You are on page 1of 2

✞ጌታ ተነስቷል✞

ጌታ ተነስቷል እልል እልል በሉ


አምላክ ተነስቷል የምስራች በሉ
ሙስና መቃብር በኃይሉ አጥፍቶ
ሁላችን አየነው ክርስቶስ ተነስቶ

አዳምን ለማዳን ቃልኪዳን ገብቶለት


ዘመኑን ጠብቆ ካሳ ሊከፍልለት
ከሰማያት ወርዶ የተሰቀለው
ሞትን በሞት ሽሮ ይኸው አየነው
አዝ= = = = =
ደቀ መዛሙርቱ እጅጉን ተጨንቀው
በጌታቸው መሞት በኀዘን ተመተው
በተዘጋ ደጃፍ ተሰብስበው ሳለ
እጆቹን ዘርግቶ ሰላም ለእናንተ አለ
አዝ= = = = =
ማርያም መግደላዊት እየገሰገሰች
በለሊት ተነስታ ወደ አምላኳ ሄደች
አይሁድ አንገላተው የሰቀሉት ጌታ
ተነስቶ አግኝታው ተመላች በደስታ

#ዮም_ፍስሐ_ኮነ

ዮም ፍስሐ ኮነ ፍስሐ ኮነ
በእንተ ልደታ ለማርያም

በባርነት ሳለን ፍስሐ ኮነ


ሀጢአት ባለም ነግሳ ፍስሐ ኮነ
በድንግል መወለድ ፍስሐ ኮነ
ቀረልን አበሳ ፍስሐ ኮነ
አዝ.......
እግዚአብሄር መረጠሽ ፍስሐ ኮነ
ልትሆኝ እናቱ ፍስሐ ኮነ
ይኸው ተፈፀመ ፍስሐ ከነ
የዳዊት ትንቢቱ ፍስሐ ኮነ
አዝ.......
የሰው ልጆች ተስፋ ፍስሐ ኮነ
የአዳም ህይወት ፍስሐ ኮነ
የኢያቄም የሀና ፍስሐ ኮነ
ፍሬ በረከት ፍስሐ ኮነ
ምክንያተ ድሂን ፍስሐ ኮነ
ኪዳነ ምህረት ፍስሐ ኮነ
ድንግል ተወለደች ፍስሐ ኮነ
የጌታየ እናት ፍስሐ ኮነ

አዝ.........
በሄዋን ምክንያት ፍስሐ ኮነ
ያጣነውን ሰላም ፍስሐ ኮነ
ዛሬ አገኘነው ፍስሐ ከነ
በድንግል ማርያም ፍስሐ ኮነ
የምስራች እንበል ፍስሐ ኮነ
ሀዘናችን ይጥፋ ፍስሐ ኮነ
ተወልዳለች እና ፍስሐ ኮነ
የዓለም ሁሉ ተስፋ ፍስሐ ኮነ
ዮም ፍስሐ ከነ ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም
ዮም ፍስሐ ከነ ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም

You might also like