You are on page 1of 11

መመሪያ ቁጥር 46/2014 ዓ.

የAማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የህልውና ዘመቻ ዝርዝር ማስፈጸሚያ


መመሪያ

የAማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የክልሉን ሰላምና ጸጥታ የመጠበቅ፣ የህዝብንና የዜጎችን
ደህንነት የማረጋገጥ Eንዲሁም Iንቨስትመንትና የመሠረተ-ልማት Aዉታሮችን ከጥቃት
በመጠበቅ በክልሉ ዉስጥ ሕግና ሥርዓት Eንዲከበር የማድረግ ኃላፊነት ያለበት መሆኑን
በመገንዘብ፤

የትህነግ Aሸባሪና የትግራይ ወራሪ ኃይል በAማራ ክልል ሕዝቦች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት
Eየፈፀመ፣ህዝብን Eየገደለና Eያዋረደ፤ ንብረቱን Eየዘረፈና Eያወደመ ብሎም Iትዮጵያን
ለማፍረስ የመጨረሻ የሞት ሽረት ትግል Eያደረገ በመሆኑ፤

ይህ ወረራ Eንዲገታና የተወረሩ የክልላችን Aካባቢዎች ነጻ Eንዲወጡ Eንዲሁም Aሸባሪዉና


ወራሪዉ ኃይል የIትዮጵያም ሆነ የAማራ ሕዝብ ስጋት ከማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ ክልላዊ
የሕልዉና የክተት ዘመቻ ጥሪ ተደርጎ Eየተተገበረ በመሆኑ፣

ይህንኑ የክተት ዘመቻ ከዳር ለማድረስ መላ የክልላችን ሕዝብ በየደረጃዉ በሚገኙ የክልሉ
Aመራሮች ግንባር ቀደምትነት Eየተመራ የሕልዉና ተጋድሎዉን የላቀ ደረጃ ላይ ለማድረስ
Eንዲቻል የተጠያቂነት Aሰራር መዘርጋት Aስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

ክልሉ በተጨባጭ Eየገጠመዉ ያለውን የሕልውና Aደጋ ለመቀልበስ በመደበኛው የሕግ


ማስከበር ሥርዓት ብቻ ማሸነፍ የማይቻል ሆኖ በመገኘቱ፤

የAማራ ክልል መስተዳደር ምክር ቤት ጥቅምት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው 6ኛ ዙር፣ 1ኛ


ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ Aስቸኳይ ስብሰባ ያስተላለፋቸውን የAስቸኳይ ጊዜ ጥሪ ውሳኔዎች
በወጡበት Aግባብ በሥራ ላይ ለማዋል የሚያስችል ዝርዝር የAፈጻጸም መመሪያ ማዉጣትና
ተግባሩንም በበላይነት የሚመራዉን Aካል ኃላፊነት በግልጽ መደንገግ Aስፈላጊ በመሆኑ፤

የፌዴራል መንግስቱ ከጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ተፈጻሚ


የሚሆን የAስቸኳይ ጊዜ Aዋጅ ያወጣ በመሆኑ የመስተዳድር ምክር ቤቱን የAስቸኳይ
ጥሪ ዉሳኔዎች Aፈጻጸም ከዚሁ Aዋጅ ጋር የሚናበብ Eንዲሆን ማድረግ በማስፈለጉ፣


 
የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በተሻሻለዉ የብሔራዊ ክልሉ ሕገ መንግስት Aንቀጽ
58 ንUስ Aንቀጽ /7/ ስር በተሰጠዉ ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ Aዉጥቷል።

ክፍል Aንድ
ጠቅላላ
1. Aጭር ርEስ
ይህ መመሪያ “የAማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የህልውና ዘመቻ ዝርዝር ማስፈጸሚያ
መመሪያ ቁጥር 46/2014 ዓ.ም” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።

2. ትርጓሜ

የቃሉ Aግባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፦

(1) “ክልል” ማለት የAማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ነው፤


(2) “የዘመቻ መምሪያ” ማለት የAማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የህልውና
ዘመቻ መምሪያ ሆኖ በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት የወጣውን የህልውና
ዘመቻ Aስቸኳይ ጥሪ ለማስፈጸም በዚህ መመሪያ Aንቀጽ /5/ መሰረት
የተቋቋመዉ Aካል ነው፤

(3) "የህልውና ዘማች” ማለት ማንኛውም የመንግሥትም ሆነ የግል የጦር መሣሪያ የያዘ
ወይም በህልውና ዘመቻው ግንባር በመገኘት የሚሳተፍ ሰው ነው፤

(4) “የህልውና ዘመቻ” ማለት በAሸባሪው ትህነግና በትግራይ ወራራ ኃይል


ምክንያት በክልሉ ህዝብና መንግሥት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የሕልዉና
Aደጋ ለመቀልበስ የሚደረግ የክተት ዘመቻ ነው፤
(5) “በደጀንነት የሚገኝ ሕዝብ” ማለት ለሕልውና ዘመቻው የሚያስፈልገውን የሎጂስቲክስ
Aገልግሎት Eና ሌሎች የደጀንነት ተግባራትን በማከናወን የሕልውና ዘመቻውን
ውጤታማ የሚያደርግ ህዝብ ነው፤
(6) “ጸጉረ-ልውጥ” Eና “ሰርጎ-ገብ” ማለት የመረጃና የስለላ ሥራ ለመሥራት በግልጽም ሆነ
በድብቅ ወደ ክልሉ የገባ ሰው Eና/ወይም በክልሉ ውስጥ Eየኖረ የAሸባሪው ትህነግ Eና
የትግራይ ወራሪ ኃይልን ተልEኮ በስለላ፣ በመረጃ ማቀበል፣ውዥንብር በመንዛት፣
በገንዘብ Eና በመሣሪያ Aቅርቦት የሚደግፍ ሰውንም ይጨምራል፤


 
(7) “Aስተዳደራዊ ወይም ሕጋዊ Eርምጃ” ማለት ማንኛውም በዚህ መመሪያ ግዴታ
የተጣለበት Aካል ይህንን መመሪያ በመተላለፍ ለሚያደርሰው ጥፋት የሚወሰንበት
Aስተዳደራዊ ወይም በሕግ የተደነገገ ቅጣት ነው፤
(8) "የመንግስት ተሽከርካሪ" ማለት በክልሉ መንግሥት የሚተዳደር ተሽከርካሪ ሲሆን
EንደAስፈላጊነቱ የመንግስት የልማት ድርጅት ተሸከርካሪን ይጨምራል፤
(9) "የግል ተሽከርካሪ" ማለት በክልሉ የሚገኝ የግል ተሽከርካሪ ነው፤
(10) “የጦር መሣሪያ” ማለት ማንኛውም በክልሉ ውስጥ በግለ-ሰብም ሆነ በመንግሥት ስር
የሚገኝ ጠላትን ለመከላከል ጥቅም ላይ የሚዉል ከወገብ ትጥቅ ዉጭ ያለ ማናቸዉም
የጦር መሳሪያና ተተኳሽ ማለት ነው፤
(11) “Aገልግሎት ሰጪ ተቋም” ማለት በክልሉ መንግሥት በሙሉ ወይም በከፊል
በሚመደብ በጀት የሚመራ በየደረጃው ያለ የመንግሥት ተቋም ነው፤
(12) “ሰው” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው Aካል ነው፤
(13) ማንኛውም በወንድ ጾታ የተገለጸው የሴትንም ጾታ ይጨምራል።

3. የተፈፃሚነት ወሰን
1. ይህ መመሪያ በመላ ክልሉ ውስጥ ተፈጻሚ ይሆናል።
2. የዚህ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ /1/ ድንጋጌ ቢኖርም መመሪያዉ በፌዴራል ተቋማትና የህግ
Aስከባሪ Aካላት፣ በግብረ-ሰናይ Eና የEርዳታ ድርጅቶች Eንዲሁም በኃይማኖት ተቋማት
ንብረቶችና ተሽከርካሪዎች ላይ ተፈፃሚነት Aይኖረውም፡፡

ክፍል ሁለት

ስለመመሪያው ዓላማ፣ መቋቋም፣ ሥልጣንና ተግባር

4. ዓላማ

ይህ መመሪያ ከዚህ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፤

(1) በክልሉ ላይ በትህነግ Aሸባሪ ቡድንና በትግራይ ወራሪ ኃይል


የተሰነዘረውን ወረራ በተቀናጀ ህዝባዊ ኃይል Eንዲቀለበስ፣ የተወረሩ
የክልሉን Aካባቢዎች ነጻ ለማዉጣትና ወራሪዉ ኃይል በAገሪቱና በክልሉ
ዳግም ስጋት Eንዳይሆን Aድርጎ ለመደምሰስ የሚደረገዉን የሕልዉና
ዘመቻ ለማስተባበር፣ ለማቀናጀትና ለመምራት፤


 
(2) በደጀንነት የሚገኘውን ሕዝብ በማስተባበር የሕልውና ዘመቻው ውጤታማ ሆኖ
Eንዲጠናቀቅ የሚያስፈልገውን የሰዉ ኃይል፣ የትጥቅና ስንቅ Eንዲሁም ሌሎች
የሎጂስቲክስ Aገልግሎትን ከደጀኑ ህዝብ Aሰባስቦ ለማቅረብ፤

5. ስለመቋቋም
1. በክልሉ ላይ የተደቀነዉን የሕልዉና Aደጋ ለመቀልበስ በክልሉ መስተዳድር
ምክር ቤት የወጣውን የህልውና ዘመቻ Aስቸኳይ ጥሪ በበላይነት የሚያስፈጽም
የዘመቻ መምሪያ (ከዚህ በኋላ "መምሪያዉ" Eየተባለ የሚጠራ) Aካል በዚህ
መመሪያ ተቋቁሟል፡
2. መምሪያዉ በክልሉ ርEሰ መስተዳድር የሚመራ ሆኖ የክልሉን የጸጥታ Aካላትና
Aግባብነት ያላቸዉን ሌሎች የክልሉንና የፌዴራል መንግሥት ተቋማትን
በAባልነት የሚይዝ ይሆናል፤
3. የዚህ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ /2/ ድንጋጌ Eንደተጠበቀ ሆኖ መምሪያዉ Aግባብነት
ካላቸዉ Aካላት የተዉጣጡ Eና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ኃላፊነት ወስደዉ
የAስቸኳይ ጥሪ ዉሳኔዉንና መመሪያዉን ተፈጻሚ የሚያደርጉ ግብረ ኃይሎችን
ወይም ኮሚቴዎችን ሊያቋቁም ይችላል፡፡
4. መምሪያዉ ለስራዉ ዉጤታማነት ሲባል በክልሉ ዉስጥ በየደረጃዉ በሚገኙ
የAስተዳደር Eርከኖች መዋቅሩን ሊዘረጋ ይችላል፡፡

6. የዘመቻ መምሪያው ሥልጣንና ተግባር


መምሪያዉ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፣
(1) በዚህ መመሪያ Aንቀጽ /9/ ስር Aገልግሎት በሙሉ ወይም በከፊል
ከሚቋረጥባቸዉ ተቋማት ዉጭ ማንኛውም የመንግሥት ተቋም መደበኛ
Aገልግሎቱን Aቋርጦ በጀቱን ጨምሮ ሁሉንም ነገር ክልሉ የገጠመዉን
የህልውና ዘመቻ ለመቀልበስ የሚያስችሉ ሥራዎች ላይ Eንዲውል
ያስተባብራል፣ ይደግፋል፣ ይቆጣጠራል፤
(2) የሃብት Aሰባሰቡ በተቀመጠዉ Aሰራር መሰረት Eየተከናወነ ስለመሆኑና
የተሰባሰበው ሃብትም ለሕልዉና ዘመቻዉ ብቻ በፍትሃዊነት ሥራ ላይ Eየዋለ
ስለመሆኑ Aፈጻጸሙን ይገመግማል፣Aስፈላጊዉን ይወስናል፤
(3) የመንግሥት ተሽከርካሪዎች ወደ Aንድ ማEከል ተሰባስበው ለሕልውና ዘመቻዉ
Aገልግሎት Eየዋሉ ስለመሆናቸው ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤


 
(4) የግል ተሽከርካሪ ባለቤቶች ለሕልውና ዘመቻው ስኬት ሲባል በተፈለገ ጊዜ ሁሉ
ተሽከርካሪያቸውን በማቅረብ ኃላፊነታቸውን Eንዲወጡ ያስተባብራል፣ ይደግፋል፣
ይቆጣጠራል፤
(5) በየደረጃው የሚገኘው Aመራር የሕልውና ዘመቻውን ተቀብሎ የሚሰለፈውን ሕዝብ
Aደራጅቶ ግንባር ቀደም ሆኖ Eየመራ ወደ ግንባር የዘመተ ስለመሆኑ ይከታተላል፣
ይመራል፤
(6) ይህን በማያደርጉ Aመራሮች ላይ ሕጋዊና Aስተዳደራዊ Eርምጃ በመውሰድ
ለመስተዳድር ምክር ቤቱ ያሳውቃል፤
(7) ሁሉም የመንግሥት Eና የግል የጦር መሣሪያ የታጠቀ ሰው የታጠቀውን የጦር
መሣሪያ ከነ ተተኳሹ ተጠቅሞ ወደ ሕልውና ዘመቻ Eንዲገባ ያደርጋል፣ ይከታተላል፣
ይቆጣጠራል፤
(8) በንUስ Aንቀጽ /7/ የተደነገገዉ Eንደተጠበቀ ሆኖ፣ ማንኛውም የግል መሣሪያ የታጠቀ
የክልሉ ነዋሪ በማንኛውም ምክንያት በሕልውና ዘመቻው ላይ የማይሳተፍ ከሆነ
የታጠቀውን የግል መሣሪያ በAደራ ለመንግሥት የማስረከብ ወይም Eድሜው 18
ዓመትና በላይ ለሆነ Eና Aካላዊ ጤንነት ላለው የቤተሰብ Aባሉ ወይም ለሌላ ሰው
በማስተላለፍ ለህልውና ዘመቻው Aገልግሎት ላይ Eንዲውል የማድረግ መብት
ይኖረዋል፤
(9) የዚህን Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ /7/ Eና /8/ ድንጋጌዎችን በሚጥሱ የመንግሥትም ሆነ
የግል የጦር መሳሪያ የታጠቁ ግለ-ሰቦችን ትጥቃቸዉን በማስወረድ ትጥቁን ለህልውና
ዘመቻው Eንዲውል ያደርጋል፤
(10) በዚህ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ /8/ መሠረት የግል የጦር መሣሪያዎቻቸውን
ለመንግሥት በAደራ ለሚያስረክቡ ግለ-ሰቦች የመሣሪያውን ሙሉ መረጃ የያዘ ደረሰኝ
ተዘጋጅቶ Eንዲሰጥ ያደርጋል፤
(11) የመንግሥትና የግል የጦር መሣሪያ ታጥቀው ወደ ህልውና ዘመቻው ለገቡ Aካላት
የተተኳሽ Eና የሎጀስቲክስ Aቅርቦት Eጥረትን Eየገመገመ Eንዲቀርብ ያመቻቻል፤
(12) ማንኛዉም Eድሜዉ፣ ጤንነቱና Aካላዊ ሁኔታዉ የሚፈቅድለት የክልሉ ነዋሪ
በሕልዉና ዘመቻዉ በግንባር በመሰለፍ በተዋጊነት፣ በAዋጊነት፣ በAግላይነት፣
Eንዲሁም ለተዋጊዉ በስንቅና ትጥቅ Aቅራቢነት Eየተሳተፈ ስለመሆኑ
ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣


 
(13) ማንኛውም ለህልውና ዘመቻው Eንቅፋት የሚሆን ወይም የትህነግ Aሸባሪና
የትግራይ ወራሪ ኃይልን የሚደግፍ ወይም በተግባር ሲንቀሳቀስ በተገኘ ግለሰብ
ወይም ቡድን ላይ Aስፈላጊውን Eርምጃ በመውሰድ ወይም Eንዲወሰድ በማድረግ
ለመስተዳድር ምክር ቤቱ ያሳውቃል፤
(14) በደጀንነት የሚገኘው ሕዝብ ለሕልውና ዘመቻው የሚያስፈልገውን የሎጂስቲክስ
Aገልግሎት በማቅረብ የሕልውና ዘመቻው ውጤታማ Eንዲሆን ያስተባብራል፤
(15) የሕልውና ዘመቻውን ተቀብሎ በግንባር ለመፋለም ከሚሰማሩት ውጭ ያለው
ማንኛውም የክልሉ ነዋሪ፦
ሀ) በየAካባቢው ተደራጅቶ የAካባቢውን ጸጥታ Eየጠበቀ ስለመሆኑ፣፣

ለ) ጸጉረ-ልውጦችንና ሰርጎ-ገቦችን ተከታትሎ በAቅራቢያዉ ለሚገኝ ለሕግ Aስከባሪ


Aካላት Aሳልፎ ስለመስጠቱ፣

ሐ) የዘማች ቤተሰቦችን መንከባከብ ጨምሮ ለሕልውና ዘመቻው የበኩሉን ኃላፊነት


ሁሉ Eየተወጣ ስለመሆኑ፣

ይከታተላል፣ይቆጣጠራል፤

(16) ለህልዉና ዘመቻዉ ዉጤታማነት ሲባል ከAቻ ክልሎች ጋር በትብብር ሊሰራ ይችላል፣
(17) ሌሎች በመስተዳድር ምክር ቤቱ የሚሰጡትን ተጨማሪ ተግባራት ያከናውናል።

ክፍል ሶስት
ግዴታዎች Eና የተከለከሉ ተግባራት
7. የተቋማት ግዴታዎች
(1) በክልሉ ውስጥ በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት የተመደበላቸውን
የሥራ ማስኬጃ በጀት ለህልውና ዘመቻው የማዋል ግዴታ Aለባቸው፤
(2) የንUስ Aንቀጽ /1/ ድንጋጌ Eንደተጠበቀ ሆኖ የዘመቻ መምሪያዉ ሲወስን
የካፒታል በጀት ለዘመቻዉ ዓላማ ሊዉል ይችላል፤
(3) ማንኛውም የመንግሥት ተቋም ሠራተኛ በህልውና ዘመቻው ስምሪት ዉስጥ
የሚሰጠውን ግዳጅ የመፈጸም ግዴታ Aለበት፤
(4) ለዚህ ግዳጅ ብቁ ያልሆነ የተቋሙ ሠራተኛ ከህልውና ዘመቻው ጋር በተያያዘ
የሚሰጠውን ተግባር በተለይም


 
ሀ/Eድሜዉ፣ ጤንነቱ፣ Aካላዊ ሁኔታዉና ልምዱ የሚፈቅድለት ሆኖ ሲገኝ
በAዋጊነት Eና በተዋጊነት በመሳተፍ፣

ለ/በስራ ቦታ ላይ በመገኘት Aስፈላጊዉን የስንቅና ሌሎች የሎጂስቲክስ


Aገልግሎቶችን በማሟላት ስራ ላይ Eርብርብር በማድረግ፣

ሐ/ በማህበራዊና ሜንስትሪሚንግ ሚዲያ በመሳተፍ ጠላትን የማጋለጥና መላ


ህዝቡን ለሕልዉና ዘመቻዉ Eንዲነሳሳ ተገቢዉን የቅስቀሳ፣ የፕሮፓጋንዳና
የማደራጀት ተልEኮ በመፈጸም፣

ኃላፊነቱን የመወጣት ግዴታ Aለበት፤

(5) ማንኛዉም በክልሉ የሚገኙ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት በየተቋሙ ስር


ለሚገኙ ሰራተኞች ስለሕልውና ዘመቻው የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም
Aስፈላጊዉን መረጃ የማድረስ ኃላፊነት Aለባቸው፤
(6) በዚህ የህልውና ዘመቻ የሚሳተፍ የመንግሥትም ሆነ የግል ሠራተኛ ወርሐዊ
ደመወዝ Aይቋረጥም።
(7) የዘመቻ መምሪያዉ በክልሉ ዉስጥ የሚገኙ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች
በሕልዉና ዘመቻዉ ስለሚሳተፉበት ዝርዝር ሁኔታ ሊወስን ይችላል፡፡

8. በህልውና ዘመቻው በግንባር ስለሚሳተፉ ሰዎች


(1) በየደረጃው የሚገኘው የክልሉ መንግሥት ሠራተኛ Eና Aመራር፤
(2) በክልሉ የሚገኝ ማንኛውም የክልሉ የጸጥታ Aካል፤
(3) ማንኛውም ለህልውና ዘመቻው ብቁ የሆነ የክልሉ ነዋሪና በየትኛውም Aካባቢ
የሚኖር ፈቃደኛ ግለ-ሰብ።

9. Aገልግሎት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የማይቋረጥባቸዉ ተቋማት


(1) የግብርና Eና የመስኖ ልማት ተቋማት፣
(2) ከመጠጥ ዉሃ Aቅርቦት ጋር ግንኙነት ያለዉ ስራ የሚሰሩ ተቋማት፤
(3) በየደረጃዉ የሚገኙ የገንዘብና Iኮኖሚ ልማት ተቋማት፣
(4) የገቢ ሰብሳቢ ተቋማት፤
(5) የጤና Eና የትምሕርት ተቋማት፤
(6) የጸጥታ ተቋማት፣


 
(7) ዝርዝሩ በየተቋማቱ ኃላፊዎች የሚወሰን ሆኖ፣የAስቸኳይ ጥሪ ዉሳኔዉን Aፈጻጸም
የማያደናቅፉ ተግባራትን በተመለከተ የAቃቤ ሕግ Eና የፍርድ ቤት ተቋማት፣
(8) ከፌዴራል መንግስትም ሆነ ከረጂ ደርጅቶች ፋይናንስ የሚደረጉና በማናቸዉም የክልሉ
መንግስት ተቀቋማት የሚገኙ የፕሮጀክት ሥራዎች/
(9) ከድንገተኛና የEሳት Aደጋ መከላከል ጋር የተያያዙና ሌሎች የከተማ Aገልግሎት
ስራዎች፤
(10) ከፈቃድ Aሰጣጥ፣ ከሕገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር Eና ከትራንስፖርት ስምሪትና
ቁጥጥር ጋር የተያያዙ ስራዎች፣
(11) ፋብሪካዎችና ነዳጅ ማደያዎች፣
(12) በዚህ Aንቀጽ ከንUስ Aንቀጽ /1/ Eስከ /11/ የተጠቀሱት ተቋማትና የሥራ
ክፍሎች Eንደተጠበቁ ሆኖ፣ የክልሉ ዘመቻ መምሪያ በየጊዜዉ Eየለየ የሚያሳዉቃቸዉ
ተቋማትና የስራ ክፍሎች፣
(13) ከዚህ በላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ቢኖሩም በEነኚህ ተቋማት ውስጥ
የሚሠሩ ሠራተኞች በህልውና ዘመቻው Eንዲሳተፉ ስምሪት የሚሰጣቸው ከሆነ
የመሳተፍ ግዴታ Aለባቸው።

10. በህልውና ዘመቻው የመሳተፍ ግዴታ


(1) ማንኛውም የክልሉ ነዋሪ በህልዉና ዘመቻው የመሳተፍ ግዴታ Aለበት፤
(2) ማንኛውም የግል ተሽከርካሪ ያለው ሰው ተሽከርካሪው ለህልውና ዘመቻው
Aገልግሎት ላይ Eንዲውል ሲጠየቅ የመስጠት ግዴታ Aለበት
(3) ማንኛውም የክልሉ ነዋሪ በAካባቢው ያለውን የጸጥታ ሁኔታ በጥብቅ
በመከታተል ኅብረተ-ሰቡን Aደጋ ላይ የሚጥል Eንቅስቃሴ መኖሩን
ሲያጠራጥረዉ Eና በሕልዉና ዘመቻዉ ላይ Eንቅፋት የሚፈጥር ድርጊት
ሲያጋጥም ከሚመለከተው የጸጥታ Aካል ጋር በመሆን Eርምጃ Eንዲወሰድ
የማድረግ ግዴታ Aለበት፤
(4) ለሕልውና ዘመቻው በግንባር ከሚሰለፈው ውጪ ያለ ማንኛውም የክልሉ ነዋሪ
ተደራጅቶ የAካባቢውን ጸጥታ የመጠበቅ ግዴታ Aለበት፤
(5) ማንኛውም የክልሉ ነዋሪ ለህልውና ዘመቻው መሳካት Aቅሙ የፈቀደውን
የሎጀስቲክስ ድጋፍ የማድረግ ግዴታ Aለበት።


 
11. የሆቴሎችና የቤት Aከራዮች ግዴታ
(1) ማንኛውም የሆቴል፣ የመኖሪያም ሆነ የንግድ ድርጅት ቤት Aከራዮች የተከራዩንና
Aብረውት የሚኖሩትን ሰዎች ትክክለኛ ማንነት በጥብቅ የመከታተልና የማወቅ፣
የሚያጠራጥር ሁኔታ ሲያጋጥም በAካባቢው ለሚገኘው የፖሊስ ጽሕፈት ቤት የማሳወቅ
Eና መረጃ Eንዲሰጥ ሲጠየቅም የመስጠት ግዴታ Aለበት፤
(2) የዚህ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ /1/ ላይ የተቀመጠው ግዴታ ሳይፈጸም ቀርቶ በህዝብና
በመንግሥት ላይ ተከራዩ ለሚያደርሰው ጉዳት Aከራዩ ተጠያቂ ይሆናል።

12. የሰዓት Eላፊ ገደብ


(1) በሁሉም የክልሉ ከተሞች ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት Eስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ
የሚደረግ የሰውም ሆነ የተሽከርካሪ Eንቅስቃሴ በጥብቅ የተከለከለ ነው፤
(2) የዚህ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ 1 ድንጋጌ ቢኖርም፦

ሀ) ለጸጥታ ሥራ የሚደረግ Eንቅስቃሴ፣


ለ) የAስቸኳይ ጊዜ ዉሳኔዉን ለማስፈጸም ሲባል በዘመቻ መምሪያዉ የተፈቀደና በግልጽ
የሚታወቅ በየደረጃዉ የሚገኝ የAመራር Eንቅስቃሴ፣
ለ) በድንገተኛ ህመም ወደ ህክምና ተቋማት የሚሄዱ፣
ሐ) ከድንገተኛና የEሳት Aደጋ መከላከል ጋር የተያያዙ Eንቅስቃሴዎች፣
መ)ከስራቸው ባህሪ Aኳያ ከተቀመጠዉ የሰዓት ገደብ በላይ Eንዲሠሩ የሚያስገድዳቸዉ
ተቋማት Eንደ የኮንስትራክሽን ድርጅቶች፣ የሆስፒታሎችና ጤና ተቋማት፣ባለ ኮከብ
ሆቴሎች፣ ነዳጅ ማደያዎች፣ የዳቦ ማምረቻና ሌሎች ፋብሪካዎች፣ ወፍጮ ቤቶች፣ Eና
የሃይማኖት ተቋማት፣ ሠራተኞችና ተሽከርካሪዎች ላይ የሠዓት ገደቡ ተፈፃሚነት
Aይኖረውም፡፡

13. የተከለከሉ ተግባራት


(1) በተጣለው የሰዓት Eላፊ ገደብ ውስጥ በጭፈራ ቤቶችና በመጠጥ ቤቶች ማናቸውንም
የመጠጥና መዝናኛ Aገልግሎት መስጠት በጥብቅ የተከለከለ ነው፤
(2) የወጣቱን ስሜትና ተነሳሽነት በመጉዳት የህልውና ዘመቻዉን Aደጋ ላይ የሚጥል
መሆኑ ስለታመነበት በማናቸውም ጊዜና ቦታ የሺሻ ማስጨስና ጫት ማስቃም
Aገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው፤
(3) ቁማር ማጫዎትና መሰል ተግባራትን መፈጸም የተከለከለ ነው።


 
ክፍል Aራት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

14. የመተባበር ግዴታ


ማንኛውም ሰው የህልውና ዘመቻውን ለማሳካት ለሚደረገው Eንቅስቃሴ
የመተባበር ግዴታ Aለበት።

15. ስለተጠያቂነት
በዚህ መመሪያ ላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት
የሚያደናቅፍ ወይም የተሰጠውን ኃላፊነት የማይወጣ ማንኛውም ሰው
በAስተዳደራዊና መደበኛው የሕግ ድንጋጌ መጠየቁ Eንደተጠበቀ ሆኖ Eስከ ስድስት
ወር በሚደርስ የEስራት ቅጣትና Eስከ Aስር ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ይቀጣል፡፡

16. ተፈፃሚነት ስለማይኖራቸው ሕጎች


1. ይህንን መመሪያ የሚቃረን ማናቸውም ሌላ መመሪያ ወይም ልማዳዊ Aሠራር
በዚህ መመሪያ ውስጥ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት Aይኖረውም።
2. የዚህ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ /1/ ድንጋጌ Eንደተጠበቀ ሆኖ፤ የዚህ መመሪያ
ድንጋጌዎች የፌዴራል መንግስት ካወጣዉ የAስቸኳይ ጊዜ Aዋጅ ቁጥር
5/2014 ዓ.ም Eና Eርሱን ተከትለዉ ከሚወጡ ዝርዝር መመሪያዎች ጋር
Eስካልተቃረኑ ድረስ ተናበዉ የሚፈጸሙ ይሆናል፡፡

17. መመሪያውን ስለማሻሻል


መስተዳድር ምክር ቤቱ ይህን መመሪያ ሊያሻሽለው ይችላል።

18. መመሪያዉ ስለሚፀናበት ጊዜ


ይህ መመሪያ በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ከጸደቀበት ከጥቅምት 25 ቀን 2014
ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

ባህር ዳር
ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ.ም
ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)
የAማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርEሰ-መስተዳድር

10 
 
11 
 

You might also like