You are on page 1of 1

ማሣሠቢያ

ለአሚጎንያን ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ መምህራን በሙሉ፡፡

ትምህርት ቤታችን አሚጎንያን ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሁለተኛውን ኳርተር ጨርሶ ሦስተኛ ኳርተር
የመማር ማስተማር ስራውን እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ትምህርት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ አንዳንድ
የመማር ማስተማሩን የሚያስተጓጉሉ እና የትምህርት ቤቱ መገለጫ መሆን የሌለባቸው ተግባራት በመምህራን እየታዩ
በመሆኑ ቀጥሎ የቀረቡት ችግሮች ሊታረሙ እንደሚገባ ትምህርት ቤቱ ያሣስባል፡፡

1. ጠዋት የስራ ሰዓት በጊዜ አለመግባትና በሰንደቅ ዓላማ ፕሮግራም ላይ በየክፍሉ አለማሰለፍ፤
2. የምሣ እና የእረፍት ሰዓት ለይ ሰዓትን ጠብቆ ወደ ክፍል አለመግባት፤
3. በትምህርት ሰዓት መግቢያ ላይ ሰዓት አባክኖ መግባትና በመውጫ ሰዓትም ሰዓቱን በአግባቡ ሣይጨርሱ
መውጣት፤
4. ተማሪዎችን ያለበቂ ምክንያት ለሽንት ቤትና ለመታጠብ እያሉ እንዲወጡ መፍቀድ፤
5. የሚያስተምሩበትን ክፍል ፀጥታ አለማሰጠበቅ እና የመሣሠሉ ችግሮች እየተስተዋሉ በመሆኑ መምህራን
አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉና ከትምህርት ቤቱ ጋር በገቡት ውል መሠረት የስራ ሠዓትን ማክበር ፤
ሙያው የሚጠይቀውን የክፍል ስርዓት ማስጠበቅ እንዲሁም ተማሪዎችን ከክፍል እንዲወጡ ባለመፍቀድ ስራን
በአግባቡ እንድትሰሩ አሳስባለው፡፡

‹‹ከ ሠ ላ ም ታ ጋ ር››

You might also like