Professional Documents
Culture Documents
Bruh Application For Universities
Bruh Application For Universities
ብሩህ የአዳዲስ ንግድ ስራ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር የሃገሪቷን ቁልፍ ችግሮችን ለመፈታት አዳዲስ ሃሳቦችን የሚያፈልቁና ስራ የሚፈጥሩ
ወጣቶችን ለማበረታታት የተዘጋጀ ዓመታዊ የውድድር ፕሮግራም ነው። ይህ ውድድር አመርቂ የንግድ ሃሳብ ይዘው ለመጡ ወጣቶች
የስልጠና፣ የመነሻ ገንዘብና የንግድ ማብቂያ ድጋፍ በመስጠት አትራፊ፣ ለወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥሩ እንዲሁም ለሌሎች ተምሳሌት
የሚሆኑ ወጣቶችን መፍጠር ዋና አላማው ነው።
ይህ ውድድር ጀማሪ ንግዶቸንና የንግድ ሃሳቦችን በቀጥታ የንግድ ልማት ድጋፍ ከሃሳብ ማጎልበት እስከ ማቋቋም ድረስ ይሰጣል።የፉክክር
ተፅእኖን ማሳደግ የሚተገበሩ እና ወደ ገበያው ውስጥ ዘልቀው ሊገቡ የሚችሉ እንዲሁም በትንሽ ጊዜ ውስጥ ገቢን የሚያስገኙ ድርጅቶችን
ይፈጥራል፡፡
ይህ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚያድግ ጅምር የንግድ ሥራ መነሻ መሠረት ይሆናል። ውድድሩ ተደማጭነቱን እና ዘላቂነቱን ለማሳደግ
ከበርካታ ባለድርሻ አካላት ጋር በመጣመር ጠንካራ ፕሮግራም የመሆን አቅም አለው። ተጠያቂነት ያለው አተገባበርን በዋነኝነት በመያዝ
እና በግልጽ የሚታዩ ወሳኝ የዘርፍ ጉዳዮችን መፍታትን ዋና ዓላማው አድርጎ ይሠራል።
• ሴቶች ፣ አካል ጉዳተኛ ወጣቶች ፣ በሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ እና ቤት የለሽ ወጣቶች እንዲያመለክቱ በጣም ይበረታታሉ
የማመልከቻ ጊዜ ከመስከረም 5 እስከ ጥቅምት 5፣ 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ ነው።
የቡድን መረጃ
1. የንግድ ሃሳቡ መስራቾች መረጃ (ሙሉ ስም፣ ዜግነት፣ እድሜ)
3. የፋይናንስ እቅድ
መልካም ዕድል!