You are on page 1of 5

ሴቶችና ህጻናት ወጣቶች ጉዳይ ስርአተ-ጾታ ስራ ሂደት አስተባባሪ

እኔ ስርዓተ ጾታን ልገልጽ የምችለው ሴቶች በማህበራዊ ግንኙነት ውስጥ ከወንዶች ጋር ያላችውን እኩል ሚና የሚገልጽ
term ነው ብዬ ነው።

በማህበረሰቡ ውስጥ ሴቶች ከወንዶች እኩል የሚያሳዩትን ተሳትፎ የጾታ እኩልነት ብዬ እገልጸዋለሁ።

የስርአተ-ፆታ ፖሊሲ ማለት ሴቶች በፖሊሲው አማካኝነት ከወንዶች ጋር እኩል በሆነ ማህበራዊ ግንኙነት ውስጥ
ተካተው እኩል የሚሰሩትን ስራ የሚያመለክት ሲሆን ብሄራዊ የሴቶች ፖሊሲ ደግሞ የሴቶች የነቃ ተሳትፎ ላይ ወሳኝ
በመሆን፣ የተሳትፎውን መድረክ እራሳቸው በማመቻቸት፣ በማንኛውም መድረኮች ላይ በብቃት እንዲሳትፉ
እራሳችውን በማስቻል፣ ሴቶች እራሳቸውን በብቃት የሚደራጁበትን ሁኔታ በመፍጠር፣ ችግሮችን ለመፍታት ሴቶች
ዋነኛ ኃይሎች መሆናቸውን በማስገንዘብ ላይ ትኩረቱን የሚያደርግ ፖሊሲ ነው።

የ ስርአተ-ፆታን ፖሊሲ ፣ ምክኒያቱም ሴቶች ያለ ወንዶች ወንዶች ያለ ሴቶች መስራት ስለማይችሉ።

አንደኛ ሴቶችን ከወንዶች ጋር እኩል ተሳተፉ ሲባል እኩል የመሳተፍ ሚና ሊኖራቸው ይገባል፣ ሴቶች እራሳቸውን
ማብቃት መቻል አልባቸው፣ ወንዶች በተሳትፎው ውስጥ ሴቶችን የማሳተፍ ፍላጎት ሊኖራቸው ይገባል። ሴቶችም
ያለባቸውን የበታችነት ስሜት ፈጽመው መቅርፍ አለባቸው። በዚህ ላይ ሰፊ ስራ መሰራት አለበት።

የማህበረሰባችን ሴቶች በቀዳሚነት የኢኮኖሚያዊ ተሳትፏቸው ላይ በተለይ በገበያው ስርዓት ላይ የከፋ ችግር
እንደሚገጥማቸው በስፋት ይስተዋላል።

ሴቶች ማህበራዊ ጉዳይ ላይ ያላቸው ተሳትፎ በወንዶች ፍቃድ እና የበላይነት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ለከፋ ችግር
ዳርጓቸዋል።

ሌላው ቤት ውስጥ የማህበረሰባችን ሴቶች ለውሳኔ ሰጪነት ከመብቃት አንፃር ከባሎቻቸው የሚደርስባቸው ተፅዕኖ እና
አምባገነንነት የከፋ ነው።

ሴቶች በማህበረሰቡ ውስጥ የተለያዩ ተሳትፎዎችን የማድረግ የራስ ተነሳሽነት አይታይባቸውም። ከሰባ በመቶ በላይ ያሉ
ባከባቢያችን የሚኖሩ ሴቶች በባሎቻቸው ላይ ጥገኞች በመሆናቸውና ከባሎቻቸው በተደጋጋሚ ከሚደርስባቸው
rejection የተነሳ በህብረተሰቡ ውስጥ ያላችው የአመራርነት ሚና አናሳ ነው። ሕብረተሰቡም ለሴት ልጅ የሚሰጠው
እጅግ ያነሰ ትኩረት በሴቶች የአመራርነት ሚና ላይ አሉታዊ ተጽእኖ አሳድሯል።

በመጀመሪያ ደረጃ ቀድሞ የነበረው እና ስራ ላይ ያልዋለው ብሄራዊ የሴቶች ፖሊሲ ተቀይሮ ተግባር ላይ ሊውል የሚችል
አዲስ ፖሊሲ መቀረፅ አለበት። ሌላው ባሎችም ሆኑ ሌሎች በህብረተሰቡ ውስጥ ተሳትፎ የሚያደርጉ ወንዶች
እንዲሁም ሕብረተሰቡ ለሴቶች ተገቢውን ትኩረት ሊሰጡ ይገባል። In my opinion, these are the best
ways/methods to increase women’s involvement in leadership.
የለም።

የሴቶች የንብረት ባለቤትነትና ተጠቃሚነት ካለፉት አስርት አመታት በፊት ከነበረበት ሁኔታ አንጻር መሻሻል አሳይቷል።
ይህ ማለት ግን ሴት ሃብት እና ንብረት ባለቤትነታቸው እና ተጠቃሚነታቸው መሉ በሙሉ ተረጋግጧል ማለት
አይደለም። በንብረት ተጠቃሚነት ረገድ አሁን ድረስ አንጻራዊ የሆነ ችግር ይታያል።

ጥቃቅን እና አነስተኛ ማህበር ንግድ የቤተ ውበት ግብርና

አልተለወጠም።

ምክንያቱም የተሰራውን ስራ የሚከታተል እና የሚገመግም አካል ባለመኖሩ በሴቶች ላይ የሚደርስ የስራ ጫና ምንም
ለውጥ ሳይታይ ቀርቷል።

በአከባቢያችን ያሉ አብዛኛዎቹ ሴቶች የስራ ጫና አልቀነሰላቸውም።

ምክንያቱም የአከባቢያችን ያሉ አብዛኞቹ ሴቶች ቤት ውስጥ በባሎቻቸው፤ እንዲሁም በማህበረሰቡ ውስጥ ደግሞ
የሴት ልጅን ሰብዓዊ ፍጥረትን በሚያንጣጥሉ አካላት ተፅዕኖ ስለሚደርስባቸው ነው። እና በቤት ውስጥ ስራዎች

ትንሽ ለውጥ አለ።

የሰዎች በስምምነት መጋባት እየጎላ መቷል።



በገጠሩ የወረዳው አከባቢዎች በወሊድ ወቅት የሚሞቱ እናቶችን ቁጥር ለመቀነስ የጤና ጣቢያዎች እና የጤና ኬላዎች
መስፋፋት አስፈላጊ ነው። እናቶች በምጥ emergency ወቅት በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም እንዲደርሱ በቂ የሆነ
የአምቡላንስ አቅርቦት በእያንዳንዱ ጤና ጣቢያ መኖር አለበት።

በከተማው የወረዳው አከባቢዎች ከፍለው ለመማር አቅም ለሌላቸው ለተወሰኑ እናቶችና ሴቶች ልጆች የገንዘብ እና
የተለያዩ የመማሪያ ቁሳቁሶች ድጎማ እየተደረገ ቢሆንም በገጠሩ የወረዳው አከባቢዎች የገንዘብ ድጎማ እጥረት፣
የመብራት አቅርቦት ችግር፣ የወጣት ሴቶች እና እናቶች የደህንነት ስጋት እና ሌሎችም መሻሻል ያለባቸው አሰራሮች
አሉ።

፠፠፠፠፠

ምንም አይነት አስተዋጽዖ አበርክቷል ብዬ አላስብም። ምክንያቱም ከዚህ በፊት የተቀረጸው ይህ ብሔራዊ የሴቶች
ፖሊሲ ተቀርጾ ብቻ በወረቅት ላይ ያለ እና በጅምር ብቻ የቀረ እንደሆነ ስለሚሰማኝ ነው።

ጽህፈት ቤቱ ሴቶችን በልማት ቡድን በማደራጅት እና በመከታተል በተቻለው አቅም ሴቶችን የማብቃት ሥራ እየሰራ
ይገኛል። ነገር ግን የወረዳው ሴክተር መስሪያ ቤቶች እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ለሴቶች ጉዳይ ተገቢውን
ትኩረት እየሰጡ ባለመሆኑ ስራው ላይ የተለያዩ እክሎች ገጥመውናል።

In our area, a non-governmental organization called PAVDA works extensively on በሴቶችን ላይ የሚደርስን
አካላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ ጥቃት መቀነስ ላይ። ሌሎች UNDP, GOAL እና WORLD VISION የተባሉ መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት
በሴቶች ልማት ላይ እና ማጎልበት ላይ ይሰሩ እንደነበር አውቃለሁ።
በሴቶችን ላይ የሚደርስን አካላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ ጥቃት መቀነስ ላይ እና በሴቶች ልማት ላይ እና ማጎልበት ላይ የሚሰሩ
ስራዎች እንዳሉ አስተውያለሁ።


ሴቶች፣ ህጻናት እና ወጣቶች።

በሁሉም የእድሜ ውስጥ ክልል ያሉ ሰዎች።

አዎ

ከ ሚዲያ

እኔ በበኩሌ COVID-19 በህብረተሰቡ ላይ ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት ሲያስከትል አላስተዋልኩም።

ማህበረሰቡ እያደረገ ያለው የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚደረገው እንቅስቃሴ በቂ ባይሆንም መንግስት በሚዲያም
ሆነ በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚሰጣቸውን የጥንቃቄ ማሳሰቢያዎች በመተግበር የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል እና
sanitizer በመጠቀም እራሱን እየጠበቀ ይገኛል።

እስካሁን ድረስ ያደረሰው ወይም የሰማነው የጎንዮሽ ጉዳት የለም።


0( zero stigma) ምክንያቱም በሽታው እዚህ ስላልተከሰተ።

You might also like