Professional Documents
Culture Documents
ፍቃድ_ለማስወጣት_የሚያስፈልጉ_መስፈርቶች
ፍቃድ_ለማስወጣት_የሚያስፈልጉ_መስፈርቶች
ሰነዶች
ሀ. አዲስ የምስክር ወረቀት ለሚጠይቁ አማካሪ ባለሙያዎች
1. በአካባቢ፣የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን በክልል እና በከተማ አስተዳደሮች አካባቢ ጥበቃ
መ/ቤቶች እንዲሁም የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ግምገማ እንዲያካሂዱ ውክልና በተሰጣቸው የዘርፍ መስሪያ
ቤቶች ውስጥ ወይም ከዚህ ጋር በተያያዘ ማንኛውም የቁጥጥር ባለሙያ ሆኖ የማይሰራ መሆን አለበት
2. የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር
3. ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ከውጪ ሀገር የተገኘ ከሆነ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የአቻ ግምት የለዉ
የትምህርት ማስረጃ ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር ማቅረብ አለበት፤
4. የተዘጋጁ ዘገባዎችና ዘገባዎቹን ማዘጋጀትዎን የሚያስረዳ መረጃ (ጀማሪ አማካሪ አመልካቾችን አይመለከትም)
5. አግባብነት ባለው የሙያ መስክ ቢያንስ የሁለት ዓመት የሥራ ልምድ ከአንድ ፎቶ ኮፒ ጋር፤
6. ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ (3×4)
ለ. አዲስ የምስክር ወረቀት ለሚጠይቁ አማከሪ ድርጅት