You are on page 1of 4

በባለሥልጣን መ/ቤት ለማኔጅመንት

አባላትና ለልማት ዕቅድ ባለሙያዎች፤

ለዲስትሪክት ሥራ አስኪያጆችና

ባለሙያዎች የአቅም

ግንባታ ሥልጠና ለመስጠት

የተዘጋጀ የሥልጠና መርሀ ግብር /TOR/

ልማት ዕቅድ ክትትልና ግምገማ ደ/ሥራ ሂደት

ዋና መ/ቤት

ሀዋሳ፤

ጥር /2014

መግቢያ

ደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን በርካታ የመንገድ እና የድልድይ ግንባታ እንዲሁም የድልድይ


ዲዛይን ሥራዎችን ሰመስራት ለክልሉ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴና እድገት ጉልህ
አስተዋጽኦ ሲያበረክት ቆይቷል፤ አሁን ባለው ደረጃ ባለስልጣን መ/ቤቱ ስምንት
ዲስትሪክቶችን የሚመራ ሲሆን እያንዳንዱ ዲስትሪክት በራሱ በርካታ ኘሮጀክቶች
እያስተዳደረ ይገኛል፡፡

ከዚህ አንጻር ባለሥልጣን መ/ቤቱ ኘሮጀክቶችን የሚያስተዳድሩ አካላት ወቅታዊ በሆነ


እውቀትና ክህሎት እንዲመሩ ለማስቻል የዋናው ቢሮ ማኔጅመንት አባላትንና የልማት ዕቅድ
ክትትልና ግምገማ ሥራ ሂደት ባለሙያዎችን፣ ከኦኘሬሽን፣ ከሬጉላቶሪና፣ አቅርቦት ሥራ
ሂደቶች የሚመለከታቸው ባለሙያዎችን እና ከእያንዳንዱ ዲስትሪክት ስራ አስኪያጅ ግንባታ
አስተባባሪና የልማት ዕቅድ ባለሙያ በኘሮጀክት አስተዳደር ዘርፍ አጭር የአቅም ግንባታ
ሥልጠና ቢሠጣቸው የተሻለ አፈጻጸምና ውጤት እንደሚያስመዘግቡ ታምኗል፡፡

ስለሆነም በመስኩ የካበተ ዕውቀትና ልምድ ያላቸው ሁለት ባለሙያዎች ከደቡብ ኘላን
ኮሚሽን ሥልጠና እንዲሠጡን ይህ የሥልጠና መርሀ ግብር /TOR/ ተዘጋጅቷል፡፡

የስልጠናው ዋና ዓላማ፡-

በዋናው መ/ቤት እስከ ዲስትሪክት ያሉ የማኔጅመንት አባላትና ተግባሩ የሚመለከታቸው


ባለሙያዎች አስተደደር ክትትልና ግምገማ ላይ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በመስጠት
ዕውቀታቸውንና ክህሎታቸውን ማጎልበትና የተሻለ አፈጻጸም እንዲያስመዘግቡ ማስቻል፡፡

ዝርዝር ዓላማ

 አጠቃላይ የመረጃ አሰባሰብ፣ ዕቅድ ዝግጅትና ኘሮጀክት አስተዳደር


 በኘሮጀክት ክትትልና ግምገማ ሂደት
 በበጀት አስተዳደርና ሪፖርት ዝግጅት
ሥልጠናው የሚሠጥባቸው ርዕሶች
 በኘሮጀክት እቅድ አዘገጃጀትና መረጃ አያያዝ
 በኘሮጀክት ክትትልና ግምገማ
 የበጀት አስተዳደርና ሪፖርት ዝግጅት
 የ BSC አተገባበር
የሥልጠናው ተሳታፊዎች
1. ከዋናው ቢሮ የማኔጅመንት አባላት በቁጥር 15
2. ከደቡብ ክልል ኘላን ኮሚሽን አሰልጣኝ በቁጥር 1
3. ከፐብሊክ ሰርቢስ ኮሚሽን አሰልጣኝ በቁጥር 1
4. ከዋናው ቢሮ የልማት ዕቅድ ደ/ሥራ ሂደት ባለሙያዎች 10
5. ከዋናው ቢሮ ኦኘሬሽን ሥራ ሂደት ባለሙያዎች በቁጥር 2
6. ከዋናው ቢሮ ሬጉላቶሪ ሥራ ሂደት ባለሙያዎች በቁጥር 2
7. ከዋናው ቢሮ አቅርቦት ደ/ሥራ ሂደት ባለሙያዎች 4
8. የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች 2
9. የዲስትሪክት ማኔጅመንት አባላት 2*8 16
የዋና መ/ቤትና የዲስትሪክት ሾፌሮች በቁጥር 16
ባጠቃላይ 70 ተሳታፊዎች የሥልጠናው ተካፋይ ይሆናሉ፡፡
የሥልጠናው ቦታ፡- ሻሸመኔ

ከሥልጠናው የሚጠበቅ ውጤት


በዕውቀት የተመራ የኘሮጀክት አስተዳደር ሥርዓትና ጥራቱን የጠበቀ ሪፖርት ማቅረብ እንዲሁም ጥራቱን
የጠበቀ የመንገድ ድልድይ ግንባታ አፈጻጸም

የስልጠና ጊዜ፡- ስልጠናው የሚሰጥበት ጊዜ ከጥር 27-29/2014 ዓ.ም ይሆናል

የተደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች፡-

 ለስልጠናው የሚያስፈልግ አጠቃላይ በጀት ማስፈቀድ


 የሥልጠና ተሳታፊ አባላትን መለየትና በጀት ጋር በማገናዘብ የሠልጣኞችን ብዛት መወሰን
 ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ነገሮችን ማመቻቸት
በሥልጠናው ለሚሳተፉ አባላት የአበል ክፍያ ሁኔታ
1. ከደቡብ ክልል ኘላን ኮሚሽን የ 1 ዐ ቀን አበል 10*402*1 = 4020
2. ከፐብሊክ ሰርቢስ ኮሞሽን የ 1 ዐ ቀን አበል 10*477*1 = 4020
3. ለዋናው ቢሮ ማኔጅመንት አካላት የ 1 ዐ ቀናት አበል 15*402*10 =60,300
4. ከዲስትሪክት ለሚመጡ ለእያንዳንዱ የሥልጠናው ተሳታፊ 16*402*10 =77,184
5. የዋና ቢሮ ባለሙያዎች 20*402*10 =80,400
6. የዋና መ/ቤት የሾፌሮች በቁጥር 348*8*10= 27,840
7. የዋና መ/ቤት የዲስትሪክት ሾፌሮች በቁጥር 348*8*10= 33,408
8. ለአዳራሽ ኪራይና በዕረፍት ሰዓት የሻይ ቡና መዝናኛ 200*70*3 =42,000
የወጪ ማጠቃለያ
 ለውሎ አበል ወጪ = ብር = 291,192
 ለአዳራሽ ኪራይ ለመስተንግዶ ወጪ = ብር 42,000
 መጠባበቂያ ድምር = ብር 5,000
 አጠቃላይ ድምር = ብር 333,902

You might also like