You are on page 1of 1

ለኢትዮጲያ የክፍያ መንገዶች ኢንትርፕራይዝ

አዲስ አበባ

ጉዳዩ ፦

ድርጅታችሁ በጨረታ ቁጥር 27/2013 ባወጣው ግልጽ ጨረታ የነዳጅ ታንከር ግንባታ ግዢ ላይ
መወዳደራችን ይታወቃል ። ሆኖም በቀን 10/09/2013 ዓም በቁጥር የኢ/ክ/መ/ኢ/4.1/1617/13 በተጻፈ
ደብዳቤ ጨረታውን ያሸነፍን መሆኑን ገልጻችሁ (10% ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና ይዘን በመቅረብ)
ውለታውን እንድንፈራረም የጠየቃችሁ መሆኑ ይታወቃል ። ሆኖም ግን ከዚህ ቀደሞ በነበረን የስልክ ልውውጥ
ኮንትራቱን ካልፈረምን እና ካልተዘጋጀ የተጠየቀውን 10% ሲፒኦ ለማዘጋጀት የማንችል መሆኑን የገለጽን
ቢሆንም እስካሁን መልስ ሊሰጠን አልቻለም ። ስለሆነም በአፋጣኝ ውለታው ተዘጋጅቶ እንድንፈራረም
እንዲደረግለን እና የጠየቅነውንም ሲፒኦ አዘጋጅተን እንድናቀርብ እንጠይቃለን።

ከሰላምታ ጋር

You might also like