You are on page 1of 1

ቀን 23/10/2014

ጉዳዩ: - የምስክር ወረቀት እንዲሰራልን ስለመጠየቅ


የKTS ክበብ አባላት በባህር ዳር ዩኒቨርሲት በBiT ቅጥር ግቢ ለተማሪወች የቴክኒካል እዉቀታቸዉን
በመጠቀም የኤሌክትሮኒክስ እቃወችን ማለትም ስልኮችንና ላፕቶፖችን በነፃ በመጠገን ከአላስፈላጊ ወጭወች
ነፃ ማድረጉ ይታወቃል። ስለሆነም ይህንን ላደረግንበት ለ16 የተመራቂ ተማሪወች የምስክር ወረቀት
በሳይንቲፊክ ዳይሬክተሩ በኩል እንዲሰራልን ስንል በትህትና እንጠይቃለን።
ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የኬቲኤስ አባላት በቴክኒካል እውቀታቸዉ ብቁ በሚባል ደረጃ ላይ ስለሚገኙና
ከቴክኖሎጂ ጋር ያላቼዉ ጥልቅ ግንኙነት መሰረት በማድረግ ማንኛዉም የግቢዉ እድሎች በሚኖሩበት ጊዜ
በየትምህርት ዘርፉ ለሚገኙ የKTS አባላት ተቀዳሚ ድጋፍ እንዲሰጠን ስንል በድጋሜ በትሁት ልቦና መጠየቅ
እንፈልጋለን።
የኬቲኤስ አባላት ከሰጎ እስከ ቅዳሜ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት እስከ አምስት ሰዓት በቋሚነት እና ቀን በሌላ ሰዓት
ደግሞ ያለምንም ማስተጓጎል ተማሪወችን ሲያገለግል መቆየቱን የተገለገሉ ሁሉ እንደማይዘነጉት በሙሉ ልብ
ለመናገር እንደፍራለን። ይህን ሲያደርጉ ተማሪወች ምንም አይነት የገንዘብ ክፍያ ሳይደረግ በሙሉ ፈቃደኝነት
አንዳን ወጭወችን የክበቡ አባላት በመስማማትና በመደጋገፍ መዝለቃቼዉም ሌላኛዉ እማኝ ሊሆን የሚችል
አንኳር ነገር ነዉ።

ከሰላምታ ጋር
የኬቴኤስ ሰብሳቢ

______________
ምስጢረ-ስላሴ ታደሰ

You might also like