Professional Documents
Culture Documents
12
12
በዚህች ዕለት ነሐሴ ዐሥራ ሁለት ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል በዓል መታሰቢያ ነው፡፡ በዚህች ቀን
በሮሜ አገር ለደጉ ንጉሥ ለቈስጠንጢኖስ ተገልጦለታልና፡፡ በጠላቶቹ ሁሉ ላይም ኃይልን ሰጠውና ድል
ነሣቸው፡፡ መንግሥቱም ጸናች፤ የጣዖታቸውንም ቤት አፍርሶ አብያተ ክርስትያናትን ሠራ፡፡ በልዩ ልዩ ክብር
አከበራቸው፡፡ ስለዚህ በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል እናደርግ ዘንድ
የቤተክርስትያን መምህራን አዘውናል፡፡ ልመናው ከኛ ጋር ይኑር፡፡ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡