You are on page 1of 13

ቤተ 

ክርስቲያናችን እኛ እንድንከብርበት እንድንጸድቅበት በዐዋጅ አውጃ እንድንጾማቸው ካዘዘችን አፅዋማት መካከል አንዱ  የነነዌ ጾም ነው፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በደቂቀ ነቢያት ከምናገኛቸው የትንቢት መጻሕፍት  የተለየው ትንቢተ ዮናስ ነው፡፡ ትንቢተ ዮናስ በሁለት ምክንያቶች
ከሌሎቹ የትንቢት መጻሕፍት  ይለያል፡፡
ልዩ የሚያደርገው ትንቢቱ በተነገረበት በዚያው ዘመን ፍፃሜውን ያገኘ በመሆኑ ነው፡፡ ሌሎች ነቢያት የተነበይዋቸው እጅግ በብዙ ትርጓሜ
የሚነግር ከዚያም አልፎ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዘመን ፍፃሜውን ያገኘ ትንቢት ነው፡፡ የዮናስ ትንቢት ግን ትንቢቱን
በተናገረበት በዚያው በነነዌ ከተማ ፍፃሜውን ያገኘ ነው፡፡(በዚያ ዘመን ተፈጸመ ቀረ ተብሎ አይነገርም፤ የነቢያት ትንቢት በየጊዜው ሲነገር
የሚኖር ነው)
   የነቢዩ ዮናስ መጽሐፍ ታሪክ ቀመስ ትንቢት መሆኑ ከሌሎቹ የነቢያት መጻሕፍት እጅጉን ይለያል፡፡
ነነዌ  በዛሬዋ ኢራን ትገኝ የነበረች የአሦር የሥልጣኔ ከተማ ነበረች፡፡ አሶራውያን ከባቢሎን በፊት በሩቅ ምሥራቅና በመካከለኛው
ምሥራቅ የነበረውን ዛሬ ኢራን የምንለውን ይገዙ የነበሩ ኃያላን ሰዎች ናቸው፡፡ የአሶራውያን መንግሥት ዋና ከተማ ነነዌ ናት፡፡ ነነዌ ከተማ እስከ
አንድ መቶ ሺህ ሕዝብ ይኖርባት የነበረች እጅግ ሰፊ ከተማ እንደነበረች የትንቢተ ዮናስ የትንቢት መጽሐፍ ይነግረናል፡፡ የነነዌ
ሰዎች በሁለት ነገሮች ምክንያት እግዚአብሔርን አሳዝነውት ነበር፡፡
   1 ኛ. በአካባቢያቸው ስለእግዚአብሔር ቃል የሚያስተምሯቸው መምህራን ባለማግኘታቸው የተነሳ ኃጢአትን ነውርን ይሠሩ ይፈጽሙ ነበር፡፡
   2 ኛ. የሀብታቸውና የብልጽግናቸው መጠን እስከ ሰማይ ጫፍ በመድረሱ ሀብትና ብልጽግና ያመጡት ጥጋብ እግዚአብሔርን እንዲረሱ
ስላደረጋቸው ነው፡፡
በዘፍ 11  ላይ ፡ የሰው ልጅ ደክሞ በሃይማኖት ጎስቁሎ በሞራሉ ወድቆ በነበረበት ጊዜ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ከዚያ ከታላቁ ክብር ከከፍታው
ቦታ ወደታች በመውረዱ ኖኅን የመሰለ መምህር ለ 120 ዓመት የሚያስተምር መምህር ላከላቸው ነገር ግን ሊማሩ አልቻሉም ስለዚህ በንፍር ውሃ
ቀጣቸው፡፡
                 የሰው ልጅ በንፍር ውሃ ከተቀጣ በኋላ እንደ ገና ተሰብስቦ በባቢሎን ወይም በዛሬዋ ኢራቅ የባቢል ግንብ የሚባለውን እስከ ሰማይ
ድረስ የደረሰውን ግንብ ሠራ ፡፡ ይህንን ሕንፃ ሲሠራ የሰው ልጅ የሥልጣኔው ማሳያ ቁንጮ አድርጎ ነበር የሠራው፡፡ በሥልጣኔው በገፋ ቁጥር
በሀብት በደረጀ ቁጥር ከእግዚአብሔር ጋር ነው የተጣሉት ሰዎች አንድ ልብ ሆነው አንድ ቋንቋ ሆነው፣ አንድ ጎሳ ሆነው ፣አንድነታችውን ለበጎ
አልተጠቀሙበትም፡፡
ሰው አንድነቱን ለጸሎት አንድነቱን ለሰላም ለወዳጅነት አንድነቱን ተባብሮ አንድ ሥራ ለመስራት መጠቀም አለበት እንጂ? አንድነቱን ለአመጽ
ለአድማ የሚጠቀም ከሆነ እግዚአብሔር ይበትናዋል ብዙ አንድነቶችን በትኖል፡፡ ለምን ቢሉ ? አንድንታቸውን ለፍቅር ለእምነት ለምግባር
ስላልተጠቀሙ:: ሰው ስለተሰበሰበ ፤አንድ ስለሆነ ስለተሰማማ ብቻ ጥሩ ነው ማለት አይደለም፡፡ የተሰበሰበበት ምክንያት የተሰማማበት ዓላማ
አንድ ሆኖ የሚሰራው ስራ ወሳኝ ነው፡፡ ‹‹ ወንድሞች በኀብረት ቢቀመጡ እነሆ መልካም እነሆ ያማረ ነው ተብሏል፡፡››

ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ ያማረና መልካም የሚሆነው ግን ለፍቅር ከተቀመጡበት ለሃይማኖት የተቀመጡበት ለበጎ ስራ የተቀመጡ
ለመረዳዳት የተቀመጡ ከሆነ እግዚአብሔርን ለማምለክ ከተቀመጡ ከሆነ ነው ፡፡ የባቢሎን ሰዎችም አንድነታቸውን ለመልካም ነገር
ስላልተጠቀሙበት እግዚአብሔር በተናቸው በየቋንቋቸው ደባለቀባቸው፡፡ በኋላ ዘመን ደግሞ የነነዌ ሰዎች የሥልጣኔ ቁንጮ ላይ ሲደርሱ
በአሶራውያን ዘመን ይህው ተከሰተ የሰው ልጅ ሰለጠነ ፣ አንድ ላይ መኖር ጀመረ ፣የከተማ ሕይወት ጀመረ አንድ መቶ ሺህ ሕዝብ በአንድ ከተማ
ውስጥ መኖር ጀመረ፡፡ ነነዌ በጣም ሰፊ ከተማ እንደሆነች ትንቢተ ዮናስ ስናነብ እናገኘዋለን የሦስት ቀን ያህል መንገድ ገብቶ ነው ከተማውን
የጨረሳት እንግዲህ አንድ ሰው በሦስት ቀን ሊጓዝባት የሚችል ሰፊ ከተማ ናት ማለት ነው፡፡ ይህች ከተማ አንድ ላይ ሆነው መኖራቸውን
በእግዚአብሔር ላይ ለማመጽ እንቢ ለማለት ነው የተጠቀሙበት እንደ ሰይጣን ስለዚህ እግዚአብሔር በዚህ እንቢታቸው ምክንያት እንዳይቀጡ
ነበር ነቢዩ ዮናስን የላከው፡፡
                 የዩናስ መጠራት
ከታሪኩ እንደምናውቀው ዮናስ የነነዌ ሰዎችን አመጽ ትዕቢት ያውቃል፡፡ የነነዌ ሰዎች ምን ያህል አመጸኞች እንደሆኑ ይረዳል፡፡ ስለዚህ እነዚህ
ሰዎች አይሰሙኝም? ሰው ከጠገበ በኋላ ሰው ከአመጸ በኋላ ሰው በራሱ ላይ ትዕቢትን ካሳደረ በኋላ ቢመክሩት አይሰማም ፡፡ በትዕቢት የተሞላ
ሰውነት ለመስማት በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ዮናስ ይህን ነው የተረዳው እነዚህ ሰዎች ጠግበዋል ከእኛ በላይ የሰለጠነ የሚያውቅ ማን ነው፡፡እኔ
አንድ ምስኪን ነቢይ ሄጄ ብነግራቸው እንዴት ይሰማሉ?
እንቢ ብሎ በዕምቢታው ፀንቶ በመርከብ ኮበለለ ታሪኩን ትንቢተ ዮናስ ስናነብ እናገኘዋለን፡፡

                        ዩናስ በመርከብ ሲኮበልል


እግዚአብሔር የዮናስን ልቡና ተረድቶታል የዮናስ አመጽ እንቢ ማለት አይሰሙኝም ከሚል እንጂ ማስተማር አይገባኝም አልታዘዝም ከሚል
እንዳልመጣ ስላወቀ እግዚአብሔር ዮናስን በመቅሰፍት አይደለም ወደ ነነዌ መልሶ የላከው በማስተማር ነው፡፡
እግዚአብሔር ዮናስን በዐራት ነገሮች አስተምሮታል
1. በነፋስ አስተምሮታል ፡- ነፋሱ መጣ መርከቡን አናውፆትል ዮናስ ግን አልሰማም
2. በውኃ አስተምሮታል፡- ነፋሱ ውኃውን አንቀሳቀሰውና ማዕበል ተነሣ መርከቢቱ ልትገለበጥ ደረሰች አሁንም ዮናስ አልሰማም
3. መርከቡ ውስጥ በነበሩ ቃለ እግዚአብሔር በማያውቁ አይሁዳዊ ባልሆኑ አሕዛብ አስተማሮታል፡- እንግዲህ ከነፋሱ ውኃው ለዮናስ ይቀርባል
ነፋሱ አይታይም አይዳሰስም ስለዚህ በማይዳሰስ ነገር የተጀመረው ትምህርት ወደ ሚዳስሰው አመጣው ዮናስ አልሰማም ከሚዳስሱ ነገሮች ደግሞ
ወደ ሚናገሩ ሰዎች አመጣ እነዚህ ሰዎች የሚናገሩ ናቸው ዮናስ አልሰማም ስለዚህ መጨረሻ ላይ እጣ አውጥተው ጣሉት
4. በመጨረሻ ያስተማረው በዓሣ አንባሪ ሆድ ውስጥ ዓሣ አንባሪው እንዳይበላው፤እንዲተፈው አድርጉ አስተማረው፡-
ዮናስ የኮበለለው በሜዲትራኒያን ባሕር ነው የዓሣ አንባሪ ዮናስን ይዞ ዞሮ በነነዌ (በዛሬ ኢራን) ባሕረ ሰላጤ ጫፍ የተፋው፡፡ እንግዲህ የአፍሪካን
ባሕር በሙሉ ዞሮ ፣ የአንታርቲካንና የሕንድ ውቅያኖስ ዞሮ ሦስት ቀን ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ውስጥ አድሮ ነነዌ ከተማ እንደደረሰ እንዲተፋው
ያደረገው እግዚአብሔር ይህን ሦስት ቀን ለዮናስ ሲሰጠው ዮናስን ለማስተማር ነው፡፡
ዮናስ የተማረው በአራተኛው መምህሩ ነው፡፡ ዓሣ አንባሪ ሆድ ውስጥ በነበረ ጊዜ የጸለየው ያለቀሰው ያንጊዜ ነው፡፡ ትንቢተ ዮናስ ውስጥ
የምናገኘውን  ጸሎት የጸለየው በዚህ ዓሣ አንባሪ ሆድ ሆኖ ‹‹ ወደ አንተ ጮኾ ስማኸኝ ያለው›› ፡፡ እግዚአብሔር እስክንማር ድረስ ይመክረናል
የሚመክረን ደግሞ በሚያውቁ መምህራን ብቻ አይደለም በማያውቁ ሰዎች ሊመክረን ይችላል፡፡ በሚናገሩ ነገሮች ብቻ አይደለም በማይናገሩም
ነገሮች ሊመክረንም ይችላል፡፡ በሚታይ ብቻ አይደለም በማይታዩ ነገሮች ይመክራል እግዚአብሔር በነፋስ፣ በውኃ፣ በእሳት ፣በአራዊት
፣በአእዋፍ፣ በመሬት መቀጥቀጥ፣ በሰማይ መናዋጥ፣ በበሽታ በእነዚህ ሁሉ በሌሎችም ይመክራል፡፡ እግዚአብሔርም ዮናስን መክሮታል በኋላ
በትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ አራት መጨረሻ ላይ ስናይ በሌሎችም ነገሮች መክሮታል እንደገና ወደ ኋላ እመለሳለው ሲል በትል ፣ፀሐይ በቅል በነፋስ
በእነዚህ ሁሉ መክሮታል፡፡ ‹‹ እግዚአብሔር ለምክርና ለተግሳጽ የማይጠቀምበት ምንም ነገር የለም ›› ችግሩ የሰው ማስተዋል አለማስተዋል
ነው፡፡ ባላስተዋልን ቁጥር ግን ምክሩ ወደ ተግሣጽም ጭምር ሊያድግ ይችላል፡፡
  የዮናስ ወደ ልቡናው መመለስና ትምህርቱ
ዮናስ በነፋሱ ነቅቶ ቢሆን ኖሮ በጣም ቀላል ነበረ ውኃ ላይ ሲደርስ ከበድ አለ ምክንያቱም መርከቧ መናወጥ ጀመረች እና ደግሞ ሰዎች ላይ ጉዳዮ
ሲደርስ ከበድ አለ ምክንያቱም ከመሀከላችን አንድ ያጠፋ ሰው አለና ዕጣ አወጥተን እንጣለው ወደሚል ፍርድ መጡ፡፡ ነፋሱ አልፈረደም
ውሃውም አልፈረደም ሰዎቹ ግን ወደ ፍርድ ጭምር መጡ ሰዎች አንስተው ጣሉት፡፡ ዓሣ አንባሪ ሆድ ውስጥም ሲገባ ፀሐይ የሌለበት ፣ነፈስ
የሌለበት፣ አየር የሌለበት፣ ቤተዘመድ በሌለበት ብቻውን ሆነ ይህ ደግሞ ከባድ ነው፡፡ እየከበደ ነው የመጣው ባልተመለሱ ቁጥር ከባድ ነው፡፡ ‹‹
እስራኤላውያንን እግዚአብሔር እስከዚያ ድረስ ሄዷል እስከ መቅሰፍት ድረስ አልመለስ ሲሉ›› እያበላቸው እያጠጣቸው ቀን በደመና ሌሊት
በፋና እየመራ አልመለስ ሲሉ እስከ መቅሰፍት ድረስ ሄዷል፡፡ ‹‹ይህ እግዚአብሔር ለልጆቹ የሚያሳየው ፍቅር ነው፡፡›› ዮናስን እንደዚህ አድርጎ
ነው የቀጣው፡፡ መጨረሻ ላይ ዮናስ ነነዌ ከተማ ገባ ተናገረ ንስሐ ግቡ ንስሐ የማትገቡ ከሆነ እግዚአብሔር ከተማዋን በእሳት ያጠፋታል ብሎ
አስተማረ ፡፡
      የሕዝቡ መመለስና ንስሐ መግባት
አንድ ትልቅ ነገር ይኸውም ዮናስ ከታች የወፍጮ እግር ከምትቆመው ደሀዋ ሴት ጀምሮ እስከ ንጉሥ ድረስ ዮናስን ሰሙት፡፡ ስለዚህ ንጉሡ ጡት
የሚጠቡት ሕፃናት፣ እናቶቻቸውን የሚጠቡ ጥጆች እንኳን ከምግብ ከወተት ተከልክለው ሦስት ቀን ሙሉ ጾም ጸሎትን አወጁ፡፡ ይኽ አዋጅ
በጣም የሚደንቀው የንጉሥ ዐዋጅ መሆኑ ነው፡፡ እንጸልይ እንጹም በሀገራችን ላይ መከራ መጥቷል ያለው ለዚህ ነው፡፡ ነነዌ በቀላሉ
እግዚአብሔር የማራት በዓለም ታሪክ ላይ ነገሥታት መኳንንት ንስሐ የሚገቡ ከሆነ ሀገር ለመማር በጣም ቀላል ናት፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ
ክርስትና ሲጀመር እንደ አውሮፓ ብዙ መከራ ብዙ ሰማዕትነት ያልጠየቀው ክርስትና ከነገሥታቱ ስለጀመረ ነው፡፡ በአውሮፓ ክርስትና የጀመረው
ከባሮች ነው ከባሮች ተነስቶ የቤዛንታይን ቤተመንግስት ለመግባት ክርስትና 400 ዓመት ፈጅቷል፡፡ መመለስ ከላይ ከጀመረ ንስሐ መግባት ከላይ
ከጀመረ ይቅርታ መስተካከል ከላይ ከጀመረ በጣም ቀላል ነው፡፡ ንስሐ፤ ይቅርታ ከታች ከጀመረ ግን እላይ እስኪደርስ ድረስ እንደ ቤዛንታይን
400 ዓመት ሊፈጅ ይችላል፡፡ ነነዌ ከላይ ነው የተጀመረው ንስሐ መግባቱ መታረሙ፣ መቀጣቱ፣ መማሩ፣ ሱባኤ መግባቱ ከነገሥታቱ ጀመረ
አባቶቻችን ነነዌ ከሁዳዴ ፆም በፊት እንድንጾመው ያወጁበት መሠረታዊ ምክንያት፡-
• በየዘመኑ ለሚነሱ መኳንንትና ነገሥታት ትምህርት ይሆን ዘንድ ነው የእነሱ መስተካከል የሕዝቡ መስተካከል መሆኑን እንዲገነዘቡ
• ወደፊት ለሚነሱት ሊቃውንት ትምህርት እንዲሆናቸው ነው፡፡
የሊቃውንት መስተካከል  የአዋቂውም  ያላወቂውም  መስተካከል  የሊቃውንት  መምህራን  መስተካከል  የደቀመዛሙርት  መስተካከል መሆኑን
እንዲያውቁ
• ለባለጸጎች ትምህርት እንዲሆናቸው የባለጸጎች መስተካከል የድሆች መስተካከል ያመጣልና እንዲማሩ
• ከታዘዙ መቅሰፍቶች ከእግዚአብሔር ቁጣ ማምለጫ መንገድ ጾም ጸሎት ኃጢአትን ማመን መመለስ መሆኑን እንድናወቅ አባቶቻችን ይህን ጾም
በዚህ ጊዜ እንድንጾመው ሥርዓት ሠሩልን፡፡
የነነዌ ሰዎች ሦስት ቀን ሙሉ ማቅ ለብሰው አመድ ነስንሰው ምድር ወርደው ከላመው ከጣመው ነገር ተቆጥበው አለቀሱ እግዚአብሔር ይምረን
እንደሆነ ይመለስልን እንደሆነ እስኪ እንለምነው እግዚአብሔርን ብለው፡፡
  እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ስለመስማቱ
የነነዌ ሰዎች ስህተታቸውን ተገንዝበው ማረን ይቅር በለን እራራልን ብለው ከልባቸው አለቀሱ ፡፡ እግዚአብሔርም የኃጢአተኛውን መመለስ እንጂ
መጥፋትን አልፈልግም የሚል አምላክ ስለሆነ ተመለሰላቸው፡፡ አባቶቻችን እንደሚነግሩን እሳቱን አሳይቶ እሳቱ ከሰማይ ወርዶ እነርሱን
ሳይበላቸው የዛፎቹን ቅጠል ብቻ ነክቶ እንዲመለስ አደረገው  ሊመጣባቸው የነበረው ቁጣ ነገር ግን ንስሐ መግባታችሁ እግዚአብሔር እንዲህ
ማራችሁ ብሎ አሳይቷቸዋል፡፡
ትንቢተ ዮናስ እንደሚነግረን ይህ ነገር ዮናስን አላስደሰተውም፡፡ ለምን ቢሉ ዮናስ ማለት ርግብ ማለት ነው ዮናስ ኤልያስ ወደ ሰፕራታ ሄዶ በነበረ
ጊዜ ስፕራታዋ መበለት ስታስተናግደው ልጇ በሞተባት ሰዓት እንደ ገና ያስነሳላት ያ ሕፃን ዮናስ ነው ይላሉ የአይሁድ ሊቃውንት፡፡ ዮናስ የዋህ፣
ቅን፣ ደግ ፣ታዛዥ ነው፡፡ ዮናስ ጸባይ እንደ ሕፃን ነው፡፡ እግዚአብሔር እንዴት እንዲህ ያደርጋል? ብሎ እግዚአብሔርን አኮረፈው እህል
አልቀምስም ውኃ አልጠጣም ብሎ ከከተማው ውጭ ቁጭ አለ፡፡ ያን ሁሉ ትንቢት ተናግሬ አንድ መዓት ማውረድ አለበት ፤አንድም
በእግዚአብሔር ላይ ይተማመን ስለ ነበር ነው፡፡ እሱ እራሱን ከከተማው አውጥቶ መዓት  ሲወርድ ማየት አለብኝ ብሎ ቁጭ አለ፡፡ ምንም
እንዳልሆነ ሲያይ ዮናስ አዘነ፡፡ እግዚአብሔር ሆይ የተናጋው የማይደርሰለት ነቢይ ተበዬ ከምቆጠር ለምን አሁን አትገለኝም አለ፡፡ መቼም
እግዚአብሔር የለመነውን ሁሉ አይሰጥም እንዳንዴ የምንለምነው ስህተት ስላለበት እግዚአብሔር ዮናስን ተረድቶታል፡፡ ከንዴቱ ከቁጣው
ከብስጭቱ ይሄን እንዳለ ስለዚህ ምንም አላለውም፡፡
ዮናስ በተቀመጠበት ኃይለኛ ፀሐይ መጣች፡፡ ፀሐይዋ አናት አናቱን ስትለው ለምን በፀሐይ ከምትመታኝ እዚሁ አትገለኝም አለው፡፡ ቀስ አለና
እግዚአብሔር ቅል አበቀለ ጥላ አደረገለት ደስ አለው፡፡ ከዚያ እንደገና ትል መጣ ትሉ ያፈራችውን ቅል በላው እንደገና ፀሐይዋ ወጣች፡፡ እንግዲህ
በዚህ ዓለም ለምን ልኑር ልሙት በቃኝ አለ፡፡ ዮናስን ይህችን ቅል አልዘራሀትም አላጠጣሀትም አልኩተኮትካትም እራሷ በቀለች እራሷ ለመለመች
እራሷ ቅል ሰራች በጊዜዋ እራሷ ደረቀች፡፡ አንተ እርሷ በቅላ እራሷ ለምልማ ለዚህ ለደረሰችው ለዚህ ቅል እንዲህ ስትበሳጭ ክፉና ደግ ቀኝና
ግራቸውን የማይለዩ መቶ ሺህ ሰዎች ለሚኖሩበት ለነነዌ ከተማ እኔ ብቀና ለምንድነው የምትበሳጨው? ከዚህ ቅል እነርሱ አይበልጡምን? አንተ
ይህች ቅል ለምን አጠፉህ ያልከኝ ታዲያ እኔ መቶ ሺህ ሰዎች ላጥፋን? ብሎ እግዚአብሔር ዮናስን በሚታየው በሚዳሰሰው ለዮናስ ቅርብ
በሚሆነው ነገር አስተማረው እግዚአብሔር እንዲህ ነው የሚያስተምረው ፡፡ እንደ ክፉ መምህር ሰው የማይገባውን አምጥቶ አይደለም
የሚያስተምረው፡፡ ሰውየው በሚገባው አቅሙ በሚችለው መጠን ያስተምረዋል ስለዚህ የእግዚአብሔርን አስተማሪነት የምንረዳበት ጾም ነው፡፡
በመሆኑም የነነዌ ጾምን ከልባችን ሆነን ከጸሎት ጋር ብንጦመው እግዚአብሔር በረከትን ይሰጠናል ቁጣውን ወደ ምሕረት መዓቱን ወደ ቸርነት
ይመልሰናል የታዘዘው መቅሰፍት ካለ ያስቀርልናል ይህን እንድናስብ አባቶታችን ይህችን ጾም እንድንጾም አዘውናል፡፡ ስለዚህ ሁላችንም እንደ ነነዌ
ሰዎች ንስሐ ገብተን እራሳችንን አስተካክለን ሥጋ ወደሙን ተቀብለን ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር እንደንችል የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል
ማርያም አማላጅነት አይለየን፡፡

Kolladeba MedhaneAlem Church ቆላድባ መድሀኒአለም ቤተክርስቲያን

ጾመ ነነዌ

" የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው


ይፈርዳሉ ፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፡፡" (ማቴ
፲፪፥፵፩)
ይህንን የተናገረው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ነው፡፡ ጌታችን ለዚህ ትምህርቱ መነሻ ያደረገው የጻፎችን
እና የፈሪሳውያንን ጥያቄ ነው፡፡ "መምህር ሆይ ከአንተ
ምልክት ልናይ እንወዳለን" ቢሉት "ክፉና አመንዝራ
ትውልድ ምልክት ይሻል ፤ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት
በቀር ምልክት አይሰጠውም ። ዮናስ በአሳ አንበሪ ሆድ
ሦስት ቀንና ሌሊት አንደነበረ የሰው ልጅም በምደር ልብ
ሦስት ቀንና ሌሊት ይሆናል፡፡የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን
ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይፈርዳሉ ፤ በዮናስ ስብከት
ንስሐ ገብተዋልና፡፡ እነሆ ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ"
ብሏቸዋል፡፡ (ማቴ ፲፪፥፵፩) ጻፎችና ፈሪሳውያን ምልክት
መጠየቃቸው ይገርማል! የተሰጣቸውን ምልክት
ሳይጠቀሙ እና በሚያዩአቸው ተአምራት ሳያምኑ ሌላ
ምልክት መሻታቸው ይደንቃል! አልተረዱትም እንጂ የእርሱ
በመካከላቸው መገኘት በራሱ ምልክታቸው ነበረ:: "ስለዚህ
ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ ድንግል ትጸንሳለች
ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ
ትጠራዋለች" አንዳለ ነቢዩ (ኢሳ ፯፥፲፬ )። ሰማያዊው
መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ያበሰራት እመብርሃን
ምልክታቸው ነበረች፤ በድንግልና ጸንሳ በድንግልና
የወለደች እመቤታችን ምልክታቸው ነበረች፤ በጌታችን
ልደት ወደ ቤተልሔም ወርደው የዘመሩ ቅዱሳን
መላእክትም ምልክቶቻቸው ነበሩ፤ "የተወለደው የአይሁድ
ንጉሥ ወዴት ነው" እያሉ የመጡት ሰብአ ሰገልም
ምልክቶቻቸው ነበሩ፡፡ ከዚህም በላይ በመካከላቸው ሆኖ
ማየት ለተሳናቸው ዓይን ሲሰጥ፣ መስማት የተሳናቸው
እንዲሰሙ ሲያደርግ፣ ለምጻሞችን ሲያነጻ እና ሙታንን
ሲያስነሳ እያዩ እንደገና ሌላ ምልክት አምጣ ማለታቸው
የሚገርም ነው! ለዚህም ነው "ክፉና አመንዝራ ትውልድ
ምልክትን ይሻል" ብሎ ወደ ነነዌ ሰዎች ትምህርት
የወሰዳቸው፡፡

ነነዌ ማናት?
ነነዌ በሰሜናዊ ኢራቅ የምትገኝ በጤግሮስ ወንዝ
አቅራቢያ የተከተመች ከተማ ነበረች፡፡ ከጤግሮስ
በስተምዕራብ ሞሱል የተባለ ከተማ አለ፡፡ከባግዳድ እና
ባስራ ቀጥሎ ሦስተኛው የኢራቅ ትልቅ ከተማ ነው፡፡ ነነዌ
የምትገኘው ከሞሱል ከተማ ትይዩ ከጤግሮስ
በስተምሥራቅ ነው፡፡ ሞሱሉንና ነነዌን የሚለያቸው
የጤግሮስ ወንዝ ነው፡፡ አሁን በአምስት ድልድዮች ከአንዱ
ከተማ ወደሌላው መሻገር ይቻላል፡፡ የጥንቷ ነነዌ አሁን
ሁለት ክፍል አላት፡፡አንዱ ኩኒክ ሲባል ሁለተኛው ናቢዩኑስ
(ነቢዩ ዮናስ) ይባላል፡፡ናቢዩኑስ አሁን ድረስ አረቦች
በቅዱስ ስፍራነት ስለያዙት አይነካም፡፡ኩኒክ ግን ብዙ
ጥናት ተካሂዶበታል፡፡
ነነዌን ማን መሰረታት?
ነነዌን ከጥፋት ውሃ በኋላ የኖኅ የልጅ ልጆች
እንደመሰረቷት ተጽፏል፡፡ "አሦርም ከዚያች አገር ወጣ
፤ነነዌንም የርሆቦትን ከተማ ካላህን በነነዌና በካላህም
መካከል ሬሴንን ሰራ፡፡" (ዘፍ ፲፥፲፩)
ነነዌ በመጽሐፍ ቅዱስ ምን ታሪክ አላት?
ነነዌ በንጉሡ በሕዝቅያስ ዘመን እግዚአብሔርን ተገዳድሮ
በገዛ ልጆቹ እጅ የተገደለው የሰናክሬም አገር ናት፡፡
"የአሦርም ንጉሥ ሰናክሬም ተነስቶ ሄደ፤ ተመልሶም
በነነዌ ተቀመጠ፤ በአምላኩም በናስራክ ቤት ሲሰግድ
ልጆቹ አድራሜሌክና ሳራሳር በሰይፍ ገደሉት፡፡" (፪ኛ ነገ
፲፱፥፴፭-፴፮)፡፡ ነነዌ ነቢዩ ናሆም ደጋግሞ ያነሳት ከተማ
ናት፡፡(ናሆም ፩፥፩-፲፬ ፣ ናሆም ፪፥፰ ፣ ናሆም ፫፥፩)
ነቢዩ ናሆም መጽሐፉን ሲጀምር "ስለነነዌ የተነገረ ሸክም"
ብሎ ነው ፡፡ ነቢዩ ሶፎንያስም ነነዌን ከኢትዮጵያ ጋር
በአንድ ምዕራፍ አንስቷታል፡፡" እናንተም ኢትዮጵያውያን
በሰይፌ ትገደላላችሁ፤ እርሱም በሰሜን ላይ እጁን
ይዘረጋል ፤ አሦርንም ያጠፋል ፤ ነነዌንም ባድማ
እንደበረሃም ደረቅ ያደርጋታል" (ሶፎ፪፥፲፬)፡፡
ይህች ነቢያት ደጋግመው ያነሷት ከተማ በነቢዩ በዮናስ
ደግሞ የበለጠ ታውቃለች፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን
የነነዌ ሰዎች ቢበድሉ እና በኃጢአት ቢተዳደፉ፣ ይመለሱ
ዘንድ ወድዶ ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ሄዶ
እንዲያስተምራቸው አዝዞታል፡፡ "የእግዚአብሔርም ቃል
ወደአማቴ ልጅ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ፡፡ ተነስተህ
ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደነነዌ ሂድ፤ ክፋታቸው
ወደፊቴ ወጥቷልና በእርሷም ላይ ስበክ፡፡" (ዮናስ ፩፥፩-
፫ ) የነነዌ ሰዎች በደላቸው በዝቶ ነበርና፣ ስርቆቱ፣
ዝሙቱ ፣ ሐሰቱ፣ ግድያው፣ አምልኮ ጣኦቱ፣ ግፉና በደሉ
ምድሪቱን ስለሞላት እግዚአብሔር አምላክ "ክፋታቸው
ወደፊቴ ወጥቷል" ብሎ ተናገረ ፡፡ ለእግዚአብሔር ጥሪ
የዮናስ መልስ ግን የተለየ ነበረ፡፡ አንተ መሐሪ ነህ፤ እኔ
ተናግሬ አንተ ምረሐቸው ቢድኑ ሐሰተኛ ነቢይ
ታስብለኛለህ ብሎ ከእግዚአብሔር ፊት ይኮበልል ዘንድ
ተነሳ፡፡ "ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ወደ ተርሴስ
ይኮበልል ዘንድ ተነሳ… ወደ ዩኢዩጴ ወረደ። ወደ ተርሴስ
የምታልፍ መርከብ አገኘ፤ ከእግዚአብሔርም ፊት ኮብልሎ
ከእነርሱ ጋር ወደተርሴስ ይሄድ ዘንድ ዋጋ ሰጥቶ
ገባ" (ዮና ፩፥ ፫)፡፡ አሁን ከፀሐይ መሰወር ይቻላል? አሁን
እግዚአብሔር የሌለበት ቦታ አለን? ቅዱሳን አበው "ዮናስ
አባቱን አዳምን መሰለ፡፡አዳም ከእግዚአብሔር ይሰወር
ዘንድ ዛፍ ስር እንደተሸሸገ ዮናስም መርከብ ስር ተሸሸገ"
ይላሉ፡፡
በእውነት ዮናስ የዋህ ነው፤ እንዲያው ገንዘቡን አወጣ፤
ጉልበቱንም ጨረሰ፡፡ቅዱስ ዳዊት ከእግዚአብሔር መሰወር
እንደማይቻል ሲነግረን እንዲህ ብሏል፡፡ "አቤቱ
ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ
ወደሰማይ ብወጣ አንተ በዚያ ነህ ወደሲኦልም ብወርድ
አንተ በዚያ አለህ እነደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ እስከ
ባሕር መጨረሻም ብበርር በዚያ እጅህ ትመራኛለች፤
ቀኝህም ትይዘኛለች" (መዝ ፻፴፰፥፯-፲)፡፡ እግዚአብሔር
ያዘዘውን መንገድ ትቶ በራስ መንገድ መጓዝ ተገቢ
አይደለምና እግዚአብሔር አምላካችን ለዮናስ መታዘዝን
ያስተምር ዘንድ ግዑዛን ፍጥረታቱ ዮናስን እንዲይዙት
አዘዘ፡፡ "እግዚአብሔር በባሕሩ ላይ ታላቅ ንፋስ አመጣ፤
በባሕሩ ላይም ታላቅ ማዕበል ሆነ። መርከቢቱም ልትሰበር
ቀረበች፤ መርከበኞችም ፈሩ፤ እያንዳንዱም ወደ አምላኩ
ጮኸ፤ መርከቢቱ እንድትቀልላቸው በውስጧ የነበረውን
ዕቃ ወደ ባሕር ጣሉት፤ ዮናስ ግን ወደ መርከቡ ውስጠኛ
ክፍል ወርዶ ነበር፤ በከባድ እንቅልፍም ተኝቶ ነበር።" (ዮና
፩፥፬) ለእግዚአብሔር ሁሉ ይታዘዝለታል፤ ንፋሱ፣ ባሕሩ፣
ማዕበሉ… እርሱ የሁሉ አስገኝ ነውና፡፡ ዮናስን ያሳፈሩት
መርከበኞች የሚደነቁ ናቸው፡፡ ታሪካቸው መልካም ልብ
እንዳላቸው ያሳያል፤ እንዴት?
1. መርከቡ ሲናወጥ ለጸሎት መቆማቸው የልባቸውን
መልካምነት ያሳያል፡፡
2. የመርከቧ አለቃ ዮናስን የቀሰቀሰበት ቃል እንዲህ
የሚል
ነበር ፡- "እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ያስበን እንደሁ ተነስተህ
አምላክህን ጥራ" (ዮና ፩፥፮ )፡፡ይህም የልቦናውን ቅንነት
የሚያሳይ ነው፡፡
3. መርከበኞቹ ባሕሩ የተናወጠው እና ማዕበሉ የተነሳው
በኃጢአታችን ነው ማለታቸውም ግሩም ልብ እንዳላቸው
ያሳያል፡፡ "እርስ በእርሳቸውም ይህ ክፉ ነገር በማን
ምክንያት እንዳገኘን አናውቅ ዘንድ ኑ እጣ አንጣጣል
ተባባሉ" (ዮና ፩፥፯ )፡፡ ይህ የሚገርም ነው! መርከበኞቹ
ያናወጠን የአየሩ ጸባይ ነው፤ የነፋሱ ሁኔታ ነው አላሉም።
ይህ መናወጥ የደረሰብን በበደላችን ነው አሉ እንጂ!
አንዲህ ያለ ወደ ራስ የሚመለከት ልብ ለሁላችን ያድለን፡፡
4. መርከበኞቹ በሌላ ሰው ላይ ለመፍረድ የማይቸኩል
ልብ
ነበራቸው፤ እናም ዕጣ እንጣጣል ተባባሉ! "ዕጣም
ተጣጣሉ ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ" (ዮና፩፥፯)፡፡
በዚህ ጊዜም አንተ ኃጢአተኛ ከእኛ ተለይ ብለው
ሊፈርዱበት አልወደዱም፡፡ መርከቧ እየተናወጠች እነርሱ
በአክብሮት ለዮናስ ጥየቄያቸውን ደረደሩለት እንጂ! "ይህ
ክፉ ነገር በምን ምክንያት እነዳገኘን አባክህ ንገረን፤
ሥራህ ምንድን ነው? ከወዴት መጣህ? አገርህ ወዴት
ነው? ከማን ወገን ነህ ?" (ዮና ፩፥፰) ፡፡ ዮናስ ስለ እራሱ
አንዲህ አለ፤ "እኔ ዕብራዊ ነኝ ባሕሩንና የብሱን
የፈጠረውን የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን
አመልካለሁ….ከእግዚአብሔር ኮብልያለሁ…" (ዮና፩፥፱)፡፡
ዳግመኛም ይህን ስለምን አደረግህ? አሉት ።ማዕበሉ
አልቆመም፤ እጣው ዮናስ ላይ ወጥቷል፤ ቢሆንም
መርከበኞቹ ግን አልፈረዱበትም! "አትፍረዱ
ይፈረድባችኋል" የሚለውን ቃል ሳይማሩት ከልባቸው
መልካምነት የተነሳ ለፍርድ አልተነሱም፡፡ ይልቁን ዮናስን
ስለራሱ እንዲፈርድ ተውት አንጂ። "ሞገዱ ከእኛ ጸጥ
አንዲል ምን እናድርግብህ ?" ነው ያሉት…. "ዮናስም
አንስታቸሁ ወደባሕር ጣሉኝ፤ ባሕሩ ጸጥ ይልላቸኋል" (ዮና
፩፥፲፩-፲፪) አላቸው፡፡
5. መርከበኞቹ ዮናስ በራሱ ላይም ከፈረደ በኋላ
ከመርከቡ
አንስተው ሊወረውሩት አልወደዱም፡፡ እንዲያውም "ወደ
ምደር ለመድረስ አጥብቀው ቀዘፉ" ነው የሚለው ፡፡ (ዮና
፩፥፲፫) የባሕሩ መናወጥ ይበልጥ ሲበረታ ግን፣
መርከበኞቹ "አቤቱ ንጹሁን ደም በእኛ ላይ አንዳታደርግ
እንለምንሃለን" ካሉ በኋላ ዮናስ በራሱ ላይ የፈረደውን
አደረጉበት፡፡ ልክ ዮናስ ወደ ባሕር ሲወረወር ማዕበሉ ጸጥ
አለ! መርከበኞቹና መርከቧም ፍጹም ሰላም አገኙ፡፡
ወደ ባሕር የተወረወረው ዮናስ ሌላ ነገር ገጠመው ።
"እግዚአብሔርም ዮናስን የሚውጥ ታላቅ አሳ አሰናዳ፤
ዮናስም በአሳው ሆድ ውሰጥ ሦስት ቀንና ሌሊት
ነበረ፡፡" (ዮና ፪፥፩-፲፩) ዮናስ በአሳው ሆድ ውስጥ
ለጸሎት ቆመ ! አሳውም እግዚአብሔር እንዳዘዘ ዮናስን
ወስዶ በነነዌ ተፋው፡፡ ሩህሩህና ይቅር ባይ የሆነው
አምላካችን እግዚአብሔር ከፊቱ የኮበለለ ዮናስን በኃይሉ
መልሶ ለአገልግሎት አቆመው ። "ዮናስም ተነስቶ እንደ
አግዚአብሔር ቃል ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነዌም የሦስት ቀን
መንገድ ያህል ታላቅ ከተማ ነበረች ፤ ዮናስም የአንድ ቀን
መንገድ ያህል ወደ ከተማይቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤
ጮሆም በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች አለ" (ዮና
፫፥፫)
የሚገርመው ነገር የነነዌ ሕዝብ መምህር ያጣ፣ ነገር ግን
ቢማር የሚመለስ ልብ ያለው ሆኖ ተገኘ! ዮናስ ስብከቱን
አንደጀመረ ሕዝቡ ሁሉ በንስሐ አና በጾም በእግዚአብሔር
ፊት ቆሙ፡፡ ንስሐው እና ጾሙ ከተርታው ሕዝብ አስከ
ንጉሡ ድረስ ነበረ፡፡ "የነነዌ ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤
ለጾም አዋጅ ነገሩ፤ ከታላቁ አሰከ ታናሹ ማቅ ለበሱ፡፡
ወሬው ወደ ንጉሡ ደረሰ፡፡ አርሱም ከዙፋኑ ተነስቶ
መጎናጸፊያውን አወለቀ፤ ማቅም ለበሰ፤ በአመድም ላይ
ተቀመጠ፤ አዋጅም አስነገረ፡፡ በነነዌም ውሰጥ የንጉሡንና
የመኳንንቱን አዋጅ አሳወጀ፡፡ እንዲህም አለ ሰዎችና
እንስሶች ላሞችና በጎች አንዳች አይቅመሱ፤ አይሰማሩ፤
ውኃም አይቅመሱ፡፡ ሰዎችና እንስሶች በማቅ ይከደኑ፤
ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩሁ፡፡ ሰዎችም ሁሉ
ከክፉ ሥራቸውና ከግፍ ይመለሱ፤ እኛ አንዳንጠፋ
እግዚአብሔርም ተመልሶ ይጸጸት እንደሆነ ከጽኑ ቁጣውም
ይመለስ እንደሆን ማን ያውቃል?" ( ዮና ፫፥፭)
የነነዌ ሕዝብ ታላቅ ንሰሐን አደረገ ፡፡ በእውነቱ ግሩም
ድንቅ ንስሐ ነው። በአንድ ጊዜ ከ ፻፳ ሺህ የሚበልጠው
የነነዌ ነዋሪ በጾም ወደ እግዚአብሔር ተመለሰ፡፡ ጾሙ
ጡት የሚጠቡ ሕጻናት እና በበረት ያሉ እንስሳትንም
ጭምር ያሳተፈ ነበር፡፡ በነነዌ የተጾመው ከጥሉላት ብቻ
አልነበረም፣ ከመላው ምግብ አንጂ! በነነዌ የተጾመው
ከምግብ ብቻ አልነበረም፤ ከማንኛውም ክፉ ሥራ እንጂ!
ለመሆኑ ይህን ቁጥሩ እጅግ የበዛ የነነዌን ሕዝብ
በእግዚአብሔር ፊት በጾም ያንበረከከው የስንት ሰዓት
ስብከት ነበር? ስንት ገጽ የንስሐ መጽሐፍ ነበር? ስንት
መንፈሳዊ ጉባኤ ነበር? ስንት የንስሐ መዝሙር ነበር? ስንት
ሰባኪያን ነበሩ? የሚገርመው ሰባኪው አንድ ዮናስ፣
ስብከቱም አንድ አረፍተ ነገር ነበር፡፡ "በሦስት ቀን ውሰጥ
ነነዌ ትገለበጣለች" የሚል ፡፡ (ዮና ፫፥፬) ስብከቱም
የአጭር ሰዓት ስብከት ነበር፡፡ በእውነቱ አንዲህ ያለ ሕዝብ
በአኛ ላይ ይፈርዳል፡፡ ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ቀን ንስሐ
ግቡ እየተባለን ንስሐ ሳንገባ በቀረን በእኛ ላይ ይፈርዳሉ፡፡
ስንት ቅዱሳት መጽሐፍ ተ ጽፈውልን፥ መጽሐፍ ቅዱሱ፣
ድርሳኑ፣ ገድሉ፣ ተአምራቱ፣... በዘመናችን ደግሞ
በመጽሔቱ፣ በጋዜጣው፣ በድረ ገጹ ... ሁሉ ቀርቦልን
ንስሐ ሳንገባ በቀረን በእኛ ላይ ይፈርዳሉ፡፡ በርካታ
ጉባኤያት ተዘጋጅተውልን፣ ሺህ ጊዜ የንስሐ መዝሙር
ተዘምሮልን፣ ንስሐ ሳንገባ በቀረን በእኛ ላይ ይፈርዳሉ፡፡
በእርግጥ ጌታችን ለዚህ ነው "የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን
ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይፈርዳሉ፤ በዮናስ ስብከት
ንስሐ ገብተዋልና" ያለን ፡፡ የነነዌ ሰዎች ከኖኅ ዘመን
ሰዎች ይለያሉ፤ የነነዌ ሰዎች ከሰዶም ሀገር ሰዎችም
ይለያሉ፡፡ የኖኀ ዘመን ሰዎች ኖኅን ባይሰሙት በፈላ ውኃ
ጠፍተዋል፡፡ የሰዶም ሰዎችም ሎጥን ባይሰሙት በእሳት
ጠፍተዋል፡፡ የነነዌ ሰዎች ግን ዮናስን ቢሰሙት ድነዋል ፤
ይህም ሰምቶ በመጠቀምና ባለመጠቀም መካከል
ያለውን ልዩነት ያሳየናል፡፡
የነነዌ ሰዎች ጾምና ጸሎት በእግዚአብሔር ፊት ደረሰ፤
ምሕረትም ተደረገላቸው፡፡ "እግዚአብሔርም ከክፉ
መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ ፤
እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር
ተጸጽቶ አላደረገውም" (ዮና ፫፥፲)፡፡ ነነዌ በሦስት ቀን
ጾም ዳነች፡፡ የዚያ ታላቅ ሱባኤ ማብቂያው ደስታ ሆነ፡፡
በዚያ ቀን በሰማይ አንዴት ያለ ደስታ ሆኖ ይሆን! "ንስሐ
ከማያስፈልጋቸው ዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ
በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ታላቅ ደስታ ይሆናል።
"(ሉቃ ፲፭፥፯) የሚገርመው በሰማይና በምድር ታላቅ
ደስታ በሆነበት በዚያ ቀን አንድ ሰው ብቻ ነበር አዝኖ
የተገኘው። "ይህም ዮናስን ከቶ ደስ አላሰኘውም፤ እርሱም
ተቆጣ" (ዮና ፬፥፩) ሕዝብ ሲድን፣ ሕዝብ በሰማይ
ያንዣበበ እሳት ሲመለስለት የእግዚአብሔር ነቢይ እንዴት
ይቆጣል?! አበው ይህንን የዮናስ ቁጣ በሉቃስ ፲፭ ላይ
ካለው የጠፋው ልጅ ታላቅ ወንድም ቁጣ ጋር
ያመሳስሉታል። (ሉቃ፲፭፥፲፩-፴፪)" ተቆጣ ሊገባም
አልወደደም" ይላል፡፡ የጠፋው ልጅ አባት ግን እንዲህ
ነው ያለው "ይህ ልጄ ሞቶ ነበር፤ ሕያው ሆኗል፤ ጠፍቶ
ነበር ተገኝቷል፤ ፍስሐ እናድርግ!"
ዮናስ በየዋህነቱ ሐሰተኛ ነቢይ ልባል ነው ብሎ ቢቆጣም
እግዚአብሔር ሊያስተምረው ወደደ። እናም ዮናስ ባረፈበት
ቦታ ላይ ቅል አበቀለለት። "በራሱ ላይ ጥላ እንድትሆን
እግዚአብሔር ቅሊቱን በዮናስ ላይ ከፍ ከፍ አደረጋት፤
ዮናስ ስለቅሊቱ እጅግ ደስ አለው፤ በነጋው ወገግ ባለ
ጊዜ እግዚአብሔር ትልን አዘጋጀ፤ እርስዋም ቅሊቱን
እስክትደርቅ ድረስ መታቻት፤ ፀሐይም በወጣ ጊዜ
እግዚአብሔር ትኩስ የምሥራቅ ንፋስ አዘጋጀ፤ ዮናስም
እስኪዝል ድረስ ፀሐይም ራሱን መታው" (ዮና ፬፥፮-፰)
በዚህ ያዘነ ዮናስ ከቁጣው ብዛት ሞትን ለመነ፡፡ አሁንም
እግዚአብሔር ዮናስን እንዲህ ብሎ አስተማረው። "አንተ
ትበቅል ዘንድ ላልደከምህባት፣ ላላሳደግሃትም በአንድ
ሌሊት ለበቀለች በአንድ ሌሊትም ለደረቀችው ቅል
አዝነሃል፤ እኔስ ቀኝና ግራቸውን የማይለዩ ከአንድ መቶ ሃያ
ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና እንስሳት ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ
ለነነዌ አላዝንምን ? አለው" (ዮና ፬፥፲)
የነነዌ ታሪክ እግዚአብሔር አምላካችን ሰውን ምን ያህል
እንደሚፈልግ የሚያስተምር ነው፡፡ እርሱ አምላካችን
በርህራሄው መርከበኞቹን፣ ዮናስን፣ የነነዌ ሰዎችን በሙሉ
እንዴት እንደፈለገ እና እንዴት እንዳዳነ ስናይ ለእኛ
ለሁላችን ያለውን ፍጹም ፍቅር እንረዳለን፡፡ ብርሃነ አለም
ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረ "እርሱ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና
እውነቱን ወደማወቅ እንዲደርሱ የሚወድ የፍቅር አምላክ
ነው" (፩ጢሞ ፪፥፬) ፡፡ በእውነተኛ ንስሐ፣ በተሰበረ ልብ፣
በጾምና በጸሎት ወደ እርሱ ለሚመለሱ ፍጹም ይቅርታን
የሚሰጥ ነው፡፡ የነነዌ ታሪክ የጾምን ፍጹም ኃይል እና ዋጋ
የሚያስተምረን ነውና ይህንኑ እያሰብን ጾመን
እንድንጠቀም የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን
አማላጅነት፣ የቅዱሳን ጸሎትና ምልጃ ከሁላችን ጋር ይሁን

ዘመናዊ አገር ኢራቅ/ፐ ኢራን

አሦር
ጥንታዊ አገር

በኦሪት ዘፍጥረት 10፡11 መሠረት የሴም ልጅ አሦር ከሰናዖር ወጥቶ ነነዌንና ሌሎችን ከተሞች ሠራ። አንዳንድ


የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ግን ከፊተኛው ቁጥር ከ 10፡10 በመውሰድ አድራጊው እንደ ናምሩድ ቆጥረውት፣ ናምሩድ
እራሱ ወደ አሦር (ወደ ሀገሩ) ወጥቶ እኚህን ከተሞች እንደ ሠራ ይላሉ። በጥንታዊ የግሪክ ታሪክ ጸሃፊዎች
ዘንድ ኒኑስ የነነዌ መስራችና የአሦር መጀመርያ ንጉስ ነበረ።
ነነዌ ከጥንት ጀምሮ ከአሹር ከተማ-አገር ይገዛ ነበር። እንደ አሹር ከ 1440 እስከ 1366 ዓክልበ. ድረስ
በሚታኒ ይቆጣጠር ነበር። ትልቅ ከተማ ነበረ።
በ 775 ዓክልበ. አካባቢ ነቢዩ ዮናስ ወደ ነነዌ ሂዶ የአሦር ሰዎች ወደ ንሥሐ እንዳመጣቸው በመጽሐፈ ዮናስ ይገለጻል።

ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሦስት ቀን ጾም የጾሙት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከተማዋም (ነነዌ)
‹‹

በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ ስትኾን መሥራቿም ናምሩድ ነው (ዘፍ.፲፥፲፩-፲፪)፡፡ ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር
መነሻ የሆነች፤ እጅግ ሰፊና ያማረች፤ የቅጥሯ ርዝመትም ፲፪ ኪሎ ሜትር የሚሸፈን ነበር፡፡ በከተማዋ ንጉሡ ሰናክሬም
ብዙ ሕንጻዎችን ገንብቶ ነበር (ዮናስ ፬፥፲፩)፡፡
በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸው በዝቶ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ሲል ዮናስ የስሙ ትርጓሜ ‹ርግብ› የሆነ
በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የነበረ ነቢይን ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር መክሮ፣ ዘክሮ
እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ሕዝብ ላከው (ሉቃ.፲፩፥፴)፡፡ ይህ ነቢይ መኖሪያው በገሊላ
በጋትሔፌር ድንበር ከተማ ነበረ፤ አባቱም አማቴ ይባላል፡፡ በዚያን ጊዜ ኢዮርብዓም ሶርያውያንን አባሮ የእስራኤልን
ድንበር እንዲመልስ ነቢዩ ዮናስ ትንቢትን ተናገረ (፪ኛነገ.፲፬፥፳፭፤ ዮናስ ፩፥፩)፡፡ ነቢዩ ኤልያስ ያስነሣው የሰራጵታዋ
መበለት ሕፃን ነቢዩ ዮናስ እንደ ሆነ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል (፩ኛነገ.፲፯፥፲፱)፡፡ መድኃኒታችን ክርስቶስም
የዮናስን ከዓሣ ሆድ መውጣት የራሱ ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎ ነግሮናል (ማቴ.፲፪፥፲፱-፵፪፤ ሉቃ.፲፩፥፴-፴፪)፡፡
እግዚአብሔር አምላክም ‹‹ሔደህ በነነዌ ላይ ስበክ›› ባለው ጊዜ ነቢዩ ዮናስ ‹‹አንተ መሐሪ ነህ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ
ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ››  ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡ እግዚአብሔርም
ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩ ነጋድያንም
ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ ጥፋቱን
ተገንዝቦ ‹‹ማዕበሉ በእኔ ምክንያት የመጣ ስለሆነ ንብረታችሁን ሳይሆን እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ›› ብሎ ተማጸናቸው፡፡
እነርሱም ‹‹ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ፣ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳይደረግብን አይሆንም›› አሉ፡፡ ወደ ባሕሩ ለመጣል
ዕጣ በተጣጣሉ ጊዜም ዕጣው በዮናስ ላይ ስለ ወጣ ነጋድያኑ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ
የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ወደ ነነዌ አደረሰው፡፡ እግዚአብሔር
የቅል ተክልን ምሳሌ በማድረግ ቅጠሉ በመድረቁ ዮናስ ባዘነ ጊዜ ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል
ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ሆኑ
ያሳዝኑኛል›› በማለት ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስሕተት መሆኑን አስረድቶታል፡፡
ዮናስም ነነዌ መሬት ላይ መድረሱን ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ አለመቻሉን ተረዳ፤ የነነዌ
ሰዎችንም ‹‹ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡ የነነዌ ሰዎችም ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ከጥፋት
አድኗቸዋል፡፡ ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ሆኖ ከላይ ታይቶአል፡፡ የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ
አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል (ትንቢተ ዮናስ)፡፡ ታኅሣሥ ፭ ቀን
የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ‹‹ወበልዐ አሐደ ኀምለ›› በማለት ንስሐ ያልገቡ አንድ አገር ያህል ሰዎች በእሳቱ እንደ
ጠፉ ይነግረናል፡፡

ጾመ ነነዌ የሦስት ቀን ሱባኤ ነው፤ በሦስት ቀናት ጾምና ጸሎት ንስሐ የገቡ የነነዌ ሰዎች ከጥፋት እንደ ዳኑ ሁሉ፣ በብሉይ
ኪዳን አስቴር ሦስት ቀን ጾማ፣ ጸልያ በእስራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች (አስ.፬፥፲፭-፲፮)፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከበዓል ስትመለስ ሕፃኑ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ላይ ጠፍቶአት ከሦስት
ቀን ፍለጋ በኋላ በቤተ መቅደስ አግኝታዋለች (ሉቃ.፪፥፵፮)፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሄሮድስ
በሰጠው ምላሽ መልስ ሦስት ቀን የሱባኤ ፍጻሜ መሆኑን ገልጿል (ሉቃ.፲፫፥፴፪)፡፡

ጾመ ነነዌ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሐሪነት የምናስታውስበት ጾም ነው፡፡ ይኸውም እኛ ፍጡራኑ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ
ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርገናል፡፡ ዮናስ ለስብከት ፈቃደኛ ባይሆን እንኳን እግዚአብሔር በተለየ
ጥበቡ እንዲሔድ አድርጎታል፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ሌላ የሚልከው ነቢይ አጥቶም አይደለም፤ እርሱንም ጭምር
ሊያስተምረው ስለ ፈለገ እንጂ፡፡ የነነዌ ሰዎች የተነሳሕያን ምሳሌ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ከገባ
እግዚአብሔር ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡ ለዚህም ነው ዮናስን ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል
ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ  ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ሆኑ
ያሳዝኑኛል›› ያለው፡፡
ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን ይህን እና ሌሎች አጽዋማትን እንድንጾም የወሰኑልን ያለ ምክንያት አይደለም፡፡
ሕጉ የተዘጋጀልን እንደ ነነዌ ሰዎች እኛም ጾመን፣ ጸልየን ከኃጢአታችን እንነጻ ዘንድ ነው፡፡ ዛሬ ዓለማችን በኃጢአት
ማዕበል እየተናወጠች ባለችበት ወቅት እኛም እንደ ነነዌ ሰዎች ከበደላችን ብንመለስ እና ንስሐ ብንገባ ቸሩ ፈጣሪያችን
እግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ ስለ ሆነ ‹‹ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ይቅር እላችኋለሁ፤›› ይለናል፡፡

ስለሆነም በነቢዩ ዮናስ ላይ የተደረጉ ተአምራትንና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመሆኑን በማስተዋል፣ ለነነዌ
ሰዎች የወረደውን ምሕረት በመገንዘብ ለእግዚአብሔርም ሆነ ለሃይማኖት አባቶች እና ለወላጆቻችን መታዘዝ ይገባናል፡፡
ስንጾምም እግዚአብሔር አምላካችን መዓቱን በምሕረት፣ ቍጣውን በትዕግሥት መልሶ በኃጢአት ለጠፋው ዓለም
ይቅርታውን ይልካል፡፡ በመጾማችን ራሳችን ከመዓትና ከመቅሠፍት ከመዳናችን ባሻገር በእኛ በደል ምክንያት አገራችን፣
ዕፀዋቱና እንስሳቱም ሳይቀር ከድርቅና ከቸነፈር ይተርፋሉና፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
ጾመ ነነዌ፤ ከየካቲት 7-9 (ከሰኞ-ረቡዕ)

📌 ነነዌ

✅ በጤግሮስ ወንዝ ምሥራቃዊ ቆሬ፥ ከዛሬዋ የሞሱል ከተማ በተቃራኒ ከባግዳድ በሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ 350 ኪ.ሜ
ርቀት ላይ የነበረች ታላቅ ከተማ ነች፤ ነነዌን በመጀመሪያ የቆረቆራት ናምሩድ ነው፡፡

📖ዘፍ 10፥11

✅ በጣም ሰፊ ነበረች “የቅጥሯም ዙሪያ በእግር የሦስት ቀን መንገድ ያህል ነበረ”

✅ እግዚአብሔር አምላካችን ነነዌን “ታላቂቱ ከተማ” በሚል ቅጽል ጠርቷል፤

📖ዮናስ 4፥11

✅ ስለ መጥፋቷ ነቢዩ ሶፎንያስ “...ነነዌንም ባድማ እንደ በረሃም ደረቅ ያደርጋታል” በማለት ትንቢት ተናግሮባታል፡፡

📖ሶፎ 2፥13

✅ እንደ ነቢያቱ ትንቢት ታላቋ ነነዌ ከ 300 ዓመታት በኋላ ጠፍታለች፤ የነነዌ ሰዎች በስብከተ ዮናስ አምነው ንስሐ
ገብተው ድነዋል፤ በዚህም ጌታችን በወንጌል ላይ ስለ ንስሓቸውና ስለ እምነታቸው /‹‹...የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ
ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና›› በማለት አመስግኗቸዋል፡፡

✅ ዮናስ ነቢየ አሕዛብ ወሕዝብ ዮናስ ማለት ርግብ የዋኅ ማለት ነው፤ በዳግማዊ ኢዮርብአም ዘመነ መንግሥት /825-
784 ቅ.ል.ክ./ በሰማርያ የነበረ ነው፡፡

📖2 ኛ ነገሥ 14፥25

✅ ቊጥሩ ከ 12 ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ነው፤ ነገዱ ከነገደ ይሳኮር ወገን ሲሆን፤ አባቱ አማቴ እናቱም ሶና(የሰራፕታዋ ደግ
ሴት የሆነችውና ቅዱስ ኤልያስን በዚያ በረሃብ ዘመን የመገበችው ናት)፡፡

✅ ኤልያስ በረሃቡ ዘመን ወደ ሰራፕታዋ መበለት ቤት በመሄድ "ውኃ አጠጪኝ ጥቂት ቁራሽም አምጪልኝ" አላት
‹‹ሕያው እግዚአብሔርን እፍኝ ዱቄት አለችኝ ጋግሬያት አንተም እኔም ልጄም (ዮናስ) በልተናት እንሞታለን›› አለችው፤
ኤልያስም "የረሀቡ ዘመን እስኪያልፍ ይበርክት" አላት፤ ከቤቷ ብትገባ ዱቄቱ በማድጋው፣ ዘይቱ በማሰሮው መልቶ
አገኘች፤ ከጥቂት ጊዜም በኋላ ልጇ ዮናስ ታሞ ሞተ፤ እናቱም ሄዳ ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስን "ሳይገባኝ ከቤቴ ገብተህ
ኀጢአቴን ተመራምረህ ልጄን ትገድልብኝ" አለችው፤ ነቢዩ ኤልያስም ወደ አምላኩ ሰባት ጊዜ ጸሎት አድርሶ ዮናስን
ከሞተ በኋላ አስነሥቶታል፡፡

📖1 ኛ 18፥10-24

✅ ነቢዩ ኤልያስ ካረገ በኋላ ደግሞ ሁሉም በተሰጣቸው አገልግሎት ተሠማርተው እግዚአቤሔርን አገለገሉ፤ ነቢዩ ዮናስ
አርባ ዓመት ሲሞላው ሀብተ ትንቢት ተሰጥቶት ማስተማር ጀመረ፡፡
✅ የሰማርያውን ንጉሥ ኢዮርብአምን ጠቃሚ ምክር በመለገስ የእሥራኤልን ድንበር ከሔማት እስከ ዐረብ ባሕር ድረስ
እንዲይዝ አድርጎታል፡፡

📖2 ኛ ነገሥ 14፥25

✅ ነቢዩ ዮናስ ምንም እንኳን የእስራኤል ነቢይ ቢኾንም ከምድረ እስራኤል ውጪ በነነዌ ስላስተማረ ነቢየ አሕዛብ
ወሕዝብ ይባላል፡፡

✅ የነነዌ ሰዎች ኀጢአት ከመሥፈርቱ በማለፉ፤ የእግዚአብሔር ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ መጣ “ተነሥተህ ወደ


ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ የክፋታቸውም ጩኸት ወደ ፊቴ ወጥቷልና ለእነርሱ ስበክ” አለው፤ ዮናስ ግን የፈጣሪው
መሐሪነት፥ ቸርነት መስፈርት እንደሌለው ያውቃልና፤ እርሱ ቢምራቸው ማን ለቃሉና ለትንቢቱ ይገዛል፤ እኔም ሐሰተኛ
ነቢይ ልባል አይደለምን ብሎ አልሔድም አለ፤ እግዚአብሔር እየደጋገመ ሲናገረው ግን ዮናስ የዋሕ ነበረና እንዲህ
የሚዘበዝበኝ ከፊቱ ብቀመጥ አይደል ብሎ ከፊቱ ለመሰወር ወደ ተርሴስ በመርከብ ኮበለለ፡፡

✅ ዮናስ ወደ መርከብ ገብቶ ጕዞ ከተጀመረ በኋላ በእርሱ ምክንያት ታላቅ ማዕበል ተነሳ፤ በመርከቡ ውስጥ
የተሣፈሩትም ሊያልቁ ሆነ፤ ሌሎች እንዲያ እየተናወጡ እርሱ ግን የእምነት ሰው፥ የዋሕና ቅን ስለሆነ ተረጋግቶ በመርከቡ
ውስጥ ተኝቶ ነበር፤ መርከበኞቹም እጅግ ሲጨንቃቸው እያንዳንዳቸው ወደ አምላካቸው ጮሁ፤ መርከቢቱም
እንድትቀልላቸው በውስጧ የነበረውን ዕቃ ሁሉ እያወጡ ወደ ባሕር ጣሉ፤ ባሕሩ ጸጥ ሊል ስላልቻለ ዮናስንም ቀስቅሰው
“ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንዳገኘን እናውቅ ዘንድ፤ ኑ ዕጣ እንጣጣል ተባባሉ፡፡”

✅ እጣ ቢጥሉ በዮናስ ላይ ወጣ፤ ዮናስም በራሱ ተጠያቂነት፤ ‹‹የእኔ ጥፋት ስለ ሆነ ወደ ማዕበሉ ጣሉኝ›› አላቸው፤
መርከበኞች ግን ዮናስን ለመታደግ የሚችሉትን ሁሉ አደረጉ፤ መርከቢቱ ወደ ምድር ትጠጋላቸው ዘንድ አብዝተው
ቀዘፉ፤ የእርሱ ወደ ባሕር መጣል ፈቃደ እግዚአብሔር ስለሆነ ልፋታቸው ሁሉ ከንቱ ሆነ፤ ሁሉም አንድ ሆነው ወደ
እግዚአብሔር ጮኹ "አቤቱ አንተ እንደ ወደድህ አድርገሃልና ስለዚህ ሰው ነፍስ አታጥፋን፤ ንጹሕ ደምንም
አታድርግብን” በማለት እያዘኑ በሐምሌ 15 ቀን ወደ ባሕሩ ጣሉት፤ ባሕሩም ከመናወጥ ጸጥ አለ፡፡

✅ ነቢዩ ወደ ባሕር ቢጣልም የእግዚአብሔር ጥበቃ አልተለየውምና ዮናስን ይውጠው ዘንድ ታላቅ ዓሣ አንበሪን
አዘዘለት፤ ነቢዩ ዳዊት ‹‹እግዚአብሔር የቀባውን እንዳዳነው ዛሬ ዐወቅሁ›› እንዳለ የመረጠውን ነቢይ ለማዳን ዓሣ
አንበሪን አዘጋጀለት፡፡

✅ ዮናስም በአሣ አንበሪ ሆድና በማዕበል ውስጥ ሆኖ ለ 3 ቀናት ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ በመጽሐፍ ቅዱስም በዓሣ
ሆድ ተጕዞ ያስተማረ፥ ትንቢትም የተናገረ የመጀመሪያ ነቢይ ሆነ፤ ዓሣ አንበሪው ዮናስን በሆዱ ቋጥሮ የሦስት ቀን ጎዳና
በባሕር ውስጥ ገስግሶ በ 3 ኛው ቀን ነነዌ ዳር ደረቅ መሬት ላይ አራግፎ ተፋው፡፡

✅ ዮናስ በግዙፉ አሣ አነበሪ ውስጥም ያለ እንቅልፍ በጾም፥ በጸሎትና በምስጋና ለ 3 ቀናት መቆየቱ ለክርስቶስ ትንሣኤ
ምሳሌ ነው፤ ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ 3 ቀን 3 ሌሊት ኑሮ ሙስና (ጥፋት) ሳያገኘው መውጣቱ አዳምና ልጆቹን ለማዳን
የመጣው ጌታችንም 3 መዓልትና 3 ሌሊት በከርሠ መቃብር አድሮ ከሙታን ተለይቶ የመነሣቱ ምሳሌ ነው፡፡

✅ ለዚህም ራሱ ጌታችን በወንጌል ‹‹ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፤ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት
አይሰጠውም፤ ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ 3 ቀንና 3 ሌሊት እንደ ነበረ፤ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ 3 ቀንና 3 ሌሊት
ይኖራል፡፡

✅ የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፤ እነሆም
ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ››
✅;እግዚአብሔር አምላክም ለሁለተኛ ጊዜ ዮናስን ወደ ነነዌ እንዲሄድ አዘዘው፤ “ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ
ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ የነገርሁህንም የመጀመሪያውን ስብከት ስበክላት” አለው፡፡

✅ ዮናስም እንቀድሞው ሳያንገራግር ወደዚህች ከተማ ገብቶ እንዲህ እያለ ‹‹እስከ ሠሉስ ዕለት ትትገፈታእ ነነዌ ዐባይ
ሃገር›› (እስከ ሦስት ቀን ድረስ ነነዌ ትገለበጣለች) ንስሐን ሰበከ፥ አስተማረ፡፡

✅ የነነዌ ሰዎችም ኃጢአታቸውን አምነው (ከኃጢአቱ የሌሉበትም ቢሆን መከራው ስለማይቀርላቸው) ከመሪ እስከ
ተመሪ፤ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሁነው፤ ንጉሡም በከተማዋ የጾም አዋጅ አስነግሮ፥ ከዙፋኑ
ወርዶ፤ ሕዝቡም ማቅ ለብሰው አመድ ነስንሰው በፍጹም ልባቸው አዝነው አልቅሰው ሕፃናት ከጡት ከብቶችም ከሣር
መሠማራት ተከልክለው ያለምግብ በበረት ተዘግተው፤ ጾሙንም በልባዊ ጸጸት ራስን ዝቅ በማድረግና በማዋረድ ንስሓ
ገቡ “የነነዌ ሰዎችም እግዚአብሔርን አመኑ”

✍‹‹... ለጾም ዐዋጅ ነገሩ፤ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ፤ ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም
ከዙፋኑ ተነሥቶ መጎናጸፊያውን አወለቀ፤ ማቅም ለበሰ፤ በአመድም ላይ ተቀመጠ...” እንዳለ ከአምላካችን ምሕረትን
አገኙ፡፡

📖ዮናስ 3፥5-9፡፡

✅ ነቢዩ ዮናስም ይህን አይቶ በየዋሕነቱ ‹‹እንግዲህማ ሊምራቸው ነው፣ እኔም ሐሰተኛ ነቢይ ልባል ነው›› ብሎ እያዘነና
ከሕይወት ሞት ይሻላል ነፍሴን ከእኔ ውሰድ እያለ ከከተማ ወጥቶ ዳስ ሠርቶ ተቀመጠ፤ እግዚአብሔርም በውኑ ትቆጣ
ዘንድ ይገባሃልን አለው፡፡

📖ዮናስ 4፥3-11

✅ አምላካችን መሐሪ በመሆኑ /አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል ፍጥረታቸውን
እሱ ያውቃልና፤ ጥበብ 3 ብለዋል፤ አምላካችንም /እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን
ካወቃችሁ በሰማይ ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን አይሰጣቸው ብሏል።

📖መዝ 102፥8-14

📖ማቴ 7፥12

✅ ቀጥሎም ነቢዩ ዮናስ እንቅልፍ እንቅልፍ ብሎት ተኝቶ ቢነቃ ከራስጌው ቅል በቅላ ፀሐይ ስትከለክልለት አየና እጅግ
ደስ አለው፤ ሁለተኛም ተኝቶ ቢነሣ ቅሏ ጠውልጋ፥ ደርቃ አገኘና አዘነ፤ እግዚአብሔርም ‹‹አንተ ላልተከልካትና ውኃ
ላላጠጣሃት ቅል እንዲህ ስታዝን እኔስ በዝናም አብቅዬ በፀሐይ አብስዬ ለምመግባቸው ሕዝቤ አላዝንምን›› አለው፤ ነገር
ግን እግዚአብሔር የዮናስን ፈቃዱን ይፈጽምለት (ሐሳዊ ነቢይ እንዳይሉት) ለምልክት እንዲሆን በሦስተኛው ቀን እሳት
ከሰማይ ወርዶ ከፍ ከፍ ያሉትን ዕፅዋት ጫፍ ጫፋቸውን በልቶ ተመልሷል፡፡

✅ ነቢዩ ቅዱስ ዮናስ በቀሪ ዘመኑ ፈጣሪውን እያገለገለ ኑሮ፤ በመልካም ሽምግልና በ 170 ዓመት እድሜም መስከረም 25
አርፏል፡፡
✅ ዮናስ በሕይወት ሥጋ ሣለ ሰማርያንና ነነዌን ብቻ ነበር ያስተማረው፤ ከሞተ በኋላ ግን ዛሬ ዓለምን የሚያስተምር
ነቢይ ነው

You might also like