Professional Documents
Culture Documents
12
12
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በመጋቢት አሥራ ሁለት ቀን በዚህች ዕለት
የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል በዓል መታሰቢያ ነው፡፡ በዚህች ቀን እግዚአብሔር ቅዱስ ሚካኤልን
ወደፈላስፋው ወደበለዓም ልኮታልና። ባላቅ እስራኤልን ይረግምለት ዘንድ በጠራው ጊዜ፡፡ በጎዳናም በፊቱ ቆሞ
አስደነገጠው፤ አህያው በሰው አንደበት እስክትናገር ድረስ፡፡ እርግማኑንም ወደበረከት ለወጠው፡፡ የጥምቀት
ልጆችን ሁሉ እግዚአብሔር በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ይጠብቀን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡