You are on page 1of 4

በእኔ አመለካከት ስርዓተ ጾታ ማለት በሴቶች እኩልነት ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራ የስራ ሂደት ነው።

የጾታ እኩልነት ማለት ሴቶች ከዚህ በፊት ከደረሰባቸው እኩይ ከሆኑ ተጽዕኖዎች ተላቀው ከወንዶች እኩል በትምህርት፣
በስራ፣ በአመራርነት እና ህብረተሰቡ ውስጥ በሚደረግ ተሳትፎ እኩል የሆነ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ነው። የጾታ
እኩልነት በህብረተሰቡ ውስጥ በመረጋገጡ ምክንያት አሁን አሁን ሴቶች የተለያዩ በደሎች በሚደርስባቸው ጊዜ የመናገር
ሙሉ መብታ ተከብሮላቸው እኩለታቸውን በማረጋገጥ ላይ ይገኛሉ። ይህ የጾታ እኩልነት መከበር መልካም ገጽታው
ነው።

‘ብሔራዊ የሴቶች ፖሊሲ’ የሚለው ስያሜ ከዚህ በፊት ስንጠቀምበት የነበርነው ፖሊሲ ሲሆን ይህ ነው የሚባል
ተጨባጭ የሆነ ተግባር አልታየበትም። ነገር ግን ‘ብሔራዊ የስርዓተ ጾታ ፖሊሲ’ የሚለው ስያሜ ተግባር ላይ ያተኮረ
የስራ ሂደት ነው።
‘ብሔራዊ የስርዓተ ጾታ ፖሊሲ’

አዲሱ ብሔራዊ የስርዓተ ጾታ ፖሊሲ በዋነኝነት ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ የምፈልገው በሴቶች የሃብት ተጠቃሚነትን
ማረጋገጥ ላይ ነው። ይህም ሴቶች ራሳቸውን ችለው በማህበረሰቡ ውስጥ እኩል እንዲንቀሳቀሱ ያደርጋቸዋል። የሴቶች
ከወንዶች እኩል በትምህርት፣ በስራ፣ በአመራርነት እና ህብረተሰቡ ውስጥ በሚደረግ ተሳትፎ እኩል የሆነ ተጠቃሚነትን
መረጋገጥ አለበት። በዚህ ሴቶችን ራስን የማስቻል የስራ ሂደት ላይ መንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ከበጀት
ድጋፍ ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ በመሉ እንዲያደርጉ እመክራለሁ።

በማህበረሰቡ ውስጥ በንግድም ሆነ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተሰማርተው ራሳቸውን ለመለወጥ ቀን ከሌት ለሚተጉ
ሴቶች የሞራል፣ የበጀት እና ቁሳዊ ድጋፍ ሲደረግ አይስተዋልም።
በአከባቢያችን ለሚኖሩ ሴት ተማሪዎች የመኖሪያ ቦታ፣ የማጥኛ ቦታ እንዲሁም ንጽህናን የመጠበቂያ የተለያዩ ቁሳቁሶች
አቅርቦት አናሳ ነው።
በገጠር ለሚኖሩ እናቶች ለሚያጠቧቸው ህጻናት ልጆቻቸው ቁሳዊ ድጋፍ ሲደረግ አይታይም።

ከላይ በተዘረዘሩት ሁሉም spaces ላይ ሴቶች እኩል የሆነ ታላቅ challenge ያስተናግዳሉ።

እዚህ እኛ ባለንበት አከባቢ የሴቶች የአመራርነት ሚና እምብዛም ነው። ለምሳሌ፣ እዚህ እኛ ባለንበት ወረዳ አጠቃላይ
ከስልሳ አምስት አመራሮች መሃከል አምስቱ ብቻ ሴት አመራሮች ናቸው። ወደ ዘጠና ሁለት በመቶ የሚጠጋው
የአመራር ቦታ የተያዘው በወንዶች ነው። ህብረተሰቡም specifically አብዛኞቹ የአከባቢያችን ወንዶች፣ ከጥንት ሲወርድ
ሲዋረድ ከመጣው እና የሴት ልጅን ሚና እርባናቢስ አድርጎ የሚቆጥረው ባህል እና ትውፊት ተከታዮች በመሆናቸው
ሴቶች መስራት እንደማይችሉ እና ጥቅም እንደሌላቸው ያስባሉ። ይህ የዘቀጠ አስተሳሰብ መቀረፍ አለበት።

ከላይ እንደጠቀስኩት በአከባቢያችን ከሚገኙ ከቀበሌ ሴቶች አንስቶ እስከ ፌዴራል አመራሮች ድረስ ሁሉም ለጉዳዩ ልዩ
ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበት።
አሉ። ከእነዚህም መሃል ሴቶችና ህጽናት ጽህፈት ቤት፣ የሴቶች ሊግ፣ ማህበር ፣ፌዴሬሽን በዋነኝነት የሚጠቀሱ
ናቸው።

በአከበቢያችን የሚገኙ ሴቶች የተለያዩ የውይይት እና የንቅናቄ መድረኮችን በማዘጋጀት እና የሚመለከታቸውን አካላት
በመጋበዝ ለራሳቸው ጉዳይ ባዘጋጇቸው ሰነዶች ላይ በሰፊው ተወያይተው የተሻለን ማህበረሰብ ለመፍጠር የሚያደርጉት
እንቅስቃሴ ይስተዋላል። ይህም የሚደገፍ እና የሚበረታታ ነው።

አዎን፣ የተወሰኑ ለውጦች ተስተውለዋል።

ሴቶች ቀድሞ ይደርስባቸው ከነበረው ጭቆና እና በወንዶች ላይ ጥገኛ ከመሆን ተላቀው ራሳቸውን ችለው፣ ራሳቸውን
በራሳቸው እየመሩ እና የራሳቸውን የንብረትና ሃብት ባላቤትነት እያረጋገጡ ይገኛሉ። ይህ ባለፉት አስር አመታት ውስጥ
ከመጡ ለውጦች ውስጥ የሚጠቀስ ነው።

ግብርና ማለትም ቡናን እና የተለያዩ የአዝዕርት አይነቶችን በማምረት እንዲሁም እንሰት በመፋቅ ይተዳደራሉ።

ምንም የተለወጠ ነገር የለም። እንደውም አሁን አሁን ሴቶች የወንዶችን ስራ ጭምር የሚሰሩበት ሁኔታ ነው በሰፊው
የሚስተዋለው እንጂ ወንዶች የሴቶችን ስራ ሲሰሩ አይስተዋልም።

በአሁን ሰዓት የሴቶች የስራ ጫና ቀድሞ ከነበረበት ለውጥ አሳይቷል ብዬ አላምንም። ምክንያቱም ቅድም እንደነገርኩህ
ሴቶች የወንዶችን ስራ ጭምር የሚሰሩበት ሁኔታ ነው በሰፊው የሚስተዋለው እንጂ ወንዶች የሴቶችን ስራ ሲሰሩ
አይስተዋልም። አሁን ድረስ ይህ ይስራ ጫና የሚበዛው ሴትች ላይ ነው፤ ይህ ደግሞ ቀሞም ይስተዋል የነበረና መቅረት
ያለበት እኩይ ባህል ነው።

ምንም የተለወጠ ነገር የለም ማለት ይቻላል። ምክንያቱም እዚህ እኛ ባለንበት አከባቢ ሴቶች በቀድመ ጋብቻ ጊዜም ሆነ
በድህረ ጋብቻ ወቅት የተለያዩ እኩይ ተግባራት ይፈጸምባቸዋል። ለምሳሌ፦ ሴት ልጅ ገና ከመውለዷ ወይም አራስ ሆና
የባሏን የወሲብ ስሜት ለማርካት በሚል ሰበብ ጊዜውን ያልጠበቀ የግብረስጋ ግንኙነት ለማድረግ በባሏ የምትገደድበት
ሁኔታ አለ። ሌላው ደግሞ በእድሜ የማይመጣጠኑ ጥንዶች ጋብቻ በሰፊው ይታያል። የ 70 እና 80 አመት ሽማግሌ ገና
እድሜዋ ለትዳር ያልደረሰ ለጋ የ 16 አመት ወጣት ልጃገረድ ለጋብቻ ሲያጭ ተመልክተናል። በዚህም ምክንያት ብዙ የክስ
መዝገቦች በሴቶች እና ህጻናት ወጣቶች ጽህፈት ቤትም ሆነ በሴቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ሲከፈቱ አስተውያለሁ።
ያሳዝናል።

በዚህ እኛ ባለንበት አከባቢ ልዩ ትኩረት የሚያስፈልጋቸው እናቶች ናቸው። እናቶች በወሊድ ወቅትም ሆነ ለተለያዩ
ድንገተኛም ሆነ መደበኛ ህመም በሚጋለጡበት ጊዜ ወደ ጤና ተቋማት በፍጥነት ለማድረስ የመንገድ መሰረተ ልማት እና
የአንቡላንስ አቅርቦት በእጅጉ አናሳ ነው። ነፍሰጡር ሴቶች በምጥ ሰዓት ወደጤና ተቋማት በፍጥነት እንዲንቀሳቀሱ
እነዚህ ነገሮች ቢሟሉ መልካም ነው። ሌላው ደግሞ ለእናቶች እና ለህጻናት የምግብ፣ የመድሃኒት እንዲሁም የመጠለያ
አቅርቦት በጣም ያስፈልጋል ብዬ አምናለሁ። በአከባቢያችን በምግብ እና በመጠለያ እጥረት ምክንያት ብዙ ሴቶች እና
ህጻናት ለሞት ሲጋለጡ ይስተዋላል። በገጠር ለሚኖሩ እናቶች እና ለሚያጠቧቸው ህጻናት ልጆቻቸው ቁሳዊ ድጋፍ
ሲደረግ አይታይም።
በትምህርቱም ዘርፍ የመማር ፍላጎት እያላቸው ነገር ግን አቅም ያነሳቸውን ሴቶችና ህጻናት ልዩ ትኩረት የሚሹ
ናቸው። ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል የሚማሩ ህጽናት ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁሶች ግብዓት ያስፈልጋቸዋል።
ለአከባቢው እናቶች እና አዛውንቶች የጎልማሶች ትምህርት እንዲሁም የደህንነት ጥበቃ በእጅጉ ያስፈልጋቸዋል።
ለተማሪዎች በቂ የሆነ የመብራት እና የመማሪያ ቁሳቁሶች አቅርቦት የተሟላ ባለመሆኑ ብዙ ሴቶች እና ህጽናት
ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለዋል። ይህ በፍጥነት መቀረፍ ያለበት አንገብጋቢ ጉዳይ ነው። በአከባቢያችን ለሚኖሩ
ሴት ተማሪዎች የመኖሪያ ቦታ፣ የማጥኛ ቦታ እንዲሁም ንጽህናን የመጠበቂያ የተለያዩ ቁሳቁሶች አቅርቦት አናሳ ነው።
ብሔራዊ የሴቶች ፖሊሲ በገጠር የሚገኙት እናቶችን ጨምሮ በተለያየ የስራ መስክ ላይ የሚገኙ አቅመ ደካማ ሴቶችን
እና ህጻናትን ተደራሽ የሚያደርግ ስለሆነ መሻሻል ያለባቸው ጥቂት ጉዳዮች ቢኖሩም እስካሁን በተኬደው መንገድ ጥሩ
የሚባል ለውጥ አምጥቷል ብዬ አምናለሁ።

በአከባቢያችን ሴቶች፣ ህጽናት እና ወጣቶች ጽህፈት ቤት ሴቶችን ራስን ማስቻል ላይ ትኩረቱን አድርጎ ታላቅ ስራ
ሰርቷል። እስካሁን የተሰራው ስራ አመርቂ ባይሆንም ሴቶች የራሳቸውን ችግር በራሳቸው መንገድ እንዲፈቱና ሴቶች
ራሳቸውን እንዲችሉና እንዲበቁ ከማድረግ አንጻር ታላቅ ጥረትን እያደረገ የሚገኝ ጽህፈት ቤት መሆኑን ማስተዋል
ችያለሁ።

የሉም።

ምንም።

ሴቶች

ከ 15 እስከ 42

ከዚህ በፊት የተሰሩት ሥራዎች መልካም ሆነው ሳለ፣ በባለሙያ ውስንነት ምክንያት ከዚህ በላይ መሰራት እያለባቸው ገና
ያልተሰሩ ብዙ ስራዎች ስላሉ ጽህፈት ቤቱ አቅሙን በማዳበር አመርቂ የሆነ ውጤት እንዲያመጣ አሳስባለሁ።
በተጨማሪም ቅድም ከላይ የዘረዘርናቸው ቁልፍ የሆኑ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚታዩ ሴቶች ላይ የሚደርሱ እንደ Sexual
and reproductive health rights ጥሰት ፣ Gender Based Violence፣ Including the most disadvantaged ወይም
vulnerable women እና Access and control over resources ላይ ቢቻል ሙሉ በሙሉ መቀረፍ ቢችሉ መልካም ነው
እላለሁ።

በአመራርነት ሃላፊነት ላይ ያሉ ሴቶች ቁጥር በጣም አናሳ መሆኑ እንደ አንድ structure that changes or
undermines the way gender equality programming is delivered ብዬ እወስዳለሁ።
ህብረተሰቡ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚያደርገው ጥረት በቂ አይደለም። እንደውም አሁን አሁን ህብረተሰቡ
ፍጹም ወደ መዘናጋት እየገባ ስለሆነ መንግስት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ይረዳሉ ብሎ ያስቀመጣቸውን
አቅጣጫዎች በመተግበር ላይ አይገኝም።

መንግስት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የወሰዳቸው እርምጃዎች የጎንዮሽ ጉዳት በእርግጥ አላቸው። የኢኮኖሚ
ግሽበት እና በተለያዩ እቃዎች ላይ እና አገልግሎቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ንረት ተስተውሏል። ከዚህም የተነሳ
ህብረተሰቡ መንግስት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ይረዳሉ ብሎ ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች በመተግበር ላይ
አይገኝም።

የቫይረሱ outbreak በግል ህይወቴ ላይ ይህ ነው የሚባል considerable የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሮብኛል ብዬ
አላስብም።

COVID-19 ጾታን ለይቶ፤ ከወዶቹ ይልቅ ሴቶቹ ላይ የከፋ ተጽዕኖ ያሳድራል ብዬ አላምንም።
0

ጠቅለል አድርጌ እናንተን ይህን ቃለመጠይቅ ያዘጋጃችሁትን አካላት ከልቤ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። በእውነት
በህብረተሰቡ ውስጥ ለሚገኙ ሴቶች እና ህጻናት ችግር በመገንዘብ እና ለጉዳዩ በመቆርቆር መፍትሄ ለማምጣት
ለምታትሩ ሁሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። አመሰግናለው።

You might also like