You are on page 1of 7

ሚዲያ

ለአንድነትና ለኅልውና

የአማራ ተወላጅ ኢትዮጵያዊያን ማኅበረሰብ አንቂዎችና የሚዲያ ባለሙያዎች በአንድነት በሚዲያው ዘርፍ ይሰሩ

ዘንድ

የተቀረፀ PéjKT

ጥቅምት 2014 ዓ.ም


ባህርዳር ኢትዮጵያ

ማጠቃለያ
መግቢያ
እናት ሀገር ኢትዮጵያ በታሪኳ ለታላቅ ክብር እንድትበቃ ከሌሎች ኢትዮጵዊያን ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር በመሆን
የጀግኖችና ሀገር ወዳድ ልጆች ማህፀን አምሐራ የተባለ ሕዝብ ጉልህ ድርሻ አለው፡፡ ይህ ኩሩና ግብረገብ የሆነ ሕዝብ
መስዋዕትነት ለዘመናት ሲከፍል የኖረ ሲሆን ኢትዮጵያ እንደ ኢትዮጵያ መልክና ቁመቷን እየመተረ፣ ግዛቷንና ዙፋኗን
እያደላደለ፣ ስምንና ዝናዋን ከአድማስ እያሻገረ ለአፍሪካ ተምሳሌትነት እንድትበቃ ያደረገ ሕዝብ ነው፡፡ ይሁን እንጅ
ይህ የሀገር ባለውለታ የአማራ ሕዝብ በትቂት ሀገር አፍራሽ ቡድኖች ያለስሙ ስም፣ ያለግብሩ ግብር ተሰጥቶት
ላለፉት ዘመናት እጅግ በተጠና መልኩ እንዲሸማቀቅ አልፎም እንዲደቅ አያሌ ሥራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡
‹‹ከእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ›› እንዲሉ በችግሩ ልክ ለዘላቂ መፍትሔ በቅንጅት ባለመሰራቱ ምክንያት የሕልውና አደጋ
እንዲገጥመው ሁኗል፡፡

I
ስለሆነም ለዚህ ችግር መፍትሔ ይሆን ዘንድ በሚዲያው ዘርፍ የአምሐራን ሕዝብ ውስጣዊ አንድነት የሚጠብቅና
ኢትዮጵን የሚታደግ በአጭርና በረጅም ጊዜ የሚተገበር ዘላቂ መፍትሔ ያሻል፡፡ ለዚህ ሀሳብ ዳር መድረስም
አንደኛው ወሳኝ ጉዳይ ቢኖር የመረጃ አያያዝ፣ ትንተናና ስርጭት ጥልቀት፣ ፍጥነት፣ ደህንነት፣ ታማኝነት፣ ወጥነትና
አንድነት ናቸው፡፡ በመሆኑም በዚህ ዘርፍ ላይ በግልም ይሁን በመንግስት፣ በማኅበራዊ ሚዲያውም ይሁን በብሮድ
ካስት ሚዲያው ላይ ተሳትፎ ያላቸው የሚመለከታቸው የአምሐራ ልጆች ሁሉ ስለሕዝባቸው ልሕቀትና
ስለኢትዮጵያ አንድነት በተባበረ ክንድ አብሮ መስራት ለነገ የማይባል የዛሬ የውዴታ ግዴታ ነው፡፡ ለአንድ ዓላማ
የቆሙ የአምሐራና ኢትዮጵያ ውድ ልጆች በጋራ በሚዲያው ዘርፍ በመሥራት በዘመናቸው ታሪክ ሰርተው ብቻ
ሳይሆን ታሪኩንም ጽፈው እንዲያልፉ ማስቻል ዘመኑ የሚፈልገው መፍትሔ ነው፡፡
የፕሮጀክቱ ዓላማ
የአምሐራ ሕዝቦችና የኢትዮጵያ ውድ ልጆች ወጥነትና አንድነት ባለው መልኩ በሚዲያው ዘርፍ ላይ በመሥራት
ሕዝባቸውን ከህልውና አደጋ መከላከልና ለዘላቂ ዘመን ተሻጋሪ ድል ማብቃት
የፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ በጀት

608,520 ብር (ስድስት መቶ ስምንት ሺ አምስት መቶ ሃያ ብር)


ፕሮጀክቱ የሚተገበርበት ጊዜ
ህዳር 5 እስከ ህዳር 11/2014 ዓ.ም ይተገበራል፡፡

ማውጫ
ማጠቃለያ......................................................................................................................................................I
ማውጫ.......................................................................................................................................................II
1. መግቢያ.................................................................................................................................................1
2. የፕሮጀክቱ ዓላማ....................................................................................................................................2
3. የፕሮጀክቱ ጠቀሜታዎች............................................................................................................................2
4. ኘሮጀክቱ የሚተገበርበት ቦታ.......................................................................................................................2
5. ፕሮጀክቱ የሚተገበርበት የጊዜ ገደብ..............................................................................................................3
6. የፕሮጀክት በጀት......................................................................................................................................3
7. የፕሮጀክት በጀት ምንጭ............................................................................................................................4
8. የፕሮጀክቱ አስፈጻሚ አካላት.......................................................................................................................4
9. የፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ ስልት.....................................................................................................................4
10. ለፕሮጀክቱ ትግበራ ያሉ ምቹ ሁኔታዎች፣ ስጋቶችና መፍትሔዎች.............................................................................4
11. የፕሮጀክት ትግበራ እቅድ...........................................................................................................................5

II
1. መግቢያ
እናት ሀገር ኢትዮጵያ ለዘመናት የታፈረችና የተከበረች ቀደምትና ባለ ደማቅ ታሪክ ባለቤት ነች፡፡ ለዚህም ክብር
እንድትበቃ በብዙ ብሔር ብሔረሰቦች ለተዋቀረችው ባለጸጋ ሀገር ከሌሎች ኢትዮጵዊያን ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር
በመሆን የጀግኖችና ሀገር ወዳድ ልጆች ማህፀን አምሐራ የተባለ ሕዝብ ጉልህ ድርሻ አለው፡፡ ይህ ኩሩና ግብረገብ
ሕዝብ ለሕይወቱ ሳይሳሳ ለእምየ ኢትዮጵያ መክፈል የሚገባውን ያክል መስዋዕትነት ለዘመናት ሲከፍል የኖረ ሲሆን
ኢትዮጵያ እንደ ኢትዮጵያ መልክና ቁመቷን እየመተረ፣ ግዛቷንና ዙፋኗን እያደላደለ፣ ስምንና ዝናዋን ከአድማስ
እያሻገረ ለአፍሪካ ተምሳሌት እንድትበቃ ያደረገ ሕዝብ ነው፡፡ ከዳር ድንበር ጠባቂው ክቡር ወታደር እስከ መሀል ሀገር
የቤተ መንግስት ንጉሥ ልጆቹን በሁሉም ዘርፍ ለሀገራቸው እንዲኖሩ ያበረከተ ባለውለታ ሕዝብ ነው፡፡
ይሁን እንጅ ይህ የሀገር ባለውለታ የአማራ ሕዝብ በትቂት መሰሪ ሀገር አፍራሽ ቡድኖች ያለስሙ ስም፣ ያለግብሩ
ግብር ተሰጥቶት ላለፉት ዘመናት እጅግ በተጠና መልኩ እንዲሸማቀቅ አልፎም እንዲደቅ አያሌ ሥራዎች ሲሰሩ
ቆይተዋል፡፡ ‹‹ከእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ›› እንዲሉ በችግሩ ልክ ለዘላቂ መፍትሔ በቅንጅት ባለመሰራቱ ምክንያት
በሀገረ መንግስት ደረጃ ሲቀነባበር የኖረው ሰይጣናዊ ሥራ ድምር ውጤት እንደ ሕዝብ በመኖርና ባለመኖር
የሚተረጎም የሕልውና አደጋ እንዲገጥመው አድርጓል፡፡

III
በዓለማችን ብሎም በሀገራችን የበለጸጉት ሀገራት የስልጣኔ ትሩፋት የሆኑ ዘመኑ ያፈራቸው በርካታ ሚዲያዎች
ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ በተለይም ብሮድ ካስት ሚዲያውና ማኅበራዊ ሚዲያው የስርጭት አድማሱና
የተጠቃሚው ብዛት ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ እየጨመረ መጥቷል፡፡ በዚህም ምክንያት ሕዝባችን ለሚዲያው
አወንታዊም ይሁን አሉታዊ ተጽእኖ ስር ነው፡፡ እንደ አማራ ክልልም የሚዲያ በተለይም በማኅበራዊ ሚዲያው በኩል
እንደ ሕዝብ አጠቃቀማችን፣ እንደ ማኅበረሰብ አንቂና እንደ ፖለቲከኛም አንድነትና መናበብ የጎደለው፣ በአማራ
ሕዝብ ላይ በተቃጣው የሕልውና አደጋ ልክ አጸፋዊ ምላሽ ለመስጠትና ለመመከት ያልተደራጀና የነገውን የአምሐራ
ሕዝብ የልዕልና ጉዞ ዳር ለማድረስ ያልተዘጋጀ ሁኖ እናገኘዋለን፡፡

ስለሆነም ለዚህ መልከ ብዙ ችግር በጥቅልና በተናጠል፣ በአጭርና በረጅም ጊዜ የሚተገበር ዘላቂ መፍትሔ ያሻል፡፡
ከነዚህም ውስጥ በሁሉም ዘርፍ ውስጣዊ አንድነቱን መጠበቅና ማጠናከር የመጀመሪያው የአምሐራ ሕዝብ የቤት
ሥራ ነው፡፡ ለዚህ ሀሳብ ዳር መድረስም አንደኛው ወሳኝ ጉዳይ ቢኖር የመረጃ አያያዝ፣ ትንተናና ስርጭት ጥልቀት፣
ፍጥነት፣ ደህንነት፣ ታማኝነት፣ ወጥነትና አንድነት ናቸው፡፡ በመሆኑም በዚህ ዘርፍ ላይ በግልም ይሁን በመንግስት፣
በማኅበራዊ ሚዲያውም ይሁን በብሮድ ካስት ሚዲያው ላይ ተሳትፎ ያላቸው የሚመለከታቸው የአምሐራ ልጆች
ሁሉ እስካሁን ካለው የሚመጣው እጅግ ፈታኝ ነውና ዘመኑን የዋጀ ዝግጅት በማድረግ ስለሕዝባቸው ልሕቀትና
ስለኢትዮጵያ አንድነት በተባበረ ክንድ አብሮ መስራት ለነገ የማይባል የዛሬ የውዴታ ግዴታ ነው፡፡ በአንድ ስም የሞቱ፣
በአንድ ጉድጓድ የተቀበሩና ለአንድ ዓላማ የቆሙ የአምሐራና ኢትዮጵያ ውድ ልጆች በጋራ በሚዲያው ዘርፍ
በመሥራት ላለፈው ደዌ ፍቱን መድሐኒት፣ ፊት ለፊታችን ለሚጠብቀን ተላላፊ በሽታም ጥሩ የመከላከያ ክትባት
በመፈብረክ በዘመናቸው ታሪክ ሰርተው ብቻ ሳይሆን ታሪኩንም ጽፈው እንዲያልፉ ማስቻል ዘመኑ የሚፈልገው
መፍትሔ ነው፡፡

2. የፕሮጀክቱ ዓላማ
የአምሐራ ሕዝቦችና የኢትዮጵያ ውድ ልጆች ወጥነትና አንድነት ባለው መልኩ በሚዲያው ዘርፍ ላይ በመሥራት
ሕዝባቸውን ከህልውና አደጋ መከላከልና ለዘላቂ ዘመን ተሻጋሪ ድል ማብቃት

3. የፕሮጀክቱ ጠቀሜታዎች
 ወጥነት ያለውና የማይቆራረጥ የመረጃ ምንጭ ለሕዝባችን ለማቅረብ
 የአምሐራ ብሎም የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነቱን ለማስጠብቅና ድርሻውን ለማጉላት ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል
 ለሴረኛና ከፋፋይ የሀገር ውስጥና ውጭ ኃይሎች በቂና አስተማማኝ ምላሽ ለመስጠት
 የቀደመ ሁለንተናዊ ልዕልናን የአምሓራ ሕዝብ እንዲላበስና ለኢትዮጵያም የኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት
 ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን በመያዝ ከዘመን ዘመን እንዲሻገሩና ተሰንደው ለቀጠዩ ትውልድ እንዲደርሱ ለማስቻል

IV
4. ኘሮጀክቱ የሚተገበርበት ቦታ
 በባሕር ዳር ከተማ ሲሆን ስልጠናው ከሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ያሉ በማኅበራዊ ሚዲያና በብሮድ
ካስት ሚዲያ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያላቸው የአምሐራ ልጆች በአካል ተገኝተው ወይም የቴክኖሎጅ አማራጮች
በመጠቀም ይሳተፋሉ

5. ፕሮጀክቱ የሚተገበርበት የጊዜ ገደብ


ህዳር 5 እስከ ህዳር 11/2014 ዓ.ም ይተገበራል፡፡

6. የፕሮጀክት በጀት
ተ.ቁ. የወጭ ዓይነት መለኪያ ብዛት የአንዱ ዋጋ ጠቅላላ ዋጋ ምርመራ
(በብር) (በብር)
1 የተሳታፊዎች አበል የተሳታፊ ቁጥር 80 650 312,000 80 ሰው *
(የቀን አበል) 650 ብር*
6 ቀን
2 የአሰልጣኝ አበል የአሰልጣኝ ቁጥር 2 2000 24,000 2 ሰው *
(የቀን አበል) 2000 ብር*
6 ቀን

3 የአስተባባሪዎች አበል ቁጥር 3 2000 ብር 36,000 3 ሰው *


(የቀን አበል) 2000 ብር*
6 ቀን
4 ለትራንስፖርት ቁጠር 30 4800 144,000
(የአንድሰው
ደርሶመልስ
የፕሌን ትኬት
ዋጋ)
5 የአዳራሽ ኪራይ ቁጥር 1 1000 6,000 1 አዳራሽ *
(የቀን የአዳራሽ 1000 ብር*
ኪራይ) 6 ቀን
6 ለሻይ ቡና የተጠቃሚዎች 80 50*2 48,000 80 ሰው *
ቁጥር 100 ብር*
6 ቀን*
2 ጊዜ
7 ስቴሽነሪ ማስታዎሻ ቁጥር 80 50 4,000
ደብተር
እስክርቢቶ ቁጥር 80 10 800
ድምር 553,200
10% መጠባበቂያ 55,320
ጠቅላላ ድምር 608,520

V
7. የፕሮጀክት በጀት ምንጭ
መንግስታዊ የሆኑና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም በጎ አድራጊ ባለሀብቶች በተለያየ መንገድ ይህን
ፕሮጀክት የሚደግፉ ይሆናል፡፡

8. የፕሮጀክቱ አስፈጻሚ አካላት


የዚህ ፕሮጀክት ዋና አስፈጻሚ አካል ላሜድ የልዩ ኩነቶች ማስተባበር ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ነው፡፡

9. የፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ ስልት


ይህ ፕሮጀክት ለአምሐራ ህዝብና ለኢትዮጵያ ፋይዳው ፈርጀ ብዙና ጊዜውን የዋጀ በመሆኑ ለሚመለከታቸው
ሁሉ የፕሮጀክቱን አላማ በማስረዳት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ በከፍተኛ ርብርብ ይሰራል፡፡

10. ለፕሮጀክቱ ትግበራ ያሉ ምቹ ሁኔታዎች፣ ስጋቶችና መፍትሔዎች


10.1. Mc$ h#n@‹C
ለወቅቱ ለኅልውና የሚሰራበት ስለሆነ የክልሉ መንግስትና ሌሎች የሚመለከታቸው ሁሉ
በግልም በህብረትም በአንድነት የዘመቱ መሆናቸው
አሁን ባለንበት ዘመን እንደ ኢትዮጵያም የማኅበረሰብ አንዎች ድርሻ እየጎላ መምጣቱ

10.2. SUèC
bz!H PéjKT TGb‰ wQT lÃU_Ñ k¸Cl# SUèC Ws_½

በቂ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት አለመቻል


ወቅታዊው የሀገሪሩ ሁኔታ የማኅበረሰብ አንቂዎችን ሙሉ ጊዜ የሚፈልግ በመሆኑ የስልጠናው ጊዜ የመረጃ
ማድረስ ጊዜአቸውን እንዳይሻማቸው

10.3. ymFT/@ húïC


በከፍትኛ ትጋትና ርብርብ በመስራት ለሚመለከታቸው የመንግስትና የግል ተቋማት ሁሉ የፕሮጀክቱን አላማ
በማስረዳት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ እንዲያደርጉና የተጣለባቸውን የህልውና አደራ እንዲወጡ በማስተባበር
ውጢታማ ማድረግ፡፡

VI
11. የፕሮጀክት ትግበራ እቅድ
ተ.ቁ ዋና ዋና ተግባራት ፈጻሚ አካል ጥቅምት ጥቅምት- ጥቅምት ህዳር
8/2014 20/2014 27/2014 5/2014
1 የፕሮጀክት ፅሑፍ ዝግጅት ላሜድ የልዩ ኩነቶች ማስተባበር ኃ/የተ/የግ/ማኅበር

2 ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ አብክመ ኮሚኒኬሽን ቢሮ


በጀት ማፈላለግ ከ----
ላሜድ የልዩ ኩነቶች ማስተባበር ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ጋር
በመተባበር
3 የተሳታፊ ምልመላ የባሕር ዳር ማእከል እቅድና ክትትል ክፍል

4 ስልጠና፣ ውይይትና የባሕር ዳር ማእከል የሚድያ ቤተሰብ ኮሚቴ


ማደራጀት

You might also like