You are on page 1of 1

ማርኛ ውክፔድያን አሁኑኑ ማዘጋጀት ትችላላችሁ - ተሳተፉበት!

ቢግ ማክ
Jump to navigationJump to search

ቢግ ማክ የሃምበርገር ዓይነት ሲሆን በፈጣን ምግብ ቤቱ ማክዶናልድስ የሚሸጥ ነው። ሃምበርገሩ


ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠረው በ 1960 ዓ.ም. በአሜሪካዊው ጅም ዴልጋቲ ነበር። ሁለት የተፈጨ
የበሬ ስጋ ክቦችን፣ ሰላጣ ቅጠል፣ ዓይብ፣ ሽንኩርት፣ ፒክልስ እና ሶስት የሰሊጥ ጠፍጣፋ ዳቦዎችን
ከማዋዣ የቢግ ማክ ሶስ (መረቅ) ጋር ይይዛል።
ቢግ ማክ በአሁኑ ዘመን በአለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተወዳጅነት በማግኘቱ ዘ ኢኮኖሚስት
የተሰኘው የሥነ ንዋይ ጋዜጣ በያመቱ ቢግ ማክ ኤንዴክስ የተባለ መረጃ ያትማል። ቢግ ማክ በያገሩ
የሚሸጥበትን ዋጋ በማዎዳደር፣ የየአገሩን የኑሮ ውድነት ለማነጻጻር ይጠቀምበታል።

You might also like