You are on page 1of 1

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን፡፡

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም፡፡ አሜን፡፡

ሚያዝያ ዐሥራ ሁለት በዚህች ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል በዓል መታሰቢያ ነው፡፡

በዚህች ቀን ክብር ምስጋና ይግባውና ልዑል እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን ወደነቢዩ
ኤርምያስ ልኮታልና፡፡ ንጉሡ ሴዴቅያስ አሳሥሮበት ከነበረው ከዓዘቅተ ወህኒ ቤት አወጣው፡፡ የንጉሡ ባለሟል
የሠራዊቱ አለቃ ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ አወጣው፡፡ ያንጊዜም ኤርምያስ የኢየሩሳሌምን ጥፋት አያሳይህ፤
በመማረክ የሚመጣውንም መከራና ፈተና አያድርስብህ ብሎ መረቀው፡፡ እንደተናገረውም ሆነለት፡፡ ስድሳ
ስድስት ዘመን ተኛ፤ ወይንና በለስም ይዞ ነበር፡፡ የእስራኤል ልጆችም ከጼዋዌ እስኪመለሱ ድረስም
አልጠወለጉም፤ አልደረቁም፡፡ ከወይኑ ከበለሱ ፍሬ አምጥቶ ለኤርምያስ ሰጠው፡፡ ስለዚህም የመላእክት አለቃ
የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን እንድናከብር የቤተክርስትያን መምህራን አዝዘውናል፡፡
አማላጅነቱ ከኛ ጋር ይኑር፡፡ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

You might also like