You are on page 1of 1

Special Issue on TExA

በቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ (ቴ.ል.አ) የሚደረጉ የስልጠና ጥሪዎችና ተያያዥ


ጉዳዮችን አስመልክቶ የተደረገ የአሰራር ማሻሻያን ስለማሳወቅ
ኢትዮ ቴሌኮም ለሰው ኃይል ልማት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚን (ቴ.ል.አ.) በማቋቋም፣ ለአካዳሚውም
ተገቢውን የሰው-ኃይል በመምረጥ፣ በመመደብና በፅንሰ-ሃሳብም ሆነ በተግባር በማብቃት እንዲሁም በተቋሙ ውስጥ ባሉ በሌሎች
የሥልጠናና ልማት ክፍሎች በመታገዝ የኢትዮ ቴሌኮም ማህበረሰብ በእውቀቱ፣ በክህሎቱና በአመለካከቱ የጎለበተ እንዲሆን በማድረግ
የተቋሙን ተልዕኮ በባለቤትነት ለማሳካትና ለሀገራችን ሁለንተናዊ ዕድገት የበከሉን ሚና ለመጫወት እንዲችል የሚያግዙ የአቅም
ግንባታ ስራዎች እንዲሰሩ ተገቢውን ኢንቨስትመንት በማድረግ ዓይነተኛ አስተዋፅዖ በማድረግ ላይ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በዚሁም መሰረት ቴ.ል.አ በአሁኑ ጊዜ ስልጠናዎችን በስፋት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ሆኖም የሰልጣኞች በስልጠና ላይ
ያለመገኘትና ስልጠናን አቋርጦ የመውጣት ችግር አካዳሚው በሚያደርገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ሲያሳድር ቆይቷል፡፡
ይህንንም ችግር ለማቃለል ቴ.ል.አ ሰልጣኞችን በስልክ በመጋበዝና በስልጠናው ላይ እንደሚገኙ ማረጋገጫ ለሰጡ ሰራተኞች
በኢ-ሜይል የስልጠና ተሳትፎ ግብዣ ሲልክ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ይህ አሰራር በቴልአ ሰራተኞች ላይ ከፍተኛ ጫና ከማሳደሩም በላይ
ውጤታማነቱም እንደሚጠበቀው ሳይሆን ቀርቷል፡፡ በመሆኑም ቴ.ል.አ በዚህ አሰራር ላይ ማሻሻያ በማድረግ ለስልጠና ውጤታማነት
ሁሉም የበኩሉን ሚና በላቀ ሁኔታ ሊወጣ የሚችልበትን የአሰራር ስርአትና የሃላፊነት ድርሻ እንደሚከተለው አስቀምጧል፡፡

ሰልጣኞች የሰልጣኝ የቅርብ የስራ ኃላፊዎች የሥልጠና አገልግሎት ሰጪ- ቴ.ል.አ.


ቅድመ-ስልጠናን በሚመለከት

•ሰልጣኞች በቴ.ል.አ. በኩል ለስልጠና


የሚጠሩት በአንድ ኢ-ሜይል ብቻ መሆኑን
በመገንዘብ ኢ-ሜይልን መከታተል፣ መረጃውን •በሚወጣው የስልጠና መርሃ-ግብር ላይ •የሰልጣኞችን ወርሀዊ የስልጠና መርሃ-ግብር
መያዝ እንዲሁም ኢ-ሜይል (Inbox) ተገቢውን ግብረመልስና የሰልጣኞች ምደባ ለስራ ክፍሉ በመላክ በስራ ክፍሉ የተረጋገጠ
እንዳይሞላ በመከታተል የራስ ኅላፊነትን መወጣት፣ ማከናወን የሰልጣኞች ዝርዝር ማዘጋጀት
•በOutlook ላይ ትክክለኛውን የስልክ አድራሻ •ሰልጠኞች በተዘጋጀው መርሃ-ግብር መሰረት •በተዘጋጀው መርሃ-ግብር መሰረት ሰልጣኞችን
ማስመዝገብ እና የተመዘገበውን ስልክ መጠቀም ስልጠናው ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ በኢ-ሜይል መጋበዝ
•በተዘጋጀውመርሃ-ግብር መሰረት በስልጠናው •ሰልጣኞች በግል ጉዳይ ወይንም በአስቸኳይ ስራ
ላይ መገኘት ምክንያት በስልጠናው ላይ መገኘት የማይችሉ
ከሆነ የሰልጣኞቹ የቅርብ አለቆች ስልጠናውን
•ሰልጣኞች የስልጠና ግብዣ እንደደረሳቸው ያልወሰደና ሊካፈል የሚገባው ምትክ ሰልጣኝ
ወዲያውኑ ለቅርብ አለቆቻቸው ማሳወቅ በመለየት ለቴ.ል.አ በኢ-ሜይል ወይም በስልክ
ወዲያውኑ ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡
•ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በስልጠናው
ላይ መካፈል የማይችሉ ከሆነ፣ ምክንያታቸውን
በበቂ ማስረጃ አስደግፈው ጥሪው በደረሰ
በ2 ቀናት ውስጥ ለቅርብ አለቆቻቸውና
ለጋባዡ የስራ ክፍል ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ማስታወሻ፣

ከስራ ባህሪያቸው አንጻር ከቢሮ ውጭ እንቅስቃሴና


የመስክ ሥራ ለሚበዛባቸው ሠራተኞች ከኢ-
ሜይል በተጨማሪ አጭር የፅሁፍ መልእክት
በስልክ አድራሻቸው እንዲደርሳቸው ይደረጋል፡፡

የስልጠና ሂደትን በሚመለከት

• ለስልጠና የተመደበውን ሙሉ ጊዜ • ሠራተኞች ስልጠናውን በሚካፈሉበት • ፋሲሊቴተሮች (አሰልጣኞች) ተገቢውን


በአግባቡ መጠቀም፣ ስልጠናውን በሙሉ ጊዜ በተቻለ መጠን ለሰራተኞች ስልጠናውን አቴንዳንስ በትክክለኛው ቀንና ሰዓት በመያዝ
ትኩረት መካፈል እንዲሁም ንቁ ተሳትፎ የሚያስተጓጉሉ ኃላፊነቶችን አለመስጠት የቀሪዎቹን ዝርዝር በወቅቱ ለስልጠና
በማድረግ እውቀትና ልምድን ለሌሎች ማካፈል ማስተባበሪያ ክፍል ማሳወቅ
ድህረ-ስልጠናን በሚመለከት
የስልጠና ሂደትን በሚመለከት
ድህረ-ስልጠናን በሚመለከት

•ሰልጣኞች ከሰለጠኑ በኋላ ያገኙትን እውቀትና • ሰልጣኞች ከስልጠናው አለበቂ ምክንያት • የሥልጠና ማስተባበሪያ ክፍሉም ከስልጠና
ልምድ ተግባራዊ በማድረግ፣ የተማሩትን ለሌሎች ከቀሩ ወይም ካቋረጡ የሰልጣኞች የቅርብ የቀሩ ወይንም ያቋረጡ ሰራተኞችን ዝርዝር
በማካፈል እንዲሁም ራሳቸውን በቀጣይነት አለቆች ከቴ.ል.አ. ሥልጠና ማስተባበሪያ በመያዝ በቀጣይ ለሚወሰዱ እርምጃዎች ዝግጁ
በማብቃት (ባዘጋጁት ቀጣይ የራስ ማብቂያ ክፍል በሚደርሳቸው ሪፖርት መሰረት በስራ ማድረግ እና ለስራ ክፍሉ በወቅቱ ማሳወቅ
መርሃ-ግብር እና ከዚህም ባለፈ) ለግልና ለጋራ ምዘና ውጤትም ሆነ ሌሎች ወደፊት በሚወጡ
ልማት መስራት እንዲሁም አስተዳደራዊ መመሪያዎች መሰረት ተገቢውን • የስልጠና ውጤታማነትንና ተግባራዊነትን
ዕርምጃ መውሰድና ማሳወቅ እንዲሁም ለመለካት የሚያስችል መጠይቅ አዘጋጅቶ
•የስልጠናውን ውጤታማነትና ተግባራዊነት ለሰልጣኞችና ለሰልጣኞች የቅርብ አለቆች
ለመለካት ለሚላኩ መጠይቆች ወቅታዊና ተገቢ • ሰልጣኞች ከሰለጠኑ በኋላ የተማሩትን በመላክ ዳሰሳ ማከናወን፣ የዳሰሳውን ውጤት
ምላሽ መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተግባር እንዲያውሉ፣ ለሌሎች እንዲያካፍሉና ማሳወቅ እንዲሁም የማሻሻያ ስራዎችን ማከናወን
በቀጣይነት፣ ራሳቸውን እንዲያበቁ ሁኔታዎችን ይጠበቅበታል፡፡
ማመቻቸት ይጠበቅባቸዋል፡፡

በስልጠናና ልማት ስራ ዙሪያ ያሉ አሰራሮችን ስለማሳወቅ

• በቴልአ ‘የለርኒንግ እና ዴቨሎፕመንት ፖሊሲ ፕሮሲጀር’ መሰረት አንድ ሰልጣኝ ቢያንስ የስልጠናውን ጊዜ ዘጠና በመቶ (90%) በስልጠናው ላይ
ካልተገኘ ስልጠናውን እንዳልተካፈለ ተቆጥሮ የወሰደው ስልጠና በግል ማህደሩ ውስጥ እንዳይመዘገብ ይደረጋል፡፡

• አንድ ሰልጣኝ ከስልጠና ያለፈቃድ የሚቀር ወይንም አቋርጦ የሚወጣ ከሆነ ከስልጠና በመቅረቱ ከስራ እንደቀረና የስነ-ምግባር ጉድለት እንደፈፀመ
ተቆጥሮ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ይደረጋል::

ቴ.ል.አ ሁሉም የኢትዮ ቴሌኮም ሠራተኞች ተቋሙን ስኬታማ ለማድረግ ፅኑ ፍላጎትና ተነሳሽነት እንዳላቸው ያምናል፡፡ በመሆኑም
ሁሉም ሰራተኞች በተጠሩበት ስልጠና ላይ መገኘታቸውና ስልጠናውን መተግበራቸው ለራሳቸውና ለተቋሙ የሚያስገኘውን ከዚህ በታች
የተዘረዘሩትን ጥቅሞች ከግንዛቤ በማስገባት የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ ያቀርባል፡፡

• ሠራተኞች ከሥልጠናው የሚገኘውን እውቀትና ልምድ መቅሰማቸው ለውስጥም ሆነ ለውጭ ደንበኞች ብልጫ ያለው አገልግሎት
እንዲሰጡ በማገዝ የደንበኞችን እርካታ የላቀ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
• በአሰራር ጉድለት ምክንያት የሚመጡ ብክነቶችን በመቀነስና ውጤታማነትን በማሻሻል የተቋሙ ገቢ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
• የሠራተኞችን የግል ምርታማነት በመጨመር ሠራተኞች በስራቸው እንዲደሰቱና የተሻለ የስራ ውጤት እንዲያገኙ ያግዛል፡፡
• በስልጠና የተያዘው እቅድ በአግባቡ እንዲከናወን በማገዝ፣ ቴ.ል.አ የተቀረፁ ፕሮራሞችን በፍጥነት የሚሰጥበትንና አዳዲስ የስልጠና
ፕሮግራሞችን የሚያመርትበትን ፍጥነት እንዲጨምር ያግዛል፡፡
• ለስልጠና የተመደበው የሰው ሃይል፣ ጊዜ እና ጉልበት፤ የስልጠና ክፍል/ላቦራቶሪ እንዲሁም መሳሪያና ቁሳቁሶች እንዳይባክኑ
ያደርጋል፡፡

ስለሆነም ከጥር 6 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም ሰልጣኝ (ሠራተኛ፣ የሥራ ኃላፊ) የስልጠና ጥሪ የሚደርሰው በኢ-ሜይል
አማካኝነት ብቻ እንደሆነ ተገንዝቦ የበኩሉን ሃላፊነት በመወጣት የተለመደውን አጋርነቱን እንዲያሳይ በትህትና እንጠይቃለን፡፡

“ራስን ማብቃትና ተወዳዳሪ ማድረግ በዋነኛነት የራስ ኃላፊነት ነው!!!”

የቴሌኮም ልህቀት አካዳሚ


ጥር 2011 ዓ.ም

Published by: Internal Communications Section

You might also like