You are on page 1of 1

ምናባዊነት

---
ሌላኛው ውስጣዊውን አለም የምንረዳበት መንገድ ልክ በንቃተህሌና ወስጥ ሆነን ማለም ነው። በተለምዶ ምናብ
እየተባለ የሚጠራው መሆኑ ነው። ይህ ከሌላው የሚለየንን ልዩ ብቃት በመጎናፀፍ ራሳችንን የምናውቅበት መንገድ
ለሁላችን የተቸረ ነገር ግን ጥቂቶች ብቻ የተጎናፀፉት ፀጋ ነው። እነዚያ ጥቂቶች ደግሞ "የበራላቸው" በመባል
አለምን ያስገረመ ወይም ያነጋገረ የአዕምሮ በረከታቸውን አሳይተውናል። አብዛኞቹ የፈጠራ ባለቤቶችና ታላላቅ
አሳቢያን ከምናባዊ አለማቸው ተነስተው ወደእውነታ በመምጣት በምናባቸው ያለሙትን በእውኑ ፈጥረውት
ተስተውለዋል። ዳቬንቺ፣ አንስታይን፣ ቴስላ፣ ሼክስፒር፣ ቤትሆቨን በሙሉ ጠቅሰን የማንጨርሳቸው በሙሉ
ምናባቸው ውስጥ በሄዱበት ጥልቀት ይዘው የተመለሱት ፀጋ እስካሁን አልደበዘዘም።
የሊቁ ያሬድ ታሪክ እዚህ ጋር ማሰቡ ምናልባት የምናነሳውን ሃሳብ ሃገርኛ ለማድረግ ሳይረዳን አይቀርም። ዩንግ
ያስቀመጣቸውን መንገዶች በመተግበር ግለሰባዊነትን/ ራስን የማወቅ ከፍታ ስለመቆናጠጥ ላማስረዳት ከሊቁ
ያሬድ የተሻለ ታሪክ የለም።
የያሬድን ሚቶሎጂ እዚህ ዳግም አንዘረዝረውም በታሪኩ ውስጥ ያሉ ቁልፍ የሽግግር ሂደቶችን ብቻ እየቆነጠርን
እንይ።
ትምህርት ሊዘልቀው ያልቻለው የፊተኛው ዘመን ሊቅ አቋርጦ ሲኮበልል ታሪኩን እናስታውሳለን። ይሄን ለማድረግ
ያሬድን መሆን ይጠይቅ ነበር። በያሬድ ከተምህርት ገበታው መኮብለል ውስጥ የምናየው አንድ ነገር አለ። የኮበለለው
ከንቃተ ህሌናው ነበር! ከንቃተ ህሌናው በመኮብለል የሄደው ወደራሱ ውስጣዊ አለም ነበር። በውስጡም
ማህበረሰቡ እንደሚጠብቀው የመርህ ሰው ሳይሆን በስንፍና የተሞላ መሆንኑ ነበረ በመኮብለሉ የተጋፈጠው። ያንን
ማንነቱን ፊትለፊት ሲጋፈጥ ጥላው ስር ያርፋል። ጥላው ከንቃተህሌናው በመኮብለል ወደ ውስጣዊ አለሙ ሲጓዝ
ያረፈበት ጥግ ነው። ጥላው ስር ባያርፍ ኖሮ ዛሬ "ሊቁ" የሚባል ያሬድ ላይኖረን ይችል ነበር። ሊቁ ያሬድ በዚያች
የዛፍ ጥላ ስር ማረፉን ከጥላው (personal shadow) የተዋወቀባት ወሳኟ አጋጣሚ አድርገህ ተመልከታት።
እዚያ ጥላ ስር ስንፍናውን ብቻ አልነበረም የተጋፈጠው፣ ውስጣዊው አለም ውስጥ የነበረ አወንታዊ አቅሙን
ጭምር እንጂ። ምክኒያቱም ውስጣዊው የተደበቀ ማንነታችን ውስጥ ሁሌም እኩይ ገፅ ብቻ ላይኖር እንደሚችል
በቀደመው ሃሳብ አንስተን ነበር። ሊቁ ያሬድ ይሄን አወንታዊ የሆነ አቅሙን ለመተዋወቅ ደግሞ ምናቡን መጠቀም
ነበረበት።
ምናቡ ባይኖርና ባረፈበት ጥላ ፣ የዛፍ ግንድ ላይ በመውጣትና መውደቅ ድግግሞች የሚየስተውላትን ትንሽ ትል
ፍቺ ባይሰጣት ጥላው ስር እንዳረፈ ስንፍናውን በመጋፈጡ ተሸንፎ ከራሱ ሲሸሽ የሚኖር ይሆን ነበር። ከዚያ በኋላ
በተጎናፀፈው ስነልቡናዊ ውህደት ራሱን በሚገባ ያወቀው የቀድሞው ሰነፍ ተማሪ በምልዓት እጅ ወዳሰጠችው
ህይወት በመመለስ ምናቡና ተፈጥሮን አዳብሎ እያስማማ ሙዚቃን ፈጠረ፣ ምልክትና ውዝዋዜዋን ጨምሮ
ደረሰላት።
----
ግለ–ሰብዓዊነት/ራስን ማወቅ —

You might also like