You are on page 1of 1

ቀን

ቁጥር
ለወላይታ ዞን አስተዳደር
ጉዳዩ፡ የትብብር ደብዳቤ እንዲፃፍ ስለመጠየቅ ይሆናል

ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው ወጣት ቴዎፍሎስ ተስፋዬ የቀበሊያችን ነዋሪ ሲሆን በ 2010 ዓ/ም ከ
አምቦ ዩንቨርሲቲ በ ሜካኒካል ምህንድስና ተመርቆ በ አዲስ አበባ ዙሪያ በቡራዩ ከተማ በ ፋንሲወር ፐላሰቲክ
ፋብሪካ ቴክኒካል ኢንጂነር ሆኖ ቢቀጠርም በጊዜው በአካባቢው ከነበረው ሁኔታ የተነሳ ብዙም ሳይቆይ ከስራው
ተፈናቀለ፡፡ ወጣት ቴዎፍሎስ ተስፋዬ የተለያዩ ስራዎችን በራሱ ፈጥሮም መንግስት ባዘጋጀው እድሎችም
ለመጠቀም ብዙ የጣረ ቢሆንም እንዳለመታደል ሆኖ እስካሁን ባረጋቸው ጥረቶች ምንም አይነት ገቢ ሳይኖረው
ቆይቷል፡፡

አሁን ግነ አቲዮ ቴሌኮም ያዘጋጀውን ዕድል በመጠቀም የሞባይል አየር ሰዓት (ካርድ) ለሚያስፈልጋቸው መስርያ
ቤቶች እና ድርጅቶች አየር ሰዓት በሚፈልጉት መልኩ ለማከፋፈል ፈቃድ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ ስለሆነ
የዞናችን አስተዳደር የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሊሆኑ ለሚችሉ መ/ቤቶች እ ድርጅቶች የድጋፍ ደብዳቤ ለዚህ
ወጣት በመጻፍ እንዲተባበር በትህትና እጠይቃለን፡፡

ከሠላምታ ጋር!

You might also like