፣ እንዲጠፋ ሲሰራበት የኖረውን አማራዊ ማንነታቸው ዳግም

አብቦ፣ የተጎዳ ስነ-ልቦናቸው ተጠግኖ አማራዊ የአስተዳደር ነጻነታቸው እውን ሁኖ ማየትና ለሠላሳ ዓመታት

ለተፈጸመው ግፍና በደል የፍትሕና የካሳ ጥያቄ ያለን መሆኑ እንደተጠበቀ ሁኖ፤ በዚህ ጽሁፍ የአካባቢውን

ስትራቴጅካዊ ጠቀሜታ እንመለከታለን፡፡ ጉዳዩ ከርስት በላይ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ሉአላዊነት

የማስጠበቅ ጉዳይ ስለመሆኑ በማስረጃዎች እንፈትሻለን፡፡ ወልቃይት የቀጣናዊ ፖለቲካዊ መስፈንጠሪያ ማዕከል እና

የብሔራዊ ደህንነታችን አስኳል ስለመሆኗ በዝርዝር እንመለከታለን፡፡ የወልቃይት ጉዳይ፣ ተለዋዋጭ የሆነውን

የምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካን የመወሰን አቅም አለው፡፡ ትልቁ ጉልበቱ ለጂኦ-ፖለቲክሱ ያለው ጠቀሜታ ነው፡፡

የተከዜ-አጥባራ ንዑስ ተፋሰስ ድንበሮች ይህን አካባቢ በሰፊው ያካልላሉ፡፡ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሱዳን በዚህ

ተፋሰስ በርካታ ከተሞቻቸውን ያደርሳሉ፡፡ ዋናው መነሻና ማዕከሉ ግን ወልቃይት ነው፡፡ በሰብል ምርት አቅሙ

የአፍሪካን የግብርና ታሪክ የቀየረ አካባቢ ስለመሆኑ ምሁራን በጥናቶቻቸው መስክረዋል፡፡ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ

ዘመን፣ የኢትዮጵያን ግብርና ልማት ለማምጣት ሲካሄድ ከነበረው ጥረት አንዱ ‹Comprehensive Package

Project (CPP)› የተሰኘው ፕሮጀክት ነበር፡፡ ይህ ፕሮጀክት በተመረጡ የኢትዮጵያ ለም አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ

የግብርና ልማት ሥራን በማከናወንና ትርፍ እህል በማምረት በምግብ እህል ራስን መቻል፣ ለውጭ ንግድ ማቅረብና

ለሌላው መማርያ መሆን በሚል ዓላማ የተጀመረ ነበር፡፡ እነዚህ የልማት ፕሮጀክቶች በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል

እንዲካሄዱ ከተመረጠበት ቦታ አንዱ የበጌምድሩ ሁመራ (Humera Agricultural Devt Unit)፤ በዛሬዋ ኤርትራ

ጋሽ ባርካና ታህታይ አዲያቦ (GBADU, TARDU) ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከፍተኛ የሆነ

የመንግስትና የብድር ገንዘብ ወጭ ተደርጎበት ሲካሄድ የነበረው የግብርና ልማት ፕሮጀክት አንዱና ዋነኛው

የወልቃይት ሁመራ ፕሮጀክት ነበር፡፡ በዚህ ፕሮጀክት የተነሳ ነበር የአፍሪካን የግብርና ታሪክ የቀየረ ሰፊ ምርት

ማግኘት የተጀመረው፡፡ ይህ እንድምታ በነጻነት ራሷን ችላ በቆመች ሀገር፣ በመኪና (ትራክተር) በማረስ የሰፊ

ግብርና ምርት ባለቤት የመሆን ተምሳሌት ለሆነችው ኢትዮጵያ ወልቃይት ትልቅ የግብርና አቅም ሊሆናት ችሏል፡፡

ከዚህ የምርት አቅሙ በተጨማሪ ወደጎረቤት ሀገር ሱዳን ለመሻገር ወሰኝ አካባቢ በመሆኑ ከዘውዳዊው ሥርዓት

ማክተም በኋላ በአካባቢው መንቀሳቀስ የጀመሩ ኃይሎች ዐይናቸውን ሲጥሉበት ታይቷል፡፡ የኢትዮጵያ

ዴሞክራሲያዊ ኀብረት (EDU) በተቀናጀ ሁኔታ ትግል ሲጀምር ወልቃይትን የትኩረት ማዕከሉ ለማድረግ ሞክሯል፡፡

አንድም አካባቢው ሰፋፊ የእርሻ ልማት ያለበት በመሆኑ ከመንግሥታዊ ኃይሎች የዕለት ተዕለት ቁጥጥር አንጻራዊ
ነጻነት ለማግኘት፤ አንድም ደግሞ ከጎረቤት ሀገር ሱዳን ድጋፍ ለማግኘት ወሳኝ ስትራቴጅካዊ ቦታ በመሆኑ

ወልቃይትን መርጧል፡፡ በዚህም ከወቅቱ የሱዳን (ኒሜሪ) መንግሥት የሎጀስቲክስ ድጋፍ ለማግኘት አግዟቸዋል፡፡

በወቅቱ ሱዳን ውስጥ የሬዲዮ ጣቢያና የካድሬ ትምህርት ቤት ከፍተው ማስተማር የቻሉት የኢትዮጵያ

ዴሞክራሲያዊ ኀብረት አመራሮች፣ ወልቃይት ዋና መንቀሳቀሻው እንደነበረ የዘመኑ ወታደራዊና አብዮታዊ ታሪክ

ጥናቶች (John Young 1997, Christopher Clapham 1998) ያመለክታሉ፡፡ ከኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኀብረት

(በተለምዶ ‹ኢዲዩ›) መዳከም በኋላ ደግሞ የግዛት ተስፋፊው ትህነግ አካባቢውን ለመቆጣጠር ብርቱ ጥረት

አድርጓል፡፡ በተለይም ከሱዳን ድጋፍ ለማግኘት ተከዜን መሻገርና አካባቢውን መቆጣጠር የግድ አስፈላጊ ሁኖ

ስላገኘው ትግሉን የሞት ሽረት ለማድረግ ተገድዷል፡፡ ከ 1972 ዓ.ም እስከ 1976 ዓ.ም ባሉት አመታት ውስጥ

ትህነግ ከደርግ ጋር ስያካሂድ በነበረው ጦርነት ምክንያት አካባቢውን በቁጥጥር ስር ቢያደርገውም፣ የወልቃይት

አማራ ግን አልተቀበለውም ነበር፡፡ በወቅቱ ሕዝብ ከማስተዳደር ይልቅ ወደሱዳን መመላለሻ ኮሪደሩን ለወታደራዊ

ዓላማ መጠቀም የመረጠው ትህነግ የደርግን ወታደራዊ ውድቀት ወደዕድል ለመቀየር አካባቢውን ተጠቅሞበታል፡፡

በመጨረሻም ከደርግ መንግስት ውድቀት በኃላ በ 1984 ዓ.ም. ህጋዊ ባልሆነ መንገድ፣ ያለሕዝቡ ይሁንታ

ወልቃይትን የትግራይ አካል አደረገው፡፡ ይሄም ማለት አሁን በስራ ላይ ያለው የኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት ከመጽደቁና

ሥራ ላይ ከመዋሉ ከሦስት ዓመት በፊት መሆኑ ነው፡፡ እዚህ ላይ ዛሬም እንደገና መነሳት ያለበትና በደንብ ሊታይ

የሚገባው አንድ መሰረታዊ ነገር አለ፡፡ ይሄውም ‹ትህነግ በታሪክ የትግራይ አካል ሁኖ የማያውቀውን ‹ወልቃይት› ከ

(በጌምድር) አማራ ህዝብ በጉልበት ነጥቆ ለምን የትግራይ አካል አድርጎ መቀጠል ፈለገ?› የሚለው ነው፡፡

በመግቢያችን ላይ እንደተመለከትነው ጉዳዩ በዋናነት ከጂኦ-ፖለቲካው ጋር ይገናኛል፡፡ እንደሀገርም ሆነ እንደሕዝብ

ከተጋረጠብን አደጋ አኳያ በዚህ ጉዳይ ላይ የጠራ ግንዛቤ ለመፍጠር ወሳኙን አጀንዳ ደግሞ ደጋግሞ ማጤንና

ማስታወስ አስፈላጊ ሁኖ አግንተነዋል፡፡ ስለሆነም ትህነግ የወልቃይትን ጉዳይ የሞት ሽረት ትግል ያደረገባቸውን

አራት ዋነኛ ምክንያቶች ተለይተው እንደሚከተለው ቀርበዋል፡- 1.) ወልቃይትን የትግራይ አካል ማድረግ፤

ኢትዮጵያን በተለይም አማራን የማዳከም አንዱና ዋነኛው የትህነግ ስትራቴጅ ሁኖ መገኘቱ ቀዳሚው ምክንያት

ነው! መላው የአማራ ህዝብ እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍ ሲል ደግሞ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ

እንደሚያውቀው፤ ትህነግ የኢትዮጵያና የአማራ ህዝብ ቀንደኛ ጠላት ነው፡፡ ትህነግ ኢትዮጵያን በመበተን ‹ታላቋ

ትግራይ›ን ለመመስረት አቅዶ የተነሳና ዛሬም ድረስ በዚሁ መርህ እየተመራ ያለ ጸረ-ኢትዮጵያ ኃይል ነው፡፡

በተለይም ደግሞ አማራን በቀዳሚ ጠላትነት ፈርጆ የተነሳና የታገለ፤ በተግባርም ዓላማውን ለመፈጸም ብዙ ርቀት

የተጓዘ፣ ዛሬም ግማሽ አካሉ መቃብር በወረደበት በዚህ ዘመን ከቀደሙት ጥፋቶቹ ሳይታረም በአውዳሚ መስመሩ

ላይ የቆመ ድርጅት ነው፡፡ ስለሆነም ሁሌም ቢሆን የተዳከመች ኢትዮጵያንና አማራን ማየት የትህነጋዊያን ያደረና

ዛሬም ያለ ህልም ነው፡፡ የትሕነግ ስሌት እጅግ በተዳከመችና በተከፋፈለች ኢትዮጵያ፤ ግዛቱን አጥቶ በተበታተነው
አማራ መቃብር ላይ ‹የታላቋ ትግራይ ሪፐብሊክ አጀንዳችንን እውን እናደርጋለን› የሚል ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ

ኢትዮጵያን ማዳከም፤ አማራውን መበተን የግቡ ማሳለጫ መንገድ አድርጎ ቆጥሮታል፡፡ የወልቃይት ጂኦ-ፖለቲካዊ

ጠቀሜታ ኢትዮጵያ በቀጠናው ላይ ለሚኖራት የበላይት እጅግ ወሳኝ ስትራቴጅካዊ አካባቢ ሲሆን፤ ለአማራ ህዝብ

ደግሞ ሁለመናው ናት፡፡ ትህነግ ይህን በሚገባ ከተገነዘበ ውሎ አድሯል፡፡ ‹ወልቃይት ለአማራ ህዝብ ሁለመናው ናት›

ስንል እንዲሁ ሳይሆን፤ እጅግ ዘርፈ ብዙ አገራዊና ክልላዊ ፋይዳ ያላት ከመሆኑም በላይ ለአማራ ህዝብ የማንነቱ

መገለጫውና ኩራቱም በመሆኑ ጭምር ነው፡፡ ስለሆነም ወልቃይትን ከአማራ መንጠቅ ለኢትዮጵያም ሆነ ለአማራ

ህዝብ ጉዳቱ ከፍተኛ ሲሆን፤ ለትህነጋዊያን ደግሞ የደደቢት ቅዠታቸው የሆነውን ‹ታላቋ ትግራይ›ን እንዲመሰርቱ

ትልቁን በር ይከፍትላቸዋል፡፡ ለዚህ ነው ትህነጋዊያን ወልቃይትን የሞት ሽረት ጉዳይ አድርገው የሚመለከቱት፡፡ 2.)

ትህነግ ወልቃይትና አካባቢውን ዳግም በመቆጣጠር ኢትዮጵያንና አማራን ለማዳከም ሌላ እድል ያገኝበታል! ትህነግ

ወልቃይትን በመቆጣጠር ከሱዳን ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር፤ ያልተገደበና በራሱ የሚመራ የውጭ ግንኙነት

በመፍጠር፤ አገር የመሆን ህልሙን እውን ለማድረግ ይጠቀምበታል፡፡ ከሱዳን ወታደራዊ ኃይል ጋር በመሻረክ

ከሁመራ እስከ ቤንሻንጉል ያለውን የኢትዮጵያ መሬት የመቀራመት ፍላጎት እንዳለው በሀገር ክህደት ተግባራቱ

አሳይቶናል፡፡ በተጨማሪም ግብጽን የመሰሉ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶችን እየመራ ለማምጣት፣ በእነርሱ የመሳሪያ

ድጋፍ ማዕከላዊ መንግሥቱንና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትን በመውጋት ኢትዮጵያን ወደፍርስራሽነት

በመቀየር ግብጽ በአባይ ፖለቲካ የነበራትን የበላይነት በቋሚነት ለማስቀጠል የባንዳነት ተልዕኮውን ለመወጣት፣

በወኪሎቹ በኩል የካይሮን ደጅ ደጋግሞ ረግጧል፡፡ የትህነግ ጭፍራዎች ከግብጽ ሚዲያዎች እኩል ጸረ-ኢትዮጵያ

የሆኑ ፕሮፖጋንዳዎችን ሲነዙ የሚውሉት ኢትዮጵያን ለማፍረስ የጋራ ውል ያላቸው በመሆኑ ነው፡፡ በዚህ ሂደት

ትህነጎች ቢሳካላቸው እስከ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ያለውንና በምናብ ካርታቸው ላይ ያሳዩንን መሬት አካተው

የ‹‹ታላቋ ትራግይ››ን ምስረታ እውን ሲያደርጉ፤ የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ደግሞ ባልተጨበጠ የታሪክ ዳራ እና የሕግ

ማዕቀፍ ከኢትዮጵያ ‹‹አለን›› የሚለውን መሬት በቀላሉ ይረከባል፡፡ ምኞታቸው ይህ ነው፡፡ በዚህ የተቀናጀና

የኢትዮጵያን ታሪካዊ ጠላቶች ባሳተፈ የወረራ ተግባር የተዳከመች ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን የተበታተነች ኢትዮጵያ

እንድትፈጠር አልመው ይሰራሉ፤ እንደሕዝብ ጨርሶ የሚጠፋ አማራ እንዲኖር ይፈልጋሉ፡፡ በጠቅላላ ሂደቱም

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ከመኖር ወደአለመኖር በመቀየር የኢትዮጵያ ጠላቶችን ማስደሰት የትህነጎች ፍላጎት ስለመሆኑ

ገሃድ ወጥቷል፡፡ ለዚህ ስኬት ደግሞ ወልቃይትንና አካባቢውን ዳግም መልሶ መቆጣጠርን የሞት ሽረት ጉዳይ

አድርገውታል፡፡ 3. ) ኢትዮጵያ በአማራ በኩል ከኤርትራ ጋር እንዳትገናኝ የማድረግ ሴራ! ትህነጎች ኢትዮጵያ

በተለይም አማራ ከኤርትራ ጋር በድንበር እንዳይገናኝ በማድረግ የኢትዮ- ኤርትራን ግንኙነት ለመገደብ

ከመፈለጋቸውም በላይ አማራ ከኤርትራ ወንድም ሕዝብ ጋር በማህበረ-ኢኮኖሚውም ሆነ በጋራ የጸጥታ ጉዳዮች

መልካም መስተጋብር እንዳይኖረው ይፈልጋሉ፡፡ እንደሚታወቀው ኤርትራዊያን ከትግራይ ልሂቃን ይልቅ


ከኢትዮጵያዊያን ጋር በተለይም ደግሞ ከአማራ ጋር የቀረበ ቀረቤታና ፍቅር አላቸው፡፡ ይሄን እውነታ የሚያውቀው

ትህነግ አማራና ኤርትራዊያን ምንም አይነት ግንኙነት እንዳይኖራቸው አድርጎ ቆይቷል፡፡ ይሄ የቆየ የፖለቲካ

መሰናክል አሁንም እንዲቀጥል ፍላጎት አላቸው፡፡ ይህ የሚሆነው ደግሞ ወልቃይት በትህጎች እጅ በጉልበት መልሶ

ሲገባ ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም ወልቃይትን ላለማጣት ትህነጎች የሞትሽረት ትግል ለማድረግ ይፈልጋሉ፡፡ 4. )

ወልቃይት ለትህነጋዊያን ትልቅ የሀብት ምንጭ፤የገዥ መደብ መሰረት መሆኑ! መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤

በአንድ በኩል የሀገርን ኢኮኖሚ በሚያቆረቁዝ ደረጃ የኮንትሮ ባንድ ንግዱን በመጠቀም፤ በሌላ በኩል ደግሞ በመቶ

ሽህዎች የሚቆጠሩ የወልቃይት አማራ ተወላጆችን በማፈናቀልና ለም መሬታቸውን በመንጠቅ በሰፋፊ የእርሻ

ልማት በመሰማራት በርካታ የትህነግ ባለሥልጣናትና ባለሟሎቻቸው የለየላቸው ከበርቴዎች ሁነዋል፡፡ በአንጻሩ

ደግሞ ተወላጁ ወልቃይቴ አማራ የበይ ተመልካች ሁኖ ሦስት አስርታትን አስቆጥሯል፡፡ በእነዚህ ዘመናት ሲከፋም

ዘሩ እንዲጠፋ በጅምላ ተገድሏል፤ ታስሯል፣ ሀገር ለቆ እንዲሰደድ፣ ወደ መሀል ጎንደርና ሌሎች አካባቢዎች በግፍና

በገፍ እንዲፈናቀል ተደርጓል፡፡ ትህነጋዊያን የእነሱን ጥቅም ለማስጠበቅ ያስችለናል ያሉትን በአስር ሺዎች

የሚቆጠሩ የቀድሞ ታጋዮቻቸውን በማስታጠቅ እንዲሁም የሰብል ምርት እጥረት ካለበት ድንጋያማ የትግራይ

አካባቢዎች ያልታጠቁ ሲቪሊያንን በአንድ ላይ በማዋሃድ ከመሀል ትግራይ አምጥተው ወልቃይት ላይ አስፍረዋል፡፡

ይህ የሆነው ግን ተወላጁን አማራ ከኖረበት ቀየው በማፈናቀል ነው፡፡ በዚህ ሂደትም በርካታ የወልቃይት አማራዎች

ዘራቸው ሲጠፋ፤ በአንጻሩ በርካታ የትህነግ ባለስልጣናትና የነሱ ጥቅም አስጠባቂዎች በልጽገዋል፡፡ ራሳቸውንም

ወደገዥ መደብነት ለመቀየር ወልቃይት የሀብት ኮረቻ፣ የብልጽግና ማማ ሁናቸዋለች፡፡ በዚህም ምክንያት

ትህነጋዊያንና ጥቅመኛ ማህበራዊ መሰረቱ ወልቃይትን ማጣት የሞት ያክል ከብዷቸዋል፡፡ (በክፍል ሁለት ጽሁፍ

የአለማቀፉ ማህበረሰብ ጩኸት የወልቃይት ጉዳይና የውጭ ኃይሎችን ሴራ እንዲሁም ከአሁናዊ ፖለቲካችን

አንጻር ወልቃይት ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ያለውን ፋይዳ እንመለከታለን) የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

ባህር ዳር ሐምሌ 1 /2013 ዓ.ም

You might also like