You are on page 1of 1

አብሮ በተያያዘው የአቴንዳንስ ዝርዝር መሰረት ሰራተኞች የቀሩበትን ምክንያት አብራርተው

እንዲገልፁ/እንዲያስረዱ የጠየቅን ሲሆን በዚህም መሰረት ምላሻቸውን ገምግመን እንደሚከተለው አስቀምጠናል።

አቶ ገዛኸኝ ወንዳቸው ፡- ብዙ ጊዜ ጠዋት ቀድመው የሚገቡና ማታም አምሽተው የሚወጡ ሲሆን አልፎ
አልፎ አሻራ መስጠትን መርሳት በተጨማሪም ተደጋጋሚ የሆነ የመብራት መጠፋት ተደማምሮ የአቴንዳንስ ክፍተት
የመጣ ሲሆን ሰራተኛው ግን ያለ ፈቃድ ከስራቸው የማይቀሩና አሁንም በስራ ገበታቸው ላይ ተግተው እየሰሩ ያሉ
መሆኑን እገልጻለኁ።
አስማማው መርሻ፡
ብዙ ጊዜ ጠዋት ሲገቡ የአሻራ ማሽን የሚስቸግራቸው እንደሆነና ለተከታታይ ቀናት መብራት በመጠፋቱ
መስጠት ያልቻሉ ቢሆንም ከስራገበታቸው ያለፈቃድ የማይቀሩ መሆኑን መሆኑን እገልጻለኁ።
ዘላለም ካሳሁን፡

ቀሪ ከተባሉባቸው ቀናት ውስጥ 15 ቀን ፈቃድ የነበራቸው ሲሆን በኮሮና ህመም ምክንያት ለአለቃቸው
ነግረው ቀርተዋል። አልፎ አልፎ አሻራ መስጠት የሚረሱ ሲሆን ከስራቸው ባህሪ አንፃር የሚያጋጥም ቢሆንም ከዚህ በኇላ
እንዲያስተካክሉ የተነገሩ ሲሆን ባላቸው የስራ እንቅስቃሰሴ ከስራቸው የማይቀሩና አሁንም በስራ ገበታቸው ላይ
ተግተው እየሰሩ ያሉ መሆኑን እገልጻለኁ።
ብርሀኑ አድኖ፡
ብዙ ጊዜ በስራ ገበታቸው የሚገቡ ነገር ግን አሻራ መስጠት የሚረሱ መሆኑን የገመገምን ሲሆን ለዚህም
ቸልተኝነታቸውንእንዲያስተካክሉጠንከር ያለማሳሰቢያየሰጠናቸውሲሆንከቢሮ ግን ቀርተውእንደማያውቁናአሁንም በስራ
ገበታቸው ላይ ተግተው እየሰሩ ያሉ መሆኑን እገልጻለኁ።
ሰለሞን ወ/ሚካኤል፡
የገጠማቸውን ምክንያት ለአለቃ ሳያሳውቁ በተደጋጋሚ እየቀሩ ተደጋጋሚ ማሳሳቢያዎችን የሰጠን ሲሁን
አሁን በመጣባቸው ቀሪም በራሳቸው ከአመት ፈቃዴ ይቀነስ ያሉ ሲሆን ያላቸው የአመት ፈቃድ ተሰልቶ
እንዲቀነስና በቀጣይ እንዲሁ የሚቀጠሉ ከሆነ ዲቪዥኑ አስተዳደረዊ ርምጃ እንዲወስድ ተወስኗል።
ተክለወይኒ ገ/ሂዎት፡

የአሻራ ማሽን እያስቸገራቸው ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቄ መፍትሄ አላገኘሁም የሚለውን


ገምግመን ምን ያህል ርቀት እንደተጓዙ መገንዘብ ስላልቻልን በቀጣይ ተከታትለው የደረሱበትን እንዲያሳውቁን
የወሰንን ሲሆን የህን ሳያደርጉ ቢቀሩ ዲቪዥኑ አስተዳደረው ርምጃ እንዲወስድ ገምግመናል።

You might also like